Emmaus - ኤማሁስ

Emmaus - ኤማሁስ ይህ ገጽ ኦርቶዶክሳዊ ትውፊት ላይ ትኩረት ያደረጉ ጽሑፎች እና ቪዲዮዎች የሚቀርቡበት ነው።

09/06/2024

አንቀጸ ብፁዓን - መግቢያ

ዛሬ ማታ በኤማሁስ ሚድያ ይጠብቁን።

21/02/2024

"Christians are united not only among themselves, but first of all they are one in Christ, and only this communion with Christ makes the communion of men first possible. The center of unity is the Lord and the power that effects and enacts the unity is the Spirit. Christians are constituted in to this unity by divine design; by the Will and Power of God. Their unity comes from above. They are one only in Christ." Georges Florovsky

https://youtu.be/Y4WdzqzU7u4?si=fVJXu11Rjl9MtKTu
18/02/2024

https://youtu.be/Y4WdzqzU7u4?si=fVJXu11Rjl9MtKTu

ባለ ረጅም ታሪክ፣ ባለ ብዙ ሥነ ጽሑፍ እና ኪነ ሕንጻ ባለቤት መሆናችን የተልእኮ ሥራችን ላይ ተጽዕኖ አምጥቷልን?

18/02/2024

"ባለረጅም ታሪክ ፣ ባለብዙ ሥነጽሑፍና ኪነ ሕንጻ ባለቤቶች መሆናችን የተልእኮ ሥራችን ላይ ተጽእኖ አምጥቷልን?"

Podcast

https://youtu.be/SZKaqLLIu64?si=ue1EQQQj6AsedPTy

https://youtu.be/l9aAFmjNk9M?si=zbXDGwnVtn3L42DA
16/02/2024

https://youtu.be/l9aAFmjNk9M?si=zbXDGwnVtn3L42DA

ታሪክን በተለያየ መነጽር ማየት የተለመደ ቢሆንም፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን በዋናነት የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ታሪክ መሆን አለበት በሚል ጭብጥ ለመወያየት ሞክረናል። እንድታዳምጡ...

05/02/2024

የሚያፈርሰው 'የጥፋት ዘር' አስቀድሞ ወደ ውስጡ ዘልቆ ሳይገባ፣ የሚፈርስ ባህል እንደሌለ የሚጠቁም ሊቅ አለ። "If our culture, which we used, rather complacently, to regard as Christian, disintegrates and falls to pieces, it only shows that the seed of corruption
was already there"። በእውነት ላይ ወደ ተመሠረተው እውነተኛው ክርስቲያናዊ ባህል ውስጥ ውሸት ሰርጎ ከገባ በኋላ እና ይኼው ውሸት ለአቅመ ባህልነት አንዴ ከበቃ፣ የመጀመሪያው እውነተኛው ባህል መፍረክረክ የሚጀምረው ወደ ውስጡ ሰርጎ በገባው የውሸት የጥፋት ዘር ነው እንደማለት ነው። ችግራችንን ሁሉ ከውጪ ማየት የለብንም፤ ጨከን ብለን የውስጡንም ማየት አለብን።

30/01/2024

"እንደ ሕጻናት ካልሆናችሁ የእግዚአብሔር መንግሥት አትገቡም" የሚል ቃል በወንጌል ተጽፏል።፤ ራሱ ጌታ ነው ያለው። የሕጻናት ጠባይ ምን ዓይነት ነው? ሕጻናት ንጹሕ ናቸው። የሚያሸንፈንም ይኼው ንጹሕ የሆነ ልባቸው ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት በእንዲህ ዓይነቱ ንጽሕና የምትወረስ ናት። "ማደጋችን" ያሳጣንን የልጅነታችንን ልብ መልሰን እንድንፈልገው ነው መልእክቱ።

27/01/2024

ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህናቲነ አስተጋብአነ ኀበ ትረፍቅ መካን - ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ አንተ ባለህበት ቅዱስ ቦታ ሰብስበን። መልካም ዕለተ ሰንበት

እንኳን የቤተ መቅደሱ የመንገድ ሥርዓቱም የሚነበብ መጽሐፍ ያክል ነው።
25/01/2024

እንኳን የቤተ መቅደሱ የመንገድ ሥርዓቱም የሚነበብ መጽሐፍ ያክል ነው።

25/01/2024

ክርስትና ፖለቲካዊውም ሆነ ማኅበራዊ ውክልና አይደለም። ክርስቲያን የሆነው እንደዚህ የተናገሩትን ሰዎች ስላመናቸው፣ ስለተከተልናቸው ነው።

"ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን፣ በዐይኖቻችንም ያየነውን፣ የተመለከትነውንም፣ እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ፤ አይተንማል፤ እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን" (1ኛ. ዮሐ. 1:1-4)

23/01/2024

በጠባቂነት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የሚሾሙ የጥንቷ ቤተክርስቲያን አባቶች ኤጲስ ቆጶስ (ἐπίσκοπος) የሚለውን ስም የወሰዱት በወቅቱ ከነበረው የሮማውያን የቤተሰብ አስተዳደር እንደነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሊቃውንት ይናገራሉ። ባርነት እንዳሁኑ ነውር ባልነበረበት በዚያን ዘመን በአንድ ሮማዊ ቤት ውስጥ የተለያየ ሚና ያላቸው ብዙ አገልጋይ ባርያዎች ሲኖሩ፣ የቤቱ ጌታ እነሱን የሚያስተባብር ክብሩ ከሌሎቹ ከፍ ያለ አንድ ታማኝ ባሪያ (master slave) በላያቸው ላይ ይሾማል። ይኼ ቁጥሩ ከባሪያዎቹ የሆነ፣ ነገር ግን በጌታው ፈቃድ master slave ሆኖ የተሾመው ታማኝ ባሪያ በወቅቱ ግሪክ ኤጲስ ቆጶስ ተብሎ ነበር የሚጠራው። የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ሆነው የተሾሙ አበው ለራሳቸው የወሰዱት ስም የዚህን የባሪዎችን አለቃ ስም ነው። ለራሳቸው ተስማሚ ሆኖ ያገኙት ቦታም ያ ነበር። ዛሬ የቃሉ ትርጉሙ የቤቱ ባለቤት ታማኝ ባሪያ ከሚለው የዚህ ወይንም የዚያ አካባቢ "ጀግና" ወደሚለው ተቀይሮ ስለ "ኤጲስ ቆጶሳት" እንዴት እንግባባ። Translation matters!

22/01/2024

ለቅዱሳን ከሚሰጡ የክብር ስሞች መሀከል አንዱ "ሰማዕተ ጽድቅ" የሚለው ነው። የእውነት ምስክሮች ማለት ነው። በእውነት ኖረው፣ እውነቱን መስክረው ያለፉ በመሆናቸው ያገኙት የክብር ስማቸው ነው። በእውነት መኖር እንደዚህ ለክብር ቢያበቃም እውነት ግን ብዙ ጊዜ ወዳጅ የላትም፤ ትገፋለች። በዚህም ምክንያት ብዙ ሰው እውነትን መናገርም፣ መስማትም አይፈልግም፤ ከባድ ፈተና ሆኗል። ዲፕሎማሲያዊ የሆነ ወዳጅነት፣ ሽንገላ የተሞላበት ንግግር፣ ምን ብናገር ልወደድ እችላለሁ በሚል የሚቀርብ ስብከት ... እውነት በተካደበት ባህል ውስጥ መንገሣቸው አይቀርም። አርነት የሚያወጣን ግን እውነት እና እውነት ብቻ ነው። ቤተ ክርስቲያንም "የእውነት ምስክሮች" ብላ የተወሰኑ ሰዎችን ስትለይና ተከተሏቸው ስትል መልእክቱ ግልጥ ነው። አርአያ ማድረግ፣ መከተል የሚገባው የእውነት ሰዎችን እንደሆነ ለማስተማር ነው። ማስተዋል ያስፈልጋል፤ በተለይ አስመሳይነት እና ጥቅመኝነት እንደ ጥበብ በተወሰደበት በዚህ ዘመን።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Emmaus - ኤማሁስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share