አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine

አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine, Magazine, Addis Ababa.

ጦርነቱ በይፋ ተጀመረ  እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ፈጸመች
19/04/2024

ጦርነቱ በይፋ ተጀመረ እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ፈጸመች

ጦርነቱ በይፋ ተጀመረ
🔥🔥🔥 🔥🔥🔥

ሆራይዘን ሚዲያ
ሚያዚያ 11/2016

ጦርነቱ በይፋ ተጀመረ እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ፈጸመች

እስራኤል ባለፈው ቅዳሜ ኢራን ለፈጸመችባት የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት ዛሬ ማለዳ ላይ የአጸፋ ጥቃት መፈጸሟን የኢራን መገናኛ ብዙኃን እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ዛሬ አርብ ጎህ ከመቅደዱ በፊት በማዕከላዊቷ የኢራን ከተማ ኢስፋሃን ፍንዳታዎች መሰማታቸውን የኢራን የመገናኛ ብዙኃን የዘገቡ ሲሆን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናትም ይህን አረጋግጠዋል።

እስራኤል በኢራን ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ቴሌቪዥን አረጋግጠዋል።

የኢራን መገናኛ ብዙኃን ደግሞ ሦስት የእስራኤል ድሮኖች በኢራን የአየር መከላከያ ሥርዓት መውደማቸውን ዘግበዋል።

ጥቃቱ ተፈጽሞባታል የተባለችው የኢራን ከተማ ኢስፋሃን የአገሪቱ አየር ኃይል መቀመጫ ስትሆን፣ በርካታ ወታደራዊም ተቋማት በውስጧ ይገኛሉ።

ጥቃቱ ከተፈጸመ ጥቂት ሰዓታት ብቻ ያለፉት በመሆናቸው አስካሁን ዒላማ ስለሆኑ ቦታዎች እና ስለደረሰ ጉዳት የወጣ መረጃ የለም። የኢራን መገናኛ ብዙኃንም የአገሪቱ የኑክሌር ተቋማት ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን አመልክተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ በረራዎች በኢራን በኩል የሚያደርጉትን ጉዞዎች በመተው ሌላ አቅጣጫን መምረጣቸውን የበረራ መከታተያ ድረ ገጾች ያሳያሉ።

የእስራኤል ጦር ሠራዊት እና የአሜሪካ መከላከያ መሥሪያ ቤት ፔንታገን ጥቃቱን በተመለከተ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም።

ይህ የእስራኤል የአጸፋ ጥቃት የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ኢራን ከ300 በላይ ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን በማስወንጨፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ ነው።

ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃቱን የፈጸመችው ሶሪያ ውስጥ በሚገኘው የቆንስላ ጽህፈት ቤቷ ላይ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት ከፍተኛ ወታደረዊ መኮንኖችን ጨምሮ 13 ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት ለመበቀል መሆኑን ገልጻለች።

የኢራን ጥቃት በእስራኤል እና በምዕራባውያን ወዳጆቿ እንዲከሽፍ በመደረጉ ይህ ነው የሚባል ጉዳት አለመድረሱን ሪፖርቶች አመልክተዋል።

እስራኤልም ለተፈጸመባት ጥቃት የአጸፋ ምላሽ በመስጠት ኢራን ዳግም ጥቃት እንዳትፈጽምባት እንደምታደርግ ስትዝት የቆየች ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግን ሁለቱም አገራት ከግጭት እንዲቆጠቡ ጥሪ ሲያደርግ ነበር።

ዘገባው የቢቢሲ ነው

ይህን መሳይ ጥቃት አይተን አናውቅም ከ አራት መቶ በላይ ሚሳኤል እና ድሮን አስገራሚ ነው!"
14/04/2024

ይህን መሳይ ጥቃት አይተን አናውቅም ከ አራት መቶ በላይ ሚሳኤል እና ድሮን አስገራሚ ነው!"

"ይህን መሳይ ጥቃት አይተን አናውቅም ‼️"
🔥🔥🔥 🔥🔥🔥 🔥🔥🔥

ሆራይዘን ሚዲያ
ሚያዚያ 6/2016

በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በወሰደ ጥቃት ኢራን በእስራኤል ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን እና የሚሳኤል ጥቃቶችን ፈጸመች።

ኢራን ጠላቷ አድርጋ በምትቆጥራት እስራኤል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ስትፈጽም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ኢራን በጋዛ እስራኤልን እየተዋጋ ያለውን ሐማስን እንዲሁም በቀጠናው የእስራኤል ጠላት የሆኑትን ሄዝቦላህ እና የየመን ሁቲ አማጺያንን በመደገፍ እስራኤል ላይ በእጅ አዙር ጥቃት ስትፈጽም ቆይታለች።

ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት የመክፈቷ ዜና ኢራናውያን ወደ አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን አንዲገልጹ አድርጓቸዋል።

ይህ የኢራን ጥቃት ድንገት የተከሰተ አይደለም። ኢራን ከ11 ቀናት በፊት በሶሪያ ዋና ከተማዋ በሚገኘው ቆንስላ ጽህፈት ቤቷ ላይ በተፈጸመው ጥቃት እስራኤልን ተጠያቂ አድርጋ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ ስትዝት ቆይታለች።

ቴህራን በቴል አቪቭ ላይ ጥቃት የምትከፍት ከሆነ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ይባባሳል በሚል አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ጀርመን ለኢራን ማሳሰቢያዎችን ሲሰጡ ቆይተዋል።

ኢራን እራሳቸውን እያጋዩ ዒላማቸውን የሚመቱ ድሮኖችን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን እስራኤል ላይ መተኮሷ ተዘግቧል።

“እስራኤል ሁሉንም ለማለት በሚቻል መልኩ መትታ እንድትጥል አግዘናል” ብለዋል ባይደን።

ምንም እንኳ አሜሪካ ይህን ብትልም የኢራን ጥቃት እንደተጀመረ በእየሩሳሌም ከተማ የአደጋ ጊዜ ደውል ተደውሎ ነበር። በከተማዋ የፍንዳታ ድምጽም ይሰማ ነበር።

"ይህን መሳይ ጥቃት አይተን አናውቅም ከ አራት መቶ በላይ ሚሳኤል እና ድሮን አስገራሚ ነው!" በማለት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ክስተቱን እና የኢራንን የጦር ብቃት በአግራሞት ሲዘግቡ አድረው ውለዋል::

Breaking news🔥ሰበር ዜና🔥🔥🔥ኢራን ጽዮናዊት እስራኤል ላይ ሚሳኤል ስታዘንብ አደረች
14/04/2024

Breaking news🔥
ሰበር ዜና🔥🔥🔥

ኢራን ጽዮናዊት እስራኤል ላይ ሚሳኤል ስታዘንብ አደረች

Breaking news🔥
ሰበር ዜና🔥🔥🔥

ኢራን ጽዮናዊት እስራኤል ላይ ሚሳኤል ስታዘንብ አደረች

Horizon Media Group

"በወራሪዋ ግዛቶች ውስጥ የጽዮናውያን ጦር ወሳኝ ወታደራዊ ኢላማዎችን በማጥቃት እና በመምታት ተሳክቶልናል።" የኢራን አብዮታዊ ጠባቂ

አሜሪካም ጽዮናዊት እስራኤል ላይ ይዘንቡ የነበሩ ሚሳኤሎችን ለማክሸፍ ሥትጥር እንዳደረችም ተዘግቧል ::

የሲ ኤን ኤኑ ሮበርትሰን ከኢየሩሳሌም በዘገባው " እንደዚህ ያለ ነገር በሰማይ አላየሁም!" ሲል ክስተቱን ገልፆታል

በተጨማሪም የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን "አሜሪካ እስራኤልን በመደገፍ የኢራንን አፈር ካጠቃች ሩሲያ ኢራንን እንደምትደግፍ አስታውቀዋል"

11/04/2024

ለወለድ ነፃ ባንክ አገልግሎት የፖሊሲና የአሠራር ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ተጠየቀ

ዒዱ : ረቡዕ፣ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ::ዒድ ሙባረክ‼️
08/04/2024

ዒዱ : ረቡዕ፣ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ::

ዒድ ሙባረክ‼️

ዒዱ : ረቡዕ፣ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ::

ዒድ ሙባረክ‼️

ዛሬ በሳዑዲ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል

BREAKING NEWS: Eid Al Fitr 1445/2024 is on Wednesday, 10 April 2024.

The Crescent was NOT SEEN in the Kingdom today

ጁምዓ፣ ከተራና ቃና ዘገሊላ የአደባባይ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ እንዲሁም የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በዓላት ሥራ ዝግ ሆነው እንዲከበሩ በፓርላማ ጥያቄ ቀረበ፡፡
03/04/2024

ጁምዓ፣ ከተራና ቃና ዘገሊላ የአደባባይ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ እንዲሁም የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በዓላት ሥራ ዝግ ሆነው እንዲከበሩ በፓርላማ ጥያቄ ቀረበ፡፡

ጁምዓ ቀን ሥራ ዝግ ሆኖ እንዲከበር ጥያቄ ቀረበ
🔸🔹🔸🔹 🔹🔸🔹🔸 🔹🔸🔹🔸

ሆራይዘን ሚዲያ
መጋቢት 25/2016

ጁምዓ፣ ከተራና ቃና ዘገሊላ የአደባባይ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ እንዲሁም የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በዓላት ሥራ ዝግ ሆነው እንዲከበሩ በፓርላማ ጥያቄ ቀረበ፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና በተባባሪነት ለሕግና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ የተመራውን፣ የሕዝብ በዓላትንና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የሕዝብ ውይይት መድረክ ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ሲካሄድ፣ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ምሁራንና ሌሎች ተቋማት ተሳትፈው ነበር፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በመወከል የተገኙት ኡስታዝ አህመዲን ጀቢል፣ በእስልምና እምነት አንድ ሰው ሦስት ተከታታይ ጁምዓ ካልተገኘ በመናፍቅነት የሚያስፈርጅ ከባድ ጉዳይ በመሆኑ፣ ዓርብ (ጁምዓ) ቀን ሥራ ዝግ እንዲሆን፣ ወይም ደግሞ አሁን በሥራ ላይ ያለውን ከአምስት ሰዓት ተኩል እስከ ሰባት ሰዓት ተኩል በአዋጁ መካተት አለበት ብለዋል፡፡

ሃይማኖታዊ በዓል የሚለው አገላለጽ በሙስሊሞች ከሆነ ዓመታዊና ሳምንታዊ በዓላት በመኖራቸው፣ ዓመታዊ የሚባሉት በአዋጁ የተጠቀሱት የኢድ አልአድሃ (አረፋ) በዓል፣ የመውሊድና የኢድ አልፈጥር በዓል ሲሆኑ፣ ሳምንታዊው ደግሞ ጁምዓ መሆኑ መታወቅ አለበት ብለዋል፡፡

አዋጁ የበዓላት አከባበርን ሃይማኖታዊ፣ ብሔራዊና ታስበው የሚውሉ በማለት በዝርዝር የጠቀሰ ቢሆንም፣ በዓላቱ የሚከበሩበትን የተለየ ቀን ገልፆ የሙስሊም በዓላትን ግን አልገለጸም ብለዋል፡፡

‹‹በአዋጁ መስከረም 1 እና 17፣ እንዲሁም ሚያዚያ 27 እየተባለ ሲጠቀስ፣ የእስልምና በዓላትን ለመጥቀስ የተቸገረበት ምክንያት፣ የሙስሊም በዓላት የሚከበሩበት ቀን በኢትዮጵያውያን ካላንደር በጨረቃ ከታየ ወይም ካልታየ በሚል ብዥታ ስለሚፈጥር በመሆኑ፣ አዋጁ መላ ኢትዮጵያውያን የሚገለገሉበት እንዲሆን ከተፈለገ የሂጂራ ካላንደር አቆጣጠርን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ታስቦ ከመዋል ይልቅ ከሥራ ዝግ ሆኖ መከበር ይገባዋል ያሉት ደግሞ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር) ናቸው፡፡

‹‹የካቲት 12 ቀን ከደርግ ዘመነ መንግሥት በፊት ቀኑ ዝግ ሆኖ ይከበር የነበረ ሲሆን፣ በ1967 የደርግ መንግሥት ሲቋቋም በዓላትን እንደ አዲስ በረቂቅ በማቅረቡ፣ በወቅቱ የነበሩት የአርበኞች ማኅበር አመራሮች ተጠርተው ቀኑ ከሥራ ዝግ መሆኑ ቀርቶ እየታሰበ እንዲውል ከተነገራቸው በኋላ፣ በወቅቱ ፍርኃትም ስለነበር ወዲያውኑ ታስቦ እንዲውል ተደርጓል፤›› ሲሉ አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዘር፣ ፆታ፣ ዕድሜ ሳይለይ በአዲስ አበባ ጥቁር ማቅ የተለበሰበት በመሆኑ፣ ቀኑን ከሥራ ዝግ በማድረግ ተከብሮ መዋል አለበት ሲሉ አበባው (ረዳት ፕሮፌሰር) ገልጸዋል፡፡

በአዋጁ ላይ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥር 10 ቀን የሚከበረው ከተራና ከጥምቀት በኋላ ጥር 12 ቀን የሚከበረው ቃና ዘገሊላ ክብረ በዓላት ከሥራ ዝግ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት ሦስት ተቋማት የተነሱትን የሥራ ዝግ መደረግ ጥያቄን በተመለከተ በፍትሕ ሚኒስቴር አዋጁን በማርቀቅ ሒደት የተሳተፉት አቶ ጠገነኝ ትርፌ፣ ‹‹ጁምዓ፣ ከተራና ሌሎች አዳዲስ በዓላት ሥራ ተዘግቶ የሚውሉበትን ቀን ባበዛን ቁጥር፣ የሥራ ቀናትን ማጣበብና ድህነትን ለመታገል ችግር ይፈጥራል፤›› ብለው ከኢኮኖሚ፣ ከማኅበራዊና ከባህል አኳያ ሊያመጡት የሚችሉት ፋይዳ ታይቶ ቋሚ ኮሚቴው ይመለከተዋል ብለዋል፡፡

‹‹አዋጁ በዓላትንና አከባበራቸውን ለመወሰን የወጣና የእረፍት ቀናትን በተመለከተ የራሱ ማዕቀፍ ያለው ቢሆንም፣ እንደ አገር የራሳችን መዳረሻ ዓላማ ያለን በመሆኑ በጋራ ሊያስተሳስሩን የሚችሉ እሴቶችን አስጠብቆ፣ አዳዲስም ካሉ የጋራ ዓላማ የሚሰንቅ መሆን አለበት፤›› ሲሉ የፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክተር አቶ አዲስ ጌትነት ገልጸዋል፡፡

አዋጁ መሠረት ያደረገው በዋናነት በዓላትን ዕውቅና መስጠትና አከባበር ላይ እንጂ፣ የእረፍት ቀን መሰየም አለመሆኑ ታሳቢ መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በኡስታዝ አህመዲን የተነሳው አዋጁ ውስጥ ‹ዓ.ም.› የሚለውን በተመለከተ፣ በአዋጁ የተገለጸው የዘመን አቆጣጠር አገሪቱ እየተከተለች ያለውን በመሆኑ ነው እንጂ የእስልምና እምነት አቆጣጠርን ችላ ተብሎ አይደለም ብለዋል፡፡

የተሰጡ አስተያየቶችም ረቂቅ አዋጁን ለማጎልበት እንደሚያግዙ ገልጸው፣ የመንግሥት ተቋማት ገለልተኛ ሆነው የተጣለባቸውን ሕዝብን የማገልገል ኃላፊነት ብቻ እንዲወጡ ማድረግ ይገባልም ብለዋል።

ዘገባው የሪፖርተር አማርኛ ነው

የጎዳና ላይ ኢፍጣር ከመብላት ከመጠጣት ባሻገር ፋይዳው ብዙ ነው :: በተለይ ለ  #ቱሪዝም
25/03/2024

የጎዳና ላይ ኢፍጣር ከመብላት ከመጠጣት ባሻገር ፋይዳው ብዙ ነው :: በተለይ ለ #ቱሪዝም

ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር በደማቅ ሁኔታ እንደሚከወን ተገለፀ
🔸🔸🔹🔸 🔹🔸🔹🔸🔹🔸 🔹🔸🔹🔸🔸

ሆራይዘን ሚዲያ
መጋቢት 15 : 2016

በኢትዮጵያ ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ለ4ተኛ ጊዜ ረመዷን 17/1445 / መጋቢት 18/2016 በደማቅ ሁኔታ እንደሚከወን ተገለፀ::

በአብዮት አደባባይ በሚከናወነው በዚህ ታላቅ መድረክ ከአዲስ አበባ ከአስራ አንዱም (11) ክፍለ ከተሞች በተውጣጡ ሐፊዞች ተደርጎ በነበረው ውድድር የፍጻሜው የሽልማት ስነ-ስርዓት እንደሚከናወንም ታውቋል ::

ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ ሙሐመድ የዝግጅቱ አስተባባሪ እንደገለፁት "በዚህ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጧር አንድነታችንን የምናንጸባርቅበት ፣ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣ ወረሐ ረመዷን ከመሆኑ አንፃር የቁርአን ክብር በአደባባይ የምናልቅበት እንዲሁም አብሮነታችንን በላቀ ደረጃ የምናሳይበት ትልቅ መድረክ ነው" ብለዋል።

አክለውም "እንደሚታወቀው ሀገራችን በብዙ ፈተና መሀል ለመሻገር ጥረት እያደረገች ትገኛለች። እንዲህ አይነቱን የፈተና ወቅት ለመሻገር ደግሞ እርስ በእርስ በመተዛዘን፣መረዳዳት በመደጋገፍና የዳበረ በጎ የኢትዮጵያዊያን መልካም እሴትን አጠናክሮ ማስቀጠል የሁላችንም ግዴታ ነው።" ብለዋል።

ዝግጅቱንም ሐላል ፕሮሞሽን እና ነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን እንደሚያዘጋጁትም ለማወቅ ተችሏል::

ዓድዋ በልኩ ሲተረክን ‼️ ተጋበዙልን Everyone
01/03/2024

ዓድዋ በልኩ ሲተረክን ‼️ ተጋበዙልን Everyone



አዲስ ዕይታ! በተለየ ምልከታ

አዲስ ምዕራፍ ፎረም የተሰኘ የሐሳብ ሜዳ የመድረክ ዝግጅት 128ኛው የዓድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ "ዓድዋ በልኩ ሲተረክ!" በሚል መሪ ሐሳብ አካሂዶ የነበረውን የፓናል ውይይት በተመለከተ ያዘጋጀነውን ልዩ ፕሮግራም ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

ዕለተ አርብ የካቲት 22 | 2016

★★★★★
📡 ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★!


!

የዛሬ ዓመት እንዲህ ደምቆ የዘንድሮ ለምን ደበዘዘ!!? ለእርምት እውነታውን ብናውቀው...
27/02/2024

የዛሬ ዓመት እንዲህ ደምቆ የዘንድሮ ለምን ደበዘዘ!!? ለእርምት እውነታውን ብናውቀው...

እሁድ ጠዋት መንገዶች ሁሉ ዓድዋን በልኩ ለመዘከር ወደ ኤሊያና ሆቴል ያመራሉ
24/02/2024

እሁድ ጠዋት መንገዶች ሁሉ ዓድዋን በልኩ ለመዘከር ወደ ኤሊያና ሆቴል ያመራሉ

ጠዋት እዛው ኤሊያና ሆቴል እንገናኝ

በክብር እንግድነት ስለሚገኙልን ክብር ይሰማናል‼️
23/02/2024

በክብር እንግድነት ስለሚገኙልን ክብር ይሰማናል‼️

በክብር እንግድነት ስለሚገኙልን ክብር ይሰማናል‼️
#ዓድዋ በልኩ ሲተርክ
አዲስ ዕይታ! የተለየ ምልከታ!
አዲስ ምዕራፍ ፎረም ✍️

ዓድዋ በልኩ ሲተረክ‼️የመግቢያ ትኬት በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኛሉእንደ አማራጭ በ CBE 1000260940938                     በ tele birr acc +25197...
20/02/2024

ዓድዋ በልኩ ሲተረክ‼️

የመግቢያ ትኬት በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኛሉ

እንደ አማራጭ በ CBE 1000260940938
በ tele birr acc +251972115454

Adwa 🇪🇹🏹🐎አዲስ ዕይታ✍️ የተለየ ምልከታ✍️  #ዓድዋ    አዲስ ምዕራፍ ፎረም /Addis Mieraf Forum  አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine Horizon ...
18/02/2024

Adwa 🇪🇹🏹🐎
አዲስ ዕይታ✍️ የተለየ ምልከታ✍️

#ዓድዋ



አዲስ ምዕራፍ ፎረም /Addis Mieraf Forum
አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine
Horizon Media Group
EBS
EBS Tv ቅዳሜ ከሰዓት


#ዓድዋ

ⓐ︎ⓓ︎ⓦ︎ⓐ︎
🇦 🇩 🇼 🇦

የመግቢያ ትኬት በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኛሉ
07/02/2024

የመግቢያ ትኬት በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኛሉ

የዘንድሮ ይለያል ‼️📯⚔️
👇👇👇👇👇👇👇

የመግቢያ ትኬት በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኛሉ
ዓድዋ!! ዘመን ተሻጋሪ ድል!!"

አዲስ ዕይታ✍️ የተለየ ምልከታ✍️

Adwa 🇪🇹🏹🐎

አዲስ ምዕራፍ ፎረም /Addis Mieraf Forum
አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine
Horizon Media Group

#ዓድዋ

ⓐ︎ⓓ︎ⓦ︎ⓐ︎
🇦 🇩 🇼 🇦

የሙስሊሞች ተጋድሎ በዓድዋ በስፋት እና በጥልቀት ይተነተናል.... የመግቢያው ትኬቱም በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኛሉ!
03/02/2024

የሙስሊሞች ተጋድሎ በዓድዋ በስፋት እና በጥልቀት ይተነተናል.... የመግቢያው ትኬቱም በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኛሉ!

ልዩ ዓድዋ ድል‼️ መሰናዶ
🗡️🏹🗡️⚔️🗡️🏹🗡️🏹

የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ብሔራዊ ክብርና ኩራትን ያጎናፀፈ፣ ለመላው ጥቁር ሕዝቦች በተለይ ደግሞ አፍሪካውያን ለነፃነታቸው ትግል መነሻና ብርታት የሆነ ታላቅ ድል ነው፡፡

ይህን ዘመን ተሸጋሪ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ድልን በአዲስ ዕይታ! በተለየ ምልከታ! .... በተለይ “የእኛ አያቶችና ቅድመ አያቶች የፈጸሙትን ገድል“ በአግባቡ እንዲወሳ በአዲስ ምዕራፍ ፎረም ዝግጅታችን በስፋት እናያለን ለገጠሙንም ችግሮችም መፍትሔ ሐሳብ እናዋጣልን።

ይምጡና የዚህ ታሪካዊ ዝግጅት አካል ይሁኑ።

አዲስ ምዕራፍ ፎረም‼️
አዲስ ዕይታ! የተለየ ምልከታ!

ቦታ፡- ግራንድ ኤሊያና ሆቴል
ቀን፡- የካቲት 17 ፡ 2016
ሰዓት፡- ጠዋት 2፡00-6፡30

የመግቢያ ትኬት በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኛሉ

ለበለጠ መረጃ ፡- 0972115454 እና 0955616161

አዘጋጅ :- ሆራይዘን ሚዲያ ግሩፕ
:- Horizon Media Group The Power of Imagination ‼️

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ።              ~~~*******~~~ጠቅላይ ምክር ቤቱ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የአብሮነት መግለጫን በደስታ...
27/01/2024

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ።
~~~*******~~~

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የአብሮነት መግለጫን በደስታ ተቀብሎታል፡፡

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ባወጣው መግለጫ፣ በፌደራል መጅሊሱ ማቋቋሚያ አዋጅ እና በምክር ቤቱ ደንብ በመመራት ከፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በአብሮነት ለመሥራት ያሳለፈውን ውሳኔ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በደስታ ተቀብሎታል፡፡

እስልምና ከመለያየት ይልቅ ለአብሮነት፣ ከመበታተን ይልቅ ለአንድነት፣ ከቂምና ቁርሾ ይልቅ ለእርቅና ለሰላም ትልቅ ቦታ የሚሰጥ በመኾኑ፣ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይህን እስላማዊ መርኅ ተከትሎ፣ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር አብሮ ለመሥራት መወሰኑ እጅግ የሚደገፍና የተወደደ ተግባር እንደኾነ ጠቅላይ ምክር ቤታችን በጽኑ ያምናል፡፡

ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ምክንያት የተፈጠሩ ክፍተቶችን ለመድፈን፣ የሻከሩ ልቦችን ለማለዘብ እና መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ለመቀጠል የሚጠበቁበትን ማናቸውንም አስፈላጊ ተግባራት ለማከናወን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ዝግጁ መኾኑን ለማስታወቅ ይወድዳል፡፡

በተፈጠሩት ችግሮች ምክንያት፣ የትግራይ ክልል ሙስሊም ኅብረተሰብ ላለፉት ሦስት ዓመታት የሐጅና ዑምራ ሃይማኖታዊ ግዴታውን ለመወጣት ሳይችል መቆየቱ በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ኾኖ፣ የክልሉ ሙስሊም ኅብረተሰብ ሐጅና ኡምራን ጨምሮ በማናቸውም መንፈሳዊ አገልግሎቶች ረገድ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መኾኑን ለማረጋገጥ ይወድዳል፡፡

ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ጦርነት በክልሉ ሕዝብ ላይ ያደረሳቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማድረግ ዝግጁ መኾኑን ከዚህ ቀደም እንደገለፀው ሁሉ፣ አሁንም ይህንኑ ለማድረግ ዝግጁ መኾኑን በድጋሚ በአጽንዖት ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጋራ ተቋም እንደመኾኑ፣ ሁሉንም ሙስሊሞች በሚያካትት መልኩ የመሥራት መርኅን የሚከተል ሲኾን፣ በሙስሊሞች መካከል ያሉ የአመለካከትና የአረዳድ ልዩነቶች በዓሊሞች ጉባዔ የሚፈቱበትን ሁኔታ በማመቻቸት፣ እንደ ጠቅላይ ምክር ቤት የሙስሊሞችን አንድነት የማጠናከር ተልዕኮውን ለመወጣት እንደሚንቀሳቀስ በዚሁ አጋጣሚ ለማሳወቅ ይወድዳል፡፡

ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
ጥር 18፣ 2016 ዓ.ል
(ረጀብ 15፣ 1445ዓ. ሒ.)
አዲስ አበባ



አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine
አዲስ ምዕራፍ ፎረም /Addis Mieraf Forum
Horizon Media Group

ገነነ እንደ ገነነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ⚫⚫⚫⚫የስፖርት እና የታሪክ ፀሐፊው ታዋቂው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።ስመ ጥሩ ጋዜጠኛ ባደረበት ሕመም ምክንያት በሕ...
23/01/2024

ገነነ እንደ ገነነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
⚫⚫⚫⚫

የስፖርት እና የታሪክ ፀሐፊው ታዋቂው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ስመ ጥሩ ጋዜጠኛ ባደረበት ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ማክሰኞ ጥር 14/2016 ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

ገነነ መኩሪያ ይሠራበት የነበረው 'አሻም' የተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ የጋዜጠኛውን ሕልፈተ-ሕይወት በፌስቡክ ገፁ አረጋግጧል።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) በአሻም ቴሌቪዥን “የገነነ” እና “ጥቁር እንግዳ” የተሰኙ ፕሮግራሞችን አዘጋጅ እና አቅራቢ ሆኖ እንዳገለገለ ጣቢያው ገልጧል።

ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ለበርካታ ዓመታት ለተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተወዳጅ የሆኑ ዝግጅቶችን በማቅረብ ሠርቷል።

ገነነ መኩሪያ እግር ኳስ እና ፖለቲካን እንዲሁም ታሪክን የሚዳስሱ በርካታ መጽሐፎችን ያሳተመ ሲሆን፣ “ኢሕአፓ እና ስፖርት” እና ሌሎች መፃሕፍትን ለአንባቢ አቅርቧል።

ሊብሮ ከስፖርት ጋዜጠኝነት ሕይወት ባሻገር በወጣትነት ዘመኑ ለበርካታ የእግር ኳስ ክለቦች በመሠለፍ ተጫውቷል።

የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ የሙያ ባልደረቦቹ እና ታዋቂ ሰዎች በሊብሮ ሕልፈተ ሕይወት ሐዘናቸውን እየገለጡ ይገኛሉ::

ገነነ ከ30 ዓመታት በላይ በስፖርት ጋዜጠኝነት ሙያው አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን በጋዜጣ፣ በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሥራውን በማቅረብ ተወዳጅነትን አትርፏል።

ገነነ መኩሪያ በዘመናት የዳበረ የስፖርት፣ የፖለቲካ፣ የሙዚቃ እና የማኅበራዊ ጉዳይ ታሪኮችን በጥልቀት እና በዝርዝር የሚያውቅ ሲሆን፣ በስፖርት እና በፖለቲካ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ መጽሐፍትን አሳትሞ ለንባብ አብቅቷል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳለው ገነነ መኩሪያ ለእግር ኳስ ስፖርት ላበረከተው ታላቅ አስተዋፅኦም በአዲስ አበባ ተሰናድቶ በነበረው የካፍ ኮንግረስ ላይ የረጅም ዘመን አግልግሎት ሜዳይ ተበርክቶለታል።

ምንጭ ቢቢሲ

የዘንድሮ ይለያል ‼️📯⚔️🔸🔹🔸🔹🔸ዓድዋ!! ዘመን ተሻጋሪ ድል!!"አዲስ ዕይታ✍️ የተለየ ምልከታ✍️Adwa 🇪🇹🏹🐎አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazineአዲስ ምዕራፍ ፎረም...
22/01/2024

የዘንድሮ ይለያል ‼️📯⚔️
🔸🔹🔸🔹🔸

ዓድዋ!! ዘመን ተሻጋሪ ድል!!"

አዲስ ዕይታ✍️ የተለየ ምልከታ✍️

Adwa 🇪🇹🏹🐎

አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine
አዲስ ምዕራፍ ፎረም /Addis Mieraf Forum
Horizon Media Group

#ዓድዋ

ⓐ︎ⓓ︎ⓦ︎ⓐ︎
🇦 🇩 🇼 🇦

አስፋዉ መሸሻ የስንብት እና የቀብር ሥነሥርዓት⚫⚫⚫የተወዳጁ የራዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ የነበረዉ አስፋዉ መሸሻ የስንብት እና የቀብር ሥነሥርዓትእሁድ ጠዋት በዋሽንግተን...
20/01/2024

አስፋዉ መሸሻ የስንብት እና የቀብር ሥነሥርዓት

⚫⚫⚫

የተወዳጁ የራዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ የነበረዉ አስፋዉ መሸሻ የስንብት እና የቀብር ሥነሥርዓት

እሁድ ጠዋት በዋሽንግተን አቆጣጠር ከጠዋቱ 10 AM ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ። (ልጁን እና ቤተሰቡን መሰናበትና መሸኘት የምትፈልጉ የዲሲና አካባቢዋ አድናቂዎቹ እሁድ ጠዋት ከ7 AM- 8 AM ዳላስ አየር ማረፊያ መገኘት ትችላላችሁ።)

ሰኞ ጥር13፣ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከጠዋቱ 1፡30 ላይ ቦሌ አየር ማረፊያ በጉምሩክ በር በኩል አቀባበል ይደረጋል።

ከጠዋቱ 4 እስከ 4፡30 ሚሊኒየም አዳራሽ ይደርሳል።

ከጠዋቱ 5 እስከ ቀኑ 6፡30 በሚሊኒየም አዳራሽ የስንብት መርሃግብር ይካሄዳል።

ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 9 ሰዓት ስላሴ ቤ/ክርስቲያን የቀብር ሥነ ሥርዓት ይፈፀማል።

EBS EBS Tv ቅዳሜ ከሰዓት EBS

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።😭😭😭ለበርካታ ዓመታት በጋዜጠኝነት ሥራው የሚታወቀው አስፋው ባደረበት ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።ኢቢኤስ የተሰኘው ጋዜ...
14/01/2024

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
😭😭😭

ለበርካታ ዓመታት በጋዜጠኝነት ሥራው የሚታወቀው አስፋው ባደረበት ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

ኢቢኤስ የተሰኘው ጋዜጠኛው ለመጨረሻ ጊዜ ያገለገበት የቴሌቪዥን ጣቢያ “ወንድማችንና የሥራ ባልደረባችን አስፋው መሸሻ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል” ሲል በፌስቡክ ገፁ አስነብቧል።

ጣቢያ አክሎ ጋዜጠኛ አስፋው፤ ባደረበት ህመም በህክምና ሲታገዝ እንደቆየ ዘግቧል።

አስፋው መሸሻ በተለይ በቅርብ ዓመታት “ኑሮን በአሜሪካ” እንዲሁም “እሑድን በኢቢኤስ” በተሰኙ ፕሮግራሞቹ በርካታ ተከታዮች አፍርቷል።

በራድዮና በቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት ያገለገለው አስፋው መሸሻ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የጤና እክል እንደገጠመው ተዘግቦ ነበር።

የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኛው የሕክምና አልግሎት ለማግኘት ባቀናበት ዩናይትድ ስቴትስ ሕይወቱ እንዳለፈ አስነብበዋል።

አስፋው፤ ለረዥም ዓመታት ኑሮውን በአሜሪካ አድርጎ ከቆየ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት ሲያገለግል ቆይቷል

የ አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine & አዲስ ምዕራፍ ፎረም /Addis Mieraf Forum ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛሉ!!

ዘገባው የቢቢሲ ነው

🚨 𝐁𝐑𝐄𝐀𝐊𝐈𝐍𝐆:- ተጠርጣሪው አልተያዘም ‼️ ሸይህ ዓብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሐመድ ሽኩር አበባው በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትሉን አጠናክሮ ቀጥሏል። አንዳንድ ማህበራዊ ሚ...
11/01/2024

🚨 𝐁𝐑𝐄𝐀𝐊𝐈𝐍𝐆:- ተጠርጣሪው አልተያዘም ‼️

ሸይህ ዓብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሐመድ ሽኩር አበባው በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትሉን አጠናክሮ ቀጥሏል።

አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠርጠሪው እንደተያዘ በማስመሰል የሚያሰራጩት መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ።


በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጠርጣሪው ሳይያዝ እንደ ተያዘ አድርጎ መረጃ ማሰራጨት ተገቢ እንዳልሆነ አዲስ አበባ ፖሊስ እየገለፀ መሐመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅም ሆነ ማንኛውም መረጃ ያለው ሁሉ

በስልክ ቁጥር
011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪም ቀርቧል ::

Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና
Addis Ababa Police

🏆 የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የ3ተኛ ዙር የጨዋታ መርሃ-ግብር በኢትዮጵያ ቀንና ሰዓት አቆጣጠርማንዱራ ስፖርት Mandura Sport
05/01/2024

🏆 የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የ3ተኛ ዙር የጨዋታ መርሃ-ግብር በኢትዮጵያ ቀንና ሰዓት አቆጣጠር

ማንዱራ ስፖርት Mandura Sport

"ተስፋዬ እንኳን ሞተ!''ን ምን አመጣው!? 👀👁️👀
31/12/2023

"ተስፋዬ እንኳን ሞተ!''ን ምን አመጣው!? 👀👁️👀

"ተስፋዬ እንኳን ሞተ!!"
🔹🔸🔹🔸🔹

ሆራይዘን ሚዲያ
ታኅሣሥ 21 : 2016

ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ የዛሬ ሁለት ዓመት ታኅሣሥ 15/2014 በኬንያ መዲና ናይሮቢ አጋ ካሃን ሆስፒታል ውስጥ ለአንድ ወር ያህል ሕክምና ሲደረግለት ቆይቶ በስተመጨረሻ በ53 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።

ተስፋዬ ባለ ትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበር። ልጆቹ የ12፣ የ9 እና የ8 ዓመት ናቸው። ተስፋዬ ነሐሴ 22/1960 ከኤርትራውያን ቤተሰቦቹ በቢሾፍቱ ከተማ ነበር ተወልዶ ያደገው።

ተስፋዬ እና አወዛጋቢ ጽሑፎቹ
--------- ---------- ----------

ተስፋዬ በደርግ ዘመን ማብቂያ አካባቢ በጦር ሠራዊቱ ተመልምሎ ሥልጠና ከወሰደ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ወታደራዊው መንግሥት ሲወድቅ ከኢሕአዴግ ጋር ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ጋዜጠኛ ሆኗል።

ዕለታዊዎቹን የመንግሥት ጋዜጦች የሚያሳትመው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ነበር። "እፎይታ" መጽሔትንም መርቷል።

የጋዜጠኝነት ሥራውን ካቆመ በኋላ አስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ በመሆን ከስምንት በላይ ሥራዎችን ለአንባቢያን አድርሷል።

"እፍታ" በሚል ርዕስ ከ1992 እስከ1993 የአጫጭር ጽሑፎች ስብስብ የሆኑ አምስት ቅጾችን አሳትሟል።

"ገዳ" በሚለው ስም በበርካቶች የሚጠራው ተስፋዬን በአንባቢያን ዘንድ በስፋት ያስተዋወቀው "የቡርቃ ዝምታ" የተሰኘው ረዥም ልብ ወለዱ ነው።

የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ እና የባለሥልጣናቱ የውስጥ ምስጢሮችን የያዙትን "የጋዜጠኛው ማስታወሻ" እና "የደራሲው ማስታወሻ" መጻሕፍትንም ለንባብ አብቅቷል።

ከህወሓት የትግል ጅማሬ እስከ ኢሕአዴግ አዲስ አበባ መግባት ድረስ ያለውን ዘመን የሚተርከው ተከታታዩ "ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ" ይጠቀሳል።

ተስፋዬን በሥነ ጽሑፍ ችሎታው የሚያሞካሹት እንዳሉ ሁሉ በሚያነሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች የሚተቹትም በርካቶች ናቸው።

በአንድ በኩል በኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች መካከል 'መቃቃርን' ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል በሚል በርካቶች ይወቅሱታል።

በሌላ በኩል ጽሑፎቹ የተዳፈኑ የጭቆና ታሪኮችን ያነሳሉ፣ የተገለሉ ማኅበረሰቦችን እውነታም ያንጸባርቃሉ ብለው የሚከራከሩ ወገኖች አሉ።

እውነት ነው የተስፋዬ ጽሑፎች አወዛጋቢ እንደሆኑ አይካድም። አድናቂዎቹም ተቺዎቹም በርካታ የሆኑት ተስፋዬ፤ በተለይም በዘመናዊ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ በጉልህ ከሚጠቀሱ ጸሐፍት አንዱ መሆኑም እንዲሁ::

"ተስፋዬ እንኳን ሞተ!''ን ምን አመጣው!? 👀👁️👀
******** // ********* // **********

የዛሬ ሁለት ዓመት ተስፋዬ ያረፈ ግዜ ታላቅ ወንድሙ ይርጋለም ገብረ አብ ቤት እዝን ሊደርሱ ከመጡ ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም አድናቂዎች መሃል እጅግ ነውረኛ የሆኑ ሰዎች እጅግ ነውረኛ የሆነ ነገር ፈፀሙ.... ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በታላቅ ወንድሙና ቤተሰቦቹ ፊት ... ሕዝብ በይፋ እያየ እየሰማ.... "ተስፋዬ እንኳን ሞተ!!" ብለው አምባረቁ :: በሥፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ሁኔታውን ከአስደንጋጭነቱ ባሻገር እጅግ አሳዛኝ እና አሳፋሪም ነበር ይላሉ :: እኛንም ከሩቅ ለሰማነው አሸማቆናል ::

እነዚህ ነውረኞች ይህ አልበቃ ብሏቸው የዛሬ ወር በ ጉቺ ሽመልስ የተፃፈ እና " የአድአው ጥቁር አፈር... " የተሰኘ በተስፋዬ ሕይወት እና የድርሰት ሥራዎቹ ዙሪያ የሚያጠነጥን መፅሐፍ በ ወመዘክር እንዳይመረቅ ሎቢ ከማርግ እና ከማወክ ባሻገር መብራት ከዋናው ቆጣሪ እስከማጥፋት የደረሰ ድምፅን የማፈን ነውረኛ ድርጊትም ፈፅመዋል ::

እነዚህ ነውረኞች ይህ ነውራቸው የመጀመሪያ አይደለም ከዚህ ቀደምም በ ፀሐፊ አብዱልጀሊል ሸይክ ዓሊ ካሳ ተደርሶ ለኅትመት የበቃና "ተምነታዊት ደሴት" እንዲሁም "ኪነት ያገነነው ዓፄ " የተሰኙ ሥራዎቹ እንዳይመረቁ ዘርፈ ብዙ ተንኮሎችን ከመፈፀም ባሻገር ፀሐፊውንም ከሀገር ከተቻለም ከምድር እስከ ማስወገድ የደርሰ ሐቅን የመቅበር ዘመቻቸውን ሴራቸውን ከውነዋል ባይሳካላቸውም::

የኢኮኖምስቱ እና ፀሐፊ አብዱልጀሊል "ተምነታዊት ደሴት " ከብዙ ውጣውረድ በኋላ በ አምባሳደር ቴአትር ሲመረቅ ፤ የጉቺ ሽመልስ " የአድአው ጥቁር አፈር.. ተስፋዬ ገብረ አብ ሕይወት እና ሚስጥር " መፅሐፍ ትላንት ምሽት ታኅሳስ 20 2016 በስካይ ላይት ሆቴል ወዳጅ ዘመዶቹ : ምሁራን እና አድናቂዎቹ በተገኙበት በደማቅ ሁናቴ ተመርቋል :: ለሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ!!

ዋናው ጉዳይ "ተስፋዬ እንኳን ሞተ!''ን ምን አመጣው!? የሚለው ነው!!.... እንዲህ ያለውስ ህመም ፈውስ የሚያገኘው መቼ ነው!? ይህ "ተስፋዬ እንኳን ሞተ!''... 'መፈክር' የመጀመሪያ አይደለም የመጨረሻም አይሆንም :: ባለፉት አምስት ዓመታት ብዙ "እንኳን ተገደለ!" "እንኳን ሞተ!" "እንኳን ታሰረ!"... ሰምተናል. አይተናል...

ፍትህን መጠየቅ ሰውነት ነው! ይህ ቢቀር... "እንኳን ሞተን ምን አመጣው!" ... ስለፍትህ የሚጮሁትን mic መቀማት እሱም ሲያቅት mixer መዝጋት በዛም ካልተሳካ ድምፅ ማፈኑ መብራት ከቆጣሪው ማጥፋት... ይህ ህመም ይህ በሽታ መቼ ነው የምታከመው እንዴት ነው የሚፈወሰው..!? የሚለው በእጅጉ ሊያሳስበን ይገባል እንላለን :: ቸር ያሰማን!

ለምንጭነት #ቢቢሲ አማርኛን ተጠቅመናል

ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ!!⚽️🇪🇹🎉
30/12/2023

ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ!!⚽️🇪🇹🎉

Address

Addis Ababa
5313

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አዲስ ምዕራፍ መፅሔት / Addis Mieraf Magazine:

Share



You may also like