Zehabesha

Zehabesha The official page of Zehabesha Newspaper and Zehabeshanews.com Ze-habesha is a free bilingual newspaper with production based in the Minnesota.

Ze Habesha LLC is an Ethiopian American media company based in Minnesota, with presence in the print and broadcast media. Zehabesha strives to provide unbiased information to the ever-growing Ethiopian American community and works toward bridging cultures
Ze-Habesha is a diversified news and information newspaper that represents America’s local and national Ethiopian community. Zehabesha, publishe

d bi-monthly by the Ze-Habesha LLC, has been in publication for 7 years. As of early 2008, Ze-Habesha has non paid subscribers, with a total circulation of 10,000 copies in Major Twin cites areas, including South Dacota, Chicago, Dallas, Atlanta, Las Vegas, and etc...
Ze-Habesha Newspaper has a number of blogs that are updated regularly with community events and news. Please Visit us www.Zehabeshanews.com

የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር  የህፃን ሔቨንን ጉዳይ አቃሎና የህዝብን ሞራል ባልጠበቀ መንገድ  ነውረኛ መግለጫ ያወጣው በዚህ ሰው እየተመራ ነው።የማህበሩ መሪና መግለጫውን ያወጣው አቶ ብርሐኑ...
08/18/2024

የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር የህፃን ሔቨንን ጉዳይ አቃሎና የህዝብን ሞራል ባልጠበቀ መንገድ ነውረኛ መግለጫ ያወጣው በዚህ ሰው እየተመራ ነው።

የማህበሩ መሪና መግለጫውን ያወጣው አቶ ብርሐኑ አሰፋ ነው።

08/18/2024
🔵“ውጤቱን በእርግጥ አልጠበኩትም ነበር። ተጫዋቼ ምን ማድረግ እንደሚችሉ አውቃለሁ፣ ነገር ግን እንደመጀመሪያ ጨዋታ ቀን እና በቂ ስላላገኙ አልጠበኩትም ውጤቱን። ደግሞ ያለፈው ሲዝን በስታምፎ...
08/18/2024

🔵“ውጤቱን በእርግጥ አልጠበኩትም ነበር። ተጫዋቼ ምን ማድረግ እንደሚችሉ አውቃለሁ፣ ነገር ግን እንደመጀመሪያ ጨዋታ ቀን እና በቂ ስላላገኙ አልጠበኩትም ውጤቱን። ደግሞ ያለፈው ሲዝን በስታምፎርድ ብሪጅ ማሸነፍ አልቻልንም፤ ስለዚህ ይህ የዛሬው ድል መልካም ዜና ነው። መጥፎው ዜና አሁንም ስድሳ አምስት እና ሰባ ጨዋታዎች ይቀሩናል። ግን ለመተማመን በድል መጀመር ጥሩ ነው።”
አሰልጣኝ ጋርዲዮላ ክለባቸው ማንቸስተር ሲቲ ቸልሲን 2ለ0 ካሸነፈ በኋላ ከተናገሩት
🔵እንደ ኦፕታ ሪፖርት ከሆነ፤ ማንቸስተር ሲቲ ያለፉትን 10 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች እያንዳንዳቸውን ሲያሸንፍ በእያንዳንዱ ድል ቢያንስ 2 ጎሎችን አስቆጥሯል።
🔵ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ ስንተኛ ሆኖ የሚጨርስ ይመስላችኋል? ኮመንት ጻፉ

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር  በታዳጊዋ ሄቨን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን አሁንም በድጋሜ ይገልጿል።ከተማ አስተዳደሩ ሀምሌ 25 / 2015 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ዳግማ...
08/18/2024

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በታዳጊዋ ሄቨን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን አሁንም በድጋሜ ይገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩ ሀምሌ 25 / 2015 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ በ7 አመቷ ታዳጊ ህጻን ሄቨን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊትና ህልፈተ ህይወት በእጅጉ ማዘኑን ገልፆ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

በህጻናት ላይ የሚፈጸምን ማንኛውም ጥቃት መከላከል በዋነኛነት የመንግስት ሃላፊነት ሲሆን በሌላ በኩል የሁሉም አካል ተመሳሳይ ድርሻ ያለው መሆኑን የገለፀው ከተማ አስተዳደሩ እንደዚህ አይነት አስነዋሪና አሳፋሪ ድርጊት በከተማችን በመፈፀሙ በእጅጉ ዛሬም በድጋሜ አዝነናል ።

የባሕር ዳር ከተማ ህዝብ ሰው ወዳድ፣ ሁሉን አክባሪ፣ ባህሉን፣ ወጉንና ታሪኩን ጠባቂ አስተዋይ ጨዋ ህዝብ ነው ። በዚህ እሴትና ባህል በተገነባ ማህበረሰብ ውስጥ የተፈፀመው ድርጊት በፍፁም ነውረኛና የከተማውን ህዝብ የማይገልፅ ሁሉም ሰው ሊያወግዘው የሚገባ ዘግናኝ ተግባር ነው ።

ሁሉም እንደሚያስታዉስዉ ወንጀሉ እንደተፈፀመ የከተማ አስተዳደሩ የሚመለታቸው ተቋማት በዋነኝነትም ከፖሊስ ፣ ከጤና ተቋም ፣ ከፍትህ እንዲሁም ከተበዳይ ወገኖች ጋር በመቀናጀት ጉዳዩ በህግ እንዲያዝ በማድረግ ልዩ ትኩረትና ክትትል በማድረግ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ ተይዞ በ20/06/2016 ዓ.ም በከፍተኛ ፍርድ ቤት የ25 አመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበት ባህርዳር ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል። በዚህ አጋጣሚ ከተማ አስተዳደሩ የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ነፃነት የሚያከብር ቢሆንም ከተፈፀመው ዘግናኝ ድርጊትና የማህበረሰቡን ሞራልና ክብር ዝቅ ያደረገ ወጀል በፈፀመው ወንጀለኛ ላይ የተሰጠው ፍርድ አስተማሪነት የሚያንሰው መሆኑን አስተዳደሩ በፅኑ ያምናል ።

ከተማ አስተዳደሩ ጉዳን በጥብቅ ለመከታተል ባለው ፅኑ አቋም ክልሉን ባጋጠመው ቀውስ ወንጀለኛው ከማረሚያ ቤት አምልጦ የወጣ መሆኑን እንዳወቀ በልዩ ሁኔታ የፀጥታ ሀይሉ ክትትል እንዲያደርግ አመራር ተሰጦ ወንጀለኛው ተይዞ ድጋሜ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ወቅት ወንጀለኛው ይግባኝ የጠየቀ እንደሆነ እና ጉዳዩ ለጥቅምት 20/2017 ዓ.ም ፍ/ቤቱ ቀጠሮ የሰጠ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ያውቃል። የፍርድ ቤቱን ነጻነት በጠበቀ መልኩ ከህግ አኳያ የይግባኙን ሁኔታ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትኩረት የምንከታተለው እና ፍትህ እንዲረጋገጥ በፅናት የምንታገል እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን።

ከተማ አስተዳደሩ በልጃችን ህፃን ሄቨን ለደረሰው ግፍ ፍትህ ሲጠይቅ ፣ለጉዳዩ ለሰጠው ትኩረት እና እያደረገ ላለው ትግል ለመላው የህብረተሰብ ክፍል ምስጋና እያቀረብን በቀጣይም ለፍትህ መረጋገጥ ለምናደርገው ትግል ህ/ሰቡ ከጎናችን እንዳይለይ ጥሪያችን እያቀረብን በቀጣይም የህፃናት ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ስለሆነ በትብብር መስራት ይጠበቅብናል።

ነሐሴ 12/2016ዓ.ም
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር

የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ማህበር የሚባል እጅግ የነውረኞችና የግፈኞች ማህበር የሚመራው ማን ነው ?በህፃን ፌቨን ላይ የተፈፀመውን አስቃቂ ወንጀል የሚቃወምና  ማህበረሰብ የናቀና የሚያስ...
08/18/2024

የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ማህበር የሚባል እጅግ የነውረኞችና የግፈኞች ማህበር የሚመራው ማን ነው ?
በህፃን ፌቨን ላይ የተፈፀመውን አስቃቂ ወንጀል የሚቃወምና ማህበረሰብ የናቀና የሚያስፈራራ የአማራ ክልል ፍርድቤት ዳኞች ማህበር የሚመራው በማን ነው ?

የዚህን ማህበር የሚመሩ ሰዎችን ስምና ፎቶ ግራፍ በውስጥ ላኩልን!

08/18/2024

እሳት ስለተነሳበት የኢትዮጵያ አውሮፕላን ዛሬ የመጣው አዲስ መረጃ

08/18/2024

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ልጅ ሰመሀል መለስ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረገችው ቃለምልልስ ‹‹ህወሀት ስለአባቴ ዋሽቷል›› አለች፡፡ ሰመሀል ትጋት ከተባለ ሚዲያ ጋር ባከናወነችው ከአንድ ሰአት ከሩብ በላይ የፈጀ የእንግሊዘኛ ቃለምልልስ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስታለች፡፡

በአሁኑ ወቅት የመጀመሪያ መፅሀፏን ለአንባቢ ለማቅረብ ስራውን በማጠናቀቅ ላይ የምትገኘው ሰመሀል ‹‹መፃፍን የምመርጠው ጥሩ ተናጋሪ ስላልሆንኩ ነው፡፡ ከማውራትና ከመናገር መፃፍ ያስደስተኛል፡፡›› ብላለች፡፡ የመለስ ፋውንዴሽንን በምትጎበኝበት ወቅት ስጎበኝ በርካታ ነገሮችን ለማንበብ መቻሏን ጠቅሳም በፋውንዴሽኑ በተለይ ስለትግራይ እንዲሁም ስለኢትዮጵያ መረጃ የያዙ የተከማቹ መፅሀፍት መኖራቸውን አስረድታለች፡፡ ‹

‹ህወሀት ከነበረው ጥሩ ልምድ ሊጠቀስለት የሚችለው እውቀትን ለማምረት የነበረው ቁርጠኝነት ነው፡፡›› ያለችው ሰመሀል ከፋውንዴሽኑ በተጨማሪ ከፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ ጋር ለረጀም ጊዜ አብራ መሆኗ በመሆኔ ትልቅ እውቅት ልታገኝበት እንደቻለች አስረድታለች፡፡

‹‹አባትሽን ለመምሰል ወይንም ለመተካት ታስቢያለሽ ወይ?›› ተብላ ተጠይቃም ‹‹በእርግጥ ከአባቴ ጋር እቀራረብ ነበር፡፡ ይሁንና እሱ ነገሮችን እንዴት ማሰብ እንዳለብኝ ይመክረኝ ነበር እንጂ በቀጥታ ያስተማረኝ የለም፡፡ በምሳ ወይንም በራት ወቅት በምናደርገው ውይይት ለጉዳዮች እንዴት አይነት አመለካከት ሊኖረኝ እንደሚገባ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ እንድገነዘብ አድርጎኛል፡፡ እሱን ለመምሰል ግን አልሞክርም፡፡ ግን መመሳሰል ሊኖር ይችላል፡፡›› በማለት መልሳለች፡፡

ስለአቶ መለስ ዜናዊ የግል ህይወት ተጠይቃም አባቷ የግል ህይወቱን መናገር የማይፈልግ እንደነበር ገልፃ ያንን እኔም መጣስ እንደማትፈልግ አስታውቃለች፡፡ ጨምራም ‹‹የአባቴን አቋም ባልጥስም ከእሱ ጋር ስሆን በጣም ደስ የሚለኝ አብሬው ዜና ማየት ነበር፡፡፡ እና በዜናው ላይ የሚሰጠው አስተያየት ወይንም ያንን ተከትሎ የሚቀልደው ነገር የማልረሳው ነው፡፡ እንዲሁም ለትግራይ ህዝብ በተለይም ለትግራይ ሴቶች ያለው ፍቅርና ለእኔ የሚሰጠኝ ነፃነት የማይረሳ ነው›› ብላለች፡፡ ሰመሀል ስለወቅታዊ ሁኔዎች ጥያቄዎች ተነስተውላት መልስ የሰጠች ሲሆን ስትናገርም ‹‹የህወሀትን ዳግመኛ ምዝገባ በተመለከተ የማውቀው ነገር የለም፡፡

ስለሁኔታው የነገረኝ ያብራራልኝ ሰውም የለም፡፡ ስለዚህ ምንም አስተያየት ልሰጥ አልችልም፡፡ የቱን መተውና የቱን መከተል እንዳለብንም አላውቅም፡፡ ግን በጉዳዩ ላይ የሀሳብ ልዩነት እንዳለተ ተገንዝቤያለሁ፡፡›› በማለት ገልፃለች፡፡ የፕሪቶሪያውን የተኩስ አቁም ስምምነት በጥቂቱም ቢሆን ለመመለክት መቻሏን ጠቅሳም የስምምነቱ ትልቁ ችግር ትግራይ በተመረጠ መንግስት መመራት እንዳለበት የሚገልፀውን መሰረተ ሀሳብ መጣሱ መሆኑን አስረድታለች፡፡ ‹‹ሁላችንንም ሊያሰባስበን የሚችለው ይህ ጥላ ነበር፡፡ ይህንን የአስተዳደር መዋቅር ከተውነው ግን መበታተን መምጣቱ አይቀርም፡፡ አሁን የተፈጠረውን መከፋፈል የፈጠረው ይህ ነው፡፡›› ያለችው ሰመሀል በትግራይ ክልል በመንግስት ተቋማት ላይ ትልቅ እምነት እንደነበረ ጠቅሳ ከጦርነቱ በኋላ ግን ይህ እምነት መጥፋቱን አስረድታለች፡፡ ይህ ደግሞ አደገኛ እንደሆነና ችግሮችንና አለመግባባቶችን ለመፍታት ወደሌላ መንገድ ለምሳሌ ጠመንጃ ወደማንሳት ሊኬድ የሚችልበትን እድል እንደሚፈጥር አሳስባለች፡፡

የትግራይን መገንጠል በተመለከተ ተጠይቃ ስትመልስ ደግሞ ‹‹በምሁራን ብቻ ሳይሆን በአብዛኛው ህዝብ ፍላጎት መመራት ይኖርብናል፡፡ መገንጠልን የሚያቀነቅኑ ምሁራን ቀድመው ለትግራይ ህዝብ ምን ይጠቅመዋል ወይንም ምን ይጎዳዋል የሚለውንም በጥልቀት ማሰብ መቻል ይኖርባቸዋል፡፡›› ብላለች፡፡

ትግራይ የጥቂት በውጭ የሚኖሩ ምሁራን ብቻ ሳትሆን በገጠር የሚኖረው አርሶ አደርም ጭምር መሆኗን ገልፃም ይህ የመገንጠል ጉዳይ በአብዛኛው ህዝብ ፍላጎት ላይ መወሰን እንዳለበት አስረድታለች፡፡ የትግራይ ሉአላዊነት ራሱ ምን መምሰል እንዳለበት በቅድሚያ ሊፈተሽ እንደሚገባው ያሳሰበችው ሰመሀል ጨምራም ‹‹ከኢትዮጵያ የበላለጡ ትልልቅ አገራት እንዳሉ መታወቅ አለበት፡፡ ወደትላልቅ ከተሞች እንደትግራይ ሆነህና እንደኢትዮጵያ ሆነህ ስትሄድ የሚኖርህ አቅም አንድ አይደለም፡፡ እንደኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን እንደአፍሪካ ስትሆን ደግሞ የበለጠ አቅም ታዳብራለህ፡፡›› የሚል አስተያየት ሰጥታለች፡፡

ትግራይ ክልል በኢትዮጵያ ፌዴራል ስርአት ውስጥ እስካለ ድረስ በአገሪቱ ህገ መንግስት መመራት እንዲያስፈልግ የጠቆመችው ሰመሀል የሚፈጠሩ ችግሮችም በዚያው መሰረት መፈታት እንደሚገባቸው ገልፃለች፡፡ ህወሀት የአባቷን የአቶ መለስ ዜናዊን ቅርስና ውርስ ወይንም ሌጋሲ እያስቀጠለ መሆኑን መናገሩን በተመለከተ ለቀረበላት ጥያቄም ‹‹ውሸት ነው፡፡›› ብላለች፡፡

ሰመሀል እንዳለችው የአባቷ የመለስ ፎቶ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚከናወኑ የህወሀት ስብሰባዎችና ጉባኤዎች ላይ ተለጥፎ የሚታይ ቢሆንም በተግባር ግን ምንም የለም፡፡ ህወሀት የመለስን ፕሮግራም በይፋ ቀይሮ ውርስና ቅርሱን እያስቀጠልኩ ነው ማለቱንም በቅሬታ አንስታለች፡፡

ፍትሕ!የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ ወይ?
08/18/2024

ፍትሕ!
የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ ወይ?

08/18/2024

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ እና ለነሐሴ ሚካኤል በሰላም አደረሳችሁ

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ እና ለነሐሴ ሚካኤል በሰላም አደረሳችሁ እያለች የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእለቱን ጸሎተ ማኅሌትና ቅዳሴ በቀጥታ ሥርጭት ታስተላልፋለች - ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ -ነሐሴ 12 ቀን , 2015 (Aug 18, 2024).

ለህግ የበላይነት እና ለፍትሃዊነት በሚል የተቋቋማችሁ ተቋማት ጉዳዩን ማውገዝና የተለየ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል።በተለይም በአማራ ክልል ለፍትህና ለህግ የበላይነት ስልጣንና ሀላፊነት ለተሰጣችሁ...
08/18/2024

ለህግ የበላይነት እና ለፍትሃዊነት በሚል የተቋቋማችሁ ተቋማት ጉዳዩን ማውገዝና የተለየ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል።

በተለይም በአማራ ክልል ለፍትህና ለህግ የበላይነት ስልጣንና ሀላፊነት ለተሰጣችሁ ተቋማትም ማለትም
1- የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ
2 . የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት
3. የአማራ ክልል የዓቃቢ ህግ ማህበረ
4. የአማራ ክልል ጠበቆች ማህበረ
5. የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር
ቢያንስ ድርጊቱን በማውገዝ ብህረሰቡ ጎን ልትቆሙ ሲገባ በዝምታ ማሳየታችሁ አግባብ አይደለም።

በሌላ በኩል ወንጀለኛው ይግባኝ የጠየቀና በክርክር ላይ ያለ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የተካሄደው  ዓለም አቀፍ የቦክስ ውድድር ተጠናቀቀ የአፍሪካ የቦክስ ኮንፌዴሬሽን ከዓለም አቀፉ የቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የቦክስ ው...
08/18/2024

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የተካሄደው ዓለም አቀፍ የቦክስ ውድድር ተጠናቀቀ

የአፍሪካ የቦክስ ኮንፌዴሬሽን ከዓለም አቀፉ የቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የቦክስ ውድድር አካሂዷል።

በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው የዓለም አቀፉ የቦክስ ፌዴሬሽን ‘ቻምፒየንስ ናይት’ የቦክስ ውድድር፤ ኢትዮጵያውያን ቦክሰኞች ጥሩ ተፎካካሪ ቢሆኑም ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

በውድድሩ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሩስያ፣ ኡዝቤኪስታን፣ ጋና፣ ካዛኪስታን፣ ሜክሲኮ እና ሞሮኮ የተወጣጡ ከ10 በላይ ፕሮፌሽናል ቦክሰኞች ተሳትፈዋል።

በውድድሩ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ፣ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትን አቶ ኢያሱ ወሰን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

በሎንዶውስኪ 2 ጎሎች ባርሴሎና ቫለንሺያን 2ለ1 አሸንፎ ጣፋጩን 3 ነጥብ ይዞ ተመልሷል::
08/17/2024

በሎንዶውስኪ 2 ጎሎች ባርሴሎና ቫለንሺያን 2ለ1 አሸንፎ ጣፋጩን 3 ነጥብ ይዞ ተመልሷል::

ብዙዎች ባቀረባችሁት ጥያቄ መሰረትብዙዎች ይህች እናት የደረሰባትን ግፍ አይታችሁ አዝናችሁ ድጋፍ ማድረግ እንደምትፈልጉ ጠይቃችሁ ነበር ይች እህታችን ልጇን በግፍ ያጣች ፍትህን ለማግኘት ስራዋ...
08/17/2024

ብዙዎች ባቀረባችሁት ጥያቄ መሰረት
ብዙዎች ይህች እናት የደረሰባትን ግፍ አይታችሁ አዝናችሁ ድጋፍ ማድረግ እንደምትፈልጉ ጠይቃችሁ ነበር ይች እህታችን ልጇን በግፍ ያጣች ፍትህን ለማግኘት ስራዋን ጥላ የተንከራተተች ብዙ ግፍ እና በደልን ያሳለፈች ናት ብዙዎች መርዳት ፈልጋችሁ ለጠየቃችሁ አካውንቱን ይዘን ቀርበናል

በነገራችን ላይ እህታችን ፍትህን እንጂ ገንዘብን አልፈልግም ብላ ብዙ ብትሞግትም በሚቀርቧት ሰወች በመለመን እና በማግባባት ስራ ጥላ በመንከራተት ምክንያት ለወደፊት የጠበቃ የሚሆን ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት አግባብተው አሳምነው አካውንቷን
ተቀብለዋል ::
እኔ ፍትህን ብቻ ነው የምፈልግ የባህር ዳር ህዝብ በችግር ከጎኔ ነበር ያጣሁ ፍትህ እንጂ ምግብ አደለም ብላ አምርራ ሞግታ ነበር በብርቱ ማግባባት ለምትፈልጊው ፍትህም ቢሆን ለጠበቃ ገንዘብ ያስፈልጋል በማለት አሳምነው አካውንቱን ተቀብለዋል ::

ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ
ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ1000177318934
አበቅ የለሽ አደባ

የጥንቃቄ መልዕክትአጭበርባሪዎች ግፍ አይፈሩም። ያሳዝናል። ሃሰተኛ የባንክ ቁጥሮችን በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ እርዳታ የሚያሰባስቡና ራሳቸው ኪስ የሚከቱ እንዳሉ ተደርሶበታል።እናቷን በትክልል...
08/17/2024

የጥንቃቄ መልዕክት
አጭበርባሪዎች ግፍ አይፈሩም። ያሳዝናል። ሃሰተኛ የባንክ ቁጥሮችን በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ እርዳታ የሚያሰባስቡና ራሳቸው ኪስ የሚከቱ እንዳሉ ተደርሶበታል።
እናቷን በትክልል አግኝታችሁ በምትሰጣችሁ አካውንት ብታስገቡ የተሻለ ነው። አለበለዚያ ርህራሄ ያልፈጠረባቸው አጭበርባሪዎች ሰለባ ትሆናላችሁ።
ፍትሕ ለሔቨን
-

ብዙዎች ባቀረባችሁት ጥያቄ መሰረት
ብዙዎች ይህች እናት የደረሰባትን ግፍ አይታችሁ አዝናችሁ ድጋፍ ማድረግ እንደምትፈልጉ ጠይቃችሁ ነበር ይች እህታችን ልጇን በግፍ ያጣች ፍትህን ለማግኘት ስራዋን ጥላ የተንከራተተች ብዙ ግፍ እና በደልን ያሳለፈች ናት ብዙዎች መርዳት ፈልጋችሁ ለጠየቃችሁ አካውንቱን ይዘን ቀርበናል

በነገራችን ላይ እህታችን ፍትህን እንጂ ገንዘብን አልፈልግም ብላ ብዙ ብትሞግትም በሚቀርቧት ሰወች በመለመን እና በማግባባት ስራ ጥላ በመንከራተት ምክንያት ለወደፊት የጠበቃ የሚሆን ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት አግባብተው አሳምነው አካውንቷን
ተቀብለዋል ::
እኔ ፍትህን ብቻ ነው የምፈልግ የባህር ዳር ህዝብ በችግር ከጎኔ ነበር ያጣሁ ፍትህ እንጂ ምግብ አደለም ብላ አምርራ ሞግታ ነበር በብርቱ ማግባባት ለምትፈልጊው ፍትህም ቢሆን ለጠበቃ ገንዘብ ያስፈልጋል በማለት አሳምነው አካውንቱን ተቀብለዋል ::

ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ
ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ1000177318934
አበቅ የለሽ አደባ

ትክክለኛ የአርሰናል ደጋፊ ይህን ፖስት ካለ ላይክና ኮመንት አያልፈውም።ዊሊያም ሳሊባ ከ66 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ 50ውን  በማሸነፍ ፈጣኑ ተጫዋች ነው።በነዚህ ጨዋታዎች 30 ንፁህ ...
08/17/2024

ትክክለኛ የአርሰናል ደጋፊ ይህን ፖስት ካለ ላይክና ኮመንት አያልፈውም።
ዊሊያም ሳሊባ ከ66 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ 50ውን በማሸነፍ ፈጣኑ ተጫዋች ነው።
በነዚህ ጨዋታዎች 30 ንፁህ ጎል (ክለቡ ግብ ሳይቆጠርበት እንዲወጣ) አስጠብቋል።

አርቲስት ማህደር አሰፋ ከቴሌቲቪ ጋር ተፈራረመች፡፡የዶቃ ፊልም ፕሮዲውሰር የሆነችው አርቲስት ማህደር አሰፋ ከኢግልላዮን ጋር በዛሬው እለት ስምምነት ፈፅማለች፡፡ በዚህ ስምምነትም ዶቃ የተሰኘ...
08/17/2024

አርቲስት ማህደር አሰፋ ከቴሌቲቪ ጋር ተፈራረመች፡፡

የዶቃ ፊልም ፕሮዲውሰር የሆነችው አርቲስት ማህደር አሰፋ ከኢግልላዮን ጋር በዛሬው እለት ስምምነት ፈፅማለች፡፡ በዚህ ስምምነትም ዶቃ የተሰኘውን ፊልሟን በቴሌ ቲቪ ፕላትፎርም ውስጥ አስገብታለች፡፡

ቴሌ ቲቪ ሰኔ 2016 ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በአጋርነት ‹‹6 ሰአት ከለሊቱ›› እና ትዝታ የተሰኙ ፊልሞችን በሞባይል መተግበሪያ ውስጥ ማካተቱ ይታወሳል፡፡ ዛሬ በተደረገው ስምምነት መሰረት ዶቃ ፊልምም በዚህ ውስጥ ተካቷል፡፡ ዶቃ ፊልምን በቴሌቲቪ አፕሊኬሽን አማካኝነት መከራየት የሚቻል ሲሆን ዋጋውም 100 ብር ነው፡፡ የአይፎን ስልክ ላላቸው አፕሊኬሽኑ ስለማይሰራ በቴሌብር አማካኝነት ፊልሙን መከራየትና መመልከት እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

ዶቃ ፊልም የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ፕሮዲውሰሯ አርቲስት ማህደር አሰፋ እንደተናገረችው ፊልሙን በእንግሊዘኛና ሌሎችም ቋንቋዎች የመተርጎም ስራው እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡ በቀጣይነት ፊልሙን በአለም አቀፍ ፌስቲቫሎች ላይ የማሳየትና የማወዳደር እቅድ እንዳለም አስረድታለች፡፡

ሳካ ሰካ!አርሰናል  የፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን በድል ጀምሯል።  መድፈኞቹ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፉ ሃቨርትስ እና ሳካ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።ጨዋታውን እንዴት አያችሁት? አርሰና...
08/17/2024

ሳካ ሰካ!
አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን በድል ጀምሯል። መድፈኞቹ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፉ ሃቨርትስ እና ሳካ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ጨዋታውን እንዴት አያችሁት? አርሰናል በዘንድሮው ውድድር ስንተኛ ሆኖ ይጨርሳል? አስተያየታችሁን ኮመንት ላይ እንጠብቃለን።

08/17/2024

በጉዲፈቻ ልጅ ወደ አሜሪካ ማምጣት ይቻላል። እንዴት? ጠበቃዎ ሙሏአለምን ስሙት።
--
የጠበቃዎን ስልክ ይያዙ⚖️። በማንኛውም የሕግ ጉዳይ ከጎንዎ የሚቆመው ጠበቃ ሙሉዓለም ምንም ነገር ድንገት ቢያጋጥምዎ በቅድሚያ በማንኛውም ሰዓት ደውሉለት።
⚫️የቤተሰብ ሕግ ጉዳዮች (ፍቺ)፣
⚫️የኢሚግሬሽን ጉዳዮች (በሁሉም ስቴቶች)፣
⚫️የቢዝነስ፣
⚫️የመኪናና የሥራ ቦታ አደጋ፣
⚫️የወንጀል ጉዳዮችና ለሌሎችም ስልክ ቁጥር ☎️651-528-2677
"ፍትሕ ሲያሻዎ፣
ጠበቃ ሙሉዓለም አለልዎ!"

ገና በ25ኛው ደቂቃ አርሰናል ወልቭስን 1ለ0 መምራት ጀምሯል።የመድፈኞቹን የሲዝኑን የመጀመሪያ ጎል ሃቨርትስ አስቆጥሯል።
08/17/2024

ገና በ25ኛው ደቂቃ አርሰናል ወልቭስን 1ለ0 መምራት ጀምሯል።
የመድፈኞቹን የሲዝኑን የመጀመሪያ ጎል ሃቨርትስ አስቆጥሯል።

08/17/2024

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ እያለች የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእለቱን ጸሎተ ቅዳሴ በቀጥታ ሥርጭት ታስተላልፋለች - ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ -ነሐሴ 11 ቀን , 2016 (Aug 17 , 2024).

የጨዋታ ቀን፡አርሰናል ከ ወልቭስ - ማን ያሸንፋል? ውጤት ይገምቱ!
08/17/2024

የጨዋታ ቀን፡
አርሰናል ከ ወልቭስ - ማን ያሸንፋል? ውጤት ይገምቱ!

ለአንድ መቶ ዓመታት ብዬ ቤት አልሰራምአባታችን አብርሃም በምድር ላይ በኖረበት ዘመን እጅግ በረከት የተትረፈረፈለት ነበር፡፡ ምንም እንኳን ከጣኦት ጠራቢና አምላኪ ቤተሰብ የተወለደ ቢሆንም እ...
08/17/2024

ለአንድ መቶ ዓመታት ብዬ ቤት አልሰራም

አባታችን አብርሃም በምድር ላይ በኖረበት ዘመን እጅግ በረከት የተትረፈረፈለት ነበር፡፡ ምንም እንኳን ከጣኦት ጠራቢና አምላኪ ቤተሰብ የተወለደ ቢሆንም እውነተኛው አምላክ እግዚአብሔር ያነጋግረው ዘንድ የተማጸነ፣ ካገኘውም በኋላ የአባቱን ሀገር ካራንን ትቶ እርሱ በመራው መንገድ ወደ ከነአን በእምነት የተጓዘ፣ በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ፣ ቅድስት ሥላሴን በቤቱ ያስተናገደ፣ በእርጅና ዘመኑ የመቶ ዓመት ሽማግሌ ሆኖ ሳለ ያገኘውን አንድ ልጁን ለመሰዋት ያልሰሰተ አባት ነው፡፡

በዘመናችን ስጋዊ በምንለው ኃብት እጅግ የተረፈው ባለጸጋ ያመረተውን የሰብል ምርት እንኳን ለማስገባት የሚያገለግሉት ከሦስት ሺህ ያላነሱ አህዮች የነበሩት አባት እንደነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ ይህን ሁሉ ይዞ ታዲያ ትልቁ ሀሳቡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን አካሔድ መጠበቅ ነበር፡፡ እስቲ ራሳችንን እንመርምረው ትንሽ ገንዘብ ስንይዝ ቅድሚያ የምንሰጠው ለማነው? የልባችንስ ቅንነት ምን ያሕል ነው፡፡

አባታችን ቅዱስ አብርሐም በምድር ላይ 175 ዓመታት የኖረ ሲሆን ከተትረፈረፈው ሀብቱ ቤት ለመስራት አልወደደም፡፡ ይልቁንም በድንኳን መኖርን መረጠ እንጂ፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ሁሌም የደግነት ምሳሌ የመስጠት አብነት ተደርጎ የሚጠራ አባት ነው፡፡ እኛ ስንት ዘመን እንደምንኖር ለማናውቅባት ዓለም ያማረ ቤት እንሰራለን፡፡ ይህ የሚያስወቅስ ባይሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማሰብስ እንዴት እንዘነጋለን፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት ስር ለምትገኘው አበባዬ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ እጃችንን እንዘርጋ፡፡

የጻድቋ ጸሎትና በረከት አይለየን!!!

ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444

እየደረሰነው ከጥቁር ገበያው !!
08/17/2024

እየደረሰነው ከጥቁር ገበያው !!

በባህርዳር የ7 አመት ህፃንን ደፍሮ የገደለው እጅግ ነውረኛ ሰው በአስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል።በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲህ አይነት አስፀያፊና ነውረኛ ተግባር የፈፀመው ወንጀለኛ ላይ አ...
08/17/2024

በባህርዳር የ7 አመት ህፃንን ደፍሮ የገደለው እጅግ ነውረኛ ሰው በአስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል።

በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲህ አይነት አስፀያፊና ነውረኛ ተግባር የፈፀመው ወንጀለኛ ላይ አስተማሪና የማህበረሰቡን ስብራት የሚጠግን እርምጃ መወሰድ አለበት።

- ፕሬዚዳንት አረጋ ከበደ
- ምክትል ፕሬዚዳንት ደሳለኝ ጣሰው
- ምክትል ፕሬዚዳንት ይርጋ ሲሳይ
በዚህች ህፃን ላይ የተፈፀመውን አስገድዶ መድፈርና መግደል ወንጀል የህዝብን እሴት የጣሰ በመሆኑ አርምጃ ልትውሰዱ ግድ ይላል

ሼር በማድረግ ድምጽ እንሁን

መምህር በሀይሉ ከባህር ዳር

08/17/2024

የባህርዳር ውሎ

ማንቸስተር ዩናይትድ የፕሪሚየር ሊጉን መክፈቻ ጨዋታ ፉልሃምን 1ለ0 አሸንፏል::ጨዋታው እንዴት ነበር? የጨዋታው ኮከብስ? ኮመንት ላይ እንጠብቃለን::
08/16/2024

ማንቸስተር ዩናይትድ የፕሪሚየር ሊጉን መክፈቻ ጨዋታ ፉልሃምን 1ለ0 አሸንፏል::
ጨዋታው እንዴት ነበር? የጨዋታው ኮከብስ? ኮመንት ላይ እንጠብቃለን::

08/16/2024

"ያን ያህል የሚጠቅም ሆኖ አልተገኘም"

ማንቸስተር ዩናይትድ ከፉልሃም - አሰላለፉን እነሆ!
08/16/2024

ማንቸስተር ዩናይትድ ከፉልሃም - አሰላለፉን እነሆ!

Address

Minneapolis, MN

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zehabesha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Our Story

Ze Habesha LLC is an Ethiopian American media company based in Minnesota, with presence in the print and broadcast media. Zehabesha strives to provide unbiased information to the ever-growing Ethiopian American community and works toward bridging cultures ZeHabesha is a diversified news and information newspaper that represents America’s local and national Ethiopian community. Zehabesha is a free bilingual newspaper with production based in the Minnesota. Zehabesha, published bi-monthly by the ZeHabesha LLC, has been in publication for 10 years. As of early 2008, Ze-Habesha has non paid subscribers, with a total circulation of 10,000 copies in Major Twin cites areas, including South Dacota, Chicago, Dallas, Atlanta, Las Vegas, and etc... Ze-Habesha Newspaper has a number of blogs that are updated regularly with community events and news. Please Visit us www.Zehabesha.com

https://www.minnpost.com/new-americans/2017/10/how-minnesota-paper-became-one-world-s-leading-sources-ethiopian-news


Other Media/News Companies in Minneapolis

Show All