ኢትዮ ዜና 24

ኢትዮ ዜና 24 ለህሊናችን ስንል ታማኝ መረጃ እናቀርባልን

https://youtu.be/uCjF0203IcY
26/07/2023

https://youtu.be/uCjF0203IcY

የሞት ፍርድ ተፈረደባትፍርድ ነጋሴ ከበደ በሞት እንድትቀጣ ተፈረደባት::በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ከታ ወረዳ ሁለት የእንጀራ ልጆቿን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድላ ያቃጠለችው ነጋሴ ከበደ...

አወይ ጊዜ በላይ ዘለቀ ቢያይ ኖሬ ደረቱ  ላይ ሁለት ጦር ያሳርፍበት ነበር ሰላቶ ከየት መጣ ብሎ
27/03/2023

አወይ ጊዜ በላይ ዘለቀ ቢያይ ኖሬ ደረቱ ላይ ሁለት ጦር ያሳርፍበት ነበር ሰላቶ ከየት መጣ ብሎ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ ጀምሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ተከለከለከነገ ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃክ አገልግሎት መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራን...
09/03/2023

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ ጀምሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ተከለከለ

ከነገ ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃክ አገልግሎት መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት እንዲያስችል አሰራር ማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

በመሆኑም የአሰራር ማሻሻያ ስራው ተጠናቆ እንዲሁም የአገልግሎቱ አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ከነገ የካቲት 30/2015ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አከባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።

አድዋ ይህንን ተአምር እየገባቹሁ እዩ ወዲያውም በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ፡፡ ይኸውም የቀስተ ደመና ምልክት ታየ፡፡ ከዚያም ቀስተ ደመና ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የሚመስል ጢስ ይወጣነበር፡፡ ...
26/02/2023

አድዋ
ይህንን ተአምር እየገባቹሁ እዩ
ወዲያውም በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ፡፡
ይኸውም የቀስተ ደመና ምልክት ታየ፡፡ ከዚያም ቀስተ ደመና ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የሚመስል ጢስ ይወጣ
ነበር፡፡ ከዚያም ጢስ ውስጥ እንደክረምት ነጎድጓድ ያለ ድምፅ ተሰማ፡፡ ከዚያም የነጎድጓድ ድምፅ የተነሣ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሽብር
ሆነ፡፡ ለመዋጋትም አልቻሉም፡፡

በአድዋ ላይ ድል ስላደረገው የጊዮርግስ መገለጥ ሃይሉ ምንጭ ምክኒያት ከዚህው ሞዓ መንግስት ጋር የሚቀዳ ታሪክ አለው።ብዙ ጊዜ በአድዋ ታቦት አብሮ መዝመቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም መዋጋቱ ይገ...

ቀና ብለን ልናያቸው ስንኳ የማንደፍር ታላላቅ አባቶች እንዲህ አዝነው ከማየት የበለጠ ልብን የሚሰብር ምን አለ!?@ሻሸመኔ
09/02/2023

ቀና ብለን ልናያቸው ስንኳ የማንደፍር ታላላቅ አባቶች እንዲህ አዝነው ከማየት የበለጠ ልብን የሚሰብር ምን አለ!?

@ሻሸመኔ

!!!!!!!    አይናችን ወደ ቤተክርስቲያናችን    !!!!!"አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ...
04/02/2023

!!!!!!! አይናችን ወደ ቤተክርስቲያናችን !!!!!
"አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?" -ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በመንግሥት አካላት የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን አስመልክቶ ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባሠፈሩት መልእክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤተ ክርስቲያን እና በክርስቲያኖችን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የማሳደድ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል::

በሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ እናስከብራለን በሚል በትግራይ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰበሰበ ወራሪ ቡድን ጋር በማበር በጠራራ ፀሐይ ሕግ ሲጥስና የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው በማለት ገልጸዋል።

በሻሸመኔ ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ እየተፈፀመ የሚገኘው ግፍ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ለማጥፋት ከሚደረግ የዘር ጭፍጨፋ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።

አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?

በሻሸመኔ እና በመላው ምዕራብ አርሲ የምትገኙ ጠንካራ ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በሙሉ ይህንን ከዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ያልተናነሰ ዘመን በጠንካራ መሠረት ላይ በታነፀው የሃይማኖታችሁ ጥንካሬ በጸሎት ፣ በጾም እና በፍፁም ክርስቲያናዊ ጥንካሬ ራሳችሁን ፣ ቤተ ክርስቲያናችሁን እና ሀገራችሁን እንድጠብቁ ሲሉም ጠይቀዋል።

በመሆኑም ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል የሚለውን የቅዱስ መጽሐፍ ቃል በማስተዋል የፌደራል መንግስትና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወገንተኝነታቸውን በማቆም እግዚአብሔር ፍርድ ከመስጠቱ በፊት ንስሐ በመግባት በግፍ የሚፈሰውን የንፁሐን ኦርቶዶክሳውያንን ደም እንዲያስቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

©EOTCMK

ሃያል ለሚሏት ሀገር የማይመጥን መሪ ዳውን ዳውን ትራንፕ
25/10/2020

ሃያል ለሚሏት ሀገር የማይመጥን መሪ ዳውን ዳውን ትራንፕ

ትራንፕ ዳውን ዳውን
24/10/2020

ትራንፕ ዳውን ዳውን

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,916 የላብራቶሪ ምርመራ 890 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 247 ሰዎች አገግመዋል...
02/10/2020

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,916 የላብራቶሪ ምርመራ 890 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 247 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 76,988 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,208 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 31,677 ደርሷል።

11/09/2020
ታከለ ኡማ ስለ ገበሪዎቹ ያለው ምንም አልገባኝም ኮንዶሚኒየም የሚሰራው ለሚቆጥብ ማህበረሰብ ነው ታዲያ  እንደሚባለው የተጎዳም አካል ካለ እነሱን በአግባቡ ቤት ገንብቶ መስጠት ነው እንጂ ከደ...
02/09/2020

ታከለ ኡማ ስለ ገበሪዎቹ ያለው ምንም አልገባኝም ኮንዶሚኒየም የሚሰራው ለሚቆጥብ ማህበረሰብ ነው ታዲያ እንደሚባለው የተጎዳም አካል ካለ እነሱን በአግባቡ ቤት ገንብቶ መስጠት ነው እንጂ ከደሃው በተሰበሰበ ገንዘብ የተሰራውን ለምን ለሌላው ይሰጣል እስቲ ሃሳብ ካለ ወዲህ በሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ:-- ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር- ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ- ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ...
18/08/2020

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ:-

- ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር
- ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
- ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
- ታከለ ኡማ፤ የማዐድንና ነዳጅ ሚኒስትር
- ተስፋዬ ዳባ፤ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ
- ዮሐንስ ቧያለው፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግነኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
- ንጉሡ ጥላሁን፤ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር
- እንደአወቅ አብቴ፤ የብረታ ብረት ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር
- ፍቃዱ ጸጋ፤ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
- ፕሮፌሰር ኂሩት ወልደ ማርያም፤ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 943 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ 338 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል**********ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 14ሺህ 540 የላቦራቶሪ ምርመራ 943 ሰዎች የኮ...
12/08/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 943 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ 338 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
**********
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 14ሺህ 540 የላቦራቶሪ ምርመራ 943 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 25 ሺህ 118 ደርሷል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 338 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 034 ሆኗል።

ካለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ የ23 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 463 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት 178 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ሲገኙ፤ 13 ሺህ 619 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 535 ሺህ 431 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

.የኮሮና ቫይረስ ክትባት አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 5 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን በዓለም ላይ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መወሰኑ...
11/08/2020

.የኮሮና ቫይረስ ክትባት

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 5 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን በዓለም ላይ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መወሰኑን አስታወቁ።



ክትባቱ በሞስኮ ጋመሌያ ኢንስቲቱዩት የተዘጋጀ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ማረጋገጫን አግኝቷል።



ፕሬዚዳንቱም ሩሲያ በቅርብ ጊዜያት የኮሮና ቫይረስ ክትባቱን በብዛት ማምረት እንደምትጀምር ገልፀዋል።



ፑቲን የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ልጃቸው መውሰዷን መናገራቸውን የኢንደፔንዳትና አርቲ ዘገባ ያመለክታል።



ልጃቸው ክትባቱን ከወሰደች በኋላ መጠነኛ ሙቀን እንደነበራት የገለፁቱት ፕሬዚዳንቱ ከቆይታ በኋላ ግን መጠናኛ ሙቀቱ መጥፋቱን ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት ሰዎችን አገደ!የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሦስት የፓርቲዉ የስራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ገልጿል። ...
10/08/2020

የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት ሰዎችን አገደ!

የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሦስት የፓርቲዉ የስራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ገልጿል።

ፓርቲዉ የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባዉን ዛሬ ምሽት ሲያጠናቅቅ የተለያዩ ዉሳኔዉችን አሳልፏል።

የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሁለት ቀናት ዝግ ጉባዔዉን ሲያጠናቅቅ በሰጠዉ መግለጫ አቶ ለማ መገርሳን ፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋን እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንን ከፓርቲዉ ማገዱን አስታዉቋል።

የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ስብሰባዉ እንደተጠናቀቀ ለክልሉ የመንግሥት ቴሌቭዥን «OBN» ዛሬ ምሽት ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ለማ መገርሳ፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በፓርቲ ዉስጥ ካላቸዉ ኃላፊነት ተነስተዋል፤ እገዳዉ ኃላፊነታችሁን በአግባብ ነት አልተወጣችሁም በሚል መሆኑም ታዉቋል።

እነዚህ የታገዱት ሦስት ግለሰቦች በነበራቸዉ ኃላፊነት ልክ ለመስራት ዝግጁ ሲሆኑ በማንኛዉም ሰዓት መመለስ አንደሚችሉ ፓርቲዉ መወሰኑን አቶ ፈቃዱ በመግለጫቸዉ ተናግረዋል።

አቶ ለማ መገርሳና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን የፓርቲዉ ስራ አስፈጻሚ አባለት የነበሩ ሲሆን ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ ደግሞ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ።
Dw

ዛሬ ከሰዓት በኃላ አቶ ጀዋር ሙሐመድ ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ይቀርባሉ****************በእነ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነ የምርመ...
06/08/2020

ዛሬ ከሰዓት በኃላ አቶ ጀዋር ሙሐመድ ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ይቀርባሉ
****************

በእነ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነ የምርመራ መዝገብ ላይ በዋስትና ጥያቄ ጉዳይ እና ዐቃቤ ህግ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ተዘግቶ ለቀዳሚ ምርመራ ችሎት እንዲመራልኝ ብሎ ባቀረበው ጥያቄ ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ከሰዓታት በኃላ ትዕዛዝ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህን ተከትሎም በቅድመ ምርመራ ችሎት የአቶ ጀዋር ሙሐመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች እንዲሁ ዛሬ ከሰዓት በኃላ በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የቅድመ ምርመራ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በችሎቱም የሁለቱ ወገን ክርክር እና የዐቃቤ ህግ ምስክር ይደመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በቦሌ ክ/ከተማ የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አስተላላፊ የሆነ ትራንስፎርመር በክሬን ጭነው ለማምለጥ ሲመክሩ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥርጣሬ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆ...
27/06/2020

በቦሌ ክ/ከተማ የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አስተላላፊ የሆነ ትራንስፎርመር በክሬን ጭነው ለማምለጥ ሲመክሩ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥርጣሬ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ እሰከጫኑበት ክሬን እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሐያት ቁ.1 በሚባል አካባቢ ሠኔ 19/2012 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 አካባቢ ለ80 አባወራዎች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን ትራንስፎርመር ከመስሪያ ቤቱ ዕውቅና ውጭ ኮድ3 ኢ.ት84535 በሆነ ክሬን ተሸከርካሪ ታግዘው በመስረቅ ለማምለጥ ሲመክሩ በአካባቢው ነዋሪ ጥርጣሬ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ም/ዳይሬክቶሬት የሆኑት ኮማንደር ያሲን ሁሴን ለአዲስ ፖሊስ ገልዋል፡፡

ምንጭ፦ የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን

የፀሀይ ግርዶሽ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተከስቷልአዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀሀይ ግርዶሽ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተከስቷል...
21/06/2020

የፀሀይ ግርዶሽ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተከስቷል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀሀይ ግርዶሽ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተከስቷል። ይህ ቀለበታዊ የፀሀይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ ከምእራብ ኢትዮጵያ ወለጋ ተነስቶ በሰሜን በኩል ታይቷል። በባህርዳር እንጂባራ አካባቢ እስከ 98 በመቶ ጨለማ እንደነበር ነው የተጠቆመው። በላሊበላ እና በአፋራ አካባቢም በተለያዩ ሰዓታት ላይ ሙሉ ቀለበቱ ታይቷል።

399 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4848 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ (399) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን...
20/06/2020

399 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4848 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ (399) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4469 ደርሷል።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አምስት (95) ሰዎች (82 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል ፣ 1 ከትግራይ ክልል፣ 1 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1122 ነው።

የሰኔ 14ቱ ግርዶሽ- የትና መቼ በኢትዮጵያ ?በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ  ከ60 - 80 ፐርሰነት ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡ ከ80 ፐርሰነት በላይ ያለውን ዋናውን ግርዶሽ ግን ...
18/06/2020

የሰኔ 14ቱ ግርዶሽ- የትና መቼ በኢትዮጵያ ?

በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60 - 80 ፐርሰነት ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡ ከ80 ፐርሰነት በላይ ያለውን ዋናውን ግርዶሽ ግን ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኝ ስፍራ ጎልቶ ይታያል፡፡

ክስተቱ ወለጋ አካባቢ ጀምሮ ከፊል ጎጃምን ፣ ከፊል ጎንደርን አልፎ ወደ ወሎ ላሊበላን አቋርጦ ይሄዳል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ፀሐይ እስክ 99 ፐርሰንት ተሸፍና ቀለበታዊውን ግርዶሽ ማየት ይቻላል፡፡

ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች/ቦታዎች ቤጊ ፣ ሜቲ፣ መንዲ ፣ ጫልቱ ፣ ቡሬ ፣ አገው ግምጃቤት ፣ እንጅባራ ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ ፣ ዳሞት ፣ ጋይንት ፣ ንፋስ መውጫ ፣ ጋሸና ፣ ሙጃ ፣ ዋጃ ፣ ቆቦ ፣ ኮረም፣ አላማጣ ፣ ጊራራ እና ላሊበላ ይገኙበታል፡፡

በአዲስ አበባ ፤ ሐዋሳ ፤ ድሬደዋ ፤ መቐለ ፤ ደሴ ፤ አዳማ ፤ በመሳሰሉት ከተሞች ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን ይኖራቸዋል።

በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2,577 ደርሷል!በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ሰኔ 8/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 2,577 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተ...
15/06/2020

በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2,577 ደርሷል!

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ሰኔ 8/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 2,577 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 98 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 3 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ 5 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የተቀሩት 90 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ዘጠና ስምንት (98) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 37 ሰዎች
• ቦሌ - 4 ሰዎች
• ጉለሌ - 4 ሰዎች
• ልደታ - 13 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 8 ሰዎች
• ቂርቆስ - 16 ሰዎች
• አራዳ - 7 ሰዎች
• የካ - 2 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 4 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 2 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 1 ሰው

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 2,577 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 590 ሰዎች
• ቦሌ - 411 ሰዎች
• ጉለሌ - 286 ሰዎች
• ልደታ - 265 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 243 ሰዎች
• ቂርቆስ - 155 ሰዎች
• አራዳ - 149 ሰዎች
• የካ - 144 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 133 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 79 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 122 ሰዎች

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 179  ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,845 የላብራቶሪ ምርመራ 179 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ...
14/06/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 179 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,845 የላብራቶሪ ምርመራ 179 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,345 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 116 ወንድ እና 63 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከሁለት ወር ህፃን እስከ 80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 176 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 3 ሰዎች የውጭ ሀገር ዜጋ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 111 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 23 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 15 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 11 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 9 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 5 ሰዎች ከሱማሌ ክልል ፣ 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 2 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም 1 ሰው ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሃምሳ (50) ሰዎች (41 ከአዲስ አበባ፣ 4 ከአማራ ክልል፣ 3 ከአፋር ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 545 ደርሷል።

ከአዲስ አበባ ያመለጠው የኮቪድ-19 ታማሚ ተያዘ!አዲስ አበባ ናሙና ሰጥቶ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ተነግሮት አምልጦ ደብረብርሃን ከገባ በኃላ ስልኩን አጥፍቶ  ለመሰወር የሞከረው ግለሰብ...
12/06/2020

ከአዲስ አበባ ያመለጠው የኮቪድ-19 ታማሚ ተያዘ!

አዲስ አበባ ናሙና ሰጥቶ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ተነግሮት አምልጦ ደብረብርሃን ከገባ በኃላ ስልኩን አጥፍቶ ለመሰወር የሞከረው ግለሰብ በጸጥታ አካላት እና የጤና ባለሞያዎች ክትትል ጫጫ ከተማ ላይ ተይዟል ፤ ከእርሱ ጋር ንክኪ ያላቸው 13 ግለሰቦች ጋር ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 245 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,709 የላብራቶሪ ምርመራ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በ...
12/06/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 245 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,709 የላብራቶሪ ምርመራ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,915 ደርሷል።
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 47 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሰባት (7) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 47 ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ75 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ70 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

3. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

4. የ29 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

5. የ48 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት።

6. የ85 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

7. የ21 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 164 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 40 ደረሷልባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6,630 የላብራቶሪ ምርመራ 164 ሰዎች የኮሮና ...
11/06/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 164 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 40 ደረሷል

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6,630 የላብራቶሪ ምርመራ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,670 ደርሷል።
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 40 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአምስት (5) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 40 ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ92 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመረ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

2. የ58 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመረ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

3. የ80 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

4. የ36 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

5. የ70 ዓመት ወንድ የሱማሌ ክልል ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛውን ምርጫ ለማራዘም የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ አፀደቀ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉም እና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ...
10/06/2020

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛውን ምርጫ ለማራዘም የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ አፀደቀ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉም እና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በ4 ተቃውሞ፣ በአንድ ድምፀ-ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኙ ስጋት ሆኖ እስካለበት ድረስ የሁሉም ምክር ቤቶች ሥልጣን እንዲቀጥል፤ እንዲሁም ወረርሽኙ ስጋት አለመሆኑ ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት ካላረጋገጡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንኑ ካፀደቀ በኋላ ከ9 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይካሄድ የሚለው የውሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል። -EBC

አንዲት እናት 4 ልጆች በሰላም ተገላገለችአዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በስልጤ ወረዳ አንዲት እናት 4 ልጆች በሰላም መገላገሏ ተሰማ። የወረዳው ሰነና ገ...
05/06/2020

አንዲት እናት 4 ልጆች በሰላም ተገላገለች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በስልጤ ወረዳ አንዲት እናት 4 ልጆች በሰላም መገላገሏ ተሰማ። የወረዳው ሰነና ገሬራ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ዜኖ ሸምሱ በቅበት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተደረገላት የቀዶ ህክምና 3 ሴት እና 1 ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች። በአሁኑ ሰዓት ህፃናቱ በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኙሉ

በጤና ተቋማት የሚሰሩ 65 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል!በኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሂደት 49 የጤና ባለሙያዎችና 16 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስት...
03/06/2020

በጤና ተቋማት የሚሰሩ 65 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል!

በኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሂደት 49 የጤና ባለሙያዎችና 16 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ባለሙያዎቹ በአብዛኛው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የጤና ተቋማት እየሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ።

የጤና ባለሙያዎችና የጤና ተቋማት ሠራተኞች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እያደረጉት ላለው ተጋድሎም ምስጋና አቅርበዋል።

መንግሥት የጤና ተቋማት ሠራተኞችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ከሚያደርገው ሥራ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ራሱን በመጠበቅ የባለሙያዎቹን ጫና እንዲቀንስም ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ v

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 14 ደረሰ!በኢትዮጵያ ተጨማሪ 87 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,932 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች ...
02/06/2020

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 14 ደረሰ!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 87 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,932 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,344 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 59 ወንድ እና 28 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ10 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 67 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 6 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 7 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከሐረሪ ክልል እና 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 28

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው - 18

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው - 41

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው 14 ሰዎች (6 ከኦሮሚያ ክልል እና 8 ከሶማሌ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 231 ደርሰዋል።በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 14 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። የመጀመሪያው የ30 ዓመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን ሁለተኛዋ የ56 ዓመት በአዲስ አበባ የተጓዳኝ ህመም ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው።

ሁለቱ (2) ግለሰቦች ህይወታቸው ያለፈና ለእስክሬን ምርመራ ወደ ሆስፒታል በመጡበት ጊዜ በተደረገ ምርመራ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ናቸው። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ አራት (14) ደርሷል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 85 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!  የሞቾች ቁጥር 12 ደርሷልባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,926 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች የኮሮና...
01/06/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 85 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! የሞቾች ቁጥር 12 ደርሷል

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,926 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,257 ደርሷል፡፡ በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 12 ደረሰ!

የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ህክምና ሲደረግለት የነበረ፤ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበት እና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትለትናው ዕለት ህይወቱ አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ሁለት (12) ደርሷል።

Address

Bol
Addis Ababa
22

Telephone

+251910122427

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ ዜና 24 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category