Maleda Sport ማለዳ ስፖርት

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት ቀዳሚ የሆንን ማለዳዎች ነን፦ ጥልቅ እይታ እና ሚዛናዊ አቀራረብ መለያችን ነው! It's official page of reporting sport events for all users

🔴 አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት እና ባይተዋሯ እንግሊዝ በጀርመን በአልተፈቱ እንቆቅልሾች ውስጥ እንግሊዝ ሰርቢያን 1-0 አሸነፈች ፣ ከዴንማርክ ጋር 1-1 አቻ ትናንት ደግሞ ከስሎቬኒያ ጋር 0-...
26/06/2024

🔴 አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት እና ባይተዋሯ እንግሊዝ በጀርመን በአልተፈቱ እንቆቅልሾች ውስጥ

እንግሊዝ

ሰርቢያን 1-0 አሸነፈች ፣ ከዴንማርክ ጋር 1-1 አቻ ትናንት ደግሞ ከስሎቬኒያ ጋር 0-0 አቻ ጨዋታዋን አጠናቀቀች።

በሶስት ጨዋታዎች አንድ ድል ሁለት አቻ በመለያየት በአምስት ነጥቦች በአንድ ንጹህ የጎል ክፍያ ብቻ ከምድቡ ቀዳሚ ሆኖ አልፏል።

የመድረኩ ባይተዋር የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን በሶስት ጨዋታዎች ሁለት ጎሎችን ብቻ አስቆጥሮ አንድ ተቆጥሮበታል።

ከምድበ ቀዳሚ ሆኖ ይለፍ እንጂ ያለፈበት መንገድ ግን በእንቆቅልሽ የተሞላ እና የድል መንገዱን በሚገባ ያላገኘ ደመነፍሳዊ ቡድን መሆኑን በእንቅስቃሴው መረዳት ይቻላል።

የሶስቱ አናብስት ቡድን ?!

ሊዮ1065 ጨዋታዎች 837 ጎሎች373 አሲስቶች44 ዋንጫዎች8 የባሎን ዶር ክብሮችየእግር ኳስ ውበት ሊዮየእግር ኳስ ባለሟል ሊዮመልካም ልደት
24/06/2024

ሊዮ

1065 ጨዋታዎች
837 ጎሎች
373 አሲስቶች
44 ዋንጫዎች
8 የባሎን ዶር ክብሮች

የእግር ኳስ ውበት ሊዮ
የእግር ኳስ ባለሟል ሊዮ

መልካም ልደት

🔴 አዘጋጇ ጀርመን ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።በውድድሩ ሶስት መንገስ የቻለችው ጀርመን ትናንት ሀንጋሪን በማሸነፍ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ የተቀላቀለች ቀዳሚዋ አገር ሆናለች።
20/06/2024

🔴 አዘጋጇ ጀርመን ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።

በውድድሩ ሶስት መንገስ የቻለችው ጀርመን ትናንት ሀንጋሪን በማሸነፍ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ የተቀላቀለች ቀዳሚዋ አገር ሆናለች።

⚪️ ወጣቱ ኮከብ አገሩን ባለድል ባደረገበት ጨዋታ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል።በሪያል ማድሪድ የቻምፒየንስ ሊግ እና ላሊጋ ዋንጫዎችን በማሳካት አመርቂ የውድድር አመትን ያሳለፈው ጁድ ቤ...
17/06/2024

⚪️ ወጣቱ ኮከብ አገሩን ባለድል ባደረገበት ጨዋታ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል።

በሪያል ማድሪድ የቻምፒየንስ ሊግ እና ላሊጋ ዋንጫዎችን በማሳካት አመርቂ የውድድር አመትን ያሳለፈው ጁድ ቤልንግሀም አገሩን እንግሊዝ ባለድል አድርጓል።

በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከሰርቢያ ጋር ያደረገችው የመድረኩ ባይተዋር እንግሊዝ ድል ለማድረግ የወጣቱን ልጇን ልዩ ግልጋሎት ፈልጋለች።

ባለተሰጥኦው ጁድ ቤልንግሀም ከሎስ ብላንካዎቹ ስኬታማ አመት በኋላ ለዩሮ ዋንጫ በሶስቱ አናብስት ስብስብ ጀርመን ላይ የከተመ ሲሆን እንግሊዝ ሰርቢያን 1-0 ስታሸንፍ የድል ጎል በማስቆጠር ዳግም እምርታን አሳይቷል።

ጁድ በውድድር አመቱ ለክለቡ እና አገሩ 25 ጎሎችን አስቆጥሮ 16 አሲስት አስመዝግቧል።

የጨዋታው ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን ያሸነፈው የእንግሊዛውያን ተስፈኛ በውድድር አመቱ በሁሉም ውድድሮች ለ 15 ኛ ጊዜ የጨዋታ ምርጥ ሽልማትን ያሸነፈበት ልዩ ምሽት ሆኗል።

⚪️ ወጣቱ ኮከብ ኬሊያን አምባፔ በሪያል ማድሪድ ቤት 9 ቁጥር መለያን እንደሚለብስ ይጠበቃል።
04/06/2024

⚪️ ወጣቱ ኮከብ ኬሊያን አምባፔ በሪያል ማድሪድ ቤት 9 ቁጥር መለያን እንደሚለብስ ይጠበቃል።

⚪️ ቀጣይ ባሎን ዶር !ቪኒሲዬስ ጁኒዬር የቻምፒየንስ ሊጉ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ክብርን አሸንፏል።
03/06/2024

⚪️ ቀጣይ ባሎን ዶር !

ቪኒሲዬስ ጁኒዬር የቻምፒየንስ ሊጉ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ክብርን አሸንፏል።

🔴 የባለ ትልቁ ጀሮ ዋንጫ መዳረሻ የት ይሆን ?ቤርናቢዩ ወይስ ሲግናል ኤዱና ፓርክ?ማድሪድ ወይስ ዶርትሙንድ ?የዋንጫ አሸናፊውን ግምት ያስቀምጡ።
31/05/2024

🔴 የባለ ትልቁ ጀሮ ዋንጫ መዳረሻ የት ይሆን ?

ቤርናቢዩ ወይስ ሲግናል ኤዱና ፓርክ?

ማድሪድ ወይስ ዶርትሙንድ ?

የዋንጫ አሸናፊውን ግምት ያስቀምጡ።

🔵 ቲያጎ ሞታ ጁቬንትስን በአሰልጣኝነት ለመረከብ ተስማምቷል።በቦሎኛ አስደናቂ የውድድር አመት ያሳለፈው ቲያጎ ሞታ ከማሲሚላኖ አለግሪኒ ጋር የተለያየውን ጁቬንትስ እስከ 2027 ለመረከብ ከስም...
23/05/2024

🔵 ቲያጎ ሞታ ጁቬንትስን በአሰልጣኝነት ለመረከብ ተስማምቷል።

በቦሎኛ አስደናቂ የውድድር አመት ያሳለፈው ቲያጎ ሞታ ከማሲሚላኖ አለግሪኒ ጋር የተለያየውን ጁቬንትስ እስከ 2027 ለመረከብ ከስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል።

🔴 ማርከስ ራሽፎርድ ከዩሮ ዋንጫ ውድድር የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጭ ተደርጓል።
21/05/2024

🔴 ማርከስ ራሽፎርድ ከዩሮ ዋንጫ ውድድር የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጭ ተደርጓል።

⚪️ በአስደናቂ ብቃት ለገናናው ክለብ ገናና ታሪክን ጽፈው ለአመታት በማይናወጥ አቋም ከዘለቁት ኮከቦች ውስጥ አንዱ ብቻ በነጩ መለያ ይቆያል።የአለም እግር ኳስ ሚዛን ደፊዎች በጊዜ ሂደት ለመ...
21/05/2024

⚪️ በአስደናቂ ብቃት ለገናናው ክለብ ገናና ታሪክን ጽፈው ለአመታት በማይናወጥ አቋም ከዘለቁት ኮከቦች ውስጥ አንዱ ብቻ በነጩ መለያ ይቆያል።

የአለም እግር ኳስ ሚዛን ደፊዎች በጊዜ ሂደት ለመበተን ተገደዋል።

የመሃል ሜዳው ኮከብ ቶኒ ክሮስ ከዩሮ ዋንጫው ውድድር በኋላ ከእግር ኳስ እራሱን ያገላል።በመሃል ሜዳ እግር ኳስን በስኬት በመጫወት አያሌ ክብሮችን በልቀት ያሳካው ጀርመናዊው ኮከብ በአገሩ ከ...
21/05/2024

የመሃል ሜዳው ኮከብ ቶኒ ክሮስ ከዩሮ ዋንጫው ውድድር በኋላ ከእግር ኳስ እራሱን ያገላል።

በመሃል ሜዳ እግር ኳስን በስኬት በመጫወት አያሌ ክብሮችን በልቀት ያሳካው ጀርመናዊው ኮከብ በአገሩ ከሚዘጋጀው የክረምቱ ዩሮ ውድድር ማግስት ከእግር ኳስ እራሱን እንደሚያገል አረጋግጧል።

በአለም እግር ኳስ አያሌ ክብሮችን በማሸነፍ ስኬታማ ከሆኑ ኮከቦች መካከል ስሙ በህያውነት የተቀመጠው ድንቅ ኮከብ እግር ኳስን በውብ ጥበብ ተጫውቶ ደግሞም ስኬትን ተጎናጽፎ በመጨረሻም ከተወዳጁ መድረክ ይሰናበታል።

የአለም ዋንጫ ሻምፒዮን
5 ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎች
6 የአለም ክለቦች ዋንጫዎች
3 የቡንደስሊጋ ዋንጫዎች
4 የላሊጋ ዋንጫዎች
5 የዩኤፋ ሱፐር ዋንጫዎች
3 የጀርመን ካፕ ክብሮች
1 ኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫ
4 የስፔን ሱፐር ካፕ ክብርች
1 የጀርመን ሱፐር ካፕ ክብር

ከያኒው ቶኒ ክሮስ እልፍ ክብሮችን አሳክቶ ከጀርመኑ የዩሮ ዋንጫ ውድድር በኋላ እግር ኳስን ይሰናበታል።

🔵 የአለም ምርጡ አሰልጣኝ ?!በባየርን ሙኒክ ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን።በባርሰሎና ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ የላሊጋው ሻምፒዮን።በማንቸስተር ሲቲ ለአራተኛ ጊዜ በተከታታይ ...
21/05/2024

🔵 የአለም ምርጡ አሰልጣኝ ?!

በባየርን ሙኒክ ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን።

በባርሰሎና ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ የላሊጋው ሻምፒዮን።

በማንቸስተር ሲቲ ለአራተኛ ጊዜ በተከታታይ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን።

በሰባት የውድድር አመታት ለስድስተኛ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን።

🔵 ለአራተኛ አመት በተከታታይ ማንንም ጣልቃ ሳያስገባ ሻምፒዮን በመሆን የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።በሰባት የውድድር አመታት ውስጥ በስድስቱ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በልቀት አሸንፏል።
20/05/2024

🔵 ለአራተኛ አመት በተከታታይ ማንንም ጣልቃ ሳያስገባ ሻምፒዮን በመሆን የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።

በሰባት የውድድር አመታት ውስጥ በስድስቱ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በልቀት አሸንፏል።

🔵 ለስቴፈን ኦርቴጋ ምቹ ሁነት የፈጠረው የኮከቡ ጉዳትኤደርሰን የማንቸስተር ሲቲ ሁለት ወሳኝ የመጨረሻ ጨዋታዎች በጉዳት እንደማይሰለፍ መረጋገጡን ተከትሎ በቶትንሀሙ ጨዋታ ተቸተቀይሮ ገብቶ አ...
16/05/2024

🔵 ለስቴፈን ኦርቴጋ ምቹ ሁነት የፈጠረው የኮከቡ ጉዳት

ኤደርሰን የማንቸስተር ሲቲ ሁለት ወሳኝ የመጨረሻ ጨዋታዎች በጉዳት እንደማይሰለፍ መረጋገጡን ተከትሎ በቶትንሀሙ ጨዋታ ተቸ
ተቀይሮ ገብቶ አስደናቂ ብቃት ያሳየው ስቴፈን ኦርቴጋ ብቃቱን ዳግም ለማሳየት ወርቃማ እድል አግኝቷል።

ስቴፈን ኦርቴጋ ማንቸስተር ሲቲ ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ በፕሪሚየር ሊጉ ለመንገስ በመጨረሻው ጨዋታ ዌስትሀምን የሚያስተናግድበትን ወሳኝ ጨዋታ ጨምሮ በኤፍ ኤ ካፑ የፍጻሜ ጨዋታ በማንቸስተር ደርቢ ውሃ ሰማያዊ ለባሾቹን በግብ ጠባቂነት የሚመራ ይሆናል።

🔴 የተረጋገጠ አርሰናል ቀጣይ አመት መለያ
16/05/2024

🔴 የተረጋገጠ አርሰናል ቀጣይ አመት መለያ

🔵 ቶትንሀምን ድል ካደረጉ 2,024 ቀናት ተቆጥረዋል ... ዛሬስ ?ማንቸስተር ሲቲ በሊጉ ከሜዳው ውጭ ቶትንሀምን ድል ማድረግ እንደ ዳገት ሆኖበት ለአለፉት 2,024 ቀናት ድል ማድረግ አልቻ...
14/05/2024

🔵 ቶትንሀምን ድል ካደረጉ 2,024 ቀናት ተቆጥረዋል ... ዛሬስ ?

ማንቸስተር ሲቲ በሊጉ ከሜዳው ውጭ ቶትንሀምን ድል ማድረግ እንደ ዳገት ሆኖበት ለአለፉት 2,024 ቀናት ድል ማድረግ አልቻለም።

ዛሬ በወሳኙ የሻምፒዮንነት ፍልሚያ ፔፕ ጋርዲዮላ በአስከፊው የሰሜን ለንደን የድል እጦት ቁጥር ውስጥ ሆነው ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ ሻምፒዮን ለመሆን ይፋለማሉ።

ቶትንሀም ከማንቸስተር ሲቲ ማን ያሸንፋል ?

🔴 ወጣቱ ተከላካይ ኮንሳ በሊቨርፑል መለያ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጎሉን አስቆጥሯል።
13/05/2024

🔴 ወጣቱ ተከላካይ ኮንሳ በሊቨርፑል መለያ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጎሉን አስቆጥሯል።

🔴 በ 50 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ የዘመናት ጽኑ የድል ክብር።ባየር ሌቨርኩሰን በ 50 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ህያው የድል ገድሉን አጠናክሮ ቀጥሏል።አዲሱ የጀርመን ሻምፒዮን በአያሌ የድል ጉዞ ውስ...
12/05/2024

🔴 በ 50 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ የዘመናት ጽኑ የድል ክብር።

ባየር ሌቨርኩሰን በ 50 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ህያው የድል ገድሉን አጠናክሮ ቀጥሏል።

አዲሱ የጀርመን ሻምፒዮን በአያሌ የድል ጉዞ ውስጥ ቀጥሎ 50 ጨዋታዎችን ባለመሸነፍ ክብር 141 ጎሎችን አስቆጥሮ የዘመናት ታሪክን በደማቁ ጽፏል።

🔵 በፓርክ ደፕሪንስ የመጨረሻ የፓሪሰን ዠርመ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው ኬሊያን ኧምባፔ በጨዋታው ጅማሮ 8 ኛው ደቂቃ ላይ ኳስና መረብን በማገናኘት ለደጋፊዎች የስንብት ስጦታ አበርክቶላቸዋ...
12/05/2024

🔵 በፓርክ ደፕሪንስ የመጨረሻ የፓሪሰን ዠርመ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው ኬሊያን ኧምባፔ በጨዋታው ጅማሮ 8 ኛው ደቂቃ ላይ ኳስና መረብን በማገናኘት ለደጋፊዎች የስንብት ስጦታ አበርክቶላቸዋል።

🔵 ሁሉንም ነገር የሰጣቸው ኬሊያን ኧምባፔ በፓርክ ደፕሪንስ የመጨረሻ በሆነው ጨዋታ ከፓሪሱ ክለብ ደጋፊዎች ጋር የጋብቻ ፍች ስንብት እያደረገ ይገኛል።
12/05/2024

🔵 ሁሉንም ነገር የሰጣቸው ኬሊያን ኧምባፔ በፓርክ ደፕሪንስ የመጨረሻ በሆነው ጨዋታ ከፓሪሱ ክለብ ደጋፊዎች ጋር የጋብቻ ፍች ስንብት እያደረገ ይገኛል።

🔴 በድንቅ ብቃት የአመታትን ድል በኦልድትራፎርድ ለአርሰናል እንዲመዘገብ ያደረገው ዊሊያም ሳሊባ የጨዋታው ምርጥ ተጫዋች ተሰኝቷል።ኮከቡ የጨዋታ ምርጥ ተጫዋች ክብርን በአንፊልድ እና ኢቲሃድ ...
12/05/2024

🔴 በድንቅ ብቃት የአመታትን ድል በኦልድትራፎርድ ለአርሰናል እንዲመዘገብ ያደረገው ዊሊያም ሳሊባ የጨዋታው ምርጥ ተጫዋች ተሰኝቷል።

ኮከቡ የጨዋታ ምርጥ ተጫዋች ክብርን በአንፊልድ እና ኢቲሃድ ላይ ማሳካቱ ይታወቃል።

🔴 ማን ያሸንፋል ?ምሽት 12:30 በኦልድትራፎርድ ማንቸስተር ዩናይትድ ከአርሰናል የጨዋታ ግምት ያድርሩን።
12/05/2024

🔴 ማን ያሸንፋል ?

ምሽት 12:30 በኦልድትራፎርድ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከአርሰናል
የጨዋታ ግምት ያድርሩን።

ከሚያዚያ ወር መጀመሪያ በኋላ የመጣ የመጀመሪያ ድል ሆኗል። ከድንቅ አጀማመር በኋላ አስከፊ የውጤት እጦት ላይ የሚገኘው ቶትንሀም ከአድካሚው ጉዞ በኋላ በበርንሌ ላይ ድል አስመዝግቧል።የቪንሰ...
11/05/2024

ከሚያዚያ ወር መጀመሪያ በኋላ የመጣ የመጀመሪያ ድል ሆኗል። ከድንቅ አጀማመር በኋላ አስከፊ የውጤት እጦት ላይ የሚገኘው ቶትንሀም ከአድካሚው ጉዞ በኋላ በበርንሌ ላይ ድል አስመዝግቧል።

የቪንሰንት ኮምፓኒው በርንሌ ጀብደኛ ቡድን ብቻ ሆኖ ወደ መጣበት ሻምፒዮንሽፕ ...

🔵 በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ተከላካይ ተጫዋች ሀትሪክ ሰርቶ አያውቅም። ጆስኮ ግቫርዲዮል አዲስ ታሪክ ለመስራት ፓናሊቲ ማስቆጠር ብቻ ነበር የቀረው ... ነገርግን ካይል ወከር ፔናሊቲውን ዩሉያን...
11/05/2024

🔵 በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ተከላካይ ተጫዋች ሀትሪክ ሰርቶ አያውቅም። ጆስኮ ግቫርዲዮል አዲስ ታሪክ ለመስራት ፓናሊቲ ማስቆጠር ብቻ ነበር የቀረው ... ነገርግን ካይል ወከር ፔናሊቲውን ዩሉያን አልቫሬዝ እንዲመታ ግቫርዲዮልን በመጠየቁ ምክንያት ሳይመታ ቀረ ... አዲሱ ታሪክም ሳይጻፍ ቀረ።

እድሉ ቢሰጠው አይሻልም ብለው ያስባሉ ?

🔴 በላሊጋው ዙፋን ደፍቶ 15 ኛ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ከፍ አድርጎ ገናና ታሪኩን ለማስቀጠል ከጫፍ የደረሰው የክለቦች ንጉሥ ሪያል ማድሪድ አሁን ካለው ስብስብ ላይ ...ኬሊያን ኧምባፔ እ...
10/05/2024

🔴 በላሊጋው ዙፋን ደፍቶ 15 ኛ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ከፍ አድርጎ ገናና ታሪኩን ለማስቀጠል ከጫፍ የደረሰው የክለቦች ንጉሥ ሪያል ማድሪድ አሁን ካለው ስብስብ ላይ ...

ኬሊያን ኧምባፔ እና አልፎንሶ ዴቪስን ሲጨምርበት ...

🔴 ቀጣይ ማረፊያው ቤርናቢዩ ወይስአንፊልድ ?ኦልትራፎርድ ?የኬሊያን ኧምባፔ ቀጣይ መዳረሻ የት ይሆናል ብለው ያስባሉ ?
10/05/2024

🔴 ቀጣይ ማረፊያው ቤርናቢዩ ወይስ

አንፊልድ ?
ኦልትራፎርድ ?

የኬሊያን ኧምባፔ ቀጣይ መዳረሻ የት ይሆናል ብለው ያስባሉ ?

🔴 ኬሊያን ኧምባፔ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከፓሪሰን ዠርመ ጋር እንደሚለያይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል።
10/05/2024

🔴 ኬሊያን ኧምባፔ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከፓሪሰን ዠርመ ጋር እንደሚለያይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል።

🔴 የቀጠለው የሻቪ አሎንሶ የድል ገድል!49 ጨዋታዎች ባለመሸነፍ በአውሮፓ አዲስ ክብረወሰን የቡንደስሊጋው ሻምፒዮንየዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ ተፋላሚ የዲኤፍቢ ፖካል ፍጻሜ ተፋላሚ
10/05/2024

🔴 የቀጠለው የሻቪ አሎንሶ የድል ገድል!

49 ጨዋታዎች ባለመሸነፍ በአውሮፓ አዲስ ክብረወሰን

የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን
የዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ ተፋላሚ
የዲኤፍቢ ፖካል ፍጻሜ ተፋላሚ

🔴 በዌብሌ ዶርትሙንድን የሚፋለመው ክለብ ማድሪድ ወይስ ሙኒክ ?ፓርክ ደፕሪንስ ላይ በማት ሀመልስ ጎል 1-0 ድል አድርጎ በድምር ውጤት 2-0 በማሸነፍ ከ 2013 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፍጻ...
08/05/2024

🔴 በዌብሌ ዶርትሙንድን የሚፋለመው ክለብ ማድሪድ ወይስ ሙኒክ ?

ፓርክ ደፕሪንስ ላይ በማት ሀመልስ ጎል 1-0 ድል አድርጎ በድምር ውጤት 2-0 በማሸነፍ ከ 2013 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፍጻሜ ትኬት የቆረጠው ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ዛሬ ተፋላሚውን ያውቃል።

በቻምፒየንስ ሊጉ አስደናቂ ብቃት ያሳየው ዶርትሙንድ ፓሪሰን ዠርመን በደርሶ መልስ አሸንፎ የፍጻሜውን ትኬት የቆረጠ ሲሆን ለባለ ትልቁ ጀሮ ዋንጫ ክብር ከዛሬው ምሽት የማድሪድ እና ሙኒክ አሸናፊ ጋር ይፋለማል።

በመጀመሪያው ጨዋታ 2-2 አቻ የተለያዩት ሙኒክ እና ማድሪድ ምሽት 4:00 ላይ በቤርናቢዩ የሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ ሲጠበቅ አሸናፊው ክለብ ዶርትሙንድን በፍጻሜው ዌብሌ ላይ ይፋለማል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251948831290

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Maleda Sport ማለዳ ስፖርት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share