Sheger Times Media

Sheger Times Media በየ15 ቀኑ ለአንባቢያን የሚደርሰው ሸገር ታይምስ መፅሄት የዩትዩብ ቻናልን ይጎብኙ
youtube.com/c/ShegerTimesMedia
(5)

 ...ሀብታም ሆኖ ደግ፣ ቱጃር ሆኖ ንጹህ ሃይማኖተኛ መሆን እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ሲሉ ይገልጹታል፡፡በጥበብና በዕውቀት ሀገር የመራ በእምነቱ የማይደራደር ፈጣሪውን የሚፈራም ንጉስ ነበር…...
01/06/2024

...

ሀብታም ሆኖ ደግ፣ ቱጃር ሆኖ ንጹህ ሃይማኖተኛ መሆን እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ሲሉ ይገልጹታል፡፡

በጥበብና በዕውቀት ሀገር የመራ በእምነቱ የማይደራደር ፈጣሪውን የሚፈራም ንጉስ ነበር…

ሙሉ ታሪኩን ይመልከቱት…

#ኢቢኤስ አነጋገሪና የተመረጡ ታሪኮች የሚቀርቡበት የመሿለኪያ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑYouTube #ለእናንተየ

እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ።**********እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በሞት ፍርድ እንዲቀጣ የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ አሳለፈ...
31/05/2024

እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ።
**********
እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በሞት ፍርድ እንዲቀጣ የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ አሳለፈ።

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ተከሳሽ ቶሎሳ ውይም ፍቅሩ አሸናፊ ላይ የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።

ተከሳሹ እናቱን በስለት (ቢላዋ) በአሰቃቂ ሁኔታ ወግቶ ህይወታቸውን እንዲያጡ አድርጓል።

ተከሳሹ ድርጊቱን የፈጸመው በቁማር የተበላዉን ገንዘብ እናቱ ያላቸውን ንብረት በመሸጥ እንዲተኩለት ለማድረግ ሲል እየደበደበ ያሰቃያቸው እንደነበር ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ አረጋግጧል።

በዚህ ብቻ ያላበቃው ተከሳሽ ሚያዚያ 21 ጠዋት በአሰቃቂ ሁኔታ የእናቱ ህይወት እንዲያልፍ አድርጓል በሚል ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

በዚህም ተከሳሹ የቀረበበትን ከባድ የወንጀል ድርጊት ማስተባበል ባለመቻሉ በሞት እንዲቀጣ ችሎቱ ውሳኔ አሳልፏል።

በተከሳሹ ላይ የተጣለው የሞት ፍርድ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ተፈጻሚ እንደሚሆን የዘገበው ኤፍቢሲ ነው።
____

https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA

https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

 👉ለማን አቤት ልበል?****“ሸገሮች  #አጋፔ የተሰኘ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋምን የተመለከተ መረጃ በዌብሳይት አግኝቼ  ባስቀመጡት ስልክ በመደወል የድርጅቱን ስራ አስኪያጅ [ስማቸው ...
31/05/2024


👉ለማን አቤት ልበል?
****
“ሸገሮች #አጋፔ የተሰኘ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋምን የተመለከተ መረጃ በዌብሳይት አግኝቼ ባስቀመጡት ስልክ በመደወል የድርጅቱን ስራ አስኪያጅ [ስማቸው ተጠቅሷል] አግኝቼ ብድር እንደምፈልግ እና የተወሰነ ገንዘብ እንዳለኝ ነገርኩት።

ከዛም ብድሩን በ25 ቀናት እንደሚያመቻችልኝ እና ያለኝን ብር በድርጅታቸው አካውንት እንዳስገባ ነገረኝ።

እኔም በሰዓቱ መስማት የምፈልገው ነገር ስለነበር እንደተባልኩት ብሩን አስገብቼ ደብተር አውጥቼ ብድሬን መጠባበቅ ጀመርኩ።

ይኸው ዛሬ 142ኛ ቀኔ ላይ ነኝ። እስከአሁን ድረስ አይደለም ብድር ሊሰጡኝ ያስቀመጥኩትን ገንዘብ እንኳን መልሱልኝ ብል የሚሰማኝ እና የሚያናግረኝ አጣሁ።

ለማን አቤት ልበል? እባካችሁን ቢጨንቀኝ ነው እናንተ ጋር መፃፌ።”
————
👉በዚህ ጥቆማ ላይ ስሙ የተገለጸውና ቅሬታ የቀረበበት ተቋም ምላሽ /ማስተባበያ ካለው ሸገር ታይምስ ሚዲያ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልፃል።
____

https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA

https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

 🙏ዮርዳኖስ ተሰማ ትባላለች ወንድሟ ነኝ አንድ እህቴ ናት እድሜዋ 14 አመት ነው ግንቦት 8 - 2016 ሐሙስ አመሻሽ 12:00 አካባቢ ከአ/አ ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ አባጃሌ ከተ...
31/05/2024

🙏

ዮርዳኖስ ተሰማ ትባላለች ወንድሟ ነኝ አንድ እህቴ ናት እድሜዋ 14 አመት ነው ግንቦት 8 - 2016 ሐሙስ አመሻሽ 12:00 አካባቢ ከአ/አ ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ አባጃሌ ከተሰኘ ሰፈር እደወጣች አልተመለሰችም።

በእለቱ ከላይ ጥቁር እጅጌ ጉርድቲሸርት ከፊለፊቱ ቡራቡሬ ስዕል ያለው እና ከታች ቡና ወይም ሽሮ ከለር መሳይ ስስ ቀሚስ ለብሳ ነበር።

ቤተሰቦቻችን ያሳደጉን በመከራና በእንግልት ነው እናታችን በጣም እየተጎዳች ነውአትቀመጥም በየቀኑ አገኛታለው ብላ ሀገር ለሐገር እየዞረች ነው።

እባከ‍ኣችሁ እህታችንን ያያ ወይም ያለችበትን የሚያውቅ ከታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች እንዲያሳውቀን በትህትና እንጠይቃለን !!!
0934490756
0925776169
0923150119
0970222977

ጥይት ከማይበሳው ቤት እስከ ምሽግ የገነቡት ዝነኞች ነገር…*******የቤቶቻቸውን መስኮቶች ሳይቀር ጥይት በማይበሳው ግብአት እንዲዋቀር ካደረጉ ጀምሮ አስገራሚና የዕብደት ተግባር ሊባል በሚች...
30/05/2024

ጥይት ከማይበሳው ቤት እስከ ምሽግ የገነቡት ዝነኞች ነገር…
*******
የቤቶቻቸውን መስኮቶች ሳይቀር ጥይት በማይበሳው ግብአት እንዲዋቀር ካደረጉ ጀምሮ አስገራሚና የዕብደት ተግባር ሊባል በሚችል ሁኔታ ዓለም በኒዩክለር ድንገት ከጠፋ በሚል ከቤታቸው ስር መደበቂያ ምሽግና ለረዥም ግዜ የሚበቃ ምግብ ያከማቹም አሉ፡፡

በዚህ ተደንቀን ሳናበቃ …

The Walking Dead በተሰኘው ፊልም ላይ የምናያቸው ‘የዞምቢዎች’ ጥቃት ሊመጣ ይችላል በሚል አስደናቂ ቤት የገነቡ አለምም እኛም የምናውቃቸው ታዋቂና ዝነኛ ሰዎች እነማን ናቸው? ያወጡበት ገንዘብስ?

ተከታዩ የመሿለኪያ ተረክ ምላሽ አለው፡፡

#ኢቢኤስ አነጋገሪና የተመረጡ ታሪኮች የሚቀርቡበት የመሿለኪያ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑYouTube #ለእናንተየ

29/05/2024

ገንዘብ ሳይኖረው ከኤቲኤም እየመዘዘ ወደ ሚሊየነርነት…*****ከለሊቱ 6፡45 ደቂቃ ላይ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ አካውንቱ ውስጥ ገንዘብ እንደሌለው እያወቀ በድፍረት ኤቲኤም ማሽኑን ብር እ...
28/05/2024

ገንዘብ ሳይኖረው ከኤቲኤም እየመዘዘ ወደ ሚሊየነርነት…
*****
ከለሊቱ 6፡45 ደቂቃ ላይ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ አካውንቱ ውስጥ ገንዘብ እንደሌለው እያወቀ በድፍረት ኤቲኤም ማሽኑን ብር እንዲሰጠው ጠየቀው፡፡

በሚደንቅ ሁኔታ ማሽኑ የጠየቀውን ገንዘብ ያለማመንታት አወጣለት፡፡

ግራ ተጋባ….. ሰክሬ ይሆን በሚል በድጋሚ ገንዘብ እንዲሰጠው ጠየቀው፡፡

የገንዘብ መክፈያ ማሽኑ ለሁለተኛው ጥያቄውም ታዛዥ በመሆን የሚፈልገውን ገንዘብ ዘረገፈለት፡፡

#ከዛማ ማን ይቻለው?

ሚስጥሩን ከደረሰበት በኋላ እኩለ ለሊት እየጠበቀ ከኤቲኤም ማሽኑ እንደ ልቡ ገንዘብ እየመዘዘ ከተራ አስተናጋጅነት ተነስቶ ወደ ሚሊየነርነት ተመነጠቀ…

ይህ እውነተኛ ታሪክ ከ #ጅማሬው እስከ #ፍፃሜው በተከታዩ ዘገባ ቀርቧል…

#ኢቢኤስ አነጋገሪና የተመረጡ ታሪኮች የሚቀርቡበት የመሿለኪያ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑYouTube #ለእናንተየ

ሀሰተኛ መረጃ ነው!!! "አምባሳደር ሀመር የትግራይ፣ የአማራ እና የኦሮሞ ፖለቲካን 'የሞት ትራያንግል’ በማለት ጠርተውታል" በሚል ርዕስ አልጀዚራ የሰራው ዘገባ የለም።ከ13,600 በላይ ተከ...
28/05/2024

ሀሰተኛ መረጃ ነው!!!

"አምባሳደር ሀመር የትግራይ፣ የአማራ እና የኦሮሞ ፖለቲካን 'የሞት ትራያንግል’ በማለት ጠርተውታል" በሚል ርዕስ አልጀዚራ የሰራው ዘገባ የለም።

ከ13,600 በላይ ተከታዮች ያሉት እና ‘Pulp Faction’ የሚል ስያሜ የሚጠቀም የትዊተር አካውንት ከአልጀዚራ ድረ-ገጽ የተወሰደ የሚመስል የስክሪን ቅጅ (screenshot) ማጋራቱን ተመልክተናል።

በስክሪን ቅጅው ላይም "Ambassader Hammer Calls Tigray, Amhara and Oromo Politics in Ethiopia, The Triangle of Death” ወይም ወደ አማርኛ ሲተረጎም "አምባሳደር ሀመር የትግራይ፣ የአማራ እና የኦሮሞ ፖለቲካን 'የሞት ትርያንግል’ በማለት ጠርተውታል’ የሚል አርዕስተ ዜና ይነበባል።

በዚሁ የስክሪን ቅጂ ላይም ጽሁፉ እ.አ.አ ግንቦት ዓ/ም መታተሙን የሚገልጽ ቀን አመላካች መስመር (dateline) ይታያል።

መረጃው እውነት ነው ብለው ያመኑ በርካታ ሰዎችም አስተያየቶቻቸውን ሲጽፉ አስተውለናል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ስክሪን ቅጂው ኤዲት ተደርጎ የተሰራ (doctored image) መሆኑን አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ቼክ የስክሪን ቅጅውን ትክክለኛን ለማረጋገጥ በአልጀዚራ ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ማህደር (Ethiopia Archive) በጥልቀት የፈተሸ ሲሆን አልጀዚራ ከላይ የተጠቀሰውን አርዕስተ ዜና በመጠቀም የሰራው ምንም አይነት ዘገባ አለመኖሩን ተመልክተናል።

በስክሪን ቅጅው ላይ ስማቸው የተጠቀሰው አምባሳደር ማይክ ሀመር የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ መሆናቸው ይታወቃል።

ኤዲት ተደርገው የሚሰራጩ ስክሪን ቅጅዎች ለሀሠተኛ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችንና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።


____

https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia

https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA

https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

“ሞታ ተገኘች”*******ከሳምንት በፊት " በአፈልጉን ማስታወቅያ "  ስትፈለግ የሰነበተች ተማሪ በውሃ ጉድጓድ ውስጥ ሞታ ተገኘች።ተማሪ ቤቴልሄም ገብረሚካኤል ነጋሽ ግንቦት 11 ቀን 2016...
27/05/2024

“ሞታ ተገኘች”
*******
ከሳምንት በፊት " በአፈልጉን ማስታወቅያ " ስትፈለግ የሰነበተች ተማሪ በውሃ ጉድጓድ ውስጥ ሞታ ተገኘች።

ተማሪ ቤቴልሄም ገብረሚካኤል ነጋሽ ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ ነው በመቐለ ከተማ ፤ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ዓዲ ሓውሲ ቀበሌ ከሚገኝ ቤትዋ እንደወጣች የቀረችው።

ዛሬ ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ/ም ግን አስክሬኗ ደብሪ ቀበሌ ጨለዓንቋ ተብሎ በሚታወቅ ኩሬ ተጥሎ መገኘቱ ተገልጿል።

የ17 ዓመትዋ ተማሪ ቤቴልሄም በመቐለ የቀላሚኖ ልዩ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ የነበረች ስትሆን ከአንድ ሳምንት የአፋልጉን ጥሪ በኋላ በውሃ ጉድጓድ አስክሬኗ ተጥሎ መገኘቱ ብዙዎችን አስደንግጧል፤ አሳስዝኗል።

የተማሪዋ አስክሬን በፓሊስ ትእዛዝ ወደ ዓይደር ሪፈራል ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል ተወስዶ ከተመረመረ በኋላ አመሻሽ በመቐለ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስትያን በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል።

በቀብር ስነሰርዓቱ ላይ ቤተሰቦች፣ የቀላሚኖ ትምህርት ቤት ኮሙዩኒቲ ፣ ወዳጆች እና አብሮ አደጎችን ጨምሮ በርካታ ህዝብ በመገኘት የተሰማው ጥልቅ ሃዘን በእንባ በመታጀብ ገልጿል።

በቀብር ስርዓቱ ላይ የተገኘው ህዝብ ፍትህ ጠይቋል።

የአሟሟትዋ ጉዳይ እጅግ በጣም ያሳዘናቸው የተለያዩ የህብረተሰብ አካላት ወንጀሉ ተጣርቶ ወንጀለኞች ወደ ህግ እንደዲቀርቡ ጠይቀዋል።(ምንጭ ቲክቫህ)
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምና ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ውባንቺ ቢሻው።ምስል: ሶሻል ሚዲያ
27/05/2024

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምና ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ውባንቺ ቢሻው።

ምስል: ሶሻል ሚዲያ

ከአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ(በእውቀቱ ስዩም)******** በቀደም እኛ ሰፈር እሚገኘው መሬት አስተዳደር ቢሮ ጎራ ብየ ጎራው አልሁ ፤ ከአስተዳዳሪው ጠረጴዛ ላይ ሜትር ፣ ችካልና በሶስ...
27/05/2024

ከአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
(በእውቀቱ ስዩም)
********
በቀደም እኛ ሰፈር እሚገኘው መሬት አስተዳደር ቢሮ ጎራ ብየ ጎራው አልሁ ፤

ከአስተዳዳሪው ጠረጴዛ ላይ ሜትር ፣ ችካልና በሶስት ጎድጓዳ ሳህኖች የተቀመጠ ናሙና አፈር ተደርድሮ ይታያል፤

“ምን እንርዳዎ ?” አለኝ አስተዳዳሪው፤

“ የሆነች ቀለል ያለች አምስት ሺ ካሬ መሬት ፈልጌ ነበር “

“የገበሬ መሬት ነው የፈለጉት?”

“ የወዛደርም ቢሆን አይደብረኝም፤”

“ አዝናለሁ ፤ ለጊዜው የሚሸጥ መሬት የለንም”

“እኔም የሚሸጥ ሳይሆን የሚሰጥ መሬት ነው የምፈልገው”

“ምን ስለሆንክ ነው ላንተ መሬት የሚሰጥህ ?”

ሰውየው ካንቱ ወደ አንተ የተሸጋገረበት ፍጥነት አስደነቀኝ ፤

እስካሁን ለናት አገሬ ካደረግሁት አስተዋጽኦ አንጻር ፤ መሬት ብቻ ሳይሆን ፥ የአየር ክልል ቢሰጠኝ አይበዛብኝም!

ሰውየው ዘበኞችን ለመጥራት ስልኩን ሲያነሳ፥ ወደ መስኮት እየጠቆምኩ፥

“ እዛ ማዳ ታጥሮ የበሰበሰ መሬት ምን ይሰራል ?”

“የወጣቶች የስራ ፈጠራ ማእከል ልንገነባበት ነው” አለኝ ፤

“ ከገነባችሁ በሁዋላስ?”

“ አልባሌ ቦታ የሚውሉ ወጣቶች ወደ ማእከሉ እንዲገቡ ይደረጋል “

“እሺ አልባሌውን ቦታ ለኔ ስጡኝ “

#2

በቀደም እኛ ሰፈር አስፋልት ዳር ያለ ስጋ ቤት ባለቤት ጫማ ያስጠርጋል፤ እኔ ወረፋ እየጠብቅሁ ነው፤

“ ቅድምኮ የግብረሀይሉ አባላት ሱቄን በሜትር ለከትውት ሄዱ” አለ ስጋ ሻጩ ፤

“ አይይ ! ሊያፐርሱት ነው ማለት ነው” አለ ሊስትሮው ፤

“ ሊያፈርሱት እንደሆነ በምን አወቅህ ?”

“ ታድያ በሜትር የለኩት ልብስ ሊያሰፑለት ነው?”
____
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።********በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን አቃቤ ህግ በመሰረተው ክስ ላይ ጠበቆቻቸው ያቀረቡት የአ...
27/05/2024

በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
********
በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን አቃቤ ህግ በመሰረተው ክስ ላይ ጠበቆቻቸው ያቀረቡት የአቃቤ ህግ የክስ መቃወሚያ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ፍርድ ቤት ዛሬ ብይን ተሰጥቷል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሶስተኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ባስቻለው ችሎት የተከሳሾቹ የእነ ቀሲስ በላይ መኮንን ጠበቆች ከዚህ በፊት ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄን ውድቅ አድርጎታል።

ችሎቱ በሰጠው ብይን መሰረት ተጠርጣሪዎቹ የተከሰሱበት አዋጅ ከ10 ዓመት በላይ የሚያሳስር ከባድ ፍርድ የሚስከትል በመሆኑ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው ይከታተላሉ ብሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ እነ ቀሲስ በላይ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የመውረዳቸውን ትዕዛዝ ለማስተላለፍ ግን አንድ የመጨረሻ ያለውን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ያለፈው ሚዚያ ወር መጀመሪያ የአፍሪቃ ኅብረት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ፤ በአካል በመቅረብ “ከኅብረቱ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ”በተባሉ ሀሰተኛ ሰነዶች በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ከህብረቱ የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ ሒሳብ ለማዘዋወር ሲሞክሩ ተገኝተዋል በሚል በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስታወሰው የዶቸቬለ ዘገባ ነው።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

በግድያ ወንጀል ተፈርዶባቸው ከታሰሩበት ማረሚያ ቤት ያመለጡ በቁጥጥር ስር ዋሉ።*********በፍርድ ቤት ዉሳኔ ተሰጥቶባቸዉ ከቦንጋ ማረሚያ ቤት ያመለጡ ፍርደኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖ...
27/05/2024

በግድያ ወንጀል ተፈርዶባቸው ከታሰሩበት ማረሚያ ቤት ያመለጡ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
*********
በፍርድ ቤት ዉሳኔ ተሰጥቶባቸዉ ከቦንጋ ማረሚያ ቤት ያመለጡ ፍርደኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ገለፀ።

የጨና ወረዳ ፖሊስን ዋቢ ያደረገው ዘገባ እንደጠቆመው በግድያ ወንጀል በ2013 ዓ.ም የ10 ዓመት ፍርደኛ ሆኖ ወደ ቦንጋ ማረሚያ ቤት የገባው ዳዊት መለሰ መጫሎ እና በተመሳሳይ ወንጀል በ2012 ዓ.ም ጀምሮ የ17 ዓመት እሥራት ተፈርዶበት ወደዚሁ ማረሚያ ቤት የገባው ወጣት መልካሙ መሸሻ መሮ በታህሳስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከቦንጋ ማረሚያ ተቋም አመልጠው መጥፋታቸውንና ማረሚያ ቤቱ የፈልጉልኝ የትብብር ደብዳቤ መፃፉን ገልፆአል።

በዚህ መሠረት ህብተሰቡ በሰጠው ጥቆማና በወረዳው ፖሊስ ክትትል ሁለቱ ግለሰቦች በወረዳው ባላ ሻሻ ቀበሌ ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከጨና ወረዳ መንግስት ኮሚንኬሽንና ከክልሉ ፖሊስ ዘገባ ለመመልከት ችሏል።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

በስካር መንፈስ ግድያ የፈፀሙ የ12 ዓመት ፅኑ እስራት ተበየነባቸው።*******ተከሳሽ መከተ ኢያሱና ተከሳሽ ሳምሶን ፈንሳ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንባቸው የቻለው በሸካ ዞን በቴፒ ከተማ አንድነ...
27/05/2024

በስካር መንፈስ ግድያ የፈፀሙ የ12 ዓመት ፅኑ እስራት ተበየነባቸው።
*******
ተከሳሽ መከተ ኢያሱና ተከሳሽ ሳምሶን ፈንሳ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንባቸው የቻለው በሸካ ዞን በቴፒ ከተማ አንድነት ቀበሌ ልዩ ስሙ ሚዛን ቴፒ ካምፖስ አከባቢ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ የግድያ ወንጀል በመፈፀማቸውና ጥፋተኝነታቸው በማስረጃ በመረጋገጡ ነው።

የሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ መርማሪ ረዳት ኢንስፔክተር ወንድማገኝ አለማየሁ እንደገለፁት ሁለቱ ተከሳሾች እና የግል ተበዳይ በቴፒ ከተማ አንድነት ቀበሌ ልዩ ስሙ ሚዛን ቴፒ ካምፖስ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ጥር 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በመጠጥ ግሮሰሪ ውስጥ በስካር መንፈስ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ወደ ፀብ ተሸጋግሮ ሁለቱ የግል ተበዳይን ራሱን እንዳይከላከል በማድረግ በስለት ወግተው ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ስለ ወንጀል ድርጊቱ ሲገልፁም ሁለተኛ ተከሳሽ የግል ተበዳይን መሬት ከጣለው በኃላ እራሱን እንዳይከላከል እጁን ሲይዘው አንደኛ ተከሳሽ በእጁ ይዞት የነበረውን ጩቤ በወደቀበት እና እራሱን መከላከል በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ የነበረውን ተበዳይ ደረቱን አንድ ጊዜ በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

ፖሊስ ወንጀሉን በምርመራ በማረጋገጥ የምርመራ መዝገቡን በሰው እና በህክምና ምርመራ ውጤት በማደራጀት መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ መላኩን ተከትሎ
የዞኑ ዐቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ ክስ መስርቷል።

የአቃቤ ህግን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሾቹ በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን የሰው ምስክሮች ማስተባበል ባለመቻላቸው ሁለቱንም ተከሳሾች ጥፋተኞች ናቸው ሲል እያንዳንዳቸው በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ዘገባ ለመልከት ችሏል።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።*********ኬንያን ከኢትዮጵያ በምታዋስነው የማርሳቢት ግዛት በወርቅ ማምረቻ ቦታ ላይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት እስካሁን የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የኬንያ ...
27/05/2024

የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።
*********
ኬንያን ከኢትዮጵያ በምታዋስነው የማርሳቢት ግዛት በወርቅ ማምረቻ ቦታ ላይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት እስካሁን የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል።

የማርሳቢት ግዛት ፖሊስ አዛዥ እንዳስታወቁት ህይወታቸው ያለፈው ዜጎች አስክሬን የተገኘው ከቅዳሜ እለት ጀምሮ በተደረገ ፍለጋ ነው።

በአደጋው ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው በፍለጋ የተገኘው የ5 ሰዎች ብቻ ሲሆን በመሬት መንሸራተቱ የተቀበሩ ሌሎች 3 ሰዎችን እስካሁን ማግኘት እንዳልተቻለ አዛዡ ተናግረዋል።

ለአደጋው እንደ መንስኤ የተገለፀው በአከባቢው ለሳምንታት የዘለቀው ከባድ ዝናብ መሆኑም ተገልፆአል።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

የዓለማችን ምርጥ 10 ዩንቨርሲቲዎች!***********👉🏽ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ፣ ጎንደር እና መቀሌ ዩንቨርሲቲዎች ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።*********ዓለም...
27/05/2024

የዓለማችን ምርጥ 10 ዩንቨርሲቲዎች!
***********
👉🏽ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ፣ ጎንደር እና መቀሌ ዩንቨርሲቲዎች ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
*********
ዓለም አቀፉ የዩንቨርሲቲዎች ደረጃ መዳቢ ማዕከል ባወጣው ሪፖርት ምርጥ 2 ሺህ ዩንቨርሲቲዎችን ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ሀርቫርድ ዩንቨርሲቲ ምርጥ 1ኛ ዩንቨርሲቲ ሲባል ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ስታንፎርድ ዩንቨርሲቲ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዩንቨርሲቲዎች ተብለዋል፡፡

ከአፍሪካ ከአንድ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ የደቡብ አፍሪካ ዩንቨርሲቲዎች ሲቆጣጠሩ ኬፕታወን ዩንቨርሲቲ፣ ዊትዋተርስራንድ ዩንቨርሲቲ እና ስቴለንስቦስች ዩንቨርሲቲ ከአንደኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ስድስት ዩንቨርሲቲዎች ከዓለማችን ምርጥ 2 ሺህ ዩንቨርሲቲዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ሲሆን አዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ባህርዳር እና ሐሮማያ ዩንቨርሲቲዎች ተካተዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ከአፍሪካ በ841ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ጎንደር ዩንቨርሲቲ በ1701ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ መቀሌ ዩንቨርሲቲ ደግሞ በ1748ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ግብጽ 20 ዩንቨርሲቲዎቿ በዓለማችን ምርጥ 2 ሺህ ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ ሲካተቱ ናይጀሪያ 5፣ ኬንያ እና ኡጋንዳ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ዩንቨርሲቲዎችን ያስመረጡ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ናቸው፡፡

ማዕከሉ የዩንቨርሲቲዎቹን ደረጃ ያወጣው ዩንቨርሲቲዎች በሚያካሂዷቸው ጥናት እና ምርምሮች፣ ትምህርት አሰጣጥ ጥራት፣ የፋኩልቲ አወቃቀሮች እና የሰው ሀይል ጥራት ዋነኛ መስፈርቶች መሆኑን የዜና ምንጩ አል አይን ዘግቧል።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

“ለእናቴ” አሸናፊዎች ነገ በድምቀት ይሸለማሉ።******በእናት ባንክ አማካኝነት የተዘጋጀው " ለእናቴ" የተሰኘው የጽሁፍ ውድድር የመዝጊያና የአሸናፊዎች ሽልማት  ፕሮግራም  ነገ ግንቦት 19...
26/05/2024

“ለእናቴ” አሸናፊዎች ነገ በድምቀት ይሸለማሉ።
******
በእናት ባንክ አማካኝነት የተዘጋጀው " ለእናቴ" የተሰኘው የጽሁፍ ውድድር የመዝጊያና የአሸናፊዎች ሽልማት ፕሮግራም ነገ ግንቦት 19/2016 ዓ.ም ከ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በሒልተን ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ይካሄዳል።

በዕለቱ የተለያዩ የሥነጽሑፍና የኪነ ጥበብ ስራዎች የሚቀርብ ሲሆን ስራዎቻቸውን ከሚያቀርቡት ውስጥ ደራሲ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር ፣ አርቲስት ዘሪቱ ከበደ፣ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፣ አርቲስት ትዕግስት ዓለሙ፣ ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ እና ኮሜዲያን ደረጄ ሃይሌ ይገኙበታል።

የተጣመሩበትን 25ኛ አመታቸውን በቅርቡ ያከበሩት የቫዮሊን ተጫዋቾች የመድረኩ ድምቀት ሆነው እንደሚያመሹም አዘጋጆቹ ለሸገር ታይምስ ሚዲያ በላኩት ጥቆማ ገልፀዋል።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

የበርበራ ኮሪደር ተገማች ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በትብብር መስራት ያስፈልጋል - ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ*******************************የበርበራ ኮሪደር ተገማች ኢኮኖ...
26/05/2024

የበርበራ ኮሪደር ተገማች ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በትብብር መስራት ያስፈልጋል - ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ
*******************************
የበርበራ ኮሪደር ተገማች ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊ እና የጸጥታ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ ገለፁ።

በበርበራ ኮሪደር በሚኖር የሰዎች ፍልሰት ሳቢያ የሚፈጠር የጋራ ተጠቃሚነት እና ፈተናዎች ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት ውይይት በጅግጅጋ ተካሂዷል።

ውይይቱ ከበርበራ ኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ በማረጋገጥ አንድ የኢኮኖሚ ማኀበረሰብ ለመፍጠር እንደሚያግዝ የተጠቆመ ሲሆን
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ “የበርበራ ኮሪደር የስራ ዕድል እና የሰለጠነ የሰው ሃይል እንቅስቃሴን በማሳለጥ ለንግድ እና ኢንቨስትመንት መግቢያ በር በመሆን እያገለገለ ይገኛል” ብለዋል።

ኮሪደሩ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በማጎልበት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግ ቢሆንም የህገ ወጥ የሰዎች ፍልሰት፣ የንግድ ወንጀል፣ የፀጥታ እና ሌሎች ማህበራዊ ችግሮች እንዲከሰቱ እድል የሚፈጠር መሆኑን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ እነዚህንና ሌሎች ተገማች ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊና የጸጥታ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ተቀናጅቶ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው በበርበራ ኮሪደር ላይ የሚከናወኑ የልማት ተግባራት የአፍሪካን የንግድ፣ የአገልግሎትና የካፒታል ዝውውርን ለማሳለጥ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አመላክተዋል፡፡

በቀጠናው የሚከናወን የንግድ እና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በማሳደግ የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በተካሄደው በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ ከሶማሌላንድ የመጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ምሁራን እና የከተማ ከንቲባዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

 …**********"ፍፁም ነው እምነቴየትግሉ ነው ህይወቴልጓዝ በድል ጎዳናበተሰዉት ጓዶች ፋና…." #ሙሉ ታሪኩን ይመልከቱት….👉🏽www.youtube.com/
26/05/2024


**********
"ፍፁም ነው እምነቴ
የትግሉ ነው ህይወቴ
ልጓዝ በድል ጎዳና
በተሰዉት ጓዶች ፋና…."

#ሙሉ ታሪኩን ይመልከቱት….
👉🏽www.youtube.com/

#ኢቢኤስ አነጋገሪና የተመረጡ ታሪኮች የሚቀርቡበት የመሿለኪያ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑYouTube #ለእናንተየ

 ❗️❗️*****በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች ወደ ውጭ ሀገር ለትምህርት፣ ለስራ እድል አለ የሚሉ ማስታወቂያዎች እየተለቀቁ እንደሆነ የገፃችን ተከታታዮች ጠቁመውናል።ሸገር ታይምስ ሚዲያ ባደረገ...
26/05/2024

❗️❗️
*****
በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች ወደ ውጭ ሀገር ለትምህርት፣ ለስራ እድል አለ የሚሉ ማስታወቂያዎች እየተለቀቁ እንደሆነ የገፃችን ተከታታዮች ጠቁመውናል።

ሸገር ታይምስ ሚዲያ ባደረገው ቀላል የሆነ ማጣራት ከስር የሚታየውና የስራ ቅጥር በካናዳ በሚል የተሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ እና #ማህተሙም በፎቶ ሾፕ የተቀናበረ ለመሆኑ ማረጋገጥ ችሏል።

በዚህ አጋጣሚ ዜጎች በተመሳሳይ መንገድ #ከመጭበርበር እንዲጠነቀቁ እየጠቆምን ይህን መረጃ ሼር በማድረግ ላልሰሙት በማሰማት ይተባበሩ።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

ከዓለም አቀፍ ግዙፍና አስተማማኝ ባንኮች ጀርባ…******በዓለማችን እጅግ አስተማማኝ የሆኑት ባንኮች እነማን ናቸው? በባንኩ ኢንደስትሪ በዓለማችን ስመ ገናና የሆኑትስ የትኞቹ ናቸው? የእነዚ...
25/05/2024

ከዓለም አቀፍ ግዙፍና አስተማማኝ ባንኮች ጀርባ…
******
በዓለማችን እጅግ አስተማማኝ የሆኑት ባንኮች እነማን ናቸው? በባንኩ ኢንደስትሪ በዓለማችን ስመ ገናና የሆኑትስ የትኞቹ ናቸው?

የእነዚህ ባንኮች የደህንነት አቅምና አስተማማኝነታቸውስ በምን እና እንዴት፣ በማንስ ይገመገማል…

ተከታዩ ጥንቅር ምላሽ አለው…
👉🏽www.youtube.com/

#ኢቢኤስ አነጋገሪና የተመረጡ ታሪኮች የሚቀርቡበት የመሿለኪያ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑYouTube #ለእናንተየ

የአሜሪካ ኤምባሲ ለ2 ቀናት ዝግ ይሆናል።👉🏽 “ግንቦት 19 ለ'ሚሞሪያል ዴይ' ፣ ግንቦት 20 ደርግ የወደቀበት ቀን ነው ”ኤምባሲው********በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤሜሪካ ኤምባሲ ሰኞ ...
24/05/2024

የአሜሪካ ኤምባሲ ለ2 ቀናት ዝግ ይሆናል።

👉🏽 “ግንቦት 19 ለ'ሚሞሪያል ዴይ' ፣ ግንቦት 20 ደርግ የወደቀበት ቀን ነው ”ኤምባሲው
********
በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤሜሪካ ኤምባሲ ሰኞ ግንቦት 19/2016 እና ማክሰኞ ግንቦት 20 ዝግ እንደሚሆን አሳውቋል።

ኤምባሲው ግንቦት 19 ' ሚሞሪያል ዴይ'ን እንዲሁም ግንቦት 20 #የደርግ መንግሥት የወደቀበትን ቀንን ምክንያት በማድረግ ሙሉ ቀን ተዘግቶ እንደሚውል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መረጃ ይፋ አድርጓል።
_
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ የሚቀርቡ የካሳ ጥያቄዎችን በሙሉ የመክፈል አቅም እንደሌለው የገንዘብ ሚኒስትር ገለፀ።********ሚኒስትሩ የፌደራል ፕሮጀክቶች በሚተገበሩበት ወቅት  የሚመጣው የካ...
24/05/2024

በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ የሚቀርቡ የካሳ ጥያቄዎችን በሙሉ የመክፈል አቅም እንደሌለው የገንዘብ ሚኒስትር ገለፀ።
********
ሚኒስትሩ የፌደራል ፕሮጀክቶች በሚተገበሩበት ወቅት የሚመጣው የካሳ ጥያቄ እጅግ የተጋነነ እና የመንግስትን አቅም እየተፈታተነ መሆኑን ጠቁሟል።

የገንዘብ ሚንስቴር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ለቋሚ ኮሚቴዉ የሚኒስትሩን የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም በገለፁበት ወቅት እንደተናገሩት መንግስት በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች እየቀረቡ ያሉ የካሳ ጥያቄዎች ዋነኛ ችግር እየሆኑ መጥተዋል ብለዋል።

የሚጠየቀው የካሳ ጥያቄ ከመንግስት አቅም ጋር የሚጣጣም አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ በመሆኑም መንግስት የተጠየቀውን የካሳ ጥያቄን በሙሉ የመክፍል አቅም የለውም በማለት ማስረዳታቸውን ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከካፒታል ዘገባ ለመመልከት ችሏል።
_
📌የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ******የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተቋማቱን የአሰራር ስርዓት በሚያስተሳስር የስልጠና፣ የጥና...
24/05/2024

ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
******
የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተቋማቱን የአሰራር ስርዓት በሚያስተሳስር የስልጠና፣ የጥናትና የምርምር ዘርፎች ላይ አብረዉ በጋራ በመስራት ተጨባጭ ለዉጥ የሚያመጡበትን የዉል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብርጋዲየር ጀኔራል ከበደ ረጋሳ ወታደራዊ ቴክኖሎጅ የሃገርን የስልጣኔ ገፅታ በመቀየር ረገድ ያለዉን ዘርፈ ብዙ ሚና በመገንዘብ ጊዜዉ ሳይቀድመን የትብብር አድማሳችን አስፍተን የተቋማቱን አቅም እና የሃገርን ኢኮኖሚ በሚያግዙ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በጋራ በመስራት የሰራዊታችንን ዘመናዊ የቴክኖሎጅ ተጠቃሚነት በፍጥነት እያረጋገጥን መቀጠል ይገባል ብለዋል።


ጀነራል መኮንኑ ዩኒቨርስቲው የብዙ ቴክኖሎጅ ዉጤቶች ግኝት የመከላከያ የልህቀት ማዓከል መሆኑን ጠቁመው የሃገርን ክብር የሚመጥን እና የሰራዊታችንን ዉጤታማ የልህቀት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚችሉ ተደራሽ የምርምር ስራዎችን በጋራ ሁነን ተቀናጅተን በመስራት ለተጠቃሚዉ ማድረስ ይገባል ብለዋል ፡፡

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ገረመዉ ሁለቃ በበኩላቸው የሃገርን የገቢ ምንጭ ማሳደግ በሚችል መልኩ የተቋማቱን ትስስር በአይሲቲ ቴክኖሎጅ ፣ በኔትዎርኪግ ሲስተምና በኦላይን ላይብረሪ አጫጭርና ረዣዥም ስልጠናዎችን በመስጠት በሃብት አስተዳደር ላይና በማማከር ሂደት ላይም ዘርፈ ብዙ ለዉጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልፀዋል።

ስምምነቱ ጠንካራ ልምድ መወራረስ በሚያስችል መልኩ አመራሩን ፣ አስተማሪዎችን እና የቢሮ ሰራተኛዉን በማሰልጠን ጭምር የተቋማቱን ፈጣንና ዘመናዊ የአሰራር አገልግሎት ምቹና ተደራሽ ማድረግ እንደ ሚቻልም ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል ፡፡

ሁለቱ ዩኒቨርስቲዎች የረዥም ጊዜ ልምዳቸዉን በመጋራት ዘላቂ የአገልግሎት አሰራር ስርዓታቸዉን ሊያዘመኑ በሚችሉ የሃብት አጠቃቀም ላይ እና የሰዉ ሃይል አስተዳደር ላይም ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተዉ እንደሚሰሩ በዉል ስምምነት ሰነዱ ላይ መጠቀሱን ከዩኒቨርስቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የቻርተር በረራ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የግል አየር መንገዶች መደበኛ የአገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት እንዲሰጡ ፈቀደ፡፡ባለስልጣኑ በፃፈው ደብ...
23/05/2024

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የቻርተር በረራ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የግል አየር መንገዶች መደበኛ የአገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት እንዲሰጡ ፈቀደ፡፡

ባለስልጣኑ በፃፈው ደብዳቤ የግል አየርመንገዶቹ የስራ እቅዳቸውን እንዲያቀርቡ ጠይቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት 12 የሚሆኑ የግል አየርመንገዶ የቻርተር በረራ እና ስልጠና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

via:-Kaleyesus Bekele Tadele

 #ኢትዮጵያውያንን አክባሪው ንጉስ!👉“በአክብሮት ያዟቸው እነሱም የንጉስ ዘር ናቸው” ************ሳቅና ፈገግታቸው ማንም እንዳያቸው የሚስብና መልካም ሰው ነበሩ፡፡በተለይም እሳቸው በህ...
23/05/2024

#ኢትዮጵያውያንን አክባሪው ንጉስ!

👉“በአክብሮት ያዟቸው እነሱም የንጉስ ዘር ናቸው”
************
ሳቅና ፈገግታቸው ማንም እንዳያቸው የሚስብና መልካም ሰው ነበሩ፡፡

በተለይም እሳቸው በህይወት እያሉ በሀገራቸው ምድር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በክብር እንዲያዙና ተገቢው አክብሮት እንዲሰጣቸው ማድረጋቸው ይነገርላቸዋል፡፡

እኚህ በበርሃ ላይ ውብ ሀገር የፈጠሩ ተወዳጅ እና ተከባሪ ንጉስ ዛሬ በህይወት ባይኖሩም በሀገራቸው ያሉ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ “በአክብሮት ያዟቸው እነሱም የንጉስ ዘር ናቸው” ማለታቸው በዛች ምድር በኖሩ እና አሁንም ድረስ ባሉ ኢትዮጵያውያን በቅብብሎሽ እየተሰማ ዛሬም ድረስ ለኢትዮጵያውያን ያላቸው ክብርና መልካምነታቸው ሲነገር ይደመጣል፡፡

👉ሙሉ ታሪካቸውን በተከታዩ ቪዲዮ ይመልከቱት
www.youtube.com/

#ኢቢኤስ አነጋገሪና የተመረጡ ታሪኮች የሚቀርቡበት የመሿለኪያ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑYouTube #ለእናንተየ

ከዛሬ ምሽት 11 ሰዓት ጀምሮ በመዲናዋ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ******ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ ከፖሊስ ስራ ጋር በተያያዘ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮ...
23/05/2024

ከዛሬ ምሽት 11 ሰዓት ጀምሮ በመዲናዋ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
******
ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ ከፖሊስ ስራ ጋር በተያያዘ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮግራም እንደሚካሄድ የገለፀው የከተማዋ ፖሊስ ተከታዮቹ መንገዶች ፡-

- ከልደታ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

- ከአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

-ከጠማማ ፎቅ በንግድ ምክር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

-ከገነት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

-ከሰንጋ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

- ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

- ከቡናና ሻይ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
_____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

“ለእናቴ”****** ከ1500 በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ በሆኑበትና በእናት ባንክ በተዘጋጀው “ለእናቴ” በሚል ስለ እናታቸው የሚያጋሩትን ፍቅርና ስሜት እንዲገልጹ በተደረገበት የስነፅሁፍ ውድ...
23/05/2024

“ለእናቴ”

******
ከ1500 በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ በሆኑበትና በእናት ባንክ በተዘጋጀው “ለእናቴ” በሚል ስለ እናታቸው የሚያጋሩትን ፍቅርና ስሜት እንዲገልጹ በተደረገበት የስነፅሁፍ ውድድር ከ1 አስከ 5 የወጡ ተወዳዳሪዎች የቀይ ምንጣፍ የሽልማት መድረክ የፊታችን ግንቦት 19 ይካሄዳል፡፡

የውድድሩ መዝጊያ ታዋቂ የሥነ ጽሑፍና የኪነ ጥበብ ሰዎች፣ የባንኩየቦርድ አባላት፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች፣ የውድድሩ አሸናፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚታደሙበት ሲሆን በመድረኩ የውድድሩ አሸናፊዎች ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት የስነ ፅሁፍ እና የኪነ ጥበብ ባለ ሞያዎች ስለ እናትነት የሚቀኙበት ልዩ የኪነጥበብ ፕሮግራምም እንደተሰናዳም የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ለሸገር ታይምስ ሚዲያ ከላኩት ጥቆማ ለመረዳት ተችሏል፡፡
_____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

የ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት።********* የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ ላይ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመ...
23/05/2024

የ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት።
*********
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ ላይ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ አስታውቋል።

ረቡዕ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከጧቱ 2፡45 ሰዓት አከባቢ ተከሳሽ አቶ ዩሀንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰብ የሴት ጓደኛው የሆነችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የግድያ ወንጀል በመፈፀሙ ተከሳሽ በፈፀመው ሰው በመግደል ወንጀል ተከሷል።

መርማሪ ፖሊስና ዐቃቢ ህግ በጋራ ተጠርጣሪው ላይ ክስ መስርተው ምርመራ በማጣራት የወንጀል ድርጊቱን የሚያስረዱ የሰው ማስረጃና የህክምና ማስረጃ በማስደገፍ ለሚመለከተው ፍ/ቤት ልከዋል።

የክስ መዝገቡ የደረሰው የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ በቀን 15/9/2016 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎአል።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ስብስባቸውን አሳውቀዋል።******የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላሉበት ሁለት የአለም ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ጨዋታዎች የሚጠቀመውን የቡድን ስብስብ አሳ...
22/05/2024

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ስብስባቸውን አሳውቀዋል።
******
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላሉበት ሁለት የአለም ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ጨዋታዎች የሚጠቀመውን የቡድን ስብስብ አሳውቋል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ለሀያ ስድስት ተጫዋቾች የመጀመርያ ጥሪ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ቡድኑ ግንቦት 29/2016 ዓ.ም ከጊኒ ቢሳው እንዲሁም ሰኔ 2/2016 ዓ.ም ከጅቡቲ ጋር ከሜዳው ውጪ ጨዋታውን ያደርጋል።
____
የሸገር ታይምስ ሚዲያ ወቅታዊ መረጃና ዘገባዎችን ለማግኘት:-
youTube
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
Telegram
https://t.me/SHEGRTIMESMEDIA
Facebook
https://www.facebook.com/shegerTimesMedia

Address

Around 22, Street Gebriele Hospital
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sheger Times Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sheger Times Media:

Videos

Share

Our Story

ሸገር ታይምስ ሚዲያ በማትሪክስ ኢንተርቴይመንት እና የፕሬስ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር እየታተመ በየ 15 ቀኑ ለአንባቢያን የሚደርስ በማህበራዊ፤ ኪነጥበባዊ፤ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን ሸገር ታይምስ የተሰኘ መፅሄት እና #ShegerTimesMedia ዩቲዩብ ቻናልን አጣምሮ የያዘ ነው፡፡ ሸገር ታይምስ ሚዲያ ለጋዜጠኝነት ሙያዊ ስነምግባር ቅድሚያ በሚሰጡ በሳል እና ሃላፊነት በሚሰማቸው ጋዜጠኞች የሚዘጋጅ ነፃ ሚዲያ ነው፡፡ ለዛም ነው ሸገር ታይምስ…በኃላፊነት!!!! የምንለው፡፡ በወዳጅነት አብረን እንሰንብት!!!!!!!!