Ethiopian

Ethiopian Ethiopian ፔጃችን like እና share አድርጉልን እናመሰግናለን!
ቅድስት ሀገሬ ኢትዮጵያ ለዘላለም ኑሪ!!!!!
(100)

Street football rules The old days :1. No referee.2. The game ends either when players are tired or their families call ...
15/11/2024

Street football rules The old days :
1. No referee.
2. The game ends either when players are tired or their families call them for dinner
3. The score is 23-22.
4. A penalty is given if a player swears on god.
5. The chubby person becomes the goalkeeper 😝.
6. If the ball owner gets angry, he take the ball, and the game is over 😁.
7. The fouls is counted if everyone agrees 🙃.
8. The wal is a good player and can be in your team side at any time 😁.
9. An extra player is allowed if the teams are not equal 😂
10. Goalkeepers can be changed during a penalty kick 😆.
11. If the ball goes over the crossbar, the game pauses for half an hour to discuss whether it's a goal or not 😄.
12. The ball owner plays for the stronger team 😝.

Greetings to everyone who lived these beautiful memories ❤️

📌የመንበር ዓለሙ ታሪካዊ የፍርድ ቤት ንግግር ፈፅመሀል የተባልሁትን ወንጀል አልፈፀምሁም።  ለዚህ የልብ ወለድ ክስ የዳረገኝን የpoletical motive በተመለከተ ግን አንድ ነገር ማንሳት...
14/11/2024

📌የመንበር ዓለሙ ታሪካዊ የፍርድ ቤት ንግግር

ፈፅመሀል የተባልሁትን ወንጀል አልፈፀምሁም።
ለዚህ የልብ ወለድ ክስ የዳረገኝን የpoletical motive በተመለከተ ግን አንድ ነገር ማንሳት እፈልጋለሁ።

አለም በአንድ ድምፅ ያወገዘውን፣ በጥቁር መዝገብ የመዘገበውን፣ በናዚው ፊትአውራሪ ሂትለር አማካኝነት በይሁዳዊያን የተፈፀመውን የዘር ማፅዳት በሚያስንቅ ሁኔታ አማራወች ላይ ባለፉት 6 ዓመታት የዘር ማፅዳት ሲፈፀም አይተናል።

አማራ በመሆናቸው ከ15 በላይ የዩንቨርሰቪቲ ሴት ተማሪወች እንደወጡ ቀርተዋል፣ ህፃናት፣ አዛውንት፣ እመጫት ንፁሀን አማራወች በተኙበት ቤታቸው ከውጭ ተዘግቶባቸው በእሳት ተቃጥለዋል፣ ነፍሰ-ጡር እናቶች የአማራ ፅንስ እንዳይወልዱ በእንጨት ተቀደው ፅንሱም እነሱም ሲገደሉ ተመልክተናል፣ አማራ መሆን ቀርቶ፤ የአማራ እንስሳት መሆን እንኳን ወንጀል ሆኖ በሬወቹ እነ ጮሬ፣ ላሞቹ እነ አደይ፣ ፍየሎቹ እነ ጠዲት፣ ስንዲት በጋጥ እንደተዘጉ ተቃጥለዋል።

አማራወች ለስብሰባ እየተጠሩ ታርደዋል፣ በጅምላ የዘር ፍጅት ተፈፅሞባቸው፣ በጅምላ ተገለውም የሰውነት ክብረ-ፀጋው ተነፍጓቸው ከሞላው የአማራ መሬት ለአማራወች አስከሬን 3 ክንድ መሬት መቃብር ተነፍጎት በጅምላ በዶዘር ሲቀበሩ አይተናል ተመልክተናል። እኔ ይሄ ሁሉ ግፍ የሚፈፀምበት፣ ሳይበድል የተፈረደበት፣ መከረኛ ህዝብ አካል በመሆኔ እና እንደ አንድ የተማረ ሙህር አማራን የማፅዳቱን ወንጀል በመቃወሜና በመሞገቴ ብቻ ወንጀለኛ ነህ ተብየ በመንግስት አይነተኛ በትር በሆነው የልብ-ወለድ ክስ ተመስርቶብኛል።

እኔ ላይ የተፈጠረው ነገር:-
''በገብረማሪያም ሰርግ፣ ወልደማሪያምን እንደማወደስ'' የሚቆጠር ነው! አማራን በጅምላ የሚገሉት እና የሚያስገድሉት በህግ ሊጠየቁ ይገባል በማለቴ፣ ንፁሀን አማራወችን ገዳይ እና አስገዳይ ቁመው ሊጠየቁበት በሚገባው የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ-ቤት እኔ ከተገዳዩ እና የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመበት ካለው አማራ በመወለዴ በሀሰት ተከስሻለሁ።

እኔ ግን እላለሁ:-
- unversal በሆነው የክርስትና እምነቴ፣
- ፋሽስታዊ የሆነው ስርዓት በሚቃወመው የፖለቲካ አመለካከቴ፣
- አማራዊ በሆነው ማንነቴ እና ህያው በሆኑት አባቶቸ እና ስም ምየ የምነግራችሁ በግልም ሆነ በቡድን ፈፅመሀል የተባልሁትን ወንጀል አልፈፀምሁም። ወንጀሌ አማራ ሁኘ መወለዴ እና የአማራን ዘር ማፅዳት ተቃውሜ በመገኘቴ ብቻ ነው። ይሄን ደግሞ ቀጣይም እስከ መጨረሻዋ እስትንፋሴ የማደርገው ነው። ለታሪክ ይመዝገብልኝ አመሰግናለሁ።

መንበር አለሙ
ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተናገረው

11/11/2024

በካንሰር የምትሰቃየውን ይህችን እህት እንታደጋት።
(እባካችሁ ቢያንስ ለ10 ሰው ሼር አድርጉላት ፀልዩላት።)

ባህርዳር 04 ቀበሌ ወጣቱን በተለያዩ ቤት እየገቡ ሲያፉሱ ዉለዋል። ከፖሊሶች ዉስጥ የቀበሌ 04 ፖሊስ ክቡሮም የሚባልም አለ፤ ከፖሊሱ በስተ ግራ ሲቪል የለበሰዉ ዋና አስተባባሪ ነዉ!በተያያዘ...
11/11/2024

ባህርዳር 04 ቀበሌ ወጣቱን በተለያዩ ቤት እየገቡ ሲያፉሱ ዉለዋል። ከፖሊሶች ዉስጥ የቀበሌ 04 ፖሊስ ክቡሮም የሚባልም አለ፤ ከፖሊሱ በስተ ግራ ሲቪል የለበሰዉ ዋና አስተባባሪ ነዉ!

በተያያዘ ዜና ዛሬ ከውጫሌ ወደ ደሴ ከተማ የውጫሌ ነዋሪ የሆኑ ወደ ስልሳ የሚጠጉ ወጣቶችን አፍነው ወደ መርሆ ግቢ ወስደዋቸው ነበር፤ በዚህም የተነሳ የልጆች ወላጆች ልጆቻቸውን ፍለጋ ተከትለው ሂደው፤ ልጆቻችንን ስጡ በማለት የጠየቁ ሲሆን መከላከያም እናንተ ሂዱ እንልካቸዋለን ብሎ መልስ ቢሰጥም ነገር ግን ወላጆች ልጆቻችንን ይዛ ካልሄድን አንሄድም በማለታቸው ልጆቻቸው ከአፈናው ተለቀዋል፡፡

ዜናነህ መኮንን - ነፍስ ይማር ታላቁ ደራሲና ጋዜጠኛ የዜና አንከር ዜናነህ መኮንን አረፈአሁን ታሪኩን የምናቀርብላችሁ ሰው ጋዜጠኛ ፤ ደራሲ ፤ ገጣሚ ሀያሲና የዜና አንከር ወይም ስመጥሩ የዜ...
11/11/2024

ዜናነህ መኮንን - ነፍስ ይማር

ታላቁ ደራሲና ጋዜጠኛ የዜና አንከር ዜናነህ መኮንን አረፈ

አሁን ታሪኩን የምናቀርብላችሁ ሰው ጋዜጠኛ ፤ ደራሲ ፤ ገጣሚ ሀያሲና የዜና አንከር ወይም ስመጥሩ የዜና አቅራቢ ነው፡፡

አንጋፋዎቹ መገናኛ ብዙሀን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በ1970ዎቹና 80ዎቹ ሲታወሱ ዛሬም ድረስ ስሙ በጉልህ ይነሳል። የታሪክ ተመራማሪ፣ የመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ተንታኝ የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ልዩና ተወዳጅ ዘጋቢ ነዉ፡፡ ዜናነህ መኮንን፡፡ ከጋዜጠኛነቱ በተጨማሪ ደራሲ ፣ገጣሚና ሃያሲም ነው። ከግርማ ሞገሱ ጋር ግርማ ሞገስን የሚያላብስ ልብስ ለብሶ በኢትዮጲያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሸቱ ሁለት ላይ “ጤና ይስጥልኝ እንደምን አመሻችሁ ከሰዓቱ ዜና ጋር ዜናነህ መኮንን ነኝ” በማለት እጅ ሲነሳ የብዙዎች ትዝታ ሆኖ አልፏል። በበርካታ የቲቪና የሬድዮ ተከታታዮች ዘንድም የሚወደድ ነው፡፡ የጀርመን ድምጽ (ዶቼ ዌሌ ሬዲዮ) የጣቢያው መክፈቻና መዝጊያ ድምፅ የዚሁ አንጋፋ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ይህ ሰዉ ኑሮውን በእየሩሳሌም ካደረገ ዘመናት ተቆጥረው ነበር።

ውልደትና እድገት

ዜናነህ በ1945 ዓ.ም ጎንደር አዘዞ በምትባል ከተማ ውስጥ መስከረም ወር ላይ አደይ አበባና አዲስ አመቱን ተከትሎ ነበር ወደዚህች ምድር የመጣው።

ውልደቱ አዘዞ ይሁን እንጂ በቤተሰቦቹ የሥራ ፀባይ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የመጣው በልጅነቱ ነበር፡፡ በመቀጠልም ወደ ጂማ ሄዶ “ቆጪ” ሰፊር ይኖሩና ፃዲቁ ዮሀንስ (አሁን የመምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ሆኗል)ይማር ነበር፡፡

ጂማ እስከ ሦስተኛ ክፍል ድረስ ከተማረ በኋላ ወደ ጎንደር በመሄድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ጨርሶ የሁለተኛውንም አጋምሷል። ከዚያም ወደ ድሬዳዋ በመጨረሻም ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ የሙዚቃ ፍቅር ስለነበረው በ60ዎቹ ገደማ ያሬድ ትምህርት ቤት ሙዚቃን ለመማር ገብቶም ነበር። የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱንም የጨረሰው እየሠራ በመማር ነበር።

የጋዜጠኝነት ሕይወት

ዜናነህ፣ በጄኔራል ዊንጌት የሁለተኛው ዙር የፖለቲካ ተማሪ ሳለ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ፓለቲካን የተለማመደው። በዚሁ አጋጣሚ በጣም ተከራካሪና ላመነበት ሟች መሆኑን ያዩ ወዳጆቹ ማስታወቂያ ሚኒስቴር እንዲቀጠር ይገፋፉት ነበር። ከዚያ 1968 ገደማ በሬዲዮ ሪፖርተርነት ተቀጠረ። የመጀመሪያው ንባቡ ‹‹የአብዮት መድረክ›› የሚባል የኢህአፓና የሜኤሶን የግጭት ሁኔታ የሚገልፅ በርካታ አድማጮች የነበሩት መሰናዶ ነበር።
እነ አሳምነው ገብረ ወልድ፣ እነ ዘውዱ ታደሠ፣ እነ መሀመድ እንድሪስ፣ እነ ንጉሴ ተፈራና እነ አብዱ ሙዘይን በኢትዮጲያ ሚዲያ ላይ ትልቅ አበርክቶ ያደረጉና የእኔም ሞዴል የምላቸው ናቸው ሲል በተለያዩ ሚዲያዎች ቃለ- መጠይቅ ሲያደርግ ይደመጣል።

በዋነኛነት ግን ወደ ጋዜጠኝነት ሞያ እንዲገባ አርአያ የሆነው አሳምነው ገብረወልድ እንደሆነ ይናገራል። ሌላዉ ደግሞ ጎንደር ትምህርት ላይ እያለ ሰኞ ሰኞ የጀርመን ራዲዮ ድምፅን አዘውትሮ ያደምጥ ስለነበር ያን ይዞ ሰልፍ ላይ ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቀል ለመላ ተማሪዎቹ ያነብ ነበር። ይህም በኋላ ለነገሰበት የጋዜጠኝነት ሙያ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበረው ይናገራል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አዘጋጅ የነበሩት አቶ ማዕረጉ በዛብህ ግጥሞቹን በጋዜጣ ላይ ያወጡለት አጋጣሚ ጥሩ መነቃቃትና የእችላለሁ መንፈስ እንዲያድርበትም ያደረገው እንደነበር ይናገራል፡፡

አንዳንዴም ስምን መልዐክ ያወጣዋል እንዲሉ ዜናነህ ዜናን ሲያነብ አድማጮቹን የሚያከብር ፤ለማህበረሰቡ ቅርብ የሆኑ ጉዳዮችን አድኖ የሚዘግብ ጎበዝ ጋዜጠኛ ነበር። መንግስትን የሚቃወሙና በመንግስት ያኮረፉ ሰዎች የዜናነህን ዜና አድማጮች ነበሩ፡፡ የዜና አቀራረቡ፣ አከፋፈትና አዘጋጉ ላይ የሚያሳየው ትህትና ዜናነህን አይረሴ አድርገውታል።
የማስታወቂያ ሚኒስተር ዉስጥ ሲቀጠር ዘመኑ ቀይ ሽብርና ነጭ ሽብር ይካሄድ የነበረበት ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ከራዲዮ ወደ ቴሌቪዥን ገብቶ ዜናንና ከየአቅጣጫው የሚባል ፕሮግራም ተሰጠው፡፡ ይህ ወቅት ጥሩ መለማመጃ ሆኖለትም አለፈ። በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ታሪክ ለ7 ዓመታት ያህል እንቁጣጣሽን አንባቢ የነበረውም ይሄው ዜናነህ ነበር። በጊዜው በነበረው ትእዛዝ መሰረት የቲቪ ወይም የሬድዮ አንከሮች እንኳን አደረሳችሁ ማለት አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ ይልቁንም እንኳን ደረሳችሁ ብቻ እንዲሉ ይገደዱ ስለነበር ነው፡፡

ምክንያቱም ያኔ የነበረው የሶሻሊዝም አስተሳሰብ በእግዚአብሄር መኖር ወይም ሀይማኖት ላይ ጥብቅ ተቃውሞ ስለነበረው ነው፡፡ ዜናነህ ግን አልፎ አልፎ አውቆ እንኳን አደረሳችሁ በማለት ተመልካችን ሰላም የሚልበት ጊዜ ነበር፡፡
አንድ ወቅት ጄኔራልን ኮሎኔል ብሎ ዘግቦ በመሪዎች ዘንድ በእኩይ አይን ታይቶ እንደነበር ያታወሳል፡፡ ዜናነህ ዜና ማንበብ ሲጀምር "ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው" ብሎ መጀመሩን ሳይቀር እንዲያቆም የተከለከለበት አጋጣሚም ነበር። ዜናነህ በኃላፊው ተፈርሞ ያልተሰጠውንና እርሱ ያላመነበትን ጉዳይ የማይዘግብ፤ የራሱን ስሜት፣ አመለካከትና አተያይ በፍፁም በሚያነበው ዜና ውስጥ ጨምሮ አድማጭን የማያደናግር ሰው ነበር፡፡

በ1967 ዓ.ም በማስታወቂያ መምሪያ ጋዜጠኝነትን “ሀ” ብሎ የጀመረው ባለ ነጎድጓዳማው ድምፁ አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ ሃሳቡን ያለ ይሉኝታና ፍርሃት በነፃነት መግለፅ መቻል ባህሪው ነው። ይህንንም የማይወዱለት ታዲያ ብዙ ዋጋን አስከፍለውታል።
በደርግ ግዜ ከ1969-1971 ለ2 አመት በሙያው ብቻ የታሰረ ጋዜጠኛ ጥቀሱ ቢባል ዜናነህ ነበር። የኢህአፓ አባል ነህ በሚል የክስ ጭብጥ አስረውት ይህ አላስኬድ ሲላቸው ደግሞ የልዑል መኮንን ልጅ ነው በሚሉ አሉባልታዎች ከከፍተኛ አንድ ማዕከላዊ እስከ ዓለም በቃኝ ድረስ እሥር ቤቶቹን አፈራርቋል፡፡ ከእስሩ ሲፈታ ለሶስት ዓመት ያህል ያለ ኪራይ ከመምሪያው ኃላፊ ጎን ብስራተ ወንጌል ውስጥ ቤት ተሰጥቶት በነፃ እንዲኖር በማድረግ የሞራል ካሣም ተከፍሎት ነበር፡፡

ሁሌም ሽክ እና በሱፍ ግርማ ሞገስን ተላብሶ የሚታየው ዜናነህ ቡና የሚጠጣው እንኳን ቦታዎችን መርጦ ነበር። በተለይ የኢትዮጵያ ሆቴል ቡና ነፍሱ ነች፡፡ ይህ የሚያስቀናቸው ሰዎች ደግሞ ጠላቶቹ ሆኑ፡፡ “ቅናት የሚባለው ነገር የእውነት ደምና አጥንት እንዳለው የተረዳሁት ያኔ ነበር” የሚለው ዜናነህ ከዚህም ተነስቶ ነበር ‹‹ነፃነት›› የሚለውን የመጀመሪያ መጽሀፉን የፃፈው። “ትምህርት ከድል በኋላ” የሚለውን አባባል እና አመለካከት አጥብቆም ይቃወም ነበር፡፡ ይህ ልዩነት አሁንም ድረስ አብሮት ዘልቋል።



አበርክቶ

ዜናነህ፣ በሙያው በትላልቆቹ ዘንድ ትልቅ ከበሬታ ያገኘ ሰው ነው፡፡ አብዬ መንግሥቱ ለማ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሲያስተምሩ “ዜና ዜናነህ አነበበ ሲባል ዘመዳዊ ተሳቢ ነው” እያሉ ስሙን ይጠሩትና ያደንቁትም ነበር፡፡
ዜናነህ “ነፃነት” የተሰኘ በአምስት ዓመቱ የጣሊያን ጦርነት የኢትዮጵያ ጀግኖች የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚዘክር ታሪካዊ ልቦለድና በአዲስ አበባ ህይወት ላይ የሚያጠነጥን የማህበረሰቡን አኗኗር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ “ከጣሪያው ስር” የተሰኘ ልቦለድን ለአንባቢያን እንካችሁ ብሏል። በ1999ዎቹ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ማለት ነው አሜሪካን ሀገር ያሳተመውና ወደ 30 የግጥም ስብስብን የያዘ “በረከተ መርገም”ን የሚሞግት “በረከተ ራዕይ” በሚል ርዕስ የግጥም ሲዲ አውጥቷል፡፡ "የመንገድ ላይ ወግ" ኢትዮጲያን ወደ ኋላ

ከሚጎትቷት ባሀርያት መካከል ቅናት ላይ የተሰራ ትያትርም ፅፏል። ዜናነህ በድርሰቶቹ ሀይማኖታዊ ፖለቲካዊና የፍትህ ጥያቄዎችን ይጠይቃል፡፡ ብዙዎቹ ሥራዎችህ እንጉርጉሮ ይበዛባቸዋል ብለው ሲጠይቁት የኔ ስራዎች የማህበረሰቡ ቅጂዎች ናቸው "ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል" ከሚል ማህበረሰብ ወጥቼ ከዚህ የተለየ ልፅፍ አልችልም ሲልም ይደመጣል።

በ1975 ላይ ቤተሰብ ለመጠየቅ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ተጉዞ ነበርና የተወለደባት አዘዞ መብራት ስላልነበራት በወቅቱ ከነበሩ ሺህ አለቃ መላኩ ተፈራ ጋር ተነጋግሮ መብራትም አስበርቶ ዜናነህ መብራት አስበራልንም ተብሎ ይነገር ነበር። ዓለም በቃኝ በእስር ላይ እያለም ስፖርቱ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴዎች ያደርግ ነበር።



የትዳር ህይወት

ዜናነህ ትዳር የመሠረተው ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ነው። ከወይዘሮ አልማዝ ጥላሁን ጋር ትዳር መሰረተ፡፡ ገና ሚስት ሳያገባ ልጆች ብወልድ ስማቸውንም “ቢታንያ (ከሞት መዳን) እና ነፃነት (የመፀሀፌን ስያሜ) ለልጆቼ እሰጣቸዋለሁ ብሎ ያልም የነበረውን ለልጆቹ ስያሜ አድርጓል፡፡ አሁን ላይ የሦስት ሴት ልጆች አባት ሲሆን የመጀመሪያ ልጁ ቢታንያ 37 አመቷ የታሪክ ምሩቅ ነች፡፡ የ30 ዓመቷ ነጻነት ደግሞ ጎበዝ ተዋናይት ነች። ሶስተኛዋ ከፈረንጅ ሴት የተወለደችው የሩሲያ ዜግነት ያላት “ሩኒያ” ትባላለች፡፡

ከትዳር አጋሩ ጋር ለ5 ዓመት ያህል አብረው ከቆዩ በኋላ በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ትኩሳት ወደ አሜሪካ ሄዳ እንድትኖር አደረገ። ከባለቤቱ ጋርም ርቀት ለያያቸው። በአንድ ሰው ደመወዝ የልጆችን ፍላጎት አሟልቶ ማስተማሩ እየከበደው ሲመጣ ከሀገር መውጣት ግዴታ ሆነበት፡፡ ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ቦታውን ሲቆጣጠረው ወደ እስራኤል ሀገር ሄደ። ልጆቹ ገና የ2 እና የ3 ዓመት ህፃን ሳሉ ነበር እናታቸው ጥላቸው የሄደችው። እነርሱ ዛሬ የደረሱበት እንዲደርሱ ትልቅ ሥራ ነበረበት፡፡

ዜናነህ አሜሪካን ሀገር ፣ጀርመን ከዚያም ወደ ስዊድን፣ ኖርዌይ ተዘዋውሯል፡፡ ኖርዌይ በነበረበት ጊዜም ሊደርሺፕን ተምሯል፡፡ ልጆቹንም በእነዚህ ሀገራት ልኮ ማስተማር ይችል ነበር፡፡ ስብእናቸው ላይ መስራትና በእንክብካቤው ስር እንዲያድጉ በመፈለጉ ነበር በእስራኤል እንዲያድጉ የወደደው።

ዜናነህ፤ ትምህርት ቤቱን ብቻ አምኖ የሚተው አባት ሳይሆን የልጆቹን የቀን ተቀን ህይወት የሚከታተልና ስለ ልጆቹም አብዝቶ የሚጨነቅ አባት ነበር። በጣም አስቸጋሪ የፈተና ግዜንም አሳልፏል። ልጆችን ያለ እናት ብቻውን የማሳደጉ ሀላፊነትም በጫንቃው ላይ አርፏል። ሌላ ማግባት ሳያምረው ልጆቹን በኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር አንፆ ያሳደገ እና የልጅ ልጅ ለማየትም የበቃ ጠንካራ ኢትዮጲያዊ አባትም ነው።

ህይወት ከሃገር ዉጭ

“አንተ ከአገርህ ልትወጣ ትችላለህ። አገር ግን ካንተ ውስጥ አትወጣም! ... እናም ኢትዮጵያ፤ አገሬ ሳልገባ አምላክ አይግደለኝ! “ሲል ይደመጣል፡፡ ዜናነህ መኮንን ከሀገሩ ወጥቶ ወደ እስራኤል ሃገር የተጓዘው በ1984 ዓ.ም አጋማሽ ነበር፡፡

ወደ እስራኤል ሀገር ከሄደ በኋላ ትምህርታዊ የሆኑ ፊልሞችን ዳይሬክት በማድረግ ሰርቷል። ለመጀመሪያ ጊዜ የ24 ሰዓት የግል ሬዲዮ ጣቢያ መስርቶ ይሰራ ነበር። በርካታ ሬዲዮ ጣቢያዎችን በማቋቋምና ወጣቶችን በማሰልጠን ዛሬ ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱ ወጣቶችንም ማፍራት ችሏል።

በኋላም በ1991 አካባቢ ወደ አሜሪካም አቅንቶ ነበር። አሜሪካንም እንዳሰበውና እንደጠበቀው ስላላገኘው 9ወር አካባቢ እንደተቀመጠ ወደ ኖርዌይ ሄዶ በሊደር ሺፕ ተምሮ ተመርቋል። ከዚያ ወደ ልጆቹ ወደ እስራኤል ሀገር ተመልሷል። እስራኤል ሀገርም በርካታ ኮርሶችን ወስዷል።

እስራኤል ሀገር መኖሬ ምርጫ ሳይሆን የፈጣሪ ፍቃድ ነው ብሎ ያምናል። እስራኤል የአለም ማእከል ነችና በየግዜው ህይወት አለ ፤ዜና አለ ፤የፈጣሪን መኖር እንዳረጋግጥ አድርጎኛልና እስራኤል ለእኔ መማሪያ ትምህርት ቤቴ ነች ይላል።

እስራኤል ሀገር ከገባ በኋላ ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ አካዳሚክ የሆኑና የፍልስፍና መፀሃፍትን ማንበቡን የሚያስታውሰው ዜናነህ በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜን ጠብቆ ከልጆቹ ጋር የሚወያይበትና መፀሀፍ ቅዱስን የሚያነብላቸው ቀን እንዳለው ይናገራል፡፡
ዜናነህ በዚህ በ30 ዓመት ጉዞ ውስጥ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በርካታ የራዲዮና የቴሌቪዥን አስተማሪ ፕሮግራሞችን መስራት የቻለ ጠንካራና ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነው።
“ጋዜጠኛ ጡረታ አይወጣም” በሚል ንግግሩ የሚታወቀው ዜናነህበጀርመን ራዲዮ ጣቢያ (ዶቼዌሌ) የመካከለኛው ምስራቅ ዘጋቢ በመሆን ሲያገለግል ነበር ።

ሶስት መንግስታትን በጋዜጠኝነት ህይወት የኖረዉ ዜናነህ አሁን ሀገራችን ያለችበትን ለውጥ ይደግፋል፡፡ ነገር ግን ሀገራችን ኢትዮጵያ እንድታድግ ማህበረሰቡ እንደገና መወለድ አለበት የሚል እምነትም አለው። ወደ ፊት ሀገሩ ትልቅ ተስፋ እንዳላት አድርጎ ያስባል፡፡ በተለያዩ ዘርፎች ትክክለኛነትን የሚያሳዩ ሞዴል የሚሆኑ ባለሙያዎችም እንደሚያስፈልጓት ይናገራል፡፡አሁንም ኑሮውን በእስራኤል አድርጎ በሶሻል ሚዲያ ላይ ድምፅ ላነሳቸው ድምፅ እየሆነም ይገኛል።

የዜናነህ አንዳንድ ትዝታዎች

ዜና ነህ መኮንን እንደሚያስታውሰው ማእከላዊ እስር ቤት ሳለ ደርግ እነ ሃይሌፊዳ ዶ/ር ንግስት አዳነን በህይወት እንደሌሉ እየታወቀ ለምርመራ ስማቸውን ሲጠራ ይገርመው ነበር፡፡ እነ ሀይሌ እና ንግስት ተገድለው ሳለ ነገር ግን ይህ በደርጎች ሳይታወቅ ስማቸው ይጠራ ነበር፡፡

ታዲያ በዚያን ጊዜ ዜናነህ ደርጎች ያሰሩትን አያውቁም እንዴ ?ያለ በት ጊዜ ነበር፡፡
የኢህአፓው ብርሃነ መስቀልም እዛው ማእከላዊ ታስሮ ነበር ትዝ ይለዋል፡፡

ዜናነህ ኩላሊት ባይኖረኝም ለሃገሬ የምሰጣት ልብ አለኝ ይላል፡፡ ይህን ከአንድ ጣቢያ ጋር ባደረገው ቃለመጠየቅ የተናገረው ነው፡፡


አንድ ወቅት ዜናነህ ኖርዌይ ሳለ መፅሀፍ መሸጫ ገብቶ አንዳንድ ኖት ይወስዳል፡፡ ታድያ ኦስሎ መፅሃፍት መሸጫ ገብቶ እያነበበ ማስታወሻ ሲፅፍ ወደ 7 ፖሊሶች ከበቡት፡፡ ምን ወንጀል ሰራሁ ሲል መፅሃፍ እያነበብክ ማስታወሻ መያዝህ ነው አሉት፡፡ እሺ ብሎ ይቅርታ ያደርጉልኛል ሲል አላደረጉለትም፡፡ ዜናነህ ስለዚህ ጉዳይ ሲያስታውስ ‹‹ ከዚህ በፊት የነበረ ማስታወሻ የያዝኩትን ሁሉ ከዚህ መፅሃፍት መደብር አለመሆኑን እየነገርኳቸው ማስታወሻዬን ወረሱት፡፡ ስፍራው የሰላም የኖቤል ሽልማት ከሚሰጥበት ኦስሎ ከተማ ህንፃ ፊት ለፊት ከፓርላማው አጠገብ ነው›› ብሎ ትዝታውን አውግቶናል፡፡

06/11/2024
03/11/2024

የአማራ ፋኖ በወሎ ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ልበ ሙሉው ጀግና ፋኖ በለጠ ሸጋው ያስተላለፈው መልዕክት
ድል ለአማራ ፋኖ💚💛❤

30/10/2024

ሲያትል በአይነቱ ለየት ያለ የመኪና ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ተዘጋጅቷል !!

ያለ ልዩነት በጋራ ለአንድ ህዝብ ለአንድ ዓላማ አደባባዩን እናጥለቀልቀዋለን ✊

ቦታ
November 7 ረፋድ 10:00 AM
መነሻ አገልግል ሬስቶራንት
መድረሻ የስቴቱ መቀመጫ Olimpia 75 ማይል (120 ኪሜ) በግል መኪና(ጥቁር መኪና ይበረታታል) ።
woldesilasie

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ምየደራ-ሸዋ ፋኖ አመራሮች ከአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዉይይት አድርገዋል። ለእንግዶቻችን የጎጃም አበበ ፎጣ ስጦታ በመሪያችን በ...
24/10/2024

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የደራ-ሸዋ ፋኖ አመራሮች ከአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዉይይት አድርገዋል። ለእንግዶቻችን የጎጃም አበበ ፎጣ ስጦታ በመሪያችን በኩል ተበርክቶላቸዋል።

አርበኛ ዘመነ ካሴ በዚሁ ጉዳይ ላይ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፏል!

""ጎጃም አበበ!!"

አቢዮቱ መሳሪያ አንጋች የፖለቲካ አቢዮት ብቻ አይደለም።ማህበራዉና ኢኮኖሚያዊ አቢዮት ጭምር ነው።ከዚህ አኳያ በኪነ ጥበቡ አካባቢ (ቀረርቶና ፉከራ፣ሙዚቃ፣ቲያትር፣ስነ-ስእል፣ስነ ግጥም ወዘተ) ከፍተኛ መነሳሳት ተፈጥሯል።በአለባበስም ረገድ የአቢዮቱ ትውልድ የራሱን መልክና ቀለም እየፈጠረ ነው።
ከዚህ ጋር በተገናኜ መቼና ለምን በዚህ ስም መጠራት እንደተጀመረ ለጊዜው በውል ባይታወቅም (ሰፊ ጥናት ይፈልጋል) በጎጃም አካባቢ በኛ እድሜ ከነጭ ኩታ መሳ ለመሳ ሲለበስ የኖረው እና በትግላችን ውስጥ ደግሞ ከትከሻችን ሳይጠፋ እንደ መለዮ የምንለብሰው ፎጣ
"ጎጃም አዘነ" ከዛሬ ጀምሮ "ጎጃም አበበ" ተብሎ የሚጠራ ይሆናል።
ማስታወሻነቱም ለደራ አማራ ህዝብ እና ለህልውናቸው ለሚዋዋደቁ የደራ ፋኖዎች ይሆናል።

(የባህል አቢዮቱ ላይ በባህል አልባሳት ዘርፍ እየሰሩ ያሉ እህቶቻች ከአመት በፊት "ጎጃም አበበ" የሚለውን ስያሜ መጠቀማቸውን አስታውሳለሁ።

አንድ አማራ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!

{ከፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም}
|አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ!|"
{ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም}

ይሄ አጀንዳ ያላደረገ የአማራ አክቲቪስትና ለአማራ እቆረቆራለሁ የሚል ምን አጀንዳ ሊያደርግ ነው።የአማራ ፋኖ በጋራ "ዘመቻ አስበራ መሐመድ" በማወጅ ደሟ ሊመለስ ይገባል!ይህ ጥቃት የሁሉም የ...
15/10/2024

ይሄ አጀንዳ ያላደረገ የአማራ አክቲቪስትና ለአማራ እቆረቆራለሁ የሚል ምን አጀንዳ ሊያደርግ ነው።

የአማራ ፋኖ በጋራ "ዘመቻ አስበራ መሐመድ" በማወጅ ደሟ ሊመለስ ይገባል!

ይህ ጥቃት የሁሉም የአማራ እናቶች ጥቃት ነው!
ይህ ጥቃት የሁሉም አማራ እህቶቻችን ጥቃት ነው!
ይህ ምስል አደባባይ ላይ ያልወጡ የአህቶቻችንና የእናቶቻችን የጥቃት ምስል ማሳያ ነው!

ስለሆነም የአማራ ፋኖ በጋራ "ዘመቻ አስበራ መሐመድ" በማወጅ ደሟ ሊመለስ ይገባል!

13/10/2024

የምንፋለምበት ምክንያት

ወዲ በሻሻ ድንገተኛ ተቅማት እያሯሯጠው ይገኛል
10/10/2024

ወዲ በሻሻ ድንገተኛ ተቅማት እያሯሯጠው ይገኛል

10/10/2024

አርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት አለው

26/09/2024
24/09/2024

አስቸኳይ ጉዳይ
''''''''''''''''''''''''''''''''''::::::
ለአንድ አመት ያህክል በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በታገዘ አፈናና ጭፍጨፋ የአማራን ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ማስቆም ያልቻለው የአብይ አህመድ አረመኔያዊ አገዛዝ አዲስ የአፈና መንገድ ቀይሷል።
ባህርዳርን ጨምሮ ትላልቅ ከተሞች ላይ የሚሰሩ የክልሉን ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት ከከተማ የፀጥታ ስራ በማስወጣት በፌደራል ፖሊስ ስም ለዚህ ተልዕኮ በተዘጋጀ አፋኝ ቡድን እንዲተኩ መመሪያ አውርዷል።
ይህ ትዛዝ ከዛሬ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ባህርዳር ብቻ 200 ያህክል የዚህ አፋኝ ቡድን አባላት ገብተዋል። ይህ ዘራፊ ቡድን ዜጎችንን እና ንፁሃንን የሚያጉርባቸው የግዞት ማዕከላትም ተሰናድተዋል። የክልሉ ፖሊስ አመራር እና አባላትም የአፈናው ሰለባ ናቸው።
የአማራ ወጣት ንቃ በየቤትህ እየታነቅህ ለክብረ ነክ ሞት ከምትዳረግ ጠላትህን በልተኸው ተቀደስ!
እናሸንፋለን!

አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ  ዘመቻ መምሪያ አዛዥ የሆነው አርበኛ ደረጀ በላይ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲል ሁለት ልጆቹን ሰጥቶል:: ትግሉ ምን ያክል መራራ ፅናት እንደሚጠይቅ አርበኛ ደረጀ ምሳ...
20/09/2024

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ ዘመቻ መምሪያ አዛዥ የሆነው አርበኛ ደረጀ በላይ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲል ሁለት ልጆቹን ሰጥቶል:: ትግሉ ምን ያክል መራራ ፅናት እንደሚጠይቅ አርበኛ ደረጀ ምሳሌ ነው::

በዚህ አንድያ ነፍስ በሚገበርበት ተጋድሎ ፖለቲካዊ ሸፍጥና ገንዝብ የምትነግዱ ጥቁር አማራዎች ሆይ ይብቃችሁ::

ተፍሎ የማያልቅ ዕዳ አለብን!

Address

Newport

Telephone

07447298788

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian:

Videos

Share


Other News & Media Websites in Newport

Show All