09/09/2021
ግብፅ ቅራኔያችንን እንፍታ በሚል ወደ ቱርክ አንካራ አቅንታ ከቱርክ መንግስት ጋር ለመወያየትና ቱርክ በወታደራዊ መስክ ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችውን ትስስር እንድታቋርጥ ድሮኖችንም ለኢትዮጵያ ከመሸጥ እንድትቆጠብ ለማግባባት ብትሞክርም ቱርክ የግብፅን ባለስልጣናት ወሽመጣቸውን ቆረጣ አዋርዳ ልካቸዋለች። ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር የፈጠረችው ትስስር በቀላሉ የማይበጠስ መሆኑንም አረጋግጣለች።
ይህን ተከትሎም የግብፅ ልኡካኑ በአንካራ የነበረን የ2ቀን ስብሰባ(ጉትጎታ) ሳይሳካ ቀርቷል ብለዋል።