Inform Ethiopia

Inform Ethiopia Ethiopia Forever

23/02/2024
😂
23/02/2024

😂

ዳኒ😂

✍️ በ17 ዓመቷ ከኮሌጅ ተባረረች✍️ በ25 ዓመቷ እናቷን በሞት አጣች✍️ በ26 ዓመቷ ጽንስ ወረደባት✍️ በ27 ዓመቷ ትዳር መሰረተች✍️ ባሏ ከፍተኛ ጭቆና አደረሰባት፥ ሆኖም ግን ሴት ልጅ ...
23/02/2024

✍️ በ17 ዓመቷ ከኮሌጅ ተባረረች
✍️ በ25 ዓመቷ እናቷን በሞት አጣች
✍️ በ26 ዓመቷ ጽንስ ወረደባት
✍️ በ27 ዓመቷ ትዳር መሰረተች
✍️ ባሏ ከፍተኛ ጭቆና አደረሰባት፥ ሆኖም ግን ሴት ልጅ ተገላገለች
✍️ በ28 ዓመቷ ትዳሯ ፈረሰ፥ ብዙ አይነት የጭንቀት በሽታም ተገኘባት
✍️ በ29 ዓመቷ በእርዳታ ትተዳደር ነበር
✍️ በ30 ዓመቷ ሞትን ተመኝታ ነበር -ራሷንም ለማጥፋት ወሰነች😥 ይሁን እንጂ የህይወቷን 👉👈 በመቀየር ከሌላ ሰው የተሻለ ነገር ለመስራት መሰነች
✍️ በ31 ዓመቷ የመጀመሪያ መጽሀፏን አሳተመች
✍️ በ35 ዓመቷ 4 መጽሐፎችን በማሳተም የአመቱ ምርጥ ደራሲ ተባለች
✍️ በ42 ዓመቷ በአንድ ቀን ውስጥ 11 ሚሊዮን ኮፒ መጽሐፎቿን ሸጠች 🤔
✍️ ይህቺ ሴት J.K. Rowling ትባላለች! በ30 አመቷ ራሳን ሊታጠፋ እንደነበረ አስበሃል?
ይህች ሴት የHarry Potter መጽሐፍ ደራሲ ከመጽሐፉ ብቻ በተገኘው ከ15 ቢሊዮን ዶላር በአለም አቀፍ ደረጃ በቱጃሮች ተርታ ተቀምጣለች!

ተስፋ አትቁረጥ! ተግተህ ሥራ! ጽኑ አላማ ይኑርህ!

በፈጣሪ ታመን! ይሳካልሃል!

መልካም ቅዳሜ!

Oluma M Wodajoአብይ አህመድ “ከዳ” ወይስ አፈገፈገ?***********************[ለሰነፍ እጅግ የረዘመ፤ ለጎበዝ አንባቢ ደግሞ አጠር ያለ ሃተታ። ሳያነቡ "አይኮምቱ"😉]በምሁ...
02/09/2023

Oluma M Wodajo
አብይ አህመድ “ከዳ” ወይስ አፈገፈገ?
***********************
[ለሰነፍ እጅግ የረዘመ፤ ለጎበዝ አንባቢ ደግሞ አጠር ያለ ሃተታ። ሳያነቡ "አይኮምቱ"😉]

በምሁራዊ ብቃቱ እና በሚሰጣቸው በሳል የአደባባይ ፖለቲካዊ ትንታኔዎቹ የማከብረው ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ “የዶ/ር አብይን መንግስት መደገፍ በቃኝ።...ተቃዋሚ ሆኛለሁ።...አሁን የሚሰማኝ ንዴት እና የመጭበርበር ስሜት ነው...” በማለት ከEMSሱ ግዛው ለገሰ ጋር ያደረገውን ዘለግ ያለ ውይይት ተመለከትኩት። ከፕሮፌሰር መሳይ ጋር በቅርቡ ሚያዚያ ወር ላይ በተደረገ አለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ላይ እኔም እሱም ወረቀት አቅራቢ ሆነን ለአጭር ጊዜ ተገናኝተን ነበር። ምንም እንኳን በፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጸም ላይ አንዳንድ reservations እንዳሉት ሲገልጽ ብሰማም፤ EMS ላይ ያየሁበትን አይነት ተስፋ መቁረጥ ያን እለት አላስተዋልኩበትም ነበር። እንደ ሁሌው በደምብ የተቀመረ ሃሳብ ነበር ያቀረበው። የሰሞኑ የEMS ውይይቱም ያን ያህል አስከፊ አልነበረም። “እንዴ?!” ያስባሉኝ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ጥሩ ጥሩ ነጥቦችንም አንስቶ ነበር። እስከ ዛሬ ልክ እንደሱ “አብይ ከዳን...አታለለን...” ብለው ከአንድ ጽንፍ ወደ ሌላ ጽንፍ ከተወነጨፉት በርካቶች አንጻርም፤ ደርዝ ያለው እና ጨዋ ሂስ ነበር ያቀረበው። በእኔ ግምት “አብይ ከዳን...አታለለን” በማለት ፕሮፌሰር መሳይ የመጀመሪው እንዳልሆነው ሁሉ የመጨረሻም ይሆናል ብዬ አላስብም። ከጃዋር እስከ ለማ፣ ከገዱ እስከ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ከ”ተደማሪ” መንጋ እስከ ጥቅመኛ ግለሰብ፣ ከዳያስፖራ እስክ ሃገር ውስጥ ደጋፊ “ተከዳን/ተታለልን” የሚለው ነገር ሲደጋገም፤ አብይ አህመድ ለዚህ ሁሉ ሰው ምን ቃል ገብቶ ነው? ማለቴ አልቀረም። በግሌ በኢትዮጵያ ታሪክ “ጎዳን” እንጂ “ከዳን” እየተባለ የሚወቀስ መሪ ስለመኖሩ አላውቅም 🤷‍♂️

በእኔ ግምገማ የአብይ “አድናዊዎች” (አንዳንዶቹ “አምላኪዎች” ነበሩ ቢባል ራሱ ማጋነን አይሆንም!) የነበሩ ግለሰቦች እና ቡድኖች “አብይ ከዳን” ሲሉ ምን ማለታቸው ነው ለሚለው ጥያቄ ያገኘሁት መልስ በተናጠል ወይም በጋራ የገባላቸው ቃል-ኪዳን ኖሮ ሳይሆን መጋቢት 2010 ፓርላማ ውስጥ ባደረገግው inaugural speech እና ከዚያም በኋላ ያደረጋቸው ንግግሮች የፈጠረባቸውን ተስፋ እና expectation እነሱ በተረዱት እና በገመቱት መንገድ fulfill ባለማድረጉ የተፈጠረ የexpectation crisis ነው። ከዚህ በተጨማሪም እንደ ሃገሪቱ መራሄ-መንግስትነቱ “ሊያደርግ ይገባዋል” ብለው የጠበቁትን ባለማድረጉም ጭምር ሊሆን ይችላል። በተለይ ንግግሩ “የአንድነት ሃይል ነኝ” ለሚለው ወገን ጆሮ የሚጥሙ እና ተስፋ የሚያጭሩ መሆናቸው የተጋነነ expectation እንዲኖር (ለምሳሌ የፌደራል አውቃቀሩን፣ ህገ መንግስቱን፣ ብሄረሰብ ተኮር የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ የህወሐትን ህልውና የተመለከቱ አፋጣኝ ለውጦች ይኖራሉ የሚል ተስፋ እንዲኖር) ያደረገ ይመስለኛል። በእርግጥም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጀመሪያው አመት የወሰዳቸው እርምጃዎች (ቤተ መንግስቱ ውስጥ የቀድሞ ነገስታትን ሃውልት በሰም ማሰራቱ፣ ቤተ መንግስቱን ዩኒቲ ፓርክ ብሎ ማሰየሙ፣ በሃይማኖት ተቋማት መሃል የነበሩ ልዪነቶች እንዲፈቱ በማድረጉ፣ አመቻማችነትን መስበኩ...ወዘተ) ብዙዎችን አስፈንጥዘው፤ ጥቂት የማይባሉትን አስከፍተዋል። እንደ ምሳሌ ብንወስድ አብይ በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያደረጋቸው የሃውልት ግንባታዎች እና ተያያዥ ንግግሮች “የአንድነት ሃይል ነኝ” የሚለውን እና የአማራ ልሂቃንን ያስደሰቱትን ያህል፤ የእነሱን ተቃራኒ በተለይም ኦሮሞ ናሽናሊስቶችን ያስቆጣ እና ያስቀየመ ነበር። ዛሬ “አብይ የኦሮሙማ መንግስት እየመሰረተ ነው” እንደሚባለው ሁሉ፤ ያኔ “አብይ ወደ አሃዳዊው የነፍጠኛ ስርአት ሊመልሰን ነው። የቄሮ መስዋዕትነት መና መቅረቱ ነው” የሚል ወቀሳ እና ትችት ሲሰነዘር ነበር። በዚህም ምክንያት ኦሮሚያ ውስጥ ነጋ ጠባ ሰልፍ ማድረግ እና መንገድ መዝጋት፤ ከሌሎች ብሄረሰቦች (በተለይ የአማራ) ተወላጆች ላይ/ጋር ጥቃት/ግጭት ሲከሰት ነበር። የዛሬውን “ሸኔ” በሰው ሃይል እንዲንበሻበሽ ያደረገው ከፊል ምክንያትም ይኽው ነበር። ህወሃቶች በየሳምንቱ “የፌደራሊስቶች ጥምረት” የሚባል hodgepodge መቀሌ ላይ ሲሰበስቡ የነበረውም “አብይ አህመድ አሃዳዊ ስርአትን ሊመልስባችሁ ነው” በሚል ነበር። ይህም በሂደት በኦሮሚያ እና በትግራይ ጦርነት እንዲነሳ ከፊል አስተዋጾ ማድረጉ የሚታወቅ ነው።

አብይ አህመድ በዋነኛነት በሁለቱ ክልሎች ተቃውሞ እና ተቋቁሞ (resistance) ሲገጥመው፤ የ”አንድነት ሃይሉ” hubs ናቸው በሚባሉት በከተሞች እና በአብዛኛው የአማራ ክልል (የነዶክተር አምባቸው ግድያ እንደተጠበቀ ሆኖ ) ያለው ድጋፍ ከፍተኛ ነበረ። ኤሊቱም “አብይ ሙሴያችን” የሚል ነበረ። ሆኖም ግን የአብይ መንግስት ወይም አብይ ራሱ ከተናገራቸው በላይ እንዲፈጽም ፣ ከኦሮሞ እና ከትግራይ ኤሊቶች ጋር የገባበትን ፍጥጫ በሃይል እንዲፈታ፤ ያልተቋረጠ ውትወታ የ”አንድነት ሃይል ነኝ” በሚለውም ሆነ በተወሰነው የአማራ ልሂቅ ዘንድ ሲስተዋል ነበረ። አማራ ክልል ላይ በአሳምነው ጽጌ መሪነት እነ አምባቸውን የቀጠፈው ድርጊት የተፈጸመውም በዚህ አውድ ውስጥ ነው። ህወሐት ጥቅምት 24/2013 ላይ በእብሪት ተነሳስቶ ያንን ጥቃት ባይፈጽምና ጦርነት ባይጀመር ኖሮም፤ የተወሰነው የአማራ የፖሊቲካ ልሂቅ እና “የአንድነት ሃይል ነኝ” የሚለው ለአብይ ያላቸው/የነበራቸው ድጋፍ አሽቆልቁሎ እንደ ኦሮሞ እና ትግራይ ልሂቃን ወደ ተቃውሞ መለወጡ አይቀሬ ነበር። ስለዚህ ዛሬ በአማራ ልሂቃን እና “የአንድነት ሃይል ነኝ” በሚለው አካባቢ የምናየው ተቃውሞ የሰሜኑ ጦርነት ለሌላ ጊዜ አሸጋግሮት (postpone አድርጎት) ነው እንጂ አይቀሬ የነበረ ነገር ነው። አዲስ የተጨመረ ነገር ቢኖር ጦርነቱን ያስቆመው የፕሪቶሪያ ስምምነት የፈጠረው ተጨማሪ ክፍፍል እና ቅሬታ ነው። ከጦርነቱ በፊት ተጀምሮ የነበረው “የኦሮሙማ መንግስት” የሚባል bogeyman ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ያገረሸውም የቀድሞውን እርሾ እና ቁርሾ ጦርነቱ ከፈጠረው አዲስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተዳብሎ ነው። በዚህ ላይ የተጨማመሩ አባባሽ ነገሮች ማለትም በኦሮሞ እና በአማራ ብልጽግና መካከል ያለው ፉክክር መካረር፣ በአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች፣ መፈናቀሎች እና ግድያዎች አለመቆም፣ በጥቅሉ በአማራ እና በኦሮሞ ልሂቃን መሃከል ያለው ያለመተማመን ወዘተርፈ ናቸው።

ከላይ ከተዘረዘረው ባሻገር “አብይ ከዳን...አጭበረበረን” የሚሉ ወቀሳዎች politically ትርጉም-አልባ ሆነው ነው የሚታዩኝ። “አብይ ከዳን....አጭበረበረን” ለማለት፤ አብይ የገባልህ ቃል...የፈረመልህ ውል ሊኖር ይገባል። አይደለም በህዝቡ ቀጥተኛ ድምጽ መሪ በማይመረጥበት ፓርላሜንታሪ ስርአት፤ መሪው በቀጥታ በሚመረጥበት ፕሬዚደንታዊ ስርአት ውስጥም ቢሆን አንድ መሪ በበአለ ሲመቱ ላይ ካደረገው ንግግር (inaugural speech) ውስጥ የሚፈጽመው እና መፈጸም የሚችለው ጥቂቱን ነው። እርግጥ ነው አብይ እንደ መጀመሪያው አመት በየመድረኩ እየወጣ ”የአንድነት ሃይል ነኝ” ለሚለው እና ለአማራ የፖለቲካ ልሂቃን ጆሮ የሚጥሙ ንግግሮችን ማድረግ ቀንሷል ወይም ትቷል 🙂 ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ “የአንድነት ሃይል ነኝ” የሚለው እና የአማራ የፖለቲካ ልሂቃን political insatiability [ፖለቲካዊ አይጠረቄነት] እና አብይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ spectrum ከራሱ የፖለቲካ እና ማህበራዊ መሰረት (ማለትም የኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቅነት) ወደ “የአንድነት ሃይል ነኝ” ባዩ እና ወደ የአማራ የፖለቲካ ልሂቃን ለመጠጋት ለፈጸመው political stride ተመጣጣኝ ግብረ-መልስ (ወይም matching reciprocation) በመፈጸም ፋንታ፤ የራሳቸው የፖለቲካ እና ማህበራዊ መሰረት ላይ ተቸክለው “አንተው ምጣ....አንተው አምጣ” ማለታቸው ነው ብዬ አስባለሁ። ይሄም አብይን በሃገሪቱ ፖለቲካዊ ሂደት “ከሁለት ያጣ” እያደረገው ለመሆኑ በቂ ማሳያ መደርደር ይቻላል። ስለዚህ እንደ አንድ ፖለቲከኛ (አንዳንዶች ሲንቁት እና “ፓስተር...ሰባኪ” ብለው political sophistication የሌለው አድርገው ሲመለከቱት እንደነበር እና ዛሬም በንቀት እንደሚመለከቱት ልብ ይሏል) በተወሰነ ደረጃ ወደ ፖለቲካ እና ማህበራዊ መሰረቱ መለስ ማለቱ የማይጠበቅ ነገር አይደለም።

አብይ አህመድ እንደ ፖለቲከኛ ስልጣን ላይ ቆይቶ ያቀደውን ማሳካት ካለበት እና across the aisle ያሉት የእሱ counterparts ደግሞ ለሰጥቶ-መቀበል ፖለቲካ ተነሳሽነት ከሌላቸው እና ስሌታቸው ሁሉ zero-sum-game ከሆነ፤ ያለው አማራጭ ወደ ፖለቲካ እና ማህበረሰባዊ መሰረቱ ማፈግፈግ ነው። ስለዚህ አብይ አህመድ “ከዳ” ሳይሆን ወደ ፖለቲካ እና ማህበረሰባዊ መሰረቱ አፈገፈገ ነው የሚባለው 😁 እንዲህም ሆኖ አብይ አህመድ ግለሰባዊ ተክለ-ሰብዕናው ለኤትኖ-ናሽናሊዝም ምቹ አይደለምና ጠቅልሎ ወደዚያ political camp አልገባም። ሊገባም አይችልም። በሁለቱ (ማለትም የሃገረ-መንግስት ናሽናሊዝም (state nationalism) እና ethno-nationalism) ድንበር ላይ ላይ straddle አድርጎ ነው ያለው። ይህ ደግሞ በፖለቲካ ውስጥ በሚፈጠር የሃይል አሰላለፍ ወቅት የሚከሰት የተለመደ balancing act ነው። ይህ ፖለቲካን ጠንቅቆ ለሚረዳ ሁሉ ግልጽ ነገር ነው። ይሄን መረዳት ከደጋፊነት እና ከተቃዋሚነት ጋር ግንኙነት የለውም። አብይ አህመድን መስራት ሲገባው ላልሰራው፤ ማድረግ ሳይገባው ለፈጽመው ከመተቸትም አይጠብቀውም። ይህ እንዳለ ሆኖም “ከተራው ዜጋ” በተለየ “ምሁር ነኝ”...“ፖለቲካ በመተንተን ጥርሴን ነቅያለሁ” የሚሉ ግለሰቦች፤ ይህን አይነት መሰረታዊ የፖለቲካ dynamics በዝርዝር መመርመር እና ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል። ይህን ትተው እንደ “አልፎ-ሂያጅ ተንታኝ” (pedestrian expert/analyst) “አብይ ከዳኝ...አታለለኝ” ሲሉ ልሂቅነታቸው...ምሁርነታቸው የቱ ጋር እንደ ሆነ ይጠፋብኛል። ከፊት ሆነው ለመንጋው የመንገዱን ወጣ-ገባነት የሚመጥን አመላካች በማስቀመጥ ፋንታ፤ መንጋውን እየተከተሉ አብረው “እምቧቧቧ....” ሲሉ ይገርመኛል። ይሄ ችግር ብሄረሰብ ሳይለይ፤ በተለይ ደግሞ “በሶስቱ ጉልቤ ብሄረሰቦች” ልሂቃን ዘንድ ስር ስድዶ መታየቱ ያሳስበኛል።

በጎደለ ሙሉ!

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አ...
31/08/2023

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሾመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ ሹመቱን የሰጡት፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆኖ እንዲቋቋም በ1294/23 የራስ ገዝ አዋጅ በረቀቀው መሰረትና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ/28/2015 ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ተከትሎ ነው፡፡

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ እንዲፈጽሙ እንዲሁም የሰው ሀብትና የፋይናንስ አስተዳደር ነጻነትን በማረጋገጥ በአገሪቱ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የላቀ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ለማስቻል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ከተሾሙት ቻንስለር በተጨማሪም አዲስ የቦርድ አመራሮች የተሰየሙለት ሲሆን፤ ቦርዱም ዩኒቨርሲቲውን በሃላፊነት ሊመሩ የሚችሉ ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንቶችን በቀጣይነት እንደሚሾም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የግብፆች ርግማን ወደ ሔሚቲ እና ቢን-ዛይድ         የዓባይ:ልጅየግብፅ ማህበራዊ ሚዲያዎች ወደ ሱዳን መጮህ ጀምረዋል። በሱዳኑ ጦርነት ውስጥ አንደኛውን መልአክ ሌላኛውን በተቃራኒው አድር...
23/04/2023

የግብፆች ርግማን ወደ ሔሚቲ እና ቢን-ዛይድ

የዓባይ:ልጅ
የግብፅ ማህበራዊ ሚዲያዎች ወደ ሱዳን መጮህ ጀምረዋል። በሱዳኑ ጦርነት ውስጥ አንደኛውን መልአክ ሌላኛውን በተቃራኒው አድርገው በመሳል በዲጂታሉ ዘርፍ ዘምተዋል። የውጭ ሃያላን የሚዘውሩት ጦርነት መሆኑን ሱዳኖች ጠንቅቀው የሚያውቁት ነው። የግብፅ ሰዎች ዛሬ ነገሩን እንዳዲስ በማጉላት አልቡርን ከሱዳናዊያን ድጋፍ እንዲሰጠው ተማፅኗቸውን እያሰሙ ናቸው። ከውጭ ሀገራት ደግሞ አረብ ኢማራትንና እና ኤርትራን ያጠለሻሉ። ከመሳሪያ እስከ ወታደር በማቅረብ ይወነጅሏቸዋል። ቻድ፣ ሊቢያ እንዲሁም በስም ያልጠቀሷቸው ሀገራትንም አንድ ላይ አስገብተው እየረገማቸው ነው። ይህ ዘመቻ ለሱዳኖች "..አይናችሁን ጨፍኑ፣ ላሞኛችሁ.." እንደ ማለት ነው።

በአዲሱ የካይሮ ዲጂታል ጩኸት የሙሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ( ሔሜቲ) ፈጣን ድጋፍ ሰጪ RSF ኃይሎች በተለያዩ ግንባሮች ያስመዘገበውን ድል ተከትሎ የመጣ ነው። የአልቡርሐን ሰራዊት SAF ከአባይ በስተምስራቅ በሚገኝ የ RSF ኃይሎች ላይ የሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ በአፃፋው ከፍተኛ ርምጃ መውሰዱን ቡድኑ ገልጿል። በዚህ ማጥቃት ባላንጣውን እስከ ጦር ካምፑ ስለማሳደዱ ያስታወቀ ሲሆን ባሕሪ ከተማ ውስጥ ደግሞ 60 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ከነሙሉ ትጥቃቸው መማረካቸውን፣ 10 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማውደመማቸውን GeoConfirmed በተደረገ ቪዲዮ በይፋ አሳይተዋል። ቪዲዮው በአልቡርን የሚመራውን ሐሱዳን ወታደራዊ ኢንዱስትሪያልዜሽን ፋብሪካ ከዋና መስሪያ ቤቱ በቁጥጥር ስር ሲያውሉ ጭምር ያሳያል።
ይህን ተከትሎ አልሲሲ በቢን ዛይድ ላይ ከጀመረው ለቅሶ ባሻገር የአቡ ዳቢ ጂኦፖለቲካል ተቀናቃኟ ሳዑዲ አረቢያም ብስጭቷን መደበቅ አልቻለችም። ከመሸ የሚወጡ መረጃዎችም ይህንኑ የሚጠቁሙ ሲሆን ሪያድ በሀገሯ የሚገኙ የኢማራት ድርጅቶች ላይ እገዳ ጥላለች እየተባለ ይገኛል።
[ ሳዑዲ ይህን መሰል የበቀል ርምጃ ከጀመረች በተዘዋዋሪ እኛንም መነካካቱ የማይቀር ነው ]

ወደዛሬው የካይሮ ዘመቻ ይዘት እንመለስና በፅሁፉ የተካተቱት ማጭበርበሪያዎችን እንመልከት። ፅሁፉ የሚረግማቸው ሀገራት የመኖራቸውን ያህል የሱዳኑ ጦርነት የሕዝብ አሰፋፈርን የመለወጥ Demographic Change ለማድረግ የተጠነሰሰ ሴራ ነው ይላል። ይህ ወቀሳ ደግሞ በሔሜድቲ በኩል አርጎ የተባበሩት አረብ ኢማራት የነደፈችው ነው ይላል። እዚጋ በሱዳን የ Denographic Change ሴራ እየተከናወነ የሚገኘው በማን በኩል ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። እውነታው ግን የግብፅ የስለላ ድርጅት ነው በሱዳን የ Demographic Change ሴራ ላይ የሚገኘው። ይኸው የግብፅ የስለላ ተቋም EGIS 15 ሚሊዮን የሚደርሱ እጅግ አክራሪ የተባሉ የ ፉላኒ እና ሃውሳ ሕዝቦችን ከናይጄሪያ ድረስ በማንቀሳቀስ ሱዳን ውስጥ ራስ ገዝ መንግስት እንዲመሰርቱ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ነው የቆየው። ይህ የካይሮ ፕሮጀክት ከአልቡርሐን ጋር የሚደረግ ሲሆን ለሔሜቲ ደግሞ ስጋት ፈጥሮ የቆየ ነበር። በዚሁ ዙሪያ ሄሚቲ ንግግር ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ይህ የግብፅ ፕሮጀክተር ቀይ መስመር ነው" ማለታቸውም ይታወሳል። (ቀደም ሲል በዚሁ ዙሪያ ፅሁፍ አጋቼያለሁኝ)።

የሕዝብ አሰፋፈር ለውጥን ለበጎ ሳይሆን ለፖለቲካዊ ተንኮል በሱዳን የምትተገብረው ካይሮ ይህን ለማሳካት ቀደም ባሉ ዘመናት በተለይም በሱዳኑ ኑሜሪ ዘመነ ስልጣን ወቅት ከሀገር ተሰድደው የቆዩ አንዳንድ የአረብ ጎሳ አባላት በተመረጡ ቦታዎች መልሶ በማስፈር ነበር ግብፅ ስትሰራ የቆየችው።
በበርካታ ምሁራን እንደተገለፀውም እነዚህ በካይሮ የሰፈራ ፕሮጀክት ስር ታላሚዎች በኢትዮጵያውያንና በኤርትራውያን ላይ ከፍተኛ ጥላቻን ያነገቡ ናቸው። ሕዝቦቹ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር ላይ እንዲሰፍሩ ስራ ላይ የቆየችው ግብፅ ሂደታዊ ግቧ የሚያስጠላ ሰይጣናዊ አላማ የነደፈችለት ነው።
ዝርዝር ብዙ ነውና በዚህ ፅሁፍ የሚቋጭ አይሆንም ለጊዜው ግን ሔሜድቲ የካይሮን የሴራ ካብ ማንደድና ማፍረሱ እየተስተዋለ ሲሆን የግብፅ ብቸኛው የጦር መሳሪያ ደግሞ Disinformation በመሆኑ ባለቻቸው አማራጭ ሱዳኖችን ለማሞኘት እየተንደፋደፉ ናቸው። ጆሮ የሚሰጣቸው ሱዳናዊ ማግኘት ዘበት ቢሆንም..። ግብፅ ለዘመናት በሱዳን ላይ ምን ያህል የክህደት ተግባራት እንደፈፀመችባቸው ሱዳኖች ጠንቅቀው መረዳት በመጀመራቸው። ከሱዳናዊ ወንድሞቼ ጋር ለአመታት በዲጂታሉ አውድ የነበረኝ ውይይትም ይህንኑ ሐቅ ስለሚያስረግጥ .... ሱዳኖችም ድጋሚ በግብፅ የውሸት ዘመቻ ስለማይሸወዱ...!!
ሰላም ለሱዳናዊያን

▪️Esleman Abay #የዓባይልጅ

‎ #ኢትዮጵያ ‎
‎ #السودان ‎
‎
‎

44 ግራም ወርቅ በላም ሆድ ውስጥ ያገቹ አርሶ አደሮች 105 ሺህ ብር ሸጡ።ጉዳዩ እንዲህ ነዉ። በጎጃም ክፍለሃገር አገዉ ምድር አዉራጃ በአዲስ ቅዳም ከተማ በአዝማች ቀበሌ በዓሉን ምክንያት ...
20/04/2023

44 ግራም ወርቅ በላም ሆድ ውስጥ ያገቹ አርሶ አደሮች 105 ሺህ ብር ሸጡ።

ጉዳዩ እንዲህ ነዉ። በጎጃም ክፍለሃገር አገዉ ምድር አዉራጃ በአዲስ ቅዳም ከተማ በአዝማች ቀበሌ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለትንሳኤ በዓል ለቅርጫ ላም ያረዱ የቀበሌ ነዋሪዎች በላሟ ሆድ ውስጥ 44 ግራም ወርቅ የተገኘ ሲሆን ወርቁን ለገበያ በማቅረብ 105 ሺህ ብር ሽጠውታል።

የዳግሎ ጦር ፕሬዚደንታዊ ቤተመንግሥቱን መቆጣጠሩን ገለጸ‼️በሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ዋና እና ምክትል ሰብሳቢ በሆኑት አልቡርሃን እና ሀምዳን ዳጋሎ ኃይሎች መካከል ካርቱም ውስጥ ግጭት ተፈ...
15/04/2023

የዳግሎ ጦር ፕሬዚደንታዊ ቤተመንግሥቱን መቆጣጠሩን ገለጸ‼️

በሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ዋና እና ምክትል ሰብሳቢ በሆኑት አልቡርሃን እና ሀምዳን ዳጋሎ ኃይሎች መካከል ካርቱም ውስጥ ግጭት ተፈጥሯል። ከደቂቃዎች በፊት በአልቡርሃን ኃይሎች ቁጥጥር ስር የነበረው የሱዳን ብሄራዊ ቴለቪዥን ጣቢያ የቀጥታ ስርጭቱ በአሁኑ ሰዓት ተቋርጧል።
የጄኔራል ዳግሎ (ሒሚቲ) የፈጥኖ ደራሽ ጦር ካርቱም የሚገኘውን ፕሬዚደንታዊ ቤተመንግሥት መቆጣጠሩን አስታውቋል። የሱዳን ሠራዊት በከባድ የተኩስ ልውውጡ ብዙዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን ቢገልጽም፤ ምን ያህል እንደሆኑ ግን አለመታወቁን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

ፎርብስ ፡ የሀብቷ መጠን ከ1.4 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ነው ብሎ ስለሷ ሳይፅፍ. ...... ዘመናዊ የግል ጄት ሳይኖራት  ... እንዲህ ዝነኛ ሆና እኛ እንኳን ስለሷ ከመጻፋችን ከብ...
14/04/2023

ፎርብስ ፡ የሀብቷ መጠን ከ1.4 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ነው ብሎ ስለሷ ሳይፅፍ. ...... ዘመናዊ የግል ጄት ሳይኖራት ... እንዲህ ዝነኛ ሆና እኛ እንኳን ስለሷ ከመጻፋችን ከብዙ አመታት በፊት ...
ጄይዚም ሳያውቃት ሳያገባት ፡ ሳያስወልዳት. ...፡ ገና ድሮ . ..ድሮ . ... ገና በአስራዎቹ እድሜ ውስጥ እያለች. .. ደቡብ አሜሪካን ውስጥ በምትገኝ ፡ 280 ሺህ ህዝብ ብቻ የሚኖርባት ሀገር ውስጥ ፡ ወጣት ወታደር ነበረች ።
ነገር ግን ፡ በውስጧ ህልም ነበር. .. ያንን ህልም ፡ ያንን ራእይ ነው ፈልጋ ያገኘችው ። ሪሃና ።
ህልምህን ፈልግ. .. የእለቱ መልእክታችን ነው ።

አባቴ እናዝናለን ፡ ካሁን በኋላ በምድር ላይ የሚቆዩት ግፋ ቢል ለስድስት ወራት ያህል ነው ። .......እኚህ በምስሉ ላይ የሚታዩት አባት  Stamatis Moraitis የሚባሉ በወጣትነት ...
14/04/2023

አባቴ እናዝናለን ፡ ካሁን በኋላ በምድር ላይ የሚቆዩት ግፋ ቢል ለስድስት ወራት ያህል ነው ። .......

እኚህ በምስሉ ላይ የሚታዩት አባት Stamatis Moraitis የሚባሉ በወጣትነት ዘመናቸው ሀገራቸው ግሪክን በወታደርነት ያገለገሉ ሰው ናቸው ።
እና በአንድ ወቅት ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን ለመጎብኘት በሄዱበት አሜሪካ ትንሽ ህመም ይሰማቸውና ወደ ሆስፒታል ይሄዳሉ ።
ሀኪሙ ግሪካዊውን ሰው በተለያየ አይነት የህክምና ዘዴ ከመረመረ በኋላ ፡ ሰውየው በማይድን የሳንባ ካንሰር እንደተያዙና ፡ ካሁን በኋላ በህይወት የሚቆዩት ለስድስት ወራት እንደሆነ ነገራቸው ። የዶክተሩን የምርመራ ውጤት ካዩ በኋላም ዘጠኝ አባላት ያሉት የዶክተሮች ቡድን ፡ ስለውጤቱ ትክክለኛነት ፈረሙበት ።

ይህን የሰሙት ሚስተር Stamatis አዘኑ ፡ ወደልጆቻቸው ቤት ከተመለሱ በኋላም መርዶውን ነግረዋቸው ተያይዘው ተላቀሱ ።
እንግዲህማ ወደ ሀገሬ ግሪክ ልሂድ ፡ ሞቴ እዛ ይሁን ቀብሬም አባት አያቶቼ ባረፉበት ቦታ ይፈፀማል በማለት ፡ ከጥቂት ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ግሪክ ተመለሱ ።

Stamatis Moraitis ወደ ግሪክ ከተመለሱ በኋላ ምንም እንኳን ከስድስት ወራት በኋላ እንደሚሞቱ ፡ በአስር ሀኪሞች የተፈረመ ፡ ወረቀት ቢይዙም ፡ ለወትሮ ከሚሰሩት ስራ አልታቀቡም ።
በህይወታቸው ውስጥ የተከሰተ ምንም አይነት ለውጥ እንደሌለ ቆጥረው ፡ እንደድሮው አትክልቶቻቸውን ይንከባከባሉ ፡ ወራት ለቀረው እድሜ ፡ ለመድረስ አመታትን የሚፈልጉ ፍራፍሬዎች ይተክላሉ ፡

እንዲህ እንዲህ እያሉ ፡ ሳይታወቅ ያቺ የቀጠሮ ወር ደረሰችና ፡ ለመሞት ቀናትን መቁጠር ጀመሩ ። ግን ምንም የለም ። ሰውነታቸው ደክሞ ከዛሬ ነገ ድንገት እወድቅ ይሆን እያሉ በስጋት በመጠባበቅም ፡ ስድስት ወሩን አለፉት ።
ሰባተኛ ወር ገባ ። ምንም የለም ።
አመት አለፈ ። ሰውየው ጭራሽ ንቁና ብርቱ መሆን ጀመሩ ። ሁለት ሶስት አመት አለፈ ። እንዲህ እንዲህ እያለ ፡ አስር አመት ሆናቸው እንደውም ፡ በፊት አልፎ አልፎ ይሰማቸው የነበረው የህመም ስሜት ራሱ ጠፋ ።

እናም በአስረኛ አመታቸው ፡ ልጆቻቸውና ፡ የልጅ ልጆቻቸው ወደ ሚኖሩበት አሜሪካ ሄደው ሊያዩዋቸው ፈለጉና ወደዛ ተጓዙ ።
ካሁን አሁን መርዶ እንሰማ ይሆን ብለው ለአመታት የጠበቁት ዘመዶቻቸው ጋር በአካል ተገናኙ ። ..........
ከቀናት ቆይታ በኋላ ፡ ከዛሬ አስር አመትበፊት ፡ ለመሞት ስድስት ወራት ብቻ እንደሚቀራቸው የነገሯቸው ዶክተሮች ያሉበት ሆስፒታል ሄደው ሰላም ሊሏቸው በዛውም አስሩም ዶክተሮች የፈረሙበትን ወረቀት ለዶክተሮቹ ሊያሳዩዋቸው ያዙና ወደ ሆስፒታሉ ሄዱ ።
ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ፡ አንድም ዶክተር ማግኘት አልቻሉም ። ሁሉም ሀኪሞች በተለያየ ጊዜ በህመም አልፈዋል ። .....
ግሪካዊው Stamatis Moraitis ከአስር አመታት በፊት ይህን ምርመራ ሲያደርጉ የስልሳ አመት አዛውንት ነበሩ ። እና ይሞታሉ ከተባሉ በኋላ ለሌላ ለ42 አመታት በህይወት ኖረው ፡ በ102 አመታቸው ከጥቂት አመታት በፊት አልፈዋል ።............
ጥያቄው አስር ዶክተር ፈረመ ? ሳይሆን ፡ ከላይ ተፈርሟል ወይ ነው ።

Wasihune Tesfaye

👉ተርበዋል ግን የሚናገርላቸው አክቲቪስት የላቸውም !! ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በተገኘው መረጃ መሰረት በደቡብ ኦሞ ዞን 337,922 ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። 🙏
06/04/2023

👉ተርበዋል ግን የሚናገርላቸው አክቲቪስት የላቸውም !! ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በተገኘው መረጃ መሰረት በደቡብ ኦሞ ዞን 337,922 ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። 🙏

ሰውነቱ መዛል የጀመረው ፡ ብዙም ሳይቆይ ነው ። ወጣት ሆኖ ወዲያ ወዲህ እያለ ሳይዘንጥ ፡   ሞተር ኒውሮን  በሚባል ያልተለመደ  በሽታ ተያዘ ። እግሮቹ ሰውነቱን መሸከም አቃታቸው ።  ከቤ...
30/03/2023

ሰውነቱ መዛል የጀመረው ፡ ብዙም ሳይቆይ ነው ። ወጣት ሆኖ ወዲያ ወዲህ እያለ ሳይዘንጥ ፡ ሞተር ኒውሮን በሚባል ያልተለመደ በሽታ ተያዘ ። እግሮቹ ሰውነቱን መሸከም አቃታቸው ። ከቤተመፅሀፍት ፡ ትምህርት ቤት መሮጥ ቀረ ፡ እና ሙሉ ለሙሉ መንቀሳቀስ አቃተውና በ21 አመቱ ፡ ዊልቸር ላይ ተቀመጠ ። እናም ያኔ የተቀመጠ ከዛ ዊልቸር ላይ ለሀምሳ አመታት አልተነሳም ፡

ልናወራ ያሰብነው ፡ታላላቅ ግኝቶችንና ምርምሮችን አበርክቶ ስላለፈው ፡ ስለታላቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ስቲቭን ዊሊያም ሃውኪንግ ነው ። እና ይህ ሰው ፡ በዛ እድሜው ዊልቸር ላይ ሲቀመጥ ፡ አይ አለም ከንቱ ብሎ ነገር አለሙን አልተወውም ። እንደውም ይብስ ምርምሩን ቀጥሎ ፡ በጠፈር ምርምር ዘርፍ ታላላቅ ግኝቶችን መጻፍ የጀመረው ከዛ በኋላ ነው ።

ስቲቭን በዚህ ሁኔት ውስጥ ሆኖ ፡ አንድ መፅሀፍ ፡ ሁለት መፅሀፍ. ..ሶስት. ...አራት. ....እያለ ምርምሮቹንና ግኝቶቹን እየጻፈ ቆየ ።
ያ በወጣትነቱ እግሮቹን ያሰረው በሽታም ወደሚፅፍባቸው እጆቹ መጣ. ... የአንድ እጁ ጣቶች ቀስ በቀስ መዛል ጀመሩ ፡ በሽታው መላ ሰውነቱን እያጠቃ ሰውነቱን ጠቅላላ ማሽመድመዱን ቀጠለ ፡ ሰውየው ግን ስራ አልፈታም ፡ቀስ በቀስ ሰውነቱ መዛሉን ቀጥሎ ጣቶቹ ብቻ መንቀሳቀስ ጀመሩ ።

ምርምሮቹንና የሚያስበውን ነገሮች እየተናገረ ሰው እንዳይፅፍለት ፡ አንደበቱ በበሽታው ከተዘጋ ቆይቷል ፡ እናም በመጠኑ በሚንቀሳቀስ ጣቶቹ መጻፍ በሚያስችለው መሳሪያ አማካኝነት ምርምሩን መጻፍ ቀጠለ ፡ ጎን ለጎንም የመፅሀፎቹ ቁጥር አስር ደረሱ ፡ አስራ አንድ ፡ አስራ ሁለት. ...እያለ እያለ ይህችን ምድር ለቆ ከመሄዱ በፊት እውቀቱን ትቶ ለማለፍ ከበሽታው ጋር መታገሉን ቀጠለ ።
ከዛስ. ..

እያለ እያለ ሙሉ ለሙሉ በድን ሆኖ ሰውነቱን ምንም ማዘዝ ተሳነው ። በተቃራኒው አእምሮው ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም እጅግ ምጡቅና አክቲቭ ነበር ።
እናም መጨረሻ ላይ ሰውነቱ ጠቅላላ ዝሎ ከመላ ሰውነቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ቀኝ ጉንጩ ብቻ ነበር ።

ፕሮፌሰር ስቲቭን ዊሊያም ሃውኪንግ በሞተር ኒውሮን በሽታ ከተለከፈበት ጊዜ አንስቶ የሰውነቱ አካላትን እየለዩ እጁ ሲታዘዝ በጁ የሚሰራ ማገዣ መሳሪያ ሲፈለስፉለት የነበሩት የካምብሪጅና የአይቴል ኮምፒውተር ሰወች በመጨረሻም ሁሉም የሰውነት ክፍሎቹ እየሞቱ ትንሽ እንቅስቃሴ የምታሳየው ብቸኛ የአካሉ ክፍል ቀኝ ጉንጩ መሆኑን ሲረዱ በሷ ሊንቀሳቀስ የሚችል መርጃ መሳሪያ ለመስራት ጥናት አደረጉ ።

በመጨረሻም አእምሮው ያሰበውን ተረድቶ ወደቀኝ ጉንጩ መልእክት የሚያስተላልፍ በመነጽር ላይ የሚገጠም divice ፈጠሩለት ። ይህ መሳሪያ እስኪሰራለት ቦዝኖ የነበረው ይህ ሰውዬ ፡ መነፅሩን እንዳገኘ ወደስራው ተመልሶ መጻፉን ቀጠለ ፡ አስራ ስምንተኛ መፅሃፉ ታተመ ፡ አስራ ዘጠነኛው. ..በመጨረሻም BRIEF ANSWERS TO THE BIG QUESTIONS የሚለውን የመጨረሻ መፅሀፉን አሳተመ ። በምን ፅፎት. .. በትንሹ በምትንቀሳቀሰው የቀኝ ጉንጩ ።

መላ ሰውነቱ በድን ሆኖ ፡ በጉንጩ ብቻ በመታገዝ ብዙ ምርምሮችን ያበረከተበት ይህ ልዩ መነፅር በብሪትሽ የሳይንስ ሙዚየም ውስጥ ተቀምጦ ይጎበኛል ።

የዚህ ሰው ጥንካሬ. .. የሚሰጠን ትልቅ ትርጉም አለና ልብ እንበለው ።

በትግራይ ሰዎች በረሃብ እየሞቱ ነው በሚል ሲገለጽ የነበረው በማስረጃ ያልተደገፈ፡ በፖለቲካ የተቃኘ ነው ሲሉ የዓለም የምግብ ፕሮግራም WFP የቀድሞ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ገለጹ። ዳይሬክተሩ ...
21/01/2023

በትግራይ ሰዎች በረሃብ እየሞቱ ነው በሚል ሲገለጽ የነበረው በማስረጃ ያልተደገፈ፡ በፖለቲካ የተቃኘ ነው ሲሉ የዓለም የምግብ ፕሮግራም WFP የቀድሞ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ገለጹ። ዳይሬክተሩ ዶ/ር ስቴፈን ኦማሞ አዲስ ባሳተሙት at the center of the world in Ethiopia በተሰኘው መጽሀፋቸው የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታን ለፖለቲካ መሳሪያነት ይጠቀማል ወይም እርዳታው እንዳይደርስ መስመሮችን ይዘጋል በሚል በህወሀትና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚቀርበው ክስ መሰረት የሌለው፡ መሬት ላይ ያለውን እውነት የማያሳይ ሲሉ ገልጸውታል። ለሄርሜላ ቲቪ በሰጡት ቃለመጠይቅም ይሄንኑ አረጋግጠዋል።
https://youtu.be/QsuH2EHf2aA
ቴሌግራም ቻናል https://t.me/anchormedia5

ሮዝመሪ አዲሱ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ። ስልጤ ዞን ባለፈው አመት አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ኤክስፖርት አድርገው ነበር አሁን አገሩን እየሞሉት ነው። ባህር ዛፍ ባበላሸው ቀይና አሲዳማ አፈር ...
21/01/2023

ሮዝመሪ
አዲሱ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ። ስልጤ ዞን ባለፈው አመት አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ኤክስፖርት አድርገው ነበር አሁን አገሩን እየሞሉት ነው። ባህር ዛፍ ባበላሸው ቀይና አሲዳማ አፈር ይበቅላል። እንደ ኖራ ደግሞ አፈሩን ያክማል።

This death staircases in Machu Picchu; Peru, is 500 years old and was built by the Incas to reach the Temple of the Moon...
12/01/2023

This death staircases in Machu Picchu; Peru, is 500 years old and was built by the Incas to reach the Temple of the Moon.

የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ  ሠራዊታቸው ‘ፀብ ጫሪ እና ተንኳሽ ኃይልን አስታግሷል’ ሲሉ ገለጹ። የፈረንጆቹን አዲስ አመት አስመልክተው ለህዝባቸው ባስተላለፉት መልዕክት በስም...
03/01/2023

የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ሠራዊታቸው ‘ፀብ ጫሪ እና ተንኳሽ ኃይልን አስታግሷል’ ሲሉ ገለጹ። የፈረንጆቹን አዲስ አመት አስመልክተው ለህዝባቸው ባስተላለፉት መልዕክት በስም ያልጠሩትን አካል ወረራ ለመፈጸም ሲፍጨረጨር ሰራዊታችን ተገቢው መልስ ተሰጥቶታል ማለታቸውን በኤርትራ ቴሌቪዥን ከተሰራጨው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። በአሜሪካን ዋሽንገተን ዲስ የኤርትራውያን ኮሚኒቲ አባል አቶ ዮሀንስ ክፍሌ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ በስም ያልተጠራው አካል ህወሀት እንደሚሆን ግምታቸውን ከገለጹ በኋላ ምናልባትም ህወሀት ጀርባ ያሉ ሃይሎችንም የሚያመለክት ይሆናል ሲሉ ለአንከር ሚዲያ በሰጡት አጭር ቃለመጠይቅ ገልጸዋል። ህወሀት ለኤርትራ ስጋት መሆን በማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል የሚሉት አቶ ዮሀንስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈጠረው የትብብር ስምምነት የጋራ ጠላትን ለመዋጋት መቼም ቢሆን አንድ ላይ እንዲቆሙ ያደርጋቸዋል ይላሉ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ በ21 ግለሰቦች በአርሶ አደርና በአርሶ አደር ልጅ ስም ለ11 ግለሰቦች ካርታ በማዘጋጀት 5 ሺህ 593 ካሬ ሜትር ይዞታ...
03/01/2023

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ በ21 ግለሰቦች በአርሶ አደርና በአርሶ አደር ልጅ ስም ለ11 ግለሰቦች ካርታ በማዘጋጀት 5 ሺህ 593 ካሬ ሜትር ይዞታን መብት በማፅናት እና አማካይ የሊዝ ዋጋው ከ11 ሚሊየን ብር የሆነ የመንግስት ባዶ ቦታን ወስደዋል እና እንዲወሰድ አድርገዋል በሚል ነው ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው፡፡

በዛሬው እለት ክስ የተመሰረተባቸው ተክሳሾች የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መልካሙ በቃናን ጨምሮ ሌሎች በተለያየ የአመራርነት እና በባለሙያነት እያገለገሉ የሚገኙ ግለሰቦች ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ግለሰቦቹ ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በጥቅም በመመሳጠር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያወጣውን መመሪያ ቁጥር 4/2007 መሰረት የይዞታ ማረጋጋጫ የሚጠይቅ ሰው ማሟላት የሚገባውን መስፈርት ያላሟሉ፣ በህገወጥ መንገድ አርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጅ ነን ያሉ 11 ግለሰቦችን የይዞታ ካርታ በማዘጋጀት አማካይ የሊዝ ዋጋው ከ11 ሚሊየን 900 ሺህ 67 ብር ከ31 ሳንቲም የሆነ የመንግስት ባዶ ቦታን በመስጠት፣ የካርታ መብት በማፅናት እንዲሁም 5 ሺህ 593 ካሬ ሜትር ይዞታን በህገወጥ መንገድ ወስደዋል ሲል ዐቃቤ ህግ በክሱ ዘርዝሯል።

በአጠቃላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1 ሀ እና የሙስና ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 9/1 ሀ እና ንዑስ ቁጥር 2 በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት እና በልዩ ወንጀል ተካፋይ በመሆን ስልጣንን ያለአግባበብ በመጠቀም በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

ከተከሳሾቹ መካከል የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መልካሙ በቃና እና የክፍለ ከተማው የመሬት ማስከበር ጥበቃ ኦፊሰር ካርታ አረጋጋጭ ባለሙያ ገለታ ደበሌ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጽህፈት ቤት ከጠበቃቸው ጋር ቀርበው ክሱ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

በታሪክ አዱኛ

የፋይናንስ ደህንነት ዋዳ ዳሪክተር አቶ ቴድሮስ በቀለ ከነ ባለቤታቸው እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንንነት አስታዳደር የመረጃ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ኃላፊ አቶ ባህሩ ደምሴን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎ...
13/12/2022

የፋይናንስ ደህንነት ዋዳ ዳሪክተር አቶ ቴድሮስ በቀለ ከነ ባለቤታቸው እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንንነት አስታዳደር የመረጃ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ኃላፊ አቶ ባህሩ ደምሴን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች ከ5ሚሊዮን ብር በላይ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ።

በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎቹ 1ኛ የፋይናንስ ደህንነት ዋዳ ዳሪክተር አቶ ቴድሮስ በቀለ እና ባለቤታቸው ወ/ሮ እሩት አድማሱ÷ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንንነት አስታዳደር የመረጃ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ኃላፊ አቶ ባህሩ ደምሴን እንዲሁም የወ/ሮ ሩት እህት ወ/ሮ ቤቴሊዬም አድማሱ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ተጠርጣሪዎቹ አቶ ቴድሮስ እና አቶ ባሀሩ በአገልግሎት ማዕከል ውስጥ የተሰጣቸውን ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም ከግብረአበሮቻቸው ጋር በጥቅም በመመሳጠር የሚሰሩበትን ድረጅት እና የባለሀብቶችን የስልክ ግንኙነት በመከታተልና በመጥለፍ መረጃ በመውሰድ ባለሀብቶች ገንዘብ እንዲከፍሉ በመጠየቅና ካልከፈሉ ደግሞ የፋይናንስ እቅስቃሴያቸው ከወንጀል ጋር ግንኙነት ያለው በማስመሰል የወንጀል ምርመራ እንዲደረግባቸው ለፖሊስ እንደሚሰጡባቸው በመግለጽና በማስፈራራት ጫና በመፍጠር ከበርካታ ሰዎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘቦ በመቀበል በሙስና ወንጀል መጠርጠራቸውን ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ገልጿል።

በዚህ መልኩ ለጊዜው 5 ሚሊዮን ብር ተቀብለው ለግል ጥቅም ማዋላቸውን ጠቁሞ ማስረጃ መሰብሰቡን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስለው በመጠቀም በወንጀሉ ተካፋይ ናቸው ተብለው በተጠረጠሩት በአቶ ቴድሮስ በቀለ ባለቤት ሩት አድማሱና በ4ኛ ተጠርጣሪ የሩት እህት በሆነችው በወ/ሮ ቤቴሊዬም አድማሱ ስም ገቢ እንዲሆን እንደተደረገና እነዚህ ተጠርጣሪዎችም የወንጀል ተካፋይ በመሆን ገንዘቡን በጋራ በመደበቅ እና በመጠቀም መጠርጠራቸውንም አብራርቷል።

በተጨማሪም 1ኛ ተጠርጣሪ በጥቅም ከተሳሰራቸው ግለሰቦች ጋር በመሆን ከዳንጓቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስልጣንን በመጠቀም ኮታና ቅድሚያ እንዲሰጣቸው በማድረግ ሲሚንቶ አውጥቶ እንዲሸጥ በማድረግ ወንጀል መጠርጠሩንም ፖሊስ ለችሎቱ አክሎ ገልጿል።

በዚህ መልኩ እየተከናወነ ለሚገኘው ምርመራው ተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ እንዲያስችለው መርማሪ ፖሊስ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ ተብሎ በስር ማቆየት የግድ አይልም ሲሉ መከራከሪያ ነጥብ አንስተዋል።

የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ በዋስ ቢወጡ ማስረጃ ሊያጠፋብን ይችላሉ ሲል ነዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል።

የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ አዱኛ
ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ተጨማሪ ምርመራ ማስፈለጉን በማመን ለፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።

(ታሪክ አዱኛ)

መቀሌ‼ዛሬ በመቀሌ ከተማ የህውሃት ከፍተኛ አመራሮችና ጦርነቱን ሲመሩ የነበሩ ጀኔራሎች ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቋል።በስብሰባው ላይ ትጥቅ ስንፈታ ✔የጉዳት ካሳ ሊከፈለን ይገባል✔ወደ መከላከያው...
10/11/2022

መቀሌ‼

ዛሬ በመቀሌ ከተማ የህውሃት ከፍተኛ አመራሮችና ጦርነቱን ሲመሩ የነበሩ ጀኔራሎች ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቋል።

በስብሰባው ላይ ትጥቅ ስንፈታ
✔የጉዳት ካሳ ሊከፈለን ይገባል
✔ወደ መከላከያው መቀላቀል አለብን
✔ጡረታችን ተከብሮ ልንሰናበት ይገባል የሚሉ ሶስት ጥያቄዎች ማንሳታቸውን ለማወቅ ተችሏል።ይህ ይደረግላችኋል ብለን የምንገባ ቃል የለም በሚል ከሰብሳቢ ምላሽ መሰጠቱም ተሰምቷል።

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ።ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ የተቋረጡ የጤና አገልግሎቶች እንደገና እንዲጀምሩ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት (EU) የ31...
10/11/2022

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ።

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ የተቋረጡ የጤና አገልግሎቶች እንደገና እንዲጀምሩ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት (EU) የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ያደረገው የማስጀመር እና የአቅም ግንባታ ስራ እንዲሰራ ለማስቻል ለተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) መሆኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የተደረገው ድጋፍ የህፃናትና ሴቶች ኑሮ ለማሻሻልና በግጭቱ ሳቢያ ከደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ እንዲሁም የጤና አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ለማድረግ ነው።

የኢትዮጵያ ኃይላት ስምምነቱን እንዲያከብሩ ኬንያና ደቡብ አፍሪቃ ጠየቁየኢትዮጵያ ፈደራዊ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባለፈዉ ሳምንት የተፈራረሙትን ስምምነት ሙሉ በሙሉ...
09/11/2022

የኢትዮጵያ ኃይላት ስምምነቱን እንዲያከብሩ ኬንያና ደቡብ አፍሪቃ ጠየቁ

የኢትዮጵያ ፈደራዊ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባለፈዉ ሳምንት የተፈራረሙትን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የደቡብ አፍሪቃና የኬንያ መሪዎች ጠየቁ። ናይሮቢን የሚገበኙት የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሬዝደንት ሲሪያል ራማፎዛና የኬንያዉ አስተናጋጃቸዉ ዊሊያም ሩቶ ዛሬ በጋራ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት ግጭት ለማቆም መስማማታቸዉን ያደንቃሉ።

ይሁንና ሁለቱ መሪዎች እንዳሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፋን ተፈራራሚ ኃይላት ስምምነታቸዉን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አለባቸዉ። የኢትዮጵያ መንግስትና የህወሓት ተወካዮች ሁለት ዓመት ያስቆጠረዉን ጦርነት በሰላም ለመፍታት የተስማሙት ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ለዘጠኝ ቀናት ከተደራደሩ በኋላ ነዉ። የሁለቱ ወገኖች የጦር አዛዦች ደግሞ ስምምነቱ ገቢራዊ ስለሚሆንበት፣ በተለይም የህወሓት ተዋጊዎች ትጥቅ ስለሚፈቱበት ስልት ካለፈዉ ሰኞ ጀምሮ ናይሮቢ-ኬንያ ዉስጥ እየተነጋገሩ ነዉ።

የንግግሩ ዉጤት በይፋ አልተነገረም። የደቡብ አፍሪቃና የኬንያ ፕሬዝደንቶች አንድናቆትና ጥያቄ የተሰማዉም የሁለቱ ወገኖች ንግግር ዉጤት በሚጠበቅበት ወቅት ነዉ። የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት በኬንያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉት ጉብኝት ዋና ዓላማ በሁለቱ ሐገራት የንግድ፣ የዜጎች ዝዉዉርና የቪዛ ጉዳይ ለመወያየት ነዉ። ሁለቱ መሪዎች የኬንያ ዜጎች ደቡብ አፍሪቃን ለዘጠና ቀናት ያሕል ያለ መግቢያ ቪዛ እንዲጎበኙ ተስማምተዋል።የደቡብ አፍሪቃ ዜጎች ከዚሕ ቀደምም ያለ ቪዛ ኬንያን መጎብኘት ይችሉ ነበር።

(ፎቶ፣ ናይሮቢ በከፊል)

የህወሓት ጀኔራሎች ጭቅጭቅ————————ወዲ 1..."ውጊያው ለእኔ ተውት...እንደባለፈው ከመንገድ አንመለስም" ብለህ ያስጨረስከን አንተ ነህ።ወዲ 2....አለም ሲያከብረኝ...እንደ ቡና ቤት የ...
20/10/2022

የህወሓት ጀኔራሎች ጭቅጭቅ
————————
ወዲ 1..."ውጊያው ለእኔ ተውት...እንደባለፈው ከመንገድ አንመለስም" ብለህ ያስጨረስከን አንተ ነህ።

ወዲ 2....አለም ሲያከብረኝ...እንደ ቡና ቤት የማታከብሩኝ እናንተ ናችሁ...በቂ ሠው አልመለመላችሁልኝም...ወሬ ብቻ ሆናችሁ።

ወዲ3...እባካችሁ...ፅንዓት......ትግራይ ታሸንፋለች!

ወዲ 4....ዝም በል...እየተሸነፍን ታሸንፋለች እያልን የትኛው አለምአቀፍ ኃይል እንዲረዳን ነው።

ወዲ 5...ወሬኞች አስጨረሳችሁን...በወሬ ተወጥረን ተዋጊያችን አልቆ አቢይ በራችን ላይ ደርሷል።

ይህ በሽብር ቡድኑ አመራሮች መካከል ሽንፈት የወለደው ወቅታዊ ጭቅጭቅ ነው።

ታዲያ ምን ይደረግ?! የሽብር ቡድኑ ሰራዊቱ መፍረስ- መፈረካከስ ፣ ቁሞ መከላከል አለመቻል፣ አመራሮች ( እነ ወዲ...) ከተደበቁበት ስውር ቦታ ላይ በተደረገ የረቀቀ ሰርጂካል ኦፕሬሽን ወደ ሲኦል የመሸኘታቸው የሽንፈት ናዳ አመራሩን ለሴራ ትንተና ዳርጎታል። ሽንፈቱ ለእኩይ አላማ በተሰባሰበው የሽብር ቡድን አመራር መካከል ከፍተኛ ጥርጣሬ ፈጥሯል።

እርግጥ ነው ከሽብር ቡድኑ አመራር መካከል በሰሩት ክፋት እንቅልፍ አጥተው ሀገራችንን በምን እንካስ በማለት እገዛቸውን ለመንግስት እየሰጡ ያሉ ሀገራቸውም በምላሹ አፉ ልትላቸው የተዘጋጀችላቸው አልጠፉም። በሌላ በኩል ህፃናት ታጣቂዎቻቸውን በአንገታቸው የሀሽሽ ማተብ አስረው የማሽላ አጥር አድርገው የማገዱ በሰው ደም በመጨማለቅ ያረጁም አሉበት።

በደም የሠከሩት አዛውንት ውጊያው ሲጧጧፍ፣ ምድር ሲሞቅ ፣ የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች ክንድ ሲበረታ፣ የሽብር ቡድኑ የመከላከል መስመር ሲናድ፣ ምሽጉ ሲደረመስ ከሩቅ ጓዳ ተወሽቀው "ያዝ" "ያዝ" ሲሉ ይቆያሉ። ሕፃናት የማሽላ አጥሮቻቸው አልቀው ሲፈርሱና ሲሸሹ ከኋላ በጥይት አረር ቆልተውና ፈጅተው ፣ ይህም አልሆን ብሎ ምቱ ሲቀርብ መፈርጠጥ የተፈጠሩበት የፈሪ መንገድ ሆኗል ።

እርግጥ ነው ዕብሪት እንጂ የውጊያ አቅም የሌላቸው የውጊያ አመራሮች መኖራቸው በውጤቶቹ ታይቷል። ያም ሆነ ይህ ምቱ ቀጥሏል። በሽብር ቡድኑ የጎሪጥ የመተያየቱ መነሻ የሆነው ጉዳይ ይሄው እውነት ነው። ይህም የመንግስታችን የፀጥታ ተቋማት በሚገርም ቅንጅት ረቂቅ ስራ ላይ መሆናቸውን የሚያበስር ውጤት ነው።

ጦርነቱ እያበቃ ነው ማለት ይቻላል——————————————————በምዕራብ ግንባር በማይፀብሪ አካባቢ የሚገኙ የጠላት አመራሮች በተለያዩ የሥነ ልቦና ጫና እና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው መረጃ ሲ...
17/10/2022

ጦርነቱ እያበቃ ነው ማለት ይቻላል
——————————————————
በምዕራብ ግንባር

በማይፀብሪ አካባቢ የሚገኙ የጠላት አመራሮች በተለያዩ የሥነ ልቦና ጫና እና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው መረጃ ሲለዋወጡ እና የበታች አመራሮችን በልመና ጭምር የሚፈርሰውን የጠላት ኃይል እንዲያረጋጉ ሲጠይቁ ተስተውለዋል። ከነዚህ መካከል፦
👉🏽 በማይጠብሪ ያለውን የጠላት ኃይል የሚያዋጉ የጠላት አመራሮች ማይፀብሪን አልፈው እየሸሹ እንደሆነ፣
👉🏽 የተበታተነውን ኃይል ለማሰባሰብ እየሞከሩረ ቢሆንም ታጣቂዎች የአመራር ትእዛዝ ረግጠው እየሄዱ እንደሚገኙ፤
👉🏽 የተሰጣቸው አቅጣጫ እንደሌለና የበላይ አካል ወሳኔ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ፣
👉🏽 በማይፀብሪ ዙሪያ መቆየቱ አስፈላጊ እንዳልሆነና ውጤት እንደሌለው እየገለፁ ነው።
:
በተጨማሪም በሞራል የተዳከመውንና እየፈረሰ ያለውን ታጣቂ ለማነሳሳት የተለያዩ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ውለዋል። ከዚህ መካከል ወደ አዲዳዕሮ የገባውን የወገን ኃይል እየደመሰሱ እንደሚገኙ፤ በማይፀብሪ ጥሩ ቁመና ላይ በመሆን ሲዋጉ እንደዋሉና የተበላሸባቸውን በማስተካከል እንደሚቀጥሉ፤ ተጨማሪ ኃይል እየመጣላቸው እንደሆነ፤ የተበተነውን ታጣቂ በማሰባሰብና ስታፍ ጭምር በማሰለፍ መከላከል እንዳለባቸው መመሪያ ተላልፏል። በተጨማሪም አመራሩ “እባካችሁ ታጣቂውን አስቁሙት፤ እስኪመሽ ለትንሽ ጊዜ ታገሱ፤ ሲመሽ መከላከያ ማጥቃት ስለሚያቆም ተረጋግተን እንነጋገራለን” እያለ በልመና ጭምር ሲጠይቅ እንደነበረ ታውቋል።

ከሥነ ልቡና አኳያ

ጠላት እየገጠመው ያለውን ሽንፈት ተከትሎ አንዱ ሌላውን የመውቀስ ሁኔታ እየተስተዋለ ሲሆን ከፍተኛ አመራሩ ፀረ ድሮን አለን በሚል ታጣቂውን ሲያታልል እንደነበረ የታችኛው አመራር መግለጽ ጀምሯል።

👉🏽 ጠላት በውጊያ እየደረሰበት ያለውን የበላይነት ለመቋቋምና ህልውናውን ለማቆየት ወታደራዊ ባልሆኑ መስኮች በተለይም ዓለም አቀፍ ጫና ለመፍጠርና ህልውናውን ለማትረፍ የሚዲያ ዘመቻና ዲፕሎማሲ ላይ ትኩረት አድርጓል።

👉🏽ጠላት በሁሉም ግንባሮች በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ያለውን ታጣቂ ሞራል ለማነሳሳት ያላስመዘገበውን ድል እንዳስመዘገበ በማስመሰል እየነገረ ሲሆን ለአብነት በማይጠብሪ እና አዲነብሪድ ጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኝ፣ የሚታዩበት ክፍተቶች እያስተካከለ እንደሆነ፣ በቂ ኃይል እንዳለውና ተጨማሪ ሀይል እንደሚላክ እያነሳላቸው ቢሆንም ታጣቂው አሁንም የአመራር ትእዛዝ ያለማክበር፣ የመጥፋት እና በቀላሉ የመፍረስ አዝማሚያ እየተስተዋለበት ይገኛል።

👉🏽 ዛታ ላይ በስጋት ወደ ጫካ ሸሽተው የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የወገንን ሕዝባዊነት በማረጋገጥ ወደ ከተማ እየተመለሱ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ጠላት በተለይም ኅብረተሰቡ ውስጥ እየተቀላቀለ የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ መሆኑን ተከትሎ ወገን በሚወስደው የአጸፋ ርምጃ ሲቪሊያን ላይ ጉዳት እንዲደርስ ሆን ብሎ እየሰራ መሆኑ፤ የወገን ጦር ሽሬን መክበቡን ተከትሎ ጠላት ሎጂስቲክሱን ወደ አክሱም እና መቀሌ ከተሞች ማጓጓዙን እንዳስቀጠለ እና በከተማው የነበሩ የጠላት አመራሮች ሕዝቡን ዘርፈው አብረው እየወጡ መሆናቸው ታውቋል።

Press Release : Blaming the Victim and Saving the Perpetrator Under the Mantle of Human RightsFor almost two years now, ...
15/10/2022

Press Release : Blaming the Victim and Saving the Perpetrator Under the Mantle of Human Rights

For almost two years now, the US and the EU have desperately tried to downplay and whitewash the TPLF’s high crimes of War of Insurrection with all its security and humanitarian ramifications in Ethiopia and the wider region at large. The ploy has invariably included unwarranted accusations and scapegoating of Eritrea.

Indeed, the EU External Service issued a deplorable statement on October 6 this month accusing Eritrea, among other things, of “playing a destructive role in the Tigray conflict”. And on October 12 this week, the US, Australia, Germany, Denmark, the Netherlands, UK, and Canada have issued a Joint Statement along the same lines.

These concerted pronouncements of willful harassment of the victims of the TPLF’s war of choice are but an extension of decades-old policies of stoking conflict in our region pursued by these powers to advance their own narrow agendas. The origins and dynamics of the current war are otherwise clear and unambiguous as the following sequences of events illustrate:

The almost two-years long vicious war in northern Ethiopia was triggered solely and only because the TPLF launched massive, premeditated and coordinated military assaults on all the contingents of the Northern Command on the night of 3 November 2020. The TPLF deployed 250,000 Militia’s and Special Forces that it had trained throughout the years for the operation that its commanders dubbed as “blitzkrieg”.
The TPLF’s pronounced objectives in launching its reckless War of Insurrection were to totally neutralized the Northern Command; capture all its heavy weaponry (which constituted about 80% of the EDF’s total ordinance) and topple the Federal Government.

Annulment of the historic Eritrea-Ethiopia Peace Agreement and subsequent acts of continued destabilization of Eritrea was an integral and pronounced part of the TPLF’s War of Insurrection.

The TPLF’s War of Insurrection was not confined to its reckless military assaults in November 2020. Even when the first offensive was foiled and against the backdrop of successive unilateral and humanitarian cease-fires that were declared by the Federal Government, the TPLF persisted in its war efforts to unleash the Second Offensive from June to September in 2021 and the Third Offensive on 24 August this year. In all these acts, the TPLF commandeered and funneled humanitarian assistance and WFP trucks to its war efforts; and, conscripted tens of thousands of child soldiers as cannon fodder in its costly human-wave war tactics.

These are the indelible facts.

In the event, these countries cannot feign ignorance and/or claim the moral high ground to pontificate to Eritrea on “peace and human rights’’. The litany of transgressions perpetrated against Eritrea in the past three decades with the support and collusion of some of these powers include: i) tacit and all-rounded support to the TPLF’s vicious and two-year long war against Eritrea when the former was at the helm of power in Ethiopia; ii) similar stance when it expelled over 75 thousand Eritreans and Ethiopians of Eritrean origin and looted their life-time wealth; and iii) deplorable collusion with the TPLF as it reneged on its treaty obligations and continued to occupy sovereign Eritrean territories in violation of the EEBC Arbitral Award in accordance with the provisions of the Algiers Peace Agreement that the US and the EU had brokered and explicitly guaranteed.

It is this backdrop of impunity that has emboldened the TPLF to unleash reckless military offensives in the past two years. Eritrea’s regional policy is otherwise centered on regional peace, stability and economic cooperation on the basis of full respect of the sovereignty and territorial integrity of the Member States. Eritrea cherishes regional peace as it has been the victim, for decades, of imposed and intermittent wars perpetrated to advance unlawful extraneous and local agendas.

Embassy of the State of Eritrea

To the United States of America

15 Oct 2022

የመጨረሻውን መጀመሪያ የሚያበስሩ የዛሬ መረጃዎች——————ጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና ጥምር ጦሩ በአሸባሪ ህወሓት ታጣቂ ላይ እየወሰዱት ባሉት ፀረ ማጥቃት እርምጃዎች የመጨረሻውን መጀመሪያ የ...
15/10/2022

የመጨረሻውን መጀመሪያ የሚያበስሩ የዛሬ መረጃዎች
——————
ጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና ጥምር ጦሩ በአሸባሪ ህወሓት ታጣቂ ላይ እየወሰዱት ባሉት ፀረ ማጥቃት እርምጃዎች የመጨረሻውን መጀመሪያ የሚያበስሩ የድል ዜናዎች እየተሰሙ ነው፡፡

👉🏽 በደቡብ ግንባር በሰሜን ወሎ ግዳን ወረዳ ወትወት፣ ሲሚዛ፣ መሆጎ፣ ጀመዶ፣ ግራኝ አገው እና ዶጊያት የነበረው የጠላት ጦር የተደመሰሰ ሲሆን፤ አሸባሪው ቡድኑ ቀሪ ኃይሉን ወደ አላማጣ አየር ማረፊያ እንዲሸሽ አድርጓል።

👉🏽 በራያ አላማጣ ግንባርም ተሰልፎ የነበረው የጁንታው ታጣቂ ክፉኛ ተመትቶ ዋጃን እየለቀቀ እና ከአላማጣ ከተማ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ተበታትኖ ምሱን እያገኘ ነው፡፡

👉🏽 በሰቆጣ ግንባር ጥራሪ ወንዝ ማዶ ላይ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ በተወሰደ የማጥቃት እርምጃ የአሸባሪው ታጣቂዎች ደቆል፣ ቆዝባ፣ መረዋ እና ዛታ ከተማዎችን ለወገን ጦር ለመልቀቅ ተገደዋል፡፡

👉🏽 በምዕራብ ግንባር አዲአርቃይ ከተማን አልፎ መጥቶ በነበረው የጠላት ኃይል በደረሰበት ጠንካራ ምት ጠጣ፣ ሲምንዛ፣ አዲአርቃይ ከተማ፣ ጃማ ወንዝ፣ ማይለሃም፣ ማይቃጫን፣ ኮሎፊያን አባማር፣ አዲጉባይ እና ቡያን እንእንዲለቅና ወደ አቄስብሎ፣ ማይፀብሪ እና ዜሮ ዜሮ እንዲሻገር ተገዷል።

👉🏽 በሰሜን ምዕራብ የነበረው የአሸባሪው ኃይል ከአዲዳሮ ተገፍቶ ወጥቷል። በዛላምበሳ በኩልም ዛላምበሳን ለቆ ፋዒ የምትባል ትንሽ ከተማ ላይ ሰፍሯል። በመሆኑም በዚህ አቅጣጫ የወገን ጦር የአዲግራት ከተማን በቅርብ ርቀት እያየ ግስጋሴውን ቀጥሏል።
-
ጠላት አሁን ላይ በተለያዩ ግንባሮች በደረሱበት ጥቃቶች ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራም አስተናግዷል። ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ለመሸሽም ተቸግሯል። በዚህም ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ውስጥ ገብቷል። የደረሰበትን ከፍተኛ ኪሳራ በሐሰትና በበሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳው ለመሸፈን ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። ለአብነትም በወገን ጦር እጅ
-
ባለችው ሽራሮ ከተማ ኅብረተሰቡን በሐሰት ፖሮፓጋንዳ በማወናበድ እንዲለቅ ቢያደርግም ሕዝቡ ወደ ቀየው ተመልሶ መኖር ጀምሯል። በዋጃ ከተማም ተመሳሳይ ውጅንበር ለመፍጠር እየሞከረ ይገኛል። ሕዝቤ ሆይ ንቃ ቀዬህን ለቀማኛ ለቀህ አትሂድ፤ ትግራዋይም በቃኝ በል ! ለከፋ ሰቆቃ የዳረገህና ወደማይቀረው መቃብሩ እየተሸኘ ያለውን ኃይል ለይተህ ምታ፤ ጨክነህ ቁረጥ።

ከባንክ እስከ ጎተራ፣ የሕወሐት የዝርፊያ ቁልቁለት። በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተመትቶ  እየፈረጠጠ ያለው ሕወሐት የራሱን ሕዝብ እየዘረፈ ነው።በዘረፋ ከሽራሮ እስከ ሽሬ ነዋሪ የሆኑ ተጋሩ ...
15/10/2022

ከባንክ እስከ ጎተራ፣ የሕወሐት የዝርፊያ ቁልቁለት።
በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተመትቶ እየፈረጠጠ ያለው ሕወሐት የራሱን ሕዝብ እየዘረፈ ነው።በዘረፋ ከሽራሮ እስከ ሽሬ ነዋሪ የሆኑ ተጋሩ ከሕወሐት ጀሌ ንብረታቸውን ለማትረፍ የሚሸሽጉበት ጥግ፣ የሚሠውሩበት ዋሻ አጥተዋል።

ሕወሓት ከሽራሮ እስከ ሽሬ ያሉትን ከተሞችን ጥሎ ሲፈረጥጥ የአንገት ሐብል የእጅ አምባር የእግር አልቦ እያስወለቀ ከትግራይ ሕዝብ እየዘረፈ ነው። ሳጥን እየሰበረ ጎተራ እየበረበረ፣ ታገልኩለት የሚለውን ሕዝብ ያለ ጥሪት እያስቀረው ነው።

ሕወሐት የድመት ጠባይ አለው። ድመት ከቸገራት የገዛ ልጇን ትበላለች። ሕወሐትም ትግል ሲጀምር የአክሱም ሕዝብን ገንዘብ በመዝረፍ ጀመረ። ትግሉን በሽንፈት ሊደመድም ሲል ደግሞ የሽሬ ሰውን ሀብት መዝረፍ ጀመረ። ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ይባል የለ።

ጁንታው አማራና አፋር ክልል ገብቶ በነበረ ጊዜ ጥሬ ድንችና ያልታጨደ እህል ሳይቀር ሲዘርፍ ነበር። ሕወሐት ከቀይና ነጭ የደም ሴሉ ጋር ስርቆት የሚባል ሌላ የደም ሴል አለው።

በአማራና አፋር ክልሎች ሕወሐት ከብር እስከ ድግር ዘረፈ ሲባል ተራ እነ ቅጽበታዊ የሥነ ምግባር ጥሰት እንደሆነ ለማሳመን የቡድኑ አመራሮች ሲጣጣሩ ነበር። ዛሬ ግን የገዛ ሕዝቡን በመዝረፍ ባህሪው መሆኑን አስመሰከረ።

ሕወሓት ከሁለት ሳምንት በፊት በመቀሌ የሚገኘውን የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ የመድኃኒት መጋዘን ዘርፎ የዝርፊያ ሱሱን አርክቶ ነበር።እና የዘረፈውን መድኃኒት ለተዋጊዎቹ እንዲውል በማድርጉ የመቀሌ ሕዝብ በከፍተኛ የመድኃኒት ችግር ውስጥ እንደገባ መነገሩ ይታወሳል፡፡

ዶ/ር አለምነው መኮንን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙየቀድሞው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ከፍተኛ አመራር የነበሩት ዶ/ር አለምነው መኮንን የኢ...
13/10/2022

ዶ/ር አለምነው መኮንን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

የቀድሞው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ከፍተኛ አመራር የነበሩት ዶ/ር አለምነው መኮንን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ። ዶ/ር አለምነው የኢንተርፕራይዝ ልማቱ ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት፤ ተቋሙን ላለፉት 10 ወራት በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ብሩ ወልዴ ከኃላፊነታቸው በመልቀቃቸው ምክንያት ነው።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ባለፈው ዓመት መስከረም ወር በአዲስ መልክ ከተዋቀሩ የፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንዱ ነው። አዲሱ ተቋም በአዋጅ የፈረሰው የፌደራል አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ልማት ኤጀንሲ መብት እና ግዴታዎች ተላልፈውለታል።

መስሪያ ቤቱ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ ከአራት ወራት በኋላ በዋና ዳይሬክተርነት የመምራት ኃላፊነት የተረከቡት፤ የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንን ከምስረታው ጀምሮ በዋና ስራ አስኪያጅነት ሲያስተዳድሩ የቆዩት አቶ ብሩ ወልዴ ነበሩ። አቶ ብሩ እስከ ትላንት ጥቅምት 2፤ 2015 በስራ ገበታቸው ላይ እንደነበሩ የስራ ባልደረቦቻቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የዋና ዳይሬክተርነት ኃላፊነታቸው “በገዛ ፍቃዳቸው” የለቀቁት ከዛሬ ጥቅምት 3፤ 2015 ጀምሮ መሆኑን አቶ ብሩ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የዋና ዳይሬክተሩን ከኃላፊነት መልቀቅ የኢንተርፕራይዝ ልማት መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ አረጋግጠዋል። በተሰናባቹ ኃላፊ ምትክ ዶ/ር አለምነው መኮንን መሾማቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለተቋሙ መድረሱንም ገልጸዋል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/8298/

Address

Churchil
Addis Ababa

Telephone

+251976197498

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Inform Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Inform Ethiopia:

Videos

Share

Category