የሐሳብ ጽዋ/ብዕር እና ብርሃን Yehassab Tsewa/Bier Enna Berhan

የሐሳብ ጽዋ/ብዕር እና ብርሃን Yehassab Tsewa/Bier Enna Berhan This page is intended to share our writing products,ideas and any other art and wisdom related issues which webelieve is good to share with friends and all

ለሁለት ጌቶች መስገድ• • • ይህ ሁሉ ማስመሰል፣ይህ ሁሉ ማጎብደድ፣ይህ ሁሉ ማወደሥ፣     ይህ ሁሉ እግር መላስ፣ሕሊናን እንደከብት፣       የድልል ጨው ማላስ፤.  ..  ..   ..  ...
08/12/2018

ለሁለት ጌቶች መስገድ
• • •
ይህ ሁሉ ማስመሰል፣
ይህ ሁሉ ማጎብደድ፣
ይህ ሁሉ ማወደሥ፣
ይህ ሁሉ እግር መላስ፣
ሕሊናን እንደከብት፣
የድልል ጨው ማላስ፤. .. .. .. ..
(መንገሥ)፤
እና
(መርከስ)።. .. .. .. ..
ውስጥን አስጎንብሶ፣ ውጪን ለማቃናት
በግ-ብስብስ ኑሮ፣ በ"ኮልኮሌው" መቅናት
ምኞትን አንቅቶ፣ እምነትን ማስተኛት
በዘልማድ መስገድ፣ ለታይታ ቁስ ጣዖት
የኖሩትን መድገም፣ የሞቱትን መሞት . .
ጧት ሠርክ ቤተ አምልኮ፣ ምን ቢመላለሱ
በፀፀት ቢወድቁ፣ ትቢያ አፈር ቢልሱ
ፈውስ የለውም ቁስሉ፣እርኩስ ነው ድግሡ
ሁለት ጌቶች ማምለክ፣
በስጋም በነፍስም ሁለቴ ነው ክሱ . .
የመምሰልን ጣዖት፣ "ማልደው" ሳያፈርሱ።
• • •
መምሰልን የሚያህል ጣዖት ተሸክመን
መኾንን የሚያህል ታቦት እንይዝ ብለን
ዘውትር ጎንበስ! ጎንበስ! ልባችንን ጎብጠን
"ራስን" ለመቻል፣ ትከሻ እያነሰን!........
[[ሰይፉ ወርቁ.አ]]•••••
Photo ጆኒ ፀጋዬ.............

13/11/2018

ሚዛን
• • •
ስጋት አለን
ትጋት የለን!

30/06/2018

ሁል ጊዜ ፋሲካ!!!

30/06/2018

ክለሣ
የትናንቱ እንዳይረሳ!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሐሳብ ጽዋ/ብዕር እና ብርሃን Yehassab Tsewa/Bier Enna Berhan posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category