16/03/2024
የጥቁር_አዝሙድ_አስደናቂ_ጥቅሞች
_____
1ኛ. ለእርጋታ
• አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶሆድ መውሰድ ቀኑን ሙሉ መረጋጋትና ንቃት ያጎናጽፋል፡፡
• እንዲሁም ከራት በኋላ ወደ መኝታ ከማምራት በፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት መውሰድ ለሊቱን ሙሉ የተረጋጋና ደስ የሚያሰኝ እንቅልፍ ያስገኛል፡፡
• አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል፡፡
2ኛ. ለሳልና ለአስም
• በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት፣ ሁለት ማንኪያ በሙቅ ውኃ ውስጥ ጨምሮ እንፋሎቱን መሳብ ይረዳል፡፡
3ኛ. የመጫጫንና ስንፍናን ለማስወገድ
• አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት በአንድ ብርጭቆ ብርቱካን ጭማቂ ውስጥ ጨምሮ ጧት ጧት ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ ልዩነቱን ያገኙታል፡፡
4ኛ. የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለማጎልበት አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናና (Nena) ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ፡፡
5ኛ. ለኩላሊት ጠጠር (የስኳር ሕመም ያለባቸው ማርን መተው ነው) ሩብ ኪሎ ጥሬ ጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ኪሎ ንጹሕ ማር ማዘጋጀት፡፡ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ፡፡ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሻይ ማንኪያ በማከል በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡
6ኛ. ለብሩሕ ገጽና ለውበት
አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ በውኃና በሳሙና መታጠብ ልዩነቱን በጉልህ ያገኙታል፡፡የጥቁር
7ኛ. ከበሽታ ሁሉ ለመጠበቅ
አንድ የሾርባ ማንኪያ አዝሙድ ዘይት ከአንድ ማንኪያ ማር ጋር አዋሕዶ ያለማቋረጥ ጧት ጧት መውሰድ በጣም ጤናማ ያደርጎታል።
8ኛ. በጭንና ጭን መካከል የቆዳ መቆጣት ሲያጋጥም በቅድሚያ አካባቢውን በውኃና በሳሙና በሚገባ ማጠብ፣ ቀጥሎ በሚገባ ማድረቅና በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማታ ቀብቶ ማደርና ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይህንኑ መፈጸም፡፡ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ውጤቱን ያዩታል፡፡
9ኛ. ለልብና ለደም ሥሮች ሕመም
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከትኩስ መጠጥ ጋር በተከታታይ
መውሰድ ስብን ለማሟሟትና የደም ሥሮችን ለማስፋት
ይረዳል፡፡
10ኛ. ለለምጽና ለመሳሰሉት
ተጠቂውን የሰውነት ክፍል በቱፋሕ (ፖም) ወይም አፕል
ኮምጣጤ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት ለ15 ቀናት መቀባት፡፡
11ኛ. ለቁርጥማት ሮማቲዝምና የጀርባ ሕመም
የተወሰነ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥቂቱ በማሞቅ የታመመውን አካል አጥንትን ዘልቆ እስኪሰማ ድረስ በዘይቱ በደንብ መታሸት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት መጠጣት፡፡
12ኛ. ለራስ ምታት
በጥቁር አዝሙድ ዘይት ግንባርንና በጆሮ አካባቢ ያለውን አካል ማሸት ለሦስት ተከታታይ ቀናት አንድ ሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡
13ኛ. ለጨጓራና ለአሲድ
አንድ ኩባያ ወተት የአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ
ዘይት በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ፡፡ ከሦስት ቀናት በኋላ በሽታው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል፡፡
14ኛ. ለራስ ማዞርና ለጆሮ ሕመም
አንድ ጠብታ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጆሮ ውስጥ መጨመር
በሻይ መልክ አዘጋጅቶ መጠጣት፡፡
15ኛ. ለቆዳ መቀረፍ
በዚህ አይነቱ ሕመም የተጠቃው የአካል ክፍል በጥቁር አዝሙድ ዘይት መቀባት ሕመሙ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መቀጠል፡፡