Gordena Online

Gordena Online # ወቅታዊ መረጃዎችና ዜናዎች : ባህል : ቅርስና ታሪክ የተመለከቱ ጉዳዮች የሚቀርቡበት ሚዲያ ነው ::

 # ብዙ ካልተወራላቸው የጉራጌ ብሎም የኢትዮጵያ ባለውለታዎች :- >> ጀነራል ይልማ ሺበሺ - ከአለምገና ቡታጅራ ወላይታ መንገድ ያሰሩ !>> ወልደስላሴ በረካ - ከአለምገና ወልቂጤ ጅማ መን...
22/04/2024

# ብዙ ካልተወራላቸው የጉራጌ ብሎም የኢትዮጵያ ባለውለታዎች :-
>> ጀነራል ይልማ ሺበሺ - ከአለምገና ቡታጅራ ወላይታ መንገድ ያሰሩ !
>> ወልደስላሴ በረካ - ከአለምገና ወልቂጤ ጅማ መንገድ ያሰሩ !
===
# ጀነራል ወልደስላሴ በረካ ለማስታወስ በቀድሞ ጉራጌ ዞን የመታሰቢያ ሐውልት ግቡሬ ላይ እንዳሰራላቸው የሚታወስ ነው ሆኖም ጀነራል ይልማ ሺበሺ ግን እሰካሁን በስማቸው የተሰራ አንድ መታሰቢያ የላቸውም ::
===
# በዚህ አጋጣሚ ለዚህ ጀግና መታሰቢያ የሚሆን የምስራቅ ጉራጌ ዞን አንዳች መታሰቢያ ቢያሰራላቸው እንላለን !
===
# Gordena Online

ፊታውራሪ ሩጋ አሻሜ.......ብልሁ የአገር ሰው !!! # ጣልያን ከአገራችን ተባሮ ነፃነት ከተመለሰ በሃላ አንድ ጉልህ ችግር አጋጠመ፡፡ ከትንሽ እስከ ትልቅ የንግድ መስክ በዓረቦች(የመኖች)...
21/04/2024

ፊታውራሪ ሩጋ አሻሜ.......ብልሁ የአገር ሰው !!!
# ጣልያን ከአገራችን ተባሮ ነፃነት ከተመለሰ በሃላ አንድ ጉልህ ችግር አጋጠመ፡፡ ከትንሽ እስከ ትልቅ የንግድ መስክ በዓረቦች(የመኖች) የተያዘ ሆነ፡፡ የአገረኛው ዜጋ ሸማች እንጂ ባለ ሃብት መሆን አልቻለም::
# ይህን አገር የሚጎዳ ችግር በዘለቄታው የሚፈታ መላ እንዲያመጡ በወቅቱ የእርሻ፡ንግድና እንዱስትሪ ምኒስትር የነበሩት መኮነን ሃብተወል ( የፀሃፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ ታላቅ ወንድም) ሰራተኞቻቸውን አዘዙ፡፡
# በወቅቱ ዕድሜው 30 ዓመት ያልሞላው ወጣቱ የምኒስትሩ ልዮ ረዳት የነበረው ሩጋ አሻሜ( ሃላ ፊታውራሪ) አንድ ሃሳብ ተገለጠለት ፡፡ በሃሳቡ መሰረትም የንግድ ፍላጎትና ተነሳሽነት ያላቸው 40 የጉራጌ ነጋድየዎች በአንድ ዓመት የሚመለስ ለያንዳንዳቸው 700 ብር በመንግስት እንዲሰጣቸው በማድረግ በመዲናችን አዲስ አበባ በየዓረቡ መደብር አጠገብ ሱቆቻቸው እየተከሉ ንግዳቸው እንዲጀምሩ ተደረገ፡፡
# የጉራጌዎች የስራ ትጋት ፡የነዋሪው መልካም ትብብር ተጨምሮበት ዓመት ሳይሞላ ከ ዓርባዎቹ ነጋዴዎች ሰላሳ ሦስቱ በዓረቦቹ ተይዞ የነበረውን ቀልብሰው ስለ ወሰዱት የመኖቹ የነበራቸውን ሱቅ እየዘጉ ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛትም የአገራችን ዜጎች በንግድ ዘርፍ መሳተፍ ጀመሩ፡ ጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድም በወጣቱ ሩጋ አሻሜ ብልሃት በአገር ልጆች ቁጥጥር ስር ገባ፡፡
===
# ከዚያ ጊዜ ወዲህ ጉራጌ በንግዱና በስራ ታታሪነት በመላው ኢትዮጵያ ይበልጥ እየታወቀ መጣ !
# Gordena Online

21/04/2024
ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ምየቡኢ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ለሁለተኛ ዙር  ያሰለጠናቸው 91  ደንብ አስከባሪዎች  እና ሚሊሻዎችን  በዛሬው ዕለት አስመርቋል።በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ...
21/04/2024

ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ም

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸው 91 ደንብ አስከባሪዎች እና ሚሊሻዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ የጸረ ሰላም ሀይሎች እንደሀገርም ሆነ እንደቀጠና ጥፋት እያደረሱ እንደሆነ አንስተዋል።

እንደኛም አካባቢ የጸረ ሰላም ሀይሉ በተለያዩ የሶዶ ወረዳ የአካባቢዎች ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ እና የዚህ ጸረ ሰላም ሀይል እያደረሰ ያለውን ጥፋት እና እንቅስቃሴ ለማስቆም መላው የአካባቢው ማህበረሰብ በከፍተኛ ወኔ በመነሳሳት በየቀበሌው በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ እና ውጤትም እየመጣ እንደሆነ ተናግረዋል።

የከተማችን ህዝብ ለየትኛውም ኢትዮጵያዊ እንኳን ደህና መጣችሁ በላለዲ ዮምጣ ብሎ የሚቀበልና የሚያስተናግድ ከየት መጣህ ? ማነህ ብሎ የማይጠይቅ አቃፊ ህዝብ" ነው ብለዋል።

ሆኖም ይህ መልካም ዕሴቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለፀረ ሰላም ሀይል ግብዓት ለመሆን ከተማችንን እንደ ምሽግ ለመጠቀም ፣ የስንቅና ሎጅስቲክስ ምንጭ ለመሆንና ከተማችንና ቀጠናችንን ለማወክ እንዲሁም ከተማችን ላይ ጤናማ ባልሆነ መልኩ በአቀራጭ ለመበልፀግና በተለያዩ አልባሌ ተግባራት ለመሰማራት ለሚሹ አካላት ከተማችን አትመችም ለዚሁ ዓላማ በግልፅ የተገኘ ይጠየቃል ያሰበ ካለም ቶሎ ከተማችን ለቆ እንዲወጣ እንመክራለም" ሲሉ ተናግረዋል።

በምትኩ ግን በሰላማዊ መንገድ ሰርቶ ለመለወጥ ለማደግና ኢንቨስት ለማድረግ የሚመጣ የትኛውም ኢትዮጵያዊ በመሉ የከተማችን ህዝብና ወጣት የምጣቢ ኑ አብረን እንለወጥ ከተማችንም አብረን እናሳድግ ይላቹሀል" በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ይህም ህዝባችን ምናያህል እራሱን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆነ እና ሰላም ወዳድ ማህበረሰብ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጽጥታ ጽ/ቤትም ከጽጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የጸረ ሰላም ሀይሉ ወደ ከተማው እንዳይገባ አስቀድሞ የመከላከልና የከተማው ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ህዝቡን ያሳተፈ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በዛሬው ዕለት የተመረቁ ደንብ አስከባሪዎች የቡኢ ከተማ ዕድገት ተከትሎ ለጸረ ሰላም ሀይሉ አጋዥ ለመሆን ወደ ከተማዋ የሚገቡ ጸጉረ ለውጦች በመከላከል የከተማዋ ዘላቂ ሰላም ማስከበር እንደሚገባቸው ገልጸዋል።በዚህ ሂደትም መላው የከተማ ማህበረሰብ ለጸጥታ አካሉ አጋዥ እንዲሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ስልጠናውን በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የፖሊስ አባላት፣የመከላከያ አባላትና የሶስቱም ቀበሌዎች አስተዳደር ጽ/ቤቶች እና ስልጠናውን በዲሲፕሊን ሲከታተሉ ለነበሩ የደንብ አስከባሪዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ሰላምናብጽጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘርጋው ንጉሴ የጸረ ሰላም ሀይሎች በአገራችን ብሎም በአጎራባች ቀበሌዎች ውስጥ በሚኖሩ ህዝብ ላይ የሞት ፣የማፈናቀል እና የዘረፋ ወንጀል እየፈጸመ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ይህ የጸረ ሰላም ሀይል እያደረሰ ያለውን ወንጀል ለማስቆም መላው የአካባቢው ህዝብ በቁጣና መነሳሳት ተገቢውን ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር በፈጣን ዕድገት ላይ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጠላትን ዓይን በመሳብ ለጥፋት ሀይሎች ምቹ ሁኔታ ሊፈጥሩ የሚችሉ አጥፊዎችና ተባባሪዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ በመገመት ለህዝብ ደህንነት ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን አስቀድሞ መረጃዎችን በመሰብሰና በመተንተን ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የዛሬ ተመራቂዎችም ከዕለት ዕለት ተግባራቸው ጎን ለጎን የጸረ ሰላም ሀይሉ በአጎራባች ቀበሌዎች ህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ወንጀል መመከት እና ወደ ከተማችን ዘልቆ እንዳይገባ አስፈላጊውን የጸጥታ ስራ መስራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ስልጠናውን በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የፖሊስ አባላት፣የመከላከያ አባላትና የሶስቱም ቀበሌዎች አስተዳደር ጽ/ቤቶች እና ስልጠናውን በዲሲፕሊን ሲከታተሉ ለነበሩ የደንብ አስከባሪዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
===
# ዘገባው የከተማ አሰተዳደሩ የመንግስት ኮምኒኬሽን ነው

የሰላም አባቶች በሶዶ ጉራጌየጎርደና ሸንጎ ! 🌟🌟🌟ሀዋሳ፣ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሰላም የሁሉ ነገር እናት ናት፤ ሰላም ካለ ሁሉ ነገር አለ፤ ሰላም ካለ ሰላማዊ ህይወት አለ፤ ሰ...
21/04/2024

የሰላም አባቶች በሶዶ ጉራጌ
የጎርደና ሸንጎ !
🌟🌟🌟
ሀዋሳ፣ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሰላም የሁሉ ነገር እናት ናት፤ ሰላም ካለ ሁሉ ነገር አለ፤ ሰላም ካለ ሰላማዊ ህይወት አለ፤ ሰላም ያላቸው ህዝቦች ተፊሪና ተከባሪ ሀገር ከጠንካራ ኢኮኖሚ ጋር ይገነባሉ።

ሰላም በእጃችን ባለ ጊዜ ብዙም የጠቀሜታው ልኬት አይታየንም። ድንገት ስያመልጠን ግን ዋጋው ከእንቁ የከበረ መሆኑን ለመረዳት አፍታም አይፈጅብንም።

በርካታ ሀገራት ሰላማቸውን ለመጠበቅ ወታደራዊ አቅማቸውን ከህግ ተቋማት ጋር አቀናጅተው ይጠቀማሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ ጥንታዊ ሀገራት ደግሞ ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሰላም መንገድ አድርገው ይመርጣሉ።

የማህበራዊ ሳይንስ ሊሂቃን ሰላም ከእጅ ከወጣ በኋላ ለመመለስ ከመሯሯጥ ይልቅ አስቀድሞ የሰላም አደፍራሽ ጉዳዮችን መከላከያ በእጅጉ አዋጭ ነው በማለት ይመክራሉ።

ሰላምን ለማፅናት አመታትን፤ ሰላምን ለማጣት ደቂቃዎች ብቻ መብቃታቸው ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል።

''የሶዶ ክስታኔ ጎርደና ሸንጎ'' በኢትዮጵያ ድንቅ የሰላም መጠበቂያ እና መመለሻ ባህላዊ ሀብት ነው። የሸንጎው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ክስታኔ ጉራጌዎች ሀብት ነው።

"የሶዶ ክስታኔ ጎርደና'' ከትላልቅና ውስብስብ ግጭቶች ጀምሮ ሸንጎ ከዕለት ዕለት አለመግባባቶችን የመፍታት አቅም አለው። ግጭቶችን አስቀድሞ ለመከላከል ዕድል ይሰጣል።

የዕድሜ ባለፀጋው እና የሶዶ ክስታኔ ሸንጎ አባል የሆኑት ሊቀ ህሩያን ብርሃኑ ዋካ ለደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት እንደገለፁት የሸንጎው መነሻም መድረሻም ሰላም ነው ይላሉ።

ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን የበረታን ማጀገን የሰነፈን ማበርታት እንዲሁም የማህበረሰቡን እሴትን ለትውልዱ ማውረስ ነው።

አቶ ጉግሳ ወሪሶ እሳቸውም የሀገር ሽማግሌ እና የሸንጎው ምክትል ሰብሳቢ ናቸው። ሸንጎው ትላልቅ እና ውስብስብ ችግር የመፍታት አቅም አለው ብለው በመፍታትም አቅሙን አሳይቷል ብለዋል።

የአከባቢው ማህበረሰብ ከዘመናት በፊት ሸንጎውን ሲያቋቁም ፍትህን ለማስፈን እና አንድነትን ለማስጠበቅ ነው። የሚገጥሙ ችግሮችን በብልሃት ለማለፍም ይጠቀሙበታል።

እንደ ሀገር የገጠመንን ችግሮችን እንዲህ አይነት በሳል እሴቶችን በመጠቀም መፍታት አለብን በማለት የሀገር ሽማግሌው አቶ ጉግሣ ይመክራሉ ።

አቶ ጌታቸው ተካ የሶዶ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ሀላፊ ናቸው። የፅ/ቤቱ ሀላፊ የሀገር ሽማግሌዎች ሸንጎ የአከባቢውን ሰላም እና ፀጥታ ለማረጋገጥ የገዘፈ ሚና እየተጫወቱ ነው በማለት አረጋግጠዋል ።

በተለይም በኦሮሚያ አዋሳኝ አከባቢዎች ከጸረ ሰላም ሀይሎች አንፃር የተጋረጡ አደጋዎችን ለመከላከል በተደረገው ርብርብ የሸንጎ አባላቱ ጥረት ውጤታ ነበር ብለዋል።

የሀገር ሽማግሌዎች ለአከባቢው ማህበረሰብ ሰላም መረጋገጥ ላበረከቱት አዎንታዊ አበርክቶ በዞን ደረጃ ዕውቅና ለመስጠት መታቀዱን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ

21/04/2024

# ዶ/ር አብይ አህመድ ሰለጎጎት ቃል ኪዳን የተናገሩት !
🌟🌟🌟
# Gordena Online

21/04/2024

ዶ/ር አብይ አህመድ በትላንትናው ዕለት ሰለጉራጌ ሕዝብ ከተናገሩት በጥቂቱ !
===
# Gordena Online

የዛሬ ጨዋታ እንዴት አገኙት !!=== # ዛሬ በነበረው ጨዋታ ምስራቅ ጉራጌ እግር ኳስ ቡድን ከዚህ በፊት የምናውቀው አይነት አልነበረም ሰብስቡ : በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ እጅግ በወረደና ...
20/04/2024

የዛሬ ጨዋታ እንዴት አገኙት !!
===
# ዛሬ በነበረው ጨዋታ ምስራቅ ጉራጌ እግር ኳስ ቡድን ከዚህ በፊት የምናውቀው አይነት አልነበረም ሰብስቡ : በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ እጅግ በወረደና ከአቅም በታች በሆነ አጨዋወት ነበር ሲጫወት የነበረው :: ተጫዋቾቹ እርስበርስ እንኳን መናበብ አቅቷቸው ተመልክተናል :: የጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን በ10 ተጫዋች ሆኖ እንኳ ሙሉ የጫወታ ብልጫ ነበረው :::
===
# ምስራቅ ጉራጌ በተለይ ከማረቆ ልዩ ወረዳ ጋር በነበረው ጨዋታ ቡድኑ እጅግ ጠንካራ የሚባል ሰብስብ ነበረው : ዛሬ የታየው ግን ከዚህ በተቃራኒ ነበር ::
===
# ዛሬ በተደረገው ጨዋታ የምስራቅ ጉራጌ እግር ኳስ ቡድን ማሸነፍ የሚችለውን ጨዋታ እንዳያሸነፍ የሆነው የመጀመሪያው ሰብስብ ባለመኖሩና አቅም ያላቸው ልጆች ቤንች እንዲሆኑ ብሎም በቅያሬ እንዲወጡ በመደረጉ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም :::
===
# አሸናፉው ጉራጌ ዞን እጅግ ድንቅ አጨዋወት ነበር ያሳየው : በዚህም የጨዋታው አሸናፊ መሆን ችሏል :: በዚህ አጋጣሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን :: ቀጣይ ለምታደርጉት ጨዋታ መልካም ዕድል ተመኝተናል !!
🌟🌟🌟
===
# GOM

 # ጉራጌ ዞን በመለያ ምት ምስራቅ ጉራጌን በመርታት ለፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል  !=== # GOM
20/04/2024

# ጉራጌ ዞን በመለያ ምት ምስራቅ ጉራጌን በመርታት ለፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል !
===
# GOM

20/04/2024

# ሙሉ 90''

# ምስራቅ ጉራጌ 1- 1 ጉራጌ ዞን አቻ !

ወደ መለያ ምት አምርተዋል !!
🌟🌟🌟
# GOM

 # 70'' # ምስራቅ ጉራጌ 1-0 ጉራጌ ዞን !🌟🌟🌟 # GOM
20/04/2024

# 70''

# ምስራቅ ጉራጌ 1-0 ጉራጌ ዞን !

🌟🌟🌟
# GOM

 # የመጀመሪያ 45'' # ምስራቅ ጉራጌ 1-0 ጉራጌ ዞን !🌟🌟🌟 # GOM
20/04/2024

# የመጀመሪያ 45''

# ምስራቅ ጉራጌ 1-0 ጉራጌ ዞን !

🌟🌟🌟
# GOM

 # የዶ/ር አብይ አህመድ የሕዝብ አቀባበል በጉራጌ መዲና ወልቂጤ ከተማ !****    **** # የጉራጌ ሕዝብ ከመንግስት በማጋጨት የራሳቸው የፓለቲካ ጥቅም ለማጋበስ ሲጥሩ የነበሩ ሀይሎች ...
20/04/2024

# የዶ/ር አብይ አህመድ የሕዝብ አቀባበል በጉራጌ መዲና ወልቂጤ ከተማ !
**** ****
# የጉራጌ ሕዝብ ከመንግስት በማጋጨት የራሳቸው የፓለቲካ ጥቅም ለማጋበስ ሲጥሩ የነበሩ ሀይሎች አሁን ወደ ጎሬያቸው ተመልሰዋል !
🌟🌟🌟
# GOM

19/04/2024

# ናልማነ !
🌟🌟🌟
> ፀጋዬ ሲሜ > ደሳለኝ መርሻ > ይታገሱ መለሰ
> ረሻድ ከድር > ምናሉሽ ረታ በጋራ ያዜሙት !
# በይ/ር ተንሳ ጉራጌ --- የተሰኘው ለልማትና ለአብሮነት የሚያነሳሳው ጉራጊኛ ዘፈን እንደ አዲሰ በአዲስ ቅንብርና በአዲስ ክሊፕ መሰራት ቢችል የማህበረሰብ አንድነት በማጠናከሩ ረገድ ከፍተኛ መነሳሳትን ይፈጥራል የሚል ምክረ ሀሳብ ለማቅረብ ወደድን !
===
# ናልማነ ❤ ጋበዝናቹ !!
# Gordena Online

19/04/2024

# የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰመሰተዳደር አቶ እንደሻው ጣሰው በወልቂጤ ከተማ ያደረጉት ቆይታ !
==
# DRT

¤  የዕለቱ ምርጥ ፎቶ ! *** 🌟🌟🌟 ***¤ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል !      🌟🌟🌟       GOM
19/04/2024

¤ የዕለቱ ምርጥ ፎቶ !
*** 🌟🌟🌟 ***
¤ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል !
🌟🌟🌟
GOM

 # Updated !========= # የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩልዩ የስፓርት ሻምፒዮና ውድድር !==== # ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉ አራት ቡድኖች ተለይተዋል ።ምድብ ''ሀ''1- ጠንባሮ ...
19/04/2024

# Updated !
=========
# የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩልዩ የስፓርት ሻምፒዮና ውድድር !
====
# ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉ አራት ቡድኖች ተለይተዋል ።
ምድብ ''ሀ''
1- ጠንባሮ ልዩ ወረዳ
2- ጉራጌ ዞን
----
ምድብ ''ለ''
1- ምስራቅ ጉራጌ ዞን
2- ከምባታ ዞን
==
# በዚሁ መሰረት በነገው እለት ለፍፃሜ የሚቀርቡ ሁለት ቡድኖች የሚለዩበት ጨዋታ ይካሄዳል ::
# 7:00 ሰዓት ጠንባሮ ዞን ከከምታ ዞን
# 5:00 ሰዓት ምስራቅ ጉራጌ ዞን ከጉራጌ ዞን ጋር እንደሚጋጠሙ የተያዘው ፕሮግራም ያሳያል ::
===
# ነገ ቅዳሜ በሚደረገው የእግር ኳስ ፍልሚያ የምስራቅ ጉራጌና የጉራጌ ዞን ግጥሚያ እጅግ ተጠባቂና ታሪካዊ ያደርገዋል ::
===
# Gordena Online !

 # የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊያ ክልል ልዩልዪ የስፓርት ሻምፒዮና ውድድር እንደቀጠለ ነው ::== # በዛሬው ዕለት በምድብ ሁለት ከምባታ ዞን ከማረቆ ልዩ ወረዳ ተጫውተው ጨዋታው አንድ አቻ በሆነ...
19/04/2024

# የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊያ ክልል ልዩልዪ የስፓርት ሻምፒዮና ውድድር እንደቀጠለ ነው ::
==
# በዛሬው ዕለት በምድብ ሁለት ከምባታ ዞን ከማረቆ ልዩ ወረዳ ተጫውተው ጨዋታው አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል ::
===
# በዚህ መሰረት ከምባታ ዞን ከምስራቅ ጉራጌ ዞን በመቀጠል 7 ነጥብ በመሰብሰብ ከምድቡ በሁለተኛነት ለሩብ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጦል ::
===
# ከምድብ ''ለ'' ማረቆ ልዩ ወረዳ , ቀቤና ልዩ ወረዳና ሀላቦ ዞን ተሰናባቾች ሆነዋል :::
===
# በነገው ዕለት የምስራቅ ጉራጌ እግር ኳስ ቡድን 7:00 ሰዓት ላይ በክሪስክሮስ ከምድብ ''ሀ'' ሁለተኛ ከወጣው ቡድን ጋር የሚጋጠም ይሆናል ::
===
# መልካም ዕድል !
# በነገው ዕለት አይቀርም !!
===
# Gordena Online

ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም ቡታጅራየስፖርት ሉዑካኑ እያስመዘገበ ባለው ውጤት እጅግ ደስተኞች ነን:-አቶ በለጠ ጫካየምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ልዑካን ቡድን በክልል ውድድር  እያስመዘገበ ባ...
19/04/2024

ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም ቡታጅራ

የስፖርት ሉዑካኑ እያስመዘገበ ባለው ውጤት እጅግ ደስተኞች ነን:-አቶ በለጠ ጫካ

የምስራቅ ጉራጌ ዞን እግር ኳስ ልዑካን ቡድን በክልል ውድድር እያስመዘገበ ባለው ውጤት እጅግ ደስተኞች መሆናቸው የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ ገለፁ።

ከንቲባው ይህንን የተናገሩት እግር ኳስ ቡድኑ በ1ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ ጨዋታዎች፣ የባህል ስፖርቶች ውድድርና የባህል ፌስቲቫል ሻምፒዮና የግማሽ ፍፃሜ መቀላቀሉን አስመልክቶ ለማበረታታት በተዘጋጀው የምሳ ግብዣ ፕሮግራም ወቅት ነው።

በመጣው ውጤት ደስተኞች ነን አብዛኛው ማህበረሰባችን ስፖርት ወዳድ ለስፖርት የሚያሳየው አንድነት ፍቅር ልዩ ትርጉም በመሆ አሻም ለማለትና የምሳ ግብዣ ለማድረግ ተገኝተናል በማለት ቡድኑ እስካሁን በስኬት እየገሰገሰ ያለበት ሁኔታ አድንቀዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን በተመሰረተበት ማግስት በማዕከላዊ ክልል የመጀመሪያ የሆነው ታሪካዊ ዋንጫ በማንሳት ታሪካዊ ቡድን እንዲሆን በስፖርታዊ ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መልዕክታቸውንና መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ ኑሪ ከተማ አስተዳደሩ ቡድኑ ለማበረታታትና የምሳ ግብዣ ለማድረግ ቀዳሚ መዋቅር በመሆን ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለዞኑም ሆነ ለክልሉ የመጀመሪያ የሆነውን ዋንጫ ቡድኑ እንደሚያነሳ እምነት እንዳላቸው በመግለፅ ቡድኑ በመንፈስ ጥንካሬ በመጎልበት ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው አንስተዋል።

የዞን መዋቅሩ የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ያነሱት የመምሪያ ኃላፊው ማህበረሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ገልፀዋል።

የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አቶ ሲሳይ መንግስቱና የመሃል ሜዳ ተጫዋችና የቡድኑ አንበል ወጣት ቴዎድሮስ ከበደ በጋራ በሰጡት አስተያየት ለተደረገላቸው የማበረታቻና የምሳ ግብዣ ፕሮግራም ለከተማ አስተዳደር ምስጋናቸው አቅርበዋል።

በቀጣይ ጊዜያት ቀሪ ጨዋታዎች ውጤት በማስመዝገብ ዋንጫ በማንሳት ለዞኑ ማህበረሰብ ለማበርከት ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ቡድኑ ቅዳሜ ዕለት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ከምድብ ሀ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ የሚያጠናቀቀውን ቡድን ቀን 7:00 የሚገጥም ይሆናል።

ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

 # ርዕሰመሰተዳድሩ በጉራጌ መዲና በወልቂጤ ከተማ !
19/04/2024

# ርዕሰመሰተዳድሩ በጉራጌ መዲና በወልቂጤ ከተማ !

ሚያዚያ 11/2016 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር  በወልቂጤ ከተማ ውይይት እያካሔዱ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳ...
19/04/2024

ሚያዚያ 11/2016

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር በወልቂጤ ከተማ ውይይት እያካሔዱ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር በሰላም እና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት እያካሔዱ ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ ወልቂጤ ከተማ ሲገቡ የዞኑ ወጣቶች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ይግለጡ አብዛ ፣የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተስፋዬ መኮንን

ሚያዝያ10/2016ዓ.ም================   የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሸው ጣሰው ነገ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር በሰላምና ልማት ዙሪያ በወልቂጤ ከተማ...
18/04/2024

ሚያዝያ10/2016ዓ.ም
================ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሸው ጣሰው ነገ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር በሰላምና ልማት ዙሪያ በወልቂጤ ከተማ ውይይት እንደሚያካሂዱ ተገለጸ።

የማዕከላዊ ኢትየዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሸው ጣሰው ክልሉ ከተመሰረተ ጀምሮ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሰላምና ልማት ዙሪያ ሲመክሩ መቆየታቸውን ተጠቁሟል፡፡

ክልሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም የክልሉን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥና በሀገሪቱ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ነገ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና በሰላም ጉዳዮች ዙርያ በስፋት እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ በዞኑ ከሁሉም ወረዳዎችንና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ከ1000 በላይ ወጣቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
====
# ዘገባው የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን ነው !

 # ዶ/ር አብይ አህመድ የፊታችን ቅዳሜ  ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም ዳግም ወደ ወልቂጤ ከተማ እንደሚመጡ ተሰምቷል  :: # በዕለቱም ከምዕራብ ጉራጌ ማህበረሰብ  ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ...
18/04/2024

# ዶ/ር አብይ አህመድ የፊታችን ቅዳሜ ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም ዳግም ወደ ወልቂጤ ከተማ እንደሚመጡ ተሰምቷል ::
# በዕለቱም ከምዕራብ ጉራጌ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ::
====
# Gordena Online

ሚያዚያ 10/ 2016 ዓ/ም ===በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የቡኢ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ስራ በመፋጠን ላይ ይገኛል ።===በተያዘው በጀት ዓመት ማለቂያ አካበቢ ይጠናቀቃል ተብሎ የ...
18/04/2024

ሚያዚያ 10/ 2016 ዓ/ም
===
በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የቡኢ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ስራ በመፋጠን ላይ ይገኛል ።
===
በተያዘው በጀት ዓመት ማለቂያ አካበቢ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የቡኢ ከተማ የንፁ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ስራው በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን ወደ ማጠራቀሚያ ታንከር የሚያስገባው ቱቦ የዝርጋታ ስራ እየተፋጠነ ወደ መጠናቀቅ እየተቃረበ ነው ።
===
# መረጃው የከተማ መንግስት ኮምኒኬሽን ነው ::

18/04/2024

# ትላንት በነበረው ጨዋታ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው የማረቆ ልዩ ወረዳ እግር ኳስ ቡድን ነገ 3:00 ሰዓት ከከምባታ ዞን ጋር የሚጨወት ይሆናል ::
==
# የማረቆ ልዩ ወረዳ ከምሰራቅ ጉራጌ ዞን በነበረው ጨዋታ ሙሉ ሜዳው በምስራቅ ጉራጌ እግር ኳስ ደጋፊዎች ተሞልቶ የነበረ ሲሆን ቡድኑ ያለአንዳች ደጋፊ እና ሙሉ የደጋፊው ጩኸት ተቋቁሞ ድንቅ በሆነ ዲሲፒልን ጥሩ አጨዋወት ማሳየት የቻለ ቡድን ነበር ::
===
# ትላንት በነበረው ጨዋታ የማረቆ ልዩ ወረዳ እግር ኳስ ቡድን ላሰየው ፍፁም ዲሲፕሊንና ፍፁም ጨዋነት ሊመሰገንና ሌሎች እንደ አርዓያ ሊወሰዱት ይገባል ::
ነገ በሚኖረው ጨዋታ ተጋጣሚ ቡድኑን አሸንፎ ወደ ጥሎ ማለፉ እንደሚቀላቀል ተስፋ እንደርጋለን !!
===
# መልካም ዕድል !
# Gordena Online
# ትላንት በነበረው ጨዋታ የደጋፊው ስሜት የሚገልፅ አጭር ቪዲዮ !
👇👇👇

 # በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቱሉቦሎ - ኬላ የአስፓልት መንገድ ዘቢዳር ተራራን አቋርጦ ኬላ ከተማ ደርሷል :: የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሰልጣን ቡታጅራ ዲስትሪክት መንገዱ 95 በመቶ መጠናቀ...
18/04/2024

# በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቱሉቦሎ - ኬላ የአስፓልት መንገድ ዘቢዳር ተራራን አቋርጦ ኬላ ከተማ ደርሷል :: የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሰልጣን ቡታጅራ ዲስትሪክት መንገዱ 95 በመቶ መጠናቀቁን ገልጿል :: ይህ መንገድ በያዘነው በጀት አመት እሰከ ሀምሌ ወር ሙሉበሙሉ ይጠናቀቃል ተብሏል :: በመጪው አዲስ አመት መንገዱ ስራ ይጀምራል ተብሎ ተሰፋ ተጥሎበታል ::
===
የቱሉ ቦሎ - ኬላ አስፓልት :-
# የመንገዱ ርዝመት 80 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል
# ግንባታው የተጀመረው በ2010 ዓ.ም ነው
# እስካሁን የ75 ኪ.ሜ የሚሸፍን ግንባታ ተጠናቋል
# መነሻውን ቱሉ ቦሎ ከተማ ላይ በማድረግ ሦስት ወረዳዎችን ያቋርጣል
# ለመንገድ ግንባታው የተመደበው በጀት 1.3 ቢሊየን ብር
# ፕሮጀክቱ ከተያዘለት በጀት የ8 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል
# የፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪ በፌዴራል መንግሥት የተሸፈነ ነው
# አካባቢው ላይ በስፋት የሚመረቱ እንደ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ባቄላ እና እንሰት የመሳሰሉ ምርቶች ወደ ማዕከል ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ይታመናል ::
===
# Gordena Online

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 9/2016(ኢዜአ)፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አ...
17/04/2024

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 9/2016(ኢዜአ)፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት 1445ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል እና ዘንድሮ የሚከበረውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል።

እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ በሙሉ ይቅርታ ወንድ 637፤ ሴት 11፤ በልዩ ሁኔታ ወንድ 3 ሴት 3 በጠቅላላው 654 ታራሚዎች ሲሆኑ ለ4 ወንዶች ታራሚዎች ደግሞ የእስራት ቅናሽ ተደርጎላቸዋል።

በክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ስር ባሉ ሰባት ማረሚያ ተቋማት ከሚገኙ የህግ ታራሚዎች መካከል በ2016 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር 658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
===
# ENA

 # የምስራቅ ጉራጌ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኞች ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል : የአንድ ቡድን ሰኬት መነሻ ብቃት ያለው አሰልጣኝ በመሆኑ !=== # GOM
17/04/2024

# የምስራቅ ጉራጌ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኞች ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል : የአንድ ቡድን ሰኬት መነሻ ብቃት ያለው አሰልጣኝ በመሆኑ !
===
# GOM

17/04/2024

# ልክ እንደ ቡኢ ዋንጫው በምስራቅ ጉራጌ እግር ኳስ ቡድን ይደገማል 🤗🤗🤗
===
መልካም እድል ለምስራቅ ጉራጌ እግር ኳስ ቡድን !
===
# GOM

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gordena Online posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Nearby media companies