Paradigm Shift

Paradigm Shift The truth

15/10/2023
"የዛሬ ሃምሣ እና ስልሳ ዓመት ኃይለስላሴ ስለአባይ ሲያወሩ አታስበው ትነካትና ወዮውልህ ፤ ትሞክራትና ወዮውልህ ሲባሉ ፣ እኔ አሁን አቅም የለኝም ፤ ልጆቼ ይሰሩታል። አሁን ቀይባህርን ትነካ...
14/10/2023

"የዛሬ ሃምሣ እና ስልሳ ዓመት ኃይለስላሴ ስለአባይ ሲያወሩ አታስበው ትነካትና ወዮውልህ ፤ ትሞክራትና ወዮውልህ ሲባሉ ፣ እኔ አሁን አቅም የለኝም ፤ ልጆቼ ይሰሩታል። አሁን ቀይባህርን ትነካትና ትለኛለህ እኔ አቅም የለኝም ልጆቼ ያመጡታል! አሁን አይቻልም ማለት ነገ አይቻልም ማለት አይደለም!" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ታሪክ ራሱን ደገመ ፤ ታላቅ ጉዞ ዛሬ ተጀመረ!

አዲስ አበባን የክልሎች እናትና የችግሮቻችን  ጋሻ ያደረገቺዉ መሪ  !!*************አዲስ አበባ የብልፅግናችን ኦኬስትራ መሪ ብቻ አይደለችም ፤ አዲስ አበባ የጭንቅ ቀን ደራሻችንም ና...
12/10/2023

አዲስ አበባን የክልሎች እናትና የችግሮቻችን ጋሻ ያደረገቺዉ መሪ !!
*************
አዲስ አበባ የብልፅግናችን ኦኬስትራ መሪ ብቻ አይደለችም ፤ አዲስ አበባ የጭንቅ ቀን ደራሻችንም ናት።

የአዲስ አበባ እንደተለመደዉ ማንም ሳይቀድማት ማልዳ በችግሩ ጠዋት ጅጅጋን አለሁልሽ ስትላት የተሰማኝ ደስታ በምንም አይሰፈርም እንጂ ወደር የሌለዉ ነበር ።

አንዳንዴ አምላክ እራሱ ካድሬ ካድሬ ከሚሸተዉ ከያ ዘመን አዉጥቶ ሰዉ ሰዉ የሚሸቱ መሪዎችን የሰጠን ምንኛ ቢወደን ነዉ እላለሁ ።
እርግጥ ነዉ የሰዉ ልጅ በምድር ሳለ ችግሮች አይገጥሙትም አይባልም ። ህይወት በራሷ ባለ ብዙ ዉጣ ዉረድ ዝክዛክ መስመር ናትና ።
በጂግጂጋ ከተማ በደረሰው የእሳት የወደመውን ታይዋን የገበያ ማዕከል መልሶ ለመገንባት እና ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ላይ የከተማችን ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ነዉ ያደረጉት።

ወገኑን ያልረዳ ገንዘብ ትርጉሙ ወረቀት ነዉና ፤ እዉነት ለመናገር የከንቲባዋ ተግባር የወንድማማችነትን ምሰሶ በማይፈርስ አለት ላይ ያፀና ነዉ ።

በመርሃ ግብሩ ላይ 20 ሚሊዮን ብር በገንዘብ እና 10 ሚሊዮን ብር በአይነት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ምክንያቶች ላጋጠሙ ችግሮች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ እጅግ እንድናመሰግነዉ ያስገድደናል ።

11/10/2023
የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ ነዋሪዎች የበዓሉ አክባሪዎችን በወንድማማችነት መንፈስ ተቀብለው ለማስተናገድ ላሳዩት ፍቅር ከፍተኛ አድናቆት አለኝ።አባገዳ ጎበና ሆላ።
09/10/2023

የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ ነዋሪዎች የበዓሉ አክባሪዎችን በወንድማማችነት መንፈስ ተቀብለው ለማስተናገድ ላሳዩት ፍቅር ከፍተኛ አድናቆት አለኝ።

አባገዳ ጎበና ሆላ።

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታዳሚ ፍፁም ሰላማዊ እና ወንድማማችነት ጎልቶ በታየበት መልኩ አክብሯል ።...
09/10/2023

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታዳሚ ፍፁም ሰላማዊ እና ወንድማማችነት ጎልቶ በታየበት መልኩ አክብሯል ።

አባገዳ ጎበና ሆላ

ኮርፖሬሽኑ በጅማ ከተማ ለሚገነባው አልባድር አጠቃላይ ሆስፒታል የግንባታ ማመከር አገልግሎት ለመስጠት ተስማማ******** የፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጅማ ከተማ ለሚገነባው አልባድር  ሆስፒታ...
09/10/2023

ኮርፖሬሽኑ በጅማ ከተማ ለሚገነባው አልባድር አጠቃላይ ሆስፒታል የግንባታ ማመከር አገልግሎት ለመስጠት ተስማማ
********

የፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጅማ ከተማ ለሚገነባው አልባድር ሆስፒታል የግንባታ ማመከር አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት ፈጸመ፡፡ ስምምነቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና ባለሀብትና የአባድር ሆስፒታል ባለቤት የሆኑት አቶ በድሩ ሰማን ተፈራርመዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በፊት ለበርካታ የመንግስት ተቋማት ፕሮጀክቶች የግንባታ ማመከር እየሰጠ ሲሆን አድማሱን በማስፋት በግል በለሀብቶች የሚገነቡ አገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች ማመከር መጀመሩምንም ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡ የአልባድር አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታ የማከከር አገልግሎትም የመጀመሪው ፕሮጀክት እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

ትርፍን ሣይሆን ፕሮጀከቱ በጥራትና በተያዘለት የጊዜ ገደብ ቢጠናቀቅ የሚያስገኘውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ግምት ውስጥ ያስገባ ሥራ ኮርፖሬሽኑ እንደሚያከናወን ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በስምምነት ሥነ ሥርዓቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡ ለዚሁ የሚረዳ ጠንካራ አደረጃጀት ኮርፖሬሽኑ አለውም ብለዋል ክቡር ዋና ስራ አስፈጻሚው፡፡

በላሀብት የአልባድር ሆስፒታል ባለቤት በበኩላቸው የአገር ምልክት እየሆነ ካለ በዘርፉ ውጤታማ ከሆነ ደርጅት ጋር አብሮ መስራታችን ኩራት ይሰማናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ጋር አብሮ ለመስራት በመስማማታችን ተጨማሪ አቅምና ልምድ ማግኘት ያስችለናል ሲሉ ተናገረዋል፡፡

ሕንጻው በላ 5 ወለል የሆነ ለአጠቃላይ ሆስፒታል ታስቦ በጅማ ከተማ እየተገነባ ያለ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሠራተኞቻቸው  ወርቅ ተሸለሙ********ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በተጨማሪ ለአራቱም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ከሰራተኛው...
05/10/2023

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሠራተኞቻቸው ወርቅ ተሸለሙ
********

ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በተጨማሪ ለአራቱም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ከሰራተኛው እውቅና አግኝተዋል፡፡

ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በኮርፖሬሽኑ ታሪክ እጅግ ስኬታማው እና የመሪነትን ገጽታ የተላበሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከሰራተኞቻቸው ወርቅ ተሸልመዋል፡፡

የወርቅ ሽልማቱን የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን(ኢሠማኮ) ፕሬዜዳንት አቶ ካሳሁን ፎሌ ለክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል ሠጥተዋል፡፡

አቶ ካሳሁን ፎሌ ኮርፖሬሽኑ ለአሰሪ ተቋማት ሞዴል ተቋም መሆኑን እና የኮርፖሬሽኑ መሪዎች የሰራተኛውን ጥቅም ለማስጠበቅ ላከናወኑት ውጤታማ ተግባርም ኢሰማኮ እውቅና እንደሚሰጠው ተናገረዋል፡፡

ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በመልዕክታቸው ለተበረከተላቸው ሽልማት አመስግነው፣ ሠራተኞች በተገኘው ውጤት ሳይኩራሩ ለአገራዊ ብልጽግና እድገት እንዲተጉ ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው መላ ሠራተኛውን ለለውጥ በማነሳሳት አገራዊ ለውጡን መነሻ በማድረግ ውጤታማ የተቋም ግንባታ በማካሔድ ትራፋማ ጠንካራ የልማት ድርጅት መፍጠር እንደቻሉ ተገልጿል፡፡

በክቡር አቶ ረሻድ ከማል መሪነት ተቋሙ አጠቃላይ ሀብቱ 260 ቢሊየን የደረሰ ሲሆን ገቢው ከዘጠኝ እጥፍ በላይ ጭማሪ በማሳየት 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የኮርፖሬሽኑ ዓመታዊ ገቢ ሆኖ መመዝገቡም ነው የተነገረው፡፡

ተቋሙ እንደ ዋናኛ ሥራው አድርጎት የቆየው የቤት ማስተዳደር ሥራ ቢሆንም ፣ በቅጡ እንኳን የቤቶችን ቁጥር የማያውቅ የነበረው ኮርፖሬሽን ፣ በአሁኑ ሰዓት መረጃዎችን አደራጅቶ ፣ቤቶቹን ቆጥሮ ለእያንዳንዱ ቤት መላያ ታግ እስከለመለጠፍ መድረሱም የሳቸው አሻራ በጉልህ የታየበት መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ከ28 ዓመት በላይ ቆሞ የነበረው ቤት ግንባታ እንደአዲስ በክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከ12 ሳይቶች በላይ ግንባታ በማስጀመር በአሀኑ ሰዓት ስደስት ሳይቶችን ማጠናቀቅ እንደታቻለም ሠራተኞቹ አንስተዋል፡፡

ከሀገር በቀሉ ኦቪድ ጋር በመጣመር በ18 ወራት አንድ መንደር መገንባት የሚያስችል ለአገር የተረፈ አቅምና ችሎታ በመፍጠር ረገድም የዋና ሥራ አስፈጻሚው ደርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተነስቷል ፡፡

የራሱን ቤቶች እንኳ በአግባቡ ማደስ የማይችለው ተቋም ግንባታው ዘርፍ አውራ ሆኖ መውጣቱና የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን እና ልምዶችን በመላ አገሪቱ ለማካፈልም ለማስፋፈትም የተመረጠ ብቁ ተቋም እንዲሆን ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው መስራታቸውም ነው ሠራተኞቹ ያነሱት፡፡

የኮንስትራክሽን ዘርፉን የግብዓት አቅርቦት የሚያቃልል በየዓመቱ ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ የሚያስገኝ የኮንክሪት ውህድና የብሎኬት ማምረቻ ተከላ ሥራም ማስጀመራቸውም የዋና ሥራ አስፈጻሚው የመሪነት ብቃት የታየበት ሌላኛው የስኬት ማሳያ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎችም የዋና ሥራ አሰፈጻሚው ራዕይና ግብ እንዲሳካ ላደረጉት የላቀ አስተዋጽኦ ከሠራተኞቹ እውቅና አግኝተዋል፡፡

እስክንድር Vs ዘመነዘመነ ካሴ መምራት ጀምሯል። ኤርትራዊው ዘመነ ካሴና እስክንድር ነጋ በመሃላቸው የተፈጠረው አለመግባባት ወደመቀጣጠሉ ደርሷል። አሁን ላይ ባለው ፉክክር ዘመነ አንድ ለዜሮ ...
03/10/2023

እስክንድር Vs ዘመነ
ዘመነ ካሴ መምራት ጀምሯል። ኤርትራዊው ዘመነ ካሴና እስክንድር ነጋ በመሃላቸው የተፈጠረው አለመግባባት ወደመቀጣጠሉ ደርሷል። አሁን ላይ ባለው ፉክክር ዘመነ አንድ ለዜሮ እየመራ እንደሚገኝ ተሰምቷል። ዘመነ አንድ ለዜሮ የመራው እስክንድርን በጥይት አንድ እግሩን አንድዶለት እንደሆነ ተሰምቷል። የማይሰበረው ስትሉት የነበረው እስክንድር በጥይት አንድ እግሩ ተቦንድሷል። አሁን ነው እንግዲህ ጉድ የፈላው። ሌላ ምንም አልልም እስክንድር በሁለት እግሩ ጫካ ገብቶ ያለ እግር ይመለሳል ወይስ የጀመረው ዘመነ እዛው ይጨርሰው ይሆን⁉️🤔 ከፈለገ ይጨርሰው እኛ ምና ገባን😂

♦️ዛሬ በአዲስ አበባ የተመረቀው ምገባ ማዕከል የምገባ ማዕከላቱን ብዛት 20 አድርሶታል‼️እነዚህ 20 የተሰፋ ብርሐን የምገባ የማዕከላት ስያሜና የሚገኙባቸው ክ/ከተሞች ዝርዝር ፦(1). የተ...
28/09/2023

♦️ዛሬ በአዲስ አበባ የተመረቀው ምገባ ማዕከል የምገባ ማዕከላቱን ብዛት 20 አድርሶታል‼️

እነዚህ 20 የተሰፋ ብርሐን የምገባ የማዕከላት ስያሜና የሚገኙባቸው ክ/ከተሞች ዝርዝር ፦

(1). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (አራዳ)

(2). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ቦሌ አየር መንገድ )

(3). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (አዲስ ከተማ)

(4). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ልደታ አዋሽ)

(5). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል(ቂርቆስ ሮሃ)

(6). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ንፋስ ስልክ ላፍቶ )

(7). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ልደታ)

(8). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ንፋስ ስልክ ቁ 2)

(9). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ቂርቆስ )

(10). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ቂርቆስ )

(11). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ቂርቆስ ኢትዮ ገልፍ )

(12). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (የካ)

(13). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል ኢኮስኮ

(14). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (የካ )

(15). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ለሚ ኩራ )

(16). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (አቃቂ )

(17). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (የካ)

(18). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ለሚ ኩራ )

(19). የተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል (ለሚ ኩራ )

(20) በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቀጨኔ መድሃኒያለም በሚባለው አካባቢ

ከስራ አጥነት ወደ  ባላቤትነት❓በላሚ ኩራ እንጀራ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩ እናቶች ተቀጣሪ ሳይሆኑ የእንጀራ ፍብሪካው ከሚያገኙ ትሪፍ እኩል የሚከፋፍሉ ናቸው።የእንጀራ ፋብሪካው ትሪፍ ማትረፍ ሲ...
22/09/2023

ከስራ አጥነት ወደ ባላቤትነት❓

በላሚ ኩራ እንጀራ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩ እናቶች ተቀጣሪ ሳይሆኑ የእንጀራ ፍብሪካው ከሚያገኙ ትሪፍ እኩል የሚከፋፍሉ ናቸው።

የእንጀራ ፋብሪካው ትሪፍ ማትረፍ ሲጀምር የሚገኘውን ትርፍ እኩል የሚከፋፍሉ ይሆናል ። አንድ አንድ የዜጎችን ጉልበት መበዝበዝ የለመዱ ሌቦች ለፋብሪካው ሰራተኞች ደሞዝ አልተከፈለም የሚል ወሬ የሚነዙት እውነታዊ ጠፍቷቸው ሳይሆን በኢትዮጵያ ምድር ያልተለመደ ስርዓት ስለመጣ ተደናግጦ ነው።

ብልፅግና ከፍታ ነው ፣ የኢንዱስትሪ ፣ የልማት ፣ የኢኮኖሚ እና የአስተሳሰብ ልህቀት እንዲመጣ የሚሰራ ጠንካራ ፓርቲ ነው። ፓርቲው ዜጎች ሰርቶ በማትረፍ በኢንዲስትሪ ሽግግር ውስጥ ጎልቶ እንዲወጡ እንጅ ጥቂት ግለሰቦች ሃብትን ተቆጣጥሮ በትንንሽ የቅጥር ደሞዝ የሚሰሩ ዜጎች ለማብዛት የሚሰራ ፓርቲ አይደለም ።

♦️የአዲስ አበባ ቀዳማይ ልጅነት የልማት ፕሮግራም‼️➤አዲስ አበባ ከተማን  የሁሉም ለሁሉም የምትመች የሰራና የመኖሪያ ከተማ የማድረግ  ራዕይ የሰነቀችው አዲስ አበባ አሰራሮቿን ቀይሳ ተግባራ...
19/09/2023

♦️የአዲስ አበባ ቀዳማይ ልጅነት የልማት ፕሮግራም‼️

➤አዲስ አበባ ከተማን የሁሉም ለሁሉም የምትመች የሰራና የመኖሪያ ከተማ የማድረግ ራዕይ የሰነቀችው አዲስ አበባ አሰራሮቿን ቀይሳ ተግባራዊ አድርጋለች ።

➤ግንባታቸው የተጠናቀቁ እና በግንባታ ላይ ያሉ ትላልቅ ፕሮጄክቶቿ ለቱሪዝም መዳረሻ ተመራጭ እና ምቹ ያደርጓታል ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ያሉ ፕሮጄክቶች የከተማዋን ውብት እና ገቢ የሚጨምሩና የነዋሪውን የህይወት የሚቀይሩ ናቸው።

➤በልደታ ክፍለ ከተማ ተገንብቶ ስራ የጀመረው የህፃናት ማቆያ ህፃናቱ ተገቢውን እንክብካቤና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ አድርጓቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የመንግሰት ሰራተኞች በነፃነት ስራቸውን እንዲሰሩ አድርጓቸዋል ። በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የተገነቡ የህፃናት ማቆያ ስፍራዎች ወላጆችን ከተጨማሪ ወጪ መታደግ የቻሉና ሌሎች ወጣቶች የሰራ ዕድል የፈጠሩ ተቋማት ሆነዋል ።

➤ከተማ አስተዳደሩ ወደ 2500 የሚሆኑ በዕውቀት እና ክህሎት የበቁ ተንከባካቢዎችን በመመደብ ከጽንስ ግዜ ጀምሮ ወላጆች ልጆቻቸውን በዕውቀት ተንከባክቦ እንዲያሳድጉ የቤት ለቤት የምክር አገልግሎት ጀምሯል ። ይህ አሰራር ህፃነት እንዳይቀነጭሩ ያስችላል ።

➤የህፃናት ማቆያው ደረጀውን የጠበቁ የህክምና ማዕከል ፣ የመጫወቻ ፣ የመመገቢያ ስፍሬዎችን የሞላና ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ እናደርጋለን ብሎ የሰነቁትን ራዕይ እውን እያደረጉ ካሉት ስራዎች አንዱ ነው።

ቃል በተግባር ያለንበት ይህ ግዙፍ የግብርና  የገበያ ማዕከል ተገንብቶ በመጠናቀቁ  የህዝባችን ዋነኛና አንገብጋቢ የሆነውን የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት የሚያቃልልና ህብረተሰቡን ቀጥታ ተ...
09/09/2023

ቃል በተግባር ያለንበት ይህ ግዙፍ የግብርና የገበያ ማዕከል ተገንብቶ በመጠናቀቁ የህዝባችን ዋነኛና አንገብጋቢ የሆነውን የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት የሚያቃልልና ህብረተሰቡን ቀጥታ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ነው።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ በማፍጠንና በመፈጠር መሪህ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እናደርጋለን የነዋሪዎቿን ህይወት ለመቀየር ሌት ተቀን እንሰራለን ።ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
09/09/2023

አዲስ አበባ በማፍጠንና በመፈጠር መሪህ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እናደርጋለን የነዋሪዎቿን ህይወት ለመቀየር ሌት ተቀን እንሰራለን ።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

05/08/2023

ከአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የተሰጠ መግለጫ
-----------
በአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰቡን እሴቶች፤ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ትውፊቶች እንዲሁም ስነ-ልቦና የሚጎዱ እና በማህበረሰባችን ዘንድ ያልተለመዱ መጤ ልምምዶች እየታዩ ይገኛል ያለው ቢሮው፣ በአንዳንድ ሆቴሎች የግብረ-ሰዶም እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ለቢሮው የደረሱ የጥቆማ መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።

ቢሮው ባወጣው መግለጫ፣ በከተማችን ያሉ ሆቴሎች እና ሬስቶራንቶች በአጠቃላይ የቱሪስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት የሀገራችንን ባህል፣ እሴት እና እምነት አክብረው እና የአገሪቱን የቱሪዝም ሥነ-ምግባር ደንብ ጠብቀው እንዲሰሩ ይገደዳሉም ብሏል።

ተቋሙ የማህበረሰባችንን እሴቶች እና ሃይማኖታዊ ትውፊቶች የሚሸረሽሩ ሥነ-ልቦናን እና ሞራልን የሚጎዱ አሉታዊ ተግባር ላይ ተሰማርቷል በሚል ከህብረተሰቡም ሆነ ከባለድርሻ አካላት በኩል የሚቀርብ ጥቆማ ካለ ተጨባጭነቱን በማረጋገጥ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት መሰረት ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የገለፀ ሲሆን፣ ማህበረሰቡ ከዚህ ፀያፍ ተግባር ጋር በተገናኘ ማንኛውንም መረጃ በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ጥቆማ እንዲያቀርብ ጠይቋል።

05/08/2023

የአዲስ አበባ ከተማ የ2016 በጀት ዓመት ዋና ዋና የርብርብ ማዕከላት፤
------------------
=> የህዝብቡን አብሮነትና ማህበራዊ መስተጋብር ለምጠናከር ከነጠላ ቡድናዊ እውነት የሚነሱ የፅንፈኝነት አመለካከትና ተግባሮች እንዲሁም አደገኛ ውጤት ለነዋሪው በማስገንዘብ እየታገልን የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፤

=> የከተማዋን ዘላቂ ሰላምና ደህንነት አጠናክሮ በማስቀጠል የወንድማማችነት እሴትን በማጠናከር የወል እውነትን የማፅናት ስራ በልዩ ትኩረት በመስራት እንዲሁም በከተማችን ያሉ ሁሉንም አቅሞች እና ዕድሎች አሟጦ መጠቀም፤

=> በተጀመረው አሰራር የተቋም ግንባታን ውጤታማነት የማሻሻል፣ የብልሹ አሰራርና የፀረ-ሌብነት ትግል ይበልጥ በማጠናከር የተጠያቂነት ስርዓቱን ማስፈንና የአመራርና ፈፃሚውን አቅም በልዩ ትኩረት መገንባት፣ የኑሮ ውድነትን ችግር ማቃለል፣ የትራንስፖርት፣ የውሃ፣ የመብራት፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ በመሬት ልማት አስተዳደር ስርዓት ላይ መሰረታዊ ለውጥ የማምጣት ስራ እና ገቢ የመሰብሰብ ስራችንን በይበልጥ በማጠናከር ልዩ ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት ይሆናሉ፤

=> የንግድ ስርዓቱን በማዘመን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሻሻል ለኢንቨስትመንት ምቹ አካባቢን በመፍጠር የሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በላቀ ደረጃ መፈፀም
=> የከተማ ግብርና የሌማት ቱርፋት ስራዎችን ማጠናከር እንዲሁም፣ ለከተማዋ አረንጓዴ አሻራ ፅዳትና ውበት ከምንግዜውም በላቀ ትኩረት ይሰራል፡፡

=> ለሁለንተናዊ የወረዳ አቅም ግንባታ በበጀት አመቱ ልዩ ትኩረት መስጠት፡፡
=> በሰላም ፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ የነበሩ መልካም ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል በተለይም የከተማዋ ነዋሪዎች አንገብጋቢ ጉዳይ የሆነውን የቤት ልማት ኘሮግራሞች በግል ዘርፉ፣ በሕብረት ስራ ማህበራት በመንግስት እና በግል የአጋርነት ኘሮግራም በስፋት ተግባራዊ ማድረግ።

=> ከተማዋን፣ የቱሪዝም፣ የኮንቬሽንና የኢግዚቢሽን ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩትን ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል፡፡

=> ሕብረብሔራዊ ወንድማማችነትንና አንድነትን እንዲሁም የወል እውነቶችን በማፅናት የከተማዋን ሰላም በማስጠበቅ የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመፍጠንና መፍጠር አሰራርን በመከተል የመረጠንን ሕዝብ በታማኝነትና በትጋት መመገልገል፡፡

"መፍጠርና መፍጠን መመሪያችን ነው!!"

የመልካም ተግባር ወሮታው ሰላም ነው ‼️በፍቅር ፣ በልማት ፣ በአንድነት ፣ በልማት ፣ በባህል ፣ በብሔር ፣ በሃይማኖት  የአካታችነት ሚዛን አስተሳስራ በቁጥር የሚያደግቱ የልማት ፕሮጀክቶችን...
05/08/2023

የመልካም ተግባር ወሮታው ሰላም ነው ‼️

በፍቅር ፣ በልማት ፣ በአንድነት ፣ በልማት ፣ በባህል ፣ በብሔር ፣ በሃይማኖት የአካታችነት ሚዛን አስተሳስራ በቁጥር የሚያደግቱ የልማት ፕሮጀክቶችን በመፈጸም በሰው ልብ ውስጥ በትጋት የነገሰች ንግስት‼️

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በአመታት ተሰርቶ የማይታወቁ ስራዎችን በወራት ዕድሜ በመጠናቀቅ አዲስ የልማት አቢዮት ያቀጣጠለች ጀግና ሴት‼️

ዜጎች ባልቶ ማደር የሚችሉበትን ከተማ የፈጠረች ፣ ለአቅመ ደካሞች ጉልበት መሆን የቻለች ፣ ተማሪዎች ስለ ምግብና ቁሳቁስ ሳይሆን ስለ ትምህርታቸው ብቻ ትኩራት እንዲያደርጉ ያስቻለች ፣ እናቶች ስራ ቦታ ሆኖ ልባቸው ለሁለት እንዲያካፍል የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራምን ያስጀመረች ንግስት ።

ለጤና ፣ ለትምህርት ፣ ለስነ ጥበብ ፣ ለመኖሪያ ቤቶች ፣ ለመንገዶች፣ ለዘላቂ ሰላምና ለከተማ ውብት ትኩራት በመስጠት በጥቂት አመታት ውስጥ በአመርቂ ውጤት የታጀበች አመራር ማናት ካላችሁ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ብቻ ነት‼️

05/08/2023

ህብረተሰቡ ከህግና ከማህበራዊ እሴቶች ያፈነገጡ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠየቀ፤
---------
አገራችን በህብረ-ብሄራዊነቷ የምትታወቅና የተለያዩ ባህሎችና ወጎች ያሏት አገር ናት። ሆኖም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከማህበረሰቡ ወግና ባህል ያፈነገጡ ድርጊቶች እያጋጠሙ መሆኑን የተመለከተ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

በከተማችን አንዳንድ ሆቴሎችና ሬስቶራንቶች የሀገሪቷን ህግ በሚጥስና ከማህበረሰቡ ወግ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ መኖሩን መረጃዎች እያመለከቱ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ መረጃ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቀዋል፡፡

ግብረ-ሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፅሙ የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ ፖሊስ በሚደርሰው መረጃ በመመስረት በህግ አግባብ እርምጃ እንደሚወስድ እያስታወቀ በዚህ ህገ-ወጥ ተግባር የሚጠረጠሩ ሆቴል ቤቶች እና ሬስቶራንቶች የሀገርቷን ህግ አክብረው የመስራት ግዴታ እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማኝኛውም የከተማችን ነዋሪ በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ ጥቆማ መስጠት የሚችል ሲሆን፤ በተጨማሪምበነፃ የስልክ መስመር፣ 991 እና 987 ፣ እንዲሁም
በቢሮ ስልኮች
=> 011-1- 11-01-11 እና
=> 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Paradigm Shift posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share



You may also like