18/03/2022
#የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ሁኔታ
የሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን መምህር የሆኑት አብዲሳ ዘርዓይ (ዶ/ር) አገሪቷ በጦርነት እና በግጭት ውስጥ ያለች ከመሆኑ አንጻር እና ፖለቲካው ዋልታ ረገጥ በመሆኑ እውነት አደጋ ላይ ወድቋል ይላሉ።
የመንግሥት ሚድያዎች ነጻ እና ሙያዊ ሥነ ምግባርን በጠበቀ ሁኔታ ሳይሆን እንደ ፕሮፓጋንዳ ማሽን በመንግሥት በኩል የሚነገረውን ብቻ ከፍ አድርጎ ማሰማት በስፋት ይታያል ሲሉ ያክላሉ።
በግል የሚንቀሳቀሱትም ቢሆኑ፣ የሚደግፉትን ወይንም የቆሙለትን አካል በጭፍን ደግፈው ስለሚሰሩ እውነት እና ሐቀኝነት (Objectice and Truth) አደጋ ላይ ወድቀዋል ይላሉ አብዲሳ (ዶ/ር)።
የመንግሥት ሚድያዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመንግሥት በጀት የሚንቀሳቀሱ መሆናቸው፣ መንግሥት በሚሾማቸው ሰዎች ስለሚተዳደሩ መንግሥት እንደሚፈልገው ብቻ እንደሚዘግቡ ያስረዳሉ።
"ነጻ የሆነ ጋዜጠኛ ቢኖር እንኳ ራሱ ያየውን እና ያረጋገጠውን ነገር አምጥቶ ለመስራት ያለው እድል ጠባብ ነው፤ ቢሰራ አየር ላይ እንደሚውል ዋስትና የለውም። ስለዚህም የተሰጠውን አቅጣጫ ብቻ ጠብቆ እንዲሰራ ይገደዳል።"
ይህ ደግሞ መገናኛ ብዙኃን ተዓማኒነት እና ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ያደርጋል። ከዚህም አልፎ ኅብረተሰቡ እውነትን በትክክል ተረድቶ ትክክለኛ አቋም እንዳይዝ፣ ትክክለኛ ውሳኔ እንዳይወስን እንዲሁም ተጠያቂነት ማስፈን እንዳይችል ያደርጋ ይላሉ አብዲሳ ዘርዓይ (ዶ/ር)።
'ፖለቲካው መስተካከል አለበት'
መገናኛ ብዙኃን በአንድ አገር ፖለቲካል ኢኮኖሚ ውስጥ የሚበቅል ነው የሚሉት የሚድያና ኮምዩኒኬሽን ምሁሩ፣ ይህ ሁኔታ እስካልተቀየረ ድረስ ሚድያውን መቀየር እንደማይቻል ያስረዳሉ።
የሚድያው ምኅዳር ውስጥ ያሉ ችግሮች እንዲፈቱ ዋልታ ረገጥ የሆነው ፖለቲካ ወደ መካከል መምጣት እና መስተካከል መቻል አለበት ሲሉም ያክላሉ።
"አንድ ሚድያ ወይንም ደግሞ አንድ ጋዜጠኛ ታዳሚ ለማግኘት ጆሮን የሚስብ ነገር ማቅረብ አለበት። አሁን ባለው የአገሪቱ ሁኔታ ደግሞ ታዳሚው ዋልታ ረገጥ የሆነ ፖለቲካ ሰለባ ስለሆነ ጋዜጠኛው ወይንም ደግሞ ሚድያው የጋዜጠኝነትን ሥነ ምግባር ተከትሎ ለመስራት ይቸገራል። ስለዚህም ከጋዜጠኛ ብዙም የምንጠብቀው ነገር ላይኖር ይችላል" ይላሉ አብዲሳ (ዶ/ር)።
የሚድያ ባለሙያው ኤልያስ በበኩሉ፣ በመንግሥት በጀት የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙኃን የኢዲቶሪያል ነጻነታቸውን ጠብቅው እንዲሰሩ መፈቀድ አለበት ይላል።
የሚድያ ማኅበራት ደግሞ የሚድያ ነጻነት እንዲኖር ጫና ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም ሚድያዎች ራሳቸው እና የሚድያ ልማት ላይ የሚሰሩ ተቋማት የጋዜጠኞች የሙያ ብቃት ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት ሌላው አስፈላጊ ነገር መሆኑን ይጠቅሳል።
በዚህ ዘገባ ላይ የተለያዩ የመንግሥት እና ከመንግሥት ጋር ቅርበት ያላቸው የመገናኛ ብዙኃንን ሐሳብ ለማካተት ብንሞክርም ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ለኢትዮጵያ መገናና ብዙኃን ባለሥልጣን ኃላፊዎችም በተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ብናደርግም አግኝተን ሐሳባቸውን ማካተት አልቻልንም።
©bbc
http://t.me/dove_broadcast
http://t.me/dove_broadcast
Any informations,entertianments and provide by this channel. http://t.me/dove_broadcast "Dove_broadcast" on YouTube https://youtube.com/chan Solomon belayneh📝 👉 for comment 👇