17/04/2024
የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ በህገ-ወጥ የግብርና ግብዓቶች ዝውውር የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ተካሄደ
=====
ሚያዚያ 8/2016 የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ በህገ-ወጥ የግብርና ግብዓቶች ዝውውር የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ተካሄደዋል።
በመድረኩ ላይ የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሁሴን ሮባ በህገ-ወጥ የግብርና ግብዓቶች ዝውውር ላይ የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ ስሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
የዕሉቱን የምክክር መድረክ የመሩት የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳደርና ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀጂ ኑሪዬ እንደገለጹት የግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ ዕድገት ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጥራታቸውን የጠበቁ የግብርና ግብዓቶችን መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል።
የሀገሪቱ የጀርባ አጥነት የሆነው የግብርናውን ዘርፍ ኢኮኖሚ ለማዘመን እየተደረገ የሚገኘው ጥረት ላይ የህገወጥ የግብርና ግብዓት ዝውውርን መቆጣጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይ ምንጩ ያልታወቀና ተመሳሳይ ዘር፣ ጸረ አረምና ጸረ ተባይ ኬሚካሎች ስርጭት በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ላይ እያሳደረ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ህገ-ወጥ የግብርና ግብዓት ዝውውርን በጋራ መከላከል እንዳለባት አስገንዝበዋል።
አንድ ዘር ምርጥ ዘር የሚሆነው ሁሉንም የጥራት ደረጃዎችን አልፎ ካልመጣ በስተቀር ዘር ሊሆን እንደማይችል ገልጸዋል።
ጥራት ያላቸው ምርጥ ዘሮች፣ አግሮ ኬሚካልና የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ በማቅረብ የዘርፉን ግቦች የማሳካት ሀላፊነት ሁሉም መረባረብ እንደለበት ተናገረዋል።
በሀገራችን በየ ዓመቱ በመደበኛ የዘር ስርዓት በኩል የሚቀርበዉ የዘር መጠን ከ20 በመቶ እንደ ማይበልጥ ጥናቶች እንደሚያሳይ ገልጸዋል።
በዘር፣ በጸረ ተባይ ኬሚካል እና በአፈር ማደበሪያ በህገ ወጥ ዝውውር የተያዘ ግብዓት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚወረስበት ስርዓት መዘርጋት፣ እንደሚያስፈልግ በአጽኖት አስገንዝበዋል።
የግብርና ግብዓት ጥራት ጉድለትና ህገ ወጥነት ችግር ለመከላከል ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ በትኩረት መስረት እንደሚገባ አቶ ሀጂ ኑሪዬ አሳስበዋል።
በመድረኩ ላይ የዞን፣ የከተማና ወረዳዎች ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ የአራቱም መዋቅር የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ የዞኑ ግብርና መምሪያ የየዘርፉ ሀላፊዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት ተገኝተዋል።
በመጨረሻም የህገ-ወጥ የግብርና ግብዓት ዝውውር ግብረ-ሀይል በማቋቋም መድረኩ ተጠናቀዋል ሲል የዘገበው የዞኑ ኮሚኒኬሽን ነው