Addis Star Media አዲስ ስታር ሚዲያ

Addis Star Media  አዲስ ስታር ሚዲያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Star Media አዲስ ስታር ሚዲያ, TV Network, Addis Ababa.

Description -
Addis Star is an independent online media platform, covering daily breaking news, special news analysis, live entertainment and events and much more.

** ኤልሳቤት ቦርን የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ  **ኤልሳቤት ቦርን በ30 አመታት ውስጥ የመጀመሪየዋ የፈረንሳይ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተሾ...
17/05/2022

** ኤልሳቤት ቦርን የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ **

ኤልሳቤት ቦርን በ30 አመታት ውስጥ የመጀመሪየዋ የፈረንሳይ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተሾመዋል፡፡ በሀገሪቱ የሰራተኛ ሚኒስትር የነበሩት ኤልሳቤት ቦርን÷ የ61 አመቱን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዣን ካስቴክስን ተክተው የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል፡፡
ተሰናባቹ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዣን ካስቴክስ የፕሬዚዳንት ማክሮን ዳግም መመረጥን ተከትሎ ለአዲሱ መንግስት የለውጥ አካል ለመሆን በሚል ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡:

Via Fana

 #ሰበር ዜና‼️ጄነራል ተፈራ ማሞ ታፍኖ ተወስዷል።እስካሁኗ ስዓት ድረስ የት እንዳለ አይታወቅም ስትል ባለቤቱ አረጋግጣለች።አዳዲስ መረጃወችን ተከታትለን እናሳውቃለን።
16/05/2022

#ሰበር ዜና‼️
ጄነራል ተፈራ ማሞ ታፍኖ ተወስዷል።
እስካሁኗ ስዓት ድረስ የት እንዳለ አይታወቅም ስትል ባለቤቱ አረጋግጣለች።
አዳዲስ መረጃወችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

G7 ስለኢትዮጵያ ምን አለ? የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ማምሻውን ባወጡት ባለ 46 ነጥብ መግለጫ የኢትዮጵያንም ወቅታዊ ሁኔታ ቀጥር 17 ላይ  አካተዋል፡፡ ዋና ዋና ጉ...
15/05/2022

G7 ስለኢትዮጵያ ምን አለ?

የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ማምሻውን ባወጡት ባለ 46 ነጥብ መግለጫ የኢትዮጵያንም ወቅታዊ ሁኔታ ቀጥር 17 ላይ አካተዋል፡፡ ዋና ዋና ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

✔-“እርዳታ ለማድረስ የሰብዐዊ ተኩስ አቁም መደረጉ በበጎ የምንቀበለው ነው፡፡ አሁንም ግጭት ወዳለባቸው አካባቢዎች የተሟላ፤ደህንነቱ የተጠበቀ፤ገደቦች የሌሉበት ዘላቂ የእርዳታ አቅርቦች እንዲኖሩ ሁሉንም ወገኖች ማሳሰብ እንወዳለን፡፡”

✔-“በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሙሉ ዘላቂ ተኩስ አቁም እንዲኖርና ለአሳታፊ ብሄራዊ መግባባትና አስተማማኝ ሰላም መሰረት ወደሆነው ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲሄዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡”

✔-“የኤርትራ መንግስት ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦሩን እንዲያስወጣ እናሳስባለን፡፡”

✔-“የኢትዮጵያ መንግስት የጋራ ምርመራ ሪፖርትን መነሻ በማድረግ የሚኒስትሮች ግብረ ሀይል ማቋቋሙን እንደግፋለን፡፡ ሁሉም ወገኖች ለአለም አቀፍ የሰብዐዊ መብት ኮሚሽን የባለሙያዎች ቡድን ትብብር እንዲያደርጉም እናሳስባለን፡፡”

✔-“በምስራቅና ደቡባዊ አካባቢ ከስምንት ሚሊየን በላይ ሰዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረው ድርቅ በጥብቅ ያሳስበናል፡፡ ሰብዐዊ ድጋፎችን ለማድረግ ቃል እየገባን አለም አቀፍ አጋሮችም ተመሳሳይ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እናሳስባለን፡፡ ”

Via: Blue24

 ጎረቤታችን ሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች።ይህን ተከትሎ የሶማሊያ ፖሊስ ምርጫ እስኪጠናቀቅ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በጸጥታ ሥጋት ሳቢያ ከአስቸኳይ አገልግሎቶች ውጪ ሁሉንም ሕዝባዊ እን...
15/05/2022



ጎረቤታችን ሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች።

ይህን ተከትሎ የሶማሊያ ፖሊስ ምርጫ እስኪጠናቀቅ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በጸጥታ ሥጋት ሳቢያ ከአስቸኳይ አገልግሎቶች ውጪ ሁሉንም ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች የሚያግድ የሰዓት ዕላፊ ተግባራዊ አድርጓል።

የታወጀው ሰዓት እላፊ እስከ ሰኞ ጧት ድረስ የሚቆይ ነው ተብሏል።

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የሚመርጠው የታችኛው እና የላይኛው ምክር ቤቶች በጋራ በሚሰጡት ድምጽ ነው።

ጎሳን መሰረት ባደረገው በዚህ ለ6ኛ ጊዜ በሚካሄድ ቀጥተኛ ባልሆነ ምርጫ 39 እጩዎች ይወዳደራሉ።

ስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ መሐመድ (ፍርማጆ) ፣ የቀድሞዎቹን ፕሬዝዳንቶች ሸሪፍ ሼክ አህመድ እና ሀሰን ሼክ ሞሐመድን እንዲሁም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አሊ ኬህሬን ከእጩ ተወዳዳሪዎቹ መካከል ናቸው።

የራስ ገዝዋ የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሰዒድ አብዱላሂ ዳኒና የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋውዛ ዩሱፍ አደንም ለፕሬዝዳንትነት ይወዳደራሉ።

ፋውዛ ዩሱፍ አደን ብቸኛዋ ሴት ፕሬዝዳንታዊ እጩ ናቸው።

የነገው ምርጫ ከአንድ ዓመት በላይ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን በምርጫው አሸንፎ ስልጣን የሚይዘው ፕሬዝዳንት የሰርጎ ገቦች ጥቃትና ረሀብ ያስከትላል ተብሎ የሚያሰጋውን ድርቅ ጨምሮ በርካታ ፈተናዎች የመፍታት ኃላፊነት ይወስዳል።

Via የጀርመን ሬድዮ

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል ተብሏል።ከተማ አቀፍ የሆነው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከ71ሺ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 2014 ዓ....
12/05/2022

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል ተብሏል።

ከተማ አቀፍ የሆነው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከ71ሺ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 2014 ዓ.ም ለመፈተን መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ ሰባ አንድ ሺ ስድስት መቶ ስልሳ አንድ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በትምህርት ቢሮ ፈተና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ተናግረዋል።

የፈተና ዝግጅቱ ተጠናቆ የህትመት ስራዉ የተዘጋጀ ሲሆን በእለቱ የማሰራጨት ስራ ብቻ እንደሚቀርም ገልጸዋል፡፡

የፈተናዉን ምዝገባ በተመለከተ የተማሪዎች የአድሚሽ ካርድ በሚቀጥለው ሳምንት በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚላክ እና ለተማሪዎቹም እንደሚተላለፍ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስምንተኛ ክፍል ፈተና 211 የመፈተኛ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን ጣቢያዎቹን ምቹ ናቸው የሚለውን ምልከታ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት ቁጥሩ ከፍ አልያም ዝቅ ሊደረግ እንደሚችል አቶ ዲናኦል አብራርተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ሶስት ሴቶችን የገደለው ወንጀለኛ ማረሚያ ቤት ውስጥ ማግባት እንደሚፈልግ ገለጸ።የ53 ዓመቱ ሌቪ ትዳሩን ለመመስረት የከተማዋን አስተዳዳሪ የመጨረሻ ይሁንታ ማግኘት አለበት።ወንጀለኛው ማርሻ ማ...
12/05/2022

ሶስት ሴቶችን የገደለው ወንጀለኛ ማረሚያ ቤት ውስጥ ማግባት እንደሚፈልግ ገለጸ።

የ53 ዓመቱ ሌቪ ትዳሩን ለመመስረት የከተማዋን አስተዳዳሪ የመጨረሻ ይሁንታ ማግኘት አለበት።
ወንጀለኛው ማርሻ ማኮኔል፣ ኤምሊ ዴላግራንዴ እና ሚሊ ዶውለር የተባሉ ሴቶችን በጭካኔ በመግደል ጥፋተኛ ተብሎ ሁለት የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ነበር።

የቀድሞው የፍትህ ሚኒስቴር ሮበርት በክላንድ ዘ ሰን ለተባለው ጋዜጣ ሲናገሩ ሰርግ የመደገስ ሀሳቡ ''ለማመን የሚከብድ ነው'' ብለዋል።
''የ13 ዓመቷ ሚሊ የሰርግ ቀኗን ማየት ሳትችል ነው የገደላት። እሱ ደግሞ ሰርግ ለመደገስ ማሰቡ ትክክል አይመስለኝም'' ብለዋል።

ወንጀለኛው ከሁለት ዓመታት በፊት በጽሁፍ ታገኘው የነበረችው ግለሰብ ጋር እንደተቀራረቡና በተደጋጋሚ ትጎበኘው እንደነበር ዘ ሰን ዘግቧል።

ወንጀለኛው ከሁለት ዓመታት በፊት በጽሁፍ ታገኘው የነበረችው ግለሰብ ጋር እንደተቀራረቡና በተደጋጋሚ ትጎበኘው እንደነበር ዘ ሰን ዘግቧል።
ከሰሞኑ ደግሞ ልትጎበኘው ስትመጣ ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ጥያቄውን ማቅረቡ ተዘግቧል።

የአገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በበኩላቸው ''ሰርጉን ለመደገስ ይፋዊ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊት በምንሰራበት አሰራር እየተጠና ነው'' ብለዋል።

ቢቢሲ አማርኛ

ሱዳን ፤ ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ከሰላ ከተማ የጎሳ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ሰዓት እላፊ ጣለች፡፡ሰዓት እላፊው በኑባ እና ቤኒ ዓምር ጎሳዎች መካ...
12/05/2022

ሱዳን ፤ ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ከሰላ ከተማ የጎሳ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ሰዓት እላፊ ጣለች፡፡

ሰዓት እላፊው በኑባ እና ቤኒ ዓምር ጎሳዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ትናንት ረቡዕ ምሽት ጀምሮ የተጣለ ሲሆን ለ24 ሰዓታት ይቆያል ተብሏል፡፡

ሌላ አዲስ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ሰዓት እላፊው እንዲከበርም የከተማዋ ባለስልጣናት አሳስበዋል፡፡

ደም አፋሳሽ ነበር የተባለለትን ግጭት የሃገሪቱ መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ገብተው እስኪያስቆሙት ድረስ የሰው ህይወት መጥፋቱ እና ጉዳቶች መድረሳቸው አል ዐይን ኒውስ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ አስገኘ። የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን ለዚህ ታሪካዊ ላሉት ስኬት እንኳንደስ ያላችሁ ብለዋል። የቡና ምርት ...
12/05/2022

የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ አስገኘ።

የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን ለዚህ ታሪካዊ ላሉት ስኬት እንኳን
ደስ ያላችሁ ብለዋል። የቡና ምርት ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ ከምታቀርባቸው የግብርና ምርቶች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ ቀጥሏል።

ሀገሪቱ በተለይም ወደ ቻይና የምትልከው የቡና ምርት በከፍተኛ መጠን አድጓል። በፈረንጆቹ 2021 ዓመተ ምህረት ላይ ቻይና ከኢትዮጵያ ያስገባቸው የቡና ምርት መጠን ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ196 በመቶ አድጓል።

በቅርቡ የኢትዮጵያን የቡና ምርት በቻይና ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ በተዘጋጀ መድረክ ላይ የሀገሪቱ የቡና ማህበር እንዳስታወቀው፥ በቻይና ከትላልቅ ከተሞች እስከ መለስተኛ ከተሞች የቡና ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ዕድገት ያሳየ ሲሆን፥ ይህም ለኢትዮጵያ ቡና አምራቾች እና ላኪዎች ሰፊ የገበያ ዕድል መፈጠሩ ተመልክቷል።

ሚኒስትሩ ባለፉት የበጀት ዓመቱ ወራት የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ምን ያህል የቡና መጠን ወደ ውጭ ተልኮ እንደሆነ አልጠቆሙም።

FBC

ታሊባን አፍጋናውያን ሴቶች ከዐይናቸው ውጭ ሙሉ በሙሉ መሸፈን አለባቸው ማለቱን ተከትሎ የጸጥታው ምክር ቤት ሊሰበሰብ ነውታሊባን አፍጋናውያን ሴቶች የፊት ገጽታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ልብስ...
12/05/2022

ታሊባን አፍጋናውያን ሴቶች ከዐይናቸው ውጭ ሙሉ በሙሉ መሸፈን አለባቸው ማለቱን ተከትሎ የጸጥታው ምክር ቤት ሊሰበሰብ ነው

ታሊባን አፍጋናውያን ሴቶች የፊት ገጽታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ልብስ (ቡርቃዓ) መልበስ አለባቸው ማለታቸውን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባ መጥራቱም ተሰምቷል፡፡

ታሊባን ባሳለፍነው ቅዳሜ ነበር በመካከለኛ እድሜ ላይ የሚገኙና እምብዛም እድሜያቸው ያልገፋ ሴት አፍጋናውያን እይታቸውን በማይከልል መልኩ የፊት ገጽታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ቡርቃዓ እንዲለብሱ ያወጀው፡፡

አዋጁ በሼሪዓ ህግ መሰረት የተላለፈ ነው፡፡ ከቅርብ ዘመዶቻቸው ውጭ ወንዶች ቢያገኟቸው እንዳይተናኮሷቸው በማሰብ የተላለፈ ነውም ነው የተባለው፡፡

አል ዓይን አማርኛ

የትግራይ ህዝብ “ለመጨረሻው ምዕራፍ ትግል” እንዲዘጋጅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥሪ አቀረቡ።ዋዜማ ራዲዮ- የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ከማዕከላዊው መንግስት ጋር...
12/05/2022

የትግራይ ህዝብ “ለመጨረሻው ምዕራፍ ትግል” እንዲዘጋጅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥሪ አቀረቡ።

ዋዜማ ራዲዮ- የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ከማዕከላዊው መንግስት ጋር ችግሮችን በዲፕሎማሲ ለመፍታት ሲደረግ የነበረው ጥረት “ባለመሳካቱና የሰላም መንገድ በመዘጋቱ የትግራይን ሕዝብ ነፃነት ለማረጋገጥ” የክልሉ ህዝብ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀረቡ።

ደብረፅዮን በመቀሌ ሌሎች የሕወሓት አመራሮች ደግሞ በተለያዩ የትግራይ ዞኖች ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበት የከፋ ስቃይ እንዲቀለበስና የትግራይ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ብለዋል።

“ሁሉም የፖለቲካ ችግር በሰላምና በዲፕሎማሲ እንደማይፈታ ብናውቅም አሁን የገባንበት ጦርነት ከመጀመሩ አስቀድመን እንዲሁም በጦርነቱ ወቅት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተናል” ብለዋል ደብረፅዮን በመቀሌ ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ።

በአለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸማጋይነት ጊዚያዊ ስምምነት ተደርጎ ወደ ክልሉ እህል መድሀኒትና ሌሎች ድጋፎች እንዲገቡ ጥረት ብናደርግም እስከ አሁን ድረስ የተገኘው ድጋፍ ችግሩን ለማቃለል በቂ አይደለም ብለዋል።

መላክ ያለበትን መልዕክት ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ባለን የመገናኛ መንገድ አድርሰናል ያሉት ደብረፅዮን የሚመለከታቸው ያሏቸውን አካላት አልዘረዘሩም።

ዋዜማ ሬድዮ

ኢትዮጵያ በይፋ የ5G ኔትወርክ አገልግሎትን አስጀመረችየ5G ኔትወርክ በአዲስ አበባ የተመረጡ ቦታዎች ለደንበኞች ክፍት መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋልኢትዮ ቴሌኮም የ5G ኔትወርክ አገልግሎት...
10/05/2022

ኢትዮጵያ በይፋ የ5G ኔትወርክ አገልግሎትን አስጀመረች
የ5G ኔትወርክ በአዲስ አበባ የተመረጡ ቦታዎች ለደንበኞች ክፍት መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል
ኢትዮ ቴሌኮም የ5G ኔትወርክ አገልግሎት አስጀመረ።
የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ የ5G ኔትወርክን በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል በይፋ አስጀምረዋል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ 6 ሀገራት የ5G ኔትወርክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።
ይህ አገልግሎት ደበኞች ባንዴ ብዙ የኔትወርክ አገልግሎት የሚሰጥ እና ከመደበኛው የኔትወርክ አገልግሎት 20 እጥፍ አገልግሎት ይሰጣል።
ዛሬ የተጀመረው ይህ የ5G ኔትወርክ በቻይናው ህዋዌ የቴሌኮም ኩባንያ እንደተገነባ ተገልጿል።
የሰዎችን ከማሽን ጋር እንዲሁም ማሽኖችን ከሰዎች ጋር በቀላሉ በማገናኘት ምርትማነትን ያቀላጥፋል። የ5G ኔትወርክ አገልግሎት አሰራሮችን በቀላሉ እንዲቀላጠፉ የሰውን ልጅ ህይወት ቀላል ያደርጋልም ተብሏል።
የዓለማችን 67 በመቶ ህዝብ የሞባይል ኔትወርክ ተጠቃሚዎች ናቸው።
የ5G ኔትወርክ ደንበኞች በሰከንድ እስከ 10 ጊጋ ባይት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙም እንደሚያደርግም ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል። ይህ አዲስ አገልግሎት በተለይም አገልግሎቶችን በርቀት በሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ እንዲሰጡ ያደርጋሉም ተብሏል።
ይህ የ5G ኔትወርክ በአዲስ አበባ የተመረጡ ቦታዎች ለደንበኞች ክፍት የሆኑ ሲሆን በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 150 የ5G ኔትወርክ ቀጠናዎች ይከፈታሉ ሲል ወይዘሪት ፍሬህይወት ገልጸዋል።
የአገልግሎቱ ተግባራዊ መሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ነው በመርሐ ግብሩ የተገለጸው፡፡

 ከኢድ አልፈጥር አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በአጥር ዘለው አፍነው ከወሰዱኝ በኋላ አሁን ከምሽቱ 3:ዐዐ አይኔን በጨርቅ አ...
09/05/2022



ከኢድ አልፈጥር አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በአጥር ዘለው አፍነው ከወሰዱኝ በኋላ አሁን ከምሽቱ 3:ዐዐ አይኔን በጨርቅ አስረው ቤቴ በር ላይ ጥለውኝ ሄደዋል።

እስከ ዛሬ የት እንዳቆዩኝ ግን አላውቅም። በጤናዬ ላይ የደረሰ ነገር የለም።

via Gobeze Sisay

የሩሲያ የድል ቀን በዓል በምስል‼️‼️በፈረንጆቹ ሜይ 9 ሩሲያውያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ሶቪዬት ሕብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችውን ድል አስበው ይውላሉ።ቭላድሚር ፑቲ...
09/05/2022

የሩሲያ የድል ቀን በዓል በምስል‼️‼️

በፈረንጆቹ ሜይ 9 ሩሲያውያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ሶቪዬት ሕብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችውን ድል አስበው ይውላሉ።

ቭላድሚር ፑቲን ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ለዚህ የድል በዓል ትልቅ ትርጉም ሰጥተውታል። በዕለቱ ሩሲያ ያላትን ዘመን አፈራሽ ጦር መሳሪያ ለዓለም የምታሳይበት ቀን አድርገውታል።

በዩክሬን ላይ ጦር የመዘዙት ፑቲን በዛሬው የድል ቀን ላይ ጦርነቱን የተመለከተ አዲስ ውሳኔ ያስተላልፋሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ፑቲን በዛሬው በዓል ላይ ጦርነቱ ማብቃቱን አልያም በዩክሬን ላይ አዲስ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለው ይናገራሉ ተብሎም ነበር።

ይኹን እንጂ ምዕራባውያን ለሩሲያ ስጋት ሆነው ቀጥለዋል ከማለት ውጪ ፑቲን ያሉት ነገር የለም።

ፑቲን በዩክሬን እየተፋለሙ ላሉት ወታደሮቻቸው “እየተዋጋችሁ ያላችሁት ለሩሲያ ደኅንነት ነው” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
BBC

ኔፓላዊው የኢቨረስት ተራራን ለ26ኛ ጊዜ በመውጣት አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበMay 8, 2022የኢቨረስት ተራራን ለመጀመሪያ ጊዜ መውጣት የተጀመረው በፈረንጆቹ 1953ዓ.ም ነበርየኔፓሉ ተራራ...
09/05/2022

ኔፓላዊው የኢቨረስት ተራራን ለ26ኛ ጊዜ በመውጣት አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ
May 8, 2022
የኢቨረስት ተራራን ለመጀመሪያ ጊዜ መውጣት የተጀመረው በፈረንጆቹ 1953ዓ.ም ነበር
የኔፓሉ ተራራ ወጭ የኢቨረስት ተራራን ለ26ኛ ጊዜ በመውጣት ባለፈው አመት በራሱ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ሪከረድ ማሻሻሉን ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡
የ52 ዓመቱ ካሚ ሪታ ሼርፓ፣ ቅዳሜ እለት 8,848.86 ሜትር ከፍታ ያለውን ተራራ በባህላዊው ደቡብ ምስራቅ ሸለቆ መንገድ 10 ሌሎች ተራራ ወጭዎችን መርቷል፡፡
በካሚ ሪታ የምትጠቀመው የመውጣት መንገድ በ1953 በኒው ዚላንድ ተወላጅ ሰር ኤድመንድ ሂላሪ እና የኔፓል ሼርፓ ቴንዚንግ ኖርጋይ በአቅኚነት ያገለገሉ ሲሆን አሁንም በጣም ተወዳጅ ነው።
በኒውዝላንዳዊው ሰር ኢድሙንድ ሂላሪ እና በኒፓላዊው ሸርፓ ቴንዚንግ ኖርጋይ የተጀመረው እና በካሚ ሪታ ጥቅም ላይ የዋለው የተራራ መውጫ መንገድ እስካሁን ድረስ ታዋቂ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ኔፓል በዚህ አመት ብቻ 316 ከግንቦት ድረስ ሰዎች የተራራ መውጫ ፍቃድ የሰጠች ሲሆን ባለፈው አመት ከሰጠችው እና ከፍተኛ ከተባለው 408 ፍቃድ ያነሰ ሆኗል፡፡
ለውጭ ምንዛሪ በከፍታ ላይ በጣም ጥገኛ የሆነው የሂማሊያ ብሔር በ2019 በተራራ ላይ መጨናነቅ እና የበርካታ ተሳፋሪዎች ሞት በመፍቀድ ትችት ገጥሞታል። የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት በተራራ ወጭዎች ላይ ጥገኛ የሆነች ኔፓል፣ በፈረንጆቹ 2019 የተራራ ወጭዎች መጨናነቅ እንዲገፈጥርና የሞት አደጋ እንዲከሰት በማድረጓ ተተችታለች፡፡
የኢቨረስት ተራራን ለመጀመሪያ ጊዜ መውጣት ከተጀመረበት ከፈረንጆቹ 1953 ጀምሮ፣ የኢረስት ተራራ በቲቤትና እና በሂማሊያ በኩል ከ10ሺ በላይ ጊዜ ተወጥቷል፡፡
እስካሁን 311ተራራ ወጭ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የሂማሊያ መረጃ ይጠቅሷል፡፡

 ዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ (ዲቪ) አሜሪካ በዕጣ የምትሰጠው የቪዛ መርሀ ግብር ሲሆን ከተወሰኑ ሀገራት በስተቀር ከመላው ዓለም በየዓመቱ ከ50 ሺህ በላይ ፍልሰተኖች አሜሪካ ገብተው የመኖር እና ...
09/05/2022



ዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ (ዲቪ) አሜሪካ በዕጣ የምትሰጠው የቪዛ መርሀ ግብር ሲሆን ከተወሰኑ ሀገራት በስተቀር ከመላው ዓለም በየዓመቱ ከ50 ሺህ በላይ ፍልሰተኖች አሜሪካ ገብተው የመኖር እና የመስራት ፍቃድ ያገኛሉ።

የአሜሪካ መንግስት ከዐለም የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን የዲቪ ሎተሪን እየተጠቀሙ ወደ ግዛቱ እንዲገቡ ማድረግ ከጀመር በርካታ አመታት ተቆጥረዋል።

ለተሻለ ኑሮና ጥሩ የሆነ ግቢ አግኝቶ ሰርቶ ቤተሰብን ለመቀየረ የዲቪ ሎተሪ የሚያመለክቱ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው።

አሜሪካ ከተወሰኑ ሀገራት በቀር በመላው ዓለም ላሉ ሀገራት በምታመቻቸው ከ50 ሺህ በላይ የቪዛ ዕድል አንድ ሀገር የሚደርሰው ከሰባት በመቶ የማይበልጥ ነው።

ከሀገራችን ኢትዮጵያ ለዚህ ዕድል የሚያመለክቱ እጅግ በርካቶች ናቸው።

ለዲቪ የሚያመለክቱ አንድም በትምህርት አልያም በስራ ልምድ የሚወጡ መስፍርቶችን እንዲያሟሉ የሚጠበቅ ሲሆን በትምህርት ደረጃ ቢያንስ የ2ኛ ደረጃን ማጠናቀቅ አለባቸው፤ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ቢሆኑ ደግሞ ጥሩ ነው፤ የትምህርት መመዘኛውን የማያሟሉ በስራ ልምድ ማካካስ የሚችሉ ሲሆን የስራ ልምድ ማስረጃ መያዝ አለባቸው።

በየዓመቱ የዲቪ ሎተሪ ሲሞላ አልያም ሲወጣ የማጭበርበር ድርጊቶች በስፋት ይስተዋላል፤ አጭበርባሪዎች ሰዎችን " የዲቪ እድል ደርሷችኃል " በማለት ያጭበረብራሉ፤ ማንኛውም ሰው ለዲቪ ሲያመለክት ሆነ ውጤት በሚታያይበት ወቅት የአሜሪካ መንግስት ለዚህ ክትትል አንዳች ክፍያ አያስከፍልም።

የ " 2023 የዲቪ ሎተሪ ዕጣ " ትላንት ምሽት ይፋ የተደረገ ሲሆን በዚህ ሊምክ መመልከት ይቻላል : https://dvprogram.state.gov/ESC/Default.aspx

* * በወላይታ የተሰራው   S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት !! * *በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማረ ወጣት ሳሙኤል ዜካሪያስ   S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት ሰራ በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ...
05/05/2022

* * በወላይታ የተሰራው S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት !! * *

በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማረ ወጣት ሳሙኤል ዜካሪያስ S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት ሰራ

በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማረ ወጣት ሳሙኤል ዜካሪያስ ETR S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት ሰርቷል።

ወጣት ሳሙኤል ዜካሪያስ ከዚህ በፍት ከአከባቢው ባገኘው ማተሪያል ተጠቅሞ ኤክስካባተር ሰርቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል።

ወጣቱ በወላይታ ሶዶ ዮኒቨርስቲ አጋዥነት Ethiopian Rocket S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት ሰርቷል፡፡

በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲት ቅጥር ግብ ለማስወንጨፍ ሙከራ እንደሚደረግ ተገልጾ ነበር፡፡

ቢሆንም የወላይታ ሶዶ ዮኒቨርስቲ የ2014 ዓ.ም አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ቅበላ ምክንያት የማስወንጨፍ ሙከራ አልተደረገም፡፡ በቅርቡ የተሳካ ሙከራ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ወጣቱ የሰራው ሮኬት አንድ ኪሎ ሜትር ድረስ የመወንጨፍ አቅም ያለው ሲሆን ሮኬቱን የሚሸከም መኪና አብረው መሰራቱን ታውቋል ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው።

የባልደራስ አመራሮችና አባላት በአዲስ አበባ ታሰሩ። የጣሊያን ወራሪ ኃይል በአምስት አመቱ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ትግል ድል የሆነበትን ዕለት ለመዘከርና አዲስ አበባ፤ አራት ኪሎ በሚገኘ...
05/05/2022

የባልደራስ አመራሮችና አባላት በአዲስ አበባ ታሰሩ።

የጣሊያን ወራሪ ኃይል በአምስት አመቱ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ትግል ድል የሆነበትን ዕለት ለመዘከርና አዲስ አበባ፤ አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሐውልቱ ስር የክብር የአበባ ጉንጉን ለማኖር የባልደራስ ለእውነተኛ ድሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮችና አባላት ዛሬ ወደ ሥፍራው አቅንተው ነበር።

ይሁን እንጂ የባልደራስ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ አምሀ ዳኛው፣ የፓርቲው አባል የሆኑት ወ/ሮ ሰናይት ታደገ እና የካሜራ ባለሙያው ሱራፌል አንዳርጌ ወደ ሐውልቱ ሲያቀኑ የድል በዓሉን እንዳያከብሩ በፖሊስ መከልከላቸው ታውቋል።

ወ/ሮ ሰናይትና አቶ ሱራፌል ደግሞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ሰምተናል።

ባልደራስ በየዓመቱ 4 ኪሎ በሚገኘው ሓውልት የአበባ ጉንጉን ያስቀምጣል።

Sintayehu chekol

81ኛው የአርበኞች ድል የመታሰቢያ በአል በመከበር ላይ ነው።81ኛው የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የመታሰቢያ በአል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።በአሉ በመከላከያ ሰራዊትማርሽ ባን...
05/05/2022

81ኛው የአርበኞች ድል የመታሰቢያ በአል በመከበር ላይ ነው።

81ኛው የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የመታሰቢያ በአል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

በአሉ በመከላከያ ሰራዊትማርሽ ባንድና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሃውልት እየተከበረ ነው።

በመታሰቢ በአሉ አባትና እናት አርበኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበባት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

(ኢ.ፕ.ድ)

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን በሰልፍ እያሰሙ ነው። ተመሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡት ባለፈው ሳምንት ተቀስቅሶ በነበረው ግጭት ሳቢያ የደረሰባቸውን በደልና በዩኒቨርሲቲው ውስ...
05/05/2022

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን በሰልፍ እያሰሙ ነው።

ተመሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡት ባለፈው ሳምንት ተቀስቅሶ በነበረው ግጭት ሳቢያ የደረሰባቸውን በደልና በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሀይማኖት እኩልነት ይከበር : ፍትህ ለክርስትና እምነት ተከታዮች : የታሰሩ ታሪዎች ይፈቱ : መብት ይከበርና የመሳሰሉትን መፈክሮች መፈክሮች በመያዝ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

አሁን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና የተለያዩ የጸጥታ አካላት ጋር ምክክር በማድረግ ላይ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንመለሳለን።

 ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በርካታ የፀጥታ ኃይሎችን አሰማርታለች።በሀገሪቱ የማርሳቢት ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት ምክንያት በርካታ ሰዎች መገዳላቸውን ተከ...
04/05/2022



ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በርካታ የፀጥታ ኃይሎችን አሰማርታለች።

በሀገሪቱ የማርሳቢት ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት ምክንያት በርካታ ሰዎች መገዳላቸውን ተከትሎ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶችና የፀጥታ ኃይሎች የተሰማሩት።

የሀገሪቱ መንግስት ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር ድርቅ፣ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እና ከኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ በቀላሉ መገኘቱ ነው ብሏል።

የኬንያ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር ፖሊስ ከደቡብ ኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ የገቡ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እና ጥይቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተናግረዋል።

የኬንያ መንግሥት በማርሳቢት የፀጥታ ኃይል ከማሰማራት በተጨማሪ ለአንድ ወር የሚቆይ የሰዓት እላፊ አዋጅ እንዲሁም ትጥቅ እንደሚያስፈታም ገልጿል።

በማርሳቢት ከተማ በቅርቡ የተፈጸመውን ግድያ አረመኔያዊ ሲል የኬንያ መንግሥት ያወገዘው ሲሆን በዚህም የአካባቢው አስተዳዳሪም መገደላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

04/05/2022

ከ33ሺ በላይ ተፈናቃዮች ከአበርገሌ ወደ ሰቆጣ መግባታቸው ተነገረ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሁለት ወረዳዎች እና የተለያዩ ቀበሌዎች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪው ተብሎ የተፈረጀው የህወኃት ቡድን ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከቤት ንብረታቸዉ እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል፡፡በዚህም የተነሳ በየእለቱ የተፈናቃዮች ቁጥር በመጨመሩ በርካታ ሰዎች ለእንግልት እየተዳረጉ ይገኛል፡፡

በተለይም ከ70ሺ በላይ ነዋሪዎች የሚገኙባት የአበርጌሌ ወረዳ እስካሁን ድረስ በህወኃት ሀይሎች እጅ ስር በመሆኑ አለመረጋጋቱ መባባሱ ተገልጿል፡፡በወረዳው ያለዉ የጸጥታ ሁኔታ ባለመረጋጋቱ የተነሳ በርካታ ሰዎች ለእግልት እየተዳረጉ በመሆኑ ከ33ሺ በላይ የሚሆኑ ተፋናቃዮዎች ከአበርገሌ ወደ ሰቋጣ እየገቡ ይገኛል፡፡

በአበርገሌ ወረዳ በየእለቱ ከጸጥታ ሁኔታ ባለመረጋጋቱ የተነሳ ህጻናት፣አዛውንቶች እና ሌሎችም ችግር ላይ ናቸው ሲሉ የአበርግሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አለሙ ክፍሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡መንግስታዊ የሆኑ እና ያልሆኑ ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎች እያደረጉ ቢሆንም ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ግን ለበርካታ ሰዎች ተደራሽ ለማድረግ እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡

በወረዳው በመድሀኒት እጥረት በረሀብ እና በጸጥታ ችግር ምክንያት ከ120 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የአበርግሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አለሙ ክፍሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ብስራት ሬዲዮ

04/05/2022

በዛሬው እለት ቤተክርስቲያን ሰብረው ገንዘብ የዘረፉ ግለሰቦች በሁለት ሙስሊም ወንድማማች እና በአከባቢው ህብረተሰብ ትብብር ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጋቸውን በጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

በሶዶ ወረዳ ጊሚሴ ቀበሌ መድሀኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን መስኮት ሰብረው ከሙዳየ ምፅዋት ውስጥ ገንዘብ የሰረቁት ትዛዙ ፍቅሬና አብርሀም ሞላ በመቅቡል መሀመድ፣በሀይሩ መሀመድ እና በአካባቢው ማህበረሰብ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ ተይዘው ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አለማየሁ ደነቀ ተናግረው ወንጀለኛ አብርሀም ሞላ ከዚህ በፊትም ነጌሳ ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የተቀመጠ ጤፍ በመዝረፍ ክስ ቢመሰረትበትም እድሜው አልደረሰም በሚል የተለቀቀ ሲሆን ሁለተኛው ወንጀለኛም ከዚህ ቀደም የማጭበርበር ወንጀሎችን ይሰራ የነበረ ግለሰብ ነው ብለዋል።

የወረዳው ቤተ-ክህነት ሥራ አስኪያጅ መልአከ መዊ አወቀ ወንድሙ በወረዳው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቤተ-ክርስቲያናት እየተሰበሩ ሙዳየ ምፅዋቶች እየተዘረፉ እንደሆነና ዘራፊው ገንዘቡን ሳይሆን የሚፈልገው ህዝቡ ተረጋግቶ እንዳያመልክ ስለሆነ የሚፈለገው መንግስትም ሆነ ማህበረሰቡ የእምነት ተቋማትን መጠበቅና ችግሮች ተፈጥረው ሲገኙ መረጃ ለህግ አካል መስጠት እንደሚያስፈልግ አስረድተው በዛሬው እለትም ሙስሊም ወንደሞቻችን ያደረጉት ተግባር የሚያስመሰግን ነው ብለው በተያዙት ወንጀለኞች ላይም አስተማሪ የሆነ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ መናገራቸውን የዘገበው የሶዶ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
Wollo TV

ከ446 በላይ ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ።የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በክልሎች ደረጃ እየተካሄደ በሚገኘው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅንቄ ከ446 በላይ ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸውን መለየት ...
04/05/2022

ከ446 በላይ ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በክልሎች ደረጃ እየተካሄደ በሚገኘው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅንቄ ከ446 በላይ ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸውን መለየት መቻሉን ገልጿል። የግብዓት፣ የፋይናንስ፣ የመሰረተ ልማት፣ ብቁ የሰው ኃይል እጥረትና የተቀናጀ የመንግሥት ድጋፍ አለመኖር ምርታማነትን ላይ እክል ፈጥሯል ሲሉ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል።

ኢ/ሚ

ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ.ማ የለስላሳ መጠጦችን ማምረት አቆመ።በሀገሪቱ ካለው የለስላሳ መጠጥ ኢንደስትሪ ከፍተኛውን የገቢያ ድርሻ (52%) የሚይዘውና የሚድሮክ ኢትዮጵያ አባል የሆነ...
04/05/2022

ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ.ማ የለስላሳ መጠጦችን ማምረት አቆመ።

በሀገሪቱ ካለው የለስላሳ መጠጥ ኢንደስትሪ ከፍተኛውን የገቢያ ድርሻ (52%) የሚይዘውና የሚድሮክ ኢትዮጵያ አባል የሆነው ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ.ማ በውጭ ምንዛሬ እጥረትና በጥሬ አቃ እጦት የ 7 UP፣ ሚሪንዳ እና ፔፕሲ ምርቶችን ማምረት አቁሟል።

ካፒታል እንደዘገበው ድርጅቱ ለወራት በጥሬ አቃ እጦት ምክንያት ከአቅም በታች በሳምንት ለሦስት ቀናት ብቻ እየሰራ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ችግሩ በማየሉ ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ እንቅስቃሴውን አቁሟል። ችግሩ እልባት እስኪያገኝ ድረስም ሰራተኞቹ ክፍያቸው ሳይቋረጥ እረፍት እንዲወጡ ተገደዋል።

የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ አስፈላጊ የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ከውጭ ለማስገባት መዘግየት ፈጥሯል። ከዚህ በፊት 21 የሚሆኑ የታሸገ ውኃ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች በውጭ ምንዛሬ እጥረትና በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሥራ ማቆማቸው ይታወሳል።

Via: Capital

04/05/2022

#ችሎት

በአዲስ አበባ ከተማ በተከበረው በዒድ አል ፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ አካባቢ የአድማ ብተና የጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ፍርድ ቤት ቀረበ።

የፌደራል ፖሊስ የ 'አድማ ብተና ዘርፍ አባል' የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በአ/አ በተከበረው የዒድ አል ፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ የሰማዓታት መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ ከፈነዳው የአድማ በታኝ የጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውሎ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ ረፋድ ላይ ቀርቧል።

መርማሪ ፖሊስ ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በዓሉ ዕለት በተመደበበት ወንጀል የመከላከል ምደባ ላይ እያለ የታጠቀውን አድማ በታኝ የጭስ ቦንብ በአግባቡ መታጠቅ ሲገባው በአግባቡ ባለመታጠቅ የጭስ ቦንቡ እንዲፈነዳና ሁከት እና ብጥብጥ እንዲፈጠር አድርጓል ያለው መርማሪ በዚህ በተፈጠረ ሁከትና ብጥብጥ የመንግስትና የግለሰብ ንብረት ጉዳት መድረሱን አብራርቷል።

በተጠረጠረበት ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል ለተጨማሪ ማስረጃ አሰባስቦ ለመቅረብ 14 ቀን እንዲሰጠው መርማሪው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በበኩሉ በዕለቱ አስቀድሞ በተመደበበት ቦታ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ እንደነበር እና በሰዓቱ በቦታው ላይ የነበሩ ሰዎች ቁጥር መጨመርና መጨናነቁን ተከትሎ ከታጠቀው ሶስት አድማ በታኝ የጭስ ቦንብ ውስጥ አንደኛው በማያውቀው ሁኔታ መሬት ላይ ወድቆበት በድንገት መፈንዳቱን ገልጿል።

ሆኖም ምንም አይነት ተንኮልም ሆነ ክፋት በውስጤ አልነበረም ወድቆ ሲፈነዳ እኔ እራሴ ደንግጬ ነበር ሲል እያለቀሰ ሁኔታውን ለችሎቱ አስረድቷል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪው ወላጆቹን በሞት ማጣቱን ገልጾ እህትና ወንድሙን በሱ እርዳታ እያስተማራቸው እንደሆነ እና ከለሊት 7:00 ጀምሮ ለጥበቃ ስራ ከመሰማራቴ ውጪ ሌላ ክፋት በውስጤ የለም ሲል ለችሎቱ አብራርቷል።

ጉዳዩን የተከታለው ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ 14 ቀን ፈቅዷል። ለግንቦት 10 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

04/05/2022

አጫጭር ዜናዎች

✔1፤ የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን ሳፋሪኮም ኩባንያ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቱን የሚጀምርበት ጊዜ ከሚያዝያ ወደ ሐምሌ አራዝሞለታል በማለት ካፒታል ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን ዘገባ ባለሥልጣኑ ማስተባበሉን ጋዜጣው ዘግቧል። ሳፋሪኮም የቴሌኮም ፍቃዱን ባገኘ በዘጠኝ ወር አገልግሎቱን መጀመር እንዳለበት በውሉ ላይ ተገልጧል። ሳፋሪኮም እና ኢትዮ ቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ይፋዊ ስምምነት ግን ገና አልተፈራረሙም። ምምነቱ ከተፈረመ በኋላም፣ ተግባራዊነቱ ሦስት ወራት እንደሚፈልግ ምንጮች ተናግረዋል።

✔2፤ ንግድ ሚንስቴር የሲሚንቶ ሽያጭን የትርፍ ሕዳግ የሚወስን እና የዋጋ ቁጥጥር የሚያደርግ መመሪያ እያዘጋጀ እንደሆነ ሪፖርተር አስነብቧል። የጅምላ እና ችርቻሮ የሲሚንቶ ገበያውን የሚመለከተው መመሪያ ያስፈለገው፣ ነጋዴዎች በሚፈጥሯቸው ዘዴዎች የስሚንቶ ግብይትን መቆጣጠር አዳጋች በመሆኑ እንደሆነ ሚንስቴሩ ተናግሯል። ሆኖም
ነጋዴዎች ምርት ይደብቁ እንደሆነ ለማወቅ በቅርቡ የተደረገው አሰሳ ውጤት አላስገኘም። መመሪያው በሁለት ሳምንት ውስጥ ለውሳኔ ይቀርባል። አንድ ኩንታል ሲሚንቶ ባሁኑ ወቅት እስከ 1 ሺህ 100 ብር ድረስ ይሸጣል።

✔3፤ የአማራ ክልል ጸጥታ ቢሮ በጎንደር ከተማ ከተከሰተው ሁከት ጋር በተያያዘ ስድስት የፖለቲካ እና ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ የክልሉ ብዙኀን መገናኛ ዘግቧል። ተጠርጣሪዎቹ የመንግሥት እና የፓለቲካ ሃላፊዎች ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ የገለጠው ዘገባው፣ ከሕዝቡ እና ከመንግሥታዊ አመራሩ ጋር ውይይት ካደረገ በኋላ የእርምት ርምጃ ይወሰድባቸዋል መባሉን አመልክቷል። በቁጥጥር ስር የዋሉትን ሃላፊዎች ማንነት እና ትክክለኛ ሃላፊነታቸውን ግን ቢሮው አልገለጸም።

✔4፤ ሕወሃት በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ለፈጸመው ጥቃት በመተባበር የተከሰሱት ሜ/ጀኔራል ገ/መድኅን ፍቃዱ ሕይወታቸው እንዳለፈ የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል። ተከሳሹ ሕይወታቸው ያለፈው፣ ወህኒ ቤት ግቢ ውስጥ ከቤተሰባቸው ጋር በመነጋገር ላይ ሳሉ በድንገት ራሳቸውን ስተው ከወደቁ በኋላ እንደሆነ ተገልጧል። ሜ/ጀ ገ/መድኅን ከተከሰሱባቸው ወንጀሎች መካከል፣ ሕወሃት ለፈጸመው ጥቃት ጠቃሚ መረጃዎችን ማቀበል እና የወታደራዊ ሬዲዮ ግንኙነቶች ማቋረጥ የሚሉት ይገኙበታል።

✔5፤ የሼህ ሞሐመድ አል አሙዲ ንብረት የሆነው አንጋፋው ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ ከሁለት ሳምንት በፊት ምርት ማቆሙን ካፒታል አስነብቧል። ሞሃ ሚሪንዳ፣ 7 አፕ እና ፔፕሲ በማምረት ላይ ነበር። ፋብሪካው ምርት ያቆመው፣ ለግብዓቶች መግዣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ስላጋጠመው እንደሆነ የፋብሪካው ምንጮች ለጋዜጣው ተናግረዋል። ፋብሪካው ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ በውጭ ምንዛሪ እና ሌሎች ችግሮች ሳቢያ በሳምንት ሦስት ቀናት ብቻ ምርት ሲያመርት እንደቆየ ዘገባው ገልጧል።

✔6፤ የብሪታንያ መንግሥት አፍሪካዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የያዘው ዕቅድ በሕጋዊ መሰናክሎች ሳቢያ ለወራት ሊዘገይ እንደሚችል የጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ተናግረዋል። ዕቅዱ ብሪታኒያ ሕገወጥ ያለቻቸውን አፍሪካዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ በመላክ በምትኩ ለሩዋንዳ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የነደፈችው ነው። ሆኖም ዕቅዱ ከውስጥ እና ከዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የመረረ ተቃውሞ ገጥሞታል።

✔7፤ ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት መርሳቢት ግዛት ላንድ ወር ከምሽት እስከ ንጋት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ መግለጫ ዙሪያ ለፌደራል መንግስት ደብዳቤ ጻፈ! ከተማ አስተዳደሩ ፓርቲው ግጭት የሚናፍቀው  ፣ ሰላም ጠል አስተሳሰብ የተላ...
03/05/2022

የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ መግለጫ ዙሪያ ለፌደራል መንግስት ደብዳቤ ጻፈ!

ከተማ አስተዳደሩ ፓርቲው ግጭት የሚናፍቀው ፣ ሰላም ጠል አስተሳሰብ የተላበሰ ፣ የከሰረ የፖለቲካ ቁማርተኛ በመሆኑ ህዝቡ በሐሰተኛ ወሬ ሳይደናበር የቀደመ ሰለማዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲሄድም ጠይቋል ፡፡

ለፌደራል የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ:- ተገቢውን የህግና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድልን ስለመጠየቅ ፣
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኩ) ባወጣው መግለጫ የፍኖተ ሰላም መስጊድ እንደተቃጠለ በመግአበባ ያልተደረገ የሌለ ያልታሰበ የማይታሰብ ወሬ ፈጥሮ በቀን 23/08/2014 ዓ.ም አሰራጭቷል ። ነገር ግን በእለቱ በፍኖተሰላም ከተማም ሆነ በምዕራብ ጎጃም ዞን እንዲሁም በአማራ ክልል ያለምንም ችግር እጅግ ሰላማዊ ፣ አብሮነትን በሚያጠናክር እና ሙስሊም ክርስቲያን በደስታ በእልልታ በሰላም 1443ኛውን የኢድ ል ፈጥር በአሉን ማክበሩን እናረጋግጣለን።

ይሁን እንጅ ያለምንም የመረጃ ምንጭ ከመሬት አፍሶ፣ ከአየር ላይ ቀዝፎ እድሜ ልኩን ግጭት የሚናፍቀው ሰላም ጠል አስተሳሰብ የተላበሰው የከሰረ የፖለቲካ ቁማርተኛ ቅጠሉን "ብር ነው" ብሎ የሚጣላ የፓለቲካ አመራር ስብስብ ያለበት መሆኑ ቢገባንም አንድ በታሪክ ትልቅ የሆነ የኦሮሚያን ህዝብ እወክላለሁ ከሚል ፓርቲ እንዲህ አይነት የውሸት መረጃ ማሰራጨቱ ፖርቲው ምን ያህል ከህዝብ የራቀ ለሰላም ጠንቅ መሆኑን ያሳየበት የዜጎችን በሃይማኖት በብሄር ሳይነጣጠሉ አብሮ የመኖር ሰዋዊ ባህሪ የሚፃረር ፀረ ሰላም ፓርቲ ሆኖ አግኝተነዋል።

ፓርቲው በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እውቅና ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስ ህጋዊ እንደመሆኑ በከተማችን ላይ ያልታየ ያልተሰማ በፍፁም ከእውነት የራቀ የውሸት መግለጫ በሬው ወለደ ብሎ ፍኖተሰላም ከተማ " መስጊድ ተቃጠለ ብሎ" መግለጫ ስለሰጠ የፌደራል መንግስት ፓርቲውን በህጋዊና በአስተዳደራዊ እርምጃ እንዲጠይቅልን ተገቢው እርምት እንዲሰጥልን እና መስጊድ ተቃጥሏል በሚል የተላለፈውን መልክት በራሱ መግለጫ ይቅርታ ጠይቆ እንዲያስተላልፉ በጥብቅ እንጠይቃለን።

ፍኖተ ሰላም ከተማ በርካታ ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ስትሆን ሙስሊሙ በቤተክርስቲያን ስራ ክርስቲያኑ በመስጊድ ስራ እየተባበሩ እና እንደ አንድ አፍ ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን ልብስና ገላ ሆነው ያለምንም ልዮነት በፍቅር ፣ በአብሮነት፣ በመተባበር የሚኖሩባት ከተማ ናት። ይህ የከተማችን እሴት ትናንትም የነበረ ነገም የሚቀጥል ነው። ማንም በሚያሰራጨው የውሸት እና የፈጠራ መረጃ ሊያውከው የማይችል የህዝብ አንድነት አለ።

የፍኖተ ሰላም ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

 # የተማሪዎች መግቢያ_ቀናት የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን እና ሪፖርት የሚያደርጉበትን ቀን እያሳወቁ ይገኛሉ። በዚህም መ...
03/05/2022

# የተማሪዎች መግቢያ_ቀናት

የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን እና ሪፖርት የሚያደርጉበትን ቀን እያሳወቁ ይገኛሉ።

በዚህም መሰረት የተማሪዎችን መግቢያ ቀን ከቆረጡ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ፦

👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2014 ዓ/ም ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ

👉 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም

👉 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም

👉 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም

👉 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም

👉 ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም

👉 ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1 /2014 ዓ/ም

👉 ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም

👉 ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14

ሲሆን ሌሎችም በቅርቡ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ ስታር

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Star Media አዲስ ስታር ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Addis Star Media አዲስ ስታር ሚዲያ:

Videos

Share

Category