15/10/2023
ሰበር መረጃ
የዘረፋ ጥምረት
ክፍል1
ተስፋ የቆረጠው የሲዳማ ክልል ፕረዚዳንትና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀዋሳ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ የዘረፋ ጥምረት በማድረግ ንግድ ባንኩንና ሲዳማን እያሯቆቱ ይገኛሉ።
የሲዳማ ህዝብ ክልል ከሆነበት ማግስት ጀምሮ በተለያዩ አሰቃቂና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀው የተጋለጠ እውነት ነው።
ሌብነት፣ዘረፋ፣ኮንትሮባንድስነት ጎሰኝነት፣ጎጠኝነት፣አፈና፣የጅምላ እስራት፣ሥራ አጥነት፣ኢ-ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል፣ ሹመት በገንዘብ፣ዝውውር በገንዘብ፣ፍትህ በገንዘብ:-
በቃ በአጠቃላይ የመንግስትነት መስፈርት እንኳን የማያሟላ ክልል ሆኖ መቆየቱ የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ ዋነኛ ማሳያ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ:-
"አንገት ላይ ጆሮ ደግፍ" እንደሚባለው ይህ ዘረፋ የኔትወርክ አድማሱን በማስፋት የሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት ተስፋና የጀርባ አጥንት በሆነው ንግድ ባንክ ጋርም የዘረፋና የሌብነት ጥምረት የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ወደ ተሟላ ዘረፋ ሥራ ተሸጋግሯል።
ከንግድ ባንክ ጋር ያለውን የዘረፋ ሥራ በዋናነት የሚመራው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ በአቶ #ካሳሁን-ጉዊሶ ማስተር ማይንድነት ነው።
ይህ ግለሰብ ለሥራ ተብሎ በተሰጠው በመንግስት መኪና ውስጥ በቁጥር ይህ ነው ተብሎ ለመጥቀስ እንኳን የሚያዳግት የውጭ ገንዘቦችን በተለይም ዶላሮችን ይዘው ነው የሚንቀሳቀሰው።
የእነዚህ የህገ ወጥ ዶላር መዳረሻቸው በይ/ዓለም ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኘው የአዋዳ CZA የሚባለው ችቡድ ፋብርካ ነው።
አቶ ከሳሁን ከዚህ ፋብርካ ባለቤቶች ጋር በሚሠራው የዶላር ጥቁር ገበያ/black Market/ ምክንያት ከአቅሙ በላይ የሆነ ህገ ወጥ ሀብት ያካበተና የብዙ ፋብርካ ባለቤት ሆኗል።
የህዝብና የመንግስ ሀብት ደጀን የሆነው የንግድ ባንክ ስብዕና በዚህ ልክ ስጎድፍና ስቆሽሽ እንደማየት የሚያሸማቅቅና ተስፋ የሚያስቆርጥ ምንም ነገር የለም ደግሞም አይኖርም ።
መንግስት የትኛውም የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ በባንክ በኩል ብቻ እንዲሆን ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ባለበት በዚህን ጊዜ የባንክ ሥራ አስኪያጆች ለዚህ ሥራ በተቃራን መቆማቸው ያሳፍራል።
በመሆኑም የሀዋሳ ንግድ ባንክ ዲስትሪክት ሥራ አስክያጅ ጉዳይ በባንኩ ቦርድና አመራር በፍጥነት ታይቶ ማስተካከያ ካልተደረገ የባንኩ ተዓማኒነት በሚገርም ፍጥነት አደጋ ውስጥ ይገባል። የሲዳማ ክልል ፕረዚዳንት ከባንኩ ሥራ አሰኪያጅ ጋር በመተባባር የሚፈፅሙት ተግባር ስለሆነ መፍትሔ መስጠት አይችልም።
ይቀጥላል-------