B̤e̤r̤e̤g̤e̤n̤a̤-A̤b̤a̤y̤e̤ M̤e̤d̤i̤a̤

B̤e̤r̤e̤g̤e̤n̤a̤-A̤b̤a̤y̤e̤ M̤e̤d̤i̤a̤ Kulito

የበርካታ በሽታ ፈዋሽና የብዙ ታሪክ ባለቤት የሆነዉ የአርቶ ፍል ዉሃ በሰንሰለታማዉ ሞቶቆማ ተራራ ከላይ በኩል ከብቶች የሚዉሉበት የተንጣለለዉ እጅግ ዉብ የሆና ሜዳማ ስፍራ በተጨማሪም አሩንጓ...
25/02/2024

የበርካታ በሽታ ፈዋሽና የብዙ ታሪክ ባለቤት የሆነዉ የአርቶ ፍል ዉሃ በሰንሰለታማዉ ሞቶቆማ ተራራ ከላይ በኩል ከብቶች የሚዉሉበት የተንጣለለዉ እጅግ ዉብ የሆና ሜዳማ ስፍራ በተጨማሪም አሩንጓዴ ፓርኩ ማራኪ አድርጓታል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ክርስቲያን ሙስሊሙ መከባበር በጥምቀት በዓል
20/01/2024

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ክርስቲያን ሙስሊሙ መከባበር በጥምቀት በዓል

ከፌዴራልና ከክልል እንዲሁም ከአጎራባች በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶች አቀባበል በስንፖዚያም።ሀበይ ወገሬቲን አሜቴንተ እንኳን ደህና መጡ
13/01/2024

ከፌዴራልና ከክልል እንዲሁም ከአጎራባች በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶች አቀባበል በስንፖዚያም።
ሀበይ ወገሬቲን አሜቴንተ

እንኳን ደህና መጡ

ዕድገቱን የሀላቢሳን ቋንቋና ባህል ወጉን ማመር ያደረገዉ ወጣት ሸምሰዲን አዳም በቅፅል ስሙ የሀላባዉ ሐጫሉ ይሉታል።ከልጅነቱ እስከ ወጣትነት በዚህ በትንሽ ዕድሜዉ የሀላብኛን ቋንቋ በተለያዩ ...
02/01/2024

ዕድገቱን የሀላቢሳን ቋንቋና ባህል ወጉን ማመር ያደረገዉ ወጣት ሸምሰዲን አዳም በቅፅል ስሙ የሀላባዉ ሐጫሉ ይሉታል።
ከልጅነቱ እስከ ወጣትነት በዚህ በትንሽ ዕድሜዉ የሀላብኛን ቋንቋ በተለያዩ መልክ በመዝፈን በጥቂት ጊዜያት ዉስጥ ሀላባን ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም እንዲታወቅ አድርጎታል።
....ጅማሬወቹ
ያኔ ትምህርት ቤቶች መዝግያ ዕለት የእሱ ግጥም አልፎም ድራማዉ የት/ቤቱ ድምቀት ነበር በየክፍሉ ከ1-3ኛ ደረጀ የወጡ ተማሪዎች የተለያዩ ሽልማቶችን ይዘዉ ሲመለሱ እሱ ግን ከወላጆች የተሸለመዉን ብር ይዞ ነበር ሰፈሩን የሚመለሰዉ
......በዚህም አልተዋም ለዚህ ደረጃ ያበቀዉም የት/ቤቱ ክነ-ጥበብ ክበብ ነበር
ወጣቱ ልጅ ጉዞዉን ቀጥሏል የሀላባን ባህል ወደፊት ለማሳደግ ገጣሚዉ እራሱ ሆኖ ቅንብርም እራሱ የሚገርመዉ ዜማዉም እራሱን አርግቶ ግስጋሴዉን ወደ ፊት አርግቷል።

ከ'ሀይ በራን'ችሎተኖ ጀምሮ
አሰምተሃል የቄረንሶን ህዝብ እሮሮ
አሁንም እያደመቃ ነዉ በሴራ ዋዜማ
ሴራዉን አስመልክቶ ለቋል አንድ ዜማ
በዕድሜ ትንሹ በስራዉ አንጋፋ
ገነ ትሰራለህ ሀላቢሳ እንዲሰፋ

የወደፊቱ ብቻ አይደለም ከኋላም ደርሶ ወደፊት መምጣት እንደሚቻል ጭምር ያስተማርከን ጀግና ወጣት ሸምሰዲን አዳም በርታ ለማለት ወደድኩኝ።

አመሰግናለዉ🙏
ታህሳስ 23/2016 ዓ/ም 🇧 🇦

እንደ በርበሬዉ ጣፋጮች በሴራዉ
31/12/2023

እንደ በርበሬዉ ጣፋጮች በሴራዉ

የሴራዉ (መንገሳ)በዓል በዛሬዉ ዕለት በዌራ ዲጆ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዉሏል።
27/12/2023

የሴራዉ (መንገሳ)በዓል በዛሬዉ ዕለት በዌራ ዲጆ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዉሏል።

የሴራዉ ድምቀት
25/12/2023

የሴራዉ ድምቀት

የሀላባ ሴራ በዓል ዋዜማ ድባብ
25/12/2023

የሀላባ ሴራ በዓል ዋዜማ ድባብ

የሴራ በዓል ድባብ 🇪🇹🇪🇹
25/12/2023

የሴራ በዓል ድባብ
🇪🇹🇪🇹

የሀላባ ሴራ(መንገሳ)በዓል ቅድመ ዝግጅት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የሀላባ ተወላጆች በዚህ መልኩ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።ሀባይ ከዘማኔ ሀላቢ ሴሪ ከበጀተ ወገሬቲን ኢልሽሾሄኔታህሳስ 4/2016 ዓ/ም
14/12/2023

የሀላባ ሴራ(መንገሳ)በዓል ቅድመ ዝግጅት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የሀላባ ተወላጆች በዚህ መልኩ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።
ሀባይ ከዘማኔ ሀላቢ ሴሪ ከበጀተ ወገሬቲን ኢልሽሾሄኔ

ታህሳስ 4/2016 ዓ/ም

ከፊታችን በመጪዉ ጥር ወር በድምቀት ለሚከበረዉ የሀላባ ሴራ (መንገሳ)በዓል የቁሊቶ ከተማን በተለያዩ ባህሉን በሚገልፁ ቀለማት የማስዋብ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
12/12/2023

ከፊታችን በመጪዉ ጥር ወር በድምቀት ለሚከበረዉ የሀላባ ሴራ (መንገሳ)በዓል የቁሊቶ ከተማን በተለያዩ ባህሉን በሚገልፁ ቀለማት የማስዋብ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

የሀላባ ሴቶች ባህል አለባበስ
10/12/2023

የሀላባ ሴቶች ባህል አለባበስ

 #የሀላባ ቀዩ ዛላ በርበሬ ከማሳ ተሰብስቦ በአዉድማ ላይ🌶🌶🌶🌶 ዛላ በርበሬን ከማሳ በአግባቡ በመሰብሰብ የምርቱን ጥራት እንጠብቅ
08/12/2023

#የሀላባ ቀዩ ዛላ በርበሬ ከማሳ ተሰብስቦ በአዉድማ ላይ🌶🌶🌶🌶 ዛላ በርበሬን ከማሳ በአግባቡ በመሰብሰብ የምርቱን ጥራት እንጠብቅ

በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ የሙዳ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የገቢ አሰባሰብ በዛሬዉ ዕለት እየተካሄዳ ይገኛል።በገቢዉ አሰባሰብ የዞኑ አመራር የከተማ አስተዳደሩን ጨምሮ የ3ቱም ወረዳ አስተባባሪዎች ተገ...
02/12/2023

በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ የሙዳ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የገቢ አሰባሰብ በዛሬዉ ዕለት እየተካሄዳ ይገኛል።

በገቢዉ አሰባሰብ የዞኑ አመራር የከተማ አስተዳደሩን ጨምሮ የ3ቱም ወረዳ አስተባባሪዎች ተገኝተዉ በይፋ አስጀምሯሉ።

የሀላባ ሴራ ባዓል(መንገሳ)ለሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ባዓል ነዉ።ይህ የዘመን መለወጫ ባዓል በብሔረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶ በየዓመቱ በወረዳዎች ደረጃ በተጨማሪ በየሁለት ዓመቱ በዞ...
30/11/2023

የሀላባ ሴራ ባዓል(መንገሳ)ለሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ባዓል ነዉ።
ይህ የዘመን መለወጫ ባዓል በብሔረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶ በየዓመቱ በወረዳዎች ደረጃ በተጨማሪ በየሁለት ዓመቱ በዞን አቀፍ ደረጃና በተለያዩ ዉጪ ሀገራት የሀላባ ብሔረሰብ ተወላጆች ባሉበት በድምቀት ይከበራል።

በዚህ ባዓል አከባበር ስነስርዓት ላይ በተለያዩ ሀላፍትና በመንግስት ተቋማት የሚሰሩ የሀላባ ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች ከተለያዩ አከባቢና ከአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በመገኛት በባዓሉ ይታደማሉ።

በባዓሉ ዕለትም ብሔረሰቡን የሚገልጹ የተለያዩ ዜማዎች፣ዉዝዋዜ፣ያከ፣የእናቶች ቃላ፣የፈረስ ግልብያና ሌሎች የተለያዩ ትዕይንቶች ይካሄዳሉ።

ሀባይ ወገሬቲን ኢልሺሾህኔ 2016 ዘማን ዶረንሻ
Beregena Abaye

የዌራ ዲጆ ወረዳ አስተዳዳር አቶ አብዲ አደም ከሰልጣኝ አመራር ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሻዋ ዞን ሎሚ ወረዳ የኢጀሬ የስንዴ ክላስተር ማሳ ጉብኝት ሲያደርጉ በፎቶተሞክሮወችን በመስ...
15/10/2023

የዌራ ዲጆ ወረዳ አስተዳዳር አቶ አብዲ አደም ከሰልጣኝ አመራር ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሻዋ ዞን ሎሚ ወረዳ የኢጀሬ የስንዴ ክላስተር ማሳ ጉብኝት ሲያደርጉ በፎቶ

ተሞክሮወችን በመስፋት ግብርና ወደ እንዱስትሪ እናሸጋግራለን
-OROMIA the real Agricultural transformation

ባረክ አለህ ለኩማ ወባረክ አለህ ለኩማ ወጀሚዓ በይነኩማ ፍል ከይርመብሩክ ወንድም ኑዘፈ መሀመድኑርና እህት መዲና ትዳራችሁ የዓሊና የፈጥማ ይሁን።
30/09/2023

ባረክ አለህ ለኩማ ወባረክ አለህ ለኩማ ወጀሚዓ በይነኩማ ፍል ከይር
መብሩክ ወንድም ኑዘፈ መሀመድኑርና እህት መዲና ትዳራችሁ የዓሊና የፈጥማ ይሁን።

በማዕከላዊ እትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ በድንች ሰብል የሚትታወቅ እንደ ስሟ አቶቲ በአማርኛ ምርታማ ወረዳ ናትበወረዳዋ የድንች ሰብል በዚህ ጊዜ የደረሰበት ደረጃ ይህን ይመ...
22/09/2023

በማዕከላዊ እትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ በድንች ሰብል የሚትታወቅ እንደ ስሟ አቶቲ በአማርኛ ምርታማ ወረዳ ናት
በወረዳዋ የድንች ሰብል በዚህ ጊዜ የደረሰበት ደረጃ ይህን ይመስላል
መስከረም 11/2016 ዓ/ም

ሰቦም ቆካንቴ ቡሼ እንኳን ደስ አለሽ ጠንካራዋ እህታችንየውማንስ ፓወር  #ወርልድና ኤሮብክስ ማሰልጠኛ ክለብ  የምረቃ ፕሮግራም  መስከረም /6/2016 ዓ.ም
18/09/2023

ሰቦም ቆካንቴ ቡሼ እንኳን ደስ አለሽ ጠንካራዋ እህታችን
የውማንስ ፓወር #ወርልድና ኤሮብክስ ማሰልጠኛ ክለብ የምረቃ ፕሮግራም መስከረም /6/2016 ዓ.ም

የሀላባ ዞን ዉሃና መዕድን ም/ል ሀላፊ የነበረዉ እንጅነር ከይሩ መሀመድ በማዕከላዊ እ/ያ ክልል የመንገድ መሠረተ ልማት ሀላፊ ሆነዉ ተሹሟል።መልካም የስራ ዘመን
09/09/2023

የሀላባ ዞን ዉሃና መዕድን ም/ል ሀላፊ የነበረዉ እንጅነር ከይሩ መሀመድ በማዕከላዊ እ/ያ ክልል የመንገድ መሠረተ ልማት ሀላፊ ሆነዉ ተሹሟል።
መልካም የስራ ዘመን

ከልዩ ወረዳ ጀምረህ በተመደብክበት ሴክተር ሁሉ ዉጤታማ ስራ እየሰራህ አሁንም ዳግም ህዝብህን በታማኝነት ለማገልገል በቅታሃልወንድምዓለም ጀማል ሚሃሌ የዌራ ወረዳ ም/አስተዳደርና ግ/ጽ/ቤት ሀ...
30/08/2023

ከልዩ ወረዳ ጀምረህ በተመደብክበት ሴክተር ሁሉ ዉጤታማ ስራ እየሰራህ አሁንም ዳግም ህዝብህን በታማኝነት ለማገልገል በቅታሃል

ወንድምዓለም ጀማል ሚሃሌ የዌራ ወረዳ ም/አስተዳደርና ግ/ጽ/ቤት ሀላፊ ሆነዉ ተሹሟሉ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልህ እመኛለዉ

ከህገሜዎች መንደር ከቆንጆዎች መፍለቂያ  #ሀላባ
24/08/2023

ከህገሜዎች መንደር ከቆንጆዎች መፍለቂያ #ሀላባ

በማዕከላዊ ክልል ሀላባ ዞን ዋነ ከተማ ቁሊቶ በወፍ በረራ
21/08/2023

በማዕከላዊ ክልል ሀላባ ዞን ዋነ ከተማ ቁሊቶ በወፍ በረራ

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ10ሺ ሜትር 3ኛ በመዉጣት የነሃስ ሜዳልያ አስገኝቷል ለሀገሬ እንኳን ደስ አለሽ Congratulation
20/08/2023

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ10ሺ ሜትር 3ኛ በመዉጣት የነሃስ ሜዳልያ አስገኝቷል ለሀገሬ እንኳን ደስ አለሽ Congratulation

ዶ/መሐመድ ኑሪዬ በም/ርዕሰ መስተዳድር መዕረግ የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊና ወ/ሮ መነቴ ሙንድኖ የክልሉ ም/ቤት ም/አፈጉባኤ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለዉ
20/08/2023

ዶ/መሐመድ ኑሪዬ በም/ርዕሰ መስተዳድር መዕረግ የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊና ወ/ሮ መነቴ ሙንድኖ የክልሉ ም/ቤት ም/አፈጉባኤ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለዉ

ፕሮጄክቶችን ጀምሮ በፍጥነት የመጨረስ ልምድ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ።በዌራ ወረዳ በመንግስትና በግብረሠናይ ድርጅቶች የተከናወኑ መሠረተ-ልማቶች ዛሬ ተመርቀዋል።----------...
06/09/2022

ፕሮጄክቶችን ጀምሮ በፍጥነት የመጨረስ ልምድ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ።
በዌራ ወረዳ በመንግስትና በግብረሠናይ ድርጅቶች የተከናወኑ መሠረተ-ልማቶች ዛሬ ተመርቀዋል።
--------------------------------------------
በምርቃት መርሀግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዌረ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድከማል ኑርዬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የተገባደደው የበጀት ዓመት ተገደን በገባንበት የህወሃት ጦርነት በተለያዩ አጀንዳዎች ተወጥረን ያሳለፍንበት ዓመት ቢሆንም እንደወረዳም እንደዞንም የተለያዩ መሠረተልማቶችን ጀምረን በፍጥነት መጨረስ የቻልንበት ነው ብለዋል።

ለአብነትም በላይኛው ሌንዳ በአልዲን ግብረሠናይ ድርጅት የተቆፈረውን ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ጨምሮ የዌራ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ግንባታ ፣ የሀማጣ ጤና ጣቢያ ግንባታና የተለያዩ መንገዶች ግንባታ በአጭር ጊዜ ተጠናቀው ለምረቃ መብቃታቸው በእጅጉ አስደሳች ነው ብለዋል።

የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር መሐመድ ኑርዬ በበኩላቸው እንኳን ለዚህ የስኬት ቀን አበቃን ያሉ ሲሆን ዛሬ ያስመረቅናቸው መሠረተ-ልማቶች የህዝባችን መሠረታዊ ችግሮች ለመቅረፍ በእጅጉ አንገብጋቢ ናቸው ብለዋል።

ከዚህ በፊት ፕሮጄክቶችን ጀምሮ በተያዘላቸው ጊዜ የመጨረስ ሁኔታ እምቢዛም እንዳልነበር የጠቀሱት ዋና አስተዳዳሪው እንደሀላባ ዞን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕሮጄክቶችን ፈጥኖ የመጨረስ ልምድ እየጎለበተ መምጣቱን ገልፀው ይህ በጎ ልምድ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ከሌላው አካባቢ በተለየ መልኩ የአልዲን ግብረሰናይ ድርጅት በሀላባ የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግርን ለመቅረፍ የጥልቅ ጉድጓድ ውሃ ቁፋሮ ፕሮጄክቶችን በጥሩ ሁኔታ እያከናወነ በመሆኑ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የህክምና ዘርፍ ሀላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃኑ የሀላባ ህዝብ በህብረተሰብ ተሳትፎ ሆስፒታልንና ሌሎች የልማት ሥራዎችን መሥራት የቻለ ህዝብ መሆኑን ገልፀው ዛሬ ለተመረቀው የሀማጣ ጤና ጣቢያ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የማሟላት ሥራ እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል።

በሀላባ ውስጥ በበርካታ ቀበሌያት ጥልቅ የውሃ ጉዶጓድ በማስቆፈር የሚታወቀው የአልዲን ግብረሰናይ ድርጅት ለሀማጣ ጤና ጣቢያ በኦክሲጂን አቅርቦት በኩል የተጠናከረ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

በመርሀግብሩ ማጠቃለያ ለተባዥ እንግዶችና ለፕሮጄክቱ ሥኬት አስተዋፅዖ ላደረጉ አካላት የሀላባን ባህል የሚያንፀባርቁ የተለያዩ የክብር ስጦታዎች ተበርክቷል።

መረጃዉ የሀላባ ቲቪ ነዉ

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2015 በጀት አመት ለመንግሥት ሥራዎች ማስፈፀሚያ እንዲሆን በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ቀርቦ የፀደቀውን 248,560,000 ብር በጀት በ...
24/08/2022

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2015 በጀት አመት ለመንግሥት ሥራዎች ማስፈፀሚያ እንዲሆን በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ቀርቦ የፀደቀውን 248,560,000 ብር በጀት በአራት ዋና ዋና የወጪ ርዕሶች ድልድሎ አድርጎ ለከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባለት አቀረበ።

የፋይናንስ ጽ/ቤቱ የ2015 በጀት አመት ለመንግሥት ሥራዎች ማስፈፀሚያ እንዲሆን በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት የፀደቀውን 248,560,000 ብር በአራት ዋና ዋና የወጪ ርዕሶች ደልድሎ አድርጎ ለከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባለት አቅርቧል።

መድረኩን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀሩና አህመድ የመሩ ስሆን የበጀት ድልድሉን የከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ረሻድ ኪያር ዘርዘር ባለ መልኩ አቀርበዋል።

በዚህም መሰረት

➜ለከተማ አስተዳደር ቋሚና ኮንትራት ሰራተኞች እንዲሁም በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃ ለተመደቡ ለመንግስት ተሿሚዎች ደሞዝ ብር 162,029,957.26(65.19%)

➜ለካፒታል ወጪዎች ብር 49,894,923.60(20.07%)

➜ለግዴታ ወጪዎች 16,070,440(6.47%)

➜ ለከተማዋ አስተዳደር ሴክተር መስሪያ ቤቶች ስራ ማስኬጃ 20,564,679.14(8.27%) ሆኖ የተደለደለ መሆኑን የጽ/ቤቱ ሃለፊ አቶ ረሻድ ኪያር ገልፀዋል።

➜ለበጀት አመቱ ከፀደቀው ጥቅል በጀት ዉስጥ ድጎማ 40,000,000 (16.09%) ብቻ ስሆን ቀሪዉ 208,560,000 (83.91%) ከከተማ አስተዳደሩ ከመደበኛ፣ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ከትምህርትና ከጤና ተቋማት ከሚሰበሰብ የዉስጥ ገቢ የምሸፈን በመሆኑ ገቢ አሰባሰብ ሥራ የበጀት አመቱ ቁልፍ አጀንዳ ልሆን እንደምገባም ኃላፊው አብራርተዋል።

አቶ ሃሩና አህመድ በበኩላቸው ሴክተር መስሪያቤቶቹ የተመደበላቸውን በጀት ከመቼውም ግዜ በላይ ወጪ ቆጣቢና ዉጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የከተማው ካብኔ አባለት በበጀት ድልድሉ ዙሪያ በርካታ ሃሳብ አስተያየቶችን አንስተው ሰፊ ውይይት ያደረጉ በተደረገው ውይይት ከመግባባት በመደረስና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።

ሃምሌ 18/2014 ዓ.ም ሀላባ ቁሊቶ

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር  በከተማዋ ውስጥ ቤት ለሌላቸው አቅመ ደካማ ቤተሰቦች አዳድስ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ በተለያዩ ቀጠናዎች ቤቶችን እያስጀመረ ይገኛል።ከተማ አስተዳሩ ከተለያዩ...
24/08/2022

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ውስጥ ቤት ለሌላቸው አቅመ ደካማ ቤተሰቦች አዳድስ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ በተለያዩ ቀጠናዎች ቤቶችን እያስጀመረ ይገኛል።

ከተማ አስተዳሩ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ባለሃብቶች ገንዘብ በማሰባሰብ በከተማዋ ውስጥ ለሚገኙ አቅመ ቤተሰቦች ቤት ለመስራት ዕቅድ የያዘ ስሆን በአሁን ሰዓት ዕቅዱን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

በዛሬው ዕለትም በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታገል ጌታቸው፣ በፓርቲው ጽ/ቤት የመንግስት ምክትል ተጠሪ አቶ ፈይሳ ሙንድኖ እንዲሁም ሌሎች የከተማና የቀበሌው አመራሮች በጫምቡላ ቀበሌ በመገኘት ለአንድ አቅመደካማ ቤተሰብ የቤት ግንባታ አስጀምረዋል።
መረጃዉ የቁሊቶ ከተማ መ/ኮ/ጽ/ቤት ነዉ

ሃምሌ 18/2014 ዓ.ም ሀላባ ቁሊቶ

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when B̤e̤r̤e̤g̤e̤n̤a̤-A̤b̤a̤y̤e̤ M̤e̤d̤i̤a̤ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share