መሳይ መኮንን ከESAT International

መሳይ መኮንን ከESAT International ኢትዮጵያ ትቅደም

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት እጅግ አስደንጋጭ ነው። አብይ አህመድ ስልጣን ከያዘ 5ዓመታት አለፉት። የዛሬዎቹ የ12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ የ7ኛ ክፍል ተ...
12/10/2023

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት እጅግ አስደንጋጭ ነው። አብይ አህመድ ስልጣን ከያዘ 5ዓመታት አለፉት። የዛሬዎቹ የ12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነበሩ። በቀደመው ፖሊሲ ላይ ማላከክ ብቻውን ከተጠያቂነት አያድንም። በ5ዓመት ውስጥ ምንም ዓይነት ስራ እንዳልተሰራ በግልጽ የሚታይበት ውጤት ነው የተመዘገበው። ከ50 በመቶ በላይ ተማሪዎች ከወደቁ ችግሩ ከተማሪዎች ሳይሆን ከፈተናው ነው የሚል የትምህርት ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሚጋሩት አሰተሳሰብ አለ።

ብርሃኑ ነጋ ቴክኒካል ጉዳይ ላይ ማተኮሩን መርጧል። መኮራረጅን ማስቀረትን (ስለመቅረቱ ግን እርግጠኛ አይደለሁም) ስኬት ተደርጎለት እንዲጨበጨብለት ይፈልጋል። በሱ የስልጣን ዘመን ከህወሀትም እጅግ የከፋው የትምህርት ፖሊሲ መጽደቁና ተግባራዊ መሆኑ ብዙም ያስጨነቀው አይመስልም። ብርሃኑ ደክሞታል። ሰልችቶታል። ከዚህ አሳፋሪ የተማሪዎች ውጤት ጋር ታሪኩ ተጽፎ ለትውልድ የሚተላለፍ መሆኑን ግን የሚጠፋው አይመስለኝም።

የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ንግግር በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር አዳመጥኩት። ፕሬዝዳንትዋ መልካም ሰው እንደሆኑ አንድ ጊዜ ቤተመንግስታቸው ጠርተውኝ ለሁለት ሰዓት ገደማ ያወራኋቸው ...
12/10/2023

የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ንግግር በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር አዳመጥኩት። ፕሬዝዳንትዋ መልካም ሰው እንደሆኑ አንድ ጊዜ ቤተመንግስታቸው ጠርተውኝ ለሁለት ሰዓት ገደማ ያወራኋቸው ጊዜ ተገንዝቤ ነበር። ሰው ሰው የሚሸቱ እንደሆነ ካጫወቱኝ ታሪካቸውና ከፈርጣማ አቋማቸው መረዳት ችዬም ነበር። ከዚህ ዘረኛና ደካማ አገዛዝ ጋር የሚቆዩ አይሆኑም የሚል ግምትም ነበረኝ። ግን አሁንም ድረስ አብረው አሉ። መኖር ብቻ አይደለም የአብይን ቲያትር እያዳመቁ ሲናገሩ ስሰማ ለእሳቸው ያለኝን ግምት መፈተሽ ጀምሬአለሁ።

በሰሞኑ ፓርላማ ላይ ያቀረቡት ሪፖርት ስለኢትዮጵያ መሆኑን እስክጠራጠር ድረስ አስገርሞኛል። እነአብይ አህመድ ደመና ውስጥ ተንሳፈው የሚኖሩ በመሆናቸው የሚናገሩትን ከቁምነገር የሚወስድ ያለ አይመስለኝም። እንደሳህለወርቅ አይነት የነቃ የበቃ career diplomat ጉም ሲዘግን መስማት ግን ያስደነግጣል። በቃ! ዋርካዎች ሁሉ እየተገነደሱብን አለቁ ማለት ነው? የአቢይን ማደንዘዢያ ''ምክክር ኮሚሽን'' ተስፋ አድርጉበት ሲሉ ትኩር ብዬ አየኋቸው። አምነውበት ነው የሚናገሩት ወይስ ተጽፎ የተሰጣቸውን?

የባህርዳር አቅራቢያ ከትላንት ጀምሮ እየሆነ ያለውን በትኩረት መከታተል ያስፈልጋል። በእርግጥ ታሪክ እየተሰራ ነው። ጢስ አባይ፥ ሰባታሚት፥ ባህርዳር ሆስፒታል፥ ፋኖ እየገፋ ነው።
12/10/2023

የባህርዳር አቅራቢያ ከትላንት ጀምሮ እየሆነ ያለውን በትኩረት መከታተል ያስፈልጋል። በእርግጥ ታሪክ እየተሰራ ነው። ጢስ አባይ፥ ሰባታሚት፥ ባህርዳር ሆስፒታል፥ ፋኖ እየገፋ ነው።

01/10/2023

ለወዳጅ ዘመዳችሁ ሼር አድርጉት
ዲቪ 2025 ቀኑ ይፋ ተደርጓል❗
DV 2025 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?
"""""""""""""'''''''''''''''""""""""""""""""""""""""""""
በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2025 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ
›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከመስከረም 23 እስከ ጥቅምት 27/2016 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።

›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦
እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም-

• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም
• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
•ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ ፎርም መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣ First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።

2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።

3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year ( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.

4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.

5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር

6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ

7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል * በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ ፣JPEG Format መሆን አለበት።

8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት

9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ

10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል

11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት

12. What is the highest level of education you have achieved, as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ

13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር ሁኔታ መምረጥ

14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።

»በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን DV-2025 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV

የሀገሬ ልጆች እንኳን አደረሳችሁ ።
27/09/2023

የሀገሬ ልጆች እንኳን አደረሳችሁ ።

26/09/2023

(በውስጥ መስመር ከደረሱኝ መልዕክቶች አንደኛውን እንደወረደ ነው ያካፈልኳችሁ)

አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 3 (በተለምዶ ዋናው ንግድ ባንክ) በር ላይ በእግረኛ መንገድ ስር ከተቀበረ ቱቦ ውስጥ የፊጥኝ ታስረው የታገቱ ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠናል። ከንግድ ባንኩ ፊት ለፊት የፖሊስ ጣቢያ ያለ ሲሆን ፖሊሶች ሌሊት ላይ ሰዎችን ከተለያዬ ቦታ እያፈኑ ቱቦው ውስጥ እንደሚከቱ ተረጋግጧል።

ATM የሚጠቀሙ ሰዎች "ውሃ ... ውሃ" የሚል ድምፅ ሰምተው የቱቦውን በር ሲከፍቱ በርካታ ሰዎች የፊጥኝ ታስረው ተመልክተዋል። የዓይን ምስክሩ "የተጎሳቆሉና ለሞት የሚያጣጥሩ እጅና እግራቸው የታሠሩ ሰዎችን አይቻለሁ፤ ውሃ ገዝተን ስናቀብል ፖሊስ መጥቶ አባረረን" ብሎኛል። ATM የሚጠቀሙ እናቶች እያለቀሱ ቢያንስ ምግብ እንስጣቸው ቢሉም ፖሊሶች እየደበደቡ በትነዋቸዋል።

25/09/2023

#ደብረታቦር

ከከተማው ዙሪያ (ሎሚዱር እና እብናት መውጫ) በደፈጣ በርካታ ወራሪ ተደምስሷል!

በደብረ ታቦርና ወረታ ከተሞች መካከል በምትገኘው #ወንጂ ቀበሌ የሚሊሻ አስተባባሪው ተሸኝቷል!!

ማዕከላዊ ጎንደር ዞን እንፍራዝ እና ቆላድባ ከተሞች በፋኖ ቁጥጥር ስር ሲሆኑ ባንዳዎች በሚገባ ጸድተዋል!

#ጎንደር

በከተማው የተለያዩ አካባቢዎች ማለት ማራኪ ፣ በቀራኒዮ መድኃኔዓለም ፣ ኮሌጅ 18፣ አይራ፣ አንገረብ፣ ስሆርሶ እና ስመክፉ ዛሬም ውጊያዎች እየተደረገ ነው!!

#ጋይንት

ጋይንት በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቷን ተከትሎ ወራሪው ኃይል ከሳሊ (ጎብጎብ) ወደ ጋይንት በእግር እየተጓዘ ነው፤ በዚህ ሰዓት መኳቢያን አልፎ ሀያ ውሀ ደርሷል!!

ጎንደር❗3ተኛ እና 6ተኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ ከተደረገ በኋላ በፋኖ ተሰብሮ እስረኞች እንዲለቀቁ አድርገዋል ተብሏል፣መጋዘናቸው ተሰብሮ መሳሪያ ተወስዷል። በተለይ 3ኛ ፖሊስ ጣቢ...
25/09/2023

ጎንደር❗
3ተኛ እና 6ተኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ ከተደረገ በኋላ በፋኖ ተሰብሮ እስረኞች እንዲለቀቁ አድርገዋል ተብሏል፣መጋዘናቸው ተሰብሮ መሳሪያ ተወስዷል። በተለይ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከፍተኛ ውጊያ ነበር ብለዋል።
መከላከያ ሰራዊት ቀራኒዮ መድሃኒዓለም አካባቢ ሆኖ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ነው ብለዋል። ከተማዋ አብዛኛው በፋኖ አባላት ቁጥጥር ስር ናት ብለዋል። የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ የለም ሲሉ ከጎንደር ነዋሪዎች በስልክ ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል። ህዝቡ ከቤት አልወጣም፣ድባቡ በጣም አሳዛኝ ነው ብለዋል።
ፋኖ ከከተማዋ ለመውጣት እንቅስቃሴም ጀምሯል ብለዋል በርካታ ሃላፊዎች በፋኖ ተገድለዋል ብለዋል፣ፓትሮል ሲያደርጉ የነበሩ አራት ፒካፕ ተቃጥለዋል።

25/09/2023

ፋኖ

21/09/2023

ኔትወርክ❗ #ቆቦ❗❗

በቆቦ የስልክ ኔትወርክ አገልግሎት ለሊቱን እንደተቋረጠ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል። የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚሉት እስከ ማታ አራት ሰዓት አካባቢ ድረስ ይሰራ እንደነበር ገልፀው አሁን ላይ አይሰራም ብለዋል። ዋግኸምራም በተመሳሳይ የስልክ አገልግሎት አይሰራም ብለዋል።
በቆቦ ከተማ ዙሪያውን ባሉ የገጠር ቀበሌዎች ከፍተኛ ውጥረት እንዳለም የመረጃ ምንጮችገልፀዋል።
ትናንት ከሰዓት ጀምሮ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም ዞን ቲሊሊ፣ደንበጫ እና ፍኖተሰላም ከሰዓት በኋላ የኔትወርክ አገልግሎት እንደተቋረጠ መዘገባችን ይታወሳል። ኔትወርክ በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ አስቸአስቸጋራ ሆኗል

ሥርዓት ወለዱ ረሃብ እየመጣ ነው!!?********እንቅልፍ ሊነሳን ይገባ የነበረው ይሄ ነበር። አምራቹን ጎጃም፣ መንዝ፣ ፎገራ፣ ራያ በጦርነት እያመሱት ነው። ትግራይ ደግሞ አዝመራ የለም። አ...
21/09/2023

ሥርዓት ወለዱ ረሃብ እየመጣ ነው!!?
********
እንቅልፍ ሊነሳን ይገባ የነበረው ይሄ ነበር። አምራቹን ጎጃም፣ መንዝ፣ ፎገራ፣ ራያ በጦርነት እያመሱት ነው። ትግራይ ደግሞ አዝመራ የለም። አንዳንድ ቦታ ላይ ደርቆ ቀርቷል። ሌላው ላይ ሳያፈራ የከብት መኖ ሆኗል። በቀጣይ አመት በርካታ ወገኖቻችንን በርሃብ እናጣለን። ይህ ግን ለገዥዎቹ ጉዳያቸው አይደለም።

አምራቹን በጦርነት እያመሱ፣ ትግራይም አዝመራ የላትም። ዋግኸምራ ተመሳሳይ ችግር አለ። ሰው ሰራሽ ርሃብም የተፈጥሮ ርሃብም የቀጣይ አደጋ ነው። ገዥዎቹ ለህዝብ ስለማያስቡ አይታያቸውም። ትግራይ ካለው ድርቅ ይልቅ አማራን ማውደምን ቅድሚያ ሰጥተዋል።
ጌታቸው ሽፈራው

አድርጉ

"የጦር ወንጀል"…በኢትዮጵያ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት እንዲኹም አኹን ድረስ በቀጠለው የአማራና የኦሮሚያ ክልሎች ግጭት ተፈጽመዋል የተባሉ ከባድ ወንጀሎችን በተመለከተ የቀረበውን ክስ የኢትዮጵያ ...
21/09/2023

"የጦር ወንጀል"…

በኢትዮጵያ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት እንዲኹም አኹን ድረስ በቀጠለው የአማራና የኦሮሚያ ክልሎች ግጭት ተፈጽመዋል የተባሉ ከባድ ወንጀሎችን በተመለከተ የቀረበውን ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ለመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ዛሬ ወይም ነገ ቀርበው እንደሚከላከሉ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ ያቋቋመው የባለሙያዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን የምርመራ ግኝቱን ሰኞ'ለት ለሕዝብ ይፋ ያደረገ ሲኾን፣ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትም በሪፖርቱ ላይ ነገ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

ሪፖርቱ በኢትዮጵያ “የጦር ወንጀል”፣ “በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል” እና ግፎች እንደተፈጸሙ የሚያመለክት መረጃ አግኝቻለኹ ብሏል።

ኮሚሽኑ፣ የመብት ጥሰቶቹ በዓለማቀፍ መርማሪ እንዲጣሩም ጥሪ ማቅረብ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት መርማሪ ኮሚሽኑ እንዲበተን ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል።
አድርጉ ።

21/09/2023

ህፃናት እና አረጋዊያን ጭምር ማቆያ ካምፕ ገብተዋል:-ኢሰመኮ❗❗
| የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ ማዕከል ህጻናትና አረጋዊያን ሳይቀር እንደሚገኙ ገለጸ፡፡

በማቆያ ማእከሉ የሚገኙት ሰዎች ውሎ እና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎች ሲሆኑ፤ አረጋውያን፣ ሕፃናት፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችም ይገኙበታል።

በዚህ ማቆያ ማዕከል ዉስጥ በሺዎች የሚገመቱ ሰዎች ይገኙ እንደነበርና ኮሚሽኑ ክትትል ያደረገበትን ጊዜ ተከትሎ እና በዚህ ሪፖርት ዝግጅት ወቅት ቁጥሩ ከግማሽ በላይ ቀንሶ በመቶዎች የሚገመቱ ሰዎች መኖራቸውን ለመረዳት ተችሏል ነዉ ያለዉ፡፡

በተጨማሪም የተሟላ መሠረተ ልማት የሌለውና ለተፈለገበት ዓላማ ምቹ ባለመሆኑ በጣቢያው የሚገኙ ሰዎችን ሰብአዊ ክብር የጠበቀ አያያዝ አስቸጋሪ አድርጎታል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መስከረም 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በአብዛኛው ውሎ እና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎች ከጎዳና ላይ ተነስተው እንዲቆዩ የሚደረግበት በሸገር ከተማ፣ በተለምዶ “ሲዳሞ አዋሽ” በመባል የሚታወቅ አካባቢ የሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ ማዕከል/ቦታን በመጎብኘት እና ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን መግለጹ የሚታወስ ነው።

በተጨማሪም በአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናት እና ማኅበራዊ ቢሮ ሥር የሚተዳደሩ ማዕከላትን/ቦታዎችን በመጎብኘት እና ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል፡፡

ኢሰመኮ ነሐሴ 24 እንዲሁም በጳጉሜን 2 እና 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በዚህ ማቆያ ማዕከል/ቦታ ባደረገው ጉብኝት እንዲሁም፣ በማቆያ ማዕከሉ የሚገኙ ሰዎችን እና የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮን ጨምሮ የሚመለከታቸውን የመንግሥት የጸጥታ አካላት በማነጋገር ክትትል ማካሄዱን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም የማቆያ ማዕከሉ አስተባባሪዎች እና ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን፣ በቦታው የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ የሕክምና ባለሞያዎችን እና ተጨማሪ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኝ የነበረውን የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ኃላፊዎችን እና ባለሞያዎችን በማነጋገር ስለጉዳዩ አስፈላጊ መረጃና ማስረጃዎችን ማሰባሰቡን ነዉ ያስታወቀዉ፡፡

እነዚህ በተለያየ ጊዜ ወደ ማዕከሉ እንዲመጡ የተደረጉ ሰዎች ብዛት በየጊዜው ተለዋዋጭ ሲሆን፣ በሺዎች የሚገመቱ ሰዎች በማቆያ ማዕከሉ ውስጥ ይገኙ እንደነበርና ኮሚሽኑ ክትትል ያደረገበትን ጊዜ ተከትሎ እና በዚህ ሪፖርት ዝግጅት ወቅት ቁጥሩ ከግማሽ በላይ ቀንሶ በመቶዎች የሚገመቱ ሰዎች መኖራቸውን ለመረዳት መቻሉን ነዉ ኮሚሽኑ የገለጸዉ፡፡

ይሁን እንጂ የማቆያ ማዕከሉ አስተባባሪዎች ለኮሚሽኑ እንዳስረዱት የጊዜያዊ ማዕከሉ ዋነኛ ዓላማ ከጎዳና ላይ እንዲነሱ የተደረጉትን ሰዎች በመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም በማገዝ ወደ መጡባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ እና ከጎዳና ላይ ውሎና አዳር እንዲወጡ ማድረግ መሆኑን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በማዕከሉ ከሚገኙት ሰዎች ውስጥ 29 በቀን ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች፣ የጥበቃ እና የግንባታ ሠራተኞች እንዲሁም ሴቶችና ሕፃናት ጳጉሜን 3 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዲለቀቁ እንደተደረገ የማዕከሉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል።

በማቆያ ማዕከሉ ለሚገኙ ሰዎች ምግብ በቀን 3 ጊዜ እና የመጠጥ ውሃ የሚቀርብ ሲሆን፤ በአንጻሩ ይህ ጊዜያዊ ማቆያ ማእከል ለሰዎች መጠለያ ወይም ማቆያ ተብሎ የተዘጋጀና የተደራጀ ሳይሆን፤ ለኢንዱስትሪ ዕቃዎች ማከማቻ ተዘጋጅቶ የነበረ ስፍራ በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያነት እንዲያገለግል የተደረገ ነው።

በዚህም ኮሚሽኑ ከተመለከታቸዉ ጉድለቶች መካከል የተሟላ የንጽሕና ቤቶች አለመኖራቸው እንዲሁም ለግል ንጽሕና መጠበቂያ የሚሆን የውሃና የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት፣ የመኝታ አልጋ፣ ፍራሽና አልባሳት አለመኖራቸው፣ ለማደሪያ የተዘጋጀው ቦታ በቂ አየርና የፀሐይ ብርሃን የማያገኝ መሆኑ እና ከፍተኛ የንጽሕና ጉድለት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

በማቆያ ማዕከሉ በቅርቡ በተባይ የሚተላለፍ ሕመም መከሰቱን ተከትሎ በመጠለያ ጣቢያው ከነበሩ ሰዎች መካከል 190 ሰዎች በሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት ያገኙ መሆኑን እና ክትትሉ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ የ3 ሰዎች ሕይወት ያለፈ መሆኑን እና 3 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ሕክምና እያገኙ እንደነበር ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል በተገኘ መረጃ ማወቅ ተችሏል።

ኢሰመኮ ሚያዝያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት እንዲሁም በመዲናዋ የሚደረጉ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ጉባኤዎች እና ሌሎች ተመሳሳይ ኹነቶች ጋር በተያያዘ በርካታ በጎዳና ላይ ያሉ ሰዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በኃይል ከጎዳና ላይ እንዲነሱ በማድረግ በአንድ ስፍራ እንዲቆዩ የሚደረጉበትን ሁኔታ በተመለከተ የክትትል ውጤቱን ይፋ ያደረገ መሆኑ የሚታወስ ነው።

ሰዎችን በግዳጅ ወደ አንድ ማቆያ ማዕከል/ቦታ ማስገባት ወይም ለኑሮ ከመረጡት ቦታ ወደማይፈልጉበት አካባቢ እንዲሄዱ ማስገደድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሚያስከትል በመሆኑ፤ ይህ አስገዳጅ አሠራር በአስቸኳይ እንዲቆም በማድረግ በጎዳና ላይ ያሉ ሰዎችን ከጎዳና ላይ ማንሳትና ተገቢ አገልግሎቶችን መስጠት በፈቃደኝነትና አስፈላጊ ሁኔታዎችን ሁሉ በማመቻቸት ሊተገበር የሚገባ በመሆኑ በአስቸኳይ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መሀከል የተፈጠረዉ ግጭት ተጧጢፎ ቀጥሏል ።
20/09/2023

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መሀከል የተፈጠረዉ ግጭት ተጧጢፎ ቀጥሏል ።

በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠውን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገቡ‼️በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠውን ፈተና የሚወስዱ ከ11 ሺህ 581 በላይ ተማሪዎችን በተረጋጋ መ...
20/09/2023

በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠውን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገቡ‼️

በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠውን ፈተና የሚወስዱ ከ11 ሺህ 581 በላይ ተማሪዎችን በተረጋጋ መልኩ ለማስፈተን ዝግጅት ማድረጉን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገለጸ፡፡የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ዳንኤል ውበት 3 ሺህ 134 ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች መኖራቸውን ገልጸዋል። ለተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ክንዱ ዘውዱ ተማሪዎች ዝግጅት እንዲያደርጉ ቀደም ብሎ መሠራቱን ገልጸዋል። ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚጓዙበት ወቅት የመጓጓዣ ኹኔታ ምቹ እንዲኾን መሠራቱንም አመላክተዋል። በዞኑ 6 ሺህ 119 ተፈታኝ ተማሪዎች መኖራቸውን ኀላፊው አንስተዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአሥተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ልጅዓለም ጋሻው በሶስት ዞኖችና በጎንደር ከተማ የሚገኙ ከ11 ሺህ 581 በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንዲያጠናቅቁ ዩኒቨርሲቲው በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጸል ሲል አሚኮ ዘግቧል።ተፈታኝ ተማሪዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተናቸውን ማጠናቀቅ አለመቻላቸውን በማስታወስ በአሁኑ ወቅት ፈተናውን ለመውሰድ ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

 #ጅቦች መብታችን ማስከበር አለብን በማለት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ መሰረቱ ።  #ጅቦቹም ''ቆይ እኛ በዚህች አገር ስንኖር መድሎ ለምን ይፈጸምብናል ? ከአንበሳ እኩል እየታየን አይደለም!'...
20/09/2023

#ጅቦች መብታችን ማስከበር አለብን በማለት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ መሰረቱ ። #ጅቦቹም ''ቆይ እኛ በዚህች አገር ስንኖር መድሎ ለምን ይፈጸምብናል ? ከአንበሳ እኩል እየታየን አይደለም!'' በማለት አቤቱታቸውን ለዳኛው ያቀርባሉ ፡፡

#ዳኛውም በመገረም ''ቆይ በዚህች አገር እናንተ ከአንበሳ የተለየ ምን በደል ደረሰባችሁ ? ለአንበሳስ ምን የተለየ እንክብካቤ ተደረገለት ?'' በማለት ይጠይቃሉ ። #ጅቦቹም ''የተከበሩ ዳኛ በዚህች አገር ውስጥ በአንበሳ ስም ስንት ነገሮች ተሰይመዋል ።

ለምሳሌ ብናይ አንበሳ ባንክ ፣ አንበሳ ኢንሹራንስ ፣ አንበሳ ሻይ ፣ አንበሳ አውቶብስ ከጫማ እንኳ ሳይቀር አንበሳ ጫማ አለ ። እስኪ በእኛ ስም የተሰየመ ነገር ይጥሩልኝ ?'' አሏቸው ። በንዴት ዳኛውም በጅብ ስም የተሰየመ ነገር ባለመኖሩ ተገርሞ እውነትም በደል ደርሶባቹሃል ስለዚህ ምን ምን በስማችሁ እንዲሰየምላችሁ ትሻላችሁ በማለት ይጠይቃሉ ፡፡

#ጅቦቹም ትንሽ አሰላሰሉና ጅብ ማዘጋጃ ፣ ጅብ ጉሙሩክ ፣ጅብ ቀበሌ፣ጅብ መሬት አስተዳደር፣ ጅብ ትራፊክ፣ ጅብ ቴሌ ተብሎ እንዲሰየምልን እንፈልጋለን ። ክቡር ዳኛ እንዲያው ቅር ካልተሰኙ ምን አለ እናንተስ በእኛ በጅቦች ስም ብትሰየሙ.."ጅብ ዳኛ"..... አሉ ይባላል። ቅኔ እንዳይመስላችሁ ደሞ!! #ሼርር ብቻ አድርጉልኝ🙏


19/09/2023

ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ይሄንን ብሏል
👇 👇

የትራፊክ አደጋ***************ዛሬ  ከሆሣዕና ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ላይ እያሉ ሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመኪና አደጋ የሆሣዕናሬከተማ እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን መሪ እና አገልጋ...
19/09/2023

የትራፊክ አደጋ
***************

ዛሬ ከሆሣዕና ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ላይ እያሉ ሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመኪና አደጋ የሆሣዕናሬከተማ እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን መሪ እና አገልጋይ የሆኑ ዮናስ ዱባለ እና አብረውት ከነበሩት ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ህይወታቸው አልፏል።

በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 4ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሶዶ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሶዶ ወረዳ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ፍሰት ቁጥጥር ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋና ሳጅን አማረ ታከለ እንዳሉት በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12:00 ሰአት ላይ የህዝብ ማመላለሻ FSR የሰሌዳ ቁጥር ደቡብ 13955 የሆነ 49 ሰዎችን ጭኖ ከአዲስ አበባ እየመጣ ከሆስአና ወደ አዲስ አበባ የሚሄድ የሰሌዳ ቁጥሩ B-20669 ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመጋጨት የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 4ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ገልፀዋል፡፡

ዋና ሳጅን ጨምረው እንዳብራሩት አደጋው የተከሰተበት ሰአት የአየር ንብረቱ ጭጋጋማ በመሆኑ እንዲሁም አደጋ የደረሰበት አካባቢ መንገዱ ብልሽት ያለበት በመሆኑ በየጊዜው አደጋ እንደሚደርስና በተደጋጋሚ በትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት የሚቀጥፍና ከፍተኛ የንብረት ውድመት የሚያስከትል በመሆኑ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት በላይ ባለማሽከርከር ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የዘገበው የሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለቤተሰቡ፣ ለቤተክርስቲያን ምእመን፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።
😭😭😭😭

19/09/2023

ደብረማርቆስ❗
በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ አሁን ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እየተሰማ ይገኛል። በርካታ የፋኖ አባላት ወደ ከተማዋ እየገቡ በመሆኑ ተኩሱ ከባድ ነው ብለዋል።

ጋይንት❗በደቡብ ጎንደር ጋይንት ዛሬ ከንጋት ጀምሮ በመከላከያ እና በፋኖ መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው።ውጊያው ከከተማ ወጣ ብሎ ሽጥ በሚባል አካባቢ ታች ጋይንት መስመር ላይ እየተካሄ...
19/09/2023

ጋይንት❗
በደቡብ ጎንደር ጋይንት ዛሬ ከንጋት ጀምሮ በመከላከያ እና በፋኖ መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው።
ውጊያው ከከተማ ወጣ ብሎ ሽጥ በሚባል አካባቢ ታች ጋይንት መስመር ላይ እየተካሄደ ነዉ ተብሏል ።
መረጃዎቻችንን በማድረግ አድርሱልን ።

ትናት በምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ ላይ ምንም የማያቁ የአማራን ልጆች ፋኖን ትረዳላችሁ ብሎ የኦሮሚያ ክልል ልዮ ሀይል የፊጥኝ እመኪና ላይ አስሮ እየደበደበ አይለመደን በሉ እያለ ከተማዋን ...
19/09/2023

ትናት በምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ ላይ ምንም የማያቁ የአማራን ልጆች ፋኖን ትረዳላችሁ ብሎ የኦሮሚያ ክልል ልዮ ሀይል የፊጥኝ እመኪና ላይ አስሮ እየደበደበ አይለመደን በሉ እያለ ከተማዋን ሁሉ ሲያዞራቸው የዋሉት አማሮች እነዚህ ናቸው። ለሰርቶ ማሳያ የተሰራን እንጨት አሸክሞ የነቀምት ከተማን ህዝብ ሰብስቦ አማሮች እየተባሉ እፊታቸው ላይ ምራቅ ሲተፋባቸው ያየ አንድ መምህር ቀድሞ ነበር መረጃውን የሰጠኝ። ልጆቹን ለመረሸን ሲሞክሩ አይሆንም ፎቷቸው ስለተያዘ እሚዲያ ላይ መረጃው ሊወጣ ይችላል ብለው ነው የተዋቸው። በተያያዘ ዜና ሻንብ ላይ የኦሮሚያ ልዮ ሀይል ህዝቡና ሽማግሌዎችን ሰብስቦ ከቱሉ ጋና እስከ ወባንጭ ድረስ ያለውን አማራ ለማፅዳት ሲመክር ውሏል። ወለጋ ላይ ያለው ደመና በህዝባችን ላይ ዳግም ሊወርድ ደም የለመደው አጉሪው ሀይል እያጉረመረመ ይገኛል። አብይ አህመድ እጅግ አደገኛ በሆነ መንገድ ይሄንን ህዝብ ሊያስጨፈጭፈው ጀሌዎቹን ልኮ እያዘጋጃቸው ነው።ከሦስት ቀን በፊት አውራ ጎዳናን መከላከያ ተብየው አማራን አፅድቶና ዘርፎ ( ገድሎ) ካለስቀቀ ቡኋላ ለኦሆዴድ አስረክቧል። 5ሺ አባወራዎችን አፈናቅለው 31 ንፁሀንን ጨፍጭፈው ነው ነው አውራ ጎዳናን ከአማራ አስለቅቀው ለኦሆዴድ ያስረከቧት። የተጀመረው ትግል እየተቀጣጠለ በሚኒሊክ ቤተ መንግስት የተቀመጠውን አሸባሪ ቡድን ማፍረክረክ ሲጀምረው መደበቂያውን ኦሮሞን ከአማራ ማጨፋጨፍ እንደሚሆን ቀድሞ የታወቀ ቢሆንም ማለቅ ካለብን ጠቅላላ እናልቃታለን እንጅ በቀላሉ እንደማንለቃቸው ያቃሉ። ይሄ ስረአት እጅግ በደም የተጨማለቀ ማወቅ የለለው በጦርነት መኖር የሚፈልግ ስረአት እንደሆነ እነ አሜሪካ ቀድመው ተናግረዋል።
Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ
ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-

19/09/2023

በምንጃር አውራ ጎዳና ቤት ለቤት ግድያ እየተካሄደ ነው። የፌደራልና የክልል ሃይሎች በጥምረት በከፈቱት ኦፕሬሽን ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በስፋት በመካሄድ ላይ ነው። አንድ የአውራ ጎዳና ነዋሪ በስልክ ''የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ በመሆኑ ዓለም ይስማልን'' ብለውኛል። የኦሮሚያ ብልጽግና ፋኖ ሰብሮ የጅቡቲ- አዲስ አበባን ዋና መንገድ ይዘጋል በሚል ስጋት አውራ ጎዳና የተሰኝችውን በአማራ ክልል ስር የምትገኝን ከተማ ወርሯል። የኦሮሚያ ልዩ ሃይል በመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ወረራውን ሰላማዊ ነዋሪዎችን በመጨፍጨፍ እየመራው ነው። ማንኛውም ነፍስ ያለው ነገርን ይገድላሉ አሉኝ ነዋሪው።

ማነህ 'የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ፈርሷል' ብለህ ለብልጽግና ስርዓት ሽንጥህን ገትረህ የሞገትከው የቀድሞ ተቃውሚ ፓርቲ አመራር እባክህን አውራ ጎዳና ስልክ ደውለህ ጉድህን ስማው!

ታሪክ ይፈርዳል። ይህም የህዝብ ዕልቂት ይመዝገብ!

Bravery is from the seed💪ፍኖ💪Today best photo
18/09/2023

Bravery is from the seed💪
ፍኖ💪
Today best photo








18/09/2023

በአማራ ክልል ግጭት ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች መታሰራቸውንና ከ200 በላይ መገደላቸውን ተመድ አስታወቀ

ዮሐንስ አንበርብር

* ሁሉም ጥሰቶች ተመርምረው ተጠያቂነት መረጋገጥ አለበት ብሏል

* መርማሪ ቦርዱ በበኩሉ የታሰሩ ሰዎች ብዛት 764 ነው ብሏል

| በአማራ ክልል በተፈጠረው ግጭትና ግጭቱን ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን፣ እንዲሁም ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታወቁ፡፡

የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ ሰሞኑን በተጀመረው የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባዔ ላይ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን የተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ በዚህም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እየተፈጸመባቸው ናቸው ያሏቸውን አገሮች በመጥቀስ ዋና ዋና ጥሰቶቹንም ዘርዝረዋል። ኮሚሽነሩ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ረገድ በአሳሳቢነት ከጠቀሷቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ፓኪስታን፣ ሊቢያ፣ ሊባኖስ፣ ቱኒዚያና ፔሩ ይገኙበታል።

በአማራ ክልል በፌዴራል መንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሰው የፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ከደረሷቸው ሪፖርቶች መረዳታቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። ግጭቱን ለመግታት የፌዴራል መንግሥት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከጣለ ጀምሮም ከ1,000 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል በቀጠለው ግጭት ሳቢያም ግድያ፣ እንግልትና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መኖራቸውን ገልጸዋል። በትግራይ ክልልም እንዲሁ የጅምላ እስራትና አስገድዶ የማፈናቀል ተግባራት መኖራቸውን፣ ይህ ችግር በተለይም በኤርትራና በአማራ ኃይሎች ተይዘዋል በሚባሉ አካባቢዎች ጎልቶ እንደሚታይ ጠቅሰዋል።

እነዚህ ሁሉ ክስተቶች ተመርምረው ጥሰቶቹን የፈጸሙ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ማድረግ ይገባልም ብለዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተፈጸሙ ሰብዓዊ ጥሰቶችን በተመለከተ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በአገሪቱ መንግሥት የታቀደውን የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ ለማድረግ፣ በተጀመሩ ምክክሮች ውስጥ የተገኘውን ዕድገት ዕውቅና ሰጥተዋል። የሽግግር ፍትሕንና ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚያበረታቱ የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ የተጀመረው ምክክር እንዲጎለብት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ሴቶችን ጨምሮ ቀጣይ ውይይት እንዲደረግበት አሳስበዋል።

በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ለመቆጣጠር ተብሎ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲከታተል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚ በሆነባቸው አምስት ማዕከላት ብቻ 764 ሰዎች ተጠርጥረው በሕግ ቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ አስታውቋል።

የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ አዝመራ አንዴሞ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም በተቋቋመው ዕዝ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች የሚገኙባቸውን ማቆያ ጣቢያዎች መርማሪ ቦርዱ መጎብኘቱን ገልጸዋል።

በዚህም በሸዋሮቢት፣ በጎንደር፣ በኮምቦልቻ፣ በባህር ዳር፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ (በኋላ ላይ አዋሽ አርባ የተዘዋወሩ) የመስክ ምልከታ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ መልካም የሰብዓዊ አያያዝ እየተደረገላቸው መሆኑን መታዘባቸውንና ይህንንም ከተያዙት ሰዎች ማረጋገጣቸውን አስረድተዋል፡፡

አክለውም ቦርዱ ምልከታ ባደረገባቸው አምስት ማዕከላት ብቻ 764 ተጠርጣሪዎች በሕ

አማራ በመሆኔ እኮራለሁ 🙏ድል ለጭቁኑ የአማራ ህዝብ 💪💪💪💪
17/09/2023

አማራ በመሆኔ እኮራለሁ 🙏
ድል ለጭቁኑ የአማራ ህዝብ 💪💪💪💪

እዩት ሲዉለበለብ ግርማና ሞገሱንበፍቅር ነግሶበት የሰማይ አድማሱን ።  !!
17/09/2023

እዩት ሲዉለበለብ ግርማና ሞገሱን
በፍቅር ነግሶበት የሰማይ አድማሱን ።
!!

ከላይ የተሰጠች የሰማይ መቀነትይቺ ናት ባንዲራ የኢትዮጵያ ማንነት !!የሚዋደቅላት አማራዉ ተራራዉየታመነ ትንታግ ፅኑ ነዉ ላደራዉ !!
17/09/2023

ከላይ የተሰጠች የሰማይ መቀነት
ይቺ ናት ባንዲራ የኢትዮጵያ ማንነት !!
የሚዋደቅላት አማራዉ ተራራዉ
የታመነ ትንታግ ፅኑ ነዉ ላደራዉ !!

16/09/2023

ትናንት ከወያኔ ጋር ተዋግቶ ደሙን አፍሶ የወያኔ ወረራን የቀለበሰው እና የአምባገነኑን አገዛዝ እድሜ ያረዘመው የአማራ ሚሊሻና ፖሊስ፣ ዛሬም የፋሽስቱን አገዛዝ እድሜ ለማራዘም ከራሱ ወንድሞች ጋር ይዋጋል ብሎ መጠበቅ እብደት ነው። (አንዳንዶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እየተሳተፉ መሆኑ ቢታወቅም) አገዛዙ በስህተት እያዋጋቸው መሆኑን የተረዱ ቀን ያስታጠቃቸው መሳሪያ እና ጥይት ወደ እሱ ማዞራቸው አይቀርም።

ከዚህ ውጭ ያለውን የጥፋት መንገድ እከተላለሁ የሚል ሚሊሻና ፖሊስ ስልጠና ሳይሆን አማኑኤል መላክ የነበረበት ነው። አገዛዙን ተማምኜ እገጥማለሁ የሚል ካለ የፋኖን በትር ይቀምሳል።

አሁን ባለው በብዙው የአማራ አካባቢ ግን ሚኒሻው እና ፖሊሱ ይሄንን አልቀበልም ብሏል።

ድል ለአማራ

ትላንት በአዳማው የብልፅግና ስብሰባ ላይ “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ክልል እየገባ ነው!” የሚል ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ሲደረግበት ውሏል። በተጨማሪOMN ጨምሮ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ክ...
16/09/2023

ትላንት በአዳማው የብልፅግና ስብሰባ ላይ “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ክልል እየገባ ነው!” የሚል ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ሲደረግበት ውሏል። በተጨማሪOMN ጨምሮ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት በንፁሃን ላይ ጥቃት እንደፈፀመ ተደርጎ እየተዘገበ ነው።

እውነታው ፋኖ እስካሁን ከክልሉ አንድ ኢንች ወደ ሌሎች ክልሎች ለመግባት እንዳልሞከረ ቢታወቅም "ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ንፁሃንን እየጨፈጨፈ ነው" በሚል በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የጂኖሳይድ ጥሪ እያስተላለፉ ነው።
ጥንቃቄ ይደረግ! ሼርርርርርር በማድረግ ለብዙ ሰው አድርሱ

15/09/2023
15/09/2023
አማራራራራራራራራራ👇ይህ ቱሉ ዲምቱ ነው:: ከአዲስ አበባ በጥቂት ኪሎሜትሮች የሚርቅ ከተማ:: የአማራ ተወላጆች የሰቆቃ ማዕከል:: አንድ የጤና ባለሙያ እንዳጫወተኝ በተላላፊ በሽታና በረሃብ ቅ...
15/09/2023

አማራራራራራራራራራ👇
ይህ ቱሉ ዲምቱ ነው:: ከአዲስ አበባ በጥቂት ኪሎሜትሮች የሚርቅ ከተማ:: የአማራ ተወላጆች የሰቆቃ ማዕከል:: አንድ የጤና ባለሙያ እንዳጫወተኝ በተላላፊ በሽታና በረሃብ ቅጣት 350 በላይ የአማራ ተወላጆች ሞተዋል:: ሁኔታውን ሲገልፀው"በህይወቴ ራሴን የጠላሁበት ዘመን" በማለት ነው::

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረሃይል መግለጫ ይሰጣል "የተያዙትን በባለ 5ኮከብ ሆቴል ውስጥ እየተንከባከብናቸው ነው:: ምቾት ሊገላቸው ነው::"

አብይ አህመድ መልዕክት አስተላልፏል "በሊቢያ በጎርፍ አደጋ ለሞቱት ልቤ ተሰብሯል:: መፅናናትን እመኛለሁ"

ዓለም ዝም ብሏል!!! እኛ ግን ዓለም ይህንን ጉድ እንዲያየው ለብዙ ሰው እንዲደር ሼር ብቻ አድርጉት🙏

 #ነእፓየነእፓ ሊቀመንበር ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ፃፉ።የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም የአዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህ...
11/09/2023

#ነእፓ

የነእፓ ሊቀመንበር ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ፃፉ።

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም የአዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግልፅ ደብዳቤ ፃፉ።

በዚህ ደብዳቤያቸው እየተጠናቀቀ ባለው 2015 ዓመት እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በሀገራችን ስለነበሩ የሰላም እና ጸጥታ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮች በወፍ በረር በመዳሰስ ችግሮቹ ወደ አዲሱ አመት እንዳይሸጋገሩ አሉኝ ያሉትን የመፍትሄ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅፈውላቸዋል።

ከደብዳቤያቸው የወሰድነው ፦

" ለአብዛኛው የሀገራችን ህዝብ ኑሮ እጅግ ከብዷል።

ሰፊው ህዝባችን ጦም እያደረ የፖለቲካ ስልጣን የያዙ እና በነሱ ጉያ ስር የተወሸቁ ጥቂቶች እጅግ የተንደላቀቀ ህይወት የሚኖሩበት አስጊ ሁኔታ ተፈጥሯል።

የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ፓርቲዎ እና መንግስትዎ እናሳካለን ብለው ለህዝብ ከሚነግሩት እውነተኛ የብልጽግና ጉዞ እየተለየ መጥቷል።

ለም መሬት እና ለሌሎች የሚተርፍ ወንዞች ያላት ሀገራችን ለበርካታ ልጆቿ የቀን ጉርስ ማቅረብ ተስኗታል።

በቅዱሳን መጽሀፍት የሰላም እና የፍትህ ምድር በመባል የምትታወቀው ሀገር ሰላም እና ፍትህ ርቋታል።

ለዓለም ተምሳሌት የሚሆን የአብሮነት እና የመተሳሰብ ባህል የነበራቸው ባለ ብዙ ቀለም ህዝቦች በመካከላቸው መተማመን ቀንሶ እርስ በርስ እየተጠራጠሩ መኖር ጀምረዋል።

በዜጎች ፊት ደስታ እና ተስፋ እየራቀ መጥቷል፣ ስጋት በኢትዮጵያ ሰማይ ነግሷል። ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ልንሸፋፍናቸው ከማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

እንደ ሀገር የገጠሙንን ችግሮች በቅንነት፣ ከፖለቲካ ርእዮት እና ወገንተኝነት ወጥተን በሀገር ልጅነት ስሜት ተወያይተን እና ተጋግዘን ለመፍታት ጊዜ እና ታሪክ አንድ ተጨማሪ እድል ሰጥቶናል።

2015 ተገባዶ አዲስ አመት ለመቀበል ቀናት በቀሩበት ወቅት፣ ሁላችንም ያለፉ ስኬቶቻችንን እና ስህተቶቻችንን ቆም ብለን ልናስተውል ይገባል።

2015ን አገባደን አዲስ ዘመን ለመቀበል እየተሰናዳን ባለንበት ወቅት፣ በተለይም ባለፉት አምስት አመታት በሀገራችን የተከሰቱ እጅግ አውዳሚ ጦርነቶች እና ግጭቶች ቆመው ሰላም የሰፈነባት ሀገር ለመፍጠር ሁላችንም ቃል ልንገባ ይገባል። ይህን አለማድረግ ሁላችንንም በታሪክ ተጠያቂ ያደርገናል።

ሀገራችን ካለችበት ውስብስብ ቀውስ እንድትላቀቅ፣ ህዝባችንም ሰቅፎ ከያዘው ዘርፈ ብዙ ችግር እንዲላቀቅ ማድረግ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ቢሆንም፣ #የመንግስት ድርሻ ከፍተኛ ነው።

በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት ሀገራችን ካለችበት ችግር እንድትላቀቅ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ያለባቸው ሲሆን፣ የመንግስት የአስፈጻሚ አካል መሪ በመሆን የእርስዎ የግል ኃላፊነት እና ተነሳሽነት እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ በታላቅ ትህትና እና ወንድማዊ ስሜት ላስታውሶት እወዳለሁ። "

ቱርክ በማጭበርበር ወንጀል የተከሰሰውን ግለሰብ በ11 ሺህ 196 ዓመት እስራት ቀጣችየክሪፕቶ ከረንሲ ድርጅት አለቃ የሆነው ተከሳሹ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ይዞ መሰወሩ ተነግሯልቱር...
11/09/2023

ቱርክ በማጭበርበር ወንጀል የተከሰሰውን ግለሰብ በ11 ሺህ 196 ዓመት እስራት ቀጣች
የክሪፕቶ ከረንሲ ድርጅት አለቃ የሆነው ተከሳሹ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ይዞ መሰወሩ ተነግሯል
ቱርክ የምናባዊ ገንዘብ (ክሪፕቶ ከረንሲ) አለቃ የነበረውን ግለሰብ መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾችን ሚሊዮን ዶላሮችን አጭበርብሯል በሚል በ11 ሺህ 196 ዓመት እስራት በይናለች።
ፋሩክ ኦዘር የተባለው የ29 ዓመት ወጣት በ2021 "ቶዶክስ ኤክስቼንጅ" የተባለ ድርጅቱ ሲከስር የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾችን ገንዘብ ይዞ ወደ አልቤንያ መሸሹ ተነግሯል።
በወቅቱ ተከሳሹ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የተገመተ እሴት ይዞ እንደተሰወረ የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በሰኔ ወር ለቱርክ ተላልፎ የተሰጠው ኦዘር፤ ህገ ወጥ ገንዘብን ህዊ ለማስመሰል በመሞከር፣ በማጭበርበርና በተደራጀ ወንጀል መከሰሱ ተገልጿል።
በኢስታንቡል የዋለው ችሎት እህትና ወንድሙንም በተመሳሳይ ወንጀል ጥፋተኛ ብሏል።
የቱርክ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች እንደዘገቡት ተከሳሾቹ ለየብቻ በበርካታ ወንጀሎች ብይን የተሰጣቸው ሲሆን፤ ከሁለት ሽህ በላይ ሰዎችን አጭበርብረዋል ተብሏል።
በዚህም ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በ11 ሽህ 196 ዓመት በእስራት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸዋል።
በቱርክ የሞት ፍርድ በ2004 ከተነሳ በኋል እንዲህ አይነት ረጅም ብይኖች የተለመዱ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
አንካራ ለተዳከመው ገንዘቧ መከላከያ ይሆን ዘንድ ክሪፕቶ ከረንሲን መጠቀም ጀምራለች።
ቶዶክስ በ2017 ተመስርቶ በሀገሪቱ ግዙፍ የምናባዊ ገንዘብ መለዋወጫ ለመሆን በቅቷል።

11/09/2023

አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ሥጋት ደቅኗል ተባለ‼️
በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ ወታደራዊ ኃይል (አትሚስ) በፈረንጆች 2024 ሙሉ ለሙሉ ከሶማሊያ ለቆ ሊወጣ በመሆኑ አልሸባብ ለኢትዮጵያ ስጋት ሆኗል ሲል ዓለም አቀፍ ጥናትና ትንታኔዎች በመስራት የሚታወቀው ዘጀምስ ታውን ፋውንዴሽን ባወጣው ዘገባ ገልጿል።

ይህም የሽብር ቡድኑ ከሶማሊያ ጋር ረዥም ድንበር የምትዋሰነውን ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ዓመታት ረጅም የሆነ ግጭት ዉስጥ ሊያስገባት እንደሚችል ጠቁሟል።

አልሸባብ ከፈረንጆች 2006 እስከ 2009 በሶማሊያ ባደረገው ወረራ ይዞት ከነበረው በሞቃዲሾ የሚገኘው እስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት ከስልጣን እንዲወርድ መደረጉን ተከትሎ፤ በኢትዮጵያ ላይ ሰፊ ቅሬታ እንዳለውም ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ ለ15 ዓመታት በሶማሊያ በቆየው የአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ኃይል ውስጥ ትልቅ ተሳትፎ የነበራት መሆኑን እና በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ እንዲሳካ ቁልፍ ሚና መጫዎቷምን ዘገባው ገልጿል።

አልሸባብ ለኹለት አስርት ዓመታት በሶማሊያ እያደረሰ ባለው ጥቃት ኢትዮጵያ የምትጫወተው ሚና የአልሸባብ የረጅም ጊዜ ዒላማ እንድትሆን አድርጓታል የተባለ ሲሆን፤ ታጣቂ ቡድኑ በኢትዮጵያ ላይ ያለው ጥላቻ እየጨመረ የመጣ ይመስላልም ነው የተባለው።

የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ ኃይል (አትሚስ) ባለፈው ሰኔ ወር ከ22 ሺሕ ወታደሮች መካከል 2 ሺሕ የሚሆኑትን ከሶማሊያ ያስወጣ ሲሆን፤ በመጪው መስከረም ወር 3 ሺሕ ወታደሮችን ሙሉ ለሙሉ ለማስወጣት ማቀዱን አመላክቷል።

ምንም እንኳን የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ ኃይል ዋነኛ ዓላማ የሶማሊያን ደህንነት በማረጋጋት ኃላፊነቱን ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ማስተላለፍ ቢሆንም፤ የአልሸባብ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በአትሚስ ካላት ወታደራዊ ተሳትፎ በተጨማሪ ባለፈው መጋቢት ወር ኢትዮጵያ፣ ጅቡቱና ኬንያ ሞቃዲሾ ላይ ተገናኝተው ባደረጉት ምክክር ተጨማሪ 1000 ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ልካለች።

በዚህም አልሸባብ የጥቃቱን ዋነኛ ትኩረት በውጭ ወታደሮች ላይ አንጣጥሮ ቆይቷል።

አልሸባብ ካለፉት ቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ድንበር ጥቃት ለማድረስ ሲሞክር የሚስተዋል ሲሆን፤ ባለፈው ሰኔ ወር ላይም በሶማሌ ክልል ዶሎ ከተማ ጥቃት ማደረሱ ይታወሳል።

በተለይም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆናቸው፤ ቡድኑ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ካለው ጽኑ ፍላጎት እና ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የጸጥታ ችግሮች ጋር ተዳምሮ አልሸባብ በሚቀጥሉት ወራትና ዓመታት ተከታታይ የሽብር ጥቃት ሊከፍት እንደሚችል ነው የተጠቆመው።

የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ዋነኛ ስጋት የሆነው እስላማዊ ቡድን በተለይ በሶማሊያ በሚፈጽማቸው አውዳሚ ጥቃቶች የብዙዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል።

09/09/2023

ባለጊዜ ስትሆን መብትህንና ግዴታህን አታቀውም

  ቃል አቀባይ ሚዲያ የሆኑት የፋና እና የዋልታ ቴሌዢዥን ጣቢያ ቅጥር ግቢዎች ታምሰዋል ።             አሻራ ሚዲያ             ጳጉሜ 3/2015ከሁለቱም ጣቢያዎች የተውጣጣን የ...
08/09/2023

ቃል አቀባይ ሚዲያ የሆኑት የፋና እና የዋልታ ቴሌዢዥን ጣቢያ ቅጥር ግቢዎች ታምሰዋል ።
አሻራ ሚዲያ
ጳጉሜ 3/2015
ከሁለቱም ጣቢያዎች የተውጣጣን የጋዜጠኞች ቡድንን መንግስት የሀሰት ዶክመንተሪ እንዲያዘጋጅ አንዳንዶችን ያለፍላጎታቸው ጭምር የላከ ቢሆንም እስካሁን ግን የተላኩ ጋዜጠኞች የደረሱበት አልታወቀም።

ይህንን ተከትሎ የጋዜጠኞች ቤተሰቦች ስልክ እየደወሉ የጣቢያዎችን ሀላፊዎችን ለማናገር የሞከሩ ቢሆንም ትክክለኛ መልስ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ታውቋል።

በዚህ የተደናገጡት የጋዜጠኞች ቤተሰቦች በትናትናው ዕለት ጷግሜ 2 በየጣቢያዎቹ ግቢ በመሄድ የጣቢያውን ግቢ አምሰውታል።

እንደ ምንጮቻችን ገለፃ ከሆነ ግን መንግስት ከሁለቱ ጣቢያ ወደ አማራ ክልል ሄደው የሀሰት ዶክመንተሪ እንዲያዘጋጁ አሰባስቧቸዋል የተባሉ ጋዜጠኞችን በራሱ ሀይሎች እንዲታገቱ አድርጎ ሳያሰገድላቸው እንዳልቀረ መረጃወች እየወጡ ነው። በማስረጃ መረጋገጥ ባይቻልም።

ምንጮች ጨምረው ስለጉዳዩ ሲናገሩ መንግስት ይህንን በጋዜጠኞች ላይ ተፈፅሟል እየተባለ እየተነገረ ያለውን አሳዛኝ ድርጊት ያስፈፀመው ፋኖ ገደላቸው በማለት የአማራ ፋኖን ስም ለማጠልሸት አስቦ የወጠነው ሴራ ነው ይላሉ።
#ንስር ሚዲያ

08/09/2023

እነ አብይ አህመድ መርዶ እየዘነበባቸው ነው። አሜሪካ በዚህ መልኩ ፈፅም ያለችውን ሁሉ ሲተገብር የኖረው፣ የአብይ አህመድ መንግስት ዛሬ ደሞ ከነጩ ቤተ መንግስት፣ በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ለምስራቅ አፍሪካ ጭምር አደጋን የደቀነ ስለሆነ የጣልኩትን ማዕቀብ ለአንድ አመት አራዝሚያለሁ ብላ፣ ክው አድርጋዋለች። ከዚህም ባሻገር በአማራ ክልል ማጀቴ ላይ የአብይ ወታደር 70 ንፁሀን አማራዎችን በግፍ መግደላቸውን ከ10 ሚሊየን በላይ የTwitter ተከታይ ያለው ታዋቂው መፅሄት ዘጋርዲያን አጋልጧል።

እነ አብይ አህመድ በአማራ ክልል ውስጥ ከኢትዮዽያም አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ ጭምር አደጋ የደቀነ ጦርነት እያካሄዱ እንደሆነ አሜሪካ ዛሬ አጋልጣለች።

በተቃራኒው፣ አብይ አህመድና ሙርከኛው ብረሀኑ ጅላ ደመሰስነው ቀጠቀጥነው ያሉት ፋኖ የማይቀመስ እንደሆነ አለም እየመሰከረ ነው። ሚኒሻው አበበ አረጋ ክልሉ ሰላም ነው ያለው ትናት ቢሆንም ዛሬ የኢትዮዽያ ህዝብ በመንግስት የተደበቀውን ሀቅ ከሌላ አገር መንግስት እየሰማ ነው። ይሄ አውርቶ አደር መንግስት በውሸት እያምታታ ህዝብ የሚያሰቃይበት ገመዱን በዲፕሎማሲም በመሬት ውጊያም እየተበጣጠሰ ነው። እናም ወገኔ ይልቅ ከአራቱም መአዘን ፊትህን 4ኪሎ ላይ ደቅነህ ተራመድ። እመነኝ ይሄ መንግስት መልሶ መንግስት እንደማይሆን በአለቆቹ ሁሉ ተመስክሮበታል።
የመከራ ግዜን ከማራዘም ውጭ አብይ አህመድ መሪ ሆኖ የሚቀጥልበት እድሉ ሁሉ አብቅቷል። የሽግግር መንግስትህን ለማቋቋም በየ አካባቢህ ያለውን የፒፒ ነገዴ አባረህ አራት ኪሎን እየጠራህ ገስግስ።

መከላከያ ሆይ አሁንስ ለማን እንደምትሞት አልገባህም ይሆን..? አሁንም አልመሸም አፈሙዝህን ወደ አስገዳይ አዙረህ አገርህን ታደግ። እመነኝ ይሄ መንግስት አብቆተለታል። ይህ የጌታቸው ረዳ ንግግ መዝሙር መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል። ይህ የትልቁ የአማራና የኢትዮዽያ ህዝብ ብሎም የዲፕሎማቶቹ የተረጋገጠ ጥሬ ሀቅ ነው። ወደፊት ሆኖ ስታየው ትንቢት እንደሰማህ ከምትገረም አሁን እጅህ ላይ ያለውን እድል ተጠቅመህ የታሪክ ባለቤት ሁን።

Abdella ሱሌማን አብደላ

Address

አድዋ ድልድይ
Addis Ababa
FACEBOOK

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መሳይ መኮንን ከESAT International posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share