28/08/2023
በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል!!
👉በተለይም የሞተር አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል!!
በኦሮሚያ ክልል 2015 ዓ.ም በነሀሴ ወር በመካከለኛ ሳምንት ባሉት ቀናቶች በደረሱ 13 የትራፊክ አደጋዎች የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ21 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
አደጋዎቹ በምስራቅ ሸዋ፣በሻሸመኔ ከተማና በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች የደረሱ ናቸዉ።
የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ የጨመረ ሲሆን ፤ መንስኤዎቹ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣በቂ እረፍት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር እንዲሁም አሽከርካሪዎች እርስ በእርስ በመሽቀዳደም መሆኑን ኢንስፔክተር መሰለ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በተለይም በምስራቅ ሸዋ ሲኖትራክ መኪና በዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ ላይ በመዉጣት የ5ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ በሻሸመኔ ከተማ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ደግሞ አንድ የሞተር ተሽከርካሪ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች ወድያዉኑ ህይወታቸዉ ማለፉን በመግለፅ የሞተር አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲያሳስቡ አሳዛኝ አደጋዎች መሆናቸዉን ኢንስፔክተሩ ጨምረዉ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ኢንስፔክተሩ አክለዉም በአንድ ሳምንት ብቻ የ16 ሰዉ ህይወት ማለፉ እጅግ አስከፊና አሳዛኝ ነዉ ሲሉ ጠቅሰዉ አሽከርካሪዎች በፍጥነት፣ጠጥተዉ እንዲሁም በመሽቀዳደም የሰዉን ህይወት ከመቅጠፍ እንዲጠነቀቁ ሲያሳስቡ እግረኞችም በተቻላቸዉ አቅም ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ ራሳቸዉን ከትራፊክ አደጋ እንዲጠብቁ በአፅኖት አሳስበዋል።
#ዜና ኦዳ ጆርናል/Oda Journal
ቴሌግራም ላይ ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇