Fanno negn

Fanno negn Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fanno negn, Digital creator, .

08/11/2023
08/11/2023
08/11/2023


Abiy Ahmed Ali Prosperity Party - ብልፅግና

08/11/2023
08/11/2023

መንገዳችን መደመር፤ መዳረሻችን ብልፅግና

ለውጥ በቀላሉ አይተከልም፡፡ ተስፋ እና ፍርሃት፤ ለውጥ የመጣለት እና ለውጡ የመጣበት አካል ትንንቅ ይፈትኑታል፡፡ የተለያዩ አካላት ለውጡን የሚመነዝሩት ከራሳቸው ፍላጎትና ጥቅም አንጻር በመሆኑ ለውጥን መሬት ለማስያዝና ለማስረፅ ፈታኝ ትግል ይጠይቃል፡፡

ለውጡ የመጣላቸው ሃይሎች የመጣውን ለውጥና የለውጡን መሪዎች በተስፋ የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ለውጥ የአሮጌውን ስርዓት ግድፈቶች፤ ቅጥፈቶችና ግሳንግሶችን አሽንቀንጥሮ ሁለመናው አዲስ የሆነ አሰራርና ስርዓት እንደሚዘረጋ በተስፋ ተሞልተው ይቀበሉታል፡፡

በተቃራኒው ለውጡ የመጣባቸው ከስልጣንና ከሃብት ማማ ያስቀመጣቸው የአቋራጭ መንገድ ስለሚዘጋባቸውና ጥቅማቸው ስለሚጓደል አሮጌው ስርዓት ተጠጋግኖም ቢሆን እንዲቀጥል ይታገሉለታል፡፡

በዚህ የሁለት ሃይሎች ግጭት የተነሳ ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ተስፋና መከራ፣ አንድነትና ልዩነት፣ ዓለም አቀፋዊ አድናቆትና ውግዘት፣ እመርታና ጉተታ፣ ነጻነትና ግጭት አስተናግደናል፡፡

ሀገራዊ ለውጡ ግን በብዙ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈም ከብልፅግና መንገዳችን አይናችንን ሳንነቅል መጓዛችንን ቀጥለናል፤ መዳረሻችንም ሁለንተናዊ ብልፅግና ነው፡፡

08/11/2023

ለኢትዮጵያ ብልፅግና ዕውን መሆን የሚተጋ ጠንካራ አመራር መፍጠር ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው - አቶ አደም ፋራህ

የአመለካከትና የተግባር አንድነትን አስጠብቆ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ዕውን መሆን የሚተጋ ጠንካራ የመንግስት አመራር መፍጠር ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

በሁሉም የኃላፊነት እርከን ላይ ለሚገኙ የመንግስት አመራሮች የሚሰጠው ስልጠና ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን÷ በመጭዎቹ ቀናትም ከ21 ሺህ 800 በላይ አመራር ወደ ስልጠና ይገባል ብለዋል።

ፓርቲው በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሕዝብ ይሁንታ ተመርጦ መንግስት በመመስረት የተቀበለውን ኃላፊነት ለመወጣት የአመራሩን አቅም ለማጎልበት እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በዚህም መንግስት ለሕዝብ የገባቸውን ቃሎች አፈጻጸም በመገምገም ጥንካሬዎችና ድክመቶችን መለየቱን ጠቁመው፥ እንደ ክፍተት የታዩትን ለመሙላትና አመራሩ በቀጣይ ውጤታማ እንዲሆን የፍላጎት ዳሰሳ ተደርጎ ስልጠና መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

አመራሩ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ሁኔታዎች እንዲዘጋጅ፣ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በብቃት እንዲወጣ የአቅም ግንባታ ስልጠናው ማስፈለጉንም ነው የተናገሩት።

የስልጠናው ዓላማ አመራሩን በእውቀት ማበልጸግ፣ የአገልጋይነት መንፈስና አስተሳሰብ እንዲላበስ ማድረግና ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ የሚያግዝ ክህሎትን ማጎልበት መሆኑንም አብራርተዋል።

ለዚህም ከዕዳ ወደ ምንዳ በሚል ዐቢይ ርዕሰ ጉዳይ በተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ሀሳቦችን የያዙ አጀንዳዎች መቀረጻቸውን ነው ያስረዱት።

በዚህም እስካሁን በሁለት ዙር በተሰጡ የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ከ13 ሺህ 500 በላይ አመራር መሰልጠኑን ጠቅሰው፥ ከጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ከ21 ሺህ 800 በላይ የ3ኛ ዙር ሰልጣኞች ወደ ስልጠና እንደሚገቡ ገልፀዋል።

የአመለካከት አንድነት በእቅዶች፣ በዓላማዎችና በመርሆዎች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር መሆኑን ያነሱት አቶ አደም፥ የተግባር አንድነት ደግሞ የተያዙ እቅዶችን በተቀራራቢ መንገድ እንዲፈጸሙ ማድረግ ነው ብለዋል።

ስልጠናው የአመራሩን አቅም በመገንባት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና እና የሀገር ግንባታ ጉዞን የሚያሳካ ጠንካራ መንግስት እንዲፈጠር ያስችላል ነው ያሉት።

አመራሩም በሀገርና ትውልድ ላይ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን ማስቀረትና የትናንት ወረትን ወደ ዛሬና ነገ ምንዳ የማሸጋገር ትልቅ የቤት ስራ እንዳለበትም አስረድተዋል።

08/11/2023

ኢትዮጵያ የጀመረችው የሁለንተናዊ ብልፅግና እንዲሳካ ለሰላም ልዩ ትኩረት ሰጥተን እንረባረባለን!

ብልጽግና ፓርቲ በሀገራችን የሚከሰቱ የግጭት መንስሄዎችን በሀገር በቀል የግጭት መፍትሄዎችና በሰለጠ የውይይት መድረክ ይፈታል ብሎ ያምናል።

የዜጎችን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥና ደህንነታቸው እንዲጠበቅም የተለያዩ የመፍትሄ አማራጮችን በመጠቀም የሰላም ግንባታ ላይ እንዲውል ጥረት እያደረገ ይገኛል።

ዘላቂ ሠላም ኢትዮጵያ ለጀመረችዉ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነዉ።
በመሆኑም አብሮነትንና መቻቻልን በማጎልበት በአከባቢያችን ያለውን የህብረተሰቡን የሰላም ባህል በማዳበር መንግስት ከህዝቡ ጋር ህዝቡም ከመንግስት ጋር በመሰናሰል ዘላቂ ሰላማችንን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም በተሟላ መልኩ ሲረጋገጥ የሀገር ውስጥም ሆነ የባህር ማዶ የፀብ ነጋዴዎች ይከስማሉ፤ ኢትዮጵያ ግን ወደተሟላ ብልፅግና፣ ወደ ላቀ ክብርና ልዕልና ታድጋለች።

08/11/2023
04/11/2023

Prosperity parti egna parti new

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fanno negn posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share