AmharicTube

AmharicTube Amharic Tube Ethiopian movies, press conference and news
(10)

የግል ባንኮች አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በሃዋላ የሚላክ 1 ዶላርን እስከ 125 ብር እየመነዘሩ ነው።
09/07/2024

የግል ባንኮች አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በሃዋላ የሚላክ 1 ዶላርን እስከ 125 ብር እየመነዘሩ ነው።

100 የኤሌክትሪክ ባሶች ግዢ ሊፈጸም ነውየአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሳደግ እና ለማዘመን አዳዲስ ባሶች ሊገዙ መሆኑ ተነግሯል።የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ በቀጣይ 2017 ...
09/04/2024

100 የኤሌክትሪክ ባሶች ግዢ ሊፈጸም ነው

የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሳደግ እና ለማዘመን አዳዲስ ባሶች ሊገዙ መሆኑ ተነግሯል።

የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ በቀጣይ 2017 አመት ዘርፉን ለማዘመን የተለያዩ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የጥናትና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወርቁ ደስታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከተማ አስተዳደሩ በየአመቱ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማሻሻል 200 እና 300 ባሶችን እየገዛ ቢገኝም ከፍላጎቱ አንጻር አሁንም እጥረት አለ ብለዋል።

አሁን ላይ ከተማ አስተዳደሩ የ100 ባሶች ግዢ ሲያደርግ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ያሳድገዋል ብለዋል።

ዜጎች ስራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ ከተማ አስተዳደሩ የሚያቀርባቸውን የድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶችን የመጠቀም ልምድ እና ፍላጎት የላቸውውም የሚሉት አቶ ወርቁ ይህ በዘርፍ ችግር እየፈጠረብን ያለው ሌላኛው ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

የከተማው የትራንስፖርት እጥረት በመንግስት ብቻ የሚቀረፍ አይደለም የሚሉት አቶ ወርቁ ማህበራትም በዘርፉ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via Ethio FM

በ28 ቢሊየን ብር ካፒታል የፓርኮች  ኮርፖሬሽን ተቋቋመዋዜማ- በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ፓርኮች በፌደራልና በከተማ አስተዳደሩ ስር ተለይተው እንዲተዳደሩ የሚስችል አዲስ ደንብ ስራ ላይ ው...
08/30/2024

በ28 ቢሊየን ብር ካፒታል የፓርኮች ኮርፖሬሽን ተቋቋመ

ዋዜማ- በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ፓርኮች በፌደራልና በከተማ አስተዳደሩ ስር ተለይተው እንዲተዳደሩ የሚስችል አዲስ ደንብ ስራ ላይ ውሏል። ለዚህም እንዲረዳ ሁለት ኮርፖሬሽኖች ተቋቁመዋል።

በፌደራል ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ስር ከሀምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመው የአንድነት ፓርኮች ኮርፖሬሽን ሲሆን እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የተቋቋመው የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ይባላል።

ዋዜማ የተመለከተችው የአንድነት ፓርኮች ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ደንብ እንደሚገለጸው 5 የፓርክ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ተቋማት ማለትም አንድነት ፓርክ፣ የአንድነት የመኪና ማቆሚያ ህንጻ፣ ሳይንስ ሙዚየም፣ ወዳጅነት አደባባይ አንድ እና ሁለት በአንድ ተቋም እንዲተዳደሩ ተደርጓል።

ኮርፖሬሽኑ የፌደራል የመንግስት የልማት ድርጅት በመሆን የተቋቋመ በመሆኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይቆጣጠረዋል።

በጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ ተፈርሞ በነጋሪት ጋዜጣ የታተመው ሰነድ እንደሚገልጸው ከሆነ ለኮርፖሬሽኑ ማቋቋሚያ የተፈቀደው ካፒታል 28 ቢሊየን ብር ሲሆን 22.14 ቢሊየን ብር በጥሬ ገንዘብና በዓይነት መከፈሉን ይገልጻል።

የተወሰነ የጊዜ ቆይታ የሚኖረው ኮርፖሬሽኑ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ እንደማይሆን ተጠቅሷል፡፡

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ታህሳስ ወር 2016 ዓ.ም 10 ፓርኮችን በጋራ በመያዝ መቋቋሙን፣ የኮርፖሬሽኑ የኢኮ ቱሪዝምና ደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ መዝገቡ ይስማው ለዋዜማ ተናግረዋል።

በአንድ የተቋቋሙት 10 ፓርኮች በፊት በየራሳቸው የሚተዳደሩ የነበሩ ሲሆን እንጦጦ ፓርክ፣ አዲስ ፓርክ፣ 6 ኪሎ ፓርክ (አንበሳ ግቢ)፣ ኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ፣ የኮሪያ ዘማቾች ፓርክ፣ ሐምሌ 19 ፓርክ ፣ ብሄረጽጌ፣ ከንቲባ ወልደጻዲቅ ፓርክ፣ አፍሪካ ፓርክ፣ አምባሳደር እና ልደታ ፓርክ ናቸው።

እነዚህ 10 ፓርኮች ከተቋቋሙበት ወር ጀምሮ በ2016 የበጀት አመት 63 ሚሊዮን 591 ሺ ብር መገኘቱን ይህም የእቅዱን 89 በመቶ ማሳካት መቻሉን አቶ መዝገቡ ተናግረዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ስር የተቋቋመው ይህ ኮርፖሬሽን ሶስት ዘርፎች ያሉት ሲሆን ኢኮ ቱሪዝም (የደንበኞች አገልግሎት ፣ጉብኝትና ሁነቶች የሚያካሂድ)፣”የእንሰሳትና እጽዋት ዘርፍ” ደግሞ (Zoo service)ና ችግኝ ማልማት ሲሆን ሶስተኛው “የምህንድስና ዘርፍ አገልግሎት” የተባለው ፓርኮችን በደረጃቸው እድሳት ማድረግና የአደባባይ ኮሪደር ስራ ዘርፎች በመባል የተዋቀሩ ናቸው።

Via [ዋዜማ]

ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር  አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 201...
08/29/2024

ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም አርፈዋል።

አምባሳደ ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት አጡ ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ አዲስ አበባ የተጠሩትን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኢ/ር...
08/29/2024

አምባሳደ ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት አጡ

ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ አዲስ አበባ የተጠሩትን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኢ/ር ስለሺ በቀለን እንዲተኩ የተመረጡት አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት ማጣታቸውን ምንጮች ጠቁመውናል።

እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉትን አምባሳደር ሌንጮን አሜሪካ እንደማትቀበል ገልፃ እሳቸውን የሚተካ ስው እንዲላክላት ጠይቃለች ተብሏል።

ምክንያቱ ምን ይሆን ለሚው ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች አምባሳደር ሌንጮ ከአመታት በፊት በአሜሪካን ሀገር ሲኖሩ ከነበረባቸው አንዳንድ ክሶች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ጠቁመው ዝርዝር ጉዳዩን ማንሳት ግን እንደማይፈልጉ ከመሠረት ሚዲያ ተሰምቷል።

"እነዚህ ክሶች በህዝብ ማህደር (public record) ውስጥ ስላሉ አሜሪካኖቹ አምባሳደሩ በሀገራቸው እንዲሾሙ አልፈለጉም። ይህንን ጉዳይ አሜሪካኖቹ ለኢትዮጵያ መንግስት አሳውቀዋል" ብለው ምንጮቹ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ዙርያ እስካሁን በኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠ ማረጋገጫም ይሁን ማብራርያ የለም።

አሜሪካ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በሀገሯ ሲሾሙ የራሷን መስፈርት በማስቀመጥ የምትመረምር ሲሆን በበርካታ አጋጣሚዎች የሌላ ሀገራት አምባሳደሮችን ሳትቀበል ቀርታለች።

Via አዲስ ማለዳ

ኩራባቸው ደነቀ አሟሟት ምክንያትና አሳዛኙ መጨረሻ
08/27/2024

ኩራባቸው ደነቀ አሟሟት ምክንያትና አሳዛኙ መጨረሻ

ኩራባቸው ደነቀ አሟሟት ምክንያትና አሳዛኙ መጨረሻSubscribe to our channel Amharic Tube and enjoy Ethiopian daily news, Ethiopian movies, Ethiopian drama and Ethiopian comedy

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ አረፈ ዛሬ ጠዋት ህይወቱ ያለፈው አርቲስት ኩራባቸው የ1979 ከአዲስ አበባ የቴአትር አርትስ ዲፓርትመንት የተመረቀ ሲሆን ባለፉት 35 አመታት ከትወና እስከ ዝግጅት ...
08/26/2024

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ አረፈ

ዛሬ ጠዋት ህይወቱ ያለፈው አርቲስት ኩራባቸው የ1979 ከአዲስ አበባ የቴአትር አርትስ ዲፓርትመንት የተመረቀ ሲሆን ባለፉት 35 አመታት ከትወና እስከ ዝግጅት ሙያዊ አደራውን በሚገባ የተወጣ ሰው ነው፡፡

ኩራባቸው በተለይ በአርትስ ቲቪ በተሰራው "እረኛዬ" በተባለው የቲቪ ተከታታይ ድራማ ድንቅ የትወና ብቃቱን አሳይቷል፡፡

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ የተወለደው በ1957 ዓ.ም በሐረር ከተማ ልዩ ስሙ ሸንኮር በሚባለው መንደር ውስጥ ነው።

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በትወና በመድረክ ቴአትሮች ላይ ከ1982 ዓ ም ጀምሮ ከተሳተፈባቸው በጥቂቱ በህፃናትና ወጣቶች ቴአትር 'የዝናቧ እመቤት ' እና 'የገንፎ ተራራ' ቴአትሮች ፤ በሀገር ፍቅር ቴአትር 'የጨረቃ ቤት' ፣ 'ዓይነ ሞራ' ፣ 'ንጉሥ ሊር' ፣ 'ፍሬህይወት' ፣ 'ጥሎሽ' ፣ 'አሉ' ፣ 'ጣውንቶቹ' ፣ 'ከራስ በላይ ራስ' እና 'የሸክላ ጌጥ' ቴአትሮች ፤ በቴአትርና ባህል አዳራሽ 'የጫጉላ ሽርሽር' ቴአትር ፤ በራስ ቴአትር 'ቅርጫው' ቴአትር ይገኙበታል።

ከዳይሬክቲንግ ሥራዎቹ ካዘጋጃቸው የመድረክ ቴአትሮች በሀገር ፍቅር ቴአትር 'ስጦታ'፣'ጥሎሽ'እና 'መዳኛ' ቴአትሮች ፤ በቴአትርና ባህል አዳራሽ 'ሶስና'፣'አንድ ክረምት'፣ጥቁሩ መናኝ' እና የጫጉላ ሽርሽር'(ዝግጅት በተዋንያን ነበር) ቴአትሮች ፤ በራስ ቴአትር 'ትንታግ' የተሰኘ ቴአትር በማዘጋጀት ተሳትፏል።

ካዘጋጃቸው ሙዚቃዊ ድራማዎች መካከል በተለይ በአንጋፋዋ አርቲስት አስናቀች ወርቁ ህይወት ላይ ተመስርቶ የተፃፈውና ያዘጋጀው 'አስናቀች ኢትዮጵያ' የተሰኘው ሥራ ስራ ይጠቀሳል።

'የተዋቡ እጆች'የተሰኘ ፊልም አዘጋጅቷል።

በበርካታ የሬድዮ ድራማዎች ላይ በተለይም ደራሲ ሀይሉ ፀጋዬ በፃፋቸውና በቅዳሜ መዝናኛ ፕሮግራም በተላለፉት በአብዛኞቹ ተሳትፏል።

ለሁለት ለሁለት ሳምንታት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረቡ 'ጩኒና ቾምቤ'የተሰኘ የህፃናት ቴአትር እና 'የማለዳ ጤዛ' የተሰኘው ድራማ ይገኙበታል።

የቴሌቪዥን ድራማዎች 'ገመና 1' እና 'ገመና 2' እና "እረኛዬ" ድራማዎች ብዙ አድናቂዎች ያፈሩለት ስራዎች ናቸው።

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ ከወ/ሮ አስቴር ታደሰ ጋር በ1985 ዓ. ም በጋብቻ ተሳስሮ ሁለት ወንዶች እና አንዲት ሴት ልጆች አፍርቷል።

የሽብር ክስ ተከሰሱየፌደራል ፖሊስ የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል ባላቸው 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀመረ የፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላ...
08/25/2024

የሽብር ክስ ተከሰሱ

የፌደራል ፖሊስ የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል ባላቸው 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀመረ

የፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ

* ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ
* አማኑኤል መውጫ አብርሃ
* ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ
* ኤልያስ ድሪባ በዳኔ
* ይዲድያ ነጻነት አበበ እና
* እሌኒ ክንፈ ተክለአብ

ናቸው።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸውን ንብረት የሆነውን አየር መንገድ፣ ንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገልጿል።

በመሆኑም እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎችን ቢሮው በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20/2016 ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ለማወቅ ተችሏል።

EBC በጥላሁን ካሳ

:በአሜሪካን ሀገር፣ ኦሃዮ ግዛት፣ በኮሎምበስ ከተማ አቅራቢያ ሁለት የ19 አመት ወጣት መንታ ወንድማማቾች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።   እንደ ኦሃዮ ፖሊስ ዘገባ ፣ እሑድ፣ ነሐሴ 25 ...
08/24/2024

:በአሜሪካን ሀገር፣ ኦሃዮ ግዛት፣ በኮሎምበስ ከተማ አቅራቢያ ሁለት የ19 አመት ወጣት መንታ ወንድማማቾች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

እንደ ኦሃዮ ፖሊስ ዘገባ ፣ እሑድ፣ ነሐሴ 25 ቀን 2024፣ ከሌሊቱ 3፡30 PM ሰዓት ላይ፣ የ19 ዓመቱ ሳሙኤል በየነ እያሽከረከረ፣ መንታ ወንድሙን ጆይል በየነን በተሳፋሪነት ከፊት አስቀምጦ፣ መብራት ሳያበሩ፣ በሰዓት 35 ማይል፣ የፍጥነት ገደብ ማሸከርከር በሚገባቸው ጎዳና ላይ፣ ከተፈቀደው ፍጥነት እጥፍ በላይ በሰዓት 75 ማይል፣ በተሳሳተ ተቃራኒ አቅጣጫ፣ ዶጅ፣ ቻርጀር መኪናቸውን እያሸከረከሩ ከፊት ለፊታቸው አቅጣጫውን ጠብቆ ሲመጣ ከነበረ ኒሳን፣ አልቲማ መኪና ጋር ፊት ለፊት ተላትመው በመጋጨታቸው፣ መንታ ወንድማማቾቹ ፣ እንዲሁም ኒሳን መኪናውን ታሽከረክር የነበረችው የ32 ዓመት ወጣት ሴት፣ ከባድ አደጋ ደርሶባቸው ለህክምና ወደ ሆስፒታል ቢወስዱም፣ ህይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እያጣራ መሆኑን አመልክቷል።

Daniel Gebremariam

" ፍትህ ለሄቨን " በህጻን ሄቨን ምክንያት ከ6,000,000 ብር በላይ የወጣበት አልበሟ የሚወጣበትን ቀን አራዘመች |ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ | veronica
08/19/2024

" ፍትህ ለሄቨን " በህጻን ሄቨን ምክንያት ከ6,000,000 ብር በላይ የወጣበት አልበሟ የሚወጣበትን ቀን አራዘመች |ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ | veronica

" ፍትህ ለሄቨን " በህጻን ሄቨን ምክንያት ከ6,000,000 ብር በላይ የወጣበት አልበሟ የሚወጣበትን ቀን አራዘመች |ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ | veronicaSubscribe to our channel Amharic Tube and enjoy Ethiopian...

የሚቆጣና የሚጠይቅ ፍትህ ስርዓት የሌለባት ኢትዮጵያ ... " የነገዋ ኢትዮጵያ በጣም ታስፈራኛለች " ግሩም ዘነበ | Girum Zenebe
08/18/2024

የሚቆጣና የሚጠይቅ ፍትህ ስርዓት የሌለባት ኢትዮጵያ ... " የነገዋ ኢትዮጵያ በጣም ታስፈራኛለች " ግሩም ዘነበ | Girum Zenebe

የሚቆጣና የሚጠይቅ ፍትህ ስርዓት የሌለባት ኢትዮጵያ ... " የነገዋ ኢትዮጵያ በጣም ታስፈራኛለች " ግሩም ዘነበ | Girum Zenebe | EthiopiaSubscribe to our channel Amharic Tube and enjoy Ethiopian da...

በባህር ዳር የሶስት ልጆች አባት   ፌቨን የተባለች  የ7 ዓመት ህፃን ደፍሮ ገድሏል በመባሉ  ሀያ አምስት ዓመት እስራት  ተፈረደበት ፌቨን የተባለች የ7 ዓመት ህፃን እናቷ ነርስ ስለሆነች ...
08/17/2024

በባህር ዳር የሶስት ልጆች አባት ፌቨን የተባለች የ7 ዓመት ህፃን ደፍሮ ገድሏል በመባሉ ሀያ አምስት ዓመት እስራት ተፈረደበት

ፌቨን የተባለች የ7 ዓመት ህፃን እናቷ ነርስ ስለሆነች የተከራዩበት ቤት ትታት ትሄዳለች።ነ ገር ግን ቤት ያክራያቸውና አሁን በማረሚያ ቤት የሚገኘው ጌታቸው የተባለ የ3 ልጆች አባት ህፃኗን በአሰቃቂ ሁኔታ አስገድዶ ደፍሮ እንደገደላት ታውቋል።

የ7 ዓመት ህፃኗ ልጅን ግቢ ውስጥ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ጠብቆ አፏ ውስጥ አሽዋ በመጨመር በአሰቃይቶ እንደገደላት እናቷ ለፍርድ ቤት አስረድታለች።

ጥቃት ፈፃሚው 25 ዓመት ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ያለ ቢሆንም ይግባኝ እንደጠየቀም ተሰምቷል።

 " በህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ስም ማንኛውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም " - እነ ደብረጾን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ጉባኤ ውሳኔበአመራሮች መካከል ክፍፍል የ...
08/17/2024



" በህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ስም ማንኛውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም " - እነ ደብረጾን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ጉባኤ ውሳኔ

በአመራሮች መካከል ክፍፍል የፈጠረው የህወሓት ጉባኤ ባወጣው መግለጫ ፥ " የተለየ ሃሳብ አለኝ " የሚል በጉባኤ ያልተገኘ አካል ወደ ጉባኤው ቀርቦ ሃሳቡ በነፃነት እንዲገልፅ ፣ በዴሞክራሲያዊ ምጉት ለሚተላለፉት ውሳኔዎች ተገዢ እንዲሆን ነሃሴ 8/2016 ዓ.ም ጥሪ ማቅረቡ አስታውሰዋል።

" የድርጅቱ ጉባኤ ከተሰየመበትና ከተጀመረበት ነሀሴ 7/2016 ዓ.ም ቀን በኋላ ተራ አባል እንጂ የማእከላዊ ኮሚቴ የሚባል ሃላፊነት የላቸውም " ብሏል የእነ አቶ ጌታቸው ረዳ አቋም በመደገፍ ጉባኤውን ላወገዙ የቀድሞ ገምቱ አመራሮቹ።

" ስለሆነም ከህግና ተቋማዊ የደርጅታችን አሰራር ውጪ በአሁኑ ወቅት በህወሓት ስም ማንኛውም የፓለቲካ ስራ ለመፈፀም ሃላፊነት ያለው የማእከላዊ ኮሚቴና የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ሆነ ሌላ አካል የለም " በማለት አብራርቷል።

" ስለዚህ ህዝባችንና መላ አባላችን ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የጉባኤውን ውሳኔ በመረዳት እንዲተገብሩና እንዲተገበር እንዲሰሩ ጥሪ እናቀርባለን " በማለት አክለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፤ ቀደም ብሎ ለዚህ ጉባኤና በጉባኤው ለሚተላለፉ ማናቸውም ውሳኔዎች ምንም እውቅና እንደማይሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

በምርጫ ቦርድ ውሳኔ መሰረት አሰራሩን ያልተከተለ ጉባኤ null and void / ምንም እውቅናና ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው።

በሌላ በኩል ፥ በአሁን ሰዓት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት እና የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫ እየሰጡ ናቸው፤ ያነሷቸውን ሀሳቦች እናደርሳችኋለን።



08/15/2024

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ያለው ጉዳይ ብሔራዊ ደህንነቷን የሚጎዳ ከሆነ ማንኛውንም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገለጸ

ሐሙስ ነሐሴ 9 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ በሶማሊያ ያለው ጉዳይ ብሔራዊ ደህንነቷን የሚጎዳ ከሆነ ማንኛውንም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሚንስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህን ያሉት።

የሶማሊያ ጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት አሁንም የሚፈለገውን አቅም አለመገንባታቸውን ተከትሎ አትሚስን ተክቶ እንደ አዲስ በሚዋቀረው ሰላም አስከባሪ ስር ግብጽ ጦር ለማዋጣት ፍላጎት ማሳየቷ እና የሶማሊያ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጦር በአዲሱ ተልዕኮ ስር እንዳይካተት መፈለጋቸውስ በኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት አስተዋጽኦ ይኖረዋል? የሚለው ጥያቄ ለአምባሳደር ነብዩ ተነስቶላቸዋል።

አምባሳደር ነብዩ በምላሻቸው ላይ እንዳሉት "ሶማሊያ ሉዓላዊ ሀገር ናት፣ እንደ ሀገር ከፈለገችው ጋር ማንኛውንም አይነት ስምምነት መፉራረም ትችላለች። ከግብጽ ጋር ያደረገችው ወታደራዊ ስምምነት ኢትዮጵያን አያስጨንቅም" ብለዋል።

የፊታችን ታህሳስ ወር ላይ የሚያበቃው የአትሚስ ተልዕኮን የሚተካ አዲስ ሰላም አስከባሪ ሀይል ለማቋቋም ውይይት እየተደረጉ እንደሆነ የተናገሩት አምባሳደር ነብዩ ሰላም አስከባሪ ሀይል ማዋጣት የሚፈልጉ ሀገራት ፍላጎታቸውን እንዲገልጹ በተላለፈው ጥሪ መሰረት ግብጽ ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት አንዷ መሆኗን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ተልዕኮ ውስጥ መሳተፏ ካላት የሰላም ማስከበር ልምድ እና አሁንም መቀጠል መፈለጓ የበለጠ የሚጠቅመው ሶማሊያን ነውም ብለዋል።

ይሁንና የሰላም አስከባሪ ጦር የማዋጣት ፍላጎት ያላቸው ሀገራት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ያስቀመጠው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እና ሌሎችም አካላት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጡበታል ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም "ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ብዙ ድጋፍ እንዳደረገ፣ የህይወት መስዋዕትነት እንደመክፈሏ እና በሶማሊያ የሚደረገው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደህንነት እና ጥቅም የሚጎዳ ሆኖ ከተገኘ ማናቸውንም እርምጃ ትወስዳለች" ብለዋል።

ሕዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ ሕወሓት 14ኛ መደበኛ ጉባኤዉን ማካሄድ ጀመረ ። በኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ዕቅቅና የተነፈገው ህወሓት የትግራይ ክልል የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና...
08/13/2024

ሕዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ ሕወሓት 14ኛ መደበኛ ጉባኤዉን ማካሄድ ጀመረ ። በኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ዕቅቅና የተነፈገው ህወሓት የትግራይ ክልል የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 14 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ባልተገኙበት ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ የፓርቲው አባላት በተገኙበት ጉባኤው ዛሬ ከሰዓት በኋላ መቀሌ ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀምሯል። ጉባኤው ዛሬ ጠዋት እንደሚጀመር ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ባልታወቀ ምክንያት ወደ ከሰዓት በኋላ ተሸጋግሯል።
በጉባኤው ላይ እንደማይሳተፉ አስቀድመው ይፋ ያደረጉት የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በፅሑፍ ባስተላለፉት መልእክት፥ መደረግ የጀመረው ጉባኤው በጥድፍያ፣ የጋራ መግባባት ሳይደረስበት፣ አደራጀነው ባሉት ኔትዎርክ ይቃወሙናል ያሉት የተወሰነ መሪነት ለማስወገድ ብቻ የሚደረግ ጉባኤ » በማለት ተችተውታል። ይህም የከፋ አደጋ የሚፈጥር እና ሊወገዝ የሚገባው ነው ሲሉም ጉባኤውን ገልፀውታል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፥ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ለሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤም ሆነ በጉባኤው ላይ ለሚተላለፉ ውሳኔዎች በሙሉ እውቅና እንደማይሰጥ ትላንት ማስታወቁ ይታወሳል። ህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ከማድረጉ 21 ቀናት በፊት ለምርጫ ቦርድ ማሳወቅ እና ፓርቲው በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርዱ ታዛቢዎች መገኘት እንደነበረባቸውም ቦርዱ በመግለጫው ጠቁሟል።
ሕወሓት በበኩሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በልዩ ሁኔታ ተብሎ የተሰጠው እውቅና እንደማይቀበለው ገልፆ እንደነበረ ይታወሳል። በዚህ ውዝግብ ውስጥ ሆኖ ህወሓት ጉባኤው ማድረግ ጀምሯል።


ዘገባ ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

   " አላስፈላጊ እና ሕዝብን የማይጠቅም፣ ትርጉም አልባ ንትርክን አስወግደን ለሕዝብ ረብ ያላቸው ጉልህ የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ ልናተኩር ይገባል " - የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒ...
08/12/2024



" አላስፈላጊ እና ሕዝብን የማይጠቅም፣ ትርጉም አልባ ንትርክን አስወግደን ለሕዝብ ረብ ያላቸው ጉልህ የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ ልናተኩር ይገባል " - የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን

የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን በህወሓት ጉዳይ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫ ፦

- ህወሓት እንዴት ሕጋዊ ሰውነቱን ሊያጣ እንደቻለ ወደኃላ መለስብሎ አስታውሷል ፤

- የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈጸም የፌዴራል መንግሥት በስምምነቱ የገባው ግዴታ የህወሓት የሽብርተኝነት ፍረጃ እንዲነሣ ሂደቱን የማሣለጥ ኃላፊነት (የስምምነቱ አንቀጽ 7 (2) (C)) እንደሆነ ፤

- የፌዴራል መንግሥት የህወሓትን የሕግ ሰውነት እና የምዝገባ ጉዳይ በተመለከተ በፕሪቶሪያ ስምምነት ውስጥ የወሰደው የተለየ ኃላፊነት ወይም ግዴታ እንዳልነበር፤

- ህወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነት እንቀጽ 7 (1) (A) መሠረት የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት፣ ሕጎች፣ የፌዴራል ተቋማትን እና ሌሎች ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን ሥልጣን የማክበር ግዴታ መግባቱም ፤ ስለዚህ ሕወሐት የሀገሪቱን የፖለቲካ ፖርቲዎች የምዝገባ ሕግ እና የምርጫ ቦርድን ሥልጣን በማክበር የመሥራት ግዴታ እንዳለበት ... ገልጿል።

የፌዴራል መንግሥት በመግለጫው ፤ ህወሓት ወደ ህጋዊ መስመር ለማምጣት ስለተኬደባቸው መንገዶች ፣ ውይይቶች ፤ በህወሓት እና ምርጫ ቦርድ በኩል ስለተነሱት ልዩነቶች አብራርቷል።

ድርጅቱ ሕጋዊ ሰውነት እና ዕውቅና እንዲኖረው ለቦርዱ የትብብር ጥያቄ ስለማቅረቡም አስታውሷል።

እንዲሁም አዋጅ እስከማሻሻል በደረሰ እርምጃ ድርጅቱ ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገባ ለማድረግ የተኬደበትን ርቀት ገልጿል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት ሕጋዊ ሰውነት እና ዕውቅና ለማግኘት የሚጠበቅበት የፓርቲ ሰነዶቹን ማለትም የፓርቲውን ፕሮግራም እና ሕገ ደንብ፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሰነዶችን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማቅረብ በተሻሻለው አዋጅ መሠረት ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት እንዳገኘ አሳውቋል።

በመሆኑም " የምዝገባ እና የህግ ሰውነትን ጉዳይ በዚህ በመቋጨት፤ የሁሉም ባለድርሻ አካል ርብርብ ሰላምን በማጽናት፣ በመልሶ ግንባታ እና በልማት አጀንዳ ላይ ሊሆን ይገባል " ብሏል።

ፌዴራል መንግሥት" አላስፈላጊ እና ሕዝብን የማይጠቅም፣ ትርጉም አልባ ንትርክን አስወግደን ለሕዝብ ረብ ያላቸው ጉልህ የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ ልናተኩር ይገባል " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ህወሓት የምርጫ ቦርድን የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ “አልቀበልም”  አለ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲው “በልዩ ሁኔታ” የሰጠውን የህጋዊ ሰው...
08/10/2024

ህወሓት የምርጫ ቦርድን የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ “አልቀበልም” አለ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲው “በልዩ ሁኔታ” የሰጠውን የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ፤ የቀድሞውን ህልውናውን “ወደነበረበት የማይመልስ” በመሆኑ እንደማይቀበለው አስታወቀ። ፓርቲው ያቀረበው ጥያቄ እስኪመለስ ድረስ፤ የህወሓት “ህገ ደንብ በሚፈቅድለት መልኩ ተያያዥ ስራዎችን እንደሚያከናውን” ገልጿል።

ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ የህወሓትን “በልዩ ሁኔታ መመዝገብ እና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ማግኘትን” አስመልክቶ የደረሰበትን ውሳኔ ይፋ ያደረገው በትላንትናው ዕለት ነበር። ምርጫ ቦርድ በዚሁ ውሳኔው፤ ህወሓት “የቀድሞው ህልውና ወደነበረበት እንዲመለስ” ያቀረበውን ጥያቄ አለመቀበሉን አስታውቆ ነበር።

ቦርዱ ለዚህ ውሳኔው በማስረጃነት ያቀረበው፤ ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ የተሻሻለውን “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር” አዋጅን ነው። አዋጁ “በአመጽ ተግባር ተሰማርቶ ለተሰረዘ ፓርቲ የቀድሞውን ህልውና መልሶ የሚሰጥ የህግ ድንጋጌ ያልያዘ መሆኑን” የጠቀሰው ቦርዱ፤ በዚህ ምክንያት የህወሓት ጥያቄ ተቀባይነት አለማግኘቱን አስገንዝቧል።

ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ የያዘ ደብዳቤ እንደደረሰው፤ ህወሓት ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 4፤ 2016 ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል። ፓርቲው በዚሁ መግለጫው፤ “በቦርዱ ውሳኔ ላይ የተካተቱት ዝርዝር ይዘቶች አዲስ በወጣው ማሻሻያ ህግ መሰረት የተቀመጡ እና ህወሓት ካቀረበው ጥያቄ ጋር የማይገናኙ ናቸው” ብሏል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር ዋጋ ጨመረ።ባለፉት 5 ተከታታይ ቀናት  ለውጥ የሌለበት የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ነበር።ዛሬ ግን በሁሉም የውጭ ምንዛሬ ዋጋዎች ላይ ጭማሪ አደርጓል።የአ...
08/09/2024

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር ዋጋ ጨመረ።

ባለፉት 5 ተከታታይ ቀናት ለውጥ የሌለበት የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ነበር።

ዛሬ ግን በሁሉም የውጭ ምንዛሬ ዋጋዎች ላይ ጭማሪ አደርጓል።

የአሜሪካ ዶላር መግዣው 101 ብር ከ0041 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 111 ብር ከ1045 ሳንቲም ገብቷል።

ፓውንድ ስተርሊግ መግዣው 122 ብር ከ6543 ሳንቲም ፤ መሸጫው 134 ብር ከ9197 ሳንቲም ሆኗል።

ዩሮ መግዣው 110 ብር ከ2157 ሳንቲም ፤ መሸጫው ወደ 121 ብር ከ2372 ሳንቲም ጨምሯል።

አንዱ የኩዌት ዲናር መግዣው 314 ብር ከ4020 ሳንቲም መሸጫው ደግሞ 345 ብር ከ8421 ሳንቲም ገብቷል።

  ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው ...
08/02/2024



ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም እጅግ በጣም ጨምሯል። መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ23 ብር ከ3201 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ24 ብር ከ7194 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።



በአንድ ሳምንት ውስጥ የብር የመግዛት አቅም ከ57 በመቶ በላይ ተዳከመ+++++የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደርን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ የብር የመግዛት አቅም በአንድ ሳምንት ጊ...
08/02/2024

በአንድ ሳምንት ውስጥ የብር የመግዛት አቅም ከ57 በመቶ በላይ ተዳከመ
+++++

የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደርን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ የብር የመግዛት አቅም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በ57.93 በመቶ ተዳከመ።

ከአንድ ሳምንት በፊት አርብ ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም 57.48 ብር ነበረው አንድ የአሜሪካን ዶላር የመግዣ ዋጋ ዛሬ አርብ ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም. ረፋድ ወደ 90 ኢትዮጵያ ብር አሻቅቧል።

ብሔራዊ ባንክ አዲሱን ፖሊሲ ይፋ ባደረገ ማግስት የኢትዮጵያ ብር ከዶላር አንጻር ያለው የመግዛት አቅም በ30 በመቶ ተዳክሞ ነበር። የብር የመግዛት አቅም ባለፉት አምስት ቀናት በየቀኑ እየተዳከመ መጥቷል።

የግል ባንኮች ዛሬ ረፋድ ይፋ ባደረጉት የውጭ ምንዛሪ ተመን መሠረት አንድ የአሜሪካን ዶላር በ90 ብር ገደማ እየተገዛ ነው።

የዶላር የመሸጫ ዋጋ በባንኮች መካከል ልዩነት አሳይቷል። ዝቅተኛው የመሸጫ ዋጋ የተመነው መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን ይኸውም 85.6 ብር ነው። ዳሽን ባንክ ደግሞ ከፍተኛ የሆነውን 98.05 ብር የመሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።

ከአዲሱ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር መመሪያ መውጣት በኋላ ባንኮች የምንዛሪ ተመናቸውን በቀን ሁለት ጊዜ እስከ መከለስ ደርሰው ነበር። ንግድ ባንክ ባለፈው ረቡዕ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም. ለሁለት ጊዜ ያህል የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ አድርጓል።

ይህን ፈጣን የሆነ የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተችተውታል። ዐቢይ ሐሙስ ዕለት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመመለከተ ከመንግሥት ኃላፊዎች እና ከባንክ ፕሬዝዳንቶች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ “[ባንኮች] ትክክልኛ እርምጃ አይመስለንም አሁን የሄዳችሁበት የዋጋ መጠን” ብለዋል።

Via:- ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ የአርብ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሪ ተመን ይፋ አድርጓል። Friday August 2,2024
08/01/2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ የአርብ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሪ ተመን ይፋ አድርጓል። Friday August 2,2024

በአዲስ አበባ ከተማ የ50 አመት እድሜ ያላቸው ዘመናዊ ጎጆ ቤቶች በኮሪደር ልማት ምክንያት ሊፈርሱ ነው    በአዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኙ...
08/01/2024

በአዲስ አበባ ከተማ የ50 አመት እድሜ ያላቸው ዘመናዊ ጎጆ ቤቶች በኮሪደር ልማት ምክንያት ሊፈርሱ ነው

በአዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኙ የሃምሳ ዓመት እድሜ ያላቸው 31 ጎጆ ቤቶች በከተማይቱ አስተዳደር ትዕዛዝ ሊፈርሱ ነው። ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን የሆኑት ጎጆ ቤቶቹ የሚፈርሱት፤ ቦታው “ለኮሪደር ልማት” ስለሚፈለግ እንደሆነ ተገልጿል።

↪️ ጎጆ ቤቶቹ የተሰሩት፤ የኢትዮጵያ ሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር በመስከረም 1966 ዓ.ም. ባስመረቀው ባለ ዘጠኝ ወለል ህንጻ አካል በመሆን ነበር።

↪️ በስተኋላ ላይ ለኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን የተላለፈው ይህ ህንጻ “በዲዛይን ልህቀቱ፣ በቦታ አጠቃቀሙ፣ ባህላዊ እሳቤን በዘመናዊ አሰራር ያወሃደ” በመሆኑ ተጠቃሽ እንደሆነ የኪነ ህንጻ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

↪️ ባለሙያዎቹ ህንጻውን እና የእርሱ አካል የሆኑትን ጎጆ ቤቶች፤ “የአዲስ አበባ ምልክት ከሆኑ” ግንባታዎች መካከል ይመድቧቸዋል።

↪️ እነዚህን ጎጆ ቤቶች ተከራይተው ለረጅም አመታት ለህዝብ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የንግድ ድርጅቶች፤ ከትላንት በስቲያ ጀምሮ ስፍራውን “በአስቸኳይ” ለቅቀው እንዲወጡ እንደተነገራቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

↪️ ይኸው ትዕዛዝ፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ማክሰኞ ሐምሌ 23፤ 2016 ለተከራዮች ባሰራጨው ደብዳቤ ላይ በጉልህ ሰፍሯል።

↪️ ፌዴሬሽኑ ተከራዮቹን “በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ” ያዘዘው፤ ከአንድ ቀን በፊት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽህፈት ቤት የደረሰውን ደብዳቤ መሰረት በማድረግ ነው።

ዶላር ዛሬ ከሰዓት ጨምሯል።በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥዋት የነበረው የዶላር ዋጋ ዛሬ ከሰዓት ጨምሯል።ባንኩ አንዱን ዶላር በ80 ብር ከ0203 ሳንቲም እየገዛ በ81 ብር ከ6207 ሳንቲም እየሸ...
07/31/2024

ዶላር ዛሬ ከሰዓት ጨምሯል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥዋት የነበረው የዶላር ዋጋ ዛሬ ከሰዓት ጨምሯል።

ባንኩ አንዱን ዶላር በ80 ብር ከ0203 ሳንቲም እየገዛ በ81 ብር ከ6207 ሳንቲም እየሸጠ ነው።

በተመሳሳይ ፓውንድ ስተርሊንግም ጨምሯል።

አንዱን ፓውንድ ስተርሊንግ በ97 ብር ከ8436 ሳንቲም እየገዛ በ99 ብር 8005 እየሸጠ ነው።

ዩሮ 86 ብር ከ5019 ሳንቲም እየገዛ በ88 ብር ከ2320 ሳንቲም እየሸጠ ነው።

(ሌሎች የከሰዓት የውጭ ምንዛሬ ዝርዝሮችን ከላይ ተመልከቱ)

ብዙ እዳ ስላለበኝ የተከፈለኝን አልናገርም " ለመጀመሪያ ጊዜ ከልጆቼ ጋር ብራንድ አምባሳደር ሆኛለሁ | የኪው ኪው አምባሰደር ትንሳኤ ብርሃነ
07/30/2024

ብዙ እዳ ስላለበኝ የተከፈለኝን አልናገርም " ለመጀመሪያ ጊዜ ከልጆቼ ጋር ብራንድ አምባሳደር ሆኛለሁ | የኪው ኪው አምባሰደር ትንሳኤ ብርሃነ

ብዙ እዳ ስላለበኝ የተከፈለኝን አልናገርም " ለመጀመሪያ ጊዜ ከልጆቼ ጋር ብራንድ አምባሳደር ሆኛለሁ | የኪው ኪው አምባሰደር ትንሳኤ ብርሃነ EthiopiaSubscribe to our channel Amharic Tube and enjoy Ethiopian...

እስከ 400 ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ ከውጭ ምንዛሬ ተመን ለውጥ በኋላ ገበያው እንዴት ዋለ?የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ጀምሮ በገበያ ስርዓት እንዲመራ መወሰኑን ተከትሎ፤ በአዲስ አበባ መርካ...
07/29/2024

እስከ 400 ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ

ከውጭ ምንዛሬ ተመን ለውጥ በኋላ ገበያው እንዴት ዋለ?

የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ጀምሮ በገበያ ስርዓት እንዲመራ መወሰኑን ተከትሎ፤ በአዲስ አበባ መርካቶ ገበያ እስከ 400 ብር የደረሰ የዋጋ ጭማሪ ተመዘገበ።

የዋጋ ጭማሪው በዋናነት የታየው፤ ከውጭ ሀገር በሚገቡ የታሸጉ ምግብ እና መጠጦች እንዲሁም ሌሎች ሸቀጦች ላይ ነው።

ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 22፤ 2016 ከሰዓት በኋላ በመርካቶ የተለያዩ የገበያ ስፍራዎች የተዘዋወረው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ፤ ከውጭ ሀገር በሚገቡ ሸቀጦች ላይ የታየውን ያህል ጭማሪ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ አለመደረጉን ለመታዘብ ችሏል።

ዘጋቢው የመጀመሪያውን ቅኝት ያደረገው “ሲዳሞ ተራ” በሚባለው የምግብ ዘይት ምርቶች በስፋት በሚሸጥበት እና በሚከፋፈልበት አካባቢ ነው።

በዚሁ ተራ ከውጭ በሚገቡ የምግብ ዘይት ምርቶች ላይ በዛሬው ዕለት ብቻ ከ30 ብር እስከ 400 ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ነጋዴዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

የዋጋ ጭማሪው “እንደ ዘይቱ ዓይነት እና ተፈላጊነት የተለያየ መሆኑን” ነጋዴዎቹ አስረድተዋል።

የዋጋ ጭማሪ ካሳዩ “በብዙ ደንበኞች ተፈላጊ ናቸው” ከተባሉት የምግብ ዘይት ዓይነቶች መካከል፤ “ሰንፍላዎር”፣ “ኦማር”፣ “ሃያት” እና “ኦርካይድ” የተባሉት ይገኙበታል።

[ፎቶ፦ ከፋይል የተወሰደ]

ስድስት የግል ባንኮች በአዲሱ የውጭ ምንዛሬ ግብይት መጠቀም አልጀመሩም  የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ “በገበያ ላይ የተመሰረተ” እንደሚሆን ቢያስታውቅም፤ ስድስ...
07/29/2024

ስድስት የግል ባንኮች በአዲሱ የውጭ ምንዛሬ ግብይት መጠቀም አልጀመሩም

የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ “በገበያ ላይ የተመሰረተ” እንደሚሆን ቢያስታውቅም፤ ስድስት የግል ባንኮች የውጭ ገንዘቦችን የሚገዙበትን እና የሚሸጡበትን የተሻሻለ ተመን እስከ እኩለ ቀን ድረስ ይፋ አለማድረጋቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ።

የየባንኮቹ ኃላፊዎች በተመኑ ላይ ለመነጋገር ዛሬ ረፋዱን በየፊናቸው ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

እስከ ዛሬ ድረስ በነበረው አሰራር ባንኮች የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዙበት እና የሚሸጡበትን ተመን የሚያወጣላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነበር።

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ጠዋት ባወጣው መግለጫ፤ የውጭ ምንዛሬ ተመኑ “በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ስርአት መሸጋገሩን” አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በኋላ “ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ” እንደሚሆንም ገልጿል። ይህን የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ለውጥ ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ከሁሉም አስቀድሞ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው።

የግል ባንኮች ያወጣሉ ተብሎ የሚጠበቀው የውጭ ምንዛሬ ተመን፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተመን ጋር “ተመሳሳይ ይሆናል” ብለው እንደሚጠብቁ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነገረቻቸው የአንድ የግል ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ ተናግረዋል። ባንኮች ተመኑን የሚወስኑት ያላቸውን የውጭ መገበያያ ገንዘብ ክምችት መሰረት አድርገው መሆኑንም አክለዋል።

ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ጀምሮ፤ “በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ስርአት እንደተሸጋገረ” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።ይህን ተከትሎ የአንድ ዶላር...
07/29/2024

ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ጀምሮ፤ “በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ስርአት እንደተሸጋገረ” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።ይህን ተከትሎ የአንድ ዶላር የምንዛሬ ዋጋ 76 ብር ገብቷል።

የኢትዮጵያ “በገበያ ላይ የተመሰረተ” የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓትን ተግባራዊ ልታደርግ ነውየኢትዮጵያ መንግስት “በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት” ተግባራዊ ሊያደርግ እንደ...
07/28/2024

የኢትዮጵያ “በገበያ ላይ የተመሰረተ” የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓትን ተግባራዊ ልታደርግ ነው

የኢትዮጵያ መንግስት “በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት” ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሆነ አስታወቀ። ውሳኔው በመንግስት ቁጥጥር ሲከናወን የቆየውን የውጭ ምንዛሬ ግብይት “በገበያው አማካኝነት እንዲበየን” የሚያደርግ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ እሁድ ማምሻውን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን ብር፤ ዶላር እና ፓውንድን ከመሳሰሉ ዋና ዋና የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሬ ተመን ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል። አሁን በስራ ላይ በሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት፤ ባንኮች አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ54 ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ ገዝተው በ58 ብር ከ64 ሳንቲም ገደማ ይሸጣሉ። በተለምዶ "ጥቁር" እየተባለ በሚጠራው ትይዩ ገበያ በአንጻሩ፤ ይህ የምንዛሪ ተመን ከእጥፍ በላይ ልዩነት አለው።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት፤ ውሳኔው “በአቅርቦት እና በፍላጎት መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ መዛባት ለማስተካከል ይረዳል” ብሏል። የውጭ የምንዛሪ ተመን ስርዓት በገበያው ፍላጎት መሰረት ሲከወን፤ “የገቢ እና የወጪ ሸቀጦችን እና አገልግሎቶችን ዋጋ ከገበያ እውነታዎች ጋር እንዲጣጣም ያስችላል” ያለው መንግስት፤ “በክፍያ ሚዛን ላይ ያለውን አለመመጣጠንም ለማስተካከል ይረዳል” የሚል ተስፋውን ገልጿል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ከ1ሺ በላይ ተማሪዎች እና ሠራተኞች ያሉት አዲስ ግሎባል ትምሕር ቤት ሊፈርስ መሆኑ ተነገረ።በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘውና ላለፉት 20 ዓመታት ከኬጂ እስከ 12ኛ ክፍል ሲያስተምር ...
07/28/2024

ከ1ሺ በላይ ተማሪዎች እና ሠራተኞች ያሉት አዲስ ግሎባል ትምሕር ቤት ሊፈርስ መሆኑ ተነገረ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘውና ላለፉት 20 ዓመታት ከኬጂ እስከ 12ኛ ክፍል ሲያስተምር የቆየው ትምሕርት ቤቱ በኮሪደር ልማቱ ምክንያት እንዲፈርስ መወሰኑ ተነግሯል።

ለ2017 የትምሕርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ግዜ እስከ ሐምሌ 15 መሆኑና ሁሉም ትምሕርት ቤቶች መዝግበው ከጨረሱ በኋላ እንደሚፈርስ መገለጹ ድንጋጤን ፈጥሮብናል ብለዋል የትምሕርት ቤቱ ማኅበረሰቦች።

በትምሕርት ቤቱ ውስጥ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆች ዛሬ ረፋድ ላይ ከወረዳው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ቢነጋገሩም ሳይስማሙ በመቅረታቸው አዲስ ኮሚቴ አዋቅረው ወደ ከንቲባ ጽ/ቤት አቤቱታቸውን ለማሰማት መወሰናቸን ከትምሕርት ቤቱ ወላጆች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Via Arts Tv world

በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ለሞቱ ዜጎች ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታወጀየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ ቅዳሜ ሐምሌ 20፤ 2016 ጀምሮ ያሉት ተከታታይ ሶስት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንዲ...
07/26/2024

በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ለሞቱ ዜጎች ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታወጀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ ቅዳሜ ሐምሌ 20፤ 2016 ጀምሮ ያሉት ተከታታይ ሶስት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንዲሆኑ አወጀ። ምክር ቤቱ የሀዘን ቀኑን ያወጀው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ባለፈው ሰኞ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ዜጎችን ለማሰብ ነው።

በጎፋ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች 257 መድረሳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትላንትናው ዕለት ባወጣው ሪፖርት አስታውቆ ነበር። የሟቾቹ ቁጥሩ እስከ 500 ድረስ ሊያሻቅብ እንደሚችልም ድርጅቱ የአካባቢውን ባለስልጣናት ዋቢ በማድረግ ገልጿል።

እንዲህ አይነት አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ብሔራዊ ሀዘን የማወጅ ስልጣን በአዋጅ የተሰጠው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። አደጋው የተከሰተው ፓርላማው በስራ ላይ በማይሆንበት ወቅት ከሆነ፤ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅ ውሳኔ ሊያሳልፉ እንደሚችሉም በአዋጅ ተደንግጓል።

በዚህም መሰረት የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፤ በጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ለማሰብ ከነገ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ብሔራዊ የሀዝን ቀን ሆኖ እንዲታወጅ መወሰናቸውን ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በእነዚህ የሀዘን ቀናት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ የሚውለበለብ ይሆናል።

የዚህ ውሳኔ ተፈጻሚነት በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ መርከቦች ላይ እንደሚሆን በተወካዮች ምክር ቤት መግለጫ ላይ ተመልክቷል።

Via (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

⚫️

Address

Santa Monica, CA
90403

Opening Hours

Monday 9am - 6pm
Tuesday 9am - 6pm
Wednesday 9am - 6pm
Thursday 9am - 6pm
Friday 9am - 6pm

Telephone

+13105709291

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AmharicTube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to AmharicTube:

Videos

Share

Nearby media companies


Other Media/News Companies in Santa Monica

Show All