NBC Ethiopia

NBC Ethiopia NBC Ethiopia is a television station broadcasting on Ethiosat 11105 H and DSTv Channel 477

የገና በዓል የንግድ ዐውደ ርዕይና ባዛር በባሕር ዳር ሊካሄድ ነው፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA- "ባዛራችን ለሰላማችን ጥርን በባሕር ዳ...
01/01/2025

የገና በዓል የንግድ ዐውደ ርዕይና ባዛር በባሕር ዳር ሊካሄድ ነው
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA- "ባዛራችን ለሰላማችን ጥርን በባሕር ዳር" በሚል መሪ ሀሳብ የንግድ ዐውደ ርዕይና ባዛር በባሕር ዳር ከተማ ሊካሄድ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ገለፀ።

ዐውደ ርዕይና ባዛሩ በባህር ዳር ከተማ በሸማቹና በአምራቹ መካከል ዘላቂ የሆነ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አደራ ጋሼ እንዳሉት ዐውደ ርዕይና ባዛሩ ከታህሳስ 25 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም "ባዛራችን ለሰላማችን ጥርን በባህር ዳር" በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል።

ባዛሩ አምራቹና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይገበያዩበታል ብለዋል።

ዐውደ ርዕዩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የማነቃቃት እድል እንዳለ ገልጸው፤ ለዚህም አዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰዋል።

ዐውደ ርዕዩና ባዛሩ በድሮው "አለ በጅምላ" ግቢ ውስጥ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል።
ህብረተሰቡ በስፍራው በመገኘት የሚፈልጋቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በቀጥታ ከአምራቾችና ከጅምላ አከፋፋዮች ማግኘት እንደሚችል መግለፃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

የተለያዩ የአለም ሃገራት አዲሱ የፈረንጆች አዲስ አመት 2025ን በተለያዩ ዝግጅቶች ተቀብለዋል።የተወሰኑ ሃገራት አዲሱን አመት አቀባበል በምስል፡-
01/01/2025

የተለያዩ የአለም ሃገራት አዲሱ የፈረንጆች አዲስ አመት 2025ን በተለያዩ ዝግጅቶች ተቀብለዋል።

የተወሰኑ ሃገራት አዲሱን አመት አቀባበል በምስል፡-

የቴሌኮም ማስፋፊያዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ  እየተሰራ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም ገለጸ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA-በተቋማት ላይ የሚነሱ ...
01/01/2025

የቴሌኮም ማስፋፊያዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም ገለጸ
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA-በተቋማት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦችን ወደ ምክር ቤት በማምጣት ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርገው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ ኢትዮ ቴሌኮምን የተመለከቱ ከህብረተሰቡ የተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጓል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ከህዝቡ ከሰበሰባቸው 2 ሺህ ገደማ ጥያቄዎች 236ቱ የኢትዮ ቴሌኮምን የአገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮ ቴሌኮም የሥራ ሂደትን የገመገመ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮምም ለተነሱለት ጉዳዮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዲጅታል 2025ን እውን ለማድረግ አቅዶ እየሰራ የሚገኘው ተቋሙ ተደራሽነት ከማስፋት እና የደንበኞቹን ቁጥር ከማሳደግ ረገድ ሞባይል ተጠቃሚዎችን 80 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

ከአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ዙሪያ የቀረቡትን ጥያቃዎች ላይ በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን ም ነው የተናገሩት፡፡

የተነሱት ጥያቄዎች ስራቸውበከፊልና ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ፣ በሂደት ላይ የሚገኙ እንዲሁም ጥናት እየተደረገባቸው የሚገኙ መሆናቸውን ስራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርትም ኢትዮ ቴሌኮም ከ2018 ጀምሮ ማሻሻያዎች እያደረገ ሲሆን በ4 ጂ ኔትዎርክ ዝርጋታ 442 ከተሞች ተደራሽ ሲሆኑ 11 ከተሞች ደግሞ የ5 ጂ ኔትዎርክ ተደራሽ መሆን መቻላቸው ተመላክቷል፡፡

በቀጣይም ማሻሻያና ማስፋፋያ በማከናወን ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ እና የደንበኞችን ፍላጎት ለማሳካት እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በ2017 ዓ.ም ከተያዘው እቅድ ተጨማሪ 1 ሺህ 298 የሞባይል ጣቢያዎችን ለመገንባት ውጥን መያዙ ተገልጿል፡፡

በ- ሰላም ይልማ

በ2025 ደስተኛ ለመሆን…ቢቢሲ እንግሊዘኛ በድረ ገጹ በአዲሱ ዓመት ደስተኛ መሆን ከፈለጉ እኚህን ስምንት ነገሮች ያድርጉ ሲል ምክር ሰጥቷል፡፡1. ከእኩያዎቻችሁ ጋር ጓደኝነት መመስረት2. ም...
01/01/2025

በ2025 ደስተኛ ለመሆን…

ቢቢሲ እንግሊዘኛ በድረ ገጹ በአዲሱ ዓመት ደስተኛ መሆን ከፈለጉ እኚህን ስምንት ነገሮች ያድርጉ ሲል ምክር ሰጥቷል፡፡

1. ከእኩያዎቻችሁ ጋር ጓደኝነት መመስረት

2. ምስጢር መያዝን መለማመድ

3. በጎ ሥራዎች ላይ ተሳትፎ ማድረግ

4. ከአያቶች እና ከታላላቅ ሰዎች ጋር መጫወት

5. ያለፈውን የሕይወት ገጸ በረከት ቆጥሮ መጻፍ

6. አልፎ አልፎ አዝናኝ እና ያልተለመዱ ነገሮችን ማከናወን

7. ይህ ቢሆንልኝ ብሎ ከመጠበቅ እንዲሆን መስራት

8. እንደቡና ያሉ የሚያነቃቁ መጠጦችን ከመጠን በላይ አለመጠጣት

የፈረንጆቹ 2024 ዓመት በጋዛ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት እና በበርካታ ምስቅልቅሎሽ ውስጥ ያለፈ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

2025 ምን ይዞ ይመጣል የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሲሆን ዓለም አዲሱን መዝገብ በጎ ወይም ክፉን ልትጽፍበት አንድ ብላ ጀምራዋለች፡፡

በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ

https://youtu.be/1Wv7TiZvhCs
01/01/2025

https://youtu.be/1Wv7TiZvhCs

National Media SC is here to support, the success of our country's transformational journey; to develop a civic-democratic political culture; which will be f...

ብሔራዊ ቤተመንግስት የኢትዮጵያን ቀደምት ስልጣኔ እና ገናናነት የገለጠ ነው - የመገናኛ ብዙሃን ሀላፊዎች፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA-...
01/01/2025

ብሔራዊ ቤተመንግስት የኢትዮጵያን ቀደምት ስልጣኔ እና ገናናነት የገለጠ ነው - የመገናኛ ብዙሃን ሀላፊዎች
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA- ዕድሳት ተደርጎለት በቅርቡ የተመረቀው ብሔራዊ ቤተመንግስት የኢትዮጵያን ቀደምት ስልጣኔ እና ገናናነት የገለጠ መሆኑን የመገናኛ ብዙሃን ሀላፊዎች ገለጹ።

የመገናኛ ብዙኃን እና የቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ብሔራዊ ቤተመንግሥትን ጎብኝተዋል።

የኤን.ቢ.ሲ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ብሩክ ከበደ ብሔራዊ ቤተመንግስት የታደሰበት መንገድ ትላንት፣ ዛሬን እና ነገን በሚያሳይ መልኩ መከናወኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ይህንን ትውልድ እንዲያየው መደረጉ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው፥ ብዙ የተለፋበት ሀገር መሆኑንም የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ቅርሶች ቅርጽና ይዘታቸውን ሳይለቁ አሁን ላለው ትውልድ በሚመጥን ደረጃ እንዲታዩ ሆነው የተዘጋጁበት መንገድ አስገራሚ መሆናቸውን ጠቅሰው፥እድሳቱን የሰሩ አካላትም ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

ትውልዱም ከየት ተነስቶ ወዴት እንደሚሄድ ሊያይበት የሚችልበት ግሩም ስራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የካፒታል ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ትእግስት ይልማ በበኩሏ ኢትዮጵያ ትልቅ ታሪክ እና ቅርስ ያላት ሀገር መሆኗን ገልጻ፤ ብሔራዊ ቤተመንግስት ይህንን ታሪክና ቅርስ አዋህዶ ለትውልድ የሚያስተላልፍ መሆኑን ተናግራለች።

በርካታ ሀገራት መሰል ቦታዎችን አዘጋጅተው ታሪካቸውን የሚያሳዩበት መሆኑን ጠቅሳ፥የብሔራዊ ቤተመንግስት የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች የኛን ታላቅነት የሚመለከቱበት ነው ብላለች።

በኢትዮጵያ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች መኖራቸውን ያነሳችው ትእግስት ብሔራዊ ቤተመንግስት በዚህ መልኩ መታደሱ ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቅሳለች።

የናሁ ቴሌቭዥን ስራ አስኪያጅ ኢዶሳ ቀጀላ በበኩላቸው፥ የብሔራዊ ቤተመንግስት ትውልድ የሚማርበት የኢትዮጵያን ክብር የሚገልጽ ስራ መሆኑን ገልጸዋል።

ቁመናችንን በትክክል የሚገልጽ እና ታላቅ ሀገር እንደሆንን በግልጽ የሚያሳይ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ቤተመንግስቱ ያለንን ቅርስ ምቹ አድርገን በማስተዋወቅ ጥቅም ላይ ብናውል የት እንደርሳለን የሚለውን ያየንበት ነው ያሉት ደግሞ የፋና ሚድያ ኮርፖሬሽን ቻናል ሁለት ስራ አስፈጻሚ እመርታ አስፋው ናቸው።

የብሔራዊ ቤተመንግስት የኢትዮጵያን ቀደምት ስልጣኔ እና ገናናነት የገለጠ መሆኑንም ጠቅሰው፥ ትውልዱ ታሪኩን ተመልክቶ ታድያ ለምን የሚለውን እንዲጠይቅና ቁጭት በመፍጠር በትጋት እንዲሰራ የሚያበረታታ መሆኑን አመላክተዋል።

ትርክት ከመፍጠር አኳያም ትውልዱ በራሱ እንዲመካ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

https://youtube.com/live/cGR2NEpa1gA
01/01/2025

https://youtube.com/live/cGR2NEpa1gA

የታህሳስ 23 ኤን ቢ ሲ የቀን ዜናዎች | NBC ዜና | ቀጥታ ሥርጭት| Live | Ethiopia transformational journey; to develop a civic-democratic political culture; which...

የመውለድ አለመቻል (መቸገር)  ስነ-ልቦናዊ ጫናዎች📌 ስሜታዊ ውጥረት እና ጭንቀትለመፀነስ የመሞከር ሂደት፣ በተለይም በሕክምና ስሜታዊ ሊያደርግና አድካሚ ሊሆን ይችላል። ብዙውን ጊዜ ሴቶች የ...
01/01/2025

የመውለድ አለመቻል (መቸገር) ስነ-ልቦናዊ ጫናዎች

📌 ስሜታዊ ውጥረት እና ጭንቀት
ለመፀነስ የመሞከር ሂደት፣ በተለይም በሕክምና ስሜታዊ ሊያደርግና አድካሚ ሊሆን ይችላል። ብዙውን ጊዜ ሴቶች የተስፋ ማግኘትና ከዚያም ተስፋ መቁረጥ ዑደት ውስጥ ይከታቸዋል። ይህም ከፍተኛ ጭንቀት ያስከትላል።

📌የጥፋተኝነት ስሜት እና በቂ ያለመሆን ስሜት
ከመውለድ መቸገር ጋር የሚታገሉ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ጥልቅ የሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ወይም በቂ ያለመሆን ስሜት ይሰማቸዋል። መፀነስ በማይችሉበት ጊዜ እራሳቸውን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

📌 የመንፈስ ጭንቀት እና ራስንን ማግለል
ለመውለድ አለመቸል (መቸገር) ወደ መገለል እና የመንፈስ ጭንቀት ሊያመራ ይችላል። በተለይም ጓደኞች፣የቅርብ ሰዎች ወይም የቤተሰብ አባላት ልጆች ሲወልዱ፣ ማኅበራዊ ስብሰባዎች(ዝግጅቶች) ፣ በዓላት፣ እና አልፎ ተርፎም ስለቤተሰብ ምጣኔ የሚደረጉ ውይይቶች አንዳንድ ሴቶችን ከማህበራዊ መስተጋብር ራሳቸውን እንዲያገሉ ሊያደርጓቸው ይችላሉ።

📌 የግንኙነት ውጥረቶች
ለመውለድ መቸገር በተለይ ከትዳር አጋር ጋር ያለውን ግንኙነት ሊያሻክር ይችላል። የመፀነስ ግፊት የመቀራረብ ትኩረትን ሊቀይር ይችላል፣ እና ጥንዶች ለመግባባት ሊቸገሩ ወይም ስሜታዊ ከፍታዎችን እና ዝቅታዎችን አብረው ሲጓዙ ውጥረት ሊሰማቸው ይችላል።

📌 የማህበራዊ ጫና ሚና
በእናትነት ዙሪያ ያሉ ማህበራዊ እና ባህላዊ ሁኔታዎችና ግምቶች የመውለድ መቸገር ስሜታዊ ጫናን ያጎላሉ። ይህ ጫና ወደ በቂ ያለመሆን እና የብስጭት ስሜት ሊያመራ ስለሚችል ጉዞውን የበለጠ ፈታኝ ያደርገዋል።

📌 የሕክምና አማራጮችን መፈለግ
እነዚህም ከአኗኗር ዘይቤ ለውጦች፣ መድኃኒቶች፣ የላቁ ሕክምና ሂደቶች ስፔሻሊስት ሃኪሞች ጋር ቀደም ብሎ ማማከር የተሻለውን መንገድ ለመለየት ይረዳል።

01/01/2025

የታህሳስ 23 ኤን ቢ ሲ የቀን ዜናዎች | NBC ዜና | ቀጥታ ሥርጭት| Live | Ethiopia

በአዲስ አበባ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መቅረብ ያስፈልጋል፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETH...
01/01/2025

በአዲስ አበባ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መቅረብ ያስፈልጋል፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአዲስ አበባ በሚገኙ ባንኮች የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መቅረብ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ከዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ መሆኑን አስታውቋል።

በሸገር ከተማ 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት እየተሰራ ይገኛል-ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA- ...
01/01/2025

በሸገር ከተማ 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት እየተሰራ ይገኛል-ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA- በሸገር ከተማ በመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የተቀናጀ የኮሪደር የመሰረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተናገሩ።

በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም በመስፋት ላይ ነው።

ለዜጎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢ እንዲሁም ደረጃውን የጠበቁ መሰረተ ልማት ያሟሉ ውብና ዘመናዊ ከተሞችን የመፍጠር ግብን የያዘው የኮሪደር ልማት በሸገር ከተማም ተጀምሯል።

የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) በመጀመሪያው ዙር 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን የሚያዘምኑ እና ለረጅም ዓመታት የሚያገለግሉ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ያካተተ ነው ብለዋል።

የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮም እንዲሁም የተሽከርካሪ፣ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የህዝብ መዝናኛና ሌሎች ወሳኝ መሰረተ ልማቶች የሚገነቡበት እንደሆነም ጠቁመዋል።

በከተማዋ የሚያልፉ ዋና ዋና መንገዶች በመኖራቸው ከፌዴራል ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ክፍለ ከተሞች ያላቸውን ጸጋ መሰረት በማድረግ የተለየ አደረጃጀት እንዲኖራቸው መደረጉን ነው ያብራሩት።

በዚህም መሰረት ኮዬ የፋይናንስ ማዕከል፣ ገላን የኢንዱስትሪ ማዕከል፣ እንዶዴ የሎጂስቲክስ ማዕከል፣ ሰበታ የወጪና ገቢ ምርቶች ማቀነባበሪያ ዞን፣ ሱሉልታ እና መነአቢቹ የግሪን ቤልት ዞን ይሆናሉ ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ስራውን ለማቋረጥ ሲል የገዛ ጣቶቹን የቆረጠው ህንዳዊ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA- አንድ የ32 አመት ህንዳዊ በዘመዱ ኩባንያ ውስጥ ...
01/01/2025

ስራውን ለማቋረጥ ሲል የገዛ ጣቶቹን የቆረጠው ህንዳዊ
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA- አንድ የ32 አመት ህንዳዊ በዘመዱ ኩባንያ ውስጥ የኮምፒውተር ኦፕሬተር ሆኖ መስራቱን ላለመቀጠል ሲል ከግራ እጁ ላይ አራት ጣቶቹን መቁረጡን አመነ።

መስራት እንደማይፈልግ ለአለቃው መናገር የከበደው የ32 አመቱ ማዩር ታራፓር የተባለው ህንዳዊ ጣቶቹን በአደጋ ምክንያት ያጣ ለማስመሰል ሲሞክር የነበረ ቢሆንም ከፖሊስ ምርመራ በኋላ ግን ስራ ላለመስራት ሲል ጣቶቹን እንደቆረጠ አምኗል።

ማዩር በመጀመሪያ በትውልድ ከተማው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ሞተር ሳይክሉን እየጋለበ ወደ ጓደኛው ቤት ሲሄድ በድንገት የማዞር ስሜት ተሰምቶት በመንገዱ ዳር እንደወደቀና ከደቂቃዎች በኋላ ሲነቃ ጣቶቹ ተቆርጠው እንዳገኛቸው ለፖሊሶች ተናገረ።

ፖሊሶችም የመጀመሪያ ግምታቸው የማዩር ጣቶች ለጥቁር አስማት ስነስርዓት ሲባል ተቆርጠው እንደተወሰዱ ሲሆን ከተጨማሪ ምርመራዎች በኋላ ግን ማዩር ራሱ ጣቶቹን እንደቆረጠ ደርሰውበታል። ዘገባው የኦዲቲ ሴንትራል ነው።

በ-ዳንኤል መኮንን

01/01/2025

📌የፑቲን እና የኪም የጠበቀ ወዳጅነት!

📌ሰሜን ኮሪያ እና አለም!

የመንግሥትን እና የሕዝብን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰራባ ተሐድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል አቀባበል ተደርጎላቸዋል።፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ET...
01/01/2025

የመንግሥትን እና የሕዝብን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰራባ ተሐድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA- የመንግሥትን እና የሕዝብን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰራባ ተሐድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የሀገር ሽማግሌዎች የሃይማኖት አባቶችና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም በሰራባ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኝተው አቀባበል አድርገዋል።

በአማራ ክልል ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው ግጭት የክልሉ ሕዝብ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ ገብቶ ቆይቷል። ከዚህ ቀውስ በመውጣት ክልሉ ወደ ሰላም እንዲመጣ መንግሥትና ሕዝብ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል።

የክልሉ ሕዝብ ወደነበረበት ሰላም መመለስ አለበት ያሉ ታጣቂዎችም ይህን የሰላም ጥሪ በመቀበል በተሐድሶ ማዕከላት አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
አስተያየታቸውን የሰጡት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰራባ ካምፕ አቀባበል የተደረገላቸው አላምረው ንጉሴና አማኑኤል ተካልኝ የክልሉ ሕዝብ በዚህ ግጭት ያተረፈው ሞትና ውድመት መሆኑን በመረዳታቸው የመንግሥትንና የሕዝብን ጥሪ መቀበላቸውን ተናግረዋል።

የገቡበት የትጥቅ ትግል ስህተት እንደነበር የገለጹት የመንግሥትን ጥሪ የተቀበሉት ታጣቂዎች የበደልነውን ሕዝብና ለመካስ ዝግጁ ነን ብለዋል።
በክልሉ ያለው ቀውስ መቆም እንዳለበት ያነሱት ወርቅየ ሀድጎና ሰለሞን አስማረ በጦርነት የሚመጣ ለውጥ እንደሌለ ባለፉት ጊዜያት ታዝበናል ብለዋል። በዚህ የትጥቅ ትግል የምናተርፈው ነገር የለም የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በጫካ የሚገኙ ወንድሞቻችንም የመንግሥት ጥሪውን እንዲቀበሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በአቀባበሉ ላይ የተገኙት የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው የክልሉን ሕዝብ ሰላም ለማድረግ የመንግሥትንና የሕዝብን ጥሪ መቀበላችው የሚመሰገን ነው ብለዋል።

በቀጣይም የክልሉን ሕዝብ ወደ ሰላም እንዲመጣና ወደ ቀደመ ልማቱ እንዲመለስ የራሳችሁን ኃላፊነት ልትወጡ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሰላም ጥሪን የተቀበሉ የታጠቁ ኃይሎች በጭልጋ ሰራባ ካምፕ ትጥቃቸውን ለመንግሥት ማስረከባቸውን የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በሪሁን መንግሥቱ ገልጸዋል።

መንግሥትና የክልሉ ሕዝብ የሚያቀርበውን የሰላም ጥሪ እየተቀበሉ የሚገኙ ኃይሎች የክልሉን ሕዝብ ልማት ለማሳደግ እንዲሠሩ ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።
አቶ በሪሁን የታጠቁ ኃይሎች የሰላም ጥሪውን መቀበላቸው የክልሉ ሕዝብ ሰላም እንዲረጋገጥ ያደርጋል ነው ያሉት።
የሰላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡ ታጣቂዎች ከስልጠና በኋላ የሥራ እድል እንደሚፈጠርላቸውም አስታውቀዋል።

ዘገባው የአሚኮ ነው።

01/01/2025

📌እስራኤል ለኢራን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠች❗️

📌ሺ፡ፑቲን እና ኪም ምን አወሩ⁉️

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስብሰባ አንኳር ጉዳዮች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ታኅሣሥ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባው በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ...
01/01/2025

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስብሰባ አንኳር ጉዳዮች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ታኅሣሥ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባው በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች ላይ ተወያይቷል። ከውይይቱ በኋላ ባወጣው መግለጫም ቀጥሎ የተጠቀሱ አበይት ጉዳዮችን ይፋ አድርጓል።

የዋጋ ግሽበት፡-

ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት ባሳለፍነው ወርኅ ሕዳር ወደ 16.9 በመቶ በመውረድ ካለፉት አምስት ዓመታት ዝቅተኛው አሃዝ ተመዝግቧል፡፡ ምርታማነትና ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ መተግበሩ ለዚህ በጅቷል። የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጥ እና አስተዳደራዊ የዋጋ ማሻሻያ ምግብ ነክ ላልሆነ የዋጋ ግሽበት ሲጨምር ምግብ ነክ ያልሆነ የዋጋ ግሽበት ባለፈው ወር ከነበረው 11.6 በመቶ ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ ጭማሪ አሳይቷል።

ዕድገትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፡-

አብዛኞቹ አመልካቾች እንደሚያሳዩት፣ በዘንድሮው የ2017 በጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በግብርናው፣ ኢንዱስትሪው፣ አገልግሎቱ ዘርፎች ዕድገት እንዳለ አመላካቾች ያሳያሉ።

የገንዘብ አቅርቦት ሁኔታ፡-

በ2017 በጀት ዓመቱ ጅማሮ ወዲህ በሁሉም የገንዘብ ዝውውር አመልካቾች ዘንድ በመጠኑ ከፍ ያለ ዕድገት ታይቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ወራት ወዲህ የገንዘብ አቅርቦት ዕድገት ቢኖርም፤ ከኢኮኖሚው ስፋት አንጻር የገንዘብ ዝውውር አመልካቾች የመቀነስ አዝማሚያ ታይቶባቸዋል፡፡

የፋይናንስ ዘርፍ መረጋጋት፡-

የባንክ ሥርዓት ዝቅተኛ የተበላሸ ብድር፣ ከፍ ያለ የመጠባበቂያ ሂሳብና በቂ ካፒታል ያለው በመሆኑ ጤናማና የተረጋጋ እንደሆነ በኮሚቴው ተገምግሟል፡፡ በአንዳንድ ባንኮች ዘንድ ከፍ ያለ የጥሬ ገንዘብ አከል ንብረት እጥረት ተከስቷል፡፡

የፊስካል ሁኔታ፡-

የበጀት እንቅስቃሴዎች ጥሩ አዝማሚያ አሳይተዋል፡፡ ይህም በዘንድሮው በጀት ዓመት ለበጀት ጉድለት ማሟያ ከብሔራዊ ባንክ ብድር እንዳይወሰድ ያደረገና የማዕከላዊ ባንኩን የገንዘብ ፖሊሲ አቋም በእጅጉ የሚደግፍ ሆኗል፡፡

የውጭ ኢኮኖሚ ዘርፍ፡-

የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ለውጥ ለውጭ ንግድ ዘርፍ ትልቅ መሻሻል ለገቢ ንግድ ግን መጠነኛ ቅናሽ ታይቶበታል፡፡ የንግድ ባንኮችም ሆነ የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፡፡

ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች፡-

የዓለም ኢኮኖሚ የሀገር ውስጥ ሁኔታዎችን የሚነካው በዋናነት በሸቀጦች ዋጋ አማካይነት ሲሆን፤ አሁን ያለው የሸቀጦች ዋጋ በጥቅሉ ለሀገራችን ምቹ ነው ሊባል ይችላል፡፡

የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የቅርብ ጊዜ የዋጋ ግሽበት ሁኔታ አበረታችና በጥቅሉ የመርገብ አዝማሚያ ቢያሳይም፣ ጠበቅ ያለ የገንዘብ ፖሊሲ መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ተገንዝቧል፡፡ በዚህም ኮሚቴው የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን አቅርቧል።

የዋጋ ግሽበት ለመቀነስና የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ተመን መኖሩን ለማረጋገጥ ሲባል የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን አሁን ባለበት 15 በመቶ እንዲቆይ ማድረግ አንደኛው ምክር ሃሳብ ነው።

ሁለተኛው ምክረ ሃሳብ ደግሞ የባንክ ብድር ዕድገት ግብ የመጠቀም ሁኔታ እንዲቀጥል፤ ነገር ግን ለዚህ በጀት ዓመት የብድር ዕድገት ግቡ ከ14 በመቶ ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል ነው፡፡

በመጨረሻም በብሔራዊ ባንክ ለባንኮች በሚሰጣቸው የአንድ ቀን የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት፣ በአንድ ቀን የብድር አገልግሎት ላይ የሚከፈሉ የወለድ ተመኖች ባሉበት እንዲቀጥሉ እና ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት የግዴታ መጠባበቂያ ተቀማጭ ሂሳብ በነበረበት እንዲቆይ ወስኗል፡፡

በሀዋሳ ከተማ የ5.6 ኪሎሜትር የኮሪደር ልማት ስራን በቀጣይ ስድስት ወራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ሀዋሳ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA-የ...
01/01/2025

በሀዋሳ ከተማ የ5.6 ኪሎሜትር የኮሪደር ልማት ስራን በቀጣይ ስድስት ወራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
ሀዋሳ | ታህሳስ 23 2017| NBC ETHIOPIA-የሲዳማ ክልል መቀመጫ በሆነችው ሀዋሳ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የ5.6 ኪሎሜትር የኮሪደር ልማት ስራን በቀጣይ ስድስት ወራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ ገልፀዋል።

በሀዋሳ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ከመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት ቀጣይ ምዕራፍ መሆኑን አንስተዋል።

ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት የእግረኛ፣ የተሽከርካሪ፣ የብስክሌት መሰረተ ልማቶችን ጨምሮ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶችን እና የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን ያካተተ መሆኑን ከንቲባው ገልፀዋል። የኮሪደር ልማቱ ሲጠናቀቅ 4 ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማሳለፍ እንደሚችል አክለዋል።

በመጀመሪያ ዙር የተመረቀው የኮሊደር ልማት በርካታ ልምድን እንድንወስድል አስችሎናል ያሉት ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ ሁለተኛው ዙር የኮሊደር ልማት የክልሉን ባህል እና ትውፊት የሚያንፀባርቁ ጉዳዮች ተካቶበት በ2.6 ቢሊየን ብር እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የቱሪስት መዳረሻ የሆነችው ሀዋሳን ለነገው ትውልድ የተዋበች፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን እና የከተማዋን ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሀሴት ኃይሉ

በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁናዊ ከፊል ገጽታ:
01/01/2025

በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁናዊ ከፊል ገጽታ:

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when NBC Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category