Tuma Media ቱማ ሚዲያ

Tuma Media ቱማ ሚዲያ Tuma Media is online media based in Addis Ababa, Ethiopia, and focuses on political, social, and eco This is official page of Tuma TV

በሺር አል አሳድ ሀገር ጥሎ ሸሽቷል
08/12/2024

በሺር አል አሳድ ሀገር ጥሎ ሸሽቷል

ከአመታት በፊት ሊቢያውያንን  በወግ በማእረግ ፡ አስተዳድረው ህዝባቸውን  በምቾት ፡ በደስታ ያኖሩ የነበሩት ታላቁ የሊቢያ መሪ ፡ ሙአመር አል ገዳፊ  የሊቢያን  ወርቅና ነዳጅ ፈልገው ጥርስ...
08/12/2024

ከአመታት በፊት ሊቢያውያንን በወግ በማእረግ ፡ አስተዳድረው ህዝባቸውን በምቾት ፡ በደስታ ያኖሩ የነበሩት ታላቁ የሊቢያ መሪ ፡ ሙአመር አል ገዳፊ የሊቢያን ወርቅና ነዳጅ ፈልገው ጥርስ ውስጥ በከተቷቸው ምእራባውያን ሴራ በራሳቸው ህዝብ ተቃውሞ ተነሳባቸው ።...........
የአረብ አብዮት እሳት ሊቢያንና ህዝቦቿን ሊበላ ጫፍ ደረሰ ።
በመጨረሻም ደጉ መሪ ሙሀመድ አል ጋዳፊ ቤተመንግስታቸውን ትተው ወደተወለዱበት ከተማ ሲርጥ በመሄድ በሚስጥር ተቀመጡ ።..................

ምእራባውያንና አሜሪካ ዋና ጠላታቸው የሆነውን ጋዳፊን ፈልጎ ማግኘት አቃታቸው ።
እና የጋዳፊን አድራሻ ማፈላለግ ጀመሩ ። ያሉበትን ቦታ ወይም ይህን ለማወቅ የሚረዳ መረጃ አጥተው በተቸገሩበት ወቅት አንድ ሰው ለፈረንሳይ የፀጥታ ሰወች የሚነግረው ሚስጥር እንዳለ አሳወቃቸው ።...
ይህ ሰው በጋዳፊ ይታመን የነበረ እና የሳተላይት ስልካቸውን ቁጥር የሚያውቅ ነው ።
ጋዳፊን የሚፈልጉ ሀገራት ይህን ቁጥር ካገኙ ፡ በሲግናል አማካኝነት ያሉበት ቦታ እንደሚታወቅ ያውቃል ።
እናም ይህን በእምነት የተሰጠውን ትልቅ መረጃ ፡ አሳልፎ ለፈረንሳይ የስለላ ድርጅት ሰጠ ።.....
ይህ መረጃ ከተገኘ በኋላ የጋዳፊን መወገድ የሚፈልጉት ምእራባውያን ፡ በዘመናዊ መሳሪያ ታግዘው ጋዳፊ ያሉበትን ትክክለኛ ቦታ አወቁ ።

ይህንንም መረጃ ጋዳፊ ያሉበትን ትክክለኛ ቦታ ፡ ለጋዳፊ ተቃዋሚዎች ሰጧቸው ። ጋዳፊ , ከድህነት አውጥተው ባበለፀጉት የሀገራቸው ህዝብ በተነሳባቸው ተቃውሞ ፡ በገዛ ሊቢያውያን ተገኝተው በግፍ ተገደሉ ።...

ጋዳፊን ማን አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው ነገር ጥያቄ ሆኖ ከቆየ በኋላ ግን. . የሰውየው ማንነት ታወቀ ። ይህ ሰው ፡ ይህ ጋዳፊ ከመሸጉበት ቦታ እንዲገኙ ስልክ ቁጥራቸውን አሳልፎ የሰጠው ከሀዲ ሰው ፡ የሶሪያው ፕሬዝደንት በሽር አልአሳድ ነበር ።............
አልአሳድ ፡ ይህንን መረጃ የሰጠው የስልጣን ዘመኑን ለማቆየት የሚያስችል ድጋፍ ከፈረንሳይ መንግስት ለማግኘት በማሰብ ነበር ።....

ከአመታት በኋላ ዛሬ ላይ ደግሞ. . ለአመታት በእርስበርስ ጦርነት ስትታመስ የቆየችው የሶሪያ ተቃዋሚ ሀይሎች ፡ እየገፉ መጥተው ፡ የዚህ ሰው ሴፍ ዞን ወደሆነችው ዋና ከተማ ደማስቆ መገስገስ ጀምረዋል ። ...
ከሰአታት በፊት እንደተሰማውም የአልአሳድ ወታደሮች ሰውየውን ትተውት እየሄዱ ነው ።.....
እና የተለየ ነገር ካልተፈጠረ የዚህ ሰው የ24 አመታት የግፍ አገዛዝ ማብቂያ ተቃርቧል ። ወይ ይሸሻል ወይ በክህደት ያስገደላቸው የጋዳፊ እጣ ይደርሰዋል ።

በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል***********ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በ...
07/12/2024

በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
***********
ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።
የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

መብራት በአዲስ አበባ በአብዛኛው አካባቢ እንደጠፋ አረጋግጠናል ። የጠፋባችሁ ኮመንት ላይ ጻፉ።
07/12/2024

መብራት በአዲስ አበባ በአብዛኛው አካባቢ እንደጠፋ አረጋግጠናል ። የጠፋባችሁ ኮመንት ላይ ጻፉ።

"ባለማስተርሱ አዝማሪ" አርፏል 😭የክራሩ ጌታ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ዋርካ፤ የዩኒቨርሲቲ ዜማዎች ማህደር እና ደራሲ፤ የባላገር ፍቅር ቴአትር ቀማሪ፤ የግጥም መፃህፍት ደራሲ...
07/12/2024

"ባለማስተርሱ አዝማሪ" አርፏል 😭

የክራሩ ጌታ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ዋርካ፤ የዩኒቨርሲቲ ዜማዎች ማህደር እና ደራሲ፤ የባላገር ፍቅር ቴአትር ቀማሪ፤ የግጥም መፃህፍት ደራሲ፤ የተወዳጅ የባህል አልበሞች ባለቤት አርፏል።

ከጎጃም ደንበጫ በጊዜው አስቸጋሪ የነበረውን ማትሪክ
በከፍተኛ ውጤት አልፎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መግባት ችሎ ነበር። እስከሕይወቱ መጨረሻ የሰራበት ባህል ማዕከል ልቡን አሸፍቶት ትምህርቱን አቋርጦ ባህል ማዕከሉን የቀን ከሌት የጥበብ ፍቅር መወጫ አደረገው።

''ባዶ ቤት በክረምት'' ፣ ''ጆኒ ምን እዳ ነው'' ፣ ''እማ በጡቶችሽ'' ፣ ''ዩኒቨርሲቲን'' ፣ ''እንኳን ደስ አላችሁ''ን ሲዘምር ሲያዘምር ሲመርቅ ሲያስመርቅ የራሱን ትምህርትና ምርቃት መስዋዕት አድርጎ ሲያገለግል ኖረ። ኋላም የዕለት ጉርሱን ለመሙላት የዩኒቨርሲቲ ተማሪው አዝማሪ ሆኖ ክራሩን አንግቦ በየምሽት ቤቱ ተንከራተተ። በዚህ ሁሉ መሃል ''የባላገር ፍቅር'' የተሰኘውን ድንቅ ሥራ ከዳግማዊ ፈይሳ ጋር አዘጋጅቶ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቴአትር ለእይታ አበቃ። ''አካላት'' የተሰኘውን የታወቀበትን ዜማ ጨምሮ ጥሩ ጥሩ የባህል አልበሞች አሳተመ። ''እንዴት ብትወደኝ ነው'' የተባለ የግጥም መድብል አካፈለ።

ጠንካራው ሰው በስተመጨረሻ ፅናቱ የታየው አቋርጦት የነበረውን ትምህርት ከሃያ አመታት በኋላ ለመጨረስ እልህ አስጨራሽ ትግል ባደረገበት ወቅት ነበር። በወቅቱ የነበርነው የትምህርት ክፍል እና የኮሌጅ ኃላፊዎችን ባሳመነው ችሎታው፣ አበርክቶው እና ፅናቱ የዩኒቨርሲቲውን የበላይ ኃላፊዎች በተለይም አካዳሚክ ስታንዳርድስ ኮሚቴውን በማሳመን አበባው ተምሮ በቴአትር ጥበባት የመጀመሪያ ዲግሪውን ለማግኘት በቃ። በአስገራሚ ታታሪነት ቀጥሎም የማስተርስ ዲግሪውን አገኘ።

አዝማሪው ባለማስተርስ ብሎም የሄደበትን ጉዞ በሚገልፅ ራሱን ጠራ። ሺሆችን ''እንኳን ደስ አላችሁ'' ብሎ ባስመረቀበት መድረክ ጋውኑን ለብሶ ክራሩን እየመታ ህብረ ዘማሪያኑን እየመራ ''እንኳን ደስ አላችሁ'' ብሎ በስሜት አነባ። የፅናት ምሳሌነቱ ለሁሉም ተገለጠ። የዩኒቨርሲቲ መምህራንን እያየ ''ይሄኮ ቦታዬ ነበር'' ብሎ በተቆጨበት ክፍል ገብቶ አስተማረ። ሕይወት እንዲህ ናትና ከዚህ አለም ድካም አረፈ።

ነፍስ ይማር
ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይስጥልን

ነብይ ኢዩ ወደ ሚዛን እየመጣሁ ነው ብሏል ።
07/12/2024

ነብይ ኢዩ ወደ ሚዛን እየመጣሁ ነው ብሏል ።

ፋና እና ዋልታ በይፋ ተዋሃዱ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ እና ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት አ.ማ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ በሚል መጠሪያ በይፋ ተዋሃዱ።የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን...
05/12/2024

ፋና እና ዋልታ በይፋ ተዋሃዱ

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ እና ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት አ.ማ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ በሚል መጠሪያ በይፋ ተዋሃዱ።

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የማብሰሪያ እና ስራ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በግራንድ ኤሊያና ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በመርሐ-ግብሩ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የሚዲያው አመራሮች የድርጅቱ ሰራተኞች፣ ተባባሪ አዘጋጆች፣ የሚዲያው አጋሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ለተመሳሳይ ዓላማ የተቋቋሙት የሚዲያ ተቋማት ውህደት አንድ ግዙፍ እና ተደራሽ ሚዲያ ለመመስረት ያለመ ነው።

ውህደቱ የፋይናንስ፣ የሰው ሃይል፣ የቴክኖሎጂና የመሰረተ ልማት አቅምን በማቀናጀት የሃብት ብክነትን ማስቀረት እንደሚያስችል ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም የማህበራቱ ውህደት ትርፋማነትንና ውጤታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ ሁለት የቴሌቪዥን ቻናሎች፣ ሶስት ሬዲዮ ጣቢያዎችና ሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይኖሩታል።

የውህደቱ ሒደት አስፈላጊውን ሕግና ሥርዓት ተከትሎ መፈጸሙም ተገልጿል።

ተማሪ  አሜን እስክንድርን ያያችሁ በምስሉ የምትለከተቱት የ12 ዓመት ታዳጊ ተማሪ  አሜን እስክንድር ይባላል።  በጀሞ 2 ህዳር 24/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10ሰዓት   እንደወጣ አልተመለሰም። ...
04/12/2024

ተማሪ አሜን እስክንድርን ያያችሁ

በምስሉ የምትለከተቱት የ12 ዓመት ታዳጊ ተማሪ አሜን እስክንድር ይባላል። በጀሞ 2 ህዳር 24/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10ሰዓት እንደወጣ አልተመለሰም። ታዲጊው ከቤት ሲወጣ የስፖርት ማልያ የለበሰ ሲሆን ስለ ታዳጊ አሜን እስክንድር ያገኛቹ ወይም ያያቹ በዚህ ስልክ ቁጥር 0910149085/ዐ911193394 ደውላችሁ እንድታሳውቁት የታዳጊው ወላጆች በትህትና ይጠይቃችኃል።

ሼር ሼር

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ካምፕ እየገቡ መሆኑን...
03/12/2024

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ካምፕ እየገቡ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያጋራው መረጃ ያመላክታል።

03/12/2024
በዳዉሮ ዞን፣ ሎማ በሳ ወረዳ መምህራን ተበደልን አለ
03/12/2024

በዳዉሮ ዞን፣ ሎማ በሳ ወረዳ መምህራን ተበደልን አለ

የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ አዲሱን የኢቢሲ ስቱዲዮ ለመመረቅ ወላይታ ሶዶ ገቡየፌደራል የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑክ አዲሱን የኢቢሲ ስቱዲዮ ለመመረቅ ወላይታ ሶዶ ገ...
02/12/2024

የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ አዲሱን የኢቢሲ ስቱዲዮ ለመመረቅ ወላይታ ሶዶ ገቡ

የፌደራል የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑክ አዲሱን የኢቢሲ ስቱዲዮ ለመመረቅ ወላይታ ሶዶ ገብቷል ኃላፊዎቹ ወላይታ ሶዶ ሲደርሱ በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ልዑኩ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፣ የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጌትነት ታደሰ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ነው።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ነገ የሚመረቀው "ኢቢሲ ወላይታ ሶዶ ስቱዲዮን ጎብኝተዋል።

"ኢቢሲ ወላይታ ሶዶ ስቱዲዮ" ለሚዲያው ተጨማሪ የይዘት ምንጭ በመሆን ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለት ይታመናል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግስት ያቀረበላቸውን የሰላ...
01/12/2024

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግስት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት አዲስ አበባ ላይ በዛሬው ዕለት የሰላም ስምምነቱን የተፈራረሙት።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና አቅርበዋል።

ከጦረኞች በላይ ጦርነትን የሚያባብሱት ስለጦርነት የማያውቁ ናቸው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ እኔ ካለኝ ልምድ አንፃር ጦርነት ጎጂ በመሆኑ የሰላምን መንገድ መርጣችሁ በመምጣታችሁ ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

ይህ አይነቱ ተግባር በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕስ መስተደድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው የኦሮሞ ህዝብ በባህልና በወጉ መሰረት በሮቹን ጠምዶና ፈረሶችን ጭኖ በመውጣት ሰላም ይውረድ ባለው መሰረት ጥሪውን ተቀብላችሁ በመምጣታችሁ በራሴና በክልሉ መንግስት ስም አመሠግናለሁ ብለዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የመከላከያ ሠራዊቱ ለሰላም ስምምነቱ ላበረከተው አስተዋፅኦም ምስጋና አቅርበዋል።

በዚህ ዓለም የሰው ልጅ የፖለቲካ ልዩነት ያለው መሆኑን ያወሱት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ እኛም ያለንን የፖለቲካ ልዩነት በጠመንጃ ከመፍታት በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ወስነን ነው ስምምነቱን የመረጥነው ብለዋል።

ይህ ስምምነት ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥም ተናግረዋል።

በመረሀ-ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጋዛሊ አባ ሲመል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ሌተናል ጄነራል ዲሪባ መኮንን የኢትዮጵያ መከላከያ መረጃ አመራሮች አባገዳዎች ሀደ ሲንቄዎችና የሃይማኖት አባቶችና ታዋቂ አትሌቶች ተገኝተዋል።
ምንጭ : የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

ሞተር ሳይክል አከራይቶ ተዳዳሪ ታዳጊው ተገደለ✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️በትላንትናው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ በወላይታ ሶዶ ከተማ ግብርና ኮሌጂ በምወሰደው መንገድ ወደ ቄራ መሄጃ...
30/11/2024

ሞተር ሳይክል አከራይቶ ተዳዳሪ ታዳጊው ተገደለ
✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️
በትላንትናው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ በወላይታ ሶዶ ከተማ ግብርና ኮሌጂ በምወሰደው መንገድ ወደ ቄራ መሄጃ ላይ ማንነታቸው የማይታወቅ ግለሰቦች ሞተር አከራይ የነበረውን ወጣት ሳሙኤል ዎጋሶን በሰለት ወግቶ ገደሉት፡፡ ገዳዮች እስካሁን ማንነታቸው አልታወቀም ፣ አልተያዙም፡፡ የሕግ አካላት ገዳዮችን ይዞ ለፍትህ ያቀርባል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ።

ለወዳጅ ዘመዶችና ለወላጅ ቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን ።

ሁለት ገበሬዎች
28/11/2024

ሁለት ገበሬዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፌዴራል ፖሊስ ከዶርማቸው እንዲወጡ ተደረጉይሄ የሆነው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ አመት ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች የExit Exam አመታችን ይስተካከልልን ብሎ ጥያቄ ...
27/11/2024

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፌዴራል ፖሊስ ከዶርማቸው እንዲወጡ ተደረጉ

ይሄ የሆነው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ አመት ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች የExit Exam አመታችን ይስተካከልልን ብሎ ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት ትናንት ማታ ሌሊት 11:00 ሰአት ላይ በፌዴራል ፖሊስ ከዶርማቸው እቃቸዉን ሰብስበዉ እንዲወጡ ተደርጓል በዚህ ሰአት ከታች እንደምትመለከቱት ዉጪ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

Address

Stadium
Addis Ababa
10000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tuma Media ቱማ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tuma Media ቱማ ሚዲያ:

Share