Selom Media

Selom Media Selom Media is a Digital News Channel founded and owned by Fekadu Alemu that reports, analyses, & fact-checks professionally. "የባለሙያዎችማዕከል"

Welcome to Selom Media, a digital News channel owned by Fekadu Alemu that reports, analyses, and fact-checks to improve the quality, transparency, and credibility of news reporting on Ethiopia about everything. We are particularly concerned with the humanitarian crisis caused by political unrest, economic crisis, ethnic conflicts, and elections in Ethiopia and around the world. We also monitor, an

alyze, and comment on the professional practice of Ethiopian journalism, with a focus on news stories broadcast both locally and internationally. Strong Journalism, Great Ethiopia!

የጋዜጠኝነት ሙያ ውግንና ለሕዝብ እንዲሆን ሙያዊ አተገባበሩ እንዲሻሻል የበኩላችንን እንወጣለን፡፡

"Kal Be Kalu Tenagerat," a widely beloved old Amharic Mezmur from the Marigeta Tsehay hymns, has been beautifully transl...
12/08/2024

"Kal Be Kalu Tenagerat," a widely beloved old Amharic Mezmur from the Marigeta Tsehay hymns, has been beautifully translated into English and sung by Deacon Yonatan Dawit.

This production is truly remarkable. Recently, we've seen a growing trend of Amharic Mezmurs being translated into English by youth Orthodox groups in the United States.

The English version, titled “The Word Spoke to Her,” is an Orthodox Tewahedo hymn performed by Deacon Yonatan Dawit and released by Ahadu Studios.

It’s a beautiful piece! Don’t miss out—listen by clicking the link below.

ሩዋንዳ 300 ሚሊየን ዶላር እንደማትመልስ ፍንጭ ሰጠች ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ሐምሌ 03፣ 2016 ዓ.ም/July 10, 2024ዐዲሱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀገሬ ከሩዋዳ ጋር ያደረገችው...
10/07/2024

ሩዋንዳ 300 ሚሊየን ዶላር እንደማትመልስ ፍንጭ ሰጠች

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ሐምሌ 03፣ 2016 ዓ.ም/July 10, 2024

ዐዲሱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀገሬ ከሩዋዳ ጋር ያደረገችውን ስምምነት ውድቅ አድርጌዋለሁ ካሉ በኋላ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ እንግሊዝ የተከፈለችው ገንዘብ የሩዋንዳ መንግሥት እንደማይመልስ አስታወቀ፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ቃለ አቀባይ ሙኩራሊንዳ እንዳሉት በስምምነቱ መሠረት ገንዘብ ስለማስመለስ የሚያትት ምንም ዓይነት አንቀጽ የለም፤ ይህ ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው ስለዚህ የሚመለስ ገንዘብ አይኖሩም ሲሉ ማክሰኞ እለት ለሩዋንዳ የዜና ወኪል ተናግረዋል፡፡

የብሪታንያ መንግስት በዚህ አመት በሚያዝያ ወር ባሳተመው መረጃ መሰረት የሩዋንዳ መንግስት እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ ከዩናይትድ ኪንግደም ያገቸው ገንዘብ መጠን (240 ሚሊዮን ፓውንድ) ሲሆን ወደ 307 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ይታወቃል።

በመጨረሻም ቃለ አቀባዪ ሁለቱም ወገኖች ተፈራርመዋል፣ ዓለም አቀፍ ስምምነት ሆነ፣ እሱን መተግበር እንጀምራለን፣ ከዚያ በኋላ እርስዎ መውጣት ይፈልጋሉ… መልካም እድል፣” ብለዋል ሙኩራሊንዳ።
--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

እንዴት ከረማችሁ?በኹለቱ ክልሎች የቀጠለው ጦርነት፣ ግድያ፣ ጠለፋ፣ አፈና እና ሰብአዊ መብት ረገጣ ለሕገ ወጦች የልብ ልብ እንዲሰማቸው፣ በሀገሪቱ ደግሞ የሕግ የበላይነት እንዲዳከም እያደረገ...
08/07/2024

እንዴት ከረማችሁ?

በኹለቱ ክልሎች የቀጠለው ጦርነት፣ ግድያ፣ ጠለፋ፣ አፈና እና ሰብአዊ መብት ረገጣ ለሕገ ወጦች የልብ ልብ እንዲሰማቸው፣ በሀገሪቱ ደግሞ የሕግ የበላይነት እንዲዳከም እያደረገ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሳደር ገለጹ፡፡

--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

"እኛ የሃይማኖት አባቶችም አልጫ የሆነውን የዘመናችንን ትውልድ በትጋት አስተምረን በቆራጥነት ገሥጸንና መክረን ወደ እግዚአብሔር ካልመለስነው ከቁጣው አንድንም፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንዳስተማረን ...
03/03/2024

"እኛ የሃይማኖት አባቶችም አልጫ የሆነውን የዘመናችንን ትውልድ በትጋት አስተምረን በቆራጥነት ገሥጸንና መክረን ወደ እግዚአብሔር ካልመለስነው ከቁጣው አንድንም፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንዳስተማረን አስተምረነው የማይመለስ ከሆነ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል። እኛ ባለማስተማራችን የሚጎዳ ትውልድ ካለ ግን እኛ የደሙ ተጠያቂዎች መሆናችንን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጾአልና ነው። የኛ ኃላፊነት እስከዚህ ድረስ ከባድ መሆኑን ባንዘነጋውም እንደዓለሙ በልዩ ልዩ ደካማ አስተሳሰቦችና ተግባራት እየተሰናከልን መሆናችን የአደባባይ ምሥጢር ከሆነ ውሉ አድሮአል፡፡

ዓለም ሲሳሳት ከመገሠጽ ይልቅ አብሮ ማጨብጨብ ተለማምደናል። ባናጨበጭብም ዝምታን መርጠናል። ነገር ግን ኃላፊነቱን የተረከብነው ጥፋት ሲፈጸም ዝም ብሎ ለማየት አልነበረም። ከዓለሙ ጋር አብሮ ለማጨብጨብ ወይም አድማቂ ለመሆንም አልነበረም፡፡ ከቅዱስ ወንጌሉ መሠረተ ሐሳብ ፍንክች ሳንል የእውነት፣ የፍትሕ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የዕርቅ፣ የይቅርታ፣ የአንድነትና የስምምነት ጠበቃ መሆናችንን ማሳየት ነበረብን፡፡ ሰውን ሁሉ በእኩልነት በመቀበልና የሁሉም እኩል አባቶች መሆናችንን በተግባር ማስመስከር ይገባን ነበር። የተዛባውን በማረም ትውልዱን ለማዳን ያደረግነው ጥረት የሚያረካ እንዳልሆነ ታዛቢው ሁሉ አይቶብናል፡፡ ያም በመሆኑ ሁኔታው እኛንም ቤተ ክርስቲያንንም ለፈተና ለመዳረግ እየዳዳ ነው። በመሆኑም በዚህ ክሥተት የእግዚብሔር ቁጣ የለበትም ለማለት አንደፍርም። በዓለሙ ብልሹ አሰራርም ተሳታፊ ከመሆን አላመለጥንም፡፡ ክሱን፣ አቤቱታውን፣ ሰውን ከሥራ እያፈናቀሉ ፍትሕ ማዛባቱን፣ በደምብ ተለማምደነዋል። ደመወዛችሁ ይብቃችሁ የሚለውን አምላካዊ መርሕ ዘንግተን የዚህ ዓለም ንዋይ እያሸነፈን ነው። ግን ዓለምን ልናሸንፍ እንጂ በዓለም ልንሸነፍ አልተጠራንም።

በዚህ ምክንያት የብዙ ምእመናን ልብ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ምክንያት እንዳንሆን መጠንቀቅ ይገባናል። በዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ቁጣ በእኛና በሕዝባችን በሀገራችንና በዓለማችን እንዳይገለጥ እነሆ አሁንም ቃሉ ተመለሱ እያለ ነውና እንመለስ። እየተዛባ ያለው ሁሉ መስተካከል ይችላል። በሃይማኖት የማይቻል ነገር እንዳለ የሚያስብ ካለ ሃይማኖት የሌለው እሱ ነው።"

በዓለ ሢመቱ ለአባ ማትያስ ቀዳማዊ፤
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) በተከሰሰባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባለሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ የካቲት 14፣ 2016 ዓ.ም/Feb 22, 2024የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1...
22/02/2024

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) በተከሰሰባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባለ

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ የካቲት 14፣ 2016 ዓ.ም/Feb 22, 2024

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ መንግሥታዊና በሕገ መንግሥት ሥርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት፣ ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም በቅጽል ስሙ ልጅ ያሬድ በተከሰሰባቸው የወንጀል ክስ የጥፋተኛነት ብይን ሰጥቷል ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በኮሜዲያን ያሬድ በልጅ ያሬድ ያቀረበው ሦስቱም ክሶች ተጠቃለው በአዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7 መሰረት እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል። በዚህ መሠረት በሦስቱም ክስ በአንድ እንዲጠቃለል የታዘዘው የወንጀል ድርጊቱ በሀሳብ፣ በጊዜና በቦታ ተመሳሳይ መሆኑን በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡

ከቀረቡበት ክሶች መካከል በኮምፒዩተር የሚፈጸም ወንጀል ድንጋጌን መተላለፍ፣ የቤተክርስቲያንና የሰዎችን ክብርና መልካም ስም ማጉደፍ እንዲሁም የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት የሚሉ ተደራራቢ ክሶች ይገኙበታል።
ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም የቀረበበት ክስ እንዲሻሻል የክስ መቃወሚያውን በጽሁፍ ያቀረበ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ሊሻሻል የሚችልበት የህግ አግባብ እንደሌለ ተጠቅሶ መልስ ተሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል። ከዚህም በኋላ ተከሳሹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን በመጥቀስ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃውን አቅርቧል።

ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረባቸውን የሰው መከላከያ ማስረጃዎችን ቃል አዳምጧል። ተከሳሹ የሰው የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻሉ እና በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በፍርድ ቤቱ በመረጋገጡ በዛሬው ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ለየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕምነት ተከታይ ምዕመናንን እና የማህበረሰቡን ክብርና ስነ-ልቦናን ከግምት ውስጥ በማስገባት የክሱ ዝርዝር ጉዳይ በሚዲያ እንዳይሰራጭ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ መቆጠቡን ፋና ብሮድካስቲንግ አስግንዝቧል፡፡

--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ በድሮን ጥቃት ከ30 በላይ ንጽሓን ሰዎች ተገደሉ ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ የካቲት 13፣ 2016/Feb 21, 2024በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃ እና ወደራ ወረዳ...
21/02/2024

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ በድሮን ጥቃት ከ30 በላይ ንጽሓን ሰዎች ተገደሉ

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ የካቲት 13፣ 2016/Feb 21, 2024

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃ እና ወደራ ወረዳ ሰኞ የካቲት 11/2016 ዓ.ም በአንድ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ሲጓዙ በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ከ30 በላይ ንጽሓን ሰዎች መገደላቸውን ቢበሲ አማርኛ የዐይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

የሞጃ እና ደራ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ሰላ ድንጋይ ወጣ ብላ በምትገኘው ሳሲት የተባለች አነስተኛ ከተማ የተነሣው ይህ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋውና መውረጃ ልዩ ስሙ ፈላ መገንጠያ አካባቢ ጥቃቱ እንደተፈጸመበት ዐራት የዓይን እማኞች መስክረዋል።

ቢቢሲ አማርኛ እንደዘገበው ከሆነ፣ ስማቸው ለደኅንነታቸው ሲባል እንዳይጠቀስ የጠየቁ ምንጮች በተሽከርካሪው ውስጥ ከ50 በላይ ተጓዦች እንደነበሩ ግምታውን ተናግረዋል፡፡ ጥቃቱ ከረፋዱ 5፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ እንደደረሰ የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ክስተቱን “እልቂት” ብለውታል፡፡

በወቅቱ የአይሱዙ ተሽከርካሪ ተሳፋሪዎችን እያወረደ እያለ ጥቃቱ እንደተፈጸመ የገለጸው ሌላኛው የዓይን እማኝ እንዳለው፣ 16 (አሥራ ስድስት) ቤተሰቦቹን በዚህ ጥቃት እንዳጣ የተናረ ሲሆን ለክርስትና የወጡ 16 የቅርብ ዘመዶቻቸው መገደላቸውን ገልጸዋል።

“እኔ የማውቃቸው ብቻ የእኔ ቤተሰቦች የሆኑ የአባቴ ወገኖች እና የእናቴ ወገኖች ከ16 ሰው በላይ ሰዎች አልቀዋል... ” ሲሉ የሟቾችን ቁጥር “30 ይደርሳል” ብለዋል።

በተጨማሪም ከሟቾቹ ውስጥ አክስታቸው እና አጎታቸው ያጡት አንድ እማኝ የአካባቢው ነዋሪ በጥቃቱ “ሙሉ ቤተሰቦቼ” አልቀዋል ሲሉ መስክረዋል።

በእጅጉ የሚገርመው በአያቱ እቅፍ ውስጥ የነበረው “ክርስትና የተነሣው ሕፃን” ጉዳት ሳይደርስበት በሕይወት መትረፉንም የአካባቢው ሰዎችን ተናግረዋል።
--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልክቶ እየተደረጉ ያሉ ኹለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን ቤተ ክርስቲያን እንደማትቀበለው አሳሰበች  ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ...
13/02/2024

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልክቶ እየተደረጉ ያሉ ኹለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን ቤተ ክርስቲያን እንደማትቀበለው አሳሰበች

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ የካቲት 05፣ 2016/Feb 13, 2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሶኖዶስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልክቶ እየተደረጉ ያሉ ኹለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን ቤተ ክርስቲያን እንደማትቀበለው የካቲት 04፣ 2016 ዓ.ም አሳሰበች፡፡

++++++++++++++++++++
“ወለእመቦ ዘሰከበ ምስለ ተባዕት ከመ አንስት ርኵሰ ገብሩ ክልኤሆሙ …ወጊጉያን እሙንቱ፤ ማንኛውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ኹለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል። ደማቸውም በላያቸው ነው "(ዘሌ.፳ ፥፲፫)

ግብረ ሰዶምን እና ተያያዥ የጾታ ሥርዐትን የሚበርዙ፣ ጾታን መቀየር፣ ኹለት ዐይነት ጾታን መጠቀምና የመሳሰሉት ተግባራት በሙሉ ሀገራችን በሃይማኖት፣ በሕግ፣ በማኅበራዊ ዕሴቶቿ፣ በሥነ ምግባር መመሪያዎቿ የማትቀበላቸው ጉዳዮችና ልምምዶች ስለኾኑ በማናቸውም ይፋዊ ግንኙነቶች እንደማንቀበላቸው በግልጽ እንዲቀመጡ ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ግብረ ሰዶማዊነት በሕገ ተፈጥሮም ኾነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ዓለምን በልዩ ጥበብ በፈጠረ አምላክ ፈቃድ መለኮታዊ ሥርዐቱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሯዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትንና ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚያናጋ የረከሰ ተግባር ነው፡፡
ግብረ ሰዶማዊነት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተገለጸው ለአንድ ሀገርና ሕዝብ ከነጎረቤቶቹ መጥፋት ምክንያት የኾነ ተግባር ሲኾን የሰዶምና ገሞራ በመቅሰፍተ እሳት መቃጠል ከእነርሱ መቀጣትም አልፎ ላለውና ለመጪው ትውልድ አስተማሪ የኾነ ምልክት እንዲኾን ነው ሏል ቋሚ ሲኖዶሱ በመግለጫው።

በመኾኑም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይኽን ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ወደ ንሥሓና ድኅነት እንዲመጡ፣ ከሥጋና ከመንፈስ ስብራት እንዲፈወሱ ዘወትር ጥሪ ታደርጋለች እንጂ ማንም ሰው የኃጢአቱ ወይም የርኩሰቱ ተባባሪ እንደማትሆን ቤተ ክርስቲኗ አሳስባለች፡፡

በ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. በወጣው የሀገራችን የወንጀል ሕግ አንቀጽ ፮ ጠቅላላ ድንጋጌ ክፍል ፪ 'ግብረ ሰዶምና ለንጽሕና ክብር ተቃራኒ የኾኑ ሌሎች ድርጊቶች' በሚለው ንዑስ አንቀጽ ርእስ ሥር ይኽ ድርጊት ወንጀል ስለኾነ በትክክል የሚያስቀጣ መኾኑን አስቀምጧል። በተለይ አንቀጽ ፮ ቁጥር ፴፩ ዕድሜያቸው ፲፰ ዓመት ያልሞላቸው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ላይ ለሚፈጸም ግብረ ሰዶማዊነት ከ፲፭ እስከ ፳፭ ዓመታት የሚያስቀጣ መኾኑ በግልጽ ተጽፏል። በተሻሻለውም የሀገራችን የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ ፲፫ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ የተከለከለ መኾኑን መግለጫው ሕግ ጠቅሶ አስረድቷል፡፡

ይኹን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲኽ ይኽን ተግባር በግልጥ በሕገ መንግሥታቸውና በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ድንጋጌዎቻቸው እንደ ጥሩ ነገር እንደ ፍትሐዊነትና አካታችነት በመቁጠር በይፋ የደነገጉ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት መኖራቸው ግልጽ ነው።

እነዚኹ ሀገራት ያላቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም መከታ በማድረግ በእምነታቸው፣ በባሕላቸው በማኅበራዊ መገለጫቸው ይኽን አጸያፊ ድርጊት ፈጽመው በማይቀበሉ የአፍሪካና የምሥራቁ ዓለም ሀገራት ላይ ቢቻል በማግባባት፣ ካልኾነም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር እንዲቀበሉ፣ የጥፋት ልማዳቸውን እንዲጋሩ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉትን ድብቅና ግልጽ እንቅስቃሴዎች ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ ይቃወማል፡፡
ይኽ ግብረ ርኩሰት በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው የሚደረጉ ኹለገብ ማግባባቶች፣ ተጽእኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በሀገራችን መንግሥት ተቀባይነት አግኝተው እንዳይፈጸሙ ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ አሳስቧል።

ከመገናኛ ብዙኃንና ከሌሎችም የመረጃ ምንጮች ለማወቅ እንደተቻለው ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት የንግድ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የፍትሕና የሰብዓዊነት ግንኙነቶች አካል በማድረግ በቃላትና በዐረፍተ ነገሮች ውስጥ አስርጎ በማስገባት አሣሪ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ ያለው ኺደት በአፋጣኝ እንዲፈተሽ የሀገራችን መንግሥት ብሎም የአፍሪካ መንግሥታት የአኅጉራችንን ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴቶች አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ቋሚ ሲኖዶስ ጥብቅ የኾነ የአደራ ጥሪውን ለኹሉም ገልጻል፡፡

በስምምነቱ ሰነድ ጤናማ መስለው የሠረጹ ዐረፍተ ነገሮች ውስጥ እንደታየው በጾታና ሥርዐተ ጾታ መብት፣ የሥርዐተ ጾታ ትምህርት ጋር በማያያዝ ጾታን በቀዶ ጥገና የመቀየር፣ ውርጃ፣ ልቅ የኾነ የተመሳሳይና ተቃራኒ ጾታ ግንኙነትን መፍቀድ፣ ግለሰቦችን እና ማኅበረሰብን መረን በማድረግ ውስብስብ ለኾኑ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ባሕላዊ ችግሮች የሚዳርጉ መኾናቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ያምናል።

በመኾኑም በብዙ መስዋዕትነት ተጠብቆ የቆየው እምነት፣ የባሕልና የሥነ ምግባር ማኅበራዊ ዕሴት የክብር ሥፍራውን ይዞ እንዲቀጥልና በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ኃጢአትንና ርኩሰትን አባብሎ በማሥረጽ፣ ለዚኽ አጸያፊ ድርጊት ትውልዱ እንዳይጋለጥ የሚመለከተው ኹሉ በልዩ ጥንቃቄ እንዲመለከተው ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ግብረ ሰዶማዊነት በማንኛውም የቃላት አግባብ ተገልጦ በጾታ መብት መካተት የማይችል የመደበኛ ተፈጥሯዊ ክስተት ጋር በጭራሽ አቻ የማይኾን በመኾኑና ተግባሩንም መቃወም ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ተልእኮዋ ስለኾነ ይኽን አስመልክተው የሚደረጉ ስምምነቶች የሀገራችንን ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴት የሚጥሱ መኾኑ ታውቆ ኹሉም ዜጎች እንዲቃወሙት፣ የፈዴራል መንግሥትም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለው ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

ግብረ ሰዶምን እና ተያያዥ የጾታ ሥርዐትን የሚበርዙ፣ ጾታን መቀየር፣ ኹለት ዐይነት ጾታን መጠቀምና የመሳሰሉት ተግባራት በሙሉ ሀገራችን በሃይማኖት፣ በሕግ፣ በማኅበራዊ ዕሴቶቿ፣ በሥነ ምግባር መመሪያዎቿ የማትቀበላቸው ጉዳዮችና ልምምዶች ስለኾኑ በማናቸውም ይፋዊ ግንኙነቶች እንደማንቀበላቸው በግልጽ እንዲቀመጡ ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስም 'ግብረ ሰዶማውያን የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም' በማለት የግብሩን አስከፊነት፣ በማኅበረ ሰብእ ላይም የሚያመጣውን ጥፋት በአጽንዖት ይነግረናል። (ሮሜ ፩÷፳፮፤ ፩ኛ ቆሮንቶስ ፮÷፱-፲)
ይኽንንም ግብረ ርኩሰት ቅዱሳት መጻሕፍት በተለያየ ሥያሜ ጠርተውታል፤ ከእነዚኽም መኻከል፡- ርኩሰት፣ ጸያፍ፣ ትልቅ ኃጢአት፣ በደልና አመጻ የሚሉት ቃላት ይገኙበታል፡፡ (ዘሌ ፲፰÷፳)
የኃጢአተኛውን ሞት የማይሻው እግዚአብሔር ሌሎች ሕዝቦች በሚበድሉበት ጊዜ በሰዶምና በገሞራ የደረሰውን ጥፋት እየጠቀሰ ከጥፋታቸው እንዲመለሱ ማስጠንቀቁን በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል፡፡(ኢሳ. ፫÷፱፣ ኤር. ፶÷፵፣ ሰቆ. ኤር. ፬÷፮፣ ሕዝ. ፲፮÷፵፱፣ አሞ. ፬÷፲፩፣ ማቴ. ፲÷፲፭፣ ፪ኛ ጴጥ. ፪÷፮)
በመኾኑም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማንኛውም በጾታ ተፈጥሯዊ ስጦታ ላይ የሚሠራ ኃጢአት ሕገ ተፈጥሮን የሚጻረር ጽኑዕ በደል እንደኾነ ታስተምራለች። የያዕቆብ ወንድም ይሁዳም “እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ኾነዋል” በማለት ይኽ ተግባር የተወገዘና በዘለዓለም እሳት የሚያስቀጣ መኾኑን አስረግጦ ይናገራል።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ግብረ ሰዶማዊነትን የምትቃወመው ተፈጥሯዊ ስላልኾነ ብቻ ሳይኾን በብሉይ ኪዳንም ኾነ በሐዲስ ኪዳን ትምህርት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ፣ ተቀባይነት የሌለው፣ ኃጢአት በመኾኑ ነው።
ጌታችንም ሲያስተምር “ፈጣሪ በመዠመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው" በማለት ጾታ የፈጣሪ ስጦታ መኾኑን እና ይኽንንም መጠበቅ ግዴታ እንደኾነ ያስረዳል። (ማቴ. ፲፱÷፲፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ግብረ ሰዶማዊነት አጸያፊ ድርጊት መኾኑን
“እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲኹም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው ሴቶችን መገናኘት ትተው ርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ፤ የሚገባውን እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው" በማለት ገልጾታል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ጾታዊ ግንኙነት ወይም የተቀደሰ ጋብቻ በተቃራኒ ጾታዎች ብቻ የሚፈጸም እንዲኾን የምታስተምረው ከዚኽ የተነሣ ነው። (፩ኛ ቆሮ. ፯÷፪፣ ፩ኛ. ጢሞ. ፩÷፱)
ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ ማንነት የሚንድ፣ መሠረተ እምነትንና ቀኖናን የሚሽር፣ ማኅበራዊ ዕሴት የሚያጠፋ፣ ከሥነ ምግባር መገለጫዎች በአሉታዊ ገጽ የቆመ፣ ሕሊናን የሚያውክ፣ ለትውልድ ጥፋት ለሀገር መውደም ምክንያት የኾነ አጸያፊ ተግባር ነው፡፡

ግልጽ የኾኑ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያዛምቱ፣ ድብቅና ግልጽ የኾኑ እንቅስቃሴዎች የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ በንሥሓ እንዲመለሱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጥብቅ ታሳስባለች።
ለወደፊቱም ማናቸውም የሥርዐተ ትምህርት መማሪያ ሲዘጋጅ፣ ሀገር በቀል ደንቦችና መመሪያዎች ሲወጡ፣ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ስምምነቶች ሲፈጸሙ፣ በሀገሪቱ ያሉ የእምነትና የባሕል ዕሴቶችን የሕግ ማዕቀፎችንና የሥነ ምግባር መርሆዎችን ተጠብቀው እንዲፈጸሙ፣ መላው ሕዝባችንም የእምነት መሠረቱን፣ የቀኖና ሥርዐቱን፣ ማኅበራዊ ዕሴቱን ጠብቆ እንዲኖር፣ ሀገራችን ሰላም እንድትኾን ኹላችንም ከወትሮው በተለየ ኹኔታ በጸሎት እንድንተጋ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ
የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ.ም.
+++++++++++++++++++++++
--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

ኢሰመኮ በአማራ ክልል አሳሳቢነቱ የቀጠለው የትጥቅ ግጭት እና በሲቪል ሰዎች ላይ ከሕግ ውጭ እየተፈጸሙ ያሉ ግድያዎች (Extra-judicial killings) እጅግ አሳሳቢ ነው አለሴሎም ሚዲ...
13/02/2024

ኢሰመኮ በአማራ ክልል አሳሳቢነቱ የቀጠለው የትጥቅ ግጭት እና በሲቪል ሰዎች ላይ ከሕግ ውጭ እየተፈጸሙ ያሉ ግድያዎች (Extra-judicial killings) እጅግ አሳሳቢ ነው አለ

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ የካቲት 05፣ 2016/Feb 13, 2024

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በአማራ ክልል ከሐምሌ 2015 ዓ.ም ጀም እየተካሄደ ያለው ጦርነት ምክንያት በንጽሐን ዜጎች ላይ እያስከተለ ያለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተለይ ከሕግ ውጭ ግድያዎች (Extra-judicial killings) እንደቀጠለ ነው ሲል ኢሰመኮ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የትጥቅ ግጭቱ በሰብአዊ መብቶች እና በማኅበራዊ እንቅስቃሴ ላይ እያስከተለ ያለውን ጉዳት/አሉታዊ ተጽእኖ ነዋሪዎችን፣ የዐይን እማኞችን፣ ተጎጂዎችን እና የተጎጂ ቤተሰቦችን እንዲሁም መንግሥትን በማነጋገር ኮሚሽኑ በቅርበት መከታተሉን ቀጥሏል።

በሰሜን ጎጃም ዞን በመራዊ ከተማ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ኃይሎች (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚጠሩት) መካከል ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ውጊያ መካሄዱን ተከትሎ፣ በሲቪል ሰዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት ኢሰመኮ ምርመራ እያከናወነ ቢሆንም፤ ኮሚሽኑ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የጠየቃቸው መረጃዎች እና ምላሽ ገና ያልደረሰ በመሆኑና በጸጥታው ሁኔታና ልዩ ልዩ ተዛማጅ ምክንያቶች ሙሉ መረጃዎች ገና በተሟላ ሁኔታ ማሰባሰብ ባለመቻሉ የምርመራ ሥራው በተሟላ መልኩ ሊጠናቀቅ አልቻለም ብሏል ኢሰመኮ፡፡

ሀኖም ኢሰመኮ እስከ አሁን ድረስ ባደረገው ክትትል ኮሚሽኑ ማንነታቸውን ማረጋገጥ የቻላቸውን ቢያንስ 45 ሲቪል ሰዎችን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች “ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት ከሕግ ውጭ መግደላቸውን፣ እንዲሁም “የፋኖ አባላት ናቸው” በሚል ተጠርጥረው የተያዙ እና ለጊዜው ብዛታቸውን ለማረጋገጥ ያልተቻለ ሰዎች በተመሳሳይ ሁኔታ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡ ኮሚሽኑ ከደረሱት በርካታ ጥቆማዎችና ከልዩ ልዩ መረጃ ምንጮች ከተሰበሰቡት የሲቪል ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ እስከአሁን ድረስ ማንነታቸውን በመለየት ለማረጋገጥ የተቻለው 45 ሲቪል ሰዎችን ብቻ ሲሆን፤ ነገር ግን የጉዳቱ መጠን ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል ምክንያታዊ ግምት ለመውሰድ ተችሏል፡፡

ምስክሮች በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ ለኢሰመኮ ሲገልጹ፣ ለቀን ሥራ በጠዋት ከቤታቸው ወጥተው ድንገት ተኩስ ሲከፈት በአንድ ቦታ ተጠልለው የነበሩ 18 ሲቪል ሰዎች የተገደሉ መሆኑን፣ ቀበሌ 02 አካባቢ በተለምዶ ሚሊኒየም ተብሎ በሚጠራ ሰፈር አንድ የጠፋ አባልን ሲያፈላልጉ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች “በፍለጋው አልተባበሩም” ያሏቸውን 8 ሲቪል ሰዎችን መግደላቸውን እንዲሁም 12 ባጃጆች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መቃጠላቸውን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሸበል በረንታ ወረዳ የዕድውኃ ከተማ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው ከወጡ በኋላ ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ፣ እንዲሁም መንገድ ላይ የተገኙ ቢያንስ 15 ሰዎች (ሴቶችን ጨምሮ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ የተገደሉ መሆኑን፤ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቋሪት ወረዳ፣ ወይበይኝ ቀበሌ፣ አብሥራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ለወታደራዊ ቅኝት በአካባቢው የተሰማሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሳ 6 ሲቪል ሰዎችን ከየቤታቸው አውጥተው ከሕግ ውጭ እንደገደሏቸው ምስክሮች ለኢሰመኮ አስረድተዋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “በዚህ ግጭት በሁሉም ወገኖች በተለይም በየአካባቢው ነዋሪዎችና በሲቪል ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ሥቃይ እጅግ እየጨመረ በመምጣቱ ሁሉም ወገኖች ብቸኛው ዘላቂ መፍትሔ ሰላማዊ ውይይት መሆኑን ተቀብለው በቁርጠኝነት ይተገብሩት ዘንድ፣ እንዲሁም የተሟላ ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥና የተበደሉም እንዲካሱ አሁንም በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን” ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ዘላቂ እልባት ለመስጠት ሰላማዊ መፍትሔ ማፈላለግን ጨምሮ፣ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል የሚያግዙ አፋጣኝ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በተለያየ ጊዜ ባወጣቸው መግለጫዎች ማሳሳቡ ይታወሳል።

--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ፈቃድ ጠየቀችሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 28፣ 2016/Feb 06, 2024የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተ...
06/02/2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ፈቃድ ጠየቀች

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 28፣ 2016/Feb 06, 2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዛሬ ጠዋት ቦሌ አየር ማረፊያ ሲገቡ ወደ ሀገር እንዳይገቡ መከልከላቸው ተገቢ አይደም በማለት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያላቸው ሓላፊነት ከግምት ገብቶ ወደ አገር እንዲመለሱ ፈቀድ ጠየቀች።

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከሀገረ አሜሪካ ሐዋሪያዊ አገልግታቸውን ጨርሰው ዛሬ ጥር 28፣ 2016 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ እንዲቆዩ ኾኗል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኑነት መምሪያ እንዳለው፣ ብፅዕነታቸውን ለመቀበል ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ ከጠዋት ጀምሮ ሲጠብቁ የነበሩ ብፁዓን አባቶች ተመልሰዋል ተብሏል፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሓላፊዎች ያደረጉት ሙከራ እንዳልታሳካ ቤተ ክርስቲያኗ በመግለጫው አስታውቃለች፡፡

--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ ተከለከሉሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 28፣ 2016/Feb 06, 2024ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እ...
06/02/2024

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ ተከለከሉ

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 28፣ 2016/Feb 06, 2024

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።

ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።

ብፁዕነታቸው ወደ ሀገረ ስብከታቸው በሚሄዱበት ወቅት “ኮበለሉ” በሚል ወሬ ሲናፈስ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ “ከመንግሥት በመጣ ትእዛዝ ነው” በሚል እገታ ፈጽሞባቸዋል፡፡

ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው ይገኛሉ ሲል ማኅበረ ቅዱሳን ዘግቧል።

በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ የፌደራል ወታደሮች ከ115 በላይ ንጹሐንን በአሰቃቂ ኹኔታ እንደገደሉ የዐይን እማኞች ተናገሩ #ፋኖን አሳድራችኋል፤ ያስጠቃችሁን እናንተ ናችሁ፤ ፋኖን ትቀልባላችሁ...
02/02/2024

በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ የፌደራል ወታደሮች ከ115 በላይ ንጹሐንን በአሰቃቂ ኹኔታ እንደገደሉ የዐይን እማኞች ተናገሩ

#ፋኖን አሳድራችኋል፤ ያስጠቃችሁን እናንተ ናችሁ፤ ፋኖን ትቀልባላችሁ” እያሉ “እየዛቱ” እንደነበር ነዋሪዎች ጥቃቱ የበቀል ነበር ብለዋል።

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 24፣ 2016/Feb 2, 2024

በአማራ ክልል በፌደራል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት የመንግሥት ወታደሮች ለባህርዳር ቅርብ በሆነችው መርአዊ ከተማ ጥር 20፣ 2015 ዓ.ም ከ115 የሚደርሱ ንጹሐን ዜጎች በአሰቃቂ ኹኔታ እንደተገደሉ የዐይን እማኞች ተናገሩ፡፡

በአማራ ክልል ሴሜን ጎጃም መርዓዊ ከተማ ሰኞ ጥር 20፣ 2016 ዓ.ም በፌደራል ወታደሮች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከተካሄደ ከፍተኛ ጦርነት በዕለቱ በልዩ ልዩ ሠፈሮች በመንገድ ላይ የተገኙ ንጹሐን ዜጎች ብቻ ከ50 በላይ እንደተገደሉ ቤተሰቦቻቸው እና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የዓይን እማኞች ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል፡፡

ዘገባው እንዳለው ከሆነ፣ ከሰዓታት ከባድ ጦርነት በኋላ መከላከያ ከተማዋን ሲቆጣጠር ስታዲየም እና ጤና ጣቢያ በተባሉ ሠፈሮች “ከስድስት ዓመት ሕጻን እስከ 75 ዓመት አዛውንት” ድረስ ግድያ ተፈጽሟል ሲሉ የዓይን እማኞች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የሆስፒታል ምንጮችን እና አምስት ሰዎችን እንዳነገረ የገለጸው የቢቢሲ ዘገባ፣ ለምሳሌ በዕለቱ ሰኞ ጥር 20/2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል “ከባድ ውጊያ” እንደነበር የተናገሩት ነዋሪዎች፣ ከዚያ በኋላ ግን ከ50 እስከ 100 የሚደርሱ ሰዎች እንደ ተረሸኑ ታውቋል።

በመቀጠልም ከረፋድ አምስት ሰዓት አካባቢ የፋኖ ታጣቂዎች መርዓዊ ከተማን ለቅቀው ከወጡ በኋላ ወዲያው “መከላከያ ሠራዊት ቤት ለቤት በመዞር እና መንገድ ላይ ያገኛቸውን ሰዎች መረሸኑን” እና ጥቃቱ እስከ ምሽት አንድ ሰዓት የዘለቀ ነበር ብለዋል የዐይን እማኞች፡፡

በተጨማሪም “አንዱን ልጅ በአምስት ጥይት እዚያው ሰፈራችን ኮብሉ ላይ ገድለው ጣሉት። እነሱን [ወንድማቸውንና ሌሎች ሰዎችን] ደግሞ ሰብስበው አንድ ላይ 13 ሰዎች ወደ አስፓልት ይዘው ወጥተው ገደሏቸው። …ፊታችን ስለገደሏቸው ነው ያመንነው” ያሉ እማኞች እንዲሁ የጅምላ ግድያውን ያዩ እማኖች መስክረዋል፡፡

ኹነቱን አስመልክቶ አንድ የሕክምና ባለሙያ ለቢቢሲ እንደተናገረው ከሆነ፣ አሥራ ሦስት (13) ሰዎች ከአስፓልት ዳር መገደላቸውን እንደሚያውቁ ለቢቢሲ ያረጋገጡ ሲሆን በአጠቃላይ በዕለቱ 85 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

የመንግሥት ሠራተኛ ወንድማቸው የተገደለባቸው ምስክርነታቸውን ሲሰጡ፣ “ታናሽ ወንድሜ ከልጁ እቅፍ ነጥለው ከወሰዱ በኋላ በጭካኔ ረሽነውታል” ብለዋል። ይህ ኹሉ ሲሆን “ፋኖን አሳድራችኋል፤ ያስጠቃችሁን እናንተ ናችሁ፤ ፋኖን ትቀልባላችሁ” እያሉ “እየዛቱ” እንደነበር ነዋሪዎች ጥቃቱ የበቀል ነበር ብለዋል።

በበሕዳር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባሕር ዳር ቢሮ በመርዓዊ ከተማ በንጹሕን ላይ ጥቃት መድረሱን ከተለያዩ ምንጮች መረጃው እንደደረሰው አረጋግጦ በጉዳዩ ላይ ክትትል እና ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለተጨማሪ ዐራት ወራት አራዘመ #“ሾላ በድፍኑ” እንዲሉ አዋጁ የተራዘመው በኹለት ተቃውሞ፣ በሦስት ድምፀ ተዐቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ ተራዝሟል ከማለት ውጭ ስ...
02/02/2024

መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለተጨማሪ ዐራት ወራት አራዘመ

#“ሾላ በድፍኑ” እንዲሉ አዋጁ የተራዘመው በኹለት ተቃውሞ፣ በሦስት ድምፀ ተዐቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ ተራዝሟል ከማለት ውጭ ስለአዋጁ መራዘም በዝርዝር ያነሡት ነገር የለም

#ሌላው ቢቀር የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ለሆኑት እንኳን በቂ መረጃ አልተሰጣቸውም

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 24፣ 2016/Feb 2, 2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በአካሄደው አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ በአማራ ክልል እና በሌሎች አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባለመቆሙ እና የዜጎች ደህንነት አሳሳቢ በመሆኑ ለስድስት ወራት ታውጆ የነበረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ ዐራት ወራት ማራዘሙን አስታወቋል፡፡

አዋጁን በድጋሜ ለምን ማራዘም አስፈለገ ለሚለው ግን በቂ ማብራሪያ አልተሰጠም፡፡ ምክር ቤቱ ምን ዐይነት ውይይትና ክርክር እንዳካሄደ እና የአሳብ ልዩነት ነበረ? ወይስ አልነበረም? በሚሉት ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጠ አካል የለም፡፡

ለመንግሥት ቅርብ የሆኑት መገናኛ ብዙሃን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና ኢቲቪ እንዳሉት ከሆነ፣ ስለአዋጁ መራዘም አስፈላጊነት የውሳኔ ሀሳቡ ረቂቅ በፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ስለመቅረቡ እንጅ መሠረታዊ ምክንያቱ ምን እንደሆነ መረጃውን አላብራሩም፡፡ “ሾላ በድፍኑ” እንዲሉ አዋጁ የተራዘመው በኹለት ተቃውሞ፣ በሦስት ድምፀ ተዐቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ ተራዝሟል ከማለት ውጭ ስለአዋጁ መራዘም በዝርዝር ያነሡት ነገር የለም፡፡

ሆኖም ከዚህ ቀደም ሐምሌ 28፣ 2015 ዓ.ም ምክር ቤቱ ባካሄደው አስቸኳይ ጥሪና ስብሰባ የሕዝቦች ሰላምና ደህንት ለማስጠበቅ ሲባል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1299/2015 በድጋሜ ቁጥር 5/2016 በሚል አራዝሞታል፡፡

ሴሎም ሚዲያ አዋጁ የተራዘመበትን ምክንያት ማብራሪያ ለማግኘት ለኹለት የምክር ቤት አባላት ምላሽ እንዲሰጡ ጥያቄ ቢያቀርብም እነኚኽ የተከበሩ የምክር ቤት አባላት ለድህነታቸው ሲባል መረጃውን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ሴሎም ሚዲያ፣ እንዲህ ዓይነት አገራዊ አዋጅ ሲታወጅ እና ሲራዘም፣ ዜጎች ስለጉዳዩ በቂ ዝርዝር መረጃ እንዲያገኙ ለመገናኛ ብዙሃን አስፈላጊውን መረጃ መስጠት የመንግሥት ትንሹ ግዴታ እንደሆነ ለአንባቢያን መግለጽ ትፈልጋለች፡፡

--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ለነገ ዐርብ ጠራሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 23፣ 2016/Feb 1, 2024የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ለነገ ዐርብ ...
01/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ለነገ ዐርብ ጠራ

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 23፣ 2016/Feb 1, 2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ለነገ ዐርብ ጥር 24፣ 2016 ዓ.ም እንደጠራ ኢትዮ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

በዚህ ልዩ ስብሰባ በዋናነት በአማራ ክልል ከሐምሌ 28፣ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ወራት ታውጆ የነበረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማብቃቱን ተከትሎ ምን አልባት አዋጁ በድጋሜ እንደሚራዘም ምክር ቤቱ እንደሚወያይ ይጠበቃል ሲል ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ከትግራይ ጦርነት ማግስት በአማራ ክልል የተጀመረው ጦርነት የፌደራሉ መንግሥት ክልሉን በኹለት ሳምንት ወደ ሰላም እመልሳሁ በሚል የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጀምሮ ስድስት ወራት ቢቆጠሩም ጦርነቱ ዛሬም አልቆመም፡፡ በወቅቱ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ይልቃል ጌትነት የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ ግባልኝ ባሉት መሠረት መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአማራ ክልል እና እንደ አስፈላጊቱ በመላው አገሪቱ ተፈጻሚ የሚሆን አዋጁ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

ሆኖም በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባለመቆሙ እና በአንዳንድ አካባቢዎች በተለይ በአሮሚያ ክልል ያለው የሰላም እጦት እና አጠቃላይ ሀገራዊ ቀውሱ ተደማምሮ በነገው ዕለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁን ለማራዘም ኹነኛ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

መንግሥት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አደረኩት ያለውን በዝርዝር ይፋ አደረገ #በአንዳንድ አካባቢዎችም ትክክለኛ ተፈናቃዮችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ መደረጉን...
01/02/2024

መንግሥት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አደረኩት ያለውን በዝርዝር ይፋ አደረገ

#በአንዳንድ አካባቢዎችም ትክክለኛ ተፈናቃዮችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ መደረጉን መግለጫው አንሥቷል

#ሌሎች ቀሪ ተግባራትን በተመለከተ በሕወሃት በኩል ማለቅ እንዳለባቸው መንግሥት አሳስቧል

#የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጉዳዩ በዋናንት ከሚመለከታቸው የአማራና የትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ ነበር ተብሏል

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 23፣ 2016/Feb 1, 2024

የፌደራል መንግሥት የፕሪቶርያው ስምምነት መሠረት ያደረጉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ማከናወኑን እና ከ37 ቢሊዮን ብር በላይ ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ድጋፍ ማድረጉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ ከምንም በላይ የፕሪቶርያው ስምምነት ተግባራዊ ምላሽ ይፈልጋል ብሏል መንግሥት በመግለጫው፡፡

ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዙ ወንጀሎችን አስመልክቶ የፌዴራል መንግሥቱ ተገቢውን እርምጃ ወስጃለሁ፡፡ በምን ጉዳይ እነማንን፣ ምን ዓይነት እርምጃ ለሚሉት ጥያቁዎች ግን ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰጠም፡፡

ለትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ለትምሀርት፣ ለመሠረተ ልማት፣ ለጤና እና ለሌሎች ወጪዎች በተመለከተ ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ከ37 ቢልዮን ብር በላይ ለትግራይ ክልል ድጋፍ ማድረጉን የፌዴራል መንግሥት በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል ፡-

የፕሪቶርያው ስምምነት ከምንም በላይ ተግባራዊ ምላሽ ይፈልጋል፡፡
ሕወሐት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲከበር መጠየቁን የፌዴራል መንግሥት በአንክሮ ተመልክቶታል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ዋነኛው መፍትሔ የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን የኢፌድሪ መንግሥት በጽኑ ያምናል።ይሄንንም በተመለከተ የፌዴራሉ መንግሥት ከመነሻው እስካሁን ያለው አቋም ወጥ እና የማይናወጥ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የፕሪቶርያው ከአቋም ባሻገር ተግባራዊ እንቅስቃሴም አድርጓል፤ እያደረገም ይገኛል፡፡

የፌዴራል መንግሥቱ ለሰላም፣ ለፖለቲካዊ መፍትሔና ለትብብር ያለውን አቋም የገለጸው ከፕሪቶርያው ስምምነት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ የመከላከያ ሠራዊቱ ወደ መቀሌ ከተማ እንዳይገባ የተደረገው ለሰላም ዕድል ለመስጠት ነው፡፡

ከስምምነቱ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተመራ የተለያዩ ተቋማት አመራሮች ያሉበትን ቡድን ወደ ትግራይ የላከው የፌዴራል መንግሥት ነው፡፡

የፌዴራል መንግሥት ተቋማትና ክልሎች ለትግራይ ሕዝብ ድጋፋቸውን ያሳዩት ወዲያው ነው፡፡ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በመቀሌ ተገኝተው ለሕዝቡ ያላቸውን አጋርነት በማሳየት የሚቻላቸውን ድጋፍ በዓይነትና በገንዘብ አድርገዋል፡፡

በፕሪቶርያው ስምምነት መሠረት የገዢው ፓርቲ ሊኖረው የሚችለውን ድርሻ በመተው ሕወሐትና የታጣቂ አመራሮች ጊዜያዊ መንግሥቱን እንዲያቋቁሙ አድርጓል፡፡ ምክንያቱም ከልዩ ልዩ አካላት ተውጣጥተው በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ የሚካተቱ አመራሮች እስኪተዋወቁና እስኪግባቡ ድረስ የትግራይ ሕዝብ የችግር ወቅት እንዳይራዘም በማሰብ ነው፡፡

በዚህም ለትግራይ ሕዝብ ሰላም ያለውን ቁርጠኝት ከፕሪቶርያው ስምምነት በላይ በመሄድ አረጋግጧል፡፡

ለትግራይ ሕዝብ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እንዲቻል የባንክ፣ የቴሌኮም፣ የመንገድ፣ የጤና፣ የትምህርትና የርዳታ ሥራዎችን የሚመሩ የሥራ ኃላፊዎች በትግራይ ተገኝተው ከክልሉ ቢሮዎች ጋር እንዲወያዩ የተደረገው የፕሪቶርያ ስምምነት በተፈረመ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ የሥራ ኃላፊዎች በጀትና ባለሞያዎችን በመመደብ በክልሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ አስችለዋል፡፡

በክልሉ ተቋርጦ የነበረውን የትምህርት ሂደት ለማስቀጠል ልዩ ልዩ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ የሰው ኃይልና የተቋም ዐቅም ግንባታ፣ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ሥልጠና፤ የዩኒቨርሲቲዎችን የአመራር ቦርድ የማደራጀት ሥራ ተሠርቷል፡፡ በትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም በኩል 165.8 ሚሊየን ብር በዕቅድ ተካትቶ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ለአንደኛና ለሁለተኛ ሩብ ዓመታት ማስፈጸሚያ 517.9 ሚሊየን ብር በገንዘብ ሚ/ር በኩል ለክልሉ ተልኳል፡፡

በትምህርት ላይ ከሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት 1.46 ቢልየን ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ በ2016/17 በትምህር ቤቶች ላይ ለሚሠሩ ሥራዎች የ111.08 ሚሊየን ብር ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ የትምህርት ተቋማት መልሶ ግንባታ 441.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሚያ ክልል የ5 ሚሊየን፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ደግሞ የ109 ሚልየን ብር የትምህርት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የክልሉን የማዕድናት ልማት ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ ለዘርፉ መሥሪያ ቤት የመገልገያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል፤ የክልሉን የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚያሳይ ኤግዚቢሽን በሚልኒየም አዳራሽ በፌዴራል ወጪ ተከናውኗል፡፡ የሞሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ሥራ ተመልሷል፡፡ በፋብሪካና በባህላዊ መንገድ ወርቅ የሚያመርቱ አካላትን በመደገፍ ሥራ ጀምረዋል፡፡ ለወርቅ ሥራ የሚያገለግሉ ሁለት ከባድ ተሸከርካሪዎች በእርዳታ ተለግሰዋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የክልሉን የዘርፍ መሥሪያ ቤት ለማጠናከር ከተወሰዱ ርምጃዎች ባሻገር ለካፒታል በጀት 4.9 ቢሊየን ብር፤ ለመደበኛ በጀት 11.4 ቢሊየን ብር፣ እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ 400 ሚሊዮን ብር፤ በድምሩ 16.7 ቢሊየን ብር በ2015/16 ለክልሉ ተሰጥቷል፡፡ በክልሉ ለሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በድምሩ 5.1 ቢሊዮን ብር ተላልፎላቸዋል፡፡ በልማት አጋሮች በኩል ደግሞ የ1.7 ቢሊየን ብር ድጋፍ ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

ከእነዚህም በተጨማሪ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በቻናል አንድ 1.7 ቢሊየን እንዲሁም በገንዘብ ሚኒስቴር በክልሉ ባቋቋመው ጽ/ቤት በኩል፣ በትግራይ ለሚከናወኑ የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች እና ለአየር ንብረት ለውጥ ፕሮጀክቶች በድምሩ ከ565 ሚልየን ዶላር በላይ ፈሰስ ተደርጓል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮጀክትም 65 ሚሊሊን ብር ለክልሉ ተላልፏል። የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር እና የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በክልሉ የሚገኙ የዘርፍ መሥሪያ ቤቶችንና ተቋማትን ለማብቃት ሥልጠና ሰጥተዋል፤ ቁሳቁስ አሟልተዋል፤ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ጾታን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች የምላሽ አገልግሎት የሚውል ከ7 ሚሊየን ዶላር በላይ ለክልሉ ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡ የክልሉን ማረሚያ ቤቶች ለመደገፍም የ28 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የከተማና መሠረተ ልማት አገልግሎቶችን ለማጠናከር ሲባል የቢሮ ዕቃዎችና የተሸርካሪዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡ የክልሉ መሠረተ ልማቶችን ለመሥራትና ለመጠገን እንዲችል ከፍተኛ ወጪ የሚያወጡ የግንባታና የጥገና ማሽነሪዎች ተሰጥተውታል፡፡ በጦርነቱ የተጎዱ ድልድዮችን በጊዜያዊነት ለመጠገን እንዲቻል ሁለት ተገጣጣሚ ድልድዮች የተለገሱ ሲሆን አራት ድልድዮችን ለመገንባት ጨረታ ወጥቷል፡፡

በጦርነቱ ወቅት የተቋረጡ የዐቅም ግንባታ ሥልጠናዎችንም በልዩ ፕሮግራም የክልሉ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ለዘጠኝ ከተሞች የፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚውል ከ409 ሚሊየን ብር በላይ እና ከ7 ሚሊየን ዶላር በላይ ለክልሉ ተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርም ለደመወዝና ለሥራ ማስኬጃ እና ለመንገድ ፕሮጀክት ጥገና ከ418.6 ሚሊየን ብር በላይ ወደ ክልሉ ልኳል፡፡ ለትግራይ ገጠር መንገድ ጥገና ከመንገድ ፈንድ ከብር 107 ሚሊየን ብር በላይ፤ የ2026 በጀት ቅድመ ክፍያ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ተልኳል፡፡ በፕላንና ልማት ኮሚሽን በኩል ደግሞ በጠቅላላው የ4.2 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የትግራይ ክልልን የባህልና ስፖርት እንቅስቃሴ ከተቋረጠበት ለማስጀመር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና የሚመለከታቸው የስፖርት ፌዴሬሽኖች ተገቢውን ድጋፍ ከማድረጋቸውም በላይ የተለያዩ የስፖርት እንቅስቃሴዎች በክልሉ እንዲከናወኑ አድርገዋል፡፡ ለክልሉ የስፖርት ክለቦችም የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡

የክልሉን የጤና ዘርፍ ዐቅም ለመገንባት እንዲቻል 164 ልዩ ልዩ ባለሞያዎች ተመድበው ድጋፍ እንዲሰጡ ተደርገዋል፡፡ ሁሉንም በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት በመደገፍ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የተቻለ ሲሆን፣ ሁሉም ሆስፒታሎች ተኝቶ የማከም አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ተችሏል፡፡

ከ830 ሺህ በላይ ሕጻናት የኩፍኝ ክትባት ከማግኘታቸውም ሌላ ከ65 ሺህ በላይ ሕዝብ የኮቪድ ክትባት አግኝቷል፡፡ ከአምቡላንሶች በተጨማሪ ወደ 2 ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፎችም ተከናውነዋል፡፡

በ2015/16፣ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ከ600.2 ሚሊየን ብር በላይ ለትግራይ ክልል የጤና ዘርፍ የገንዘብና የግብአት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ትግራይ በቱሪዝም ሀብት የታወቀ ክልል ነው፡፡ ይሄንን ሀብት መልሶ ወደ ጥቅም ለማዋል እንዲቻል ቱሪስቶችን የማበረታታት ሥራ ተጀምሯል፡፡

አልነጃሺ መስጅድንና የገርዓልታ ገዳምን ለቱሪስቶች የማስከፈት እንቅስቃሴም ተከናውኗል፡፡ የውኃ ሀብትን ለመጠቀምና ውኃን ለሕዝቡ ለማዳረስ እንዲቻል ለዘርፉ ተቋም ልዩ ልዩ ድጋፎች የተደረጉ ሲሆን፣ የክልሉን ቢሮ የማደራጀትና በቁሳቁስ የማሟላት ሥራ ተሠርቷል፡፡ ለተበላሹ የአገልግሎት ሰጪ ሀብቶችም ጥገና ተከናውኗል፡፡
በክልሉ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን መልሶ ወደ ሥራ ለማስገባት በተደረገው ሁለገብ እንቅስቃሴ 217 ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት ተችሏል፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የገበያ ትሥሥር እንዲፈጠር በተለያዩ ባዛሮችና ኤክስፖዎች ላይ የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪዎች እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ የመሠረታዊ ሸቀጦችን ተደራሽነት ለማስፋት መንግሥት በወሰደው ርምጃ የተለያዩ የምግብና የመጠቀሚያ ሸቀጦች ለትግራይ ክልል ቀርበዋል፡፡

የነዳጅ ማደያዎችን እንዲጠገኑ በማድረግ፣ በክልሉ በቂ ነዳጅ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ የትግራይ ክልል ንግድ ፈቃድ ላላቸው 7 ሺህ 240 ነጋዴዎች፣ ከተለመደው አሠራር ወጣ ብሎ ከሐምሌ 1/ 2014 ጀምሮ በአዲስ አበባ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

51.3 ሚሊየን ብር ለዘር ግዥ ወጪ ተደርጓል፡፡ በ2015/16 13.4 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ለክልሉ የቀረበ ሲሆን፣ ለ1427 አርሶ አደሮች መጠቀሚያ የሚሆን 1720 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በዚሁ የምርት ዘመን ፕሮጀክቶች በኩል ለክልሉ ተገዝቶ ሥራ ላይ ውሏል፡፡

በ2015/16 የምርት ዘመን ክልሉ 80 ሺ የተለያዩ ማዳበሪያዎች ጠይቆ ሁሉም ቀርቦለታል፡፡ ለ2016/17 ምርት ዘመን ደግሞ ክልሉ ከጠየቀው መካከል የ70 ሺ ቶን ማዳበሪያ ተገዝቷል፡፡ ለግብርና መገልገያ የሚሆኑ የትራክተሮች፣ የውኃ ፓምፖች ድጋፍ ለአርሶ አደሮች ተለግሷል፡፡ በልማታዊ ሴፍቲኔት በኩል 6.2 ሚሊየን ብር የተላለፈ ሲሆን፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የግብርና ሚኒስቴር ባደረጉት ስምነት መሠረት ደግሞ 700 ሺ ኩንታል እህል ተገዝቶ ለክልሉ ቀርቧል፡፡

ለ55 ወረዳዎች በየወረዳው አንዳንድ መኪናና ሞተር ሳይክል፤ እንዲሁም ኮምፒውተሮችና ፕሪንተሮች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በዘላቂ የመሬት አስተዳደር ፕሮግራም አማካኝነትም 89.2 ሚሊየን ብር ለክልሉ በቁሳቁስ መልክ ተሰጥቷል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ብቻ 11ሺ ኩንታል ምርጥ ዘርና 30 ትራክተሮች ለትግራይ ገበሬዎች ተለግሷል። ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ድጋፍ አድርገዋል።

የዊዝሆልዲንግ ታክሶችን ጨምሮ ብር 3.9 ቢሊየን ብር ወደ ክልሉ ትልልፍ ተደርጓል፡፡ ከክልሉ ግብር ከፋዮች የተሰበሰበ ብር 138.06 ሚሊየን ብር ወደ ክልሉ ሂሳብ ተላልፏል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ ለተጠቀሱትና ለሌሎችም ወጪዎች ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ከ37 ቢልዮን ብር በላይ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ክልል ድጋፍ አድርጓል፡፡ በተመደበው በጀትና ድጋፍ የክልሉ ዕቅድ ተግባራዊ ተደርጎ ለሕዝብ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣም ይጠብቃል፡፡

ተፈናቃዮችን ወደ መደበኛ መኖሪያቸው ለመመለስ እንዲቻል የፌዴራሉ መንግሥት የሚመለከታቸውን አካላት አቀናጅቶ ሥራ ጀምሯል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎችም ትክክለኛ ተፈናቃዮችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ አድርጓል፡፡ የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጉዳዩ በዋናንት ከሚመለከታቸው ከአማራና ከትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ ነበር።
በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት በሕወሐት በኩል ታጥቀው ሲዋጉ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ አለባቸው፡፡ ለዚህም የሚረዳ የተሐድሶ ኮሚሽን የፌዴራሉ መንግሥት አቋቁሟል፡፡ በፌዴራሉ መንግሥት በኩል የሚጠበቅበትን የሰው ኃይልና በጀትም መድቧል፡፡

ከሰሜኑ ጦርነት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን በተመለከተ የፌዴራል መንግሥቱ ተገቢውን ርምጃ በእርሱ በኩል ወስዷል፡፡ ተጠያቂ መሆን ያለባቸውንም ተጠያቂ አድርጓል፡፡

ሌሎች ሥራዎችንም ለማከናወን እንዲቻል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዐዋጅ ረቂቅ ዝግጅት አጠናቋል፡፡ ይህ ሂደት እንዲሳካም እንደ ሌሎቹ ክልሎች ሁሉ የትግራይ ክልልም ተገቢው ሚና እንዲጫወት ይጠበቃል፡፡
ለትግራይ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት ሲባል የፌዴራሉ መንግሥት እነዚህን ተግባራት ከሚገባው ባሻገር ተጉዞ አከናውኗል፡፡ ለክልሉ ሕዝብ መደረግ ያለባቸው ድጋፎችንም በራሱ ዐቅምም ሆነ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለማከናወን የፌዴራሉ መንግሥት ምንጊዜም ዝግጁ ነው፡፡

አሁንም ቢሆን ለትግራይና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት ሲባል የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሚያደርጉ፤ የክልሉን ዕቅዶች ወደ መሬት በሚያወርዱ፤ የክልሉን ሕዝብ ችግሮች በተጨባጭ ለመፍታት በሚያስችሉ ገቢራዊ ነገሮች ላይ ማተኮር አማራጭ የሌለው ነው ብሎ የፌዴራሉ መንግሥት ያምናል፡፡

እነዚህ ነገሮች ተግባራዊ ተደርገው የትግራይ፣ በአጠቃላይም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት እንዲረጋገጥ የፌዴራል መንግሥቱ ያለውን ቆራጥ አቋም በድጋሚ ያረጋግጣል፡፡

የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ለፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት መፈጸም ሙሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ የፌደራል መንግሥቱ ጥሪውን ያቀርባል።

ጥር 23 ቀን 2016 ዓ ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

የአብን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ  ታሠሩሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 23፣ 2016/Feb 1, 2024የአብን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለ...
01/02/2024

የአብን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ታሠሩ

ሴሎም ሚዲያ፣ ሎንደን፣ ጥር 23፣ 2016/Feb 1, 2024

የአብን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ትናንት ማታ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ገዳማ ከመኖሪያ ቤታቸው በመንግሥት የጸጥታ አካላት ተይዘው መታሠራቸውን የቅረብ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ፡፡

እኒህ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት ቢኖራቸውም ዐራት የሚሆኑ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ትናንት ረቡእ ጥር 22፣2016 ዓ.ም የመኖሪያ ቤታቸውን በር በማንኳኳት “ያለምንም ማንገራገር ለሕግ ትፈለጋለህ” በማለት በሌሊት ተይዘው ወደ እሥር መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው አስረድተዋል፡፡

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት ጊዚያት በተለይ ከሰሜኑን ጦርነት በኋላ በአማራ ክልል መንግሥት እየወሰደ ያለውን ሕገ ወጥ ግድያና በማንነት ላይ የተመሠረተ የጅምላ እሥር እንዲቆም፣ መንግሥት አገሪቱን መምራት አልቻም፣ መንግሥት (ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢሕ አሕመድ) ሥልጣን ይልቀቁ እና የመሳሰሉ ጠንካራ ትችቶችን በሕዝብ ተወካዮች ስብሰባ ላይ ሲያነሡ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደ/ር ደሳለኝ ጫኔ በሕዝብ ተወካዮች ስብሰባ ላይ ብዙም ሲሳተፉ አልነበረም። ዛሬ ግን ምክንያቱ በምን እንደሆነ ባይገለጽም ከትናንት ማታ ጀምሮ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ መታሠራቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ከወራት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምክር አባል የኾኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እንዲሁ ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሣ እስካሁን በእሥር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ አቶ ክርስቲያን ታደለ ጠንካራ ሐሳቦችን እና ትችቶችን በሕዝብ ተወካዮች ስብሰባ ላይ በማንሣት ዋና መነጋገሪያ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

አብን እስከዛሬ የኹለቱን አባላት እሥር አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ የለም፡፡
--------------------
Facebook: https://www.facebook.com/selommedia
Twitter: https://twitter.com/MediaSelom
LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/selom-media
Gmail: [email protected]
Website: Under construction

Address

United Kingdom, Regent Streets
London

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Selom Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Selom Media:

Share

Nearby media companies


Other Media/News Companies in London

Show All