Bisrat
መጋቢት 10፤2016 - በህንድ የባለቤቷን አባት በዱላ ስትደበድብ የነበረችዉ ግለሰብ በድብቅ ካሜራ ምስል ድርጊቷ ተጋለጠ
በህንድ ካርናታካ፣ ቤት ውስጥ ጥቃትን በሚያሳይ ቪዲዮ አንዲት ሴት አማቷን በዱላ ስትደበድብ አመላክቷል፡፡ኡማ ሻንካሪን የተባለቻ የካርናታካ ኤሌክትሪክ ቦርድ መኮንን የ87 አመቱን አማቷን ፓድማናብሃ ሱቫርናን በብረት ዱላ በጭካኔ ስትደበድብ ምስሉ አሳይቷል፡፡
የድርጊቱ ቪዲዮ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መሰራጨቱ የአካባቢውን ህብረተሰብ እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አስደንግጧል፤ የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚከለክሉ ህጎች እና የአረጋውያን ደህንነት ላይ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን ለማውጣት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል።ቪዲዮ ላይ ኡማ ሻንካሪካን ከፓድመናብሃ ሱቫርና ጋር ሲጨቃጨቁ እና አዛውንቱ ሴትየዋ እንዳታጠቃቸዉ ሲማፀኑ ታይተዋል፡፡ ነገር ግን ተማጽኗቸዉ ሳይሳካ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። የተከሳሿ የትዳር አጋር በውጭ አገር ስራ ላይ ነበረ ተብሏል፡፡
ሴትየዋ አማቷን በዱላ ለምን እንደመታቻቸው ግልፅ አይደለም። የ87 ዓመቱ አዛውንት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ግል ሆስፒታል ገብተዋል።ተከሳሿ ኡማ ሻንካሪ በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን በፓድማናብሃ ሱቫርና ሴት ልጅ ክስ ቀርቦባታል። ተከሳሿ ላይ ፍርድ ቤቱ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜን ፈቅዷል፡፡
በስምኦን ደረጄ
#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #India
የብስራ
የካቲት 7፤2016 - በቀድሞዉ አጎና ሲኒማ ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የያ ቴሌቪዥን ጣቢያ እና በፓስተር ዘነበች የሚመራው ቤተክርስቲያን ወደሙ
👉 እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 5 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ፈጅታል
ትላንት የካቲት 6 ቀን 2016 ዓመት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አራት በቀድሞዉ አጎና ሲኒማ ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የህንፃው አንደኛ እና ሁለተኛ ወለል በዉስጣቸዉ ከያዙት ንብረት ጋር ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በህንጻዉ ላይ ሙሉ በሙሉ ወድመት ከደረሰባቸዉ መካከል በቅርቡ የተቋቋመው እና የሩቅ ምስራቅ ፊልሞችን በአማርኛ ትርጉም ለተመልካቾች ሲያቀርብ የነበረዉ ያ ቴሌቪዥን እና በፓስተር ዘነበች የሚመራው ቤተክርስትያን ይገኙበታል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 20 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ እና ስድስት የዉሀ ቦቴዎች እንዲሁም ሁለት አምቡላንሶች ከ108 የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ጋር የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ህንጻዎች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር በተደረገዉ ጥረት 105 የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ፣ የዉሀና ፍሳሽና የመብራት ኃይል ባለሙያዎች ተሳትፈዋ
ዛሬ ታህሳስ 6 ፤2016 ከ ቅዳሜን ከኛ ጋር ከ 8:00 - 10:00 ድረስ
መስከረም 23፤2016 - በባሌ ጎባ ከተማ በደመራ ጫፍ ላይ ያለውን አበባ በማውረድ ጀግና ለመባል በሚደረግ ጨዋታ የአንድ ወጣት ህይወት ሲያልፍ ሁለቱ ቆሰሉ
መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም በባሌ ጎባ ከተማ 01 ቀበሌ የደመራ በዓልን ለማክበር ሶስት ቡድኖች ተሰብስበው እያከበሩ ደመራው አናት ላይ ያለውን አበባ በማውረድ ጀግና ለመባል የሞከረው ወጣት ህይወቱ ማለፉን የባሌ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ገዳዩች ኮማንደር ናስር ዑመር ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
አንበሴ ግዛው ፣ ወንድማገኝ ሞገስ እና ሲሳይ ገብሬ የተባሉ ወጣቶች ወደ ደመራው አናት ላይ አበባ ተክለው በተለኮሰ እሳት ውስጥ በመውጣት አበባውን ለማውረድ እና በአካባቢው ጀግና ለመባል ባደረጉት ጥረት ጉዳት ደርሶባቸዋል ነዉ የተባለዉ፡፡ በዚህም አንበሴ ግዛው የተባለው ግለሰብ ህይወቱ ማለፉንም ጣቢያችን ሰምቷል፡፡
በአካባቢው ይህ አይነት ድርጊት እንደ ባህላዊ ጫወታ የሚታሰብ ሲሆን ወጣቶች በቡድን በመሆን ይህ ዓይነቱን ፉክክር በየዓመቱ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል፡፡ በባሌ ጎባ ሆስፒታል ፣ወንድማገኝ ሞገስ እና ሲሳይ ገብሬ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን አንበሴ ግዛው በዛሬው ዕለት ህይወቱ ማለፉን የባሌ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ገዳዩች ኮማንደር ናስር ዑመር ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የ
መስከረም 15፤2016-በትራኮን ሪል እስቴት ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር አስር ሰዓት ወስዷል
👉 በእሳት አደጋው ወቅት ሁለት የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን አንዱ ከህንፃ ወድቋል
በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት 1:05 ሰዓት ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሀጫሉ ሁንዴሳ መንገድ ትራኮን ሪል እስቴት እየገነባ ባለዉ አፓርታማ 5ኛና 6ኛ ፎቅ ላይ የተነሳዉ የእሳት አደጋ ለሊት 10 ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋሉን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በእሳት አደጋው በሁለት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ሲያደርስ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።
አደጋዉ የደረሰባቸዉ ሁለቱም የእሳት አደጋ ሰራተኞች ሲሆኑ አንደኛዉ ሰራተኛ እሳቱን በማጥፋት ሂደት ከህንጻዉ ላይ ወድቆ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በአሁን ሰዓት በአለርት ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።
የእሳት አደጋዉ በአካባቢዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 9 ሰዓት መፍጀቱን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር የዉሀ ቦቴዎችን ጨምሮ 18 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ከ94 የ
ነሐሴ 25፤2015-የየካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ንጹህ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት እያገኘን አደለም ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የየካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ንጹህ የመጠጥ ዉሃ ማግኘት እንዳልቻሉ ቅሬታቸዉን በምስል አስደግፈዉ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል ፡፡
ነዋሪዎቹ ይህ ንጽህናዉን ያልጠበቀ ዉሃ በየግል የዉሃ ቧንቧቸዉ መምጣት ከጀመረ ከሶስት እስከ አራት ወር ያስቆጠረ መሆኑን ገልጸዉ ዉሃዉ ቆሻሻ ከመሆኑም በላይ አልፎ አልፎ ሽታ እንዳለዉም አክለዉ ተናግረዋል፡፡
በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ ዉሃ እንደሚያገኙ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ዉሃው የደፈረሰ፣ ሽታ ያለዉና ለምንም አገልግሎት የማይዉል እንደሆነ ገልጸዉ ለጤናችን እጅግ አሳሳቢ ከመሆኑ ባለፈ ንጹህ ዉሃ እስኪመጣ እጅግ በርካታ ዉሃ መፍሰስ እንዳለበት ተናግረዋል ፡፡
ይህ ደግሞ ያልተገባ የዉሃ ብክነት እንደሚያስከትል በመግለጽ ነዋሪዎቹ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ ፍለጋ ላልተገባ ወጭ እንደተዳረጉ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዢን ተናግረዋል፡፡
ጣቢያችን የነዋሪዎቹን ቅሬታ በተመለከተ ለአዲስ አበባ የዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ያሳወቀ ሲሆን በዚህም የውሃ ብክለት ሊኖር የሚችለው የተሰበረ የውሃ ማስተላለፊያ መስመር ሲኖር እንደሆነ ገልጿል።
ውሀ በሰዓቱ የማይመጣ ከሆነ ሊፈጠር የሚችል እንደሆነ እና ስለ አካባቢ ችግር መረጃው እንደሌላቸውና ጉ