27/11/2024
የሳኡዲ ዜጋ የሆነው ዶክተር ሰኢድ አልቃህጣኒ ይባላል
ለአስቸኳይ ቀዶ ጥገና ወደ ሆስፒታል እንዲመጣ ጥሪ ይደረግለታል እሱም እየተቻኮለ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል ነገር ግን የተወሰኑ ደቂቃዎች ዘግይቶ ስለነበር ቀዶ ጥገና የሚያደርገው ልጅ አባት ዶክተሩ ላይ በሃይለኛው እየጮሀ ይሰድበው ጀመር " ልጅህ ቢሆን የታመመው አታረፍድም ነበር " እያለ ይጮህበታል።
ዶክተሩም ስድብ እና ጩሀቱን ከምንም ሳይቆጥር ቀዶ ጥገና ክፍል ይገባ ለረጅም ሰአት በተደረገ ኦፕሬሽን ታማሚውን በተሳካ ሁኔታ ጨርሶ ይወጣል የታማሚው አባትም ይደሰታል ነገር ግን ዶክተሩ ቀዶ ጥገናውን ጨርሶ እየተቻኮለ ወደቤቱ ይመለሳል።
በእዚህ ጊዜ አብረውት የነበሩት የዶክተሩ ረዳቶች " ዶክተሩ ልጁ ሙቶበት የልጁን አስክሬን ቤት አስቀምጦ ነው ያንተን ልጅ ለማዳን የመጣው " ይሉታል :'( አንዳንዴ ሰዎች በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ሳናውቅ ለመፍረድ አንቸኩል ።
ከማሕበራዊ ሚዲያ የተገኘ