Hola Media ሆላ ሚዲያ

Hola Media ሆላ ሚዲያ Hadiya Mass Media is the of voice of voiceless.

የነደብረፅዮን ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ዳግም እልቂት አውጇል!በነደብረፅዮን የሚመራው የህወሃት ክንፍ የትግራይን ወጣት ዳግም ለጦርነት ለመማገድ አደገኛ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ይህ ቡድን ከዚህ...
27/01/2025

የነደብረፅዮን ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ዳግም እልቂት አውጇል!

በነደብረፅዮን የሚመራው የህወሃት ክንፍ የትግራይን ወጣት ዳግም ለጦርነት ለመማገድ አደገኛ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ይህ ቡድን ከዚህ በፊት ባወጀው ጦርነት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው እናቶች ካለልጅ ቀርተዋል። ብዙዎችም በዚህ ጦርነት አካላቸውን አጥተው ከአላማቸው ወደኋላ ቀርተዋል። ይህ ሁሉ የሆነው በስልጣን ጥም የሰከረው የሽማግሌዎቹ ስብሰብ ህወሃት ባመጣው ጣጣ ቢሆንም ቡድኑ አሁንም ዳግም በክልሉ ሌላ እልቂት ለማስከተል አደገኛ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ይህን የተመለከተው የክልሉ ህዝብ የ80 አመት አዛውንት እንዲኖሩ እና 20 አመት የሞላው እንዲሞት አንፈቅድም በሚል በሌሎች የህወሃትን እንቅስቃሴ በሚቃወሙ መፈክሮች ወደአደባባይ በመውጣት ላይ ይገኛል።

በመቐለ እና ሌሎች የትግራይ ከተሞች የተቃዉሞ ሰልፍ ተካሄደ፣ ሰሞኑን የትግራይ ጦር ሀይሎች አመራሮች ያሳለፉት ዉሳኔ ፍፁም የተሳሳተ፣ የትግራይ ህዝብን ዳግም ዋጋ የሚያስከፍል ነዉ በማለት ህ...
27/01/2025

በመቐለ እና ሌሎች የትግራይ ከተሞች የተቃዉሞ ሰልፍ ተካሄደ፣ ሰሞኑን የትግራይ ጦር ሀይሎች አመራሮች ያሳለፉት ዉሳኔ ፍፁም የተሳሳተ፣ የትግራይ ህዝብን ዳግም ዋጋ የሚያስከፍል ነዉ በማለት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የተቃዉሞ ድምፁን አሰምቷል።

በህብረ-ብሔራዊነት የደመቀች ጠንካራ ሀገር የመገንባት የጋራ ህልም‼️እንደ ሀገር የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በርካታ ሪፎርሞች በማድረግ ሀገራችን ከነበረችበት አስከፊ  ሁኔታ በማላቀቅ ብልፅግናን ...
02/01/2025

በህብረ-ብሔራዊነት የደመቀች ጠንካራ ሀገር የመገንባት የጋራ ህልም‼️

እንደ ሀገር የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በርካታ ሪፎርሞች በማድረግ ሀገራችን ከነበረችበት አስከፊ ሁኔታ በማላቀቅ ብልፅግናን ማረጋገጥ የምትችል የወንድማማችነት እሴትና በህብረ-ብሔራዊነት የደመቀች ጠንካራ ኢትዮጵያ ለመገንባት የብልጽግና ጉዞ መጀመራችን ይታወቃል፡፡

የፓርቲያችንም ተልዕኮ በመደመር እሳቤ ሀገራችንን በጋራ በማነፅ፣ ከመገፋፋት ይልቅ በመደጋገፍ በእውነተኛ ህብረ ብሄራዊ አንድነት ሀገርን መገንባት ነው ፡፡ በለውጡ ሂደት ከህዝባችን ጋር ይበልጥ የሚያቀራርቡ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካው ዘርፍ በርካታ ተግባራት መሰራታቸው የሚታወቅ ነው። በተለይም በብልፅግና የጉዞ መንገዳችን የጀመርነው ተስፋ ሰጪ ለውጥ በርካቶችን ያስደመመ የፀረ ለውጥ ኃይሎን ደግሞ አንገት ያስደፋ የድል ታሪክ እያስመዘግብን እንደሆነ ይታወቃል።

በመሆኑም ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን በማይናወጥ መሰረት ላይ እንዲገነባ ለእኛ እንዲደረግልን የምንፈልገውን ለሌሎችም የምናደርግበት፣ በእኛ ላይ እንዲፈፀም የማንፈልገውን በሌሎች ላይም የማንፈፅምበት፣ እርስ በርስ መፈራረጅን የምናቆምበትና እጅ ለእጅ ተያይዘን በፍቅር፣ በይቅርታና በአንድነት የምንጓዝበት ጠንካራ አገር የመፍጠርን ተልዕኮ በጋራ ልንፈጽም ይገባናል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ ቤት

ክርሰቲያኖ ሮናልዶ በ 2024 ያሳካቸው ክብረወሰኖች!! #ፖርቹጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ 2024 በግሉ ስፖርታዊ እና ከስፖርት ውጭ የሆኑ ክበረወሰኖችን ያሳካበት አመት ነበ...
02/01/2025

ክርሰቲያኖ ሮናልዶ በ 2024 ያሳካቸው ክብረወሰኖች!!

#ፖርቹጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ 2024 በግሉ ስፖርታዊ እና ከስፖርት ውጭ የሆኑ ክበረወሰኖችን ያሳካበት አመት ነበር፡፡

“እኔ ክብረወሰኖችን አላሳድድም ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል” ያለው የ39 ዓመቱ ሮናልዶ፤ አሁንም አዳዲስ ክብረወሰኖችን በእጁ ማስገባቱን ቀጥሏል። ከነዚም መካከል ፡
በተከታታይ ለ21 ዓመታት ለብሔራዊ ቡድኑ ግብ ማስቆጠር የቻለ በታሪክ የመጀመሪያው ተጨዋች ፤ ለሳዑዲ አረቢያው አል ናሰር የሚጫወተው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዘንዶሮ የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን፤ በ31 ጨዋታ 35 ጎሎች መረብ ላይ በማሳረፍ በሳውዲ ሊግ በአንድ የውድድር አመት ብዙ ጎል በማስቆጠር ደረጃውን በቀዳሚነት ይዟል ።

በሁሉም ውድድሮች ከ900 በላይ ጎሎችን በማስቆጠር በአለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ሰው ፤ የዩቲዩብ ገጹን ባስተዋወቀ በ90 ደቂቃዎች ውስጥ 1ነጥብ 69 ሚሊየን ተከታዮችን በማግኘት አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል።

በሁሉም በማህበራዊ ትስስር ገጾችም አንድ ቢሊየን ተከታዮችን በማፍራት ቀዳሚው ሰው ነው።

Hola Media ሆላ ሚዲያ

ማስታወቂያ *******በየትኛዉም የዓለም ክፍል ከሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶ በባንካችን ስዊፍት ኮድ SINQETAA ወይም ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በሆኑት ሪሃ (Ria) እና ደሃብሺል...
02/01/2025

ማስታወቂያ
*******

በየትኛዉም የዓለም ክፍል ከሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶ በባንካችን ስዊፍት ኮድ SINQETAA ወይም ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በሆኑት ሪሃ (Ria) እና ደሃብሺል (Dahabshiil) በኩል የሚላክልዎትን የውጭ አገር ገንዘብ ከባንካችን ይቀበሉ፡፡

Maallaqa biyya alaa firaaf aantee keessan irraa karaa 'SWIFT Code' Baankii keenyaa (SINQETAA) ykn dhaabbilee daddabarsaa maallaqaa Idil-addunyaa ta’an 'Ria' fi 'Dahabshiil', isiniif ergame baankii keenyaan fudhadhaa.


  👉 ይሄ ከሃዲ ሆድ አደር ባንዳ፣ ግብፅን ስቃወም ቆይቶ መጨረሻ ላይ በግብፅ ፍርፋሪ ተታለው ሃገሩን ከጀርባ ስወጋ ቆይቶ አሁን ሳውዲ ለኢትዮጵያ መንግሥት አሰልፈው ሰጥታለች። 👉 ከህግ በላ...
09/12/2024



👉 ይሄ ከሃዲ ሆድ አደር ባንዳ፣ ግብፅን ስቃወም ቆይቶ መጨረሻ ላይ በግብፅ ፍርፋሪ ተታለው ሃገሩን ከጀርባ ስወጋ ቆይቶ አሁን ሳውዲ ለኢትዮጵያ መንግሥት አሰልፈው ሰጥታለች።

👉 ከህግ በላይ ማንም የለም‼️
👉 እና መሣይም ትመጣላችሁ‼️

የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!“አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን” ስንል የነዋሪዎቿን ህይወት እና አኗኗር ማሳመርንም የሚያካትት ነው። ለዚህ አንዱ ማሳያ የሆነው ለካሳንችስ ልማት ...
09/12/2024

የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!

“አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን” ስንል የነዋሪዎቿን ህይወት እና አኗኗር ማሳመርንም የሚያካትት ነው።
ለዚህ አንዱ ማሳያ የሆነው ለካሳንችስ ልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ የገነባነዉን ማዕከል ነዉ።

ዛሬ አገልግሎት የምናስጀምረው የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደር በውስጡ:-

• በ1200 መኖሪያ ቤቶች 6500 ነዎሪዎችን የያዘ መኖሪያ መንደር ነው።
• 1.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ የአስፋልት መንገድ አለው።
• ከ20 በላይ አውቶቡሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ተርሚናል አለው።
• በ2 ወር ጊዜ ዉስጥ የተገነቡ ከቅድም አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከነምገባ ማዕከሉ ይዟል።
• በ3 ሺፍት ለ270 እናቶች የስራ እድል የፈጠረ የእንጀራ መጋገርያ ፋብሪካ አለው።
• 500 አረጋዉያን እና አቅመ ደካሞችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል የምገባ ማዕከል አለው።
• በቀን 60 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው የዳቦ ፋብሪካ እና የዕህል ወፍጮዎችን ይዟል።
• ደረጃውን የጠበቀ የህጻናት መጫወቻ እና የህጻናት ማቆያ አለው።
• ⁠ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም አረንጓዴ ቦታዎችና መናፈሻዎች ተገንብተዋል።
• በቋሚ እና በጊዜያዊነት ለ1646 ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ሶሪያ ላለፉት 60 ዓመታት የተመራችዉ በአንድ ቤተሰብ የዉርስ ስልጣን ያዉም ፍፁም አምባገነን በሆኑ መሪዎች ነዉ።ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ መርህዎችን የተገበረች ፣ ነፃና ፍትሃዊ በሆነ ምርጫ በህዝ...
08/12/2024

ሶሪያ ላለፉት 60 ዓመታት የተመራችዉ በአንድ ቤተሰብ የዉርስ ስልጣን ያዉም ፍፁም አምባገነን በሆኑ መሪዎች ነዉ።
ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ መርህዎችን የተገበረች ፣ ነፃና ፍትሃዊ በሆነ ምርጫ በህዝብ የሚመረጥ ፓርቲ መንግስት የሚመሰርትባት ፣ በአምስት አመታት ልዩነትም ምርጫ የሚካሄድባት ፣ ፓርላማ ያላት፣ ነፃ የሆነ የዳኝነት አሰራርን የተገበረች፣ ከሁሉ በላይ ህዝቦቿ አምባገነኖችን ለመሸከም ፍቃደኛ የልሆኑባት የብዙሃን ሀገር ነች።

የሶሪያን እና የኢትዮጵያን መንግስት የሚያመሳስላቸዉ ምንም አይነት ጉዳይ የለም።

በዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ላይ ማሻሻያ ተደርጓል። በነፍስ ወከፍ ለአንድ ተማሪ በቀን ከነበረው 22 ብር ወደ 100 ብር አድጓል።
08/12/2024

በዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።

በነፍስ ወከፍ ለአንድ ተማሪ በቀን ከነበረው 22 ብር ወደ 100 ብር አድጓል።

ገስግስ በዘረጋኸው የብልፅግና መዳረሻ ጎዳናአላማ ያለው እንዲህ ይሄዳል። መዳረሻውን የሚያውቅ መሪውን ይዞ በጎዳና ይገሰግሳል። መዳረሻውን የማያውቅ ሁላ እሱን መከተል ይፈራል። ደፋር እና አዋ...
08/12/2024

ገስግስ በዘረጋኸው የብልፅግና መዳረሻ ጎዳና

አላማ ያለው እንዲህ ይሄዳል። መዳረሻውን የሚያውቅ መሪውን ይዞ በጎዳና ይገሰግሳል። መዳረሻውን የማያውቅ ሁላ እሱን መከተል ይፈራል። ደፋር እና አዋቂ ብሎም ማገናዘብ የሚችል ብቻ ነው ያንተን የብልፅግና ሞተር ሊሳፈር የሚችለው። ሞተርህ ሃይለኛና ለኢትዮጵያ ብርሃን የሚሆን ነውና ንዳው ዝምብለህ፣ መንገዱም ያንተው ነው፣ መሪውንም የጨበጥከው አንተው ነህ። ማን በመንገድህ ቆሞ ያስቆመሃል? ማንም አያስቆምህ!

ኢትዮጵያ ሶሪያ አይደለችም !አንዳንድ ውጪ ቁጭ ብለው ኢትዮጵያ ለዓመታት የማተራመስ ተልዕኮ ይዘው በተደጋጋሚ ብዙ ዋጋ ያስከፈለንን ሙከራ ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ቋንቋ ሚናገሩ ጠላቶቻችንና የጠላቶ...
08/12/2024

ኢትዮጵያ ሶሪያ አይደለችም !

አንዳንድ ውጪ ቁጭ ብለው ኢትዮጵያ ለዓመታት የማተራመስ ተልዕኮ ይዘው በተደጋጋሚ ብዙ ዋጋ ያስከፈለንን ሙከራ ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ቋንቋ ሚናገሩ ጠላቶቻችንና የጠላቶቻችን ተላላኪዎች ኢትዮጵያን እንደ ሶሪያ እንደትሆን ያላረጉት ክፋት፣ ያልሞከሩት መንገድ፣ ያልፃፉት ፅሁፍ ያልደገፉት ሽፍታ፣ ያልከፈቱት ሚዲያ፣ ያልጮኹበት የምዕራቡ ኤምባሲ የለም። ዛሬም የአሳድን መውደቅ ተከትሎ ለኢትዮጵያ ያላቸውን እኩይ ምኞት በአደባባይ ሲገልፁ እያየን ነው።

ኢትዮጵያ ግን እንደተመኙት ሶሪያን አልሆነችም ወደ ፊትም አትሆንም፤ ጠላቶቻችን ባይዋጥላቸውም ኢትዮጵያ እስከነ ተላላኪዎች የፈጠሩባት ፈተናዎቿ ዓለም እየመሰከረው እንዳለው፣ በአይን እንደሚታየው GDPዋ በ5 ዓመት 80 ቢሊየን ዶላር ወደ 205 ቢሊየን ዶላር ተመነደገ የአፍሪካ 5ኛ ትልቁ ኢኮኖሚ ሆነ፤ አዲስ አበባ የሶሪያዋን ፍርስራሽ ከተማ አሊፖን ሳይሆን እንደ ስሟ አዲስ አበባ 🏵️ ሆነች፣ ስንዴ ምትለምን ሳይሆን በሚሊየን ቶኖች ትርፍ አምራች ሆናለች፤ የጦር ሃይሏ ከጥቂት 10ሺዎች ወደ ፍፁም ኢትዮጵያዊነትን የታጠቀ በአፍሪካ በብዛቱም ሆነ በጥራቱ አንደኛ የእግረኛ ጦር ሀይልነት ተመነደገ፤ ተላላኪዎች ሊያስቆሙት የተዋደቁለት ህዳሴው ግድብ 200ኪ.ሚ ባህር አንጣሎ ይዞ በኩራት በውበት " ኑ " እያለ የሚጣራ የአፍሪካ ታዕምረ ምህንድስና ሆኖ 97% ተገባዷል... ብዙ ማለት ይቻላል።

ነገሩን ለማሳጠር የገዛ ሀገሩን ሶሪያ ለማድረግ የተጋው ተላላኪ ፈረሰ እንጂ ኢትዮጵያ የቀጠናው ልዕለ ሀያል የአፍሪካ ኩራት ሆና ከየትኛውም ዘመኗ በላይ ጠንክራ መጥታለች፤ እርግጥ ነው እንደዚሁ የኢትዮጵያን ሶሪያ መሆን ሚመኙ አካላት በየጢሻው ሚፈጥሯቸው ፈተናዎች አሉ፤ ነገር ግን እሱም ቢሆን የጥቂት ግዜ ጉዳይ ነው የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተላላኪዎች ሚዲያ ላይ ብቻ መቀረታቸው አይቀርም።

ባይሆን የአሳድ እጣ ሚጠብቀውን ኢትዮጵያ ባህር አሳጥቶ ህዝቡን የመከራ ቋት ውስጥ 33ዓመታት ቆልፎ የሚገኘው አምገነን ገዢ ስለሆነ ባህሩን ለኢትዮጵያ መልሶ እንደ አሳድ ሳይረፍድበት መስመር እንዲይዝ ቢመክሩት ጥሩ ነው። (ላኪያቸው ስለሆነ)

በተረፈ አዎ ኢትዮጵያ ሶሪያ አይደለችም!

ሰላምና እድገት ልምላሜ ለእናት ኢትዮጵያ ! 🇪🇹

  ኮሪደር ውጤቱ ደሰ የሚል ገፅታ ለከተሞች ይፈጠራል🇪🇹ሌሎች ክልል ከተሞችም አንዲሁ በልማቱ መፎካከር መጀመር አለባችሁ በበጎነት በማየት 🇪🇹🇪🇹
08/12/2024

ኮሪደር ውጤቱ ደሰ የሚል ገፅታ ለከተሞች ይፈጠራል🇪🇹

ሌሎች ክልል ከተሞችም አንዲሁ በልማቱ መፎካከር መጀመር አለባችሁ በበጎነት በማየት 🇪🇹🇪🇹

19ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል በውቢቷ አርባ ምንጭ ከተማ በደማቅና እና ባማረ ሁኔታ አክብረናል።የዓመት ሰው ይበለን። አርባምንጮች እናመሰግናለን!ፈጣሪ ኢትዮ...
08/12/2024

19ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል በውቢቷ አርባ ምንጭ ከተማ በደማቅና እና ባማረ ሁኔታ አክብረናል።
የዓመት ሰው ይበለን።
አርባምንጮች እናመሰግናለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!!
አዳነች አቤቤ

ሞተርህ ለኢትዮጵያ ብርሃን የሚሆን ነውና ንዳው ዝምብለህ፣ መንገዱም ያንተው ነውሹፌሩ በትክክለኛው መንገድ ላይ እያሽከረከረ ነው። የብልፅግናው ሞተር አስተማማኝ እና ጠመዝማዛውን መንገድ በብቃ...
08/12/2024

ሞተርህ ለኢትዮጵያ ብርሃን የሚሆን ነውና ንዳው ዝምብለህ፣ መንገዱም ያንተው ነው

ሹፌሩ በትክክለኛው መንገድ ላይ እያሽከረከረ ነው። የብልፅግናው ሞተር አስተማማኝ እና ጠመዝማዛውን መንገድ በብቃት ማለፍ የሚችል ነው። ደፋር እና አዋቂ ብቻ ነው ያንተን የብልፅግና ሞተር ሊሳፈር የሚችለው። ገስግስ አለቃ።

በደ/ጺዮን የሚመራው ህገ ወጥ ቡድን  ህዳር 29 / 2017 ዓ.ም በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ የሀሰት ክስ ለማሰማት ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም ፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ግን ምንም አይነት  የድጋፍም ሆ...
08/12/2024

በደ/ጺዮን የሚመራው ህገ ወጥ ቡድን ህዳር 29 / 2017 ዓ.ም በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ የሀሰት ክስ ለማሰማት ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም ፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ግን ምንም አይነት የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ እንደማይፈቅድ በደብዳቤ አሳውቋል።

08/12/2024
የ20ኛ የኢትዮጵያ ብሔር  ብሔረሰቦች  ቀን በማዕከላዊ ክልል እንድታዘጋጅ  ተወሰነ ። የማዕከላዊ  ኢትዮጵያ ክልል  ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ...
08/12/2024

የ20ኛ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በማዕከላዊ ክልል እንድታዘጋጅ ተወሰነ ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንቴና ፈቃዱ የእርክብክብ ተደርገዋል ።

Address

Hossana

Telephone

+12483746559

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hola Media ሆላ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hola Media ሆላ ሚዲያ:

Videos

Share