ክርስታናዊ ጋብቻ

ክርስታናዊ ጋብቻ ኢትዮጵያ

29/08/2023

🇪🇹🔊🔊✞✟

ዛሬ እስት እንወያይ   ? ሀሳቡን ያካፍሉን በሰፊው እመለሳለሁ
28/03/2023

ዛሬ እስት እንወያይ ? ሀሳቡን ያካፍሉን በሰፊው እመለሳለሁ

  ተመለሶዋል እንደምን ከረማችሁ ውድ ቤተሰቦቸ ተመልሻለሁ 💟💟
14/03/2023

ተመለሶዋል እንደምን ከረማችሁ ውድ ቤተሰቦቸ ተመልሻለሁ 💟💟

መልካም የትዳር ዘመን ይሁንላችሁ ።ይተቤ
26/05/2022

መልካም የትዳር ዘመን ይሁንላችሁ ።

ይተቤ

ውድ   ገጽ/page ተከታዮች በሙሉ እና ዘንድሮ ለምትጋቡ በገጻችን ስም መልካም የትዳር ዘመን እንድሆንላችሁ እንመኛለን ። እና ወቅቱን ያማከለ እና ለክርስቲያን በምመጥን መልኩ   እንደምንቀ...
03/05/2022

ውድ ገጽ/page ተከታዮች በሙሉ እና ዘንድሮ ለምትጋቡ በገጻችን ስም መልካም የትዳር ዘመን እንድሆንላችሁ እንመኛለን ።

እና ወቅቱን ያማከለ እና ለክርስቲያን በምመጥን መልኩ እንደምንቀርብ ቃል እንገባላችዋለን መልካም ቀን


 #እንኳን-የጌታችንና-የመዳንታችን-እየሱስ-ክርስቶስ-የትንሳኤ-በዓል-በሰላም-አደረሳችሁ          ክርስታናዊ ጋብቻ
23/04/2022

#እንኳን-የጌታችንና-የመዳንታችን-እየሱስ-ክርስቶስ-የትንሳኤ-በዓል-በሰላም-አደረሳችሁ

ክርስታናዊ ጋብቻ

13/04/2022

ሼር

• የተወለድነው በሌሎች ሰዎች እርዳታ ነው፡፡
• ስማችንን የተቀበልነው ሌሎች ሰዎች ባወጡልን መሰረት ነው፡፡
• የገቢ ምንጫችን የሚመጣው ከሌሎች ሰዎች ነው፡፡
• ክብርና እውቅና የሚሰጡን ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
• ገላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠቡን ሌሎች ሰዎች ናቸው፣ ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጥቡንም ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
• ከዚህ አለም ስንሰናበት ቤታችንና ንብረታችን በሌሎች ሰዎች ይወሰዳል፡፡
• እጃችንን ይዘው በመደገፍ መራመድ ያስለመዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው፣ በመጨረሻም እጃችንን ይዘው በመደገፍ የሚያራምዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
• በመወለዳችን ምክንያት በደስታ የደገሱና የበሉት ሌሎች ሰዎች፣ ስንሞትም በኃዘን የሚደግሱና የቀብር ስርአታችን የሚከናወነው በሌሎች ሰዎች ነው፡፡

ይህ ሁሉ እውነታ እያለ “ነኝ” እና “አለኝ” በምንለው ነገር የምንመካበት ጉዳይ አይገባኝም፡፡ እስቲ ያወሳሰብናትን ሕይወትን ቀለል እናድርጋትና ለመከባበርና ለመዋደድ ቅድሚያን በመስጠት እንኑር፡፡

Dr Mehret debeb

 #ክርስቶስ-ገላጭ_ወይስ_እራሳችን_ገላጭ?✔በዚህ ዘመን ብዙ ክርስቲያን በጋብቻው ጌታን /ክርስቶስን ሳይሆን  #ስሜቱን ሰገልጥ ማየት የተለመደ ሆናል ። ሰሞን እንደየነው ወድማችን አገልጋይ በ...
07/04/2022

#ክርስቶስ-ገላጭ_ወይስ_እራሳችን_ገላጭ?

✔በዚህ ዘመን ብዙ ክርስቲያን በጋብቻው ጌታን /ክርስቶስን ሳይሆን #ስሜቱን ሰገልጥ ማየት የተለመደ ሆናል ። ሰሞን እንደየነው ወድማችን አገልጋይ በሰርጉ ላይ ሲጨፍር ታይቷል በሚያዘጋጀው ላይ ቀርበው ስያሻቃብጥ አይታችኋል ብየ እገምታለሁ በቅዱስ መድረክ ቆሞ እያገለገ ግን የአለም ጥበብ አድናቅ ነው ። እናል ወገኖቼ በዚህ ዘመን የአብዘኛው አገልጋዮች ጋብቻ ክርስቶስ ገላጭ አደለም ከነአለባበስ

✅ወድ የዚህ #ገጽ-ተከታዮች እስት እናንተም አይታችሁ የታዘባችሁትን ነገር አካፈሉን

 #በጣም-የተመቼኝ-መልክት ተባሬክ ወንድሜ
31/03/2022

#በጣም-የተመቼኝ-መልክት ተባሬክ ወንድሜ

# #ተለከፍኩ...ምን ላድርግ

#እስቲ የዝማሬ ምንጭ የሆነው በእኔ በባሪያው ውስጥ ሳይንቀኝ ስላኖራቸው ዝማሬዎች ሀሳብ ላጋራቹ።አሁን አሁን ሳስተውል መዝሙሮቼ በአብዛኛው ማለት ይቻላል ስለ ህልውናው እና በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ስለሚተረከው የእግ/ር ክብር ስለሆነው ስለ እየሱስ ክርስቶስ ከሆነ ሰንብተዋል😍😭።ምን ላድርግ ብላቹ ነው ምን አይነት ልክፍት እንደያዘኝ እንጃልኝ ከነዚህ ህያው ርዕሶች ዞር እንዳልል ተሰፍቼ ቀርቻለው🙏።አንዳንድ ወገኖች ወጣት አይደለህ እንዴ ሞቅ ያለ ዝማሬ በደንብ አርገ ካልከተፍክ😉 አትወጣም አትታወቅም ያለዚያ ማንም አይፈልግህም ይሉኛል😗። እንደዚህ እያላቹ ለእኔ አስባቹ ለተጨነቃቹ ይኸው መልሴ። ሞቅ ያለ ዝማሬ ላላቹኝ እኔ ባለሁበት አለም አስቀድሞም በህልውናው ግለት ሞቆኛል አልቀዘቀዝኩም ሌላ እሳት አያስፈልገኝም። ሌላው ደግሞ አትወጣም አትገለጥም ላላቹኝ ቀድሞስ ቢሆን ከህልውናው አልውጣ እንጂ እዛው ልክረም ላርጅ እንጂ መች ልውጣስ መታወቅን ዝነኝነትን ተራብኩ አልኩ ስለዚህ ያለሁበት ተመችቶኛል ካዘለለኝ እዘላለው ካስጨፈረኝም እንደዛው ሆኖም ግን ዳንሱዋ ግን ትለፈኝ ማንፀው የለምና ።ትንሹዋን የሚባርክ መሰማትን ዕድልን የሚሰጥ አምላክ እንጂ መቀላጠፍና በየሚዲያው ያለዕረፍት ያለዝግጅት ከሰኞ እስከ እሁድ መሰየም አይመስለኝም እወዳችዋለው😍 ይህ መልዕክቴ ነው አድርሱልኝ።
👇👇👇
https://youtu.be/bfYMe_hI6_s

28/03/2022

እስት ውድ ቤተሰቦቼ ለባለቤታችሁ/ለምስታችሁ እና ለፍቅረኛችሁ አድናቆት ለግሱለት/ላት

ክርስታናዊ ጋብቻ

✅ውድ  #ክርስታናዊ-ጋብቻ-ገጽ-ተከታታዮችና-ቤተሰቦቼ ስለጠፋው ይቅርታ  #ተመልሻለሁ-ሰላም-የጌታ-ቤተሰቦች!!
28/03/2022

✅ውድ #ክርስታናዊ-ጋብቻ-ገጽ-ተከታታዮችና-ቤተሰቦቼ ስለጠፋው ይቅርታ #ተመልሻለሁ-ሰላም-የጌታ-ቤተሰቦች!!

28/01/2022

!!

ተሳድጄ ነበር ወደ ናዝሬት የሄድኩት። ወትሮም መጠጣት ልማዴ ነው፣ ናዝሬት ከሄድኩ በኋላ ደግሞ ባሰብኝ። ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ የከተተኝ ደግሞ አዲስ አበባ በፖሊስ መታደኔ ነበረ። "ደሞ ነገ ልያዝ" እያልኩ አልኮል መጠጣቴ ጨመረ። አንድ ቀን እንደተለመደው በመጠጥ ጢምቢራዬ ዞሮ በአንዲት እህት ጋባዥነት ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ። ሰፈሬ ጌጃ ሰፈር ስለነበረ ጌጃ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ሰርግ ሲኖር ምግብ ለመብላት ከሰፈር ልጆች ጋር እየገባን ምግቡ እስኪጀመር ድረስ ስብከት ከምንሰማው በቀር ብዙም ሃይማኖታዊ ስብከት ለመስማት ፍላጎቱም አልነበረኝ። ዛሬ የምሰማው ስብከት ግን ለየት አለብኝ። ሰክርያለሁ ግን የምሰማው የእግዚአብሔር ቃል ሰርስሮ ውስጤ እየገባ ነበር። የደነደነው ልቤ በቃሉ ጉልበት ሲቀልጥ ይታወቀኛል ። ከሰፈሬ፣ከጓደኞቼ ፣ከቤተሰቤ እርቄ ተሳድጄ ባለሁበት፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ በናዝሬት ተገናኘኝ። ተምበርክኬ በእንባ ኃጢአቴን ተናዘዝሁ። ለረጅም ሰአት ብንበረከክም የአሸዋው ቁርቋሬ አልተሰማኝም ነበር። ተሰብኮ እንዳለቀ እጄን አንስቼ የሁሉ ወዳጅ የሆነውን ኢየሱስን የህይወቴ አዳኝና ጌታ አድርጌ ተቀበልኩኝ። ለመጀመሪያ ግዜ ገንዘቤ ቁም ነገር ላይ የዋለው መፅሐፍ ቅዱስ የገዛሁ ቀን ነበር። በጣም ደስ አለኝ። አንብቤ አልጠግብ አልኩኝ። የምኖርበት ቤት ሲመሽ ከተወሰነ ሰአት በኋላ መብራት ስለሚያጠፉ ሻማ ገዝቼ በሻማ ማንበቤን ቀጠልኩ። እስከ አሁን ይገርመኛልእስር ቤት ገብቶ የሻማ ከመጠየቅ በሻማ ወደማንበብ ገበሁ። ክብር በድንቅ ላዳነኝ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን። በሚገርም ፍጥነት ህይወቴ ተለውጦ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ። የቀደመው ድርጊቴ ተለወጠ። ብዙም ከቤት አልወጣም ነበር። ቤቴ ተቀምጬ መፅሐፍ ቅዱሴን አነባለሁ። ቸርች እሄዳለሁ። ቤተሰቦቼ ቤት መዋሌ አሳሰባቸው። ። በኋላም የመለወጤን ምስጢር ደረሱበት። አንድ ከቸርች ስመለስ ቤታችን ሽማግሌዎች በኔ ጉዳይ ተጨንቀው ተሰብስበዋል። ቁጭ አርገው ይመክሩኝ ጀመር። "ተው ሃይማኖትህን አትለውጥ" አሉኝ። ህይወቴ እንጂ ሃይማኖቴ እንዳልተለወጠ ነገርኳቸው። ናዝሬት ሄዶ ብሶበት ይመጣል ብለው ሲጠብቁኝ ከናዝሬት መልካም ሆኜ ተመለስኩ። ዛሬ የጌታ ፀጋ ባገዘኝ መጠን በኑሮ የተጎዱ ወገኖችን ስረዳ እንባዬ ይመጣል። እንኳን ሰው ለማገዝ ቀርቶ ራስን ችሎ መኖር በአዕምሮዬ አስቤውም አላውቅም። ክብር የሁሉ ወዳጅ ለሆነ ለኢየሱስ ይሁን። በልዩ ልዩ ጉዳይ ህይወታችሁ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ያላች ወገኖቼ ፣ዛሬ የቃሉ ሰባኪ ሆኜ ሃያ ሁለት አመት ጌታ በኔ ሆኖ በተከላት ቤተክርስቲያን አገለገለ የተባልኩት እኔ ህያው ምስክር ነኝ እግዚአብሔር ሰውን ይለውጣል። ህይወትን መልካም ያደርጋል። በብዙ ነገር ተስፋ ብትቆርጡም በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ አትቁረጡ እርሱ አዳኝ ነው።
በድጋሚ እንኳን ለተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልገሎት ቤተክርስቲያን ሃያ ሁለተኛ አመት እንኳን አደረሳችሁ።
ክብር የሁሉ ወዳጅ ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን!
የሚወዳችሁ ወንድማችሁ ሚኪ!

29/12/2021

♦ ???
==================================

📌ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታህሳሥ ወር አለመወለዱን ያውቃሉ???

መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል 1ቆሮ 2፡15

ዮሐንስ 8:31-32
ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፡— እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤
እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡ አላቸው።

1) በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስ በታህሳስ ወር ተወልዷልን???
2) የሚደረገው ስርዓትስ ከክርስትና ጋር ግንኙነት አለው??
3) የገና ዛፉስ ከየት መጣ???
4) መብራቱ እና አፉፋውስ(ፊኛ) ከየት መጣ???
5) ቅዱስ ኒቆላዎስስ ( የገና አባት ) የተባሉት ከየት መጡ???

✍️መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል 1ቆሮ 2:15

📌 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ፦
=========================
መሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በታህሳስ እንዳልሆነ ይናገራል።

✍️1ዜና 24፡7-19 ንጉሥ ዳዊት ካህናትን በተራቸው ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ገብተው ያጥኑ ዘንድ መደባቸው 24 ካህናት ነበሩና በወር 2 ካህን ማለትም( ከ 1-15 እና ከ 16-30) በ 12 ወር 24 ካህናትን አደረገ ።

✍️በእስራኤላዊያን ቀን አቆጣጠር መሰረት ደግሞ የመጀመሪያ ወራቸው ኒሳን (Nisan) ይባላል።
አስቴር 3፡7 , 8፡9
የእስራኤል የመጀመሪያ ወር ኒሳን በኢትዮጵያውያን ቀን አቆጣጠር ሚያዚያ መሆኑ ነው።

✍️ በምድቡም መሰረት
=====================
📌በአንደኛው ወር (ኒሳን)
ከ 1-15 ቀን== ዮአሪም
ከ 16-30 ቀን== ዮዳኤ

📌በሁለተኛው ወር (እያር)
ከ 1-15 ቀን==ካሪም
ከ 16-30 ቀን==ሥዖሪም

📌በሶስተኛው ወር (ሲቫን)
ከ 1-15 ቀን==መልክያ
ከ 16-30 ቀን==ሚያሚን

♥በአራተኛው ወር ( ታሙዝ)
ከ 1-15 ቀን== አቆስ
ከ 16-30 ቀን== ♦አብያ♦

በሉቃስ ወንጌል 1፡5- 13 #ከአብያ ቤተሰብ የሆነ ስሙ ዘካርያስ የሚባል ሰው እናገኛለን በ 4ኛው ወር (ታሙዝ) የወሩ ሁለተኛ አጋማሽ ማለት ከ 16-30 ቀን በክፍሉ ተራ ለማጠን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ይገባል።
በመቅደስ ውስጥ እያጠነ መልአኩ ገብርኤል ተገልጦ ልጅ እንደሚወልድ ይነግረዋል ተራውንም ጨርሶ ወደ ቤቱ ይመለሳል ከዚያም ዩሐንስ መጥምቁ ይፀነሳል።

✍️መጥምቁ ዩሐንስ በተጸነሰ በ6ኛው ወር መልአኩ ገብራኤል በናዝሬት አውራጃ ገሊላ በሚባል አካባቢ ወደምትኖር ስሟ ማርያም ወደምትባል ድንግል ሴት ያቀናል ከመንፈስ ቅዱስ እንደምትጸንስና ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትወልድ ይነግራታል። ሉቃ 1:26 ኢየሱስም በ 10ኛው ወር ( #ቴቬት) ይፀነሳል ቴቬት 10ኛ ወራቸው በኢትዮጵያ አቆጣጠር በጥር ወር ኢየሱስ ይፀነሳል ከጥር ጀምሮ 9 ወር ስንቆጥር መስከረም (ቴስር) መጨረሻ ጥቅምት መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ ይወለዳል ።

📌መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ የሚናገር ከሆነ የገና በዓል እየተባለ በታህሳስ ወር የሚከበረው ከየት መጣ ??

ክርስትና ከተጀመረ ከ 313 በኃላ ቤተክርስቲያን ነፃነቷን ስታገኝ ከአህዛብን አለም የመጡትን አዳዲስ አማኞች ተከትሎ የገባ የአህዛብ በዓል ነው። ታሪክ እንደሚነግረን አህዛቦች የብርሃን አምላካችን የተወለደበት ብለው ጨለማው አለፈ የበጋው ብርሃን መጣ በማለት እሳትን እያነደዱ የለመለመ ዛፍን እየቆረጡ ያከብሩ ነበር። ይህ አህዛባዊ በዓል በቤተክርስቲያን ውስጥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ተብሎ ተቀየረ ። ቆይቶም የካቶሊክ ቅዱስ የተባሉት ኒቆላዎስ የገና አባት ተብለው በየቤተክርስቲያኑ ውስጥ ተቀባይነት ካገኙ ዘመናትን አስቆጥረዋል ።

ገላትያ 4 (Galatians)
8፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን ሳታውቁ በባሕርያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ተገዛችሁ፤
9፤ አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
10፤ ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
11፤ ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።

የገና በዓል እንዲህ ስር የሰደደ እና በብዙኀን ዘንድ ተቀባይነት ቢያገኝም እውነት ሊሆን አይችልም እውነቱ የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው ብቻ ነው።

♦ከተወለደበት ቀን ይልቅ ወደ ተወለደው ማንነት መዞር ይሁንልን ቀኑ ሳይሆን ኢየሱስ ነው መፍትሄው

📌"ኢየሱስም ሞቱን እንድናስብ ነው ያዘዘን"

ይሁዳ 1፡17
እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤

የወንጌል እውነት ቤተክርስቲያን ጅማ
Gospel truth ministry Jimma

27/10/2021
በጣም ደስ የምል ታርክ ነው አንብባችሁ ጨርሱ💔💔💔💔💔
20/10/2021

በጣም ደስ የምል ታርክ ነው አንብባችሁ ጨርሱ💔💔💔💔💔

ሰው ሊያዋራ ወደ ኋላ የቀረ ጓደኛዬን ቆሜ ስጠብቅ ድንገት በኔ በኩል መልከ መልካም ሴት መጣች። ልከኛ ነች! መሃከለኛ ቁመት፣ መሃከለኛ ፀጉር፣ በመሃከለኛ የሰውነት ቅርፅ ያላት ሴት...የማላውቀው ሃይል አናግራት አዋራት አለኝ!
አጠገቤ ስትደርስ «እንተዋወቅ» አልኳት! ማነሽ? ወዴት ነሽ? ገለመሌ የለም፣
«ሰላም እባላለሁ» አለችኝ!
«ሰላም የሚባሉ ሴቶች ብዙ ግዜ ፀረ-ሰላም ናቸው ይባላል» አልኳት!
«ይሆናል ...» ብላ ሳቀች!
«ፀሃይ ነው ለምን ትንሽ አረፍ ብለሽ ቡና ምናምን ጠጥተን መንገድሽን አትቀጥዪም?» አልኳት!
«እሺ» አለችኝ!
ጓደኛዬን ጥዬ አንዱ ካፌ ይዣት ገባሁና ሻይ ቡና ብለን ስንወጣ «ለክፉም ለደጉም ስልክ ቁጥር ብንለዋወጥ» አልኳት!
«እሺ» አለችኝ። (ልጅቷ እምቢ አታውቅም ጎበዝ)
ቁጥሯን ተቀብዬ በመነገው ደወልኩላትና «ነገ ከተመቸሽ እንገናኝ?» አልኳት
«እሺ ....!»
ብዙ ግዜ ተገናኘን! ተቀራረብን! ወደድኳት! ፈራ ተባ እያልኩ «ወደድኩሽ» አልኳት። ትንሽ አስባ «እሺ» አለችኝ።
«ፍቅረኛዬ ብትሆኚ ደስ ይለኛል»
«እሺ ....»
የእሺታዋ ብዛት ግራ ቢገባኝም ወድጄዋለሁ። ምንም ነገር አትቃወም! እምቢ አታውቅ! አትጨቃጨቅ! በቃ ሁሉን እሺ ነው! እንዲህ ቦታ እንሂድ? እሺ! እንዲህ እናርግ? እሺ! ... ሁለት አመት ከአምስት ወር ሆነን አንድም ቀን ፀባይዋ ሳይለወጥ! አንድም ቀን ኮምፕሌን ሳታደርግ! እንዲሁ ግራ እንዳጋባችኝ ሁለት አመት ከአምስት ወር በፍቅር!!
የሆነ ቀን ቀለበት ከኪሴ አውጥቼ «አግቢኝ» አልኳት!
«እሺ ....!»
እሺ ጠላሁ!
በቃ ደበረኝ! ቆይ እስከዛሬ በኔ ስሜት፣ በኔ ፍላጎት፣ በኔ እቅድ እሺ ብቻ እያለች ኖረች! የራሷ ስሜትስ? የራሷ ፍላጎትስ? የራሷን ህልም የት አርጋው ነው ሰው ህልም ውስጥ ጭልጥ ብላ ምትጠልቀው?
ተጋባን!
«ልጅ እንውለድ?»
«እሺ!»
አሁን ነፋሱ ወደነዳት የምትንሳፈፈ ፌስታል ያህል ቀለለችኝ! በቀደዱላት ቦይ የምትፈስ ወራጅ ውሃ መሰለችኝ! አዎ ውሃ! ከገደቧት የምትረጋ፣ መንገድ ከሰጧት የምትጓዝ፣ እሳት ላይ ሲጥዷት የምትሞቅ፣ ፍሪጅ ሲጨምሯት የምትበርድ የራሷ ቅርፅና መልክ የሌላት ውሃ መሰለችኝ!
ለምን አመሸህ? ለምን ይሄን አላረግክም? ብሎ ጭቅጭቅ እሷጋ የለም! እንኳን ባመሽ ባድር በነጋታው ምንም እንዳልተፈጠረ በፈገግታ ትቀበለኛለች! ብስጭት ብዬ ስናገራት መልስ አትሰጥም! ይሄን አርጊ ያን አታርጊ ስላት ለምን? ማለት የለም «እሺ» ነው! በቃ እሺ ብቻ!

በጓደኞቼ ሚስቶች እቀናለሁ። ሲቆጡ ቁጣቸው ውስጥ የኔነት አለ። ሲቀኑ ቅናታቸው ውስጥ ስስት አለ! ሲከፉ መከፋታቸው ውስጥ ፍቅር አለ! የኔዋ ግን በቃ በድን! ታግዬ እንኳ ላስከፋት የማልችል፣ ሁሉን ነገር ከመቀበል ውጪ እምቢ የማታውቅ ግኡዝ ፍጥረት ትመስለኛለች!
አንዳንዴማ ነካ ሚያድጋት ሁሉ ይመስለኛል! እኔው አጥፍቼ እኔኑ ይቅርታ ስትጠይቀኝ ብግን እላለሁ። አስከፍቻት ውዬ ስመለስ ከበር በፈግታ ስትቀበለኝ እየተወነች ይመስለኛል! አንዳንዴ ስጋ የለበሰች አሻንጉሊት ያገባሁ ሁሉ ይመስለኛል!
ለካ ጠብ ብቻ ሳይሆን ቅጥ የለሽ ሰላምም ይረብሻል! ለካ አለመስማማት ብቻ ሳይሆን ዝም ብሎ መስማማትም ይጨንቃል! «እንኳን ሰው ድንጋይና ድንጋይ እንኳ ይጋጫል» ይላሉ አበው።
በተጋባን be 3t Aመቱ «እንፋታ» አልኳት
«እሺ!» አለችኝ!
ለምን? የለ! ድንጋጤ የለ! በቃ «እሺ ብቻ!» ...«እሺ» ብላ መቀበሏ የበለጠ አናደደኝ! ከዚች ጋርማ መኖር አልችልም። አልኩት ራሴን! ጠኋት ተነስቼ ወደምሄድበት እሄዳለሁ ቤቱን እሷ ቤቢን ይዛ ትኑርበት። ልጄ ሲናፍቀኝ እየመጣሁ አየዋለሁ! አልኩ በሆዴ!
በጠኋት ሻንጣዬን ይዤ ልወጣ ስነሳ እሷ ቀድማኝ ቤቢን ይዛው ሄዳለች! ፍሪጁ ላይ አንድ ወረቀት ተለጥፏል። ጠጋ ብዬ አየሁት
«ራስህን ጠብቅ» ይላል!
ግራ ገባኝ! እንዳሰብኩት ነፃነት አልተሰማኝም። የሆነ ሃዘንና ድብርት የቀላቀለ ነገር ይሰማኛል። ሳምንቱን ሙሉ ሰከርኩ! ከሳምንት በኋላ ደወልኩላት! ስልኳን አታነሳም። በህቷ ስልክ ስደውል ቤተሰብ ጋር እንዳለችና ልታናግረኝ እንደማትፈልግ ነገሩኝ! ይሄን ስሰማ የሆነ ደስ ነገር አለኝ! ማለት አለ አይደል እሷም እንደሰዉ እንደምትከፋ በማወቄ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ!
አንድ ወር ቆይቼ ደወልኩላት። አሁንም አታነሳም። ግራ ተጋባሁ! ጨነቀኝ! ምንም ያልበደለችኝን ሚስቴን ምን ሁኚ ብዬ ነው ያባረርኳት? ትዳሬን ምን ይሁን ብዬ ነው ያፈረስኩት? ምን አርጊ ምን ፍጠሪ ነው ያልኳት ቆይ? ፀፀት ሁለመናዬን ወረረኝ! ቢቸግረኝ የቅርብ ጓደኛዬን ይቅርታ ጠይቆ እንዲያመጣት ላኩት። እሷ ማንንም ስለማታስከፋ እሺ እንደምትለው እርግጠኛ ነበርኩ!
ለማሰቢያ የሚሆን ግዜ እንዲሰጣት ነግራው አሰናበተችው። ካሁን አሁን መጣች ብዬ ስጠብቅ የፍቺ ወረቀት በሬ ድረስ ላከችልኝ!
ምድርና ሰማይ ዞረብኝ! ወረቀቱን በእጄ አንጠልጥዬ ስበር ቤተሰቧ ቤት ሄጄ በሩን አንኳኳሁ።
ራሷ ከፈተች! ፊቷ ላይ ምንም አይነት ለውጥ አላየሁም።
«ምንድነው ይሄ?» አልኳት
«እንፋታ ብለኸኝ የለ? የፍርድቤት መጥሪያ ነው» አለችኝ። ድምጿ ውስጥ የቀድሞ ልስላሴዋ የለም። ሌላ ሴት ነው ምትመስለው።
እግሯ ላይ ወድቄ ይቅር እንድትለኝ ለመንኳት! ዝም ብላ ስታየኝ ቆይታ አንድ ቃል ከአፏ አወጣች
« #እምቢ!»
ጆሮዬን አላመንኩም። እምቢ የሚለው ቃል ለካ እንዲህ ያማል? እምቢታዋ ውስጥ ከእሺታዋ የሚበልጥ ጥንካሬ አለ! እምቢታዋ ጨካኝ ነው! ያስፈራል ! ከዚያን ቀን ወዲህ ለመታረቅ ያልፈነቀልኩት ድንጋይ ያልሰደድኩት ሽማግሌ የለም! ነገር ግን ሁሉም እምቢታዋን ለማሸነፍ የሚያበቃ ጥንካሬ አልነበራቸውም!

 -ቀን-ተመኘውላችሁ
06/08/2021

-ቀን-ተመኘውላችሁ

 #ተመልሰናል     ሰላማችሁ ይብዛ ውድ ወዳጆቸ!
03/08/2021

#ተመልሰናል
ሰላማችሁ ይብዛ ውድ ወዳጆቸ!

09/07/2021
04/07/2021
09/03/2021

💠✅ ካልጨረሳችሁት አትጀምሩት #ይነበብ ✅💠

ፈጣሪ አህያን ፈጠረና እንዲህ አለው አህያ ትሆናለህ፡፡ ሸክሞችን በጀርባህ በመሸከም ፀሐይ ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ ያለመታከት ትሰራለህ የምትመገበው ደግሞ ሳር ነው፡፡
ምንም አይነት ኢንቴለክት(የማሰብ፣የማመዛዘን ችሎታ) የለህም፡፡ እናም 50 ዓመት ትኖራለህ አህያው እንዲህ ሲል መለሰ…
አህያ እሆናለሁ ችግር የለውም ነገር ግን 50 ዓመት በጣም
ብዙ ነውና ሃያውን ብቻ ስጠኝ፡፡ እግዚያብሔርም የፍላጎቱን
ሰጠው፡፡
_________
ፈጣሪ ውሻን ፈጠረና እንዲህ አለው….
የሰውን ልጅ ቤት ትጠብቃለህ፡፡ የሰው ልጅም እውነተኛ ጓደኛ
ትሆናለህ፡፡ ከጌታህ የሚጣልልህን ፍርፋሪ ትመገባለህ፡፡ እናም
30 ዓመት በሕይዎት ትኖራለህ፡፡ ውሻም ትባላለህ፡፡
ውሻው ሲመልስ…
ጌታየ 30 ዓመት እጅግ ብዙ ነው አስራ አምስቱ ዓመት ይበቃኛል
አለ፡፡
ፈጣሪም የፍላጎቱን ሰጠው…
_________
ፈጣሪ ዝንጀሮን ፈጠረና እንዲህ አለው….
ዝንጀሮ ትሆናለህ፡፡ በዛፎች ቅርንጫፍ ወዲያና ወዲህ
እየተንጠላጠልክ ትርኢት ትሰራለህ፡፡ በድርጊትህም አስገራሚ
ትሆናለህ እናም 20 ዓመት ትኖራለህ፡፡
ዝንጀሮው ሲመልስ…
ሃያ ዓመት መኖር በጣም ብዙ ነውና አስሩ ብቻ ይበቃኛል አለ፡፡
ፈጣሪም የሚኞቱን ሰጠው፡፡
__________
በመጨረሻም ፈጣሪ ሰውን ፈጠረና እንዲህ አለው….
የሰው ልጅ ትባላለህ፡፡ በምድር ላይ ካሉት ፍጡራን አመዛዛኝ፣
አሳቢና ምክኒተዊ ፍጡር አንተ ብቻ ነህ፡፡ በሌሎች ፍጡራን ላይ
ለመንገስም የማሰብ ችሎታህን ትጠቀማለህ፡፡ በሌሎች
ፍጡራን ላይ ነግሰህም 20 ዓመትን ትኖራለህ አለው፡፡
የሰው ልጅ የተሰተውን የማሰብ ችሎታው ተጠቅሞ ሲመልስ…
ጌታየ እሽ! የሰው ልጅ እሆናለሁ፡፡ ነገር ግን ሃያ ዓመት መኖር
እጅግ ሲበዛ ትንሽ ነው፡፡ ስለሆነም ሠላሳ ዓመት አህያው
የተቃወመውን፣ አሥራ አምሥት ዓመት ውሻው አልፈልገውም
ያለውን እናም ደግሞ አስሩን ዓመት ዝንጀሮው የማይፈልገውን
ስጠኝ ሲል ጥያቄውን አቀረበ (ከራሱ ጋር የሌሎችን ደማምሮ
75ዓመት አደረሰው)፡፡
ፈጣሪም የፍላጎቱን ሰጠው…
___________
እናም የሰው ልጅ ሕይዎት ከዛን ጊዜ ጀምሮ 20ውን ዓመት እንደ
ሰው ይኖራል (ሳያገባ ትዳር ሳይመሰርት ለአንድ ሆዱ ሲኖር
ማለት ነው)፡፡ ከዛ በኋላ አግብቶ ትዳር ሲመሰርትና የቤተሰብ
ኃላፊ ሲሆን 30ውን ዓመት ልክ እንደ አህያው የአህያውን ሚና
ወስዶ ይኖራል፡፡
የቤተሰብ ኃላፊነቱን ይሸከማል፤ የአባወራነቱን ኃላፊነት
ለመወጣትም ቀን ከሌት ያለመታከት ይሰራል፡፡ ቀጥሎም ልጆቹ
እያደጉ ሲሄዱ 15ቱን ዓመት ልክ እንደውሻው አይነት ኑሮን
ይመራል፡፡ ቤቱን ይጠብቃል ይንከባከባል፣ ከልጆቹ ተርፎ
የሚሰጠውንም ይበላል፡፡ አርጅቶ እየሸመገለ በሄደ ጊዜም ጡረታ
ይወጣና 10ሩን ዓመት እንደ ዝንጀሮው አኗኗር ዘይቤ ይኖራል፡፡
ልጆቹን አጎራብቶ ከአንደኛው ቤት ወደ ሌላኛው ቤት በመዘዋወር
የልጅ ልጆቹን በማጫወት፣በማዝናናት ያለፉ ዘመናትን ታሪክ
በማውራት ያሳልፋል፡፡ ሕይዎት ማለት ይች ናት!

ከወደዱት ሼርርርር

ርኩስ ጋብቻ ፍጻም(አጋብ)46ኛ የአሜሪካኖች ፕሬዝዳንት  ጆ ባይደንልቤ እንድያልፈ ሳልፈልግ ያለፍ መር ነው ግን ሁሉም ትራምፕ በመውደቁ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደተደሰተ አውቃለው ። የኔ ጉዳይ ...
08/11/2020

ርኩስ ጋብቻ ፍጻም(አጋብ)
46ኛ የአሜሪካኖች ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

ልቤ እንድያልፈ ሳልፈልግ ያለፍ መር ነው ግን ሁሉም ትራምፕ በመውደቁ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደተደሰተ አውቃለው ። የኔ ጉዳይ ከአባይ ግድባችን ሳይሆን ያለው መር ምን አይነት ነው? የምለው ነው ።
ሰንቶቻችን ነን #የግብረሰዶማዊ(666) አባል መሆኑን የምናቅ?

ጆ ባይደን በአንድ ወቅት የሁለት ወጣቶችን ማለትም ብራያን ሞሰትለር እና ጃይ ማሺዩ የተባሉ የረጅም ጊዜ white house (የኋይት ሐውስ) ሰረተኞችን የወንድ ለወንድ ጋብቻ ያስፍጸሙ(officiate) እንደ ቄስ ቆሞው ያጋቡ ናቸው ። ትላንት በአሜርካ ሀገር በምርጫ ያሸነፍው ።

ወገነ እንጠቀቅ ሰውዩ ሶዶማዊነትን በአለም እንደምያሰፋፋ እና ለግብረሶዶማዊያን ጥበቃ እንደምደረግላቸውም ተናግረዋል ።

?

 #እባካችሁበዚህ አሰቸጋረ ወቅት ላይ   እንድሁም ያልተረጋገጠ መረጃዎችን ሆነ ብላችሁ እየለቀቃችሁ ተከታዮቻችሁን አታስደነግጡ ።
05/11/2020

#እባካችሁ

በዚህ አሰቸጋረ ወቅት ላይ እንድሁም ያልተረጋገጠ መረጃዎችን ሆነ ብላችሁ እየለቀቃችሁ ተከታዮቻችሁን አታስደነግጡ ።

ካውንስሉ አስቸኳይ የጾምና ጸሎት አወጀ !!!የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ፣የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ፣በሀገር ውስጥና ውጭ የሚትገኙ መርዎች እና አ...
05/11/2020

ካውንስሉ አስቸኳይ የጾምና ጸሎት አወጀ !!!

የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ፣
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ፣
በሀገር ውስጥና ውጭ የሚትገኙ መርዎች እና አገልጋዮች፣

በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በተለያዮ ስፍራዎች በግፍ ሰለተገደሉት እና ሰለተፈናቀሉት ንጹሐን ዘጎች በጠፍው ክቡር የሰው ሕይወት እና የንብረት መውደም እንደወንጌላዊያን አማኞች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን መግለጽ እንወዳለን ።

በተጨማረም በሰሜን የሀገራችን ክፍል በወንድማማች መሀከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ግጭት በመግባቱ እጅግ አሳዝኖናል አስደግጦናል ። በተለይም ልዩነቶችን በውይይት መፍታት ስቻል ወደ እርስ በርስ ግጭት መግባታችን አሸናፈ ተሸናፈ የለለው የንጹሐን ዘጎችንም ሊጎዳ የሚችል ሰለሆነ ሁሉም ወገኖች በሰከነ መንፈስ ለሰላም እድል እንድሰጡ እንማፀናለን ።

እንዲህ አይነቱ የእርስ በርስ ግጭት መቋጫ የሌለው በመሆኑ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች የሃማኖትና የብሔር ልዩነት መሰረት ያደረጎ የንጹሐን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በጽኑ እያወገዘን እንዲህ ዓይነት ግጭት መቋጫ የሌለውና ለዘመናት የዘለቀውን ኢትዮጵያዊ የአብሮነት የማሸረሽር በመሆኑ በእግዚአብሔር ቃልም ሆነ በኢትዮጵያዊነት ባህልም ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል ።

እኛ በአገር ውስጥም በውጭ የምንኖር የወንጌል አማኞች የሆነን ኢትዮጽያዊያን ለሀገራችን ከመጸለይ ጎን ለጎን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም በመኖር ለሀገራችን ሰላም እና አንድነት የበኩላችንን አሰተዋጽዖ ልንወጣ ይገባል ።

የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ይላል (1ኛ ጢሞ 2:1-2)

ሰለዚህ በጸጥታና በሰላም ለመኖር ከፈለገን ለአገራችንና ለህዝባችን አጥብቀን ልንጸልይ ይገባል ።

በመሆኑ ከነገ ጥቅምት 27 ቀን 3013 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት የጾምና የጸሎት ጥር እያስተላለፍን ይኸው መርሃ ግብር በመላው ሀገራችን እና በውጭ በሚኖሩ የወንጌል አማኝ ቤተ እምነቶች በአንድ መንፈስ በእግዚአብሔር ፈት በጸሎት እንዲንቀርብ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን ።

በተጨማረም በመግለጫው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝዳንት መጋቢ ጻዲቁ አበዶ ሃገረቱ ውስጥ የተፈጠረውን የእርስ በርስ ግጭትን እንዳይፈጠር ያለ ምንም ወገንተኝነት በመምከር እና በመገስጽ ቆይተናል ያሉ ሲሆን አሁን መፍትሄዉ በንጹ ልብ ወደ ፈጣረ በጸሎት መቅረብ ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አሰተላልፈዋል ።

ወደ ሰላም እንዲመጣ ከዚህ ቀደም በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ የጠቀሱት የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፈ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ አሁንም ሃገር ሰላም እስከምትሆን ድረስ የሚቻለን ሁሉ አቅማችንን ተጠቅመን ቀጥለን እንሰራለን ስሉ ተናግረዋል ።

እግዚያብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! !!
ዶ/ር ኢያሱ ኤልያስ
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዘዳንት
ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

 ...(አርቲስት አስቴር በዳኔ)ይድረስ ለአቢያተ ክርስቲያናት ህብረትና ሌሎች የእምነት ተቋማት ሀገራችን ከቀን ወደ ቀን አኪልዳማ (የደም መሬት) እየሆነች ነው ። ከተፈጥሮ አደጋ እስከ ሰው ...
04/11/2020

...

(አርቲስት አስቴር በዳኔ)

ይድረስ ለአቢያተ ክርስቲያናት ህብረትና ሌሎች የእምነት ተቋማት ሀገራችን ከቀን ወደ ቀን አኪልዳማ (የደም መሬት) እየሆነች ነው ። ከተፈጥሮ አደጋ እስከ ሰው ሰራሽ እልቂት ወገኖቻችንን እያሰቃየ እያየን ዝም የምንለው እስከመቼ ነው ። በየጊዜው ለሚከሰቱ ክስተቶች ሀዘናችንን ብቻ ገልጸን ማለፍ በቂ አልመሰለኝም ። ሁላችሁም በግል ጸሎት እያደረጋችሁ እንዳለ አምናለሁ ። አሁን የምጠይቃችሁ ከመንግስት ፍቃድ ጠይቃችሁ ሦስት ቀናት ስራ ተዘግቶ ሁላችንም ወጥተን በሀገር አቀፍ ደረጃ ፆም ጸሎት እናድርግ ወደ እግዜአብሄር እንጩህ ጌታ ይሰማናል ።
ሌላ ማለት ስላቃተኝ ነው ። ያለን ብቸኛ መፍትሄ እሱ ብቻ ነው ።

''የአማራ ነፍስ የጆርጅ ፍሎይድን ነፍስ እንኳ አታክልም'' (ዶክተር ደረጀ ከበደ)-----------------------------------------------------------''ኢትዮጽዬ እ...
03/11/2020

''የአማራ ነፍስ የጆርጅ ፍሎይድን ነፍስ እንኳ አታክልም'' (ዶክተር ደረጀ ከበደ)

-----------------------------------------------------------

''ኢትዮጽዬ እንድትድን እና እንደ ሃገር እንድትቀጥል ስንት ሚሊዮን አማራ ማለቅ አለበት? ስንት ሚሊዮን ኦርቶዶክስ ማለቅ አለበት? ስንት ኦርቶዶክስ አማኞች መታረድ አለባቸው? እስኪ መልሱልን ፡ ይህ ምን አይነት ሎጂክ ነው? ለሶስተኛ ክፍል ተማረ እንኳ ትነግሩታላችሁ ወይ? ኢትዮጵያ የምትድነው አማራ እያለቀ እኛ ወንጀሉን ስንሸፋፍነው ነው የሚል ሎጂክ ከየት የመጣ ነው?

ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ ሲገደል ብዙ ኢትዮጵያዊያን ለሰልፍ ወጥተው ነበር ። ዛሬ ግን ከ200 በላይ አማራ በአንድ ቀን ሲጨፈጨፈ ለሰልፍ የሚወጣ ኢትዮጵያዊ አላየንም ። ለምን?

ዘማረ ዶ/ር ደረጀ ከበደ

03/11/2020

,,,አሁንስ ተስፋየ ማነው?
ተስፋየ እግዜአብሄር ነው...
የሀገራችን ተስፋ እርሱ ብቻ ነው...ነገ መልካም ይሆናል ።

 #ያማልእግዞኦ  ማረን
02/11/2020

#ያማል
እግዞኦ ማረን

15/10/2020

ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
❖መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ።
◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho
◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo
❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho
መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo
❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so
◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro
◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So
❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so
◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo
◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo
◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To
◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co
◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No
❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no
◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko
❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho
❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO
❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe
❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo
✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo
✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo
❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo
✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo
✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po
✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go
✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do
❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to
❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co
❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to
❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to
✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo
✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa
◄◄ሼር▻▻ይደረግ
‼️እስካሁን የተማማርናቸውን ትምህርቶች እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን በVideo ለማግኘት የ"youtube" ቻናላችንን Subscribe አድርጉ።
🔸Subscribe ያላደረገ video ሊደርሰው ወይም መከታተል አይችልም።
✅ Subscribe Us On youtube Channel
👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q

 ዘማሪ አቤል ሻወልና እጮኛዋ ቲጅ የጋብቻ ስነ_ስርአተ ዛሬ መስከረም 30/01/2013 ዓ.ም በ5ኪሎ መካነየሱስ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል ።
10/10/2020



ዘማሪ አቤል ሻወልና እጮኛዋ ቲጅ የጋብቻ ስነ_ስርአተ ዛሬ መስከረም 30/01/2013 ዓ.ም በ5ኪሎ መካነየሱስ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል ።

 📖በኤርትራ መንግስት በአደባባይ ወንጌል መናገርንና ማምለክን ፈቀደ📣🎶
03/10/2020


📖በኤርትራ መንግስት በአደባባይ ወንጌል መናገርንና ማምለክን ፈቀደ📣🎶

03/10/2020


📖በኤርትራ ሀገር ወንጌል በአደባባይ መናገርና ማምለክ ተፈቀደ📣🎶

✔ከትላንት በስትያ ዘማሪ አቤነዘር ለዘማሪት ኤደን ቀለበት🌟 ማድረጉን በሶሻል ምድያ አይተናል ግን ከዛ ቦሀላ ብዙ መረጃዎች ይወጡ ነበረ ይሁንና እንደደረሰኝ መረጃ መሰረት ኤደን ከዚህ በፍት ...
03/10/2020

✔ከትላንት በስትያ ዘማሪ አቤነዘር ለዘማሪት ኤደን ቀለበት🌟 ማድረጉን በሶሻል ምድያ አይተናል ግን ከዛ ቦሀላ ብዙ መረጃዎች ይወጡ ነበረ ይሁንና እንደደረሰኝ መረጃ መሰረት ኤደን ከዚህ በፍት አግብታ ከቀድሞ ባለቤቷም አንድ ልጅ አፊርታለች በትዳራቸው ባለመስማማት ተለያይቷል ። ከሶስት ዓመት በፍት የቀድሟ ባለቤት ለላ ምስት አግብታል ።
ለምን ተፋቱ የፍችው መንሰኤ ምንድ ነው?
ይህስ ለክስቲያን ያሰፈልጋል?
እመለሳለው መልስ ይዠ መልካም ቆይታ

28/09/2020

«ዝምታ ወርቅ አይደለም»
*************************************
ሰውዬው ከሚስቱ ሌላ አንዲት ሴት ወደደና እፍ ክንፍ አለ፡፡

ልጁን እና ሚስቱን እየተወ ከዚህችኛይቱ ጋር ማምሸት፣ ብሎም ማደር ጀመረ፡፡

በመጨረሻም አንድ ቀን ወደ ሚስቱ
መጣና ድንገተኛ የሆነ ጥያቄ አቀረበ፡፡

«እኔ እና አንቺ እንድንፋታ እፈልጋለሁ፤ ለምን ብለሽ ምክንያቱን አትጠይቂኝ፡፡ መፋታት ብቻ
እፈልጋለሁ፡፡ ደግሞም ሌላ ቀን አይደለም፣ ነገ እንዲሆን እፈልጋለሁ» አላት፡፡

ሚስቱ በሁለት ነገሮች ተጨነቀች፡፡

በአንድ በኩል ምንም ነገር አትጠይቂኝ ብሏታል፡፡

በሁለተኛ ነገር ልጇ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና ልትቀመጥ ጥቂት ቀናት
ቀርቷታል፡፡

«ባልፈልገውም፣ ባልስማማበትም፤ ካልክ የግድ እቀበለዋለሁ፡፡ ነገር ግን በኛ ምክንያት ልጃችን መጎዳት የለባትምና የአንድ ወር ጊዜ ያህል እንታገሥ፡፡» አለችው፡፡

እርሱም አሰበና «ጥሩ አንድ ወር መታገሥ አያቅተኝም፤ ነገር ግን በዚህ አንድ
ወር ውስጥ ሽማግሌ መላክ፣ ምክንያቱን
መጠየቅ የለም፤ ስለ ፍቺው ማናችንም ምንም ነገር ማንሣት የለብንም፤ በዚህ ቃል ግቢ» አላት፡፡

እርሷም «እስማማለሁ፤ ግን አንተም የምነግርህን ለመፈጸም ከተስማማህ ነው፤

ታድያ በዚህ አንድ ወር ጠዋት ጠዋት ከዕንቅልፌ ስነሣ፣ ማታ ማታም ወደ
አልጋዬ ስሄድ ያኔ የሠርጋችን ዕለት አቅፈህ
እንደ ወሰድከኝ አድርገህ አቅፈህ ትወስደኛለህ» ስትል ጠየቀችው፡፡

ነገሩ ያልጠበቀው እና ያልተለመደ ዓይነት ቢሆንበትም፣ ቀላል እና ሊያደርገው የሚችል ስለሆነ እሽ ብሎ ቃል ገባላት፡፡

አንዱ ወር ተጀመረ፡፡

ጠዋት ጠዋት ከዕንቅልፏ ስትነሣ አቅፎ፣ ከፍ አድርጎ፣ ወደ በረንዳ ካደረሳት በኋላ ወደ ሥራው ይሄዳል፡፡

ማታ ማታም እንዲሁ አቅፎ ወደ አልጋዋ ይወስዳታል፡፡

ስለ ፍችው አይነጋገሩም፡፡

እየዋለ እያደረ ሲሄድ የሰውነቷ ጠረን፣ የምትለብሳቸው ልብሶቿ፣ የዓይኖቿ እና የፀጉሯ ሁኔታ፣ የገላዋ ልስላሴ እና የአካሏ ቅርጽ እየሳቡት መጡ፡፡

በየቀኑ እያቀፈ ሲያወጣት እና ሲያስገባት ሰውነቷ እየቀለለው፤ ለርሱም እርሷን አቅፎ መሸከሙ አንዳች እንግዳ የሆነ የደስታ ስሜት እየፈጠረለት መጣ፡፡

ከራሱም ጋር ሙግት ጀመረ፡፡ «ለምንድን ነው እንፋታ ያልኳት፤ አሁን የሚሰማኝን ስሜት ያህል ስሜት ከአዲሷ ወዳጄ ጋር ለምን አይሰማኝም? ለምንስ ነበር ይህንን ነገር እንዳደርገው ቃል ያስገባችኝ ? ይህን የመሰለውን ገላዋን፣ እንዲህ የሚማርከውን ጠረንዋን፣ እንዲህ የሚያስደስተውን ፈገግታዋን፣ እንዲህ የተዘናፈለውን ፀጉሯን፣ እንዲህ ልዩ የሆነውን አካሏን እንዴት እስከ ዛሬ አላስተዋልኩትም ?እርሷ ናት ከኔ ጋር የነበረችው ወይስ እኔም ከርሷ ጋር ነበርኩ?»

የወሩ መጨረሻ እየደረሰ መሆኑን ሲያውቅ ከእርሷ መለየቱ ጨነቀው፡፡

እንዲያውም ይህ ሁኔታ የፈጠረበትን እንግዳ ስሜት እየወደደው መጣ፡፡

ነግቶ እና መሽቶ እርሷን አቅፏት እስከሚወስዳት በጉጉት መጠበቅ ጀመረ፡፡

በሌላም በኩል ደግሞ በዚህ ድርጊቷ በውስጡ ያሳደረችበትን ስሜት እያሰበ ያደንቃትም ጀመር፡፡

ብልህነቷን፣ አስተዋይነቷን እና በቀላል ድርጊት ቀልቡን ልትገዛው መቻሏን ሲያስበው «ምን ዓይነት አስገራሚ ሴት ናት?» ይላል፡፡

ወሩ ሊያልቅ ሁለት ቀን ሲቀረው የመፋታቱን ሃሳብ በውስጡ መረመረው፡፡ ነገር ግን አላገኘውም፡፡

በዚህ ሁኔታ መፋታቱ ደግሞ ለሕይወቱ የማይፈታ ዕንቆቅልሽ እንደሚሆንበት እያሰበ ተጨነቀ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አንድ ወር ውስጥ ፍችን በተመለከተ ላለመነጋገር ቃል ተግባብተዋልና እንዴት አድርጎ ይናገር፡፡

ዛሬም በደስታ ስሜት አቅፎ ከአልጋዋ እንደወሰዳት ሁሉ ማታ ወደ አልጋዋ መለሳት፤ ከበፊቱ እጅግ በጣም ቀለለችው፤
አሳዘነችውም፡፡

በወሩ መጨረሻ፡፡ወደ አዲሲቱ ወዳጁ ዘንድ ሄደና «የፍችውን ሃሳብ ሠርዤዋለሁ፡፡ እኔና ባለቤቴ ፍቅር የሌለን መስሎኝ ነበር፡፡ እኛ ግን ለካስ ፍቅር አላጣንም፡፡ ያጣነው ሁለት ነገሮች ብቻ ነው፡፡ መነጋገር እና መቀራረብ፡፡
ለዚህ ያደረሰንም አለ መቀራረባችን እና
አለመነጋገራችን ብቻ ነው፡፡ አሁን ግን መነጋገርባንችል እንኳን መቀራረብ ግን ችለናል፡፡ ዛሬ ደግሞ መነጋገር እንችላለን፡፡ ስለዚህ ሌላ የሚሆንሽን ፈልጊ» አላት፡፡

ሴትዮዋ ተናደደችና በጥፊ መታችው፤ ከአጠገቧ የነበረውንም ውኃ ቸለሰችበት፤

«ይሄ ለብዙው ኃጢአቴ የተከፈለ ቅጣት ነው» እያለ ወጥቶ ሄደ፡፡

ከዚያም ወደ አበባ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ገባ፡፡

ያኔ ሲጋቡ የገዛላትን ዓይነት አበባ ገዝቶ ወደ ቤቱ ከነፈ፡፡

«ጓደኛዬ ትዳር ማለት አግብተው የሚኖሩት
ሳይሆን በየጊዜው የሚጋቡት ነው ያለው እውነቱን ነው፡፡

ትዳር እንደ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና
አንድ ጊዜ አልፈውት ሰርተፊኬቱን የሚሰቅሉት አይደለም ያለው እውነቱን ነው፡፡ ትዳር እና ተክል ክብካቤ ይፈልጋሉ፡፡

እንዲሁ ቢያድጉ ይደጉ ተብለው የሚተው ነገሮች አይደሉም፡፡

«ልክ እዚህ ሀገር ችግኝ የመኮትኮት፣ የማጠጣት፣ የመከባከብ እና የማሳደግ እንጂ የመትከል ችግር እንደሌለብን ሁሉ፤ እኛም ጋር የመጋባት ችግር የለም፡፡

ፍቅር ግን ማግባትን ብቻ ሳይሆን ማጠጣትን፣ መኮትኮትን፣ ማረምን፣ ከብት
እንዳያበላሸው አጥር ማጠርን፣ በየጊዜው ማዳበርያ መጨመርን ጭምር ይፈልጋል፡፡

በርግጥ በዕድሉ የሚበቅል ዛፍ እንዳለው ሁሉ በእድሉ የሚኖር ትዳርም ይኖር ይሆናል፡፡ይህ ግን ሕይወትን ለራስ ጥረት ሳይሆን ለአጋጣሚዎች ብቻ አሳልፎ መስጠት ነው»ያለው እውነቱን ነው፡፡እኔ አልሰማሁትም እንጂ እርሱስ ተናግሮ ነበር፡፡»

መኪናውን አቆመና ወደ ግቢው ውስጥ ገባ፡፡

በረንዳ ላይ ትጠብቀው የነበረችው ባለቤቱ የለችም፡፡

በሩንም አንኳኳ፡፡ የሚከፍት ግን አልነበረም፡፡

ደግሞ ሲያንኳኳ ገርበብ ብሎ የተዘጋው በር በራሱ ጊዜ ተከፈተ፡፡

ባለቤቱ ግን በዚህች በወሩ ሠላሳኛ ቀን ሳሎንም የለችም፡፡

እየተገረመም፣ ግራ እየተጋባም ወደ መኝታ ቤቱ ዘለቀ፡፡

አልጋው ላይ ፈገግ እንዳለች ጋደም ብላለች፡፡

አበባውን እንደያዘ ጠጋ አለና በእጁ ጉንጯን ነካው፡፡ ቀዝቅዟል፡፡ በቁልምጫ ጠራት፡፡ መልስ ግን አልነበረም፡፡

ግራ ተጋብቶ ዓይንዋን ገለጥ አደረ ገው፡፡

ሊገለጥለት ግን አልቻለም፤ በርከክ አለና ሰውነቷን ደባበሰው፤ ቀዝቅዟል፡፡

«የመጨረሻው ቀን ነው፤ ይህችን ቀን ማየት
አልፈልግም፤ ለልጄ ስል እስከዛሬ ታግሻለሁ፤
በቃኝ» የሚል ጽሑፍ ራስጌዋ ላይ አገኘ፡፡

እርሷ ፍችውን አትፈልገውም፤ ስለዚህም ሳትፋታ ሞተች፡፡

በርሱ ውስጥ የነበረውን የሃሳብ ለውጥ
አላወቀችም፤ ምክንያቱም ላይነጋገሩ ቃል
ተግባብተው ነበርና፡፡

እርሷ የዛሬዋን ቀን በስጋት እና በጭንቀት ነበር የጠበቀቻት፡፡

የመለያያቸው ቀን፤ የሕይወቷን ግማሽ የምታጣበት ቀን፡፡ የማትፈልገውን ነገር የምታደ ርግበት ቀን ናትና፡፡

እርሱ ግን የዛሬዋን ቀን በጉጉት ነበር የጠበቃት፡፡

የሚነጋገሩባት ቀን፤ ፍችውን እንደተወው
የሚነግርባት ቀን፤ ፍቅሩን የሚነግርባት ቀን፤
ይቅርታ የሚጠይቅባት ቀን፤ ለፍቅሩ ሲል ትን ሽም ብትሆን ቅጣት ከፍሎ የመጣባት ቀን፤ በእርሱ እና በባለቤቱ መካከል የመነጋገር እና የመቀራረብ እንጂ፣ የመዋደድ እና ስሜት ለስሜት የመስማማት ችግር እንደሌለ መረዳቱን የሚገልጥባት ቀን ናትና፡፡

ግን ምን ያደርጋል፤ ሁለቱም ይህንን በየልባቸው ያውቁታል እንጂ አልተነጋገሩም፤ ሃሳባቸውንም በሌላ መንገድ አልተለዋወጡም፡፡

በዚህ የተነሣም በችግሩ መፍቻ ቀን ዋናው ቸግር ተፈጠረ፡፡

ሁለት የትዳር ነቀርሳዎች፡- አለመቀራረብ እና
አለመነጋገር፡፡

አብረው አንድ አልጋ ላይ እያደሩ፤ አብረው እየበሉ፤ አብረው እየኖሩ የማይቀራረቡ ባል
እና ሚስት አሉ፡፡

አንድ አልጋ ላይ የሚተኙት አንድ አልጋ ላይ መተኛት ስላለባቸው ብቻ ነው፡፡

ከመጋባታቸው በፊት የነበራቸው ጉጉት እና ናፍቆት አሁን የለም፡፡

ሳይተኙ እንቅልፍ ይወስዳቸዋል፡፡

አብረው ይበላሉ፤ በአንድ ማዕድ መሆኑ፣ አንድ ጠረጲዛ ላይ መሆኑ እንጂ ያኔ በፊት ለምሳ ሲገባበዙ የነበረው ናፍቆት እና ጉጉት የላቸውም፡፡

ዝም ብሎ መብላት ብቻ፡፡

እያንዳንዷን ቀን ልዩ፣ ደስታ የሚፈጠርባት
እና ከትናንት የተለየች ለማድረግ አይጥሩም፡፡

ዛሬም እንደ ትናንቱ፣ ነገም እንደ ዛሬ ነው፡፡

በስንት ልመና በስንት ጥየቃ፣ በስንት ደጅ ጥናት በስንት ጥበቃ፣እንግዲህ ምን ቀረሽ አገባሁሽ በቃ፣ እንደተባለው ይሆንባቸዋል፡፡

አገባኋት በቃ፤አገባሁት በቃ፤ ከንግዲህ ምን ቀረ? ብለው ያስባሉ፡፡

ሰው ተፈጥሮ አላለቀም፡፡ በየጊዜው ነው
የሚፈጠረው፡፡

ፈጣሪም ሰውን እንደ ተወለደ እንዲያልቅ አላደረገውም፡፡

በየቀኑ፣ በየሰዓቱ፣ በየደቂቃው ላስተዋለው ሰው እንግዳ ፍጥረት ነው፤ አዳዲስ ነገር ይታይበታል፡፡

ይህ ግን መቀራረብን ይጠይቃል፡፡

ባል እና ሚስት ከተቀራረቡ ሳይፋቱ በየቀኑ ይጋባሉ፤ ጋብቻቸው እየታደሰ ይሄዳል፡፡

የትና ንቷ ሚስት ከዛሬዋ ትለያለች፤ የዛሬው ባልም ከትናንቱ የተለየ ነው፡፡

ለውጥ፣ ዕድገት፣ ብስለት፣ አለ፡፡ መልክም ተለውጧል፡፡ ግን ቀርቦ የሚያየው ያስፈልገዋል፡፡

የዚያ ባል ችግሩ ሚስቱን አግብቷት እንጂ ቀርቧት አያውቅም ነበር፡፡

አብሯት ይኖራል እንጂ ከርሷ ጋር አይኖርም ነበር፤ ምድር በፀሐይ ዙርያ ስለምትዞር
ይመሻል ይነጋል እንጂ በእነርሱ የተለየ የሕይወት ጉዞ ምክንያት አይመሽም አይነጋም፡፡

በማክሰኞ እና በረቡዕ መካከል ከስሙ በቀር በሕይወታቸው ውስጥ ልዩነት የለውም፡፡

ሌላው ችግር ደግሞ ያለ መነጋገር ነው፡፡

መነጋገር ማለት በሚያውቁት ቋንቋ ማውራት ማለት ይደለም፡፡

እርሱንማ ከብትም ሲገናኝ እምቧ እምቧ ይባባላል፡፡ ይህ ግን መነጋገር አይደለም፡፡

በየጊዜው፣ በየሰዓቱ፣ ሁለመናን መለዋወጥ ማለት ነው፡፡ ካልተነጋገሩበት የምሥራች፣ የተነጋገሩበት መርዶ ይሻላል፡፡

ካልተነጋ ገሩበት ፍቅር የተነጋገሩበት ጠብ ይበልጣል፡፡

ካልተነጋገሩበት ስጦታ የተነጋገሩበት ንጥቂያ ይሻላል፡፡

ባል እና ሚስቱ ባለመነጋገራቸው ችግሩን በሁለት አቅጣጫ ፈቱት፡፡

የሁለቱም ፍላጎት ችግሩን ላንዴ
እና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ነበር፡፡ የሁለቱም ፍላጎት ፍቺ የሚባለውን ነገር ላለማየት ነበር፡፡

የሁለቱም ፍላጎት ሠላሳኛዋን ቀን መገላገል ነበር፡፡

ነገር ግን ባለ መነጋገር ምክንያት በሁለት አቅጣጫ ሆነ፡፡

እርሷ ሞትን መረጠች፤ እርሱ ደግሞ ይቅርታን መረጠ፡፡

ችግሩ የመጣው በዚህ ጉዳይ ላለመነጋገር ሲወስኑ ነው፡፡

እርሷ በጉዳዩ ትጨነቃለች፤ ለምን ይሆን ከኔ መለየት የፈለገው? የሚለው ጥያቄ ያሳስባት ነበር፡፡

በሃሳብ ብዛትም እየከሳች ሄዳ ነበር፡፡

ለዚህም ነበር በየቀኑ ሲያቅፋት ትቀልለው የነበረው፡፡

እርሱ ግን መቅለሏን እንኳን ለመጠየቅ ፈራ፡፡

እርሱ ከራሱ ጋር እንጂ ከእርሷ ጋር አይነጋገርም ነበር፡፡

እናም አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ቢሆንም እንኳ፤ በትዳር ውስጥ ግን ዝምታ ወርቅ አይደለም፡፡
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
በምስል እና በቪድዮ የተደገፍ አስተማሪ ይዘት ያላቸው ቁምነገሮች እየሰራን ስለሆነ ከዚህ በታች ባለው YouTube channel ሊንክ በመግባት Subscribe በማድረግ ያበረታቱን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን::
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q

24/09/2020

/እውነተኛ ታሪክ/
⚂አራት ሚስቶች የነበሩት አንድ ሀብታም ነጋዴ ነበር፡፡
አራተኛ ሚስቱን ከሌሎች
አብልጦ በእጅጉ ይወዳታል፡፡ ስለሚወዳትም ጥሩውን ሁሉ ለእርሷ በመስጠት
ይንከባከባታል፤ያስደስታታል፡፡
ሦስተኛ ሚስቱን መውደድም ብቻ አደለም
ይኮራባታል፣ ይመካባታልም ጭምር፡፡ ይዟት በአደባባይም ለመታየት ይፈልጋል
ነገር ግን ጥላው እንዳትሄድ በጣሙን ይሰጋል፡፡ ሁለተኛ ሚስቱንም እንዲሁ
ይወዳታል፡፡ ይች ሁለተኛ ሚስቱ በነገሮች አስተዋይና ብልህ ታጋሽም በመሆኗ
ይመካባታል፡፡ ነጋዴው አንዳች እክል የገጠመው እንደሁ ችግሩን ታቅፎ
እሚያመራው ወደ ሁለተኛ ሚስቱ ነው ፡፡ እሷም በአስቸጋሪው ሰዓት ከጭንቀቱ
ትገላግለዋለች፡፡
የመጀመሪያ ሚስቱ በጣም ታማኝ አጋሩ ናት፡፡ ቤቱንና ንግዱን
የምትመራለትና የምታስተዳድርለት እሷው ነች፡፡ እሷ በጣም የምታፍቅረው
ቢሆንም እሱ ግን ስለማያፈቅራት አንድም ቀን በትውስታው ውስጥ ቦታ
ሰጥቷት አያውቅም ነበር፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ህመም ተሰማውና ማለፉን ባሰበ ጊዜ የተድላ ዓለሙን
እያስታወሰ እንዲህ አሰበ “አራት ሚስቶችና የተትረፈረፈ ሀብት አለኝ ነግር ግን
በሞት ጊዜ ብቻየን እሆናለሁ፡፡ እንዴት ብቻየን እሆናለሁ?” በማለት አራቱንም
ሚስቶች በማስጠራት ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡
“ሁላችሁንም በጣም እወዳችኋለሁ:: የሚያምሩ አልባሳትንም እያለበስኩ
ሳስጌጣችሁ ኖርኩ፡፡ አሁን ግን ልሞትናውና ከብቸኝነቴ ታድኑኝ ዘንድ ተከተሉኝ”
አላቸው፡፡
⚂አራተኛው ሚስቱ “በፍጹም አይሆንም” ስትል መልሱን ሰጥታው
ከአካባቢው ተሰወረች፡፡ ነጋዴው በሰማው ምላሽ ልቡ ተነካ፡፡
⚂ ለሦስተኛዋ
ሚስቱ “በሕይዎቴ ሙሉ ስወድሽ ኑሪያለሁ አሁን አብረሽኝ ልትሆኝና
ወደምሄድበት ልትከተይኝ ትፈቅጃለሽ?” አላት በአዘኔታ ሁኖ መልስ ሲጠባበቅ
“አይሆንም ሕይዎት አትጠገብም ፡፡ እዚህ መኖር መልካም ነው፡፡ እናም ከአንተ
ሞት በኋላ አግብቸ መኖር እሻለሁ” አለችው፡፡ ይህ ሀብታም ነጋዴ ልቡ ዝቅ
ሲልና ወደ ቀዝቃዛነት ሲለወጥ ተሰማው፡፡ አሁንም በተስፋ መቁረጥ ሁኖ
“በሕይዎቴ ሙሉ እርዳታን ስፈልግ ወደ አንች ስመላለስ ኑሪያለሁ፡፡ ስትረጅኝም
ነበር፡፡ አሁንም እርዳታሽን ፈልጊያለሁና እርጅኝ” ሲል ⚂ሁለተኛ ሚስቱን ጠየቃት፡፡
“በዚህ ሰዓት ልረዳህ ባለመቻሌ አዝናለሁ፡፡ ማድረግ የምችለው አንተን ወደ
መቃብርህ መሸኘት ብቻ ነው” ስትለው መብርቅ የመታው ያህል ክው አለ፡፡
በድንጋጤ ስሜት ተውጦ እያለ “የትም ብትሄድ እከተልሃለሁ፤ አንተጋ
እሆናለሁ!” የሚል ድምጽ ሲያስተጋባ ተሰማው ዓይኑን ሲያነሳ የተጎሳቆለ እይታ
ያላት የመጀመሪያ ሚስቱ ነበረች ነጋዴው ሳግ እየተናነቀው “ሲኖረኝና ስችል
ልንከባከብሽ ይገባኝ ነበረ” በማለት እቅፍ አድርጎ ወደሰውነቱ አስጠጋት፡፡
በመሠረቱ ሁላችንም በሕይዎታችን አራት ሚስቶችን አኑረን ይሆናልና የእኛም
ታሪክ ሊሆን ይችላል፡፡
1. አራተኛው ሚስታችን # ፈራሹ__ስጋችን ነው፡፡ ለምቾቱና ለውበቱ ተጨንቀን
ብንደክምም ቀሪ እንጅ ተከትሎን አይሄድም፡፡
2. ሦስተኛው ሚስታችን አለን የምንለው ነገር
ነው፡፡
ይሄም እኛ ስንሞት ወደሌሎች የሚተላለፍ ነው፡፡
3. ሁለተኛው ሚስታችን #ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችን ናቸው፡፡ በሕይወት ዘመናችን
የቱንም ያህል ቀረቤታና ቁርኝት ቢኖረንም ማድረግ የሚችሉት እስከ መቃብር
መሸኘት ብቻ ነው፡፡
4. የመጀመሪያዎ ሚስታችን ናት፡፡በመልካም ስራ እናድሳት ነገ አብራን ትኖራለች ቁስና ሀብት ስናሳድድ
ጎን ገፍተናት ቢሆንም አብራን የምትሆነው እሷው ነችና በመጨረሻው ሰዓት በመጨረሻ ነው ያታሪኩ ጭብጥ፡፡
ታሪኩ አስተማሪ ሁኖ ካገኛችሁት ሼር ያርጉት።
አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሼርና ላይክ በማድረግ ለወዳጅዎ ያካፍሉ::
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
➹share & like
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በምስል እና በቪድዮ የተደገፍ ብዙ ነገሮች አሉን YouTube channel በመግባት ማግኘት ይችላሉ።Subscribe ማድረግም አይርሱ::
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q

🌹👏✅መልካም ጋብቻ ሎዛከክርስታናዊ ጋብቻ ገጽ
20/09/2020

🌹👏
✅መልካም ጋብቻ ሎዛ
ከክርስታናዊ ጋብቻ ገጽ

🌹🌹ሎዛ ዛሬ ሊቲሞሸር ነው🌹🌹መልካም ጋብቻብርቅየ የኢትዮጵያ ልጅ
20/09/2020

🌹🌹ሎዛ ዛሬ ሊቲሞሸር ነው

🌹🌹መልካም ጋብቻ
ብርቅየ የኢትዮጵያ ልጅ

🌹🌹ትዳር ከእግዚአብሄር እንጅ ከሰው አደለም💖🌹💖🌹💖🌹💖🌹💖🌹💖🌹💖🌹ብዙ ጊዜ በዘመናችን ውስጥ የምገኙ ሰዎች ትዳር  #በምርጫ ብዛት የሚትገኝ ይመስላቸዋል ግን አደለም ለአይን ያሸበረቀ ሁሉ ለት...
18/09/2020

🌹🌹ትዳር ከእግዚአብሄር እንጅ ከሰው አደለም💖🌹💖🌹💖🌹💖🌹💖🌹💖🌹💖🌹

ብዙ ጊዜ በዘመናችን ውስጥ የምገኙ ሰዎች ትዳር #በምርጫ ብዛት የሚትገኝ ይመስላቸዋል ግን አደለም ለአይን ያሸበረቀ ሁሉ ለትዳር የምሆን አደለም ።

አንድ ጋደኛ አለኝ ብዙ ጊዜ በአንድ አቋም አይጸናም ብዙ ሴቶችን ይወዳል እንዳየም አንድ ቆንጅ ሴት ካለፈች ይከተላታል የራሱ ለማድረግም ስጥር አየዋለሁ ግን እንድ እለዋለሁ አንተ ሌጅ ያለህን፣የሰጠህን ብትይዘው ይበጀሃሌ እለዋለሁ ። ይሆ እስከ ዛሬ አላገባም
🌹💖🌹

👌💖 ክርስታናዊ ጋብቻመልካም ምስት ከእግዚአብሄር ዘንድ ናት እንድሁም መልካም ባል ።💖 ብዙ ጊዜ ምርጫችን ትክክል የማይሆንበት ምክንያት እግ/ር በነገራችን/በጋብቻን ላይ ጣልቃ ሰለማናስገባ ነ...
16/09/2020

👌💖 ክርስታናዊ ጋብቻ

መልካም ምስት ከእግዚአብሄር ዘንድ ናት እንድሁም መልካም ባል ።💖

ብዙ ጊዜ ምርጫችን ትክክል የማይሆንበት ምክንያት እግ/ር በነገራችን/በጋብቻን ላይ ጣልቃ ሰለማናስገባ ነው ... 👏ይቀጥላል
👉Page like and share በማድረግ ለወዳጁ ያድርሱ👍👎

15/09/2020

Address

አድስ አበባ
Addis Ababa
ተመሰገን

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ክርስታናዊ ጋብቻ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category