06/01/2024
ለመላው የክ/ከተማችን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!
የክርስቶስ መወለድ ጨለማ በብርሃን ፣ ክፋት በቀናነት ፣ ስስት በልግስና ፣ ጥፋት በቀናነት ፣እንዲሁም ጥላቻ በፍቅርና በይቅርታ ድል የተደረጉበት እንደመሆኑ መጠን በአሉን ስናከብር የኢትዮጵያዊነት እና የብልፅግናችን ሰው ተኮር ተግባራት አንዱ ክቡር እሴት የሆነውን መተሳሰብ ከጎረቤቶቻችን እና ከአካባቢያችን ጀምረን ተግባራዊ በማድረግ ልግስናችንን በገቢር የምንገልጥበት ነው።
በያዝነው በጀት ዓመት የክ/ከተማችንን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ በስራ እድል ፈጠራ ፤ በሰላምና ፀጥታ ተግባራት ፤ በሰው ተኮር ተግባራት፤ በህብረተሰብ ተሳትፎ የአካባቢ ልማት ስራዎች ፤ የትምህርት ለትውልድና የቀዳማይ ልጅነት መርሃ ግብር ንቅናቄዎች ፤ አቅም ለሌላቸው ወገኖቻችን የቤት ማደስና ማዕድ በማጋራ ፤ አገልገሎት አሰጣጣችንን ለማሻሻል ተቋማትን የማዘመን ስራ ፤ የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ እና ገበያ ለማረጋጋት የእሁድ ገበያ ቦታዎችን በማስፋትና የሌማት ቱሩፋት መርሃ ግብሮችን በልዩ ትኩረት እየተገበርን እንገኛልን፡፡
በመሆኑም መላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች እነዚህን ተግባራት ስናከናውን እንደ ከዚህ ቀደሙ ተሳትፎአቹ እዳይለየን እያልኩ
በአስተዳደራችን በተግባር አፈፃፀም ሂደት የተፈጠሩ ቅሬታዎች እና ህፀፆች ካሉ እንድናርማቸው እድል በመስጠት የጀመርናቸውን ትላልቅ የልማት ስራዎችና ፕሮጀክቶች በስኬት አጠናቀን ለህዝባችን ለማስረከብ የምናደርገውን ብርቱ ጥረት የማገዝና የመደገፍ የተለመደ ቀናነታችንን የምናጎለበትበት ፣ በተጨማሪም የክ/ከተማችንን ህዝብ ፈጣንና ታዳጊ መሰረታዊ የመልማት ፍላጎት በሚፈለገው ፍጥነትና ስፋት እንዳንመልስ እንቅፋት የሚፈጥሩብንን ከየትኛውም አቅጣጫ የሚነሱ የጥላቻና የግጭት ፀረ-ሰላም አመለካከትና ተግባራትን እንደሁልጊዜው ከሰፊው ሰላም ወዳድ ህዝባችን ጋር በመቀናጀትና እጅና ጓንት በመሆን የፅንፈኞችን ከንቱ ህልም እስከወዲያኛው የምናጨናግፍበትን ወኔና ተነሳሽነት የምንሰንቅበት ነው።
በዚህ አጋጣሚ የአስተዳደሩ አመራሮች እና የመንግስት ሰራተኞች ሌት ተቀን በፍጹም አገልጋይ መንፈስ ህብረተሰቡን ለማገልገል እንደሚተጉ እየገለፅኩ በድጋሚ መልካም በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!
በዓሉ የሰላም፤የፍቅር የብልጽግና እና የስኬት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡
መልካም የገና በዓል!!
አቶ ንጋቱ ዳኛቸው
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና አስ አስፈጻሚ
ታህሳስ 27/2016ዓ.ም
አዲስ አበባ
Hordoftoota amantaa kiristaanaa magaalaa keenya keessa jirtan hundaaf baga guyyaa dhaloota Yesuus Kiristoosiin isin gahe jenna!!Akkuma dhaloota Kiristoos guyyaa dukkanni ifaan, hammeenyi amanamummaadhaan, araadaan arjummaadhaan, badiisni amanamummaadhaan, guyyaa itti mo'ame ture, akkasumas jibba jaalalaa fi dhiifama gochuudhaan.Kun bakka ollaa keenyaa fi naannoo keenya irraa eegaluun arjummaa keenya dammaqinaan itti ibsinu yoo ta’u, kunis gatii guddaadha.
Adeemsa hojiirra oolmaa bulchiinsa keenyaa keessatti komii fi komiin uumamu yoo jiraate, akka sirreessinu carraa nuuf kennuudhaan, hojiiwwan misoomaa fi pirojektoota gurguddoo jalqabnee fi proojaktoota misoomaa gurguddaa jalqabnee fi dabarsinee ummata keenyaaf kennuun, jibbaa fi jibba kallattii kamirraayyuu ka’ee fedhii misoomaa bu’uuraa ummata godina keenyaa saffisaa fi bal’ina barbaadamuun deebii kennuuf nu gufachiisu malees akkuma yeroo hunda qindoominaan ummata keenya nagaa jaallatuu fi harka wal qabannee hojjennu waliin hookkaraa fi kaka'umsa abjuu bu'aa hin qabne warra finxaaleyyii ni caccabsina.Ummata ishee eebbisaa!!Ayyaanni kun kan nagaa, jaalala, badhaadhinaa fi milkii akka ta'u hawwa.Baga gammaddan Ayyaana Qillee!!Hogganaa Olaana
Aanaa Kolfee Karaaniyoo, Muddee 27/2016, Addis Ababa.