Birana news

Birana news ትኩስ ዜና

...............................ልሸቀትም ….ውርደትም ነው!!..................ይገርማል በጣም!!እኔ እምለው  ለምንድ ነው አንዳንድ ሰዎች መንቀፍን እና ማቅለልን ...
14/04/2024

...............................ልሸቀትም ….ውርደትም ነው!!..................
ይገርማል በጣም!!
እኔ እምለው ለምንድ ነው አንዳንድ ሰዎች መንቀፍን እና ማቅለልን ለዕውቀታቸው መለኪያ መሳሪያ አድርገው የሚያስቡት?.......
ዌል ....በቅን ሀሳብ እና በተነጠረ ዕውቀት ይህ ልክ አይደለም …እንዲህ ያለው ነገር ላይ ይህ ግብዓት ቢጨመር እንዲያ ያለ ውጥዓት/output/ ሊያመጣ ይችላል የሚል ቀና እና ገንቢ ሀሳብ መስጠት የአባት ነው፡፡ ከዛ በመለስ ግን አውቃለሁም …አለሁም ለማለት የማያስቅፈውን በመንቀፍ እና በማጥላላት የተጠመዱ ሰዎችን ሳይ ግን ግርምምም ይለኛል!!!
አሁን እንደው ማን ይሙት የበዛ ወርቅ እንዲህ ያለ ልብ ስብር የሚያደርግ መዝሙር ማውጣት ያስነቅፋል?….. አጃኢብ እኮ ባካችሁ!!!
ትላንት ዘፈነች …እኛም …በትዝታዎቿም ተክዘን …በአዝናኙም ስራዋ ተዝናንተን ነበር፡፡ዛሬ ደግሞ መጨረሻዬ አሳሰበኝ …ዓለም በቃችኝ …ብላ አምላኳን ደጅ ጠናች….ጠናችናም ….የልቧን ውስጥ ስጋት …ፍርሃቷን ….እኔ ያንተ ባሪያ ባከበርከኝ ልክ …ሳልከብር …የትም ሜዳ ስዋልል …ስዋትት… ከርሜ …ሲመሽብኝ ….በዓለም ድካም ጉልቤቴ ሲዝል …ከእቅታዬ በፊት ለይቅርታ ደጅህ መጣሁ …እናም ይቅር በለኝ ብሎ ማለት …..ምኑ ነው የሚያስኮንነው?…
አንዱ እኮ ነው ከዚሁ መንደር /ብዙ አውቃለሁ፣አነባለሁ/የሚል ሰው ነው ደግሞ ፡፡
የትም ጨፍራ ሲበቃት …ዘፈኑ ሲያልቅባት …በመዝሙር ልትሸቅል መጣች የሚል የልጅም የጅልም ሀሳብ ብጤ ጫጭሮ …መመለሷን ሊመፃደቅበት ሲሞክር አይቼ በግኜ ነው ይህን መፃፌ ፡፡
እውነት ለማውራት በዛር ወርቅ መዝሙሯን የሰራቸው ለራሷም ብቻ አይመስለኝም፡፡ እንደ እኔ ላለን በዓለም ክፋት በብዙ ለምንመላለስ ሰዎች ነው፡፡ መዝሙሯን ሰምቶ የራሱ ሁኔታ የማያሳስበው አማኝ ቢኖር ይህ የተመፃደቀባት ሰው ብቻ ይመስለኛል፡፡ ሰው እንዴት በራሱ ዕውቀት ይመፃደቃል?….እንደምን የመጀመሪያውን ጠጠር አንስቶ ሊወረውር ተጣደፈሳ?
ወዳጄ ሀጥያታችን እንደጠጉራችን እየበቀለብን የሚታይ ቢሆን ኑሮ ከቤትም አትወጣም ነበር፡፡ ይቅር ይበልህ!!!
እንደ ጴጥሮስ ፀፀት እንደ ማርያም መቅደላዊት ያለ የመማር ፍላጎት /ይቅር የመባል/ ሲኖርህ ሸጋ ነው…ያንተ ዕውቀት …የዚህ ዓለም ንባብ እንዲህ ያለውን የልብ መሰበር እንድትረዳ ካላደረገህ ከፎረሽክ ሰንብተሃል ማለት ነው!!! ወርደኃል ወዳጄ …
ይህ ልሸቀትም ውርደትም ነው….ከንቱ ዕውቀት!!!!

........ልጆችን በልጅነት ጥብቆ .....ይህች ልጅ ዛሬ በየ ማህበራዊው ሚዲያ እየተመላለሰች ያለ አቅሟ ስትብጠለጠል አየሁና ምን አድርጋ ይሆን ብዬ የቀረበችበትን መሰናዶ አየሁት፡፡ እናም...
08/04/2024

........ልጆችን በልጅነት ጥብቆ .....
ይህች ልጅ ዛሬ በየ ማህበራዊው ሚዲያ እየተመላለሰች ያለ አቅሟ ስትብጠለጠል አየሁና ምን አድርጋ ይሆን ብዬ የቀረበችበትን መሰናዶ አየሁት፡፡ እናም ለካ ሕዝቤ እንዲህ ከፍ ዝቅ እያደረገ የወቀሳት ለዚህ ነው ብዬ አልኩና እኔም የእውነት የተሳመኝን ነገር ለማለት ሲዳዳኝ ከኔ በፊት በሷ ጉዳይ ብዙ ያሉ ሰዎች አሉ እና የእኔን ሀሳብ ለራሴው ፍጆታ አውዬው አለፍኩ፡፡ ቆይቼ አሁንም ፋታ ሳገኝ ወደዚያው መንደር ስመለስ …አንድ ሰው አብዛኞቹን በልጀቱ እና በቤተሰቦቿ ላይ እንዲሁም በቴሌቪዥኝ ጣቢያው ላይ ትችት ያቀረቡትን ሰዎች ሲነቅፍ አነበብኩ፡፡ እናም ሰውዬው ምን እያለ ነው ስል እራሴን ጠይቄ…እኔም ከጹሑፉ ስር የራሴን ሀሳብ አሰፈርኩለት፡፡ ደግሞ ማምሻዬንም ወደ ጎራው መለስ ስል አሁንም ይህ ሰው ሌላ ሀሳብ አስፍሮ አነበብኩ፡፡ ልጅቱንም ቤተሰቦቿንም ደግሞ ልክ ናቸው …መብቷ ነው …ምናምን የሚሉ ሀሳቦችን ማለቴ ነው፡፡
እርግጥ ነው በመብት ደረጃ የመሰለውንም ያመነበትንም ነገር መፃፍ ይቻላል!! መፃፍ ከመቻል ወዲህም ወዲያም ግን ጥርት ንጥር ያለ አመክንዮ ቢቀድም ሸጋ ነበር፡፡
እውነት ለማውራት በዚች ልጅ ውስጥ ያየሁት አስተዳደጓ ነው፡፡ እንዲህ ያለውን የልጅ ባህሪ ከመዘመን፣ከመሰልጠን፣ከመንቃት እና ከመብቃት ጋር ማያያዙ ተገቢ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ልጅነት የራሱ የሆኑ ጥብቆዎች አሉት…ተፈጥሮ፣ባህል፣ሐይማኖት የሚባሉ ነገሮች ተገምደው የሚሰፉት ግብረ ገብነት አለው፡፡
እርግጥ ነው ተፈጥሮ በልዩ ሁኔታ ብቁም ንቁም አድርጋ የምትፈጥራቸው ለዕውቀት የተሰጡም በክሎት የተካኑም /gifted and talented/ የሆኑ ልጆ አሉ፡፡ ይህ መሰጠታቸው እንዳለ ሆኖ ከሰው ጋር አግባብቶ የሚያኖራቸውን ማህበረሰባዊ ፋይዳው ወሳኝ የሆነው ግብረ ገብነታቸው ላይ ካልተሰራ ግን ሁሉ ነገር ኪሳራ ነው፡፡
ልጅ በዕድሜው…. ነገሮችን በመረዳት መጠኑም ልክ እያወቀ ማደግ አለበት ባይ ነኝ፡፡ ከዕድሜው እና ከመረዳት መጠኑ በላይ ነገሮችን ቀድሞ አውቆ ቀድሞ መሞከር ልክ ማሳው ላይ ከተዘሩት እና ወቅታቸውን ጠብቀው በልክ ካደጉት ሁሉ ቀድሞ በወውጣት አንገቱን አሰግጎ አደግኩ አደኩ እንዳለው እና ቀድሞ እንደተበጠሰው የእህል ዘር አይነት መሆን ነው፡፡ ከልክ በታች ሆኖ መዘግየትም አረም ነው ተብሎ እንደሚያስነቅል ሁሉ የልጆች ዕድገት በዕድገት ስርዓታቸው ልክ መሆን አለበት፡፡
ልጅ ሲያጠፋም ሆነ ያልተገባ ባህሪ ሲያሳይ በልምጩም በቁንጥጫው፣ መግራት አይገድላቸውም፡፡ እናን እንዳልገደለን ሁሉ ማለቴ ነው፡፡
ወደ ልጅቱ ስመለስ ቤተሰቦቿ ጋር አንድ ዘመናዊነት ባያሌው ያጠቃው ክፍተት ይታየኛል … ..አለ አይደል የሆነ ማቀማጠል አይሉት ማጨማለቅ …ብቻ ልጅቱ በተፈጥሮ በተሰጣት ፈጣንነት ልክ ረገብ …ረጋ የሚያደርጋት ምክር እና ተግሳፅ …ያስፈልጋታል ባይ ነኝ፡፡
ስቼም ከሆነ እታረማለሁ !!

https://youtu.be/63FUDZDloqQ
07/04/2024

https://youtu.be/63FUDZDloqQ

በአየር ሃይል ውስጥ ከአሰልጣኝነት እስከ ተመራማሪነት ያገለገሉት እኚሁ ግለሰብ ለአንድ የግል መረጃ አቀባይ በምስል በተደገፈ ማስረጃ

አኮቴትኢቢኤስ እና ድንቅ ተግባሩ  በዓለማችን ካለው ሕዝብ ውስት እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ካልሆኑ በስተቀር አብላጫውን እጅ የሚይዘው ሰው ሕይወቱን ፈቅ የሚያደርገው ተቀጥሮ በመስራት ነው፡፡ አንድ...
17/01/2024

አኮቴት
ኢቢኤስ እና ድንቅ ተግባሩ

በዓለማችን ካለው ሕዝብ ውስት እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ካልሆኑ በስተቀር አብላጫውን እጅ የሚይዘው ሰው ሕይወቱን ፈቅ የሚያደርገው ተቀጥሮ በመስራት ነው፡፡ አንድም ቀን …ተቆጥሮ በወር በሚከፈል ቋሚ ደሞዝ… አልያም በስራ ልኬት ተቀጣሪ ባመረተው ልክ የሚከፈል፡፡ ይህ የአብዛኞቹ ቀጣሪ መስሪያ ቤቶች የአከፋፈል ስርዓት ነው፡፡ ከዛ በመለስ ሰራተኛውን ለማትጋት እና ለመቅጣት በሰራተኞቹ የሕብረት ስምምነት መሰረት ቅጣት ወይንም ዓመት እየቆጠሩ የደሞዝ ጭማሪ ከማድርግ ውጪ ለሰራተኞቻቸው ብዙ ርቆት ሄደው ለክፉ ቀን የሚሆኑ ቀጣሪዎች ማየት ብዙ አልተለመደም፡፡
መግቢያዬ ላይ እንደገለፅኩት መንግስታዊም ይሁኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞቻውን ለማበረታታት አንዳንድ ወጪያቸውን ሲሸፍኑ ይስተዋላል፡፡ ገሚሶቹ ደግሞ እንዲህ ካለው ሰራተኛን ከማትጋት ሀሳብ በብዙ መልኩ ነፃ ናቸው፡፡ በጣም ጥቂቶቹ ደግሞ ዛሬ ልናወራለት እንደፈለግነው የቴሌቪዥን ጣቢያ በልዩነት ወጥተው ያልተለመደ እና ይበል የሚያሰኝ ድጋፍ ሲያደርጉ ይስተዋላሉ ….
ከዚህ ቀደም በታሪካችን የምናውቀው መኖሩንም …መስራቱንም የማናውቀው የአንድ የሚዲያ ተቋም ጋዜጠኛ ወይንም የሆነ ክፍል ሰራተኛ የነበረ ሰው ስም ተጠርቶ እዛ ተቋም ውስጥ ይሰራ እንደነበር ተጠቅሶ ማለፉ/መሞቱ/ ይነገራል፡፡እርግጥ ነው በሟች ዘመን የነበሩ ሰዎች ግለሰቡን ቢያውቁትም ቅሉ …ሰራተኛው በጡረታ ይሁን ወይ በሌላ ጉዳይ ከተገለለ በኃላ ማንም ሰው መኖሩን ሳያውቅ አልያ ዘንግቶት በሞቱ ምክንያት ብቻ ስሙ ይጠራል፡፡ ከዛም የቀብር ስነ ስርዓቱ በስንት ሰዓት እንደሚፈፀም ተጠቅሶ ይታለፍና ማምሻውን ደግሞ ‹‹በድርጅታችን ውስጥ ይህን ለሚያክል ጊዜ ሲሰሩ የነበሩ የአቶ እከሌ እከሌ የቀብር ስነ ስርዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንዲህ ባለ ቦታ ተፈፀመ..›› ተብሎ ከፍየል ጭራ ያነሰች ዜና ብጤ ይሰራላቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ እድለኞች እና በወቅቱ በድርጅቱ ውስጥ አለቃ ብጤ ሆነው የሰሩ ከነበሩ …ትንሸ ከዚች ዘለግ ያለች መሰናዶ ብጤ ይሰራላቸዋል፡፡ በቃ አበቃ…. ስንት ዓመት ሙሉ በዕውቀትም በጉልበትም ሰርተው ዛሬ ባደረሱት ተቋም ውለታቸው ከዚህ ዘሎ አያውቅም፡፡
ለዛሬው ጉዳዬ መነሻ የሆነኝ ኢቢየስ ግን እንዲህ ካለው ወቃሳ ከሚድንበት ማማ ላይ ተቀምጦ ታይቷል፡፡ኢቢየስ በሚዲያው መስክ በልዩነት የራሱን ቀለም እና አዳዲስ መሰናዶዎችን ይዞ የመጣ የሚዲያ ተቋም ነው፡፡
ዕጣ ፈንታው ሆኖ ነው መሰል …መወደድን እንደ ሸማ ለብሶ የሰነበተው የአስፋው መሸሻ ሕመም ከተሰማ በኃላ …ድርጅቱ/ ኢቢኤስ/ ያደረገው ነገር እጅግ እጅግ የሚያስመሰግነው ነገር ነው፡፡
አስፋው መሻሻ በጠና ታሟል እና ከፍተኛ ሕክምና እና ክትትል ያሻዋል ከተባለበት ጥቅምት ወር ጀምሮ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ወደ አሜሪካን ሀገር ወስዶ በማሳከም ከፍተኛውን ድርሻ አበርክቷል፡፡ እንዲህ ያለው ነገር መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ቢጋባባቸው እና እንደ ልምድ ቢወስዱት እንላለሁ፡፡
ኢቢኤስ በዚህም ብቻ አላበቃም …አስፋው መሸሻ የሄደበት ሀገር ሁሉ ሰው በሕይወት ውጥረት መካከል የሚዳክርበት ሜዳ በመሆኑ ልክ እንደ ሀገር ቤት ሌት ተቀን እየተፈራረቁ የሚያድሩለት አስታማሚዎች የማይገኙበት በመሆኑ የተነሳ አንድያ ልጁን ሙሉ ወጪውን ከፍሎ …ሲሰራ የሚያገኘውን ደመወዝ ሳይቀር ከፍሎ የአስፋው መሸሻን ሕይወት ለመታደግ ያደረገው ጥረት እንዲህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ አይደለም፡፡ አስፋው መሸሻ የልጄን የጃፒን ነገር አደራ እንዳለ ኢቢየስ አደራውን መቀበል የጀመረው አስፋው ገና በሕይወት ሳለ ጀምሮ ነበር፡፡ ልጁ ጃፒም ቢሆን ይህንን ጉዳይ በግሉ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ገልፆታል፡፡
መቼም ሁሉ ሰው እንኳ ዛሬን ቆሞ በዓለም ሲመላለስ ቢታይም ሞት ይሉትን ነገር ተቀሸክሞ ነውና የሚኖረው …አስፋው መሻሻ ከዛሬ ነገ ሀገሬ ገብቼ እንዲህ ከፍ ዝግ ብሎ በፀሎት በምልጃ ያልተለየኝን ሕዝብ ለማመስገን ያብቃኝ እያለ ሞት ቀደመው፡፡ የአስፋውን ሞት ተከትሎም እናት ድርጅቱ ዘወትሮአዊው የዕለተ እሁድ መሰናዶዎች በሙሉ አቁሞ በሀዘን መግለጫ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡ የስራ ባልደረቦቹም በሙሉ ማቅ ለብስው፣ሀዘን ተኮራምተው፣በእንባ ጎርፍ ተሞልተው የወዳጃቸውን ገሚሶቹ እንደሚሉት ደግሞ የአባታቸውን የአስፋው መሸሻን ሀዘን በቀጥታ ስርጭት አሳይተውናል፡፡ ኢቢኤስ ለአንድ ሰራተኛው በዚህ መጠን ተጨንቆ ስንት እና ስንት ሺ ብሮችን ከስሮ እንዲህ ማድረጉ እጅጉን የሚያስመሰግነው ጉዳይ ነው፡፡ ሁሉ ሰው እንደሚያውቀው የትኞቹም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከአዘቦት ቀናት ይልቅ በሰንበት ቀናት በተለይ ዕሁድ ዕሁድ ከማስታወቂያ የሚያገኙት ገቢ የት ድረስ እንደሆነ ማሰብ ብዙ አይከብድም ፡፡ታድያ እነዚህ ሁሉ ፕሮግራሞች እና ማስታወቂዎችን ወደ ጎን ተወት አድርጎ እንደ ቤተሰብ ሀዘን መቀመጡም አስደንቆኛል እና ይበል እሰየው ብያለሁ!!!
ሰው መቼም ካልሄደ ውለታውም ጥቅሙም አይታወቅም እና አስፋው መሸሻ ሕልፈት እውነት እስካይመስላቸው ድረስ ባልደረቦቹ ሲንገበገቡ ማየት በድርጅታቸው ውስጥ እንዴት ያለ የስራ ፍቅር እና ስምምነት ቢኖር ነው እንዲህ ሁሉ ነገራቸው ሁሉ ቤተሰባዊ የሆነው የሚል ጥያቄን ያጭራል፡፡ ይህ የሆነው ድርጅቱ ሰላማዊ በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ማወቅ ቀላል ነው፡፡

ተቀብለናል!!!አጠፉም አላጠፉም ይቅርታ መጠይቅ ትልቅነት ነው !!የሰው ልጅ ሀሳብ ብዙ ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሀሳቡን ይመቸኛል …እንዲህ አድርጌ ብገልፀው ይሻለኛል ብሎ ባለበት መንገድ ሀሳቡን ይገ...
12/01/2024

ተቀብለናል!!!
አጠፉም አላጠፉም ይቅርታ መጠይቅ ትልቅነት ነው !!

የሰው ልጅ ሀሳብ ብዙ ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሀሳቡን ይመቸኛል …እንዲህ አድርጌ ብገልፀው ይሻለኛል ብሎ ባለበት መንገድ ሀሳቡን ይገልጣል፡፡ ጥሩ በመናገር እና ቃላትን አዋቅሮ ንግግርን አሳምሮ በቻለው መጠን የልቡን ሀሳብ ያወጣል፡፡ ሀሳቡን መሸጥ በቻለበት መጠን ይሸጣል፡፡ በሌላኛው ወገን ደግሞ አንዲህ ያለውን ሀሳብ ወዶት የተረዳው ደስ ብሎት ይገዛዋል፡፡ አልያም ይህ ሀሳብ እንዲህ ባለ መልኩ ባይገለጥ ጥሩ ነበር ብሎ …ማስተካካየ የሚሰጥም አድማጭ ተመልካች ብዙ ነው፡፡
ከሰው ልጆች ባህሪያት ውስጥ አንዱ ስህተት ነው፡፡ ሁሉ ሰው ሰህተት ይሰራል፡፡ ማንም ሰው እንደ ክርስቶስ ፈፁም ነኝ ካላለ በስተቀር ከስህተት ሊነፃ አይችልም፡፡ፍፅምና በሰው ልጆች ዘንድ ከቶ የለም፡፡ በኃይማኖት በቁ ነቁ የምንላቸው አባቶች ሳይቀሩ ከስህተት የነጡ አይደሉም፡፡ በዓለም እንዳለን ሰዎች ደጋግመው ደጋግመው በጥፋት መስመር ላይ አይገኙ ይሆን መሳሳታቸው የማይቀር እውነት ነው፡፡
ወዲህ ደግሞ ስራ ልስራ ብሎ ሕይትን ፈቅ ለማድረግ በብዙ መልኩ ጎንበስ ቀና የሚል…ስራ የሚሰራ ሰው ሁሉ …ስህተት ሊሰራ ግድ ነው፡፡ እጅ እግሩን አጣጥፎ ምንም ሳይሰራ በቤተሰብ ወይ በሌላ አካል እየተደገፈ የሚኖር ሰው ከሚሰራው ሰው ጋር ሲነፃፀር የሚሰራው ስህትት እምብዛምነ ነው፡፡ ይህ ማለት ባለመስራት ስህተት የማይሰራው ሰው ይሻላል ማለቴም አይደለም፡፡ሰርቶ መሳሳት የአባት ነው፡፡ በመስራት እና በመንቀሳቀስ ውስጥ የሚፈጠሩ ሰህተቶች በሙሉ ስህተቱ በተፈጠረበት ሰዓት የሚያስከትሉት ተግዳሮቶች ቢኖሩም ሲያልፉ ግን መማሪያ እና ማስተማሪያነታቸው ይበልጣል፡፡
ሌላው አንዳንድ ስህተቶች ስህተት ናቸው ተብለው የሚፈረጁት በሶስተኛ ወገን ሲተያዩ ይሆናል …ሰህተት ሰራ የተባለው ሰው የሰራሁት ስህተት አይደለም ….ስህተቱ የተረዳችሁበት መንገድ ነው….እኔ ይህን ያደረኩት እንደዚህ ያለ ሸጋ ውጥኣት ወይንም መልካም ውጤት እና መረዳት ያመጣል ብዬ ነው ሲል ይሰማል፡፡አሁን እዚህ ጋር ያለው ቁም ነገር በአንድ ስው ንግግር እና ስራው ውስጥ የተፈጠረው ነገር ስህተት ነው የሚል ሌላ ሰው ከተነሳ እና ክህተቱን በአመክንዩ ማስረዳት ተችሎ መግባባት ላይ ካልተደረሰ …ያ ሰው እንዳይከፋ እና ወዳጅነት እንዳይሻክር ጉዳዩ ላይ ይቀርታ መጠየቅ እና ሀሳቡ ላይ በለመስማማት መስማማት ብልህነትም ተገቢም ነው፡፡
ለዛሬው ጉዳዬ መነሻ የሆነኝ የዝነኞቹ ኮሜዲያን የይቅርታ መልዕክት ነው፡፡በዓባይ ቲቪ እየተዘጋጀ በሚቀርበው የዋሸው እንዴ መሰናዶ ላይ ከሴት ልጅ ጥቃት ጋር ተያይዞ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ተነስቶ ነበር፡፡በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ታድያ የዓባይ ቲቪ ተመልካቾችም ሆኑ የኮሚዲያኑ አድናቂዎች ቅር የተሰኙበተን ጉዳይ አንስተው ቅሬታቸውን ሲገልፁላቸው ነበር፡፡ወዲህ ደግሞ ገሚሶቹ ኮሜዲያኑ ሊያስተላልፉ የፈለጉትን ነገር ተረድተው ችግሩ ያለው አድማጭ ተመልካች ጋር ነው እንጂ እነርሱ ምንም አላጠፉም ያሏቸውም ነበሩ፡፡
በመግቢያዬ ላይ እንደጠቀስኩት ኮሜዲያኑ ይህንን ነገር የገለፁት ሰው በተረዳው መልኩ መግለፅ ተፈልጎ ሳይሆን የሴትን ልጅ ጥቃት አስመልክቶ ከተለመደው ገለፃ በተለየ መልኩ በቀልድ አዋዝቶ ሁነኛ መልዕክት ለማስተላለፍ እንደነበረ ገልፀዋል፡፡ እርግጥ ነው እነርሱ እንዳሉት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲህ ባለ መልኩ የሚቀልድ ሰብዕና አላቸው ብለን አናስም፡፡…..በመስኩ ያካበቱት የሰው ፍቅር እና መውደድ ላይም የሚቀልድ ስነ ምግባርም የላቸውም፡፡ ሁሉም ኮሜዲያን በየ ግላቸው የየራሳቸው ክብር እና አክባሪም አላቸው እና፡፡
ወደ ዋነና ነገረ ጉዳዬ ስመለስ እኛ ‹ልንገልፅ የፈለግነው ነገር እንዲህ የሚልን ሀሳብ ነበር ሰው የተረዳው በሌላ ነው ስለዚህ ምንም ዓይንት ስህተት አልሰራንም› ብለው ሳይሉ እርግጥ ነው የተከሰተው ነገር በሰዎች የመረዳት መጠን እና ነገርን ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ከመመልት የተፈጠረ የሀሳብ አለመረዳት ቢሆንም …ለተከተሰተው ነገር ግን ይቅርታ እንጠይቃለን ብለው ማለታቸው ትልቅነታቸውን እና ለአድናቂዎቻቸው ያላቸውን ክብር እና ፍቅር የሚያሳይ በመሆኑ ልናከብራቸው እና ልናደንቃቸው ይገባል፡፡
እንዲህ ያለው ሰህተት ይሁን በሀሳብ አልተግብቶም የተከሰተው ስለሰራችሁ ስለሆነ ችግሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ ባትሰሩ ባትንቀሳቀሱ መች ስህተቱ ይሰራ ነበር፡፡ ዋናው እንዲህ ባለው አጋጣሚ ወደፊት የትኛው ርዕሰ ጉዳይ እንዴት መነሳት እንዳለበት …እንዲሁም የትኛው ርዕሰ ጉዳይ ደግሞ ቢነሳ ብዥታ ይፈጥርና እንደ አሁኑ ያለ ችግር ይፈጥራል የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን እንዳስተማራችሁ አድርጎ ማለፉ ነው፡
ተቀብለናል!!!

.......................የሚሄድ ነገር ያጓጓል .............ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነፍሱን የነጠቀው ብላቴና .ሁሉ ስራ በፍቅር በፍላጎት እና በኃላፊነት ሲሰራ ግብኣቱ ...
09/12/2023

.......................የሚሄድ ነገር ያጓጓል .............
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነፍሱን የነጠቀው ብላቴና .

ሁሉ ስራ በፍቅር በፍላጎት እና በኃላፊነት ሲሰራ ግብኣቱ ከውጥኣቱ ጋር በልክ ይገጥምና ትክክለኛውን የስራ ትርጉም ይወስዳል፡፡ ከዛ በመለስ ግን ወር ቆጥሮ ደሞዝ ለመውሰድ እና ሰሩ ለመባል ብቻ የሚሰሩ ስራዎች የኃላ የኃላ በሕዝብ እና በሀገር ላይ የሚያስከትሉት ኪሳራ እንዲህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ አይደለም …የትየለሌ ነው፡፡
‹‹ኣረ መላ በለኝ ልጄን፣የወንድሜን ልጅ፣ እከሌን …ዘመዴን …አዝማዴን አንድ ቦታ ወሽቅልኝ ››
ተብለው በአምቻና በጋብቻ ስለተዛመዱ ብቻ የስራ ቦታው የሚጠይቀውን በቂ የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ሳይዙ እንዲያው በዘ ፈቀደ በሲሾም ያልበላ…ያላስበላ በሲሻር ይቆጨዋል ስሜት በየ ድርጅቱ እንዲሰገሰጉ የተደረጉ ሰዎች ተገልጋዩን ሲያማርሩት እና በሚሰሩት ሰራ ሳቢያ ሀገር ከማትወጣው ኪሳራ ውስጥ ስትገባ በብዙ አስተውለናል፡፡
ለተመደቡበት ቦታ የሚሆን የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሰዎችም ቢሆን በሚፈጥሩት ቸልተኝነት ተነሳ የብዙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ሕይወት አደጋ ላይ ወድቋል፡፡
ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራን አልፎ ሕዝብ ሊያመላልስ ቀርቶ ቆሞ ቦታ ሊይዝ የማይገባውን ተሸከርካሪ በአሁኑ ዋጋው አንድ ኪሎ ሸንኩርት መግዛት በማይችል መደለያ አሳልፈው እና ወደ ስራ አሰማርተውት ከነ ጫናቸው ተሳፋሪዎች አደጋ ያደረሰ መኪና ቢቆጠር ብዛቱ ቀላል አይደለም፡፡
እንዲህ ያለው ስህተት እንደየ ሴክተር መስሪያ ቤቱ እና እንደሚሰጡት አገልግሎት ይለያያል፡፡
ለዛሬ ጽሑፌ መነሻ ሀሳብ የሆነኝ ጉዳይ የተከሰተው አንድ ዳተኛ እና ቸልተኛ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ሰራተኛ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልገውን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ በዳተኝነት ምናልባትም በዕውቀት ማነስ ምክንያት ወደ አንድ ቤተሰብ ቤት የሚገባ የቆጣሪ መስመር ላይ በፈጠረው ስህተት እጅግ አስገራሚ እና አስደናቂ የሆነ ብሩህ አእምሮ ያለው የ12 ዓመት ታዳጊ ሕይወቱን ሊያጣ ችሏል፡፡
ይህ ሟች ቴዎድሮስ ናሆም የተባለን የ12 ዓመት ታዳጊ ከዚህ በፊት ላይ የመጨረሻው ፊደል የሚል ውድድር ላይ ከአባቱ ከአቶ ናሆም ጋር ቀርቦ ያደረገውን ጨዋታ መመልከት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢትዮጵያን እንዴት ያለ ታዳጊ ልጅ እንዳሳጣት መረዳት ይቻላል፡፡
ከሟች ቴዎድሮስ አባት ጋር በጊዜ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናሌ ( ) ላይ በነበረኝ ቆይታ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ቤተሰቡ እጅግ እጅግ በጣም ከባድ ሀዘን ውስጥ መሆኑን ነው፡፡ በተለይ አባትየው አቶ ናሆም ያለበት ሁኔታ እንዲህ በቀላሉ በቃል የሚገለጥ አይደለም፡፡ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው፡፡
‹‹የሚሄድ ነገር ያጓጓል …ሊሄድብኝ ነው ለካ ዘመኔን ሙሉ የጓጓሁለት›› ብሎ ተንሰቅስቆ አንሰቀሰቀኝ…..እህህህህ
በጣም ያብከነከነኝ ነገር ቢኖር ያ ከንቱ ሰራተኛ ዛሬም ምንም እንዳልተፈጠረ እዛው መስሪያ ቤቱ ውስጥ ስራውን ቀጥሏል፡፡ ምናልባትም ሌላ ቦታ ሌላ ተመሳሳይ ስህተት ሰርቶ ሌላ ነፍስ ነጥቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም በድርጅቱ ሰራተኛ ምክንያት ለተፈጠረው ነገር ካሳም አልከፈለም ይቅርታም አልጠየቀም፡፡
ከቻላችሁ ከአባትየው ጋር ያደረኩትን ቆይታ ከታች ያኖርኩላችሁን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ ተመልከቱት እና ልባችሁ ይፍረድ፡፡
ያቆየን
ኤልሻድ የሺ
ሕዳር 29 2016 ዓ.ም

https://youtu.be/0NHABVe6Np0?si=IHvl3FmAeWR3pY4r
02/11/2023

https://youtu.be/0NHABVe6Np0?si=IHvl3FmAeWR3pY4r

አባታቸው ጥሏቸው ከሄደ እና ሌላ ሚስት ካገባ በኃላ በ14 ዓመቷ የቤተሰቡን ኃላፊነት የወሰደችው እርሷ ነች።በለምጣ ምክንያት ከፈቅ ሊወረውሯትን ነበር።አርሴማ ከትምህርት ቤት የሚሰጣት....

https://youtu.be/guCN3PK7Z5s?si=i6IcKuLNU7g21tjv
29/10/2023

https://youtu.be/guCN3PK7Z5s?si=i6IcKuLNU7g21tjv

ትላንት ወደድኩሽ አፈቀርኩሽ ብሎ ካገባት እና ለዓመታት አብረው ከኖሩ በኃላ 2ተኛ ልጃቸውን የ5 ወር ነፍሰጡር ሆና ሳለ አንድ ቀን እንደው ድንገት ከቤት ወጥቶ ይጠፋል።ከዛም ትንሽ ቆይቶ .....

እባካችሁ ሼር በማድረግ የልጄን አባት አፋልጉኝ!በሰላም እንዲመጣ ፀልዮልኝ!
25/06/2023

እባካችሁ ሼር በማድረግ የልጄን አባት አፋልጉኝ!
በሰላም እንዲመጣ ፀልዮልኝ!

ላታመልጪኝ አታሩጪኝ አሉከሳምንታት በፊት በሀዋሳ ከተማ አንዲት ፀጋ ጌታቸው የተባለች ግለሰብ በክልሉ ሀገረ ገዥ ጠባቂ ከፍቃዷ ዉጪ ተጠልፋ መሰንበቷ በብዙ ያነጋገረ ጉዳይ ነበር፡፡ ትላንት ባ...
19/06/2023

ላታመልጪኝ አታሩጪኝ አሉ
ከሳምንታት በፊት በሀዋሳ ከተማ አንዲት ፀጋ ጌታቸው የተባለች ግለሰብ በክልሉ ሀገረ ገዥ ጠባቂ ከፍቃዷ ዉጪ ተጠልፋ መሰንበቷ በብዙ ያነጋገረ ጉዳይ ነበር፡፡ ትላንት ባልዘመነ ዘመን የነበረን ጥልፊያ እና ግፊያ በዛሬው የዘመነ ዘመን ልድገም የሚሉ ድኩማን የአንዲትን እንስት ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት በጣሰ፣በረገጠ መልኩ ከውዴታዋ ውጪ በግዴታ ጠልፈው ትዳር ይሉትን የዘመን አረንቋቸውን ሊመሰርቱ ሲዳዳቸው ይታያል፡፡ ትናንት በዛ ዘመን የሰብዓዊ መብት ብርሃን ባልፈነጠቀበት በጎጂ በብዙ በተንሰራፉበት ወቅት የጥልፊያ እና ያለ አቻ ጋብቻ ጉዳይን አሜን ብሎ ከመቀበል ውጪ ምርጫ አልነበረም፡፡ ዛሬ በዚህ ትውልድ ግን እንደምንም አድጎ እንዲያ ያለው ኃላ ቀር ልምምድ ሊደገም የማይገባው ነገር ስለ መሆኑ እሙን ነው፡፡ የዛሬዎች ኃላ ቀር ጠላፊዎች ደግሞ ጉዳዩ እንዲ ለአደባባይ በቅቶ ሲያስነቅፋቸው ባህላችን ነው በሚል ምሽጋቸው ውስጥ ይገባሉ፡፡ ለዚህም ነው እንግዲህ ከሳምንታት በፊት በባንክ ሰራተኛዋ ፀጋ ላይ ደርሶ የበረው ክስተት የፈጠረው ሁካታ እና መረበሽ ሳያበቃ ሌላ ጀግና ነኝ ያለ ሳምሶን ሸኑ የተባለ ግለሰብ ሜላት መሀመድ የተባለችን የ14 ዓመት ታዳጊ ጠልፎ የተሰወረው፡፡
እውነት እና ንጋት እያደር እንዲጠራ …ወንጀለኛም ከሕግ ጥላ ስር ቢደበቅ እንጂ ሊያመልጥ እንደማይችል እንዲታወቅ ሆኖ እንሆ ተማሪ ሜላት መሀመድን በመጥለፍ ተሰውሮ እጅግ አላስፈላጊ ነገሮችን ሲደርግ የቆየው ሳምሶን ሸኑ በቁጥጥር ስር መዋሉን ከወንድሟ መስማት ችያለሁ፡፡፡

ሚዲያ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ያልታዩ፣ ያልተሰሙ እና ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማምጣት ለተመልካች ያደርሳል! ለቻናላችን አ.....

ምን ዋጠው…የት ገባከናዝሬት እስከ ደብረ ብርሃን ተፈልጎ ደብዛው ጠፍቷል…ወጣቱን ሰው ለስራ ብለው ጠርተው ምን አደረጉት …የት ወሰዱት…ቤተሰቦቹ በጉዳዩ ላይ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ያድምጡ፡፡ ...
18/06/2023

ምን ዋጠው…የት ገባ
ከናዝሬት እስከ ደብረ ብርሃን ተፈልጎ ደብዛው ጠፍቷል…ወጣቱን ሰው ለስራ ብለው ጠርተው ምን አደረጉት …የት ወሰዱት…ቤተሰቦቹ በጉዳዩ ላይ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ያድምጡ፡፡ ይህንን ፕሮግራም ሼር በማድረግ ለሰዎች በማዳረስ ለወጣቱ በቶሎ እንድረስለት፡፡

ዮሀንስ ካሳሁን በአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወንድማችን ሀሙስ ግንቦት 29/2015 ከቀኑ 7 ሰአት በተለምዶ ለማጅ ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ኮድ 2 AA 91249 ካኪ ከለር ኮሮላ የግል መኪናውን ኮንት.....

መልካም ጋብቻአደይ የእውነት ተሞሸረች ተወዳጇ ተዋናይት በእምነት ሙሉጌታ ወይንም አደይ እጅግ በአማረ እና በሰመረ መልኩ በሜቄዶንያ የሠርግ ሥነ-ሰርዓቷን አከናውናለች፡፡ ሙሉውን የሰርጓን ዝግ...
21/04/2023

መልካም ጋብቻ
አደይ የእውነት ተሞሸረች
ተወዳጇ ተዋናይት በእምነት ሙሉጌታ ወይንም አደይ እጅግ በአማረ እና በሰመረ መልኩ በሜቄዶንያ የሠርግ ሥነ-ሰርዓቷን አከናውናለች፡፡ ሙሉውን የሰርጓን ዝግጅት ሊንኩን በመጫን ይመልከቱ፡፡

አርቲስት በእምነት ሙልጌታ በሜቄዶንያ ያደረገችው የሰርግ ሦሤሥነ-ስርዓት።( )

ህፃኗን ልሰርቅ አቅጄ ነው የገባሁት!ከወር በፊት ሶልያና ዳንኤል የተባለችውን ህፃን ሰርቃ የጠፋችው የቤት ሰራተኛ እውነቱን አፈረጠችው፡፡
04/04/2023

ህፃኗን ልሰርቅ አቅጄ ነው የገባሁት!
ከወር በፊት ሶልያና ዳንኤል የተባለችውን ህፃን ሰርቃ የጠፋችው የቤት ሰራተኛ እውነቱን አፈረጠችው፡፡

AboutPressCopyrightContact usCreatorsAdvertiseDevelopersTermsPrivacyPolicy & SafetyHow YouTube worksTest new featuresNFL Sunday Ticket 2023 Googl

አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን በአድዋ ድል በዓል ላይ በጊዮርጊስ ቤተክርስትያን በተሰበሰቡ ምዕመናን እና በሕፃናቱ ላይ የተፈፀመው ተግባር በማምር በእንባ ገለጸ።
04/03/2023

አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን በአድዋ ድል በዓል ላይ በጊዮርጊስ ቤተክርስትያን በተሰበሰቡ ምዕመናን እና በሕፃናቱ ላይ የተፈፀመው ተግባር በማምር በእንባ ገለጸ።

አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን በአድዋ ድል በዓል ላይ በጊዮርጊስ ቤተክርስትያን በተሰበሰቡ ምዕመናን እና በሕፃናቱ ላይ የተፈፀመው ተግባር በማምር በእንባ ገለጸ።
04/03/2023

አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን በአድዋ ድል በዓል ላይ በጊዮርጊስ ቤተክርስትያን በተሰበሰቡ ምዕመናን እና በሕፃናቱ ላይ የተፈፀመው ተግባር በማምር በእንባ ገለጸ።

https://www.youtube.com/watch?v=WJLn31CInzQ
09/02/2023

https://www.youtube.com/watch?v=WJLn31CInzQ

ጤና ይስጥልን ይህ እሠይ ሚዲያ ነው፡፡ውድ ቤተሰቦቻችን አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን በቻናላችን በየጊዜው በዚህ ሊንካችን ታገኛላችሁ፡፡በዝግጅቶቻችን ላይ ያላችሁን አስተያየትና ጥቆ...

https://www.youtube.com/watch?v=tLaS4slGy0Q
09/02/2023

https://www.youtube.com/watch?v=tLaS4slGy0Q

ጤና ይስጥልን ይህ እሠይ ሚዲያ ነው፡፡ውድ ቤተሰቦቻችን አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን በቻናላችን በየጊዜው በዚህ ሊንካችን ታገኛላችሁ፡፡በዝግጅቶቻችን ላይ ያላችሁን አስተያየትና ጥቆ...

https://www.youtube.com/watch?v=qDOKz2R40fI
09/02/2023

https://www.youtube.com/watch?v=qDOKz2R40fI

ጤና ይስጥልን ይህ እሠይ ሚዲያ ነው፡፡ውድ ቤተሰቦቻችን አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን በቻናላችን በየጊዜው በዚህ ሊንካችን ታገኛላችሁ፡፡በዝግጅቶቻችን ላይ ያላችሁን አስተያየትና ጥቆ...

https://www.youtube.com/watch?v=aJWtn1Powa8
09/02/2023

https://www.youtube.com/watch?v=aJWtn1Powa8

ጤና ይስጥልን ይህ እሠይ ሚዲያ ነው፡፡ውድ ቤተሰቦቻችን አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን በቻናላችን በየጊዜው በዚህ ሊንካችን ታገኛላችሁ፡፡በዝግጅቶቻችን ላይ ያላችሁን አስተያየትና ጥቆ...

https://www.youtube.com/watch?v=Ch5TlItariQ
09/02/2023

https://www.youtube.com/watch?v=Ch5TlItariQ

ጤና ይስጥልን ይህ እሠይ ሚዲያ ነው፡፡ውድ ቤተሰቦቻችን አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን በቻናላችን በየጊዜው በዚህ ሊንካችን ታገኛላችሁ፡፡በዝግጅቶቻችን ላይ ያላችሁን አስተያየትና ጥቆ...

https://www.youtube.com/watch?v=xxNeESYWc08
08/02/2023

https://www.youtube.com/watch?v=xxNeESYWc08

ጤና ይስጥልን ይህ እሠይ ሚዲያ ነው፡፡ውድ ቤተሰቦቻችን አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን በቻናላችን በየጊዜው በዚህ ሊንካችን ታገኛላችሁ፡፡በዝግጅቶቻችን ላይ ያላችሁን አስተያየትና ጥቆ...

ፓትርያርክነቱ ይቅርብኝያልተሰማው አቡነ ማቲያስን የመግደል ሴራ ሲጋለጥ
25/01/2023

ፓትርያርክነቱ ይቅርብኝ
ያልተሰማው አቡነ ማቲያስን የመግደል ሴራ ሲጋለጥ

AboutPressCopyrightContact usCreatorsAdvertiseDevelopersTermsPrivacyPolicy & SafetyHow YouTube worksTest new features 2023 Google LLC

https://youtu.be/CkS_R7wXbKk
16/01/2023

https://youtu.be/CkS_R7wXbKk

አዲስ መረጃ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ያልታዩ፣ ያልተሰሙ እና ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማምጣት ለተመልካች ያደርሳል! ለቻ.....

መልካም በዓልየእስክስታዋ ንግስትን የእንዬ ታደሰ ልጆችን ድንቅ እና አስገራሚ የመድረክ ላይ ብቃት፡፡ ፈረንጇን ፈታይ ይመልከቱ!
07/01/2023

መልካም በዓል
የእስክስታዋ ንግስትን የእንዬ ታደሰ ልጆችን ድንቅ እና አስገራሚ የመድረክ ላይ ብቃት፡፡ ፈረንጇን ፈታይ ይመልከቱ!

አዲስ መረጃ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ያልታዩ፣ ያልተሰሙ እና ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማምጣት ለተመልካች ያደርሳል! ለቻ.....

መልካም ዜናበጣም ደስ ይላል!በመጨረሻ የአርቲስቱ እናት ፀሎት ሰመረ!ከንቲባዋ ለአርቲስቱ እናት ያልተጠበቀ ስጦታ አበረከቱላቸው፡፡
05/01/2023

መልካም ዜና
በጣም ደስ ይላል!በመጨረሻ የአርቲስቱ እናት ፀሎት ሰመረ!ከንቲባዋ ለአርቲስቱ እናት ያልተጠበቀ ስጦታ አበረከቱላቸው፡፡

አዲስ መረጃ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ያልታዩ፣ ያልተሰሙ እና ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማምጣት ለተመልካች ያደርሳል! ለቻ.....

ይቅርታ እጠይቃለሁ!! የተባለው ሁሉ ውሸት ነው!...ወዳጆቹ እውነቱን ተናገሩ
14/12/2022

ይቅርታ እጠይቃለሁ!! የተባለው ሁሉ ውሸት ነው!...ወዳጆቹ እውነቱን ተናገሩ

Addis Merejaኢትዮ አዲስ መረጃ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ያልታዩ፣ ያልተሰሙ እና ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማምጣት ለተመልካች ያደርሳል! ለቻ...

12/12/2022

ጤና ይስጥልን ይህ እሠይ ሚዲያ ነው፡፡ውድ ቤተሰቦቻችን አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን በቻናላችን በየጊዜው በዚህ ሊንካችን ታገኛላችሁ፡፡በዝግጅቶቻችን ላይ ያላችሁን አስተያየትና ጥቆ...

የታሪኩ የመጨረሻዎቹ ሰዓታት እና አሳዛኙ የእናቱ አሁናዊ ሁኔታነፍስ ይማር
11/12/2022

የታሪኩ የመጨረሻዎቹ ሰዓታት እና አሳዛኙ የእናቱ አሁናዊ ሁኔታ
ነፍስ ይማር

አዲስ መረጃ በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ያልታዩ፣ ያልተሰሙ እና ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ በማምጣት ለተመልካች ያደርሳል! ለቻ.....

Address

Addis Ababa

Telephone

+251980160305

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Birana news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Birana news:

Share