Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት

Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት welcome to the OFFICIAL Mesrak Sport | ምስራቅ ስፖርት is one of GSMN
ሀገራዊ ስፖርት በልዩነት!

ውሹ ስፖርት በድሬዳዋ  ድራገር ሊ ክለብ የድሬዳዋ ውሹ ሻምፒዮና ሆነ፡፡በድሬዳዋ ውሹ ፌዴሬሸን ከወጣቶችና ስፖርት ኮሚሸን ጋር በመተባበር ከሰኔ 21 እስከ 23/2016 የተካሄደው ዓመታዊ የው...
01/07/2024

ውሹ ስፖርት በድሬዳዋ
ድራገር ሊ ክለብ የድሬዳዋ ውሹ ሻምፒዮና ሆነ፡፡

በድሬዳዋ ውሹ ፌዴሬሸን ከወጣቶችና ስፖርት ኮሚሸን ጋር በመተባበር ከሰኔ 21 እስከ 23/2016 የተካሄደው ዓመታዊ የውሹ ማሰልጠኛ ክለቦች ሻምፒዮና የውስጥ ማጣሪያ ውድድር በድራገር ሊ ክለብ አሸናፊነት በድምቀት ተጠናቋል፡፡

በኮሚሽኑ ሁለገብ ሜዳ በተዘጋጀው የአስተዳደሩ ውሹ ሻምፒዮና 6 የማሰልጠኛ ሴንተር ክለቦች በአርት እና በሳንሹ ጠንካራ ፉክክር አድርገዋል፡፡ በዚህ ውድድር በአርት እና በሳንሹ በአጠቃላይ ውጤት ድራገር ሊ ክለብ የዓመቱ ሻምፒዮና ሆኗል፡፡
2ኛ ኑንግተን ክለብ ፤ 3ኛ ቲያንሺ ክለብ በመሆን ውድድራቸውን ፈፅመዋል፡፡ በስፖርታዊ ጨዋነት ኑንግተን ክለብ የመልካም ፀባይ ዋንጫ ተሸላሚነትን አግኝቷል ፡፡
ለአሸናፊዎች የተፈጋጀውን የዋንጫ እና የወርቅ ፤ የብር ፤ የነሐስ ሜዳሊያዎችን ከድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ማልማትና ማስፋፋት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ከአቶ ኢብሳ ዱሪ እና ከሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡

ሰኞ 24 ፣ ሰኔ ፣ 2016ዓም

ለ23ኛ ጊዜ የተካሄደውን የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲጠናቀቅ ሃገራችን ኢትዮጵያ 4ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፤ላለፋት ስድስት ቀናት ከ50ሺ ሰው በላይ የመያዝ አቅም ባለው የጃፑማ ሁለገብ ስ...
30/06/2024

ለ23ኛ ጊዜ የተካሄደውን የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲጠናቀቅ ሃገራችን ኢትዮጵያ 4ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፤

ላለፋት ስድስት ቀናት ከ50ሺ ሰው በላይ የመያዝ አቅም ባለው የጃፑማ ሁለገብ ስታዲየም ከ50 ሃገራት የተውጣጡ 2500 አትሌቶችን በሁሉም የአትሌቲክስ ተግባራት ሲስተናግድ ከርሞ በዛሬው እለት ምሽት ላይ በደማቅ ስነ-ስርዓት ሻምፒዮናውን አጠናቋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያም በ32 ሴት እና በ36 ወንድ አትሌቶች በ21 የአትሌቲክስ የውድድር ተግባራት ተሳትፋ 27 ሃገራት በሜዳልያ ሰጠረዥ ውስጥ ከገቡ ሃገራት መካከል በ5 ወርቅ፣ በ4ብር እና 1ነሃስ በአጠቃላይ በ10 ሜዳልያዎች ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያንና ናይጄሪያን ተከትላ 4ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ስታጠናቅቅ በመጨረሻው ቀን በተካሄዱ ውድድሮች የሚከተሉት ውጤቶች ተመዝግበዋል፦

🌻 በ1500 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ፦
🥇ሳሮን በርሄ 4:06.05 🇪🇹
6ኛ ትዕግስት ግርማ 4:10.49
7ኛ ነፃነት ደስታ 4:12.49

🌻 በ3000 ሜትር መሠናክል ሴቶች ፍፃሜ፦
🥈አለምናት ዋለ 9:35.19 🇪🇹
4ኛ መሠረት የሻነህ 9:40.65
7ኛ ወሰኔ አሰፋ 10:04.65

🌻በ5000 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ፦
🥈ንብረት መላክ 13:42.95 🇪🇹
6ኛ መዝገቡ ስሜ 13:48.29
7ኛ ኃ/ማርያም አማረ 13:48.66

🌻በ400 ሜትር መሠናክል ሴቶች ፍፃሜ፦
8ኛ ባንቻየሁ ተሠማ 1:01.30

🌻በከፍታ ዝላይ ወንዶች ፍፃሜ፦
5ኛ ዱፕ ሊም 2.05 ሜትር
13ኛ ማል ጎኝ 1.90 ሜትር

🌻በስሉስ ዝላይ ሴቶች ፍፃሜ፦
10ኛ ፖች ኡመድ 12.29 ሜትር
11ኛ አጁሉ አዶላ 11.67 ሜትር

🌻በጦር ውርወራ ወንዶች ፍፃሜ፦
6ኛ ኦክት ጀምስ 69.08 ሜትር
7ኛ ኡታጊ ኡጉላ 68.75 ሜትር
10ኛ ኦታዋ ኦኬሎ 63.65 ሜትር

🌻በ4X400 ሜትር ሪሌ ወንዶች ፍፃሜ፦

7ኛ መልካሙ አሰፋ፣ ዮሐንስ ጌታነህ፣ ዮሐንስ ተፈራ እና አበበ ለሜቻ በ3:16.32 በሆነ ሰዓት አጠናቀዋል።

ስለ አስተናጋጇ ከተማ ዱዋላ በጥቂቱ፦

ዱዋላ በካሜሩን ውስጥ ከሚገኙ ከተሞች ትልቋ እና የኢኮኖሚ ዋና ማዕከል ነች። የካሜሩን ሊቶራል ክልልም ዋና ከተማም ነች። የመካከለኛው አፍሪካ ትልቁ ወደብ በከተማዋ ይገኛል። የአገሪቱ ዋና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዱዋላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በከተማዋ በመኖሩ በርካታ ወጪና ገቢ መንገደኞችን እና ቱሪስቶችን ታስተናግዳለች። ከተማዋ የካሜሩን የንግድ እና የኢኮኖሚ ዋና ከተማ በመሆኗ አብዛኛውን ከአገሪቱን ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ማለትም ዘይት፣ ኮኮዋ እና ቡና፣ እንጨት፣ ብረታ ብረት እና ፍራፍሬ የመሳሰሉትን በከተማዋ አልፈው ወደ ተለያዩ ሃገራት ኤክስፖርት ይደረግባታል። እ.ኤ.አ. በ2023 በከተማዋ በተደረገ ቆጠራ 5,066,000 ህዝብ እንደሚኖርባት ይገመታል ከተማዋ በዉሪ ወንዝ ዳርቻ ላይ የምትገኝ ሲሆን የአየር ንብረቷም ሞቃታማ ነው።

Credit :- EAF

"ስፖርት ለአብሮነትና ለአንድነት!"በድሬዳዋ የአስተዳደሩ ገጠር ስፖርት ፌስቲቫል  ማጠቃለያ የምስጋና እና እውቅና ኘሮግራም ሲካሄድ።በክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ ፓርክ #ሰኔ 22 ቀን 2016
30/06/2024

"ስፖርት ለአብሮነትና ለአንድነት!"
በድሬዳዋ የአስተዳደሩ ገጠር ስፖርት ፌስቲቫል ማጠቃለያ የምስጋና እና እውቅና ኘሮግራም ሲካሄድ።
በክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ ፓርክ #ሰኔ 22 ቀን 2016

12:00 አዳማ ከተማ - መቻል29ኛ ሳምንት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየምእሁድ ሰኔ 23/2016 credit :- EPLSCMesrak sport ምስራቅ ስፖርት
30/06/2024

12:00 አዳማ ከተማ - መቻል

29ኛ ሳምንት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም

እሁድ ሰኔ 23/2016

credit :- EPLSC

Mesrak sport ምስራቅ ስፖርት

ውጤትሀምበሪቾ 0 - 2 ወልቂጤ ከተማ                    19' መድን ተክሉ                    67' ጋዲሳ መብራቴ29ኛ ሳምንት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግበሃዋሳ...
30/06/2024

ውጤት
ሀምበሪቾ 0 - 2 ወልቂጤ ከተማ
19' መድን ተክሉ
67' ጋዲሳ መብራቴ
29ኛ ሳምንት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
በሃዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ

Credit :-EPLSC

Mesrak sport ምስራቅ ስፖርት

ውጤትሻሸመኔ ከተማ 0 - 2 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ                       40' ሱሌማን ሀሚድ                      63' አዲስ ግደይ29ኛ ሳምንት የ2016 የኢትዮጵያ...
30/06/2024

ውጤት
ሻሸመኔ ከተማ 0 - 2 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
40' ሱሌማን ሀሚድ
63' አዲስ ግደይ

29ኛ ሳምንት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም

Credit :_ EPLSC
Mesrak sport ምስራቅ ስፖርት

የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በድሬዳዋ ደምቋል።2ኛ ቀኑን የያዘው ሻምፒዮናው የቀጠለ ሲሆን ትናንት በመክፈቻው  ጨዋታ የድሬዳዋው ክለብ መስቀለኛ 3 - 3  ጊንጪ ከተማ አቻ ተለያይቷል።...
30/06/2024

የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በድሬዳዋ ደምቋል።

2ኛ ቀኑን የያዘው ሻምፒዮናው የቀጠለ ሲሆን ትናንት
በመክፈቻው ጨዋታ የድሬዳዋው ክለብ መስቀለኛ
3 - 3 ጊንጪ ከተማ አቻ ተለያይቷል።

ድሬዳዋ ስታዲየም የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራን ፤ የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሐመድ ጨምሮ ሌሎች የአስተዳደሩ እና የፌዴሬሽኑ አመራሮች እንዲሁም የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ ጨዋታ ቸሃ የጆካ 2 ለ 0 ሽረ አፍሪካ ሆቴልን አሸንፏል።

የ2016 የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የእግር ኳስ ውድድር ከ10 ክልሎች እና ከ2 የከተማ አስተዳደር የተወጣጡ 43 ክለቦች ተሳትፈዋል፥
ከሰኔ 22 እስከ ሐምሌ 16 /2016 ድረስ የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የእግር ኳስ ውድድር ይቆያል።

ይህ ውድድር በከተማዋ ሳቢያን ሜዳ ፤ ምድር ባቡር እና በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ጠዋት ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

Mesrak sport / ምስራቅ ስፖርት

28/06/2024

በድሬዳዋ የገጠር ስፖርት ፌስቲቫል 2ኛ ቀን የቮሊቦል ጨወታ እንቅስቃሴ

28/06/2024

በድሬዳዋ የገጠር ስፖርት ፌስቲቫል 2ኛ ቀን የአትሌቲክስ ውድድር እንቅስቃሴ ሲቃኝ
ሰኔ 20/2016

ስፖርት ለአብሮነትና ለአንድነት! የድሬዳዋ ገጠር ስፖርት ፌስቲቫል ተጀመረ።በድሬዳዋ ከተማ ከሰኔ 19 እስከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የሚካሄደው የአስተዳደሩ ገጠር ስፖርቶች ፌስቲቫል ተጀ...
26/06/2024

ስፖርት ለአብሮነትና ለአንድነት! የድሬዳዋ ገጠር ስፖርት ፌስቲቫል ተጀመረ።

በድሬዳዋ ከተማ ከሰኔ 19 እስከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የሚካሄደው የአስተዳደሩ ገጠር ስፖርቶች ፌስቲቫል ተጀምሯል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ደረጃ ፀጋዩ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የአስተባባሪ ኮሚቴ አባል እንደተናገሩት" በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የገጠር ወረዳዎች በስፖርት በማሳተፍ ለሀገራችን ያላቸውን የስፖርት እድገት ለማሳለጥ እና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍለቅ የምናደርገው እንቅስቃሴ የዚህ ፌስቲቫል ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል"፡፡
ውድድሩ የእርስበርስ ትስስር ፤ አብሮነት ፤ ወንድማማችነትን፤ እህትማማችነት በማጠናከር ተተኪ ስፖርተኞች ከማፍራት ባሻገር የአስተዳደሩን ልማትና እድገት በማፋጠን በጋራ የምንቆምበት እና የበለጠ ምንቀራረብበት መድረክ” መሆኑን አንስተዋል"፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሐመድ በበኩላቸው ፤ "ይህ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ከድሬዳዋ ባለፈ ለሀገር የሚጠቅሙ ስፖርተኞች ለማፍራት የሚያስችል መድረክ ነው ብለዋል፡፡
ስፖርተኞች በተለመደው ስፖርታዊ ስነ-ምግባር በጥሩ ጨዋታ ለመጣችሁበት ወረዳዎችም አንባሳደር ሆናችሁ ለወረዳችሁ ገፅታ ግንባታ አስተዋጽኦ በማድረግ አብሮነትና አንድነትን በወረዳዎች መሐል በማጠናከር የተሻለ ወንድማማችነት ፤ እህትማማችነትን ለመፍጠር የሚያግዝ እንደሆነ ኮሚሽነሩ አቶ ካሊድ ተናግረዋል"፡፡

በዕለቱ ተሳታፊ ልዑክ አርማቸውን ይዘው በክብር እንግዶች ፈት በሰልፍ አልፈዋል፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር እና በተማሪዎች ማርሽ ባንድ የደመቀው የድሬዳዋ የገጠር የስፖርት ፌስቲቫል ተጀምሯል፡፡ ከአሰሊሶ እና ቢዬ አዋሌ እግር ኳስ ቡድኖች ጋር የዕለቱ የክብር እንግዶች ትውውቅ አድርገዋል፡፡

በመክፈቻው በተካሄደው ጨዋታ አሰሊሶ 3 - 2 ቢዬ አዋሌን በጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ አሸንፈዋል፡፡ በተመሳሳይ በተካሄደው ሁለተኛው ጨዋታ ዋሒል ወረዳ 3 ለ 2 ቀልአድ ወረዳን አሸንፈዋል፡፡

ከአስተዳደሩ አራቱም ወረዳዎች ተሳታፊ ሲሆኑ ፤ በአጠቃላይ ከ1 መቶ 28 የገጠር የስፖርት ተወዳዳሪ ልዑክ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ይህ የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ ከሰዓት በኮሚሽኑ ሁለገብ ሜዳ በሚካሄደው የቮሊቦል ውድድር ይቀጥላል፡፡

DYSC -ሰኔ 19፤ 2016

29ኛ ሳምንት መርሃ ግብርየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በ2016ምስል EPLSCምስራቅ ስፖርት Telegram :-
23/06/2024

29ኛ ሳምንት መርሃ ግብር

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በ2016

ምስል EPLSC

ምስራቅ ስፖርት
Telegram :-

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በ2016ምስል EPLSCምስራቅ ስፖርት Telegram :-
23/06/2024

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች
28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በ2016

ምስል EPLSC

ምስራቅ ስፖርት
Telegram :-

28ኛ ሳምንት ደረጃ ሰንጠረዥየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በ2016ምስል EPLSCምስራቅ ስፖርት Telegram :-
23/06/2024

28ኛ ሳምንት ደረጃ ሰንጠረዥ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በ2016

ምስል EPLSC

ምስራቅ ስፖርት
Telegram :-

ውጤትቅዱስ ጊዬርጊስ 1 - 1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ21'ኤፍሬም ታምራት(በራስ ላይ) 41'ባሲሩ ኡመር28ኛ ሳምንት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እሁድ ሰኔ 1...
23/06/2024

ውጤት
ቅዱስ ጊዬርጊስ 1 - 1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
21'ኤፍሬም ታምራት(በራስ ላይ) 41'ባሲሩ ኡመር

28ኛ ሳምንት
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም
እሁድ ሰኔ 16/2016

ምስል :- EPLSC

ምስራቅ ስፖርት
Telegram :-

የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት መቻል በአንድ ነጥብ ልዩነት  ይከተላል !🔘 የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሰዋል ? የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት  በዋንጫ ፉክክር ውስጥ እጅግ ተጠባቂ በ...
23/06/2024

የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት መቻል በአንድ ነጥብ ልዩነት ይከተላል !

🔘 የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሰዋል ?

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት በዋንጫ ፉክክር ውስጥ እጅግ ተጠባቂ በነበረው የዛሬው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በ1 ለ 1 አቻ ውጤት በመለያየቱ የሊጉ መሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወሳኝ ሁለት ነጥብ ማሳካት ሳይችል ቀርቷል.

በዚህ መሠረት ትላንት ሲዳማ ቡናን 4 ለ 1 ካሸነፈው መቻል በአንድ ነጥብ ብልጫ መሪነቱን በ58 ነጥብ ቢቀጥልም ቀጣዮቹን ሁለት ጨዋታዎች ተጠባቂ አድርጎታል.

በቀጣይ በ29 ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መቻል ከ አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሻሸመኔ ከተማ. 30ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መድን እንዲሁም መቻል
ከ ድሬደዋ ከተማ ይሆናል.

  ዜና | በድሬዳዋ የገጠር  ስፖርቶች ፌስቲቫል  ሊካሄድ ነው ! የገጠር ስፖርቶች ውድድር ከፊታችን እሮብ ሰኔ 19 ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ ይካሄዳል ።የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮ...
23/06/2024

ዜና | በድሬዳዋ የገጠር ስፖርቶች ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው !

የገጠር ስፖርቶች ውድድር ከፊታችን እሮብ ሰኔ 19 ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ ይካሄዳል ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሐመድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ" የአስተዳደሩ የገጠር ስፖርቶች ውድድር በድሬዳዋ ከተማ ከፊታችን እሮብ ሰኔ 19 እስከ 22 ቀን ፣2016ዓም በድምቀት ለማካሄድ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል ።

የውድድሩ ዋና አላማ ከስፖርታዊ ውድድርነት ባሻገር በአስተዳደሩ የገጠርና ከተማ ወረዳዎች መካከል የማህበረሰቡን አብሮነት በማጎልበት የድሬዳዋን መልካም ገጽታ የሚገነባ መሆኑን ጠቁመዋል።
ድሬዳዋ የአብሮነት መዲና በመሆኗ ፤ ይሄን የህብረተሰቡን የተሳሰረ የአንድነትና ፍቅር የሚመጥን ውድድር ለማዘጋጀት ኮሚሽኑ ከስፖርት ፌዴሬሽኖች በጥምረት አስፈላጊ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ ኮሚሽነሩ አመላክተዋል።

በድሬዳዋ ለተከታታይ 4 ቀናት የሚቆየው የ2016 የገጠር ወረዳዎች የስፖርት ፌስቲቫል በ3 የስፖርት አይነቶች በአትሌቲክስ ፤ በቮሊቦል በሁለቱም ፆታ እንዲሁም በእግር ኳስ ውድድሮች እንደሚከናወን ገልፀዋል ።

በአራቱ የገጠር ወረዳዎች ላይ ባለፉት ወራት በቀበሌዎች መካከል በተደረጉ የውስጥ ውድድሮች በማጠናቀቅ 128 ምርጥ ተወዳዳሪዎች ተመርጠው የሚሳተፉበት ነው ተብሏል ።

የስፖርት ልዑካን ቡድኖች በመጪው ማክሰኞ ሰኔ 18 ቀን 2016 ድሬዳዋ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግም ተናግረዋል።

ለቡድኖቹ የማረፊያ ቦታ እንደተዘጋጀም የተናገሩት ኮሚሽነሩ በተለይም የአስተዳደሩን ገጠር ማህበረሰብ በስፖርት ተሳታፈነቱን ለማጎልበት ፤ ምርጥ ስፖርተኞችን ለማፍራት ፤ የከተማዋን እና የገጠሩን ህብረተሰብ የአብሮነት እሴታቸውን ከማጠናከር ባለፈ አንድነትንና ፍቅርን በስፖርቱ መድረክ የሚያጠናክሩበት የባህል ምሽት ኘሮግራሞች መዘጋጀቱ ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል ።

ባለፉት ጊዜቶች ተቋርጦ የቆየውን የገጠር ወረዳዎች የስፖርት ውድድሮች በኮሚሽኑ በኩል ትኩረት የተሰጠው እንደሆነ የተናገሩት አቶ ካሊድ በቀጣይ ስፖርታዊ ተሳትፎ ለማጠናከር መታቀዱ ተገልፃል ።

የዘንድሮው የአስተዳደሩ የገጠር ወረዳዎች የስፖርት ፌስቲቫል እሮብ ሰኔ 19 ቀን 2016 ሳቢያን ሜዳ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት በታላቅ ደምቀት ይከፈታል ።

እሁድ 16 ቀን፣ሰኔ 2016ዓም

ምስራቅ ስፖርት | Mesrak Sport

ድሬዳዋ በዊልቸር ቅርጫት ኳስ የነሐስ ሜዳሊያ አገኙ ! የድሬዳዋው ኮከብ ተጫዋች ፍቃዱ ኃይሉ ዋንጫ ተሸልሟል፡፡    8ኛው የኢትዮጵያ ዊልቸር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና በአዋሳ በተካሄደው ውድድር...
22/06/2024

ድሬዳዋ በዊልቸር ቅርጫት ኳስ የነሐስ ሜዳሊያ አገኙ !
የድሬዳዋው ኮከብ ተጫዋች ፍቃዱ ኃይሉ ዋንጫ ተሸልሟል፡፡

8ኛው የኢትዮጵያ ዊልቸር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና በአዋሳ በተካሄደው ውድድር የድሬዳዋ ዊልቸር የቅርጫት ኳስ ቡድን በወንዶች 3ኛ በመሆን የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቋል፡፡ ከድሬዳዋ ፍቃዱ ኃይሉ ኮከብ ተጫዋች በመሆን የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
በአዋሳ አስተናጋጅነት ሰኔ 12ቀን 2016 በተጠናቀቀው የዊልቸር ቅርጫት ኳስ ውድድር የድሬዳዋ ልዑካን በሁለቱም ፆታ 25 አባላት ተሳትፈዋል፡፡
በዚህ ዓመታዊ ሀገር አቀፍ ውድድር በሴቶች ኦሮሚያ ፤በወንዶች አዲስ አበባ አንደኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ ድሬዳዋ በወንዶች 3ኛ ሆኗል፡፡በሴቶች 5ኛ ደረጃን በመያዝ ጥሩ ተፎካካሪ ሆነው በማጠናቀቅ ልዑካን ቡድኑ ድሬዳዋ ገብተዋል፡፡በስፍራው ከተገኙት የውድድር ተሳትፎ ኬዝ ቲም ከፍተኛ ባለሙያ ከወ/ት መቅደስ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#ሰኔ 15 ፣ 2016

ያለ ምባፔ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ድል ማድረግ ይችላል?በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በምድብ 4 ውስጥ የተደለደለችው ፈረንሳይ ትናንት ከኔዘርላንድስ ጋር በነበራት ፍልሚያ ወሳኝ አጥቂዋን ኪሊያን...
22/06/2024

ያለ ምባፔ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ድል ማድረግ ይችላል?

በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በምድብ 4 ውስጥ የተደለደለችው ፈረንሳይ ትናንት ከኔዘርላንድስ ጋር በነበራት ፍልሚያ ወሳኝ አጥቂዋን ኪሊያን ምባፔን አላሰለፈችም።

ባለፈው ፈረንሳይ ከኦስትሪያ ጋር በነበራት ጨዋታ የአፍንጫ ስብራት የገጠመው አዲሱ የሎስ ብላንኮዎቹ ፈራሚ ምባፔ በትናንቱ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ባይሰለፈም ሰፊውን የካሜራ ትኩረት አግኝቷል።

ምባፔ ስሜቱን ለካሜራ መደበቅም አልቻለም። እንደ ቢቢሲ ስፖርት ዘገባ ምባፔ ጨዋታውን በጭንቀት ይከታተለው ነበር። ለቡድን አጋሮቹም ድጋፉን በጩኸት ሲያሰማ ታይቷል።

የ25 ዓመቱ ፈረንሳዊ ኮከብ ኪሊያን ምባፔ የአፍንጫ ስብራት ከገጠመው በኃላ ባለፈው ሐሙስ ሀገሩ ከኔዘርላንድስ ጋር ለሚኖራት ጨዋታ ጭምብል ለብሶ ልምምድ ሲያደርግ ነበር። አሠልጣኙ ዲዲየር ዴሾም ምባፔ ፈርንሳይ ከኔዘርላንድስ ጋር ለሚኖራት ጨዋታ ሊሰለፍ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልጸው ነበር። በመጨረሻ ግን ዴሾ በዚኽ ጨዋታ ጉዳት ላይ ያለውን ኮከብ ምባፔን ማሰለፍ አዋጭ ኾኖ ስላላገኙት ተጫዋቹን ተጠባባቂ አድርገውታል።

ምባፔ ባልተሰለፈበት በዚኽ ጨዋታ ፈረንሳይ ያገኘችውን በርካታ የጎል እድል ሳትጠቀም ቀርታለች። ምባፔ ሳይኖር ግብ ማስቆጠር ያልቻሉት የብሔራው ቡድኑ አሠልጣኝ ዲዲየር ዴሾ "ይህ ብዙ አያሳስበኝም " ብለዋል። "አንዳንድ ጊዜ በርካታ እድል ተፈጥሮልህ ኳስን ከመረብ ላታገናኝ ትችላለህ እና ጉዳዩ በሌላ መልኩ ሊታይ የሚችል ነው" ሲሉ የተነሳባቸውን ትችት ተከላክለዋል።

ፈረንሳይ የብዙ ባለተሰጥኦ ተጨዋቾች ስብስብ እንደኾነ የዘገበው ቢቢሲ የምባፔ አለመኖር ግን አሳሳቢ ስለመኾኑ ገልጿል። ለዚህም ፈረንሳይ ባለፉት 2 ዓመታት ያለ ምባፔ በተጫወተቻቸው 7 ጨዋታዎች ማሸነፍ አለመቻሏን እንደ ማስረጃ ያቀርባል።

ዴሾ ከጨዋታው በኃላ በሰጡት አስተያየት "ጨዋታው በጣም ወሳኝ ቢኾን ኖሮ የምባፔን መሰለፍ እና አለመሰለፍ ጉዳይ ደግሜ አስብበት ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።

አጥቂውን አለማሰለፋቸው በሳል ውሳኔ ስለመኾኑ ደጋግመው የተናገሩት ዴሾ ትልቁን ስዕል ማየት እንደሚገባ ይናገራሉ። ውሳኔያቸውም ጉዳት ላይ ለሚገኘው ምባፔም ኾነ ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጠቃሚ ስለመኾኑ አስረድተዋል።

ምስራቅ ስፖርት

በአውሮፓ ዋንጫ አስገራሚ ሽንፈቶች እና ድሎች ከዓለም ዋንጫ ቀጥሎ የብዙዎችን ቀልብ የሚስበው የአውሮፓ ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታ ባሳለፋቸው ዘመናት የተለያዩ አስገራሚ ውጤቶችን ለታዳሚያኑ አስ...
22/06/2024

በአውሮፓ ዋንጫ አስገራሚ ሽንፈቶች እና ድሎች

ከዓለም ዋንጫ ቀጥሎ የብዙዎችን ቀልብ የሚስበው የአውሮፓ ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታ ባሳለፋቸው ዘመናት የተለያዩ አስገራሚ ውጤቶችን ለታዳሚያኑ አስመልክቷል፡፡ ቢቢሲ በድረ ገጹ የከተባቸውን ትውስታዎች በጥቂቱ እንመልከት፦

እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ1988 በምድብ ጨዋታ ላይ እንግሊዝ በአየርላንድ 1 ለ 0 ተረትታለች፡፡

👉1992 በምድብ ጨዋታ ስዊድን 2 – 1 እንግሊዝ

👉1992 በፍጻሜ ጨዋታ ጀርመን 0 – 2 ዴንማርክ

👉1996 በምድብ ጨዋታ ቼክ ሪፐብሊክ 2 – 1 ጣሊያን

👉2004 የምድብ ጨዋታ ላቲቪያ 0 – 0 ጀርመን

👉2004 የፍጻሜ ጨዋታ ፖርቱጋል 0 – 1 ግሪክ

👉2016 በጥሎ ማለፍ እንግሊዝ 1 – 2 አይስላንድ

👉2020 በጥሎ ማለፍ ኔዘርላንድ 0 – 2 ቼክ ሪፐብሊክ

👉2024 በምድብ ጨዋታ ቤልጅየም 0 – 1 ስሎቫኪያ

ከእነዚህ አስገራሚ እና ያልተጠበቁ ውጤቶች ውስጥ በ1992 ዴንማርክ ጀርመንን 2 ለ 0 አሸንፋ ዋንጫ ያነሳችበት ውጤት በእጅጉ አስገራሚ ነው፡፡ ውጤቱን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ዴንማርካውያን የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ሳያልፉ የቀሩ ቢኾንም በወቅቱ ወደ ጦርነት የገባችው የምድቡ አላፊ ዩግዝላቪያን ተክተው የአውሮፓ ዋንጫው ሊጀመር 15 ቀናት ብቻ ሲቀሩት እንዲሳተፉ የተነገራቸው መኾኑ ነው፡፡

ከምድባቸው ማለፍ ተስኗቸው ለእረፍት በየቦታው የተበታተኑት የዴኒማርክ ተጨዋቾች ከያሉበት ተሰባስበው በአውሮፓ ዋንጫ ላይ መሳተፋቸው ብቻ ሳይኾን በወቅቱ ጠንካራ የነበረችውን ጀርመን 2 ለ 0 አሸንፈው ዋንጫ ማንሳታቸው በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ ፈጽሞ የማይዘነጋ ክስተት ነው፡፡

ሌላኛው አስገራሚ ውጤት የተመዘገበው ደግሞ በ2004 ግሪክ የአውሮፓ ዋንጫ አዘጋጇን ፖርቱጋልን በሜዳዋ እና በደጋፊዋ ፊት 1 ለ 0 አሸንፋ ዋንጫ ያነሳችበት ውጤት ነው፡፡

ግሪክ ለአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታው ሳትጠበቅ ለፍጻሜ መድረሷ ብቻ ሳይኾን በጀርመናዊው አሰልጣኝ ኦቶ ሪሃግል እየተመራች ፖርቱጋልን አሸንፋ የመጀመሪያዋን እና ብቸኛዋን የአውሮፓ ዋንጫ ድሏን ማሳካቷ ከአስገራሚ የአውሮፓ ዋንጫ ክስተቶች ውስጥ አንዱ እንዲኾን አድርጎታል፡፡

በጀርመኑ 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫስ ምን አይነት ያልተጠበቁ ሽንፈቶችን እና ድሎችን እንመለከት ይኾን?

ምስራቅ ስፖርት

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ካሜሩን አቀና በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ወደ ካሜሩን ዱዋላ አቀና፡፡23ኛው...
19/06/2024

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ካሜሩን አቀና

በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ወደ ካሜሩን ዱዋላ አቀና፡፡

23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በካሜሩን አስተናጋጅነት በዱዋላ እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ልዑክም ዛሬ ጠዋት ወደ ካሜሩን ያቀና ሲሆን÷ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የሥራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አሸኛኘነት አድርገውለታል፡፡

ሰኔ 12፣ 2016

ኢትዮጵያ እና የኦሎምፒክ ውድድሮችኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ መካፈል ከጀመረች 76 ዓመት ሆኗታልበኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ 58 ሜዳሊያዎች ያገኘችው ኢትዮጵያ የፊታችን ሀምሌ በሚካሄደው ...
19/06/2024

ኢትዮጵያ እና የኦሎምፒክ ውድድሮች

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ መካፈል ከጀመረች 76 ዓመት ሆኗታል

በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ 58 ሜዳሊያዎች ያገኘችው ኢትዮጵያ የፊታችን ሀምሌ በሚካሄደው ፓሪስ ኦሎምፒክ ላይም ትሳተፋለች

ምስል አልአይን

የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ (ምስራቅ ስፖርት )፤ ሰኔ 12/2016 ፦ በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ...
19/06/2024

የአውሮፓ ዋንጫ
የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ

(ምስራቅ ስፖርት )፤ ሰኔ 12/2016 ፦ በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል።

ውድድሩ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።

"የሞት ምድብ" የሚል ስያሜ በተሰጠው ምድብ 2 ክሮሺያ ከአልባኒያ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ 57 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ቮልክስፓርክ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሁለቱም አገራት በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸው ሽንፈት አጋጥሟቸዋል። ክሮሺያ በስፔን 3 ለ 0 እንዲሁም አልባኒያ በጣልያን 2 ለ 1 ተሸንፈዋል።

የ57 ዓመቱ የክሮሺያ አሰልጣኝ ዝላትኮ ዳሊች ቡድናቸው በስፔን ከደረሰበት ሽንፈት በኋላ በጨዋታው ላሳየው ብቃት ደጋፊዎችን ይቅርታ ጠይቀዋል።

በአውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛ ተሳትፎውን እያደረገ የሚገኘው የአልባኒያ ብሔራዊ ቡድን ከወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ጣልያን ጋር በነበረው ጨዋታ ያሳዩት የአልሸነፍ ባይነት ስሜት አድናቆት አስችሯቸዋል።

ክሮሺያና አልባኒያ እርስ በእርስ ሲገናኙ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በመጀመሪያ ጨዋታቸው ሽንፈት የገጠማቸው ሁለቱ አገራት በውድድሩ ላይ ለመቆየትና ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ተስፋቸውን ለማለምለም የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ይላቸዋል።

በፊፋ የአገራት የእግር ኳስ ደረጃ ክሮሺያ 10ኛ፣ አልባኒያ 66ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የ35 ዓመቱ ፍራንስዋ ሌትክሲየር የሁለቱን አገራት ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመራሉ።

በምድብ 1 አዘጋጅ አገር ጀርመን ከሀንጋሪ ከምሽቱ 1 ሰዓት 60 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ስቱትጋርት አሬና ስታዲየም ይጫወታሉ።

ጀርመን በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ ስኮትላንድን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች። በአንጻሩ ሀንጋሪ በስዊዘርላንድ የ3 ለ 1 ሽንፈት ገጥሟታል።

ሁለቱ አገራት በአውሮፓ ዋንጫ መድረክ ሲገናኙ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

ከአራት ዓመት በፊት በተደረገው 16ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በምድብ 6 ተገናኝተው ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ካይ ሃቫርትዝ እና ሊኦን ጎሬትዝካ ለጀርመን እንዲሁም አዳም ዛላይና አንድራስ ሻፈር ለሀንጋሪ ግቦችን በወቅቱ ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

አገራቱ በውድድርና የወዳጅነት ጨዋታዎች እስካሁን 37 ጊዜ ተገናኝተው ጀርመን 13 ጊዜ ስታሸነፍ 12 ጊዜ ደግሞ ሀንጋሪ አሸንፋለች፤ 12 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

ለመጨረሻ ጊዜ አገራቱ የተገናኙት እ.አ.አ በ2022 በዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ ውድድር ላይ ሲሆን ሀንጋሪ አዳም ዛላይ ባስቆጠረው ግብ ጀርመንን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ጀርመን የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈች ጥሎ ማለፍ መግባቷን የምታረጋግጥ ይሆናል። በአንጻሩ ሀንጋሪ ከውድድሩ በጊዜ ላለመሰናበት ጀርመንን የማሸነፍ ከባድ ፈተና ይጠብቃታል።

የ41 ዓመቱ ኔዘርላንዳዊ ዳንኤል ማኬሊ የሁለቱን አገራት ጨዋታ በመሐል ዳኝነት ይመሩታል።

በምድብ 1 ሌላኛው መርሐ ግብር ስኮትላንድ ከስዊዘርላንድ ጨዋታ ከምሽቱ 4 ሰዓት 50 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ኮሎኝ ስታዲየም ይደረጋል።

ስኮትላንድ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በጀርመን 5 ለ 1 የተሸነፈች ሲሆን ስዊዘርላንድ ሀንጋሪን 3 ለ 1 አሸንፋለች።

በ53 ዓመቱ ሙራት ያኪን የሚመራው የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ወደ ጥሎ ማለፉ ይገባል።

በአንጻሩ ስኮትላንድ በውድድሩ ያላትን ቆይታ ለማራዘም ከመጀመሪያው ጨዋታ ሽንፈት አገግማ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ይኖርባታል።

የ40 ዓመቱ ስሎቫኪያዊ ኢቫን ክሩዝሊያክ የሁለቱን አገራት ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

በተያያዘ ትናንት በምድብ 6 በተደረጉ ጨዋታዎች ተርኪዬ ጆርጂያን 3 ለ 1 እንዲሁም ፖርቹጋል ቼክ ሪፐብሊክን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።

ይቺን ለቅምሻ28ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሃ ግብርየ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየምምንጭ EPLSCMesrak sport ምስራቅ ስፖርት
17/06/2024

ይቺን ለቅምሻ
28ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሃ ግብር
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም

ምንጭ EPLSC

Mesrak sport ምስራቅ ስፖርት

ይቺን ለቅምሻ !27ኛ ሳምንት ደረጃ ሰንጠረዥ የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምንጭ EPLSCምስራቅ ስፖርት
17/06/2024

ይቺን ለቅምሻ !
27ኛ ሳምንት ደረጃ ሰንጠረዥ
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም

ምንጭ EPLSC

ምስራቅ ስፖርት

ይቺን ለቅምሻ !ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች27ኛ ሳምንት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ምንጭ EPLSCምስራቅ ስፖርት
17/06/2024

ይቺን ለቅምሻ !
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች
27ኛ ሳምንት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም

ምንጭ EPLSC
ምስራቅ ስፖርት

ዜና NEWS | ፀረ አበረታች ቅመሞች ለመከላከል በድሬዳዋ !እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር የፀረ አበረታች ቅመሞች (ፀረ- ዶፒንግ )በመከላከል  ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ የኢትዮጵያ ፀረ አበረ...
17/06/2024

ዜና NEWS | ፀረ አበረታች ቅመሞች ለመከላከል በድሬዳዋ !

እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር የፀረ አበረታች ቅመሞች (ፀረ- ዶፒንግ )በመከላከል ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ዳሬክተር በአቶ መኮንን ይደርሳል የተመራው የዘርፉ ባለሞያ ቡድን ከድሬደዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ከአቶ ካሊድ መሐመድ እና ከኮሚሽኑ ዳሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዛሬ በኮሚሽነሩ ጽ/ቤት ባደረጉት ምክክር "በዋንኛነት በድሬዳዋ የፀረ አበረታች ቅመሞች ላይ እየተሰሩ ያለውን ስራ ለመገምገም ያለመ የስራ ኃላፊዎች እና የባለሙያዎች የጋራ መድረክ ነው፡፡

በዚህ ውይይታቸው ከተነሱ ሀሳቦች "በድሬዳዋ ምን እየተሰራ እንደሆነ በኤጀንሲው የማብራሪያ ጥያቄ ቀርቧል፡፡ ይህን በተመለከተ በአስተዳደሩ የፀረ አበረታች ቅመሞችን በስፖርት ዘርፍ ለመከላከል እንደ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን በተለይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራን በእቅድ ተካቶ ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ ተሰርቷል፡፡ ለአሰልጣኖች ፣ለስፖርተኖች ፣ ለስፖርት አመራሮች ተከታታይ የስልጠና መድረክ እንደተዘጋጀም በማሳያነት ተብራርቷል"፡፡

ፀረ አበረታች ቅመሞችን የሚመለከት በኮሚሽኑ የህክምና ክፍል ከትምህርትና ስልጠና ኬዝ ቲም ጋር በቅንጅት የስፖርት ቤተሰብ እና ባለድርሻ አካላት ላይ ያተኮረ የቅደመ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጥ ሰራዎች መከናወናቸውን በኮሚሽነሩ አቶ ካሊድ መሐመድ እና በባለሙያዎች ተገልጿል፡፡ በቀጣይ ፀረ አበረታች ቅመሞችን በድሬደዋ ለመከላከል የበለጠ በአደረጃጀት ዙሪያ ማጠናከር እንደሚገባም የጋራ መግባባት ተደርሷል፡፡

ሰኞ 10 ፣ ሰኔ ፣ 2016ዓም
ድሬዳዋ

17/06/2024

በምስራቅ ኢትዮጵያ ETG የዲዛይን እና የግንባታ አማካሪ

➲ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ኢድ አል-አድሃ( አረፋ) በዓል አደረሳችሁ ፤

➲ ድርጅታችን በግንባታው ዘርፍ በምንሰራው ዘመናዊ ዲዛይን ስራዎቹ እና ለግንባታው ጥራት ዋነኛው መለያችን ነው፡፡

➲የምስራቅ ድምፅ የስፖርትና መዝናኛ የምንጊዜም የክብር አጋር ETG የዲዛይን እና የግንባታ አማካሪ ➲በዓሉ የሰላም የጤናና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

➲ከETG ዲዛይንና የግንባታ አማካሪ ድርጅት ጋር ለሌላ ስኬት፤ ኑ..ሀገርንና መሠረተ ልማትን እንገነባለን፡፡

መልካም በዓል

ውጤትወላይታ ድቻ 2 - 1 ሀድያ ሆሳዕና54' አብነት ደምሴ 11' ተመስገን ብርሃኑ83' ብሩክ ማርቆስ(በራስ ላይ)27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እሁድ ሰ...
16/06/2024

ውጤት
ወላይታ ድቻ 2 - 1 ሀድያ ሆሳዕና
54' አብነት ደምሴ 11' ተመስገን ብርሃኑ
83' ብሩክ ማርቆስ(በራስ ላይ)

27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም
እሁድ ሰኔ 09/2016

ምስል ምንጭ:-EPLSC

Mesraksport ምስራቅ ስፖርት

ውጤትሻሸመኔ ከተማ 0 - 2 ኢትዮጵያ መድን          45' ምንተስኖት ከበደ(በራስ ላይ)          90+3' አብዲሳ ጀማል27ኛ ሳምንት  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ...
16/06/2024

ውጤት
ሻሸመኔ ከተማ 0 - 2 ኢትዮጵያ መድን
45' ምንተስኖት ከበደ(በራስ ላይ)
90+3' አብዲሳ ጀማል

27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም

እሁድ ሰኔ 09/2016

ምስል ምንጭ EPLSC

Mesraksport ምስራቅ ስፖርት

Address

Ethiopia, , Dire Dawa
Addis Ababa

Telephone

+251915750424

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት:

Videos

Share

Category

Nearby media companies



You may also like