Gorgora.com

Gorgora.com ይህችን ዐማራዊ ገጽ ተወዳጇት ታተርፉባታላችሁ!!! personal Amhara ዐማራ!!!

03/12/2020

ፍኖተ ተዋሕዶ

የዛሬ ወር አካባቢ ተጉለት አማራ ቤተክርስቲያን ሲቃጠል አፉችሁ የተያዘ ምንም ያልተነፈሳችሁ ያላወገዛችሁ ያልተቃወማችሁ ዛሬ ደርሶ ምክንያቱን እንኳን በቅጡ ሳታጣሩበ ደርሳችሁ አውጋዥ የሆናችሁት በምን ሚዛናዊ መለኪያ ነው? እ ንገሩና የብአዴን የመንፈስ ልጆች ? ቤተክርስቲያኑን ለማቋቋም እንኳን አካውንት ተከፍቶ የእርዳታ ጥሪ ተላልፎ ነበር እስኪ ስንቶቻችሁ ተሳተፋችሁ ነው? በነገራችን ላይ የጂሩ እነዋሪ ህዝብ አንዳች ስህተት የለበትም ስህተቱ ወረዳውን እንመራዋለን የሚሉ ደንባራ ብአዴናውያን ነው አንዳንዴ ስንራመድ እያስተዋልን በመንጋ እየተነዳችሁ ህዝብ ከመፈረጂ ምክንያቱን ከምንጩ አጥርተን እንተች።
የዩቲዩብ ቻናላችንን ተቀላቀሉ! ለወደፊቱ ይጠቅመናል መረጃ የምናስቀምጥበት ቋታችን ነው
https://www.youtube.com/channel/UCU1wTaLCYyECpIXC02bPMsw
የቴሌ ግራም ቻናላችንንም እንዲሁ ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEe-Z_8LLoBRSPfdEA
https://t.me/joinchat/AAAAAETW6_7pzC2pYu2hpA

03/12/2020
ፍኖተ ተዋሕዶ

ፍኖተ ተዋሕዶ

በፕሮቴስታንቱ ዓለም እየደረሰ ያለ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ኪሳራና የሥነ–ምግባር ዝቅጠት ያጋለጠ ቃለመጠየቅ

እራሳቸውን "ሐዋርያ" እና "ነብይ" እያሉ የሚጠሩ
የፕሮቴስታንቱ ዓለም ጉዶች በራሳቸው ስሜት እየተነዱ ከራሳቸው አፍልቀውና አመንጭተው ጌታ ነገረን መልዕክት መጣልን እንዲህ ይሆንልሃል እንዲያ ይደረግልሃል ጠላትህ ተሰበረ ተወጋ በማለት የዋሁንና ሞኙን ሕዝብ የህልም ዓለም ተስፋ በመስጠት ቁስሉን በመነካካትና ጎዶሎውን እየነገሩት ችግሩንና ብሶቱን በማይክራፎን ጮክ አድርገው እየነገሩት ስስ አንጀቱን እየሸነቆጡ ብሶቱን እያወሩለት እያስለቀሱት ሕዝቡን እያጭበረበሩና እያታለሉ እንዳለ የአደባባይ ምስጢ ነው ።

እነሆ ከዛ ሁሉ ቅጥፈት በኃላ የልባቸው ደርሶ የአማኙን ትዳር አፍርሰው ኪሱን አራቁተው የሺዎችን ነፍሳት ወደ ሲዖል ነድተው ሲያበቁ እንዲሁ እንደዋዛ በሚዲያ ብቅ ብለው በኩራት ተለጥጠውና ተኮፍሰው ከካሜራ ፊት ቁጭ ብለው ተሳስተን ነበር ዝም ብለን ነበር ስናወራ የነበረው ስብከቱም ስብከት ፈውሱም ፈውስ አልነበረም የውሸት ብለው ሲያወሩ ከመስማት የበለጠ ምን ኪሳራ አለ?

ይህ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቴስታንቱ ዓለም የሞራል ዝቅጠትና የሞራል ኪሳራ ነው!

በጣም የሚገርመው ነገር ዛሬም ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ የራሳቸውን ቅዠት የሚቃዡና የፈጠራ ወሬ የሚያወሩ እንደ ሐዋርያ ዳንኤል አይነት መኖራቸው ነው ግርምቴን ደግሞ እጥፍ የሚያደርገው ደግሞ ዛሬም ድረስ የእነዚህ "ሐሰተኛ ነብይና ሐዋርያ" ነን ባዮች አድናቂና ተከታዮች አለመንቃታቸውና ዛሬም በፅኑ እንቅልፍ ውስጥ መሆናቸው ነው

እናንተ የሐሰተኛ ነብያትና ሐዋርያት መጫወቻ የሆናችሁ ፕሮቴስታንቶች ሆይ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁት መቼ ይሆን? እንዳታስተውሉስ አዚሙን ያደረገባችሁ ማን ይሁን?

03/12/2020

የደብረ ኤልያስ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ካለመናበብ በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው አለፈ....!

በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረ ኤልያስ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ የነበሩት ም/ኮማንደር ባይህ ጥላሁን መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ስአት አካባቢ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በከተማው ውስጥ የነበረውን የፀጥታ ስምሪት እየመሩ ነበር፡፡

ታዲያ በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ ባጋጣሚ በሌላ አቅጣጫ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ የፀጥታ ሀይሎች ጋር ተገናኝተው ስአቱ ጨለማ ስለነበር ግራ ቀኝ ማነህ ማነህ እየተባባሉ እንዳለ ካለመናበብ በድንገት በተተኮሰ ጥይት ተመተው ህይወታቸው አልፏል የምስራቅ ጎጃም ዞን ፓሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

በወቅቱ በሌላ የፀጥታ ሀይል ላይ የደረሰ ተጨማሪ ጉዳት ባይኖርም በድንገት በተፈፀመው ድርጊት ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የተገለፀው፡፡ ሟቹ ም/ኮማንደር ባይህ ጥላሁን ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

ስርዓተ ቀብራቸውም ዛሬ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ/ም በደብረ ኤልያስ ከተማ ደበረ ገነት ቅዱስ ኤልያስ ቤተክርስትያን ስርአተ ቀብራቸው ይፈፀማል፡፡
Gorgora.com

03/12/2020

የአብን ከፍተኛ አመራሮች አሜሪካ ገቡ!!!

03/12/2020

ፍኖተ ተዋሕዶ

አፈንጋጩ አባ ሳዊሮስ ከሊቀ ጳጳስነት ወደ ሊቀ ባንዳነት ከግብፅጋ የተጀመረ ምስጢር ተጋለጠ!

ባንዳው ጳጳስ በኢትዮጵያ ላይ የጦር ነጋሪት እየጎሰመች ካለችው ግብፅ ጋር ምን አገናኛቸው?

አባ ሳዊሮስ ከባድ ምስጢር አመለጣቸው
ጀዋር መሐመድ ከግብፅ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት እንዳለውና ከግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ድርድር ላይ እንዳሉ ተናገሩ ።

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ አሳፋሪ ሊባል በሚችል መልኩ ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ አባላት ጋር ቁጭ ብለው የእነ ቄስ በላይ ሥልጣነ ክህነት እንዲያዝ የወሰኑትን ውሳኔ በማግስቱ አይናቸውን በጨው አጥበው ቅጥፈትና ውሸት በተሞላበት ንግግር የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ የተሳሳተና ተቀባይነት የሌለው በጥቂት ሰዎች ግፊት የተወሰነ ነው በማለት በOMN ቲቪ ላይ ቀርበው እግዚአብሔርን ሳይፈሩ ሰውንም ሳያፍሩ ሲደሰኩሩ ነበር ።

የእለቱ አሳፋሪ ንግግር ማንነታቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳየና ከፀጋ መንፈስ ቅዱስ ተገፈው እርቃናቸውን ካስቀራቸው መግለጫ ውስጥ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ "የትግራይ ጳጳሳት አልደገፉትም" የምትለዋና ንግግራቸውና ስለ ቀድሞው የውጭ ሲኖዶስ ታሪክ ሲናገሩ "አራት ሆነው ከሀገር ወጥተው ሃያ አራት" ሆነው ተመለሱ የምትለዋ ንግግራቸው ይሰመርበት ።

ከOMN መግለጫ በኃላ የእነ አባ ሳዊሮስ አሰላለፍ ተቀይሮአል ከአሳፋሪውና ህገ ቤተ ክርስቲያንን ከጣሰው መግለጫ በኃላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ በቋሚ ሲኖዶስ እንዲሁም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንም አይነት ጥያቄ አልቀረበባቸውም ዝም ጭጭ ነው የተባሉት እዚህጋ ጠርጥር ደግሞ ጠይቅ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ኃላፊዎችና የፓትርያርኩ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እነማን ናቸው?

መልሱን አፈንጋጩና አማፂው አባ ሳዊሮስ በመግለጫቸው ላይ የትግራይ ጳጳሳት ከኛ ጋር ናቸው ካሉት ጋር እዚህጋ አገናኝል ከዛ በተዋህዶ ላይ እየተሴረ ያለውን ሴራና ከውስብስቡ የቤተ ክርስቲያን ፈተና በስተጀርባ ያሉትን ስውር እጆች እነማን እንደሆኑ አስላውና ድረስበት።

በጣም የሚገርመው ነገር የእነ አባ ሳዊሮስ መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስን ምልዓተ ጉባዔ ውሳኔ የሻረና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባልነት እስከ ማሰረዝ የሚደርስ ከባድ ክህደትና ጥፋት ሆኖ ሳለ በየትኛውም ደረጃ ያለ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጠርቶ ማብራሪያ የጠየቃቸው አካል የለም እነ አባ ሳዊሮስ ግን ጭራሽ ከሰሞኑ ሌሎች ዘጠኝ የትግራይ ጳጳሳትን ይዘን መግለጫ እንሰጣለን እያሉ እየፎከሩ ነው።

ምን ይሄ ብቻ አባ ሳዊሮስ የባጥ የቆጡን ሲቀባጥሩ ከባድ ምስጢር አምልጦአቸዋል ይሄውም ግብፆች የጀዋር መሐመድ የቅርብ ወዳጅ እንደሆኑና በጀዋር መሐመድ አመቻችነት አባ ሳዊሮስን የሚያግዙ በጎጥና በዘረኝነት መንፈስ የተለከፉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የካዱ ለሆዳቸው ያደሩ ህሊናቸውን የሸጡ መለኮሳት ግብፅ ድረስ ይዘው ሄደው ጵጵስና እደሚያሾማቸውና ከግብፅ ጵጵስና ተሹመው የሚመጡና ሀገር ቤት ካሉ ሰቃልያነ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተሰባስበው የራሳቸው ፓትርያርክ እንደሚሾሙ እየቃዡ ነው

ጎበዝ ለረጅም ጊዜ እነ ጀዋር የግብፅ ተላላኪ ናቸው ሲባሉና በወሬ ሲታሙ እንሰማ ነበር አሁን ግን እድሜ ለአባ ሳዊሮስ ሃሜቱና ግምቱ እውነት መሆኑና እንደ ጋሪ ፈረስ እየጋለባቸው ያለው ጀዋር መሐመድ ከግብፅ መንግስት ጋር ተነጋግሮ ጳጳሳት ሊያሾምላቸው መሆኑኑን አንዳች ነገር አንደበታቸውን ፀፍቶ አናግሮአቸዋል ።

አንባቢ ሆይ ይሄን መረጃ እንደተራ ነገር የምታይ ከሆነ አንተ ጀዋርንም ግብፅንም አታውቃቸውም ማለት ነው ወዳጄ ግብፆች በዓባይ የመጣ በሕይወታቸው የመጣ እንደሆ እዚህ ጋር ልብ ይለዋል ።

ያውም የህልውና ጉዳይ ነው ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል እንድትሆን ከማድረግ ወደኃላ አይሉም።

እናም አባ ሳዊሮስ በዓይናችን እያየን በጆሮአችን እየሰማን ከሊቀ ጳጳስነት ወደ ሊቀ ባንዳነት የቁልቁለት ጉዞውን ተያይዘውታል።

ያደቆነ…… እንዲል ብሂሉ እነ አባ ሳዊሮስ የለከፋቸው በሽታ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመካድ ጀምሮ እነሆ አሁን ሀገርን ወደ መክዳት ተመነደገ ።

ህሊና ባዶ ሲሆንና ፀጋ እግዚአብሔር ሲለይ እንደዚህ ነው የሚያሳዝነው ነገር ይሄ ሁሉ ክህደትና ቅሌት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል ነው።

በመጨረሻም ጥያቄ ለአንባብያን
1,የአባ ሳዊሮስ ወአቶ በላይ መኮነን ግሩፕ + የትግራይ ጳጳሳትና የቤ ክህነቱ ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት + ጀዋር መሐመድና መሰሎቹ + ግብፅ የእነዚህ ጥምረትና ሴራ የት ድረስ ያስኬዳቸዋል?

በቀደመው በአባቶቻችን ዘመን ለግራኝ አህመድ፣ለዮዲት ጉዲት ፣ ለለፋሺስት፣ ለሃሳዊያንና ለቀሳጣዊያን ለሐራጥቃዊያን ያልተንበረከከች ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬስ የእነዚህን ባንዳዎች ሴራ እንዴት ታልፈው ይሆን? ይቆየን

ዲ/ን አብርሃም ወርቁ

03/11/2020

ፍኖተ ተዋሕዶ

ትክክለኛው ራዕየ ማርያም ይሄ ነው።
ጋላ፣ሻንቅላ፣ፈላሻ ብላ ቤተክርስቲያን ማንንም ጠርታ አታውቅም እንዲህም ብላ አልጻፈችም።ይህ ጥንታዊው መጽሐፍ ነው።**

=>ቅድሥት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በሐሰት ትርክት መቼም ልታሸንፏት አችሉም። ቤተክርስቲያኒቱን ለማስጠላት ማንም ተነስቶ ያሰራጨውን የሐሰት ማስረጃ መከራከሪያ አድርጋችሁ የሐሰት ወሬን ብትናገሩ ከእናንተ ንግግር የተነሳ ቅድሥት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አትታወክም ።ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሌላው አካል እድትጠላ ለማድረግ ብትሞክሩም እውነት ግን መቼም አለችና ሐሰታችሁን ጉድ ታደረገዋለች ፤እሷ ባልፃፈችው ነገር ላይ እየተነሳችሁ ጣታችሁን አትቀስሩ ይልቁኑ መርምሩ ።ቅድሥት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሰረተች በቅዱሳን ሰማዕታት ተጋድሎ የጸናች ጨዋ እመቤት ነች።

=>በትክክለኛው ራዕየ ማርያም መፅሐፍ ላይ ጋላ፣ ሻንቀላ፣ፈላሻ ሌላውም አይገባም የሚለውን ፅሁፍ አታገኙትም የለምም ኖሮም አያቅም ።ይህንን ያልተረዱ ሰዎች የቤተክርስቲያን ጠል የሆኑ ሰዎች ያስገቡትን ጽሁፍ ይዞ ቤተክርስቲያንን መክሰስ ይቁም ።ጥላቻችሁን በልክ አርጉት ኦርቶዶክስ ባላረገችው ነገር አትውቀሷት አዎ ጥላቻችሁን በልክ አድርጉት እንደአባታችሁ እንደ ዲያብሎስ ሐሰትን እየፈጠራችሁና በሐሰተኞች ወሬ እየተነዳችሁ ሐሰትን እንደ እውነት አድርጋችሁ በማውራት ራሳችሁን አታዋርዱ።ቅድሥት ቤተክርስቲያን ማንም ላያዋርዳት አንድ ጊዜ በመለኮት ክብር ከፍ ብላ ተቀምጣለች።የሚጧሏት ሁሉ ከእግሯ በተቻ ይደቃሉ እርሷ ግን ከክብር ወደ ክብር እየተሻገረች ዘመናትን በክብር ታልፋለች።

እባካችሁ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ትውልዱን ከሐሰተኛ መረጃ እንጠብቅ።
የዩቲዩብ ቻናላችንን ተቀላቀሉ! ለወደፊቱ ይጠቅመናል መረጃ የምናስቀምጥበት ቋታችን ነው
https://www.youtube.com/channel/UCU1wTaLCYyECpIXC02bPMsw
የቴሌ ግራም ቻናላችንንም እንዲሁ ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEe-Z_8LLoBRSPfdEA
https://t.me/joinchat/AAAAAETW6_7pzC2pYu2hpA

03/11/2020

ፍኖተ ተዋሕዶ

ሃይማኖትህን የምታስፋፋው በብልሃት እንጂ ፣የማህበረሰብ እሴቶችን በመደርመስ አይደለም ። በተለይ ድህነቱን ተጠቅመህ እሴቶቹን ከደረመስክ ክፉ ነህ። የኛ ሃገር ምሁር (የፕሮቴስታንት ዶክተር) የህዝቡን እሴት የማያውቅ የሃይማኖት ፅንፈኛ ነው።በአብይ ፆም ሃይማኖተኛ ህዝብ መሃል ሄደህ፣ ሃይማኖትህ ስህተት ነው ከማለት በላይ ፅንፈኝነት ይኖር ይሆን? እሱ ዩኒቨርሲቲ ተምሮ ያላዳበረውን መቻቻልና ዲሞክራሲ፣ ያልተማረው አርሶ አደር እንዲወልድለት ይጠብቃል። በመዲናዋ አዲስ አበባ አዳራሽ ሞልቶ የማሪያምን ምስል ሲረግጥ የሚውል ፀብ አጫሪ ፣ ዛሬ የባህል ተፅኖ ያልተላቀቀው አርሶ አደር ስህተት በመስራቱ ሲዘባበት ማየት እንዴት ያፀይፋል። የዚች ሃገር ችግር ምሁሩና ፊደል ቀመሱ ነው! አርሶ አደሩማ በባህል ተተብትቦ ብዙ ያላራገፈው ሸክም አለው ፣ ያስተማረህ ይህንን ሸክም እንድታቀልለት እንጂ እሴቶቹን በሚጎረብጥ መልኩ እንድትደረምስለት አይደለም። ዛሬ ከተማ ቁጭ ብለህ አትራቀቅ ፣ ወገንህን ጠጋ ብለህ አስተምረው ፣ እሴቶቹን ሳትደረምስ ሃይማኖትህን አስፋፋ !

በአብይ ፆም ሃይማኖተኛ ህዝብ መሃል ሄደህ፣ ሃይማኖትህ ስህተት ነው እያልክ ስትሰብከው፣ በማተቡ የሚምለው አርሶ አደር ምን እንዲያደርግ ጠብቀህ ነበር ? እስኪ በረመዳን ህዝበ ሙስሊሙ ጋር ሄደህ ሃይማኖቱን አጥላላና የሚደርስብህን ታየዋለህ !! አባቴ እጅህን ቆርጦ በኪስህ አሸክሞ ነው የሚልክህ ። እንዲያውም የእነዋሪ ህዝብ ጨዋ ነው ። ህክምና ልስጥ ብለህ ሃይማኖት ሰበካን ምን አመጣው ።

ድርጊቱን እያበረታታው እንዳልሆነ ይታወቅልኝ ። ግን ፊደል ቀመሱ ቀፈፈኝ ! ምሁሩ ከመንጋው በላይ አደገኛ ለመሆኑ ግን በቂ ማስረጃዎች አሉ! የኢትዮጵያ ችግር ደሃው አርሶ አደር ሳይሆን ፅንፈኛው ምሁር ነው !!

እኔ አልፆምም፣ ሃይማኖተኛም አይደልሁም ፣ የኦርቶዶክስ ወገኖቼ መልካም የአብይ ፆም ይሁንላቹህ። ከምሁር ትንኮሳ ይሰውረን !!!
(ዩሪ ታደሰ)
የዩቲዩብ ቻናላችንን ተቀላቀሉ! ለወደፊቱ ይጠቅመናል መረጃ የምናስቀምጥበት ቋታችን ነው
https://www.youtube.com/channel/UCU1wTaLCYyECpIXC02bPMsw
የቴሌ ግራም ቻናላችንንም እንዲሁ ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEe-Z_8LLoBRSPfdEA
https://t.me/joinchat/AAAAAETW6_7pzC2pYu2hpA

03/11/2020

Gorgora.com

ሥልጡን መሆን የመጣውን ይቀበላል፣ ከልክ ካለፈ በህግ አምላክ ብሎ ይጠይቃል፤ ያስጠነቅቃል ፣ከዚህ ሲያልፍ ልኩን ያስገባዋል።

ደግሞ አማራ ሲመክርህ ለክርህ ታመን ሲልህ ለእምነትህ እና ለማንነትህ በጥቅም አትንሸንገል ማለት ነው።

እውነቱን ለመናገር እነዋሪ የገጠማት አጤ ቴዎድሮስ ከገጠማቸው ጋር ሄዶ ልክክ ይላል። የሚሊኒየሙ ጀግናው መሪዬ መይሳው ካሣ ከሩቅ አገር የሚመጡትን ነጮችን መድፍ ሥሩልኝ ፣አገሬን ከዘመናዊነት ጋር አስተዋውቁልኝ ሲላቸው እኛ ጥበብ የለንም እምነትን ልንሰብክ ነው የመጣን ይሉና ይገግሙ ነበር ፤ ግን ያላቸውን ጥበብ ደብቀው የእምነት ሸቀጣቸውን ለማራገፍ ይሻኮቱ ነበር።

03/11/2020

ሙስጠፌ ኡመር እንዲገደሉ የተሸረበው ሴራ ከሸፈ

የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ሙስጠፌ ኡመርና ነፍጠኛ ቧሏቸው የክልሉ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት እንዲደርስ ትዕዛዝ የሰጠው የኦብነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጋፍዲፍ ካሊፍ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) አባል የሆኑት አቶ ጋፍዲፍ ሀሊፍ ናቸው በኘሬዝዳንቱና በክልሉ በሚኖሩና እነሱ ነፍጠኞች ባሏቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጥቃት እንዲደርስ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያቸው ትዕዛዝ ያስተላለፉት።

በዚህም ግለሰቡ ዛሬ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

የሽብር ጥቃቱ እንዲካሄድ ያነሳሳቸውም ለምን የካራ ማራ በዓል እንደ ሀገራዊ የድል በዓል ይከበራል? ከሚል መሆኑንም የኔታ ትዩብ አስታውቋል።
የዩቲዩብ ቻናላችንን ተቀላቀሉ! ለወደፊቱ ይጠቅመናል መረጃ የምናስቀምጥበት ቋታችን ነው
https://www.youtube.com/channel/UCU1wTaLCYyECpIXC02bPMsw
የቴሌ ግራም ቻናላችንንም እንዲሁ ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEe-Z_8LLoBRSPfdEA
https://t.me/joinchat/AAAAAETW6_7pzC2pYu2hpA

03/11/2020

የሰናኦር ግንብ ለአማራ ህዝብ ምኑ ነው?
/ክፍል አንድ/

በእርግጥ ይህንን ርዕስ እንዲህ በቀላሉ አንስቶ ለመወያየት አስቸጋሪ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ "የአማራ ብሔርተኝነት" ተብሎ በደምሳሳው በሚጠራው ድንኳን ውስጥ የገባው አብዛኛው የቢቸግር ብሄርተኛ /Makeshift nationalist/ አፉ ከእኛ ጋር ቢሆንም ቅሉ፥ ልቡ ከጀበና ቅርጿ ተምኔታዊት-ኢትዮጵያ ጋር በፅኑ ፍቅር የወደቀ፤ እንዲሁም "የአንድነት ካምፕ" ኒቆዲሞሳዊ የሌሊት ደቀመዝሙር በመሆኑ ነገሮችን ከአማራ ህዝብ ጥቅም አንፃር ከመመርመር ይልቅ፥ በትናንት ተረት፣በዛሬ ተረኞች ሽንገላ እና በአጉል ጀብደኝነት ስለሚነዳ እንደዚህ ዐይነት ወሳኝ ጉዳዮች በአይነኬነት እንዲታለፉ ምክንያት ይሆናል።

ነገር ግን ጣፍጦ ተዋጠም፥ አልያ መርሮ አቅለሸለሸም ስለ አባይ ግድብ በተለይ ከአማራ ህዝብ ጥቅም አንፃር ያለውን እውነት በግልፅ መነጋገር ያስፈልጋል።

የአባይ ግድብ ማለት በዚያች ሀገር ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ ለተፈፀሙ ግፎች መገለጫነት የቆመ የሀጥያት ሐውልት አልያም የሰናኦር ግንብ ተምሳሌት ነው። ይህንን የምለው ከግድቡ ጋር በተያያዘ በአማራ ህዝብ ላይ ሆን ተብሎ በሴራ፣በተንኮልና በፖለቲካ ሸፍጥ በተፈፀሙ አራት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው።

1. አባይን በዘላቂነት ከአማራ ይዞታ ማውጣት /Permanent Dispossession on the Proprietorship of Abay/

2. ለግድቡ መሳካት፥አማራን የመስዋዕት በግ ማድረግ
/"Sacrifice the plum tree to preserve the peach tree"/

3. የአማራን ህዝብ በጅምላ ማቆርቆዝ /Grand exploitation of the mass/

4. የአማራን ህዝብ ጭሰኛ ማድረግና ከሰብዓዊነት ወደ ቁሳዊነት ማውረድ /Peonization and objectification of the Amhara people/

ዝርዝር ነጥቦችን አንድ በአንድ እያነሳን እንመልከት:-

1. አባይን በዘላቂነት ከአማራ ይዞታ ማውጣት /Permanent Dispossession on the Proprietorship of Abay/:-

ከስምንት ወር በፊት አንድ የመለስ አማካሪ የነበሩ ሰው በአባይ ግድብ የቦታ መረጣ ላይ ለመለስ ቀርቦ የነበረውን አማራጭ ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። በእርግጥ የአባይ ግድብ ይፋ በተደረገ ወቅት አዲስ አበባ የነበርንና ለጉዳዩ ቅርበት የነበረን ሰዎች በዚህ ዙሪያ ብዙ መባሉን ዛሬም እናስታውሳለን።

የአባይ ግድብ በወቅቱ ከቀረበው የዋጋ ጥናት በጣም ዝቅ ባለ ወጪ በአማራ ምድር መሰራት እንደሚችል ከዚህ በፊት በተሰሩ ጥናቶች ላይ ማሻሻያ ተደርጎ ፈጣሪ ነብሱን አይማረውና ለመለስ ዜናዊ ቢቀርብለትም፥ አንድም የመረብ-ባሮ የታላቋ ትግራይን ህልም በመሰነቁ፣ በሌላ በኩልም አማራ ፈጣሪ የሰጠውን ፀጋ እንዳያለማ፥ ይልቁንም ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ የአባይን ልማት ከአማራ ለመነጠል ሲል ብቻ ዛሬ የተሰራበት ቦታ ላይ ግንባታውን አስጀምሯል። በወቅቱ የወያኔ ትግሬ ካድሬዎችና የተላላኪው ብአዴን ባሪያዎች ቴክኒካል የሚመስሉ ትንታኔዎችን እየሰጡ ሲያደነቁሩን ነበር፥ ምንም እንኳን ጥረታቸው "Lecturing birds on how to fly" አይነት ቢሆንም።

የአባይ ግድብ በቤኒሻንጉል ክልል የመሰራቱ ብቸኛ ምክንያት በአማራ ጥላቻ የናወዘ የፖለቲካ ወሳኔ ነው። ይህ የፖለቲካ ውሳኔ አባይን ከአማራ ምድር ነጥሎ ከግድቡ ጋር በተጓዳኝ የሚኖሩ የልማት ፀጋዎችን በሙሉ ከአማራ ህዝብ እና ምድር ላይ በግፍ ለመግፈፍ ታስቦ የተፈፀመ ነው።

በእርግጥም ጠላቶቻችን አማራን ለመስበር የሚጠቀሙበት ትልቁ የመውጊያ ጦር አንድም የአማራን ምድር የመልማት ፀጋውን ከተቻለ እንደ ዓባይ ግድብ ወደሌላ ስፍራ መውሰድ፥ አልያም እንደጣና ወይም እንደ ጢስ አባይ ፏፏቴ ባለበት ሥፍራ መግደል ነው።

ፈጣሪ በችሮታው የሰጠንን ሀብት በግፍ ከምድራችን ላይ አውጥተው፣ከግድቡ በተጓዳኝ የሚፈጠረውን ሰፊ የመልማት ፀጋችንን ለፍፃሜው አጨልመው የሚሰሩት ግድብ ለአማራ ህዝብ የሀጥያት ግንብ፥ ምስለ-ሰናኦር ነው። ከዚህ የዘለለ ትርጉም ሊሰጠው የሚሞክር ካለ፥ እሱ አንድም ወቅቱን የመገንዘብ ችግር ያለበት፥ አልያም የራስ-ከድ እና የራስ-ጠል የአማራ "ምሁራን" ስብከት ሰለባ የሆነና በገሃድ ጠፍታ በምናቡ ዓለም ካለቺው "እምዬ ኢትዮጵያ" ጋር በማይድን የመስተፋቅር ልክፍት የተያዘ ሰው ብቻ ነው።

2. አማራን የመስዋዕት በግ ማድረግ /"Sacrifice the plum tree to preserve the peach tree"/

አባይንና ተያያዥ የመልማት ፀጋውን ከአማራ ምድር አውጥተው መውሰዳቸው ሳያንስ፥ ይህ የግድብ ስራ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት የሚያገኘው ከጣና በለስ የሀይል ማመንጫ ነው።

ከአስር ወራት በፊት "ጣና እንደምን ተገደለ?" በሚል ርዕስ ባወጣሁት ፅሁፍ ለመግለጽ እንደሞከርኩት የጣና ሐይቅን የለሆሳስ ሞት እያፋጠኑ ካሉ ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ የጣና በለስ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ነው። ይህም የሆነው ምንም እንኳን በፕሮጀክት ጥናቱ ላይ ከሐይቁ የሚወሰደው ውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ካመነጨ በኋላ ተመልሶ ወደ ሃይቁ ይገባል ቢልም፥ ወደተግባር ሲቀየር ግን ሆን ተብሎ በትህነግ ሴራ እና በብአዴን ተላላኪነት 12 ማይል ያህል በሰው ሰራሽ ቦይ ከሐይቁ የሚወሰደው ውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ካመነጨ በኋላ ወደ ሐይቁ ከመመለስ ይልቅ የበለስ ወንዝን እንዲቀላቀል ተደርጓል። ይህም የጣና ሐይቅን የውሃ ፍሰት ሚዛኑን ክፉኛ ስላዛባው፥ ከእንቦጭ አረም ጋር ተደምሮ ጣናን ሞቱን እያፋጠነው ነው።

እንግዲህ ጣና በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ እያቃተተ በሚያመርተው የኤሌክትሪክ ኃይል ነው፥ ከአማራ ምድር በፖለቲካ የሴራ ውሳኔ የተነጠቀው የአባይ ግድብ የሚገነባው።

የአባይ ግድብንና ተያያዥ የመልማት ፀጋዎቻችንን ከአማራ ምድር መንጠቅ አንድ ነገር ሆኖ፥ የነጠቁትን ለማልማት ደግሞ በጣና ሞት ላይ የሚመረትን ሀይል መጠቀም ለጠላቶቻችን "ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል" ሲሆን፥ ለአማራ ህዝብ ግን ድርብ-ጉዳት /Double Jeopardy/ ነው።

03/11/2020

ሥልጡን መሆን የመጣውን ይቀበላል፣ ከልክ ካለፈ በህግ አምላክ ብሎ ይጠይቃል፤ ያስጠነቅቃል ፣ከዚህ ሲያልፍ ልኩን ያስገባዋል።

ደግሞ አማራ ሲመክርህ ለክርህ ታመን ሲልህ ለእምነትህ እና ለማንነትህ በጥቅም አትንሸንገል ማለት ነው።

እውነቱን ለመናገር እነዋሪ የገጠማት አጤ ቴዎድሮስ ከገጠማቸው ጋር ሄዶ ልክክ ይላል። የሚሊኒየሙ ጀግናው መሪዬ መይሳው ካሣ ከሩቅ አገር የሚመጡትን ነጮችን መድፍ ሥሩልኝ ፣አገሬን ከዘመናዊነት ጋር አስተዋውቁልኝ ሲላቸው እኛ ጥበብ የለንም እምነትን ልንሰብክ ነው የመጣን ይሉና ይገግሙ ነበር ፤ ግን ያላቸውን ጥበብ ደብቀው የእምነት ሸቀጣቸውን ለማራገፍ ይሻኮቱ ነበር።

03/11/2020
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

ታላቅ ሕዝባዊ የስብሰባ ጥሪ በሰሜን አሜሪካ ለምትገኙ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ደጋፊዎች፣ አማራዎችና የአማራ ጉዳይ ያገባናል ለምትሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤
በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የአብን ደጋፊዎች፣ አማራዎች እና የአማራ ጉዳይ ያገባናል ከሚሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በአብን ዓላማና ፕሮግራም፣ በንቅናቄው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ በአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፣ ሊያጋጥሙ በሚችሉ ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ለማድረግ የፓርቲያችን ሊቀመንበር ረ/ፕ በለጠ ሞላ እና የቀድሞው የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ወደ ሰሜን አሜሪካ ይጓዛሉ፡፡

አመራሮቹ በቆይታቸውም ማርች 14 በዲሲ፣ ማርች 15 በዳላስ፣ ማርች 21 ሚኒሶታ፣ ማርች 22 በዴንቨር፣ ማርች 28 በሲያትል፣ ማርች 29 በአትላንታ፣ ኤፕሪል 5 በሎስ አንጀልስ፣ አፕሪል 8 በኒቪዳ እና አፕሪል 11 በሳንዲያጎ ከተሞች ውይይት ያደርጋሉ፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት ስቴቶችና ከተሞች የምትገኙ ደጋፊዎቻችን፣ አማራዎችና የአማራ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በአቅራቢያችሁ በሚገኘው የውይይት መድረክ ላይ እንድትሳተፉ አብን ጥሪውን ያቀርባል።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

03/11/2020

🦅🦅 #ንስርነት🦅🦅

ንስር ከሌሎች አዕዋፋት ረጅም ዕድሜም እንደሚኖር ይታወቃል፡፡ ቢያንስ እስከ ሰባ አመታት በህይወት መቆየት ይችላል፡፡ ይህን ሁሉ ዘመን በህይወት ሲኖር ግን ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነዉለት አይደለም፡፡ በህይወት ዘመኑ እጅግ የሚያሳምም የመታደስ ዉሳኔ ህመሙን ችሎ ካልፈጸመው ያለዉ አማራጭ መሞት ብቻ ይሆናል፡፡
ንስር እድሜዉ አርባ አመት ሲሞላዉ አካሉ ያረጃል፡፡ ሹል፣ ረዣዥም እና ጠንካራ ጥፍሮቹ ይዶለዱሙና ይደክማሉ፡፡ ለንስሩ የዕለት ምግቡን መንጭቀዉ ማንሳት ያቅታቸዋል፡፡ ንስሩ የሚታወቅበት ያ የሾለ ምንቃሩ ወይም አፉ ከዕድሜ ብዛት ወደ ደጋንነት ይቀየራል፡፡ ክንፎቹም ይዝላሉ፡፡ ላባዎቹ ይነትቡና ያ በበረራ ፍጥነቱ ይታወቅ የነበረዉ ፍጡር እንደዶሮ ጫጩት መብረር ያቅተዋል፡፡

በዚህን ጊዜ ንስሩ ሁለት አማራጮች ብቻ ይኖሩታል፡፡ ወይ አምስት ወራት የሚፈጅ እጅግ የሚያሳምም የመታደስ ዉሳኔ መወሰን አሊያም መሞት፡፡ ደግነቱ ንስር በደመነፍሱ አሮጌ አስተሳሰብ ሞትን እንደሚያስከትልበት ስለሚረዳ ሁሌም አንደኛዉን አማራጭ ብቻ በመዉሰድ በአዲስ አስተሳሰብ ይወስናል፡፡ ንስሩ የመታደስ ዉሳኔዉን ተግባራዊ ማድረግ የሚጀምረዉ ለመታደስ በሚፈጽማቸዉ ተግባራት የሚያጋጥሙትን ህመሞች አስቀድሞ በመረዳትና ህመሙን የመታገስ አዲስ ንስራዊ አስተሳሰብ በመያዝ ነዉ፡፡ ያረጀ ምንቃሩን ለማስወገድ በተደጋጋሚ ከአለት ጋር መጋጨት ግድ ይለዋል፡፡ በዚህ በሚያሳምም ሂደት አሮጌዉ ምንቃር ተነቅሎ ይወገዳል፡፡ በአሮጌዉ ፈንታም አዲስ፣ ጠንካራና የሾለ አዲስ ምንቃር ይተካል፡፡ በዚህ አዲስና ጠንካራ ምንቃርም እነዚያ ያረጁና እንደወትሮ በቅልጥፍና በጥንካሬ ምግብ መንጭቀዉ ማንሳት የተሳናቸዉን ጥፍሮቹን ህመሙን ቻል አድርጎ ይነቃቅላቸዉና ያስወግዳቸዋል፡፡ በተወገዱት ጥፍሮች ምትክም አዲስ፣ የሾሉ ጠንካራ ጥፍሮችን ያበቅላል፡፡ በአዲስ ምንቃር እና ጥፍሮቹ በመጠቀምም የወየቡና የነተቡ ላባዎቹን በማስወገድ ክንፉን ያድሳል፡፡

ይህ የንስር አዲስ ህይወት ጉዞ ቢያንስ አምስት ወራትን ይወስዳል፡፡ በህመም የተሞላ ከሞት በስተቀር ሌላ አማራጭ የሌለዉ የዉሳኔና የተግባር ምዕራፍ የህዳሴ ጊዜ ነዉ፡፡ ንስሩ ይህን የህዳሴ ጊዜ እንደፈጸመም ወደ ከፍታዉ ይመለሳል፡፡ ሰማይ ላይ ከአዕዋፋት በላይ በተለመደዉ ፍጥነቱ ከነሙሉ ንስራዊ የእይታ ችሎታዉ ከፍ ብሎ መብረር ይጀምራል፡፡ እንደዶሮ ጫጩት መጫር አቁሞ ወደ ንስርነቱ ይመለሳል፡፡ ይታደሳል፡፡
አማራነት ንስራዊነት ነው።
ያለለት ወንድዬ

03/11/2020

"የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያ በማለቱ ብቻ በማንነቱ የተጨፈጨፈና የታደነ ህዝብ ነው" - እስክንድር ነጋ

አሁን በተጨባጭ የኢትዮጵያ ስጋት ራሱን ብልፅግና ብሎ የሚጠራው ኢህአዴግ ነው። ባልደራስና መኢአድ በጥምር የመሰረትነው ፓርቲ ደግሞ ኢትዮጵያን የሚያድን ፓርቲ ነው። አማራ ባለፉት 30 አመታት ኢትዮጵያ በማለቱ ብቻ በማንነቱ የተጨፈጨፈና የታደነ ህዝብ ነው። አሁንም እየታደነ ያለ ህዝብ ነው። ከዚህ አደጋ ለመውጣትም ከኢትዮጵያዊነት የመራቅ አዝማሚያ በተለይ በወጣቶቹ እየታዬ ነው።

እስክንድር ነጋ - ከየኔታ ትዩብ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ተቀላቀሉ! ለወደፊቱ ይጠቅመናል መረጃ የምናስቀምጥበት ቋታችን ነው
https://www.youtube.com/channel/UCU1wTaLCYyECpIXC02bPMsw
የቴሌ ግራም ቻናላችንንም እንዲሁ ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEe-Z_8LLoBRSPfdEA
https://t.me/joinchat/AAAAAETW6_7pzC2pYu2hpA

03/11/2020

ረ/ፕ በለጠ ሞላና ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ወደ አሜሪካ ለውይይት አቅንተዋል። የአማራ ጉዳይ አላስተኛ ብሎህ እንጂ ዶክተር ደሳለኝ የእናት ሞት ቀላል አልነበረም። እናመሰግንሃለን፣ መልካም ጉዞ!
የዩቲዩብ ቻናላችንን ተቀላቀሉ! ለወደፊቱ ይጠቅመናል መረጃ የምናስቀምጥበት ቋታችን ነው
https://www.youtube.com/channel/UCU1wTaLCYyECpIXC02bPMsw
የቴሌ ግራም ቻናላችንንም እንዲሁ ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEe-Z_8LLoBRSPfdEA
https://t.me/joinchat/AAAAAETW6_7pzC2pYu2hpA

03/11/2020

በታከለ ኡማ አላሰራ አለኝ የሚል ክስ የቀረበባቸው አቶ ፀጋ አራጌ ከሃላፊነታቸው ተነሱ

አቶ ፀጋ አራጌ አዲስ አበባ በኦነጎች ብቻ መጥለቅለቅን በመቃወም የሚታወቁ የአዴፓ አመራር ነበሩ።

በዚህም ከኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ ጋር በመሆን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አቶ ታከለ ኡማን በመገዳደራቸው ተደጋጋሚ አቤቱታ ለአብይ አህመድ ሲቀርብባቸው ነበር።

አብይ አህመድም ለታከለ ምቾት በማሰብ አቶ ፀጋ አራጌን በነገው እለት የፌደራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ለመሾም ምክር ቤቱን ጠርቷል።

ከአቶ ፀጋ በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በሚያካሂደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባው፦

1. ወ/ሮ አዳነች አበቤ፦ የፌዴራል ጠቅላ ዐ/ሕግ፣

2. አቶ ላቀ አያሌው፦ የገቢዎች ሚንስትር፣

3. ዶ/ር ሊያ ታደሠ፦ የጤና ጥበቃ ሚንስትር፣ አድርጎ እንደሚሾም የደረሰን መረጃ ያሳያል።

03/11/2020

በሸዋ ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ከተማ:- እምነታችሁን ካልለወጣችሁ የህክምና አገልግሎት አንሰጣችሁም ያለዉ እና በወንጀል ሊጠዬቅ የሚገባዉ ድርጅት
በሸንቁጥ አየለ
በሸዋ ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ከተማ የህክምና አገልግሎት በነጻ አገልግሎት እሰጣለሁ ብሎ የገባዉ ድርጅት በቀጥታ ህዝቡን ሀይማኖታችሁን ካልለወጣችሁ የነጻ ህክምና አግልግሎት አንሰጣችሁም ማለት ጀመረ::
በወረዳ ደረጃም ህዝብን በመቀስቀስ የነጻ ህክምና አገልግሎት እንስጣችሁ በማለት ጥሪ አደረገ::ህዝብም የእዉነት መስሎት ከየአካባቢዉ በመሰብሰብ የነጻ ህክምና ለማግኘት ሞከረ::

ሆኖም በነጻ ህክምና ሽፋን የህዝብ እምነት ለማስለወጥ የተዘጋጀዉ ድርጅት በይፋ "እምነታችሁን ከለወጣችሁ ብቻ ነዉ የነጻ ህክምና የምንሰጣችሁ" በማለት በህዝብ እምነት ላይ መሳለቅ ጀመረ::

ህዝቡም ጥያቄ ማንሳት እና መጮህ ጀመረ::ይሄ አስመሳይ ተኩላ ድርጅትም በህዝቡ ላይ መሳለቁን ቀጠለ::"የምትድኑት ሀይማኖታችሁን ከለወጣችሁ ብቻ ነዉ"ብሎም በአደባባይ ህዝቡ ያልዳነ እና እምነት የሌለዉ ህዝብ መሆኑን ይሄ ተኩላ ድርጅት ተናገረ::

የወረዳዉ ህዝብም ህዝባዊ እርምጃ ወስዷል::የሀገርም ሆነ የህዝብ ድህነት መዘባበቻ ሊሆን አይገባዉም::የህዝብን ቁሳዊ ድህነት በመጠቀም ህዝብን ማንቋሸሽ እና አንድን ህዝብ እምነት የለህም ማለት በጣም ታላቅ ወንጀል ነዉ::ስለሆነም ይሄ ድርጅት በወንጀል ሊጠዬቅ የሚገባዉ መሆኑን እናሳስባል::

03/11/2020

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የታገቱ የአማራ ተማሪዎችን በተመለከተ ፍትህ ይሰጠን ስንል ለአማራ ክልል የተለያዩ የመንግስት ተቋማት አቤቱታ ብናቀርብም አጥጋቢ ምላሽ አላገኘንም ሲሉ የታጋች ቤተሰቦች ተናገሩ።

ቁጥራቸው 17 እና ከዛ በላይ የሚሆኑ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የአማራ ተማሪዎች በማንነታቸው ተለይተው በታጣቂዎች ከታገቱ ዛሬ 98 ቀናትን አስቆጥረዋል።

የተማሪዎችን መታገት ተከትሎ የመንግስት ያልተገባ ዝምታን እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ደግሞ አንዳንድ የመንግስት አካላት የሰጧቸው እርስ በርስ የሚጣረሱ መረጃዎች አግባብ አለመሆናቸውን በመጥቀስ መንግስት በአስቸኳይ የማስለቀቅ ኃላፊነቱን ይወጣ በሚል በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ከጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉ ይታወሳል።

ሰልፉን ተከትሎ መንግስት የታጋች ቤተሰቦችን አዲስ አበባ ድረስ በመጥራት ያወያየ እና ከአንድ ወር በላይ የተቆጠረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ስለታገቱ ልጆቻቸው አንድም መፍትሄ አለመገኘቱን ነው ወላጆች የሚናገሩት።

ይህን ተከትሎም የ14 ታጋች ተማሪ ቤተሰቦች ትናንት መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ባህር ዳር በማቅናት በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በመግባት ፍትህ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን የአማራ ሚዲያ ማዕከል ያነጋገራቸው ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የታጋች ወላጅ አባት ተናግረዋል።

የታጋች አባት እንደሚሉት በትናንትናው እለት ወደ ባህር ዳር በመሄድ የርዕሰ መስተዳድር ቢሮን፣የፖሊስ ኮምሽንንና የሴቶች ጉዳይን በመጨረሻም የአማራ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ቢሮን አንኳኩተዋል።

የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳደር ቢሮ ብንገባም ስብሰባ ላይ ናቸው በመባሉ አልተሳካልንም ያሉት ምንጫችን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮምሽን ተወካይን ብናነጋግርም እስካሁን አዲስ ነገር የለም፣ወደ ፌደራል በመደወል እንጠይቃለን፣ እናፈላልጋለን ከማለት ውጭ አጥጋቢ ምላሽ አልሰጡንም፣ የሴቶች ጉዳይም ተመሳሳይ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ወደ አማራ መገናኛ ብዙሀን በማምራት አጠቃላይ የተሰማቸውን ቅሬታና መንግስትም በአስቸኳይ ፍትህ እንዲሰጣቸው ማሳሰባቸውን ምንጫችን ገልፀዋል።

ከልጆቻችን መታገት በተጨማሪ አንዳንድ የመንግስት ካድሪዎች እየመጡ የማስፈራራትና የመሰለል ሁኔታም እያጋጠመን ነውና መንግስት ካሉ ያስለቅቅልን፣ተገድለው ከሆነም ቁርጡን ሊነግረን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

03/11/2020
በፕሮቴስታንቱ ዓለም እየደረሰ ያለ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ኪሳራና የሥነ–ምግባር ዝቅጠት ያጋለጠ ቃለመጠየቅ

በፕሮቴስታንቱ ዓለም እየደረሰ ያለ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ኪሳራና የሥነ–ምግባር ዝቅጠት ያጋለጠ ቃለመጠየቅ

እራሳቸውን "ሐዋርያ" እና "ነብይ" እያሉ የሚጠሩ
የፕሮቴስታንቱ ዓለም ጉዶች በራሳቸው ስሜት እየተነዱ ከራሳቸው አፍልቀውና አመንጭተው ጌታ ነገረን መልዕክት መጣልን እንዲህ ይሆንልሃል እንዲያ ይደረግልሃል ጠላትህ ተሰበረ ተወጋ በማለት የዋሁንና ሞኙን ሕዝብ የህልም ዓለም ተስፋ በመስጠት ቁስሉን በመነካካትና ጎዶሎውን እየነገሩት ችግሩንና ብሶቱን በማይክራፎን ጮክ አድርገው እየነገሩት ስስ አንጀቱን እየሸነቆጡ ብሶቱን እያወሩለት እያስለቀሱት ሕዝቡን እያጭበረበሩና እያታለሉ እንዳለ የአደባባይ ምስጢ ነው ።

እነሆ ከዛ ሁሉ ቅጥፈት በኃላ የልባቸው ደርሶ የአማኙን ትዳር አፍርሰው ኪሱን አራቁተው የሺዎችን ነፍሳት ወደ ሲዖል ነድተው ሲያበቁ እንዲሁ እንደዋዛ በሚዲያ ብቅ ብለው በኩራት ተለጥጠውና ተኮፍሰው ከካሜራ ፊት ቁጭ ብለው ተሳስተን ነበር ዝም ብለን ነበር ስናወራ የነበረው ስብከቱም ስብከት ፈውሱም ፈውስ አልነበረም የውሸት ብለው ሲያወሩ ከመስማት የበለጠ ምን ኪሳራ አለ?

ይህ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቴስታንቱ ዓለም የሞራል ዝቅጠትና የሞራል ኪሳራ ነው!

በጣም የሚገርመው ነገር ዛሬም ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ የራሳቸውን ቅዠት የሚቃዡና የፈጠራ ወሬ የሚያወሩ እንደ ሐዋርያ ዳንኤል አይነት መኖራቸው ነው ግርምቴን ደግሞ እጥፍ የሚያደርገው ደግሞ ዛሬም ድረስ የእነዚህ "ሐሰተኛ ነብይና ሐዋርያ" ነን ባዮች አድናቂና ተከታዮች አለመንቃታቸውና ዛሬም በፅኑ እንቅልፍ ውስጥ መሆናቸው ነው

እናንተ የሐሰተኛ ነብያትና ሐዋርያት መጫወቻ የሆናችሁ ፕሮቴስታንቶች ሆይ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁት መቼ ይሆን? እንዳታስተውሉስ አዚሙን ያደረገባችሁ ማን ይሁን?

03/11/2020

በህዝብ ህልውና ላይ የሚፈፀም ዘላለማዊ ክህደት ይቁም!
||==========================||
ታግተው ይሙቱ ይኑሩ ባለታወቀ የደሀው የአማራው ገበሬ ልጆች ላይ 1 ወር ሙሉ በመንግስት ሚዲያ ሲዋሽና መላው የአማራን ህዝብ ያሳዘነው በዚህ ስብሰባ ላይ እንዴት ሊቀመጥ ቻለ?? አዴፓ ቢያዘጋጀው እንኳን የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ የውሀ ሽታ በሆነበት ሁኔታ የአማራ ሙህራንና ከዚህ አይነት ሰው ጋር በምን ጉዳይ ለመምከር ተቀመጡ??

2,የታገቱ ንጹህ የገበሬ ልጆችን በድርድርም ይሁን በሀይል ከአጋቹ ማስለቀቅ ያልቻለው #አዴፓ ፣ በታገቱት ተማሪዎች ጉዳይ አንድም ነገር ያልተነፈሰው ም/ጠሚው በዚህ መድረክ ላይ መሠየማቸው ምንድነው ፋይዳው?

3, ከ37,000 ሽህ በላይ የአማራ ተማሪዎች በአገሩ እንዳይማር ተለይቶ ቦዘኔ በሆነበት በዚህ ሰአት ፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ በሰላም እየተማረ አማራው ሲገደልና ሲፈናቀል በሰአቱ መድረስ ያልቻለውና መንግስትን ፈጣን ማስተካከያና መመሪያ እንዲሰጥ ማስጠንቀቅ ያልቻለ #አዴፓ ዛሬ ምን ሊፈይድ ለውይይት ተቀመጠ??...

My Conclusion!

ይች ስብሰባ የተዘጋጀችው #በአብይ አህመድ ትዕዛዝና በአዴፓ አስፈጻሚነት ሲሆን ፣ ከመንግስትና ከፖለቲካ ድርጅት ውጭ የሆነው የአማራ ወጣትም ከአዴፓ ዳጎስ ያለ አበልና ጠገብ የሚያደርግ መኖ እንደሚያገኝ ስለሰማ ተገኝቷል። #አብን የራሱ የፖለቲካ አጀንዳ ሊኖረው ስለሚችል አልናገርም።
(Endreas Z Abyssinia)
የዩቲዩብ ቻናላችንን ተቀላቀሉ! ለወደፊቱ ይጠቅመናል መረጃ የምናስቀምጥበት ቋታችን ነው
https://www.youtube.com/channel/UCU1wTaLCYyECpIXC02bPMsw
የቴሌ ግራም ቻናላችንንም እንዲሁ ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEe-Z_8LLoBRSPfdEA
https://t.me/joinchat/AAAAAETW6_7pzC2pYu2hpA

03/11/2020

የሰናኦር ግንብ ለአማራ ህዝብ ምኑ ነው
/ክፍል አንድ/

በእርግጥ ይህንን ርዕስ እንዲህ በቀላሉ አንስቶ ለመወያየት አስቸጋሪ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ "የአማራ ብሔርተኝነት" ተብሎ በደምሳሳው በሚጠራው ድንኳን ውስጥ የገባው አብዛኛው የቢቸግር ብሄርተኛ /Makeshift nationalist/ አፉ ከእኛ ጋር ቢሆንም ቅሉ፥ ልቡ ከጀበና ቅርጿ ተምኔታዊት-ኢትዮጵያ ጋር በፅኑ ፍቅር የወደቀ፤ እንዲሁም "የአንድነት ካምፕ" ኒቆዲሞሳዊ የሌሊት ደቀመዝሙር በመሆኑ ነገሮችን ከአማራ ህዝብ ጥቅም አንፃር ከመመርመር ይልቅ፥ በትናንት ተረት፣በዛሬ ተረኞች ሽንገላ እና በአጉል ጀብደኝነት ስለሚነዳ እንደዚህ ዐይነት ወሳኝ ጉዳዮች በአይነኬነት እንዲታለፉ ምክንያት ይሆናል።

ነገር ግን ጣፍጦ ተዋጠም፥ አልያ መርሮ አቅለሸለሸም ስለ አባይ ግድብ በተለይ ከአማራ ህዝብ ጥቅም አንፃር ያለውን እውነት በግልፅ መነጋገር ያስፈልጋል።
የአባይ ግድብ ማለት በዚያች ሀገር ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ ለተፈፀሙ ግፎች መገለጫነት የቆመ የሀጥያት ሐውልት አልያም የሰናኦር ግንብ ተምሳሌት ነው። ይህንን የምለው ከግድቡ ጋር በተያያዘ በአማራ ህዝብ ላይ ሆን ተብሎ በሴራ፣በተንኮልና በፖለቲካ ሸፍጥ በተፈፀሙ አራት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው።

1. አባይን በዘላቂነት ከአማራ ይዞታ ማውጣት /Permanent Dispossession on the Proprietorship of Abay/

2. ለግድቡ መሳካት፥አማራን የመስዋዕት በግ ማድረግ
/"Sacrifice the plum tree to preserve the peach tree"/

3. የአማራን ህዝብ በጅምላ ማቆርቆዝ /Grand exploitation of the mass/

4. የአማራን ህዝብ ጭሰኛ ማድረግና ከሰብዓዊነት ወደ ቁሳዊነት ማውረድ /Peonization and objectification of the Amhara people/
ዝርዝር ነጥቦችን አንድ በአንድ እያነሳን እንመልከት:-

1. አባይን በዘላቂነት ከአማራ ይዞታ ማውጣት /Permanent Dispossession on the Proprietorship of Abay/:-
ከስምንት ወር በፊት አንድ የመለስ አማካሪ የነበሩ ሰው በአባይ ግድብ የቦታ መረጣ ላይ ለመለስ ቀርቦ የነበረውን አማራጭ ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። በእርግጥ የአባይ ግድብ ይፋ በተደረገ ወቅት አዲስ አበባ የነበርንና ለጉዳዩ ቅርበት የነበረን ሰዎች በዚህ ዙሪያ ብዙ መባሉን ዛሬም እናስታውሳለን።
የአባይ ግድብ በወቅቱ ከቀረበው የዋጋ ጥናት በጣም ዝቅ ባለ ወጪ በአማራ ምድር መሰራት እንደሚችል ከዚህ በፊት በተሰሩ ጥናቶች ላይ ማሻሻያ ተደርጎ ፈጣሪ ነብሱን አይማረውና ለመለስ ዜናዊ ቢቀርብለትም፥ አንድም የመረብ-ባሮ የታላቋ ትግራይን ህልም በመሰነቁ፣ በሌላ በኩልም አማራ ፈጣሪ የሰጠውን ፀጋ እንዳያለማ፥ ይልቁንም ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ የአባይን ልማት ከአማራ ለመነጠል ሲል ብቻ ዛሬ የተሰራበት ቦታ ላይ ግንባታውን አስጀምሯል። በወቅቱ የወያኔ ትግሬ ካድሬዎችና የተላላኪው ብአዴን ባሪያዎች ቴክኒካል የሚመስሉ ትንታኔዎችን እየሰጡ ሲያደነቁሩን ነበር፥ ምንም እንኳን ጥረታቸው "Lecturing birds on how to fly" አይነት ቢሆንም።

የአባይ ግድብ በቤኒሻንጉል ክልል የመሰራቱ ብቸኛ ምክንያት በአማራ ጥላቻ የናወዘ የፖለቲካ ወሳኔ ነው። ይህ የፖለቲካ ውሳኔ አባይን ከአማራ ምድር ነጥሎ ከግድቡ ጋር በተጓዳኝ የሚኖሩ የልማት ፀጋዎችን በሙሉ ከአማራ ህዝብ እና ምድር ላይ በግፍ ለመግፈፍ ታስቦ የተፈፀመ ነው። በእርግጥም ጠላቶቻችን አማራን ለመስበር የሚጠቀሙበት ትልቁ የመውጊያ ጦር አንድም የአማራን ምድር የመልማት ፀጋውን ከተቻለ እንደ ዓባይ ግድብ ወደሌላ ስፍራ መውሰድ፥ አልያም እንደጣና ወይም እንደ ጢስ አባይ ፏፏቴ ባለበት ሥፍራ መግደል ነው።
ፈጣሪ በችሮታው የሰጠንን ሀብት በግፍ ከምድራችን ላይ አውጥተው፣ከግድቡ በተጓዳኝ የሚፈጠረውን ሰፊ የመልማት ፀጋችንን ለፍፃሜው አጨልመው የሚሰሩት ግድብ ለአማራ ህዝብ የሀጥያት ግንብ፥ ምስለ-ሰናኦር ነው። ከዚህ የዘለለ ትርጉም ሊሰጠው የሚሞክር ካለ፥ እሱ አንድም ወቅቱን የመገንዘብ ችግር ያለበት፥ አልያም የራስ-ከድ እና የራስ-ጠል የአማራ "ምሁራን" ስብከት ሰለባ የሆነና በገሃድ ጠፍታ በምናቡ ዓለም ካለቺው "እምዬ ኢትዮጵያ" ጋር በማይድን የመስተፋቅር ልክፍት የተያዘ ሰው ብቻ ነው።

2. አማራን የመስዋዕት በግ ማድረግ /"Sacrifice the plum tree to preserve the peach tree"/ አባይንና ተያያዥ የመልማት ፀጋውን ከአማራ ምድር አውጥተው መውሰዳቸው ሳያንስ፥ ይህ የግድብ ስራ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት የሚያገኘው ከጣና በለስ የሀይል ማመንጫ ነው። ከአስር ወራት በፊት "ጣና እንደምን ተገደለ?" በሚል ርዕስ ባወጣሁት ፅሁፍ ለመግለጽ እንደሞከርኩት የጣና ሐይቅን የለሆሳስ ሞት እያፋጠኑ ካሉ ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ የጣና በለስ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ነው። ይህም የሆነው ምንም እንኳን በፕሮጀክት ጥናቱ ላይ ከሐይቁ የሚወሰደው ውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ካመነጨ በኋላ ተመልሶ ወደ ሃይቁ ይገባል ቢልም፥ ወደተግባር ሲቀየር ግን ሆን ተብሎ በትህነግ ሴራ እና በብአዴን ተላላኪነት 12 ማይል ያህል በሰው ሰራሽ ቦይ ከሐይቁ የሚወሰደው ውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ካመነጨ በኋላ ወደ ሐይቁ ከመመለስ ይልቅ የበለስ ወንዝን እንዲቀላቀል ተደርጓል። ይህም የጣና ሐይቅን የውሃ ፍሰት ሚዛኑን ክፉኛ ስላዛባው፥ ከእንቦጭ አረም ጋር ተደምሮ ጣናን ሞቱን እያፋጠነው ነው።

እንግዲህ ጣና በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ እያቃተተ በሚያመርተው የኤሌክትሪክ ኃይል ነው፥ ከአማራ ምድር በፖለቲካ የሴራ ውሳኔ የተነጠቀው የአባይ ግድብ የሚገነባው። የአባይ ግድብንና ተያያዥ የመልማት ፀጋዎቻችንን ከአማራ ምድር መንጠቅ አንድ ነገር ሆኖ፥ የነጠቁትን ለማልማት ደግሞ በጣና ሞት ላይ የሚመረትን ሀይል መጠቀም ለጠላቶቻችን "ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል" ሲሆን፥ ለአማራ ህዝብ ግን ድርብ-ጉዳት /Double Jeopardy/ ነው።

ይቀጥላል....
[ዴቭ ዳዊት]

03/11/2020

Gorgora.com

ያለ ፍርድ በትህነግ/ህወሓት ከዓመት በላይ ያለምንም ወንጀል ሁመራ ላይ የሚገኙት የወልቃይት ጠገዴ የግፍ እስረኞች:-
1).አለምሸት አዳነ. 13)ባበይ ሀይሉ
2.)ሳሙኤል ብርሃኑ 14)ጥላሁን ቢያድግልኝ
3).አለምነው መኮነን 15)ማማይ የኔሁን
4).ሀብቴ ልጃለም. 16)ብርሃኑ አሰፋ
5)ታዝቦ አዳነ. 17)ኃይሉ ወንድም
6).አደራጀው በሪሁን. 18).ባበይ ደምሴ
7)ፍቃዱ ገ/ሔር. 19)ጠውር ርስቀይ
8)ሲሳይ ማለደ. 20)ብርሃኔ በርሄ
9)አስፋቸው ማሾ. 21)ማሙየ አርኩ
10)በላይ ፍቃዱ. 22)ጌታ አመኑ
11)ኃይሌ ገረመው 23)መለስ ሽበሽ
12)ገብሩ ወዳጀ. 24)ፋሲል መካኒክ

በግፍ በትህነግ/ህወሓት ለታሰሩት ወንድሞቻችን ድምፅ ልንሆናቸው ይገባል!

©አብየ

03/11/2020

"ሞተዋል ወይም በሕይወት አሉ ይበሉን'' የታጋች ተማሪዎች ቤተሰብ !
• ተለቀዋል የተባሉት ታጋቾች የት ናቸው?!
ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ በነበሩበት ወቅት ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምንም መፍትሄ እንዳልተገኘለት የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ተማሪዎቹ ከታገቱ ወራት የተቆጠሩ ሲሆን ወላጆች ልጆቻቸው መታገታቸውን ከሰሙ ጀምሮ ለሚመለከታቸው አካላት ልጆቻቸውን እንዲመልሱላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል።
ዛሬ ደግሞ ከአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር ባህር ዳር ተገኝተው ነበር። ወይዘሮ እንዳለች ይመር ሴት ልጃቸው እስታሉ ቸኮለ ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንደኛዋ እንደሆነች ይናገራሉ።
'' እኔ እንዳልሰማ ቤተሰቡ ሲጠነቀቅ ነበር፤ አባትየውም ሲመላለስ ነው የከረመው። ድንጋጤውም ምኑም ተጨማምሮበት አሁን ጨጓራውን ሲታመም ነው እኔ ወደ ባህርዳር የመጣሁት። እኔ ጉዳዩን አልስማ እንጂ ልጄ ድምጿን ካጠፋች ብዙ ጊዜ ሁኗታል።'' '' ይኀው መጥፋቷን ከሰማን ወዲህ ስልክ እንደውላለን፤ ምንም ነገር የለም። ያው ምን አማራጭ አለን ቤተክርስቲያን እየተሳለምን ማልቀስ ነው'' ይላሉ እንባ እየተናነቃቸው።
ምናልባት ከመንግሥት አካል የተሰጣቸው ምላሽ እንዳለ የጠየቅናቸው ወይዘሮ እንዳለች '' ወደ ትምህርት ቤታቸው ተመልሰዋል። ዩኒቨርሲቲ ገብታ ትምህርቷን እየተከታተለች ነው አሉን። ብንጠብቅ ብንጠብቅ ምንም የለም፤ እስቲ አሁን መልስ ካገኘን ብለን ነው ባህርዳር የመጣነው'' ይላሉ።
'' በቃ ወይም ሞተዋል ወይም በሕይወት አሉ ይበሉን፤ እኛም እርማችንን አውጥተን አርፈን እንቀመጥ።''
ሌላኛው ልጃቸው እንደታገተችባቸው የሚገልጹት መሪጌታ የኔነህ አዱኛ ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ስትመለስ የታገተች ልጃቸውን በተመለከተ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ድረስ መሄዳቸውን ገልጸዋል።
ወደ ባህር ዳር በመምጣት ከክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር የወሰኑበትን ምክንያት ሲገልጹም "አቶ ደመቀ መኮንን በህይወት እንዳሉ፤ ታገቱ በተባለው አካባቢ ምንም ጉዳት እንደደረሰ የሚሳይ ምልክት አለመኖሩን ነግረውናል። ምከሩ ብለው በተለይ እናቶችን አበረታቱ ብለው ተመለስን። ከተመለሰን በኋላ በአጭር ጊዜ መፍትሔ ይመጣል ብለን ነበር። 35 ቀን ሆነን ውጤት ባለመገኘቱ ዛሬ ክልል መጥተናል" ብለዋል።
"ያው ይለቀቃሉ እናስለቅቃለን ተረጋጉ ነው ያሉን። መቼ እንደሚለቀቁ አልነገሩንም ፤ የተለቁቁም ያልተለቀቁም አሉ" ተብለን ነበር የሚሉት ደግሞ አቶ ላቀው ጓዴ ናቸው። ተማሪዎቹን ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን በመግለጽ ውጤቱን እንደሚነገራቸው ቢገለጽላቸውም ምላሽ በመዘግየቱ ምክንያት አቤት ለማለት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን እና የመንግሥት ዝምታ
በባህር ዳር ቆይታቸውም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ እና ፖሊስ ኮሚሽን በመሄድ ስለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ቢሞክሩም በተለያየ ምክንያት ኃላፊዎችን ሳያገኙ መቅረታቸውን ገልጸውልናል። ከሦስት ወራት በላይ የልጆቻቸውን ድምጽ ያልሰሙት ወላጆች በእነዚህ ጊዜያት ብዙ ችግሮች እንደገጠሟቸውም ነው ያስታወቁት።
የእህቷን ጉዳይ ለመከታተል አዲስ አበባ የነበረችው የታጋች ተማሪ እህት ፍቅርዓለም ቸኮለ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ እንደምትገኝም ወይዘሮ እንዳለች ይመር ለቢቢሲ ገልጸዋል። '' እህቴ ጠፋች፤ ፈልጉልኝ፤ ሰኔ ላይ ተመራቂ ናት እያለች ስትጮህ ይዘው እስር ቤት ከተቷት። መታሰሯን ከሰማን ወር ሆነው፤ ግን ከዚያም ይበልጣል። የእስታሉ ታላቅ እህቷ ነች፤ ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀች ሁለት ዓመ

03/11/2020

ትናንት ማምሻውን ሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ ላይ የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ቃጠሎ ደርሶበታል::

በቃጠሎው ሦስት የእምነቱ ተከታዮች በድንጋይ ተደብድበው ህክምና ላይ መሆናቸው ታውቋል::

የረብሻው መንስኤ የህክምና እርዳታ እናደርጋለን በማለት ወደ ስፍራው አቅንተው በህገወጥ መንገድ ከአካባቢው ማህበረሰብ ሀይማኖት እና ወግ ጋር የማይጣጣም የሀይማኖት ስብከት ማድረጋቸው የከተማውን ወጣቶች አስቆጥቷል።

ምሽቱን ከከተማው ፖሊስ በተጨማሪ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አድማ በታኝ ችግሮችን ለመቆጣጠር ከደብረርሃን ወደ እነዋሪ ከተማ እንደገባ ምንጮች ከቦታው ገልፀዋል::
Gorgora.com

03/11/2020

ባልታወቀ ሰዎች የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምንም መፍትሄ እንዳልተገኘለት የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ይናገራሉ፡-

- '' በቃ ወይም ሞተዋል ወይም በሕይወት አሉ ይበሉን፤ እኛም እርማችንን አውጥተን አርፈን እንቀመጥ።''

- "አቶ ደመቀ መኮንን በህይወት እንዳሉ፤ ታገቱ በተባለው አካባቢ ምንም ጉዳት እንደደረሰ የሚሳይ ምልክት አለመኖሩን ነግረውናል። ምከሩ ብለው በተለይ እናቶችን አበረታቱ ብለው ተመለስን። ከተመለሰን በኋላ በአጭር ጊዜ መፍትሔ ይመጣል ብለን ነበር። 35 ቀን ሆነን ውጤት ባለመገኘቱ ዛሬ ክልል መጥተናል"

- '' እህቴ ጠፋች፤ ፈልጉልኝ፤ ሰኔ ላይ ተመራቂ ናት እያለች ስትጮህ ይዘው እስር ቤት ከተቷት። መታሰሯን ከሰማን ወር ሆነው፤ ግን ከዚያም ይበልጣል። የእስታሉ ታላቅ እህቷ ነች፤ ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀች ሁለት ዓመት ሆኗታል። አዲስ አበባ ስራ እየፈለገችም ነበር።''

- " 95 ቀን እያለቀስን ነው፤ አዝመራ አልተሰበሰበም። እናቶች በአእምሮ እየተጎዱ ነው። እኛም እየሰራን አይደለም። ልጆቻችንን አረጋግተን ማስተማር እንፈልጋለን። ልጆቹ እኛንስ ምን ይገጥመናል? ትምህርት ምን ይጠቅመናል? ብለው አንማርም ብለው ደብተርም አላነሱም። በዚህ ተጎድተናል።''

- '' ሞተው ከሆነ ሰምተን ከዘመድ ጋር ተላቅሰን ወደ ሥራችን ተመልሰን ረጋ ብለን እንድንቀመጥ ነው የምፈልገው። ከተገኙና በህይወት ካሉ በድምጽም ቢሆን ብንገናኝ። ከሁለት አንዱን መንግሥት ቢነግረን እረፍት እናገኛለን። መንግስት በአፋጣኝ እናቶች አእምሯቸው የበለጠ ሳይዛባ እንዲስተካከሉ ቶሎ ከሁለት አንዱን ቢለይልን ነው የምፈልገው"

ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ https://
telegra.ph/BBC-03-11
BBc

03/11/2020

ስንቶቻችን ይኼን አስደናቂ ሚስጢር እናውቃለን?

በአባ ገብረ መስቀል ተሰማ ሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ ጋሸና ከተማ አቅራቢያ ላይ የተሰራው ዳግማዊ ላሊበላ ብዙ ሚስጥሮችን ይዟል።

1. በፎቶ ቁጥር አንድ ላይ የተፈለፈለችው ቤተ ክርስቲያን በዳግማዊት ኢየሩሳሌም አምሳል ሲሆን በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ላይ እሷን የሚመስል የቤተ ክርስትያን ዲዛየን የለም።

2. በፎቶ ቁጥር አራት ላይ የተሰራው በሶስት ማዕዘን የተሰራው እጅግ አስደናቂ ሙሉ የድንጋይ ፍልፍል ቤተ ክርስትያን ሲሆን የላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን የተሰራው በመስቀል አምሳል በ 'ተ' ፊደል ቅርጽ ሲሆን ይሄኛው ግን የተፈለፈለው በሶስት ቅስቶች ነው።የዚህ አይነት ዲዛየንም የመጀመርያው ነው።

3. በፎቶ ቁጥር ሁለት የተሰራው የኢትዪጵያን ካርታ ቅርጽ ይዞ የተፈለፈለ ሲሆን ኢትዮጵያን በሁለት ግዙፍ ፍልፍል መስቀሎች መሀል አድርጎ የተሰራ እጅግ አሰናቂ ኪነ ሕንጻ ነው::

4. በፎቶ ቁጥር 3 የተሰራው ደግሞ የላሊበላን አፍሮ አይገባ መስቀል ዲዛየን ይዞ የተሰራ ሲሆን የዚህ አይነት ፍልፍል ሕንጻም እስካሁን አልታየም።

“አፍሮ አይገባ ገባሬ ተዓምር ዘ ላሊበላ” ከንጹህ ወርቅ የተሰራ ሲሆን ሰባት ኪሎ አካባቢ ይመዝናል፡፡ በብቸኝነት የሚገኘው ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በግዝፈቱ ቀዳሚ በሆነው በቤተ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። መስቀሉ አፍሮ አይገባ የሚለውን ስያሜ ያገኘው “የተጣሉትን በማስታረቅ - የታመሙትን በመፈወስ” በሚፈጽመው ተዓምር ነው፡፡

አፍሮ አይገባ በ1989 ዓ.ም. ተሰርቆ ወደ ቤልጅየም ተወስዶ ነበር፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላም ግንቦት 21 ቀን 1991ዓ.ም በከፍተኛ ጥረት ከቤልጅየም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በነበረበት መቅደስ ለመቀመጥ ችሏል፡፡
በቴሌግራም ያግኙን
https://t.me/joinchat/AAAAAEe-Z_8LLoBRSPfdEA

©ናኪ ሆቴል

03/11/2020

የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ መቋቋሙን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ!!!

ባለፉት ሰላሳና አርባ ዓመታት አማራ-ጠል ኃይሎች የፈጠራ ትርክቶች ደርሰውና የአማራን ሕዝብ ድምጽ-አልባ አድርገው ለከፍተኛ ጉዳት ዳርገውት ኖረዋል። ይሁንና ሕዝባችን ድምጽ እንዲያገኝ አሥራት በተቆርቋሪ ልጆቹ ተመስርቶና በአማራ ሕዝብ ወዳጅ ኢትዮጵያውያን ተደግፎ ለፍትሕ፣ ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ ድምጽ በመሆን ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ይህንን የሕዝብ ሚድያ ከምሥረታው አንስቶ ሕዝብን በማስተባበር ከዚህ ያደረሰው መሥራች ኮሚቴ፤ በዘላቂነት አመራር ሊሰጥ የሚችል፤ የማኅበረሰባችንን አስረጫጨት፣ ስብጥርና አደረጃጀት ያገናዘበ ጠቅላላ ጉባዔ አዋቅሯል። ይህ ፶፩ (ሃምሳ አንድ) አባላት የሚኖሩት ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ ካለው ሕዝብ የተውጣጡ ግለሰቦች፣ በተለያዩ ክፍላተ-ዓለም ከሚኖረው የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ከተውጣጡ ግለሰቦችና በማኅበረሳባችን ከተለያዩ አደረጃጀቶች ወኪሎች የተዋቀረ ነው። ጠቅላላ ጉባዔው የተለያዩ የስራ ክፍሎች ሲኖሩት፤ በሰብሳቢ፣ በምክትል ሰብሳቢና በጸሐፊ ይመራል።

ጠቅላላ ጉባዔው ከአባላቱ መካከል፤ ፲፭ (አሥራ አምስት) ግለሰቦች የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በማድረግ በድምጽ ብልጫ መርጧል። ከ፲፭ቱ መካከል ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹና ዶ/ር አበበች በላይ ቦርዱ እራሱን እያዋቀረ በነበረበት ሂደት ላይ በመልቀቃቸው ምክንያት በምትካቸው በተጠባባቂነት በጠቅላላ ጉባዔው ተመርጠው የነበሩት አቶ ፍስሐ ወርቁና አርቲስት ቤተልሔም ዳኛቸው ተተክተው በቦርድ አባልነት እንዲያገለግሉ ተወስኗል።

ይህም የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በ፲፩ (አስራ አንድ) የሥራ መደቦች እንደሚከተለው ተዋቅሯል።
✔️1ኛ) ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ (ሊቀመንበር)፣
✔️2ኛ) አቶ ተፈሪ ጋሻው (ም/ሊቀመንበር)፣
✔️3ኛ) አቶ ግዛቸው ምትኩ (ጸሐፊ)፣
✔️4ኛ) አቶ ዘላለም ስንሻው (ፋይናንስ)፣
✔️5ኛ) አቶ ሰለሞን አያሌው (ህግ፣ ስነምግባርና ቁጥጥር)፣
✔️6ኛ) አቶ እሸቱ ቢያድጎ (የሰው ሀይልና አስተዳደር)፣
✔️7ኛ) ዶ/ር ጋሻው አያሌውና አቶ ፍስሐ ወርቁ (ሚዲያ፣ ቴክኖሎጂና ስነዳ)፣
✔️8ኛ) ልጅ ተድላ መላኩ (የሕዝብ ግንኙነት)፣
✔️9ኛ) ዶ/ር አክሎግ ቢራራ (አድቮኬሲና የውጭ ግንኙነት)፣
✔️10ኛ) አቶ በሪሁን አዳነ (ምርምር እና አቅም ማጎልበት)፣
✔️11ኛ) ዶ/ር ደረጀ ተክለማርያም፣ ወ/ሮ ኤደን ሲሳይና አርቲስት ቤተልሔም ዳኛቸው (ማደራጃና የሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማሰባሰብ)፣
✔️12ኛ) ወ/ሮ ቢታንያ አበበ በቦርድ አባልነት ተመድበዋል።
አሥራት የሕዝብ ሚድያ እንደመሆኑ መጠን፤ የሕዝብ ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ፤ ቦርዱ ጠቅላላው ሕዝብ የሚሳተፍባቸው የቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች መዋቅር ዘርግቷል። እንዲሁም፤ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች፤ ሕዝቡ በየአካባቢው የሚሳተፍባቸውን ድጋፍ ሰጭ ማዕከሎች በማዋቀር ለመሥራት ዕቅድ ይዟል።

በመሆኑም፤ መላው የአማራ ሕዝብና የአማራ ወዳጅ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ይህንን ቦርድና የአሥራትን ሚድያ ለማስቀጠል፣ እንዲሁም አገልግሎቶቹ ሰፍተው ለሕዝብና ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ ይጎለብት ዘንድ በሚደረገው ጥረት ሕዝባዊ ተሳትፎና ትብብር እንዳይለየው በሕዝባችን ስም እንጠይቃለን።
እናመሰግናለን፤

የአሥራት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ
መጋቢት ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓመተ ምህረት

Address

በረራ
Amsterdam, NY

General information

Amhara

Website

Products

Amhara

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gorgora.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gorgora.com:

Videos

Share

Category

Nearby media companies


Other Video Creators in Amsterdam

Show All