05/05/2022
❝...ጎንደርን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ከቱርክ ሀገር በግማሽ ቢሊዬን ብር የተገዛ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አምጥተው ይዘንባቸዋል...❞ ይህንን የተናገሩት የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ናቸው። ኧረ ስለ ኒኪሉየር መስሪያው ዩራኒየምም ሳይቀር አብረው አውርተዋል..?!.
የኒኩሊየር ጦር መሳርያ ያላቸው አካላት በጣም ጥቂት ሀያላን የሚባሉ ሀገራት ናቸው። እሳቸው የጠቀሷት ቱርክ እራሱ መሳርያው የላትም..! መሳርያውም እንደ ተራ AK47 በወደብ አምጥተህ የምትገጣጥመው አይደለም። ይህ ሰውየ እንዲህ አይነት ቅጥፈትን ያለምንም ማስረጃ በአደባባይ ሲናገር ስሰማው እጅግ በጣም ነው የተገረምኩት። ለዚህ የቅጥፈት ንግግሩ የክልሉ መጅሊስ መረጃው ደርሶት ከሆነ ክስ ከፍቶ ህግ ፊት ሊገትረው ይገባል። እንዲህ አይነት የወረደ እብለት በአደባባይ የሚናገር ከሆነ ሀይማኖቱን ለምዕመኑ እንዴት አድርጎ ነበር የሚያስተምረው? የሚለው ግን ያስገርማልም፥ ያስደነግጣልም..!