Ajora Media-አጆራ ሚዲያ

Ajora Media-አጆራ ሚዲያ This page are give a wide coverage to world news, events, special occasion. joins us.

 🎉🎉
01/04/2024

🎉🎉

01/04/2024
culture🇱🇺💖🇱🇺
15/09/2023

culture🇱🇺💖🇱🇺

Culture🇱🇺💖🇱🇺
15/09/2023

Culture🇱🇺💖🇱🇺

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2014 ውድድር ሲዳማ ቡና የሦስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን የቡድኑ አበላትም በ16 ጎሎች ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነው ይ...
02/07/2022

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2014 ውድድር ሲዳማ ቡና የሦስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን የቡድኑ አበላትም በ16 ጎሎች ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነው ይገዙ ቦጋለን ደስታ ተጋርተዋል።

መልካም ዜና🙏 ለወጣቶች፦  በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባለተሰጥኦ ታዳጊዎች ወደ አንድ ማዕከል ሊሰባሰቡ ነው!!===================በተዘጋጀላቸው ልዩ ማዕከል ትምህርታቸውን ይማራሉ፣ፈጠ...
02/07/2022

መልካም ዜና🙏 ለወጣቶች፦ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባለተሰጥኦ ታዳጊዎች ወደ አንድ ማዕከል ሊሰባሰቡ ነው!!
===================
በተዘጋጀላቸው ልዩ ማዕከል ትምህርታቸውን ይማራሉ፣ፈጠራ ስራቸው ላይ ይመራመራሉ ተብሏል።ድንቅ ተግባር ነው።

በቡራዩ ከተማ በተገነባውን የኢትዮጵያ የባለ ልዩ ተሰጥኦና ተውህቦ ኢንስቲትዩትን ያለውን አጠቃላይ ሂደትና ልጆቻቸው መጥተው የሚያርፉበትን ስፍራ የክልል ቢሮ ኃላፊዎች ትናንት ጎብኝተዋል።

በዚህ ወቅት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ Belete Molla Getahun ተከታዩን መልእክት አስተላልፈዋል።























ማዕከሉ በ2015 በጀት ዓመት ባለተሰጥኦዎችን ለማሳደግ፣ ለማስተማርና ለማሰልጠን መቀበል ይጀምራል ተብሏል።

ከቄለም ወለጋ ጊዳሚ የተገኘው የ 25 አመቱ ወጣት ራጂ አሸናፊ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከወሰዳቸው 60  ኮርሶች ሁሉንም A+ በማምጣት በከፍተኛ ውጤት ተመርቋል፣ በዚህም የተነሳ...
02/07/2022

ከቄለም ወለጋ ጊዳሚ የተገኘው የ 25 አመቱ ወጣት ራጂ አሸናፊ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከወሰዳቸው 60 ኮርሶች ሁሉንም A+ በማምጣት በከፍተኛ ውጤት ተመርቋል፣ በዚህም የተነሳ የአሜሪካው MIT ዩኒቨርሲቲ የ PHD ስኮላሽፕ እንዲማር እንደጋበዘው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ገልፀዋል።

የመረጃና ደህንነት ተቋማት ሃላፊዎችና ሰራተኞች በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ እየለማ የሚገኝን የፓፓያ ክላስተር ጎበኙሰኔ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /...
02/07/2022

የመረጃና ደህንነት ተቋማት ሃላፊዎችና ሰራተኞች በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ እየለማ የሚገኝን የፓፓያ ክላስተር ጎበኙ

ሰኔ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢንሳ/፣ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት፣ የፋይናንስ ደህንነት እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሃላፊዎችና ሰራተኞች በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በክላስተር የለማ የፓፓያ ምርት ጎበኙ።

በጉብኝቱ የምስራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ፤ በዞኑ ለፓፓያ እና አቮካዶ ክላስተር ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አርሶ አደሮችም በክላስተር በመደራጀት ከፍተኛ ምርት በማግኘት ህይወታቸውን በመለወጥ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አሁን ላይ በዞኑ በ1 ሺ 690 ሄክታር መሬት ላይ የፓፓያ ክላስተር ለምቶ በመመረት ላይ መሆኑንም አብራርተዋል።

በቀጣይም የፓፓያ እና አቮካዶ ምርትን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በክላስተር ፓፓያ ማልማት ከጀመሩ ወዲህ የተሻለ አምራች እየሆኑና በኑሯቸውም ላይ ለውጥ ማምጣቱን ኢዜአ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ገልጸዋል።

አርሶ አደሮቹ በሚያገኙት ገቢ ሀብት እያፈሩ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

የተቋማቱ ሃላፊዎችና ሰራተኞች በቆይታቸው በዱግዳ ወረዳ ለመኸር እርሻ ዝግጅት እየተደረገ የሚገኘውን የስንዴ ክላስተርም ጎብኝተዋል።

We are on the side of the Sudanese who are fighting for their freedom .«ከወታደራዊ በዝባዥ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ከሚታገሉት ሱዳናዊያን ጎን ነን። በ...
01/07/2022

We are on the side of the Sudanese who are fighting for their freedom .«ከወታደራዊ በዝባዥ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ከሚታገሉት ሱዳናዊያን ጎን ነን። በኢትዮጵያ ላይ የሆነ ነገር ሲጀምሩ ነው ውስጣዊ አመፁ የሚቀጣጠልባቸው። በሱዳን ለየት ያለ ህዝባዊ አመፅ እየተደረገ ነው። ትግላቸው አፍርቶ ከግብፅ ፈረስ ከሆነው ከጀነራል ቡረኃን አገዘዝ ነፃ እንዲወጡ ወንድማዊ ምኞታችን ነው።

ሊንኩን ከፈታችሁ Retweet በማድረግ አጋርነታችንን እናሳውቃቸው!
https://twitter.com/SuleimanAbdell7/status/1542742013367418881?t=KyROEM2Rg4gULJvDObyAwQ&s=19

ሱሌማን አብደላ

01/07/2022
01/07/2022
Israel is headed for new elections a fifth time in three years after parliament voted 92-0 to dissolve itself and Israel...
01/07/2022

Israel is headed for new elections a fifth time in three years after parliament voted 92-0 to dissolve itself and Israeli Prime Minister Naftali Bennett resigned. Bennett's former coalition partner, Yair Lapid, is set to take over as acting prime minister until elections are held November 1.

Bennett, appearing emotional, handed power to Lapid, in a ceremony at the prime minister's office.

"I'm passing you the sacred baton and the responsibility for the State of Israel. I hope you protect it and that God will protect you," Bennett said.

Lapid said that he would do whatever he can to make sure the State of Israel remains Jewish and democratic.

Before the ceremony, Lapid visited Israel's Holocaust Memorial to honor his late father, a Holocaust survivor. In a statement, Lapid said he promised his father that he would always keep Israel strong and capable of defending itself and protecting its children.

The outgoing government was an eight-party coalition that included parties from the right and left. For the first time in Israel's history, it included an Arab party – the four-seat Raam, headed by Mansour Abbas. Several weeks ago, Bennett lost his narrow coalition majority when two hardline lawmakers defected, making it impossible to govern.

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ተጠባቂውን ጨዋታ ለመምራት ደቡብ አፍሪካ ገቡአዲስ አበባ፣ሚያዝያ 14፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተስማ ተጠባቂውን የማማሎዲ...
22/04/2022

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ተጠባቂውን ጨዋታ ለመምራት ደቡብ አፍሪካ ገቡ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 14፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተስማ ተጠባቂውን የማማሎዲ ሰንዳውስን እና ፔትሮ አትሌቲኮ ጨዋታ ለመዳኘት ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል፡፡

የ2021/22 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ወደ ፍፃሜው እየተጠጋ ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ አራት ውስጥ የሚገቡ ክለቦች የሚለዩበት የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ከነዚህ ጨዋታዎች አንዱ የሆነውን የማማሎዲ ሰንዳውስን እና ፔትሮ አትሌቲኮን ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አርቢተር ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ይመሩታል፡፡

ኢንተርናሽናል ዳኛው ቀደም ሲል በፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ክስ ቀርቦበት በብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ከሚደረግበት አዳማ ከተማ እንዲሰናበቱ መደረጋቸው ይታወሳል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመለከተ የተነሱ ችግሮችን ለማጣራት የተላከው አጣሪ ኮሚቴ በፈተና አስተራረም ዙሪያ የደረሰበትን ሂደት በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ...
14/04/2022

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመለከተ የተነሱ ችግሮችን ለማጣራት የተላከው አጣሪ ኮሚቴ በፈተና አስተራረም ዙሪያ የደረሰበትን ሂደት በተመለከተ በሰጠው መግለጫ የተላለፉ ነጥቦች

➽ፈተናው ታርሞ ውጤት ሲታይ ቅሬታ ስለነበር ሳይስተካከል መለቀቅ የለበትም የሚል ቅሬታ ትምህርት ቢሮው ማቅረቡን

➽የተነሱ ችግሮች ሳይጣሩ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቆረጥ እንደሌለበት ቢሮው መግለጹ

➽የውጤት መቀያቀርና የፈተና አስተራረም ስሕተት ስለነበር አጣሪ ኮሚቴ ወደ አዲስአበባ መሄዱን

➽በትምህርት ቤታቸው ጎበዝ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ውጤት ያላመጡበት ምክንያት፣ አንዳንድ ተማሪዎች በአንድ ትምህርት ከፍ ያለ ውጤት በአንደኛው ደግሞ የወረደ ያመጡበትን፣ አንድም ተማሪ የመግቢያ ፈተና ውጤት ሳያመጣ የቀረባቸው ትምህርት ቤቶችንና የውጤት መቀያየር ለምን ኖረ? የሚለውን ጥያቄ ይዞ ኮሚቴው መሄዱ ተገልጿል።

➽የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ታሳቢ ያደረገ አይደለም የሚለው ጥያቄም ሌላው ጉዳይ ነበር፡፡

➽የፈተና ማሽኑ አስተራረም ችግር ይኖርበታል በሚል በእጅ ፈተና በማረም ለማረጋገጥ ተሞክሯል

➽የውጤት አገላለጹ ምን ያክል ትክክል ነው የሚለውንም ማየቱን ገልጿል

➽የፈተና ቡክሌት መቀያየር ችግር እንደተመለከቱም አንስቷል።

➽ምንም ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶችን ርእሰ መምህር በመውሰድ የጎበዝ ተማሪዎችን ፈተና በእጅ የማረም ሥራ ተሠርቷል፡፡

➽በአማራ ክልል የተማሪዎች ውጤት ለመቀነሱ በጦርነት ምክንያት የሥነ ልቦና ችግር በማጋጠሙ መኾኑንም ኮሚቴው ገልጿል፡፡ እነዚህን ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል መመዘን ፍትሐዊ አለመኾኑን ቢሮው መጠየቁንም አመላክቷል።

➽ከሲቪክስ ውጤት በተጨማሪ በሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ላይም ጥርጣሬ አለን መታየት አለበት የሚል ጥያቄ መቅረቡ ተገልጿል

➽ፈተናዎች ወጥተዋል የሚል ወሬ በመናፈሱ ተማሪዎች ሳይረጋጉ መፈተናቸው በውጤታቸው ተፅዕኖ መፍጠሩንም አንስቷል።

➽በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ ችግር እንዳይፈጠር የሶፍትዌር ባለሙያ ጭምር በኮሚቴው መካተቱን ተመልክቷል።

➽ትምህርት ሚኒስቴርም ኮሚቴው ማጣራት የሚገባውን ጉዳይ እንዲያጠራ ትብብር ማድረጉንም ኮሚቴ ገልጿል፡፡

➽የፈተናዎች ስርቆት መኖሩን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በተደረገው ውይይት መገለፁን እና ከዚህ አዙሪት ለመውጣት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት ማመላከቱን

➽በተደረገው ውይይት ጦርነቱ በተማሪዎች ውጤት ላይ ተፅዕኖ ማሳረፉን መስማማታቸውንም አስታውቋል።

➽በፈተናው ጉዳይ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ዓይናችን ከጉዳዩ ላይ አናነሳም፣ የተወከልነው የሕዝብ ጥያቄ ለመመስ ነው፣ ሌላ ጉዳይ የለንም ብሏል

➽በትምህርት ሚኒስቴር በኩልም በአጭር ጊዜ በጉዳዩ ዙሪያ የደረሰበትን ውጤት እንደሚገልጽ አመላክተዋል

➽አሁን የተፈጠረው ችግር እንዲፈታ ጥሩ ሂደቶች መኖራቸውን ኮሚቴው አንስቷል፡፡

Via #አሚኮ

ለባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የተዘረጋ የኤሌክትሪክ ሽቦ ቆርጠው የሰረቁ ሁለት ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ************************(ኢ ፕ ድ) ለአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ት...
14/04/2022

ለባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የተዘረጋ የኤሌክትሪክ ሽቦ ቆርጠው የሰረቁ ሁለት ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ
************************
(ኢ ፕ ድ)

ለአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የተዘረጋ የኤሌክትሪክ ሽቦ ቆርጠው የሰረቁ ሁለት ተከሳሾች በጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተከሳሽ ፀጋዬ ቴዎድሮስ እና ያብስራ ተስፋዬ በ1996 ዓ.ም የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)ሀ እና የቴሌኮሙኒኬሽንና የኤሌክትሪክ ሀይል መሰረተ ልማት አውታሮችን ደህንነት ለመጠበቅ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 464/2005 አንቀጽ 4ን በመተላለፍ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል፡፡

ተከሳሾቹ ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት የሆነ 40 ሜትር ርዝመት እና 80 ሺ ብር የዋጋ ግምት ያለውን የባቡር የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ ሽቦ ቆርጠው መውሰዳቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የተከሳሾቹን ጥፋተኝነት በማስረጃ በማረጋገጥ እና ጥፋተኞችን ያርማል ሌሎችን ያስጠነቅቃል በማለት ፀጋዬ ቴዎድሮስ በ7 አመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት እንዲሁም ያብስራ ተስፋዬ በ7 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከልም ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል።

Via

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የማኔጅመንት ቡድን አዋቀረ ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት መስፍን ጣሰው አዲስ የማኔጅመንት ቡድን አዋቅረዋል፡፡ ...
14/04/2022

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የማኔጅመንት ቡድን አዋቀረ !

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት መስፍን ጣሰው አዲስ የማኔጅመንት ቡድን አዋቅረዋል፡፡

በአዲሱ የማኔጅመንት ቡድን፤ ቀደም ሲል በተጠባባቂነት የሃላፊነት ቦታዎች ይዘው ሲያገለግሉ የነበሩ ሀላፊዎች ቦታው የጸደቀላቸው ሲሆን አንዳንድ ሀላፊዎች ከቦታቸው ተነስተው በሌሎች ባልደረቦቻቸው ተተክተዋል፡፡

በዚህም መሰረት በተጠባባቂነት በቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ረታ መላኩ ሹመቱ ፀድቆላቸዋል።

የበረራ ኦፕሬሽን ም/ል ፕሬዝደንት የነበሩት ካፒቴን ዮሀንስ ሃ/ማርያም በካፒቴን ዮሴፍ ሀይሉ ተተክተዋል፡፡

ቺፍ ኮሜርሺያል ኦፊሰር የነበሩት ኢሳያስ ወ/ማርያም የዓለም አቀፍ አገልግሎት ሀላፊ በነበሩት ለማ ያደቻ የተተኩ ሲሆን፤ መስፍን ብሩ የዓለም አቀፍ አገልግሎት ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስትራቴጂክ ፕላኒንግ ም/ል ፕሬዝደንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ቡሴራ አወል የፍሊት ፕላኒንግ ም/ል ፕሬዝደንት በነበሩት ዳንኤል አበበ ተተክተዋል፡፡

የሰው ሀይል አስተዳደር ተጠባባቂ ም/ል ፕሬዝደንት የነበሩት ዋሲሁን አስረስ በዘነበወርቅ ገ/ፃዲቅ ተተክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት እስክንድር አለሙ እና የጥገና ክፍል ተጠባባቂ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበሩት ቅዱስ መልካሙ ቦታቸው ጸድቆላቸዋል፡፡

ሀይለመለኮት ማሞ የኢትዮጵያ ሆሊዴይ እና ዲጂታል ሴልስ ም/ል ፕሬዝደንት ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ ጌትነት ታደሰ የአየርመንገዱ ዋና ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር፣ ታደለ ባረጋ የግራውንድ ሰርቪስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር፣ መንግስቱ በዜ ኢንተርናል ኦዲት ኮምፕሊያንስ እና ቢዝነስ ሰስቴኔብሊቲ ም/ል ፕሬዝደንት ሆነው መሾማቸውን ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡

Via EthioTube

"የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያለማከለ እንቅስቃሴ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አይችልም "       -ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ ዱራሜ፣ሚያዝያ 06/2014 ዓ.ም "የፈተናዎች መብዛት ከብልጽ...
14/04/2022

"የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያለማከለ እንቅስቃሴ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አይችልም "
-ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ

ዱራሜ፣ሚያዝያ 06/2014 ዓ.ም "የፈተናዎች መብዛት ከብልጽግና ጉዞ አያደናቅፈንም" በሚል መሪ ቃል የከምባታ ጠምባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አባላት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ።

በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ በተቀመጡ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ላይ ግልጸኝነት መፍጠር የሚያስችልና የጉባኤውን ሀሳቦች የሚያዳብርበት እንደሆነም ተገልጿል ።

በውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የዱራሜ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ አሸናፊ ኃይሉ እንደገለፁት እስካሁን በሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ የተሰሩ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሴቶቻችን የሚያነሷቸው የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች የሚፈቱበትና በችግሮቹ መፍትሄዎች ላይ ሴቶችን ግምባር ቀደም ሚናቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል ።

የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሀብት ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊዋ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያለማከለ እንቅስቃሴ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደማይችል ገልፀው ፣ ሴቶች ፓርቲያችን ላስቀመጠው ውሳኔዎች ግብ ስኬት በግንባር ቀደሚነት እንድሳተፉም አሳስበዋል ።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው በጉባኤው ከተቀመጡት ውሳኔዎች አንዱ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ጉዳይ እንደሆነ ገልጸው ለተግባራዊነቱም ሁሉም በየደረጃው የየበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ከቃላት ባለፈ በተግባር ለመግለጥ ልዩ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል ያሉት ኃላፊው ሴቶቻችን ግምባር ቀደም ሚናቸውን ልጨወቱ ይገባል ስሉም አሳስበዋል ።

ከውይይት መድረኮቹ ጎን ለጎን አሁን እየታዬ ያለውን የኑሮ ውድነት ማቃለል የሚያስችል “ምግቤን ከጓሮዬ ጤናዬን ከምግቤ” የሚል የከተማ ግብርና ይፋዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እንደሚኖርም ተገልጿል ።

በከተማ ግብርናው ሁሉም ሴቶች ባላቸው ውስን ቦታ ፕላስቲክና መሰል ቁሳቁሶችን በመጠቀም የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬዎችን እንዲያለሙ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩም ከከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል ።

ለመድረኮቹ ተገቢው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ መጀመሩን የገለጹት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊዋ ወ/ሮ ብዙነሽ ታዴዎስ በተመሳሳይ ቀን በዞኑ በሚገኙ በ7ቱም ከተማ አስተዳደሮች እየተካሄደ እንደሆነም ገልጸዋል።

Via

በከምባታ ጠምባሮ ዞን አንጋጫ ከተማ አስተዳደር የሴቶች የጓሮ አትክልት ልማት ንቅናቄ መድረክ " ምግቤን ከጓሮዬ ጤናዬን ከምግቤ " በሚል መሪ ቃል በደመቅ ሁኔታ  እየተካሔደ ነው ፡፡ በመድረ...
14/04/2022

በከምባታ ጠምባሮ ዞን አንጋጫ ከተማ አስተዳደር የሴቶች የጓሮ አትክልት ልማት ንቅናቄ መድረክ " ምግቤን ከጓሮዬ ጤናዬን ከምግቤ " በሚል መሪ ቃል በደመቅ ሁኔታ እየተካሔደ ነው ፡፡
በመድረኩ ለይ ሁሉም በለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በከተማው መልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ፣ በመጀመሪያው ዙር የፓርቲ ጉባኤ ውሳኔዎችና በከተማው የሴቶች የጓሮ አትክልት ልማት ስራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል ፡፡

ከ94 ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት መድረክ ቅዳሜ ይካሄዳል፡-የደቡብ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤትበደቡብ ክልል 94 ሺህ 200 ወጣቶች የሚሳተፉበት ክልል አቀፍ የውይይት መድረክ ሚያዚያ 8/20...
14/04/2022

ከ94 ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት መድረክ ቅዳሜ ይካሄዳል፡-የደቡብ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት

በደቡብ ክልል 94 ሺህ 200 ወጣቶች የሚሳተፉበት ክልል አቀፍ የውይይት መድረክ ሚያዚያ 8/2014 እንደሚካሄድ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰንበቶ አባባ የውይይት መድረኮቹ ወጣቱ በብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን በአግባቡ ተረድቶ ወደቀጣዩ ተግባር በእውቀት እንዲገባ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል፡፡

መድረኮቹ ለወጣቱ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችሉ፣መካተትና መሻሻል አለባቸው የሚሏቸውን ጉዳዮች በነጻነት የሚያነሱባቸውና የወጣቱን ወሳኝ ችግሮች ለመፍታት እንደመነሻ የሚሆኑ ሀሳቦች የሚገኙበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ያለወጣቱ ተሳትፎ የትኛውም ጉዳይ ግቡን እንደማይመታ ያምናል ያሉት አቶ ሰንበቶ የጉባኤው ውሳኔዎች ወደተግባር የሚቀየሩት በወጣቱ ስለሆነ ሁሉም ወጣቶች በመድረኮቹ በንቃት እንዲሳተፉም አሳስበዋል፡፡

በመድረኮቹ የፓርቲዉ አባል ያልሆኑ ወጣቶችም ጭምር እንደሚሳተፉ ያስታወቁት ጽህፈት ቤት ሃላፊው የውይይት መድረኮቹ በ157 አካባቢዎች እንደሚካሄዱና ለዚህም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ወጣቱ ለአካባቢው፣ለክልሉና ለአገሪቱ ይበጃሉ የሚላቸውን ሀሳቦች በቅንነት በማንሳት የጸናና ዘላቂ ሰላም ያለው፣ የበለጸገ አገርና ህዝብ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት የራሱን ሚና እንዲጫወትም አቶ ሰንበቶ ጠይቀዋል፡፡

በመድረኮቹ ማጠናቀቂያ ላይ የኑሮ ውድነቱን ለማስተካከልና የምርት አቅርቦቱን ለማሳደግ የሚያስችል የከተማ ግብርና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የሚካሄድ ሲሆን በከተማ ግብርና መልካም ተሞክሮ ያላቸው ግለሰቦች ጥረትም ጉብኝት ይካሄዳል ብለዋል፡፡

የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከ840 ሺህ በላይ አባላት እንዳሉት ያመለከቱት አቶ ሰንበቶ አባባ በቀጣይ እስከ ገጠር ቀበሌያት የሚገኙ ሁሉንም ወጣቶች በጉባኤው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ለማወያየት እቅድ መያዙንም አስታውቀዋል፡፡

Most Populated Cities In Africa (2022)1. Lagos🇳🇬 21 million people2. Cairo🇪🇬 20.4 million people3  Kinshasa🇨🇩 13.3 milli...
14/04/2022

Most Populated Cities In Africa (2022)

1. Lagos🇳🇬 21 million people
2. Cairo🇪🇬 20.4 million people
3 Kinshasa🇨🇩 13.3 million people
4. Luanda🇦🇴 6.5 million people
5. Nairobi🇰🇪 6.5 million people
6. Mogadishu🇸🇴 6.0 million people
7. Abidjan🇨🇮 4.7 million people
8. Alexandria🇪🇬 4.7 million people
9. Addis Ababa🇪🇹 4.6 million people
10 Johannesburg🇿🇦 4.4 million people
11 Dar es Salaam🇹🇿 4.4 million people
12 Casablanca🇲🇦 4.3 million people
13 Accra🇬🇭 4.1 million people
14 Durban🇿🇦 3.4 million people
15 Kano City🇳🇬 2.8 million people

🌐Source: WorldAtlas

In The memory of ፩ ብር!Via
14/04/2022

In The memory of ፩ ብር!
Via

ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በላከልን መልዕክት በዛሬው ዕለት የመሰረተ ልማት መጋራት እና   ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ  ከበርካታ ዙር ውይይቶች በኋላ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋ...
14/04/2022

ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በላከልን መልዕክት በዛሬው ዕለት የመሰረተ ልማት መጋራት እና ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ከበርካታ ዙር ውይይቶች በኋላ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጾልናል።

ውይይቶቹ በኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን የተመሩ መሆኑን የገለፀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለሥልጣኑ ላሳየው ብቁ የአመራር ጥበብ ምስጋና አቅርቧል።

ስምምነቶቹን ለማጠናቀቅም ቀጣይ ሥራዎች የሚከወኑ እንደሆነም ገልጿል።

ስምምነቶቹ ከሳፋሪኮም ኢንቨስትመንት እና ከኔትዎርክ ዝርጋታ ጋር ተደምረው በዚህ ዓመት ለሚጀመረው አገልግሎት ጠንካራ መሠረት፣ ለቴሌኮም ሴክተሩ እድገት እንዲሁም ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ዲጂታል አካታችነት ዕቅድ መሳካት ወሳኝ ምዕራፍ ይሆናሉ ብሏል።

Arjen Robben just went on to finish the Rotterdam Marathon. He did 42 kilometers with a time of 3:13:57.
14/04/2022

Arjen Robben just went on to finish the Rotterdam Marathon. He did 42 kilometers with a time of 3:13:57.

Sara Zewde (Founding principal at Studio Zewde in Harlem, New York City)A native of the Gulf Coast, Sara Zewde’s view of...
14/04/2022

Sara Zewde (Founding principal at Studio Zewde in Harlem, New York City)

A native of the Gulf Coast, Sara Zewde’s view of architecture completely shifted after Hurricane Katrina happened in 2005. Following the traditional path of going to design school (she studied urban planning at MIT and landscape architecture at Harvard), completing internships, and then securing a job after graduation, Zewde eventually ventured out to establish her own practice, which does a hybrid of landscape architecture, urban design, and public art.

Last year, Studio Zewde won the Architectural League of New York’s award for 2021 Emerging Voice. Made up of a multidisciplinary team, the Harlem–based firm utilizes “design methodology that syncs site interpretation and narrative with a dedication to the craft of construction.” Zewde’s work bridges the gap between built environments and the communities that coexist within them. As stated on her firm’s website, “Studio Zewde is devoted to creating enduring places where people belong.”

Architectural Digest: What obstacles have you overcome while navigating your career path in this field?

Sara Zewde: It’s been a bumpy road, but remaining clear-minded about my commitment to elevating culture, ecology, and craft in my design practice helped me to navigate obstacles along the way.

What piece of advice would you give to BIPOC (black indigenous and people of color) who are interested in architecture but don’t know how or where to start?

Read. Read what feels relevant to your interests in design, whether or not it directly relates to architecture.

Her theses at Harvard was titled Ecologies of Memory : Landscape Architectural Methods in an Expanded Understanding of Culture.

While at Harvard, Zewde was named the 2014 National Olmsted Scholar by the Landscape Architecture Foundation.[2] At MIT, she received the Silberberg Memorial Award for Urban Design and the Hebbert Award for Contribution to the Department of Urban Studies and Planning.[2] Prior to teaching at Harvard, Zewde taught at the Columbia Graduate School of Architecture, Planning and Preservation and the University of Texas at Austin School of Architecture.

https://www.architecturaldigest.com/story/black-women-architects-and-designers

https://studio-zewde.com/about

https://en.m.wikipedia.org/wiki/Sara_Zewde

https://nextcity.org/features/valongo-port-sara-zewde-rio-landscape-architect

ዛሬ ልዩ ቀን ነው የቤት ግንባታው እንደምታየው ኮሽና ሳይቀር ተገንብቶ ይህንን ደረጃ ደርሷል። በእውነት ለዚህ ቅዱስ ዓላማ የተዘረጉ እጆች ይባረኩ። ዛሬ ደግሞ ሄኔን በጎ አድራጊዎች አብረውን...
13/04/2022

ዛሬ ልዩ ቀን ነው የቤት ግንባታው እንደምታየው ኮሽና ሳይቀር ተገንብቶ ይህንን ደረጃ ደርሷል። በእውነት ለዚህ ቅዱስ ዓላማ የተዘረጉ እጆች ይባረኩ። ዛሬ ደግሞ ሄኔን በጎ አድራጊዎች አብረውን የጉልበት ስራ የሰሩ ነው የዋሉት አመስግኑልኝ። በእውነት ለዚህ ስራ እዝህ ደረጃ እንድደርስ ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ በውጭም በሀገር ውስጥም ያሉ ወዳጆቻችንን ፈጣሪ አብዝቶ ይባርካቸው። የወረዳው ሾፌሮችን በልዩ ሁኔታ አስግኑልኝ የጉልበት ስራ የሚሰሩ ወጣቶችን ሳይሰላቹ እያመላለሱ ነበር።እንዲሁም ከዳምቦያ ከተማና አከባቢያ ረዥም ጉዞ ተጉዘው ቡና ተሸክመው አሸሜ ያሉንን ወዳጆችም አመስግኑልኝ። አሁንም ስራው አላለቀም የደረስን በትን መሳወቅ ግድ ስለሚል ነው። ቀጣይ በሮችና መስተወቶች ይገጠማሉ፣ቤቱ ይለጠፋል፣ቤት ተርቶ ባዶ መሆን ስለሌለበት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ይሟላሉ ስለዚህ ቃል የገባችሁ ወንድሞቻችን ድጋፋችሁን ቀጥሉ እንላለን። ሼር አድርጉ።

Via

”ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታን ንግግር እንጂ ጦርነት አይፈታውም‘ – አቶ ሞገስ ባልቻ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትርበየትኛውም የዓለም ክፍል ያለውን ያልተረጋጋ የፖለቲካ...
13/04/2022

”ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታን ንግግር እንጂ ጦርነት አይፈታውም‘ – አቶ ሞገስ ባልቻ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር

በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለውን ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ ንግግር እንጂ ጦርነት አይፈታውም ሲሉ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡ አገራዊ ምክክሩ አገራዊ ተስፋ የሚሰጥ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሞገስ ባልቻ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደጠቀሱት፤ በየትኛውም የዓለም አካባቢ ያለውን ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ የሚፈታው በጦርነት ሳይሆን በውይይት መድረክ ነው፡፡

ከጦርነት ይልቅ ንግግር ለመግባባት አዎንታዊ ሚና እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያየ ማህበራዊ ትስስር ውስጥ ያለ በመሆኑ መለያየት እንደማይችል፤ መፍትሄው ደግሞ ተነጋግሮ አንድ መሆንና በተግባቦት ችግሮችን መፍታት የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ አገራዊ ምክክሩ ጠቃሚ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ የማያግባቡና ልዩነት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ደግሞ በመከባበር መፍታት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ልዩነት መከባበሪያ እንጂ መጠፋፊያ መሆን የለበትም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አካታች አጋራዊ ምክክር መድረኩም የፖለቲካ ጡዘቶችን በተወሰነ ደረጃ መልክ ያስይዘዋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡

እንደ ኃላፊ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ውይይት ማድረግ ከተቻለ፣ ሕዝቡን ማሳተፍ ከተቻለ፣ የፖለቲካ ኃይሎች ሀሳባቸውን አቅርበው በዚህ ጉዳይ ላይ መናጋገር ከቻሉ የማያግባባቸው ጉዳይ አይኖርም ብለዋል፡፡

«ምክክሩ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ቤት የምንገነባበት ስለሆነ ያገባኛል በሚል እሳቤ አዎንታዊ ሚና ልንጫወት በምንችልበት መልኩ መሰለፍና ማገዝ ይገባል፡፡ ለዚህ የበኩላችንን ታሪካዊ ኃላፊነት መወጣት ይኖርብናል» ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከአገራዊ ምክክሩ ባሻገር ሁሉም ሰው በትብብር መሥራት ከቻለ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተስፋ ያላትና ውጤት ማምጣት የምትችል አገር ትሆናለች ብለዋል፡፡

ያጋጠሙ ፈተናዎች ያልፋሉ ያሉት አቶ ሞገስ፤ ባለፉት አራት ዓመታት ያሉ ሁኔታዎች ሲታዩ በአንድ በኩል ተፈጥሮ በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲካና የጥፋት ኃይሎች ፈተናዎችን ተሻግረናል፤ ይህም የኢትዮጵያን መጻኢ ጊዜ ጥሩና ተስፋ ሰጪ መሆኑን እንደሚያሳይ ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም ሁሉም ሰው እጅ ለእጅ ተያይዞ በቋንቋ፣ በባህል፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢ ከመገፋፋት፣ እንዲሁም ወገንን ከመጥላትና ጭፍን ከሆነ አስተሳሰብ በመውጣት በወንድማማችነትና እህትማማችነት ስሜት አብሮነትን ሊያሳይ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን የጋራ ቤትና የጋራ አገር ብለው መንቀሳቀስ ከቻሉ ኢትዮጵያ ከራሷ ሕዝብ አልፋ ለምሥራቅ አፍሪካ ዜጎች ልትበቃ የምትችል ናት ብለዋል።
#ኢዜአ

13/04/2022

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን አዳዲስ የግጭት ቀጠናዎችን በመፍጠር የሀገር ሕልውናን አደጋ ላይ ለመጣል ለሚንቀሳቀሱ የብሔር ፖለቲካ ፓርቲዎች ማስጠንቀቂያ መስጠት አለበት!!

በኦሮሚያና በአማራ የብሔር ፖለቲከኞች መካከል ከቀን ወደ ቀን እንካ ሰላንቲያውና አተካራው እየጨመረ መጥቷል፤ ከዚህም ከዚያም የሚወረወሩ የመግለጫ ጋጋታዎች ከቀን ወደ ቀን በስፋት እየተገለጡ ነው። በአንፃሩም ሕዝቡ ሁሉንም ሁነት በትዝብት እየመለከተው ነው፤ እስከ ዛሬም ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ያስቀራት የኤሊቶቿ ግጭት እንጂ ከታች ወደ ላይ የሚመዘዝ የሕዝብ ለሕዝብ ግጭቶች አይደሉም፤ በሕዝብ መካከል ግጭቶቾ ተፈጠሩ ቢባል እንኳ መንስኤው የሚመዘዘው ከፖለቲካ ኤሊቶቹ ሰፈር ነው።

በፖለቲካኞች ሽኩቻ የሀገር አንድነት ስጋት ላይ በሚወድቅበት ወቅት ዋናው ኃላፊነት የሚወድቀው በሀገር መከላከያው ላይ ነው። እንደሚታወቀው የመከላከያው ወገንተኝነት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ብቻ ነው፤ መንግስትም ቀደም ሲል በተደጋጋሚ "መከላከያ ብሄር የለውም" የሚል መግለጫ ሲሰጥ ነበር። ስለዚህም ሀገራችን ሉዓላዊነቷ በውጭም ሆነ በውስጥ አደጋ ላይ በወደቀበትና የኢትዮጵያ ሕዝብም በኢኮኖሚ ድቀት ቀውስ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት አዳዲስ የግጭት ቀጠናዎችን ለመፍጠር ደፋ ቀና ለሚሉ የብሔር ፖለቲካ ፓርቲዎች ጀግናው መከላከያ ኃይላችን ያለ ወገንተኝነት የሚመለከታቸውን ሁሉ የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነቷን ከሚያናጉ ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴዎች እንዲታቀቡ ቀጥተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ መስጠት ይኖርበታል።

Via

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ajora Media-አጆራ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share