12/09/2023
*የኢትዮጵያ ዩኒየን ወንጌል ክፍል መልዕክት*
እንኳን ለ2016 ዓ/ም በሰለም አደረሳችሁ አደረሰን! አዲሱ ዓመት የፍቅር፣ ሰላምና በሁሉም ዘርፍ ለፈጣሪ ክብርና ለሰው ጥቅም የምንሰረበት ዘመን ይሁንልን!
“አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፤ አቤቱ፥ *በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም* ፤ በዓመታት መካከል ትታወቅ፤ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።” ዕንባቆም 3፥2፡፡ እያለ የዩኒየኑ ወንጌል ክፍል መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ደም የተዋጃችሁ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ የዩኒየኑ ወንጌል ሥራ እቅድ፣ በግንቦት 12/2015 ዓ/ም በደቡብ ምዕረብ ፊልድ አንሾ አጥቢያ በነበረው መንፈሳዊ ስብሰባ፣ ከባለፈው ሰኔ 01/2015 ዓ/ም እስከ ያካቲት 02/2016 ዓ/ም ድረስ ማለትም ጳጉሜን ሳይጨምር በ240 ቀናት የሚከናወን ወንጌል ሥራ በኢትዮጵያ ዩኒየን ፕሬዝደንት ፓ/ር ሌንጫ ተክሌ አማካይነት ጥቅስ ተነቦ በፀሎት መከፈቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የዩኒየኑ ወንጌል ክፍሉም በሰኔ ወር " *ስለ ወንጌል"* በሚል መርህ (“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23) በፀሎትና በገንዘብ ድጋፍ በወንጌል ሥራ፣ በሐምሌና ነሐሴ ወራትም በተለያዩ ተግባራት በ90 ቀናት ውስጥ ስለተሰተፋችሁ ፈጣሪ ይባርካችሁ ይላችኀል፡፡ አሁን ደግሞ "ወንጌሉ ምስክር እንዲሆን መስካሪዎች መሆን" በሚል መርህ (ማቴ.24:14) ከነሐሴ 25/2015 ዓ/ም ጀምሮ በወንጌሉ ዘርፍ ትምህተ ጉባዔ (ሴሜናር) እየሰጠ መሆኑን አስታውሶ፣ ከመስከረም 01/2016 ዓ/ም እስከ ያካቲት 02/ 2016 ዓ/ም ድረስ " ለ150 ቀናት *ክርስቶስ ለሞተለት ነፍስ እሰራለሁ* " በሚል መርህ መላው የቤተክርስቲያን አበላት የሚሠተፉበትን የወንጌል እቅድ ማቀዱን ስገልጽ በታለቅ አክብሮትና ደስታ ነው፡፡ ስለዚህ በፊልድ መሪዎች ብሎም በሁሉም ፊልዶች ስር በሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት መሪዎች አማካይነት በሚደረሰው ወንጌል ሥራ እቅድ እንዲትሳተፉ ዘንድ ጥሪውን በታላቅ አክብሮትና ትህትና አቅርቧል፡፡
" *ወደ ዓለም ሁሉ እሄዳለሁ፤ የምስራች ነጋሪ ነኝ!"
ወ/ም ደነበ በቀለ
የኢንተርናሽናል ሚሽናሪ ሶሳይቲ [ሰቬንዝ ዴይ አድቬንቲስት] ቼርች ሪፎርም ሙቭመንት ኢትዮጵያ ወንጌል ክፍል አስተባባሪ🙏
*Ethiopian Union Missionary Department Message*
Happy New Year 2016!
May the new year be a time of love, peace and in all areas we strive for the glory of the Creator and the benefit of humanity!
“Lord, I was afraid when I heard your fame; Lord, *perform your work between the years*;
Be known among the years. Think of mercy at the time of death.”
Habakkuk 3:2. In this Biblical verse, the Union Missionary Department expresses its good wishes for all. My dear brothers and sisters who
redeemed by the blood of our Lord Christ Jesus, as you know, the union gospel work plan geared in South West Field Ansho local church on May 12/2015 A.D. during the spiritual meeting held in union wise. The work that will be done since last June 01/2015 A.D. and will be continued till February 02/2016 A.D. for 240 days without including leap year opened by the Ethiopian Union President by Pr. Lencha Tekle in reading a verse and praying for the successfulness of the activities. Therefore, the Union Missionary Department would like to express deep heartful thanks for those who participated in gospel activities in all sides since the month of June unto the end of the last August within the 90 days. Now the seminar is being given in the field of the gospel works with the principle of "Being witnesses; Gospel to be a witness" (Matthew 24:14) starting from August 25/2015 AD. Finally, the Missionary Department would like to request all churches members, who are found under the fields, in order to participate 150 days missionary activities in following the guidance of respective leaders.
Happy New Year!
"*I will go to all the world; I am a bearer of good news!"
Mrs. Denbe Bekele
International Missionary Society [Seventh Day Adventist] Church Reform Movement -Ethiopian Union Missionary leader
Report: IMSEM🙏