Channel 7 Ethiopia

Channel 7 Ethiopia ቻናል 7 ኢትዮጵያ ዲጂታል የመርጃ አውታር ነው ፡፡
ለአስተያየ

አቡነ ማትያስ ከአሜሪካ ህክምና ላይ ሆነው የላኩት መልዕክት
22/09/2023

አቡነ ማትያስ ከአሜሪካ ህክምና ላይ ሆነው የላኩት መልዕክት

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

ተመልከቱ ዛሬ በአራት ኪሎ
21/09/2023

ተመልከቱ ዛሬ በአራት ኪሎ

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ! በ2016 ዓ.ም ቻናል 7 ኢትዮጵያ የተለያዩ አዳዲስ ፕሮግራሞችን እና የማህበረሰብ ችግር ፈቺ የሆኑ ልዩ ልዩ መረጃዎችን ከFastM...
11/09/2023

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ!

በ2016 ዓ.ም ቻናል 7 ኢትዮጵያ የተለያዩ አዳዲስ ፕሮግራሞችን እና የማህበረሰብ ችግር ፈቺ የሆኑ ልዩ ልዩ መረጃዎችን ከFastMereja ጋር በጋራ አብረን እንደምንሰራ ለመግለፅ እንወዳለን።

ቻናል 7 ኢትዮጵያ
Channel 7 Ethiopia

ጎቤ እና ሺኖዬ ጭፈራ በአዲስ አበባ ቄሮ እና ቀሬ ተገናኝቷል! እንድትመለከቱት ጋበዝን!
07/09/2023

ጎቤ እና ሺኖዬ ጭፈራ በአዲስ አበባ ቄሮ እና ቀሬ ተገናኝቷል! እንድትመለከቱት ጋበዝን!

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

ለዉርስ ብሎ ወንድሙ ላይ የግድያ ሙከራ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱን የዳዉሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ ።ተከሳሽ  በተላ ባቴ ላይ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለው በዳ...
10/08/2023

ለዉርስ ብሎ ወንድሙ ላይ የግድያ ሙከራ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱን የዳዉሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ ።

ተከሳሽ በተላ ባቴ ላይ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለው በዳዉሮ ዞን በሎማ ባሶ ወረዳ ቤሮ ያማል ቀበሌ ልዩ ስሙ ፊናት ተብሎ በሚጠራበት መንደር ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም የግል ተበዳይ ወንድሙን በእርሻ መሬት ዉርስ በመካከላቸዉ በተፈጠረ አለመግባባት በፈፀመዉ የግድያ ሙከራ ወንጀል ክስ ጥፋተኝነቱ በመረጋገጡ ነዉ።

የወረዳ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚያስረዳዉ ተከሳሹ እና የግል ተበዳይ ወላጆቻቸዉን በሞት በመለየታቸዉ የእርሻ መሬትና ሌሎች ንብረቶች ላይ ክፍፍል ለማድረግ በታላቅና በታናሹ ወንድም መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ታናሽ ወንድም የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ድረስ በመሄድ አልጋ ላይ ተኝቶ እያለ በመሳደብ ከአልጋ ጎትቶ በማዉረድ ሲደበድበዉ የግል ተበዳይ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲታገል ተከሳሽ በእንጨት መፍለጫ መፍለጫ/ፋስ/ ግንባሩ ላይ በብረቱ በኩል በመምታት የሞተ መስሎት ጥሎ ከአንድ ግለሰብ ቤት ይሸሸጋል፡፡

የተሸሸገበት ግለሰብ ሁኔታን ሲነግረው ለማጣራት ሲመጣ ጉዳት ደርሶበትና በህይወት መኖሩን በማረጋገጡ ለፖሊስ ጉዳዩን በማሳወቅ ተጎጂውን ወደህክም ተቋም ተወስዶ ህይወቱን ማትረፉን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል፡፡

የሎማ ቦሳ ወረዳ ፖሊስ ተከሳሽን በቁጥጥር ስር አድርጎ ምርመራ አጣርቶ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በህክምና ማስረጃ በማደራጀት ለዳዉሮ ዞን ዐቃቤ ህግ መዝገቡን ልኳል።

የዞኑ ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ መርምሮ ተከሳሹን በፈፀመው ከባድ የሰው ግድያ ሙከራ ወንጀል ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት አቅርቦታል፡፡

የዳዉሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ ግለሰቡን ከሶ ያቀረበውን የክስ መዝገብ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ ተከሳሹ ክሱን እዲያስተባብል ዕድል ቢሰጠውም ክሱን ማስተባበል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

በዚሁ መሰረት የዳዉሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ በተላ ባቴ በ12 አመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉን ከዞኑ ፖሊስ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

የፍርድ ውሳኔውን እየተጠባበቀ የነበረው ተጎጂ ከወንድሙ ግድያ ቢተርፍም በወንዝ ሙላት ተወስዶ ህይወቱ ማለፉን ታውቋል፡፡

ዘገባዉ፦ክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ነው!

በድሬዳዋ ሊሰርቅ የሰው ቤት ገብቶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ውስኪ ሲጠጣ የተገኘው ሌባ በ3 አመት እስራት ተቀጣ!!ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ ነዋሪነቱ በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ...
09/08/2023

በድሬዳዋ ሊሰርቅ የሰው ቤት ገብቶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ውስኪ ሲጠጣ የተገኘው ሌባ በ3 አመት እስራት ተቀጣ!!

ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ ነዋሪነቱ በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት በማሰብ ሀምሌ 9 ቀን 2015ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰአት ገደማ በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ጎሮ 32 መንገድ ከሚገኘው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በር ሰብሮ በመግባት ነበር አስገራሚ የሆነውን ተግባር የፈፀመው።

ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ የግል ተበዳዮችን ቤት በር ሰብሮ ከገባ በኋላ ጤረጵዛ ላይ ታብሌት ስልክ ተቀምጦ ይመለከታል እሱን ይዞ ለመውጣት ያስብና ቀና ሲል ውስኪ ብፌ ውስጥ ያያል ልቡ ሸፈተ ቆይ በዚህ ውስኪ ለምን ትንሽ ዘና አልልም ይልና ብርጭቆ አቅርቦ ሶፋ ላይ ፈልሰስ ብሎ ተቀምጦ ልክ እንደራሱ ቤት እየተዝናና እያለ ነበር ከተወሰነ ሰአት በኋላ የግል ተበዳዮች መምጣታቸውን ይሰማና ጠረጴዛ ላይ የነበረውንና የዋጋ ግምቱ 12ሺ ብር የሚያወጣ ታብሌት ስልክ ብድግ አድርጎ በድንጋጤ ሽንት ቤት ይደበቃል የግል ተበዳዮችም ወደ ቤታቸው ሲገቡ ውስኪውን እና ብርጭቆ ጤረጴዛ ላይ ይመለከታሉ ታዲያ በዚህ ሰአት ማነው እዚህ ቤት የገባው ብለው በድንጋጤ ቤታቸውን ሲፈትሹ ተከሳሹን ግለሰብ ከነሰረቀው ንብረት ሽንት ቤት ውስጥ እጅ ከፍንጅ በመያዝ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይደውላሉ።

በዚህም መሰረት ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ ወደ ጣቢያ ይወሰዳል ለፈፀመው ከባድ የስርቆት ወንጀልም በአቃቤ ህግ ክስ ይመሰረትበታል።

በፖሊስ ተጣርቶ በአቃቤ ህግ የተመሰረተበትን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሀምሌ 21 ቀን 2015ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰን ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው በሶስት አመት ከሶስት ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

ውስኪ ያዘናጋው ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ እንዳሻው መሆን ሳይችል ወደማረሚያ ወርዷል ሲል የድሬዳዋ ፖሊስ ነው የዘገበው።

የአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ሊግ ተመሠረተChannel 7 Ethiopia የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሙስሊም ወጣቶች ሊግን በከተማ እና በክፍለ ከተማ ደረ...
08/08/2023

የአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ሊግ ተመሠረተ
Channel 7 Ethiopia

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሙስሊም ወጣቶች ሊግን በከተማ እና በክፍለ ከተማ ደረጃ በዛሬ እለት አዋቅሮ የትውውቅ መርሃ ግብር አካሂዷል ።

በዚህ የምስረታ መድረክ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ እንዳሉት ሀገር ለቀጣይ ትውልድ በሚል ስትገነባ ዋነኛው ተሳታፊ ወጣቱ መሆኑን ተናግረው ወጣቶች የተሰጣችሁን አሉታዊ ስም ወደ አዎንታዊ በመቀየር ታሪክ መሥራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

የከተማው እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በወጣቱ ላይ ያለው እምነት ከፍተኛ በመሆኑ ብዙ አደራ ይሰጣል ያሉት ፕሬዝዳንቱ ሼህ ሱልጣን አማን በቀጣይም እስከታችኛው እርከን በመውረድ ወደ ሕብረተሰቡ መድረስ ያለበት መሆኑን አሳስበው ዑማውን በተገቢው የማገልገል ሕልም ይዛችሁ ተጓዙ ሲሉ የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ይህን ሰርፕራይዝ ተመልከቱ!! ኢንጂነሯ ሊስትሮ በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፍሬህይወት ታምሩ ሰርፕራይዝ ተደርጋለች!!
03/07/2023

ይህን ሰርፕራይዝ ተመልከቱ!! ኢንጂነሯ ሊስትሮ በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፍሬህይወት ታምሩ ሰርፕራይዝ ተደርጋለች!!

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን የ‘ግሎባል ኢኮኖሚ’ ሽልማት አሸናፊ ሆኑየኢትዮጵያ ምርት ገበያ መሥስራቿ ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን ጀርመን ኪል ከተማ የሚገኘው ኪል ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተቋም የ...
20/06/2023

ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን የ‘ግሎባል ኢኮኖሚ’ ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ መሥስራቿ ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን ጀርመን ኪል ከተማ የሚገኘው ኪል ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተቋም የሚያዘጋጀውን 18ኛውን ግሎባል ኢኮኖሚ ሽልማትን አሸናፊ ሆኑ።

ሰኞ ሰኔ 12/2014 ዓ.ም. ምሽት ላይ በኪል ከተማ በተከናወነ ሥነ ሥርዓት ላይ ሽልማታቸውን የተቀበሉት ዶ/ር ዕሌኒ፣ ሽልማቱ ኢትዮጵያ ወስጥ ላከናወኗቸው ተግባራት እውቅና የሚሰጥ በመሆኑ እንደተደሰቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ላለፉት 18 ዓመታት በኪል ሲካሄደ የቆየው የግሎባል ኢኮኖሚ ሽልማት የዘንድሮውን ዶ/ር ዕሌኒ በቢዝነስ ዘርፍ ሲያሸንፉ፣ የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ንጎዝ ኦኮንጆ በፖለቲካ ዘርፍ እንዲሁም የአፍሪካ ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሌዎናርድ ዋንታቼኮ በምጣኔ ሃብት ዘርፍ አሸንፈዋል።

ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን አሁን ላይ በተባባሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ውስጥ የተቋቋመውን የግል እና የመንግሥት ሴክተሮችን በማጣመር ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የተቋቋመውን “ቲምቡክቱ” የተሰኘውን መርሃ ግብር ከኒው ዮርክ በኃላፊነት እየመሩ ይገኛሉ።

ኪል ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተቋም ዶ/ር ዕሌኒ ለሽልማቱ ብቁ እንዲሆኑ በዳኞች የተቀመጡ ምክንያቶችን ሲገልጽ በኢትዮጵያ ያላቸውን አስተዋጽኦ ዘርዝሯል።

ኢኮኖሚስቷ በአበርክቷቸው የበርካታ አርሶ አደሮችን እና ወጣቶችን ሕይወት ማሻሻላቸው የተጠቀሰ ሲሆን፣ በተለይ በአፍሪካ ጭምር ቀዳሚ ነው ባለው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አማካኝነት ለ15 ሚሊዮን አርሶ አደሮች መተዳደሪያን እንዳስገኙ አመልክቷል።

ከዚያም በኋላ “ብሉሙን” የተሰኘ ተቋም በማቋቋም ከግብርና ጋር ለተያያዙ የሥራ ፈጠራ እና የሃሳብ ማፍለቂያ የሚሆን ማዕከል ለወጣቶች እንደፈጠሩም ጠቅሷል።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ በመንግሥታቱ ድርጅት አማካኝነት ለሥራ ፈጣሪ አፍሪካውያን በሚሆን ተግባር ላይ መሰማራታቸውን ገልጿል።

ተቋሙ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው ጽሁፉ ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን “ቁርጠኛ፣ ደፋር፣ አርቆ አሳቢ እና ማኅበራዊ ኃላፊነት የሚሰማት” ሲልም አሞካሽቷቸዋል።

ሽልማቱን አስመልክቶ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበራቸው ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን የተበረከተላቸው ሽልማት የፈጠረባቸውን ስሜት ሲናገሩ “በጣም ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ። በኢትዮጵያ የተሰራው ሥራ ለሌሎች አገራት ሊጠቅም እንደሚችል የሚያሳይ ነው” ብለዋል።

በተለይ በምርት ገበያ የተሰራው ሥራ ለአፍሪካ ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል የተበረከተላቸው እውቅና ማሳያ እንደሆነም ተናግረዋል።

“ኢኮኖሚስት ለመሆን ያቀድኩት በ15 ዓመት ዕድሜዬ ነው” የሚሉት ዶ/ር ዕሌኒ፣ ከልጅነት ህልማቸው መካከል አንዱ የሆነውን “በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ ከርሃብ እና ድህነት ለመውጣት ሃሳብ ከሚያመነጩት አንዷ መሆን ነበር” ይላሉ።

ዶ/ር ዕሌኒ በስፋት የሚታወቁበት ምርት ገበያ በኢትዮጵያ ያለው ግብይትን ሥርዓት ለማስያዝ፣ ግልጽነት ለመፍጠር፣ በአምራቾች፣ ንግድ ላይ በተሰማሩ እና በላኪዎች መካከል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ግብይት እንዲኖር ማገዙን ተናግረዋል።

“በነበረው የባንክ ሁኔታ፣ በነበረው የቴሌኮም ሁኔታ...ብዙ ሰው ‘እንዲህ አይነት ሥርዓት ሊዘረጋ አይችልም። የኢትዮጵያ ሁኔታ አይፈቅድም’ ብለው በጭራሽ ያላመኑ ብዙ ሰዎች ነበሩ” ካሉ በኋላ “ይህንን ማድረግ መቻላችን እና ለዓለም ማስመስከራችን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው እገምታለሁ” ሲሉ አክለዋል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ለወጣቶች የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ድጋፍ ለማድረግ እና ሃሳቡን ለማስተዋወቅ ቀዳሚ ሆነው መትጋታቸውን አንስተዋል።

በዚህም መነሻ ከ7 ዓመት በፊት የተመሠረተው ብሉሙን የተሰኘው የወጣቶች ሥራ ፈጠራ እና ሃሳብ ማፍለቂያ ተቋም መሠረት እንደጣለ እገምታለሁ ብለዋል።

አሁን የጀማሪ ሥራ ፈጠሪዎችን ለመደገፍ በመንግሥት ደረጃ ያለውን ፖሊሲ ለማዘጋጀት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ እንዲሁም ግለሰቦች በተመሳሳይ ሥራ ላይ መሰማራታቸው ጠቅሰዋል።

“ስለዚህ ብሉሙንም ልክ እንደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ መሠረት የጣለ ሥራ ነው ብዬ ነው የማምነው፤ ብዙዎችም ይህንን ይመሰክራሉ ብዬ አምናለሁ” ሲሉ ገልጸዋል።

ይህም ሽልማት ለዚህ ተግባራቸው እውቅና ሰጥቷል።

“በጣም ነው ክብር የተሰማኝ። ኢትዮጵያም በጥሩ ሁኔታ እንደምትጠራ እና ለኢትዮጵያ ክብር የሚያስገኝ አድርጌ ነው የቆጠርኩት” ብለዋል።

ዶ/ር ዕሌኒ ገብረ መድኅን ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል በተባባሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ስር የተቋቋመውን እና እሳቸው የሚመሩት ቲምቡክቱ የተሰኘውን መርሃ ግብር ሀሳብ በማበልጸግ ቆይተዋል።

ይህ መርሃ ግብር በመጪው መስከረም በመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሚመረቅ ሲሆን መቀመጫው ከኒው ዮርክ ወደ ሩዋንዳ ኪጋሊ ተዘዋውሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ አገራት ውስጥ ሥራውን ያከናውናል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው።

አነጋጋሪው የፕሮፌሰር መምህር ዘበነ ለማ የትምህርት ደረጃ ተገለጠ https://youtu.be/-LCEB4kBkXg
20/03/2023

አነጋጋሪው የፕሮፌሰር መምህር ዘበነ ለማ የትምህርት ደረጃ ተገለጠ
https://youtu.be/-LCEB4kBkXg

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

የአደይ ድራማ በእምነት ሙሉጌታ https://youtu.be/gTjNEPWBsQw
18/03/2023

የአደይ ድራማ በእምነት ሙሉጌታ
https://youtu.be/gTjNEPWBsQw

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

ተደምጠው የማይጠገቡት ፕሮፌሰር ዘበነ ለማ "በአሜሪካ የዶክትሬት ድግሪዬን ስማር አንደኛ ወጥቼ ነው የጨረስኩት፣ ሃሳብ የሚጀምረው ከልብ ሳይሆን ከኩላሊት ነው" ይሉናል አዲስ ነገር ይዤ መጥቻ...
17/03/2023

ተደምጠው የማይጠገቡት ፕሮፌሰር ዘበነ ለማ "በአሜሪካ የዶክትሬት ድግሪዬን ስማር አንደኛ ወጥቼ ነው የጨረስኩት፣ ሃሳብ የሚጀምረው ከልብ ሳይሆን ከኩላሊት ነው" ይሉናል አዲስ ነገር ይዤ መጥቻለሁ ብለዋል ተመልከቷቸው
https://youtu.be/m5EQkHoOcio

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09292...

ራኬብ አለማየሁ ለተመልካች ብር ልትከፍል ነው!!ባሉበት ሆነው እየተመለከቱ ገንዘብ የሚሰሩበት ነገር ነው ይዤ የመጣውት የጋዜጠኛ ራኬብ አለማየሁ አዲስ ስራ ምንድነው እንዴት ገንዘብ ትከፍላለች...
17/03/2023

ራኬብ አለማየሁ ለተመልካች ብር ልትከፍል ነው!!
ባሉበት ሆነው እየተመለከቱ ገንዘብ የሚሰሩበት ነገር ነው ይዤ የመጣውት የጋዜጠኛ ራኬብ አለማየሁ አዲስ ስራ ምንድነው እንዴት ገንዘብ ትከፍላለች የሚለውን ማብራሪያ ከራሷ አንደበት እንድትመለከቱ ጋበዝን
https://youtu.be/vJTNkyq3adY

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

በአረብ ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ይህን መልዕክት ተመልከቱhttps://youtu.be/zhS4eIgu7x0
06/03/2023

በአረብ ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ይህን መልዕክት ተመልከቱ
https://youtu.be/zhS4eIgu7x0

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

ፍቅር ከብሄር በላይ ነው፣ አሁን ሃብታም ሆኛለሁ፣ 16 ልጆች መውለድ ፈልጋለሁ!! ማሜ ማሜhttps://youtu.be/Eu3s1WmxmMc
03/02/2023

ፍቅር ከብሄር በላይ ነው፣ አሁን ሃብታም ሆኛለሁ፣ 16 ልጆች መውለድ ፈልጋለሁ!! ማሜ ማሜ

https://youtu.be/Eu3s1WmxmMc

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

በርካታ ማሳካት የምፈልጋቸው ህልሞች አሉኝ አሁን ጥሩ ስም አለኝ! አርቲስት ሰላም ተስፋዬ https://youtu.be/QA70hvJbjL8
18/01/2023

በርካታ ማሳካት የምፈልጋቸው ህልሞች አሉኝ አሁን ጥሩ ስም አለኝ! አርቲስት ሰላም ተስፋዬ
https://youtu.be/QA70hvJbjL8

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09292...

ቤት መግዛት አቅም የለኝም ብለው ተስፋ ቆርጠዋል? አሁን ለኪራይ በወር ስንት ብር እየከፈሉ ነው? ይህ ሁሉ ግምት ውስት በማስገባት አነስተኛ ገቢ ላላቸው የቀረበ የመኖሪያ ቤት አማራጭ ተመልከ...
11/01/2023

ቤት መግዛት አቅም የለኝም ብለው ተስፋ ቆርጠዋል? አሁን ለኪራይ በወር ስንት ብር እየከፈሉ ነው? ይህ ሁሉ ግምት ውስት በማስገባት አነስተኛ ገቢ ላላቸው የቀረበ የመኖሪያ ቤት አማራጭ ተመልከቱ

https://youtu.be/kwNE6ulIPxE

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

"በላይክ መጠን ብዛት ብር እንከፍላለን" ኢትዮቲክቶክኢንፎቴክ ሶፍትዌር ሶሉሽን ከየትም ዴሊቨሪ ጋር በጋራ በመሆን ኢትዮቲክቶክ የተሰኘ ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ አደረጉ። ኢትዮቲክቶክ አሜሪካን ሀገ...
23/12/2022

"በላይክ መጠን ብዛት ብር እንከፍላለን" ኢትዮቲክቶክ

ኢንፎቴክ ሶፍትዌር ሶሉሽን ከየትም ዴሊቨሪ ጋር በጋራ በመሆን ኢትዮቲክቶክ የተሰኘ ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ አደረጉ። ኢትዮቲክቶክ አሜሪካን ሀገር በሚገኝ ኢንፎቴክ ሶፍትዌር ሶሉሽን እና በየትም ዴሊቨሪ አማካኝነት የተሰራ ሲሆን በዛሬው እለትም ሁለቱ ተቋማት በቀጣይነት በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ኢትዮቲክቶክ ለኢትዮጵያዊያን እንዲስማማ ተደርጎ በኢትዮጵያዊያን የበለፀገ መተግበሪያ ነው ያሉት የኢንፎቴክ ሶፍትዌር ሶሉሽን ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ቀዳማይ ሙሉዓለም ከባህል እና ወግ ጋር የሚጋጩ ቪዲዮዎችን የሚቆጣጠር ስርዓት መዘርጋቱን ገልፇል።

አፕሊኬሽኑ ከ1 ወር በኋላ በፕሌይስቶር እና አፕስቶር ላይ እንደሚለቀቅ የገለፁት የየትም ዴሊቨሪ ስራ አስኪያጅ አቶ መንሱር ጀማል ናቸው አቶ መንሱር አክለውም ኢትዮቲክቶክ በላይክ መጠን ለቪዲዮ ባለቤቶች ገንዘብ እንደሚከፍል ገልፀው ከሶስት ወር በኋላ ቀጥታ ስርጭት (live) እንደሚጀምሩም ተናግሯል።

ሙሉ የቪዲዮ መረጃን በዚህ ሊንክ ተመልከቱ
👉 https://youtu.be/fW9CzGpIYIo
👉 https://youtu.be/fW9CzGpIYIo

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09292...

አሸዋ ቴክኖሎጂስ እና አፈሪኮም ቴክኖሎጂስ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙየቴክኖሎጂ ተቋም የሆኑት አሸዋ ቴክኖሎጂስ እና አፍሪኮም ቴኮኖሎጂስ በጋራ ለመስራት ዛሬ ታህሳስ 12/2...
21/12/2022

አሸዋ ቴክኖሎጂስ እና አፈሪኮም ቴክኖሎጂስ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የቴክኖሎጂ ተቋም የሆኑት አሸዋ ቴክኖሎጂስ እና አፍሪኮም ቴኮኖሎጂስ በጋራ ለመስራት ዛሬ ታህሳስ 12/2015 ዓም በአይሲቲ ፓርክ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። ኢትዮጵያ የአለማችንን መልክ እየቀየረ ወደሚገኘው የዲጂታል ኢኮኖሚ እየተቀላቀለች ትገኛለች።

አፍሪኮም ቴክኖሎጂ በሀገር ውስጥ እና በተለያዩ የአለማችን ሀገራት የተለያዩ ሶፍትዌሮችን በመስራት ልምድ ያለው የቴክኖሎጂ ተቋም ሲሆን ashawa.com በኢ ኮሜርስ በይነመረብ ላይ ያለ የገበያ ቦታ ሲሆን ምርቶችን በጅምላ እና በችርችሮ ሽያጭ የሚካሄድበት ፕላትፎርም ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በ13 የቴክኖሎጂ ሴክተሮች ላይ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ ያለ ተቋም ነው።

የአፍሪኮም ቴክኖሎጂስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ዘይኑ ባደረጉት ንግግር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እውን ለማድረግ ሁለቱ ድርጅቶች በጋራ መስራታቸው ትልቅ አስተዋዖ ይኖረዋል ያሉ ሲሆን፣
አሁን ያለውን የገበያ የማነዋል አሰራር ስርዓት ወደ ዲጂታል ለማሳደግ እንዲሁም በውጪ ሀገር ከፍተኛ ገንዘብ እየፈሰሰባቸው የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን በሀገር ውስጥ በመስራት የስራ እድል እና የውጪ ምንዛሬን ለማዳን የሁለቱ ድርጅቶች አብሮ መስራት ከፍተኛ አሰረተዋዖ ይኖረዋል ያሉት ደግሞ አቶ ዳንኤል በቀለ የአሸዋ ቴክኖሎጂስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ናቸው።

የአይሲቲ ፓርክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሱራፌል ሽመልስ በበኩላቸው አይሲቲ ፓርክ የውጪ ንግድን ለማሳለጥ ከፍተኛ ስራ እየሰራ ያለ ተቋም ነው የሁለቱ የቴክኖሎጂ ተቋማት አብሮ መስራት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እውን ለማድረግ ከፍተኛ ድርሻ አለው ብለዋል።

 #ተከፈተ7ኛው የአፍሪ ፕሪንት እና ፓኬጂንግ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ የሳይን እና ግራፊክስ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ። ፕራና ኢቬንትስ እና አጋሩ ኤክስፖ ቲም አዘጋጅ...
20/12/2022

#ተከፈተ
7ኛው የአፍሪ ፕሪንት እና ፓኬጂንግ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ የሳይን እና ግራፊክስ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ። ፕራና ኢቬንትስ እና አጋሩ ኤክስፖ ቲም አዘጋጅነት የዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ታዋቂ የኢንዱስትሪው ባለሙያዎች፣ የዘርፉ ተጠቃሚዎች፣ እንዲሁም የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተከፍቷል። ኤክስፖውን የከፈቱት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት እና ግብዓት ዘርፍ አማካፊ አቶ ዳንኤል ኦላኒ ናቸው።

ዝግጅቱ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ድጋፍ የተደረገለት ሲሆን የፓን አፍሪካ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ አሳታሚዎችና ማኀበር ተቋማዊ አጋርነት ይከናወናል።

ከ3ሺ በላይ የንግድ ጎብኚዎች ከዓውደ ርዕይ ተሳታፊዎች ጋር ጠቃሚ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። አውድርዕይው ለሶስት ቀናት ይቆያል።

ፎቶ: ጥላሁን ደሳለኝ

ኢትዮጵያዊያን ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ የ28 ሰዎች አስክሬን በዛምቢያ ሉሳካ ተጥሎ ተገኘታህሳስ 02/2015 ዓ.ም አዲስ አበባዛሬ ጠዋት በዛምቢያ ሉሳካ ንግዌሬሬ አካባቢ 28 ኢትዮጵያውያን ...
11/12/2022

ኢትዮጵያዊያን ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ የ28 ሰዎች አስክሬን በዛምቢያ ሉሳካ ተጥሎ ተገኘ

ታህሳስ 02/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ
ዛሬ ጠዋት በዛምቢያ ሉሳካ ንግዌሬሬ አካባቢ 28 ኢትዮጵያውያን ናቸው የተባሉ አስከሬኖች መገኘቱን የዛምቢያ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ። ፖሊስ ጥቆማ ደርሶት በቦታው ሲደርስ አንድ ሰው በህይወት ማግኘቱን ገልፇል።

የዛምቢያ ፖሊስ ምክትል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዳኒ ምዋሌ እንደገለፀው በህይወት የተገኘዉ ግለሰብ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በአሁኑ ሰአት የህክምና ክትትል እየተደረገለት ነዉ ብለዋል።

የፖሊስ ቅድመ ምርመራ እንደሚያመለክተው በአጠቃላይ 28 ሰዎች እድሜያቸው ከ20 እስከ 38 የሆኑ ወንዶች በንግዌሬሬ አካባቢ በሚገኘው ቻሚኑካ መንገድ ዳር ነው ተጥለው የተገኙት ተብሏል።

ህይወት መኮንን በሞት እንድትቀጣ ተወሰነህዳር 26/2015 ዓ.ም የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ተከሳሿን በወንጀል ቅጣት አወ...
05/12/2022

ህይወት መኮንን በሞት እንድትቀጣ ተወሰነ
ህዳር 26/2015 ዓ.ም የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ተከሳሿን በወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 02/2006 መሰረት በእርከን 39 ስር በማሳረፍ በሞት እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡ በተከሳሽ ላይ የተወሰነው እስኪፈፀም ድረስ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንድትቆይ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

https://channel7.et/?p=2129

ህዳር 26/2015 ዓ.ም የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ…

በአዲስ አበባ ዛሬ የተሰሙ ጉዶች4 ህፃናትን የደፈረው 3 ወር ብቻ በፍርድ ቤት ተፈርዶበት የፍትህ ያለህ እየተባለ ነው፣ በአንድ መንደር ውስጥ 6 ህፃናት በአንድ ጊዜ ተደፍሯል የፍትህ ያለህ ...
24/11/2022

በአዲስ አበባ ዛሬ የተሰሙ ጉዶች
4 ህፃናትን የደፈረው 3 ወር ብቻ በፍርድ ቤት ተፈርዶበት የፍትህ ያለህ እየተባለ ነው፣ በአንድ መንደር ውስጥ 6 ህፃናት በአንድ ጊዜ ተደፍሯል የፍትህ ያለህ እየተባለ ነው ተመልከቱ
https://youtu.be/xiLlkYpFHJo

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09292...

ትውልደ ኢትዮጵያዊ በዜግነት እንግሊዛዊ የሰራው ሆቴል ነው
21/11/2022

ትውልደ ኢትዮጵያዊ በዜግነት እንግሊዛዊ የሰራው ሆቴል ነው

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09292...

ይህ በኳታር ዶሃ የአለም ዋንጫ የደጋፊዎች መንደር ነው። 200 ዶላር በአንድ ምሽት አዳር ያስከፍላሉ!! ወደ ብር ሲመነዘር ወደ 10ሺ ብር አካባቢ ይመጣል።
09/11/2022

ይህ በኳታር ዶሃ የአለም ዋንጫ የደጋፊዎች መንደር ነው። 200 ዶላር በአንድ ምሽት አዳር ያስከፍላሉ!! ወደ ብር ሲመነዘር ወደ 10ሺ ብር አካባቢ ይመጣል።

በኮንታ ዞን  አመያ ዙሪያ ወረዳ በጎሽ መንጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፋን ፖሊስ አስታወቀ።የኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጋዳ ሸበራ ቀበሌ ጥቅምት  17 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 ሰ...
28/10/2022

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ በጎሽ መንጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፋን ፖሊስ አስታወቀ።

የኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጋዳ ሸበራ ቀበሌ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 ሰዓት የጤፍ ማሳ ዉስጥ አረም በማረም ላይ በነበሩ ሰዎችን ከጫካ የወጣ የጎሽ መንጋ አንድ ግለሰብን በቀንድ ወግቶ የገደለዉ ሲሆን በሌሎች ሁለት ሰዎችን የአካል ጉዳት ማድረሱን ተከትለዉ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በዞኑ በዚሁ ወረዳ ሴሬ ቀበሌ ሚያዝያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ማሳዉን ከዝሆን ለመጠበቅ ሲሞክር ዝሆኑ ኩንቢ ጥቃት ደርሶበት ህይወቱ ማለፋንና በተደጋጋሚ ጊዜ በጎሽ ጉዳት እያደረሰ ነዉ ያሉት አዛዡ የሚመለከተዉ አካላት የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዉ ህ/ሰቡ ከመሠል የዱር እንስሳት እራሱን እንዲጠብቅ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

ዘገባዉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነዉ።

ደስ የሚል ውሎ ታዳጊዎቹ ከመከላከያ ጋር እንድትመለከቱት ጋበዝን አበረቷቷቸው
25/10/2022

ደስ የሚል ውሎ ታዳጊዎቹ ከመከላከያ ጋር እንድትመለከቱት ጋበዝን አበረቷቷቸው

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09292...

የዶሮ እና የእንስሳት ሃብት ዓውደርዕይ በኢትዮጵያ ይካሄዳል በኢትዮጵያ በነፍስ ወከፍ የዶሮ ምርት ፍጆታ ዝቅተኛ ነው ከምስራቅ አፍሪካም ጭምር እጅግ ያነሰ ነው በኢትዮጵያ 57 እንቁላል እና ...
18/10/2022

የዶሮ እና የእንስሳት ሃብት ዓውደርዕይ በኢትዮጵያ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ በነፍስ ወከፍ የዶሮ ምርት ፍጆታ ዝቅተኛ ነው ከምስራቅ አፍሪካም ጭምር እጅግ ያነሰ ነው በኢትዮጵያ 57 እንቁላል እና 2.85 የዶሮ ስጋ ፍጆታ ነው።
11ኛው የዶሮ ኤክስፖ እና 7ኛው የእንስሳት ሀብት ዓውድርዕይ እና ጉባኤ ከጥቅምት 17 እስከ 19/2015 ዓም በአዲስ አበባ ሰካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።

በዘንደሮ የዶሮ እና የእንስሳት ሃብት ዓውደርዕይ ብሄራዊ የኔዘርላንድስ ተሳትፎ ማረጋገጥ የተቻለ ከመሆኑም ባሻገር ከ10 ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሃንጋሪ፣ ህንድ፣ ኬንያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ስኮትላንድ፣ ቱርክ እና ዩናይትድ ስቴትስ የተውጣጡ ከ70+ በላይ ኩባንያዎችን ተሳታፊ ይሆናሉ።

እነዚህ ተሳታፊዎች ከጠቅላላው የእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ ሰፊውን የሚወክሉ ሲሆን ከመላው ኢትዮጵያ እና ከጎረቤት ሀገራት ከሚመጡ ከ4,000 በላይ የዘርፉ የንግድ ባለድርሻ አካላት እና ባለሙያዎች ጋር የንግድ ግንኙንት ለመፍጠር መዘጋጀታቸው ተገልፇል።

እነዚህ ኹነቶች በወተት፣ ዶሮ እና የስጋ እሴት ሰንሰለቶች ልማት ላይ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ፣ የእውቀት ሽግግርን በማምጣት እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስተዋወቅ ለዘርፉ ልማት ያላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማረጋገጥ መቻላቸውን የፕራና ኢቨንትስ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ለማ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዶሮ ሃብት ብዛት 57 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእነዚህም ውስጥ 34.26% እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ሲሆን፣ 32.86% የቄብ ዶሮዎች እንደሚሆኑ ይገመታል። በኢትዮጵያ በነፍስ ወከፍ የዶሮ ምርት ፍጆታ በዓለም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን በነፍስ ወከፍ 57 እንቁላል እና 2.85 የዶሮ ስጋ ፍጆታ ከምስራቅ አፍሪካ አማካይ ጭምር እጅግ ያነሰ መሆኑ ተገልፇል።

11ኛው የዶሮ ኤክስፖ እና 7ኛው የእንስሳት ሃብት ዓውድርዕይ እና ጉባዔ ከጥቅምት 17 – 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል አዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

Digital Finance Ethiopia Showcase 2022ሀገራችን ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ነድፋ ትግበራ ላይ ትገኛለች። ብሄራዊ ባንክም ናሽናል ዲጂታል ፔይመንት  ስት...
12/10/2022

Digital Finance Ethiopia Showcase 2022

ሀገራችን ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ነድፋ ትግበራ ላይ ትገኛለች። ብሄራዊ ባንክም ናሽናል ዲጂታል ፔይመንት ስትራቴጂ በመቅረፅ ትግበራ ላይ ይገኛል። ይህን የሀገራችንን ስትራቴጂ ለመደገፍ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ (DFS) 2022 ተዘጋጅቷል።

በሀገሪቷ የሚገኙ በቴክኖሎጂ የታገዙ የፋይናንስ አገልግሎቶች ምንድናቸው የሚሉትን ለማሳየት ከ40 በላይ የሚሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ለህዝብ የሚያስተዋወቁበት፣ እርስበርስ ትብብር የሚያደርጉበት ኤግዚብሽን በተጨማሪም በዲጂታል ፋይናንስ ላይ ያተኮረ ውይይት ይደረጋል።

በዚህ ኤግዚብሽን ላይ ባንኮች፣ ማይክሮ ፋይናንሶች፣ የሃዋላ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የመሳሰሉ የፋይናንስ ተቋማት የሚሳተፉ ሲሆን በተጨማሪም የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ግለሰቦች አባል ሆነው ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ይህ ፕሮግራም ጥቅምት 9 እና 10 2015 ዓም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ይካሄዳል ለጎብኚዎች ክፍት ነው ሁላችሁም ተጋብዛቿል።

Digital Finance Ethiopia Showcase 2022 ሀገራችን ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ነድፋ ትግበራ ላይ…

የመጀመሪያው የኢንሹራንስ ወር በኢትዮጵያየመጀመሪያው የኢንሹራንስ ወር በኢትዮጵያ “ጠንካራ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 5 እስከ 26 2015 ዓም...
12/10/2022

የመጀመሪያው የኢንሹራንስ ወር በኢትዮጵያ
የመጀመሪያው የኢንሹራንስ ወር በኢትዮጵያ “ጠንካራ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 5 እስከ 26 2015 ዓም ይከበራል።

የመጀመሪያው የኢንሹራንስ ወር በኢትዮጵያ “ጠንካራ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት…

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Channel 7 Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Channel 7 Ethiopia:

Share

Nearby media companies