ዜና ማእድ ከተለያዩ ሚዲያዎች

  • Home
  • ዜና ማእድ ከተለያዩ ሚዲያዎች

ዜና ማእድ ከተለያዩ ሚዲያዎች Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዜና ማእድ ከተለያዩ ሚዲያዎች, TV Channel, .

መረጃ ወለጋ አጋምሳ ሐሮ !ህግ ለማስከበር በሚል ወለጋ የገባው የመከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ልዩሀይል አካባቢውን ለቆ ወደ ነቀምት ሄዷል። ይሄን ተከትሎ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ኦነግ እ...
29/08/2022

መረጃ ወለጋ አጋምሳ ሐሮ !

ህግ ለማስከበር በሚል ወለጋ የገባው የመከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ልዩሀይል አካባቢውን ለቆ ወደ ነቀምት ሄዷል። ይሄን ተከትሎ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ኦነግ እና ከብርሸለቆ ማሰልጠኛ መሳሪያ ዘርፎ ኦነግን የተቀላቀለው ኃይል በወለጋ አማራ ላይ ዳግም ጦርነት ከፍቷል።

ከትናንት ጀምሮ ወለጋ አጋምሳ እና ሐሮ የሚባል ቦታ የሚገኙ አማራዎችን ከበባ በማድረግ ለመ*ጨ*ፍ*ጨ*ፍ ሙከራ ቢያደርጉም ህዝቡ ራሱን በመከላከል ከመካከላቸው በወጡ ጀግኖች ከበባውን ሰብረው ህዝባቸውን ማውጣት ችለዋል።

በሌላ መኩል ከህወሓት የተማሩትን ሕዝባዊ ማዕበል በማስነሳት ነፍጠኛን እንወራለን በማለት ቅስቀሳ እየተደረገ እንደሆነ ከቦታው መረጃ እየወጣ ነው። በአሁኑ ሰዓትም በኦነግ ሸኔ እና በወለጋ አማራዎች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነው።

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ባህር ዳር መሆናቸው ተሰምቷል‼️ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከ2 ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት ...
18/05/2022

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ባህር ዳር መሆናቸው ተሰምቷል‼️

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከ2 ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ተናግረዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው ረፋድ ላይ ከወጡ በኋላ የደረሱበት ሳይታወቅ እስከ ረቡዕ አመሻሽ ድረስ ቆይተዋል።

ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ዛሬ ምሽት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፤ የጄነራል ተፈራ ጠበቃና የሚያውቋቸው ሰዎች ባለቤታቸው ባሕር ዳር ውስጥ በሚገኘው ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሉ እንደነገሯቸው ገልፀዋል።

ወ/ሮ መነን ባለቤታቸው በላኩት መልዕክት ደህና መሆናቸውን እና አሁን ያሉበት ቦታ በመግለጽ ቤተሰባቸው እንዲረጋጋ መልዕክት ልከዋል ብለዋል። ከአማራ ክልል የፀጥታና ደኅንነት እንዲሁም ፖሊስ ማብራሪያ ለመጠየቅ የተደረገ ሙከራ አለመሳካቱን ቢቢሲ አስነብቧል።
©ቢቢሲ

እንቅፍ ጠፋ እኮ ህልም የምናይበት
13/05/2022

እንቅፍ ጠፋ እኮ ህልም የምናይበት

እንኳን በሰላም ተመለስክጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ስለነበረው ነገር በራሱ ማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዲህ ሲል ገልጿል።"የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በአጥር ዘለው አፍነው ከወሰዱኝ በኋላ...
09/05/2022

እንኳን በሰላም ተመለስክ

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ስለነበረው ነገር በራሱ ማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዲህ ሲል ገልጿል።

"የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በአጥር ዘለው አፍነው ከወሰዱኝ በኋላ አይኔን በጨርቅ አስረው ቤቴ በር ላይ ጥለውኝ ሄደዋል!

ከኢድ አልፈጥር አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በአጥር ዘለው አፍነው ከወሰዱኝ በኋላ አሁን ከምሽቱ 3:00 አይኔን በጨርቅ አስረው ቤቴ በር ላይ ጥለውኝ ሄደዋል።
እስከ ዛሬ የት እንዳቆዩኝ ግን አላውቅም። በጤናዬ ላይ የደረሰ ነገር የለም።"

09/05/2022
የአማራ ፋኖ በደቡብ ወሎ በገራዶ በጀኔራል አሳምነው ፅጌ ማስልጠኛ ተቋም ውስጥ ለ4 ወር ሲሰለጥኑ የቆዩ ፋኖዎችን አስመረቀ።ባህርዳር:- ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም                የደ...
08/05/2022

የአማራ ፋኖ በደቡብ ወሎ በገራዶ በጀኔራል አሳምነው ፅጌ ማስልጠኛ ተቋም ውስጥ ለ4 ወር ሲሰለጥኑ የቆዩ ፋኖዎችን አስመረቀ።

ባህርዳር:- ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም


የደቡብ ወሎ ፋኖ በገራዶ ለ4 ተከታታይ ወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በከፍተኛ ድምቀት አስመረቀ።

የአማራ ህዝብ የገጠመውን የህልውና ችግር በአሸናፊነት ለመወጣት አማራ በየአካባቢው ራሱን ማደራጀትና አቅሙን ማጎልበት እዳለበት ተመራቂ ፋኖዎች መልእክት አስተላልፈዋል።የገራዶና አካባቢ ማህበረሰብ እንደ አማራ ከወትሮው በተሻለ መልኩ ራሱን ማደራጀት እዳለበትና ይህ የሁለተኛ ዙር ምረቃትም በቀጣይ ወጣቱ በተሻለ መልኩ መሰልጠንና መደራጀት እዳለባቸውና አማራ ራሱን አስከብሮ ሀገሩንም እድጠብቅ የአካባቢው ማህበረሰብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

#ድል ለአማራ💚💛❤
#ድል ለኢትዮጵያ 💚💛❤
💚💛❤

ጎበዜ ሲሳይ የታለ?*****በኃይል መሰወር በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ነው። ይኼ ወንጀል ከወንጀልነቱም ባሻገር ዜጎች በመንግስታቸው ላይ የሚኖራቸውን አመኔታ የሚሸረሽር ነው። ጋዜጠኛ ...
07/05/2022

ጎበዜ ሲሳይ የታለ?
*****
በኃይል መሰወር በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ነው። ይኼ ወንጀል ከወንጀልነቱም ባሻገር ዜጎች በመንግስታቸው ላይ የሚኖራቸውን አመኔታ የሚሸረሽር ነው። ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ክብርት አዳነች አበቤ (የከተማችን ከንቲባ)፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና የብሔራዊ ደኅንነት አገልግሎት ግልጽ ማብራሪያ ሊሰጡ ይገባል።

አዲስ አበባ ከተማ ዜጎች ኅልማቸውን እውን የሚያደርጉባት የኢትዮጵያውያን ሁሉ መዲና እንጂ ዜጎች በማንነታቸው (ፖለቲካዊ፣ ብሔር፣ ኃይማኖት) ምክንያት በ«ፀጥታ አካላት» በኃይል የሚሰወሩባት ልትሆን አይገባም። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሰል ጥፋት በፈፀሙት ላይ የማያዳግም እርምጃ ከመውሰድ በተጨማሪ እሳቸው በሚመሩት መንግስት መሰል ነውሮች በመፈፀማቸውም የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል።
©ክርስቲያን ታደለ

07/05/2022
07/05/2022
የአማራ ፋኖ የሀገሪቱን ፖለቲካ  አሰላለፍ  እየለወጠዉ መሆኑ በስልጠናው ብቻ የደነገጠዉ የኦነግ የጫካ ልሳን OMN ተናገረ የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ልሳን OMN በአማረኛ የዜና እወጃው ፋኖ በአ...
07/05/2022

የአማራ ፋኖ የሀገሪቱን ፖለቲካ አሰላለፍ እየለወጠዉ መሆኑ በስልጠናው ብቻ የደነገጠዉ የኦነግ የጫካ ልሳን OMN ተናገረ

የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ልሳን OMN በአማረኛ የዜና እወጃው ፋኖ በአሸባሪነት እንዲፈረጅልኝ ሲል ጠይቋል።😂
Omn ይህን ይበል ፋኖ ድረስልኝ ተብሎ ሀገርን ከብተና የሚታደግ ጀግና እንጂ ሰፈር ለሰፈር እየተሽሎከለከ ሴት፣ ህፃናት እና ሽማግሌ የሚያርድ ከንቱ አይደለም አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል ።
ፋኖን በዚህ ደረጃ እየፈሩት የሚገኙት የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጀው የዘር ጭፍጨፋ የሚፈፅሙበት ብቻ ናቸው!!

የአማራ ፋኖ የሀገሪቱን ፖለቲካ አሰላለፍ እየለወጠዉ መሆኑ በስልጠናው ብቻ የደነገጠዉ የኦነግ የጫካ ልሳን OMN ተናገረ

በፋኖ ላይ የሚደረገው መንግስታዊ ትንኮሳ መነሻዉ ድንጋጤ ነው።

እንኳን ለሚያዚያ 27 ፤ የአርበኞች የድል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!!  የኢትዮጵያ አርበኞች፤ ለሃገር ነጻነት፣ አንድነትና ክብር፤ የኢጣልያ ፋሽስት ወራሪ ሃይልን በመመከት፤ ከሁሉም የሀገሪቱ ...
05/05/2022

እንኳን ለሚያዚያ 27 ፤ የአርበኞች የድል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!!

የኢትዮጵያ አርበኞች፤ ለሃገር ነጻነት፣ አንድነትና ክብር፤ የኢጣልያ ፋሽስት ወራሪ ሃይልን በመመከት፤ ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመጉረፍ ጠላትን ያስጨነቀበት እና ድል ያደረገበት አልበገር ባይነትን ያስመሰከሩበት ቀን ነዉ፡፡

የምስራቅ አማራ ፋኖ በየጁ ቅርንጫፍ ላለፍት 3 ወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች ነገ ያስመርቃል   ባህርዳር ።   ሚያዝያ  26/2014 ዓ.ም                           የምስራቅ ...
04/05/2022

የምስራቅ አማራ ፋኖ በየጁ ቅርንጫፍ ላለፍት 3 ወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች ነገ ያስመርቃል

ባህርዳር ። ሚያዝያ 26/2014 ዓ.ም


የምስራቅ አማራ ፋኖ በየጁ ቅርንጫፍ ላለፍት 3 ወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች ሚያዝያ 27 ያስመርቃል።

ፋኖወች በደመቀ ሁኔታ በማስመረቅ አማራ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በሚያደርገው ትግል ዋጋ ያላቸውን ተዋጊወች ለማበርከት ቀጠሮ ይዟል።

መላው የወልድያ፣ የሰሜን ወሎ፣ አማራ እና የአማራ ሰቆቃ ይብቃ የሚል በሙሉ በቦታው ከጧቱ 2:00 ጀምሮ በመልካቆሌ ሜዳ በመገኝት የምርቃት ፕሮግራሙ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል ያለው የአማራ ወጣቶች ማህበር በወልዲያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል።

የምስራቅ አማራ ፋኖ በተለያዩ አካባቢዎች እና በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ፋኖዎችን ማስመረቁ እና እያስመረቀ መሆኑ ይታወቃል።

አሳሳቢው የሳይበር ጥቃት!“በህዳሴው ግድብና በፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች ከሽፈዋል” – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርበህዳሴው ግድብና በከፍተኛ የፋይናንስ ተቋ...
04/05/2022

አሳሳቢው የሳይበር ጥቃት!

“በህዳሴው ግድብና በፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች ከሽፈዋል” – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

በህዳሴው ግድብና በከፍተኛ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች መክሸፋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ገለፀ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያን መልካም ነገር ማየት በማይፈልጉ የውስጥና የውጪ ኃይሎች የሚደገፉ አካላት ህዳሴው ግድብ ላይ በተቀናጀ መልኩ የሳይበር ጦርነት ከፍተው ነበር። ጥቃቶቹ ምንም ጉዳት ሳያደርሱ እንዲመክኑ ተደርጓል።

በተመሳሳይም በኢትዮጵያ ከፍተኛ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ በርካታ የሳይበር ጥቃቶች በባለሙያዎች ጥረት እንዲከሽፉ ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል። የሃገሪቱን ሰላምና ዕድገት በማይፈልጉ ሃገራት የሚደገፍ ድርጅት የህዳሴው ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል በማቀድ ‘ብላክ ፒራሚድ ወር’ በሚል ስያሜ የሳይበር ጦርነት ከፍቷል። ይሁንና የጥፋት አላማ አቅደው ሲያሴሩ የነበሩት ሁሉ እንዳሰቡት ሕልማቸው ሳይሳካ ተጨናግፏል ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳስታወቁት፤ ከህዳሴው ግድብ ውኃ ሙሌት ጋር በተያያዘ ብላክ ፒራሚድ ወር የሚባል የኮምፒውተር ቫይረስ ተሠርቶ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ተደርጓል። በተለይም የፋይናንስ ተቋማት የሚጠቀሙባቸውና እርስ በእርሳቸው የተሳሰሩ 37 ሺህ ኮምፒውተሮችን ላይ ጥቃት በመፈጸም የህዳሴው ግድብን ለማስተጓጎል ተሞክሯል። ጥቃቶቹም በኢንፎርሜሽን ደህንነት አስተዳደር ጥብቅ ክትትል ምንም ጉዳት ሳያስከትሉ እንዲቋረጡና እንዲመክኑ መደረጋቸውን አስታውቀዋል። ፡

የዘርዕያቆብ አዝመራው ሻለቃ አዛዥና የጎንደር ከተማ ፋኖ ሰብሳቢ ፋኖ ሰለሞን አጠናዉ በሌለበት ቤቱ ፍተሻ ተካሄደበት።  ባህርዳር። ሚያዝያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም                  ...
03/05/2022

የዘርዕያቆብ አዝመራው ሻለቃ አዛዥና የጎንደር ከተማ ፋኖ ሰብሳቢ ፋኖ ሰለሞን አጠናዉ በሌለበት ቤቱ ፍተሻ ተካሄደበት።
ባህርዳር። ሚያዝያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

የዘርዕያቆብ አዝመራው ሻለቃ አዛዥና የጎንደር ከተማ ፋኖ ሰብሳቢ ፋኖ ሰለሞን አጠናዉ በሌለበት ቤቱ የቡድን መሳሪያ ጭምር በታጠቁ በመከላከያ እና የልዩ ኃይል ልብስ የለሱ አካላት ከበባ አድርገው ካደሩ በኋላ ንጋት ላይ ብተው ፍተሻ ማድረጋቸውን የገለጸው የሻለቃው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ማቲዎስ መንግስቱ ነው።

ፋኖ ማቲዎስ እንዳለው ሰለሞን አጠናው በሌለበት ቤቱ ተፈትሾ አንድ ህጋዊ የክላሽን ኮፕ መሳሪያተወስዶበታል።

በዚህ ሚያዝያ 24/2014 ንጋት ላይ በተደረገው ፍተሻም የፋኖ ሰለሞን አጠናው ባለቤት የመፈተሻ ወረቀት የጠየቀች ቢሆንም ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ነው የተጠቆመው።

በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ አራዳ አካባቢ በአንድ ቀደም ሲል በራያ ግንባር የተሰዋ እና ቤተሰቦቹ ከ6 ወራት ቆይታ በኋላ ሂደቱን ጠብቀው ሀዘኑን የተረዱ የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረ ውባንተ ጌታሁን በወንድሙ በፋኖ ገብርዬ ጌታሁን ቤት የለቅሶ ስነ ስርዓት እየተደረገ ነበር።

በወቅቱም የቡድን መሳሪያ በታጠቁ የመንግስት አካላት ጫና ለቅሶው መቋረጡ ተገልጧል።

የፋኖ አባላትም "ጎንደርን የብጥብጥ ማዕከል ማድረግ የለብንም" በሚል እሳቤ በትዕግስት ለቅሶውን አቋርጠው ወደየቤታቸው መመከሳቸውን አስታውቋል።

መሳሪያ እንዲያወርዱ ፍላጎትና እንቅስቃሴም ጭምር መጀመሩን አውቀናል ብሏል ፋኖ ማቲዎስ።

በተያያዘ ፋኖ በሰለሞን አጠናው አካውንት ገንዘብ በመላክ ለመወንጀል እየተሰራ ነው በሚል አካውንቱን ማዘጋት እንደተቻለ ተገልጧል።

ፋኖ ሰለሞን ሚያዝያ 18/2014 በጎንደር ከተማ የሀይማኖት ግጭት ለማስመሰል ታቅዶ የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዝና በማረጋጋት በኩል ትልቅ ሚና እንደነበረው ለአሚማ ማረጋገጡ ይታወሳል ሲል የዘገበው አማራ ሚዲያ ማዕከል ነዉ።

ጋዜጠኛው በምን ሁኔታ እንዳለ ባለማወቃችን አሳስቦናል! ~  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንዔል በቀለ (ዶ/ር) ከሰሞኑ በታሰረው በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ...
03/05/2022

ጋዜጠኛው በምን ሁኔታ እንዳለ ባለማወቃችን አሳስቦናል!

~ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንዔል በቀለ (ዶ/ር) ከሰሞኑ በታሰረው በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ሁኔታ መስጋታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከትናንት በስቲያ እሁድ ሲቪል በለበሱ ሰዎች መወሰዱን ገልፀው መግለጫውን እስከሰጡበት ጊዜ ድረስ ጋዜጠኛው በምን ሁኔታ ላይ እንዳለና የት እንደሚገኝ እንደማይታወቅም ነው ያስታወቁት፡፡

ኮሚሽነር ዳንዔል በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞችን እና የሚዲያ አካላትን ሁኔታ መከታሉ የፕሬስ ነፃነት አንዱ አካል መሆኑን በመጠቆምም አጠቃላይ የሚዲያ ምህዳሩ በተለያዩ መንገዶች ተጽዕኖ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የታክስ፣ የወጪ፣ የመረጃ አቅርቦት፣ የዐቅም እና የመሰረተ ልማት ጉዳዮችንም በማሳያነት አንስተዋል፡፡ ይህ መንግስትን ጨምሮ በዘርፉ የተሰማሩ የሲቪል ማህበረሰብ አካላትን የተቀናጀ ስራ የሚጠይቅ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ከአሁን ቀደም የኢሳት ጋዜጠኛ የነበረው ጎበዜ ሲሳይ አሁን ላይ በዲጂታል የሚዲያ ዘርፍ በግል ተሰማርቶ ይሰራ ነበር፡፡ የጋዜጠኛውን እስር በተመለከተ ከመንግስትም ሆነ ከጸጥታ አካላቱ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ እንዳልተሰጠ የአል አይን ዘገባ ያመለክታል።

03/05/2022
የአሊ አላሙዲን የለስላሳ መጠጥ ድርጅት ስራውን ማቆሙ ተገለፀ።ባህርዳር ።ሚያዚያ 25/2014/                   አሻራ ሚዲያ የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ የለስላሳ መጠጦችን ማም...
03/05/2022

የአሊ አላሙዲን የለስላሳ መጠጥ ድርጅት ስራውን ማቆሙ ተገለፀ።
ባህርዳር ።ሚያዚያ 25/2014/
አሻራ ሚዲያ

የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ የለስላሳ መጠጦችን ማምረት እንዳቆመ ካፒታል ጋዜጣ አረጋግጧል ። እንደ ሰበን አፕ፣ ሚሪንዳ ፔፕሲ፣ ኩል የተፈጥሮ ማዕድን ውሃ ያሉ መጠጦችን በማምረት ታዋቂ የሆነው ሞሃ አሁን ላይ የማምረት ሂደቱን አቁሟል።

የካፒታል ጋዜጣ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ኩባንያው ምርቱን ለማቆም የተገደደው ለምርቶቹ የሚሆን ጥሬ ዕቃዎች እጥረት ስላጋጠመው ነው ።

እንደ ካፒታል ምንጮች ዘገባ፣ ከጥቂት ወራት በፊት ጀምሮ ኩባንያው በጥሬ ዕቃ እጥረት እና በውጭ ምንዛሬ እጦት ሳቢያ ከአቅሙ በታች በሳምንት ሦስት ቀን እየሠራ የነበር ቢሆንም ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ለስላሳ መጠጥ ድርጅቱ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ስራውን ሙሉ በሙሉ ማቆሙ ነው የተነገረው። ችግሩ እስኪስተካከል ድረስ ሰራተኞችም ዕረፍት እንዲወስዱ መደረጋቸው ተገልጿል ።

ከ2 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ተማሪዎች በድንኳን ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው!!በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ የተፈናቀሉ ከሁለት ሺህ በላይ ተማሪዎች በድንኳን ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ...
03/05/2022

ከ2 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ተማሪዎች በድንኳን ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው!!

በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ የተፈናቀሉ ከሁለት ሺህ በላይ ተማሪዎች በድንኳን ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን በአማራ ክልል ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡

የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ እንዳስታወቁት፤ በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ የተነሳ የተፈናቀሉት ተማሪዎቹ በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በወለህ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በድንኳን ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛል። ተማሪዎቹ አቅም በፈቀደ መጠን በየአካባቢው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት ሁኔታ ተመቻችቶ ነበር፡፡ ነገር ግን የተፈናቃዩ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱና ተፈናቃዩም ለትምህርት ቅበላ በማያመች መልኩ ዘግይቶ መቀላቀል በመጀመሩ ችግሩን ለመፍታት በድንኳን ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ኢዲ ሙባረክ
03/05/2022

ኢዲ ሙባረክ

1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል  እየተከበረ ይገኛልሚያዚያ 24/2014 ዓ.ምንሥር ብሮድካስት1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛ...
02/05/2022

1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል እየተከበረ ይገኛል

ሚያዚያ 24/2014 ዓ.ም
ንሥር ብሮድካስት

1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ታላቁን የረመዳን ወር ለ30 ቀናት ዱኣ በማድረግ፣ በሰላት እና ጾም በመጾም ያሳለፈው ህዝበ ሙስሊሙ የጾም መገባደጃ ምልክት የሆነችው ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ ዛሬ ኢድ አልፈጥርን በተለያዩ ሁነቶች እያከበረ ይገኛል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአደባባይ እና ከዚያም በኋላ ከቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጎረቤቶቻቸው ጋር በመሆን በዓሉን ያከብራሉ፡፡

በተለይም በአዲስ አበባ ስታድየም የዕምነቱ ተከታዮች በኢድ ሰላት ለማክበር እየተሰባሰቡ ይገኛሉ።

ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪ ጋር በተያያዘ ከተዘጋጁ መርሀ ግብሮች መካከል አንዱ በሆነው ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ ላይ ለመታደምም የጎረቤት ሀገራት የእስልምና ተቋማት ተወካዮች አዲስ አበባ እየገቡ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንዳሉትም ፥ ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ያዳበራቸውን መልካም ስራዎች ከረመዳን ውጪ ባሉት ወራትም የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስና የተቸገሩትን በመርዳት እንዲሁም የማዕድ ማጋራቱን ስራ በቀጣይነት በመፈፀም ከፈጣሪው የሚያገኘውን ምንዳ ከፍ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

Amhara Nation***************
02/05/2022

Amhara Nation
***************

"በዒድ ሰላት ወቅት የተከሰተው ክስተት በክርስቲያኑና በሙስሊሙም መካከል የተፈጠረ አይደለም።" - የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት"አንዳንድ አካላት ችግሩን ከመንግስት ጋር ለማያ...
02/05/2022

"በዒድ ሰላት ወቅት የተከሰተው ክስተት በክርስቲያኑና በሙስሊሙም መካከል የተፈጠረ አይደለም።"

- የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

"አንዳንድ አካላት ችግሩን ከመንግስት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውም የተሳሳተ መሆኑን አረጋግጠናል።

በዒድ ሰላት ወቅት የተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ በስፍራው ከነበሩ በጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎቻችን ደርሶናል። በአንድ ፌደራል ፖሊስ ድንገት (ባርቆብኝ ነው ብሏል) በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ ምክንያት የተፈጠረ ግርግር ነበር። የአስለቃሽ ጭሱ እንደተተኮሰ በቦታው የነበሩ የበአሉ ታዳሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ተደናግጠዋል።ወደ ፌደራል ፖሊሱ በማቅናት ይዘውታል።ፖሊሱም ድንገት ባርቆበት እንደሆነ ተናግራል። ሆኖም ህዝቡ ከፍተኛ የሆነ መረበሽ ውስጥ ስለገባ ለመግባባት አልተቻለም።

በመጨረሻም የፌደራል ፖሊሱ በኤግዚቢሽን ማዕከል አካባቢ ወደ ሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ካንፕ እንዲገባ ተደርጓል።ይህን ተከትሎ ሌሎች ፖሊሶች ከካምፑ ሲወጡ ተኩስ የፈጠረው ግርግር ባለመረጋጋቱ ችግሩ ሊባባስ ችሏል።

ከዚህ በተረፈ ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጋር ችግሩን የሚያይዘው ነገር አለመኖሩ ተረጋግጧል። በመንግስት በኩልም ሆነ ተብሎ የተፈጠረ ችግር አለመኖሩን አረጋግጠናል።በመሆኑም ህዝቡ እንዲረጋጋ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።"

የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_mereja

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዜና ማእድ ከተለያዩ ሚዲያዎች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዜና ማእድ ከተለያዩ ሚዲያዎች:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share