15/05/2023
ጀርመን ለዩክሬን ከፍተኛ ደረጃ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች።
ቁቤ ቲቪ (ግንቦት 15፣ 2023)ፊንፊኔ!
ጀርመን ለዩክሬን 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ዩሮ የጦር መሳሪያ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታወቀች።
እርዳታው ይፋ የሆነው የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌኒስኪ በዚህ ሳምንት በበርሊን የስራ ጉብኝት ለማድረግ ካቀዱ በኋላ ነው።
የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ቦሪስ ፒስቶሪየስ ሀገራቸው ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል። ጀርመን ለዩክሬን 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ዩሮ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጣለች።
ብሉምበርግ እንደዘገበው ይህ ለዩክሬን ከተበረከተ ትልቁ የጦር መሳሪያ ልገሳ ነው። ድጋፉ ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ታንኮች እና ሌሎች ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ይገኙበታል።
በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ለመከታተል ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
https://www.youtube.com//videos
https://www.facebook.com/Qubeetv2023/?ref=pages_you_manage