Atinafu Chafo

Atinafu Chafo Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Atinafu Chafo, TV Network, Arba Minch, Addis Ababa.

18/02/2020

በድንግል ማርያም ስም ይህ ታምር ሳታነቡና ሼር ሳታረጉ አትለፉ
ይህ የምትመለከቷት ሚዳቋ በሸጎሌ ቅድስት አርሴማ ገዳም አንድ አባት ኪዳን
አድረሰዉ ከቤተክርስቲያን ይወጣሉ ሲወጡ ይች የምትመለከቷት ሚዳቋ
የካህኑን እግር ትጠልፍና እየጮኸች ወደ ዋሻዉ እየመራቻቸዉ ትሔዳለች
እሳቸዉም እሷን እየተከተሉ ዋሻ ዉስጥ ገቡ ሚዳቋም ሔዳ የሚፈልቅ ዉሐ ጋር
ቆመች ያም የእናታችን የሠማህቷ የቅድስት አርሴማ ፀበል ሆነ በዛች ሚዳቋ
መሪነት የሚገርመዉ ካህን አያጠምቅም ቦታዉ ላይ ገና ስትደርሱ እርኩስ መፈስ
ያለበት ሰዉ መጮህ ይጀምራል ይያዛል ጠማቂዎቹ መላህክት ናቸዉ በመንፈስ እዛ
ዋሻ ዉስጥ ያሉ ፀበሎች የቅድስት አርሴማ የኪዳነ ምህረት የመጥምኩ የቅዱስ
ዮሐንስ የክርስቶስ ሰምራ ዮርዳኖስ ፀበል ይኖራሉ ደጇን የረገጠ ማንም
ሳይፈወስ አይመለስም ድንግል ምስክሬናት ዋሻ ዉስጥ እየተፀለየበት በድጋይ የተፈለፈለ አለ ገና መሠረተ ድጋይ ተጥሏል ቤተክርስቲያን ሊሰራ መው

መተት ጨሌ ቡዳ ሟርት ኤቻይቪ ኩላሊት መዳኒት ያለተገኘለት በሽታ ሁሉ በፀበሉ ድነዉ
ምስክርነት እየሰጡነዉ

ሚዳቆዋም ፀበሉን የማያዉቁ ሰዎች እየመራች
ትወስዳለች ቦታዉ ከአዲስ አበባ ጎጃም በረዳ ታክሲ 3 ብር ሩፋኤል በሚለዉለዉ
ትገቡና ከሩፋኤል ሸጎሌ ኪዳነምህረትና አርሴማ በእግራቹ ትኤዳላችሁ ከዛ
ተሣልማችሁ ወደቀኝ ዞራችሁ ቀጥታ መለስ ፓርክ በኩል ትገቡና ቀጥታ
ኮብልስቶን መገዱን ይዛችሁ ስቴዱ ዋሻዉንና ተአምረኛዉን ፀበል ትደርሳላችሁ
የቅድስት አርሴማ ረድኤቷና በረከቷ አይለየን በእግዚሐብሔር ስም ለሁሉም ሼር
አርጉ መሔድ የምትችሉ የበረከቱ ተካፋይ ሁኑ ወስብአት ለእግዚሐብሔር
ወላዲቱ ድግል ወለመስቀሉ ክብር ይቆየን አሜን

Source. https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1140393346124208&id=100004606607250&_rdr

15/02/2020
15/02/2020
14/02/2020

ሀጢአቷን የምትፅፈዉ ሴት
አንዲት ሴት ነበረች ሀጢአቷን የምትፅፍ ልቧ በሀጢአት የሰከረ ለሀጢአትም ተገዚ የሆነች ይህች ሴት የተለያየ ሀጢአት የምትሰራ ናት፡፡
ትዘሙታለች፡ ትዋሻለች ፡ታማለች ትሰርቃለች ትገድላለች በአል ትሽራለች ትሰክራለች በትእቢት የተሞላች ሴት ናት ልብሷ ኃጢአት ነበር፡፡
ነገር ግን የምትሰራዉን ኃጢአቷን እፃፈች ታስቀምጥ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን የፃፈችዉን ኃጢአቷን ብታየዉ ስንክሳር አክሎ ተመለከተችዉ፡፡ ስንክሳር ማለት በ365 ቀኖች የሚዉሉ የቅዱሳንን ታሪክ ሰብስቦ የያዘ ትልቅ መፅሃፍ ነዉ፡፡የዚች ሴትም ኃጢአት ይህን አክሎ ነበር፡፡ አንዳቸዉ ደነገጠችና ኃጢአቷን ተሸክማ አባት ወዳለበት ወደ አንፆኪያ ሄደች ፡፡ አባ ባስልዮስን አገኘቻቸዉ፡፡"አባቴ በዚሀ ለዉ ኃጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለቻቸዉ፡፡ አባ ባስልስም ይፋቅልሽ አሏት ገልጣ ብታየዉ ሁሉም ተፍቆ አንዲት ኃጢአት ብቻ ቀርታ አየቻት፡፡ በጣም ከባድ ኃጢአት ነበረች ሲሰሯት የምትከብድ ሊነግሯት የምታሳፍር ነበረች፡፡ አባቴ ይችሳ አለቻቸዉ አባ ባስልዮስም ይችን ኃጢአትሽንሽ ማስረዝር የሚችል ልጀ ቅዱስ ኤፍሬም ነዉ ሂደሽ ለ እርሱ ንገሪዉ አሏት አበ ባስልዮሰም ይህን ያሏት ሀጢአቷን መፋቅ አቅቷቸዉ አይደለም የራሳቸዉ ክብር ከሚገለጥ የቅዱስ ኤፍሩም እንዲገለጥ ፈልገዉ ነዉ፡፡
ደግሞም ስትመላለስ ንስሀ እንዲሆናት ጭምርም ነዉ፡፡ እሷም አባ ባስልዮስ እንዳሏት ቅዱስ ኤፍሬም ወዳለበት ወደ ሶሪያ ሄደች፡፡ በባዶ እግሯ እንቅፋቱ አየመታተ እሾሁ እየወጋት እግሯ ሲደማ ልብሷን እቀደደች አየጠመጠመች ተጉዛ ከ ቅዱስ ኤፍሬም ደረሰች አባቴ በዚህ ያለዉ ኃጢአሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችዉ ቅዱስ ኤፍሬም ግን ይሄ ለኔ አይቻለኝም ለአባቴ ለአባ ባስልዮስ እንጅ አላት ቅዱስ ኤፍሬም ሀጢአቷን መደምሰስ አቅቶት አይደለም በፈሊጥ ቀኖና ሲሰጣት እንጅ ስትመላለስ ሀጢአቷ እንዲቀልላተም ነዉ፡፡ ሂደሽ ለአባ ባስልዮስ ንገሪአቸዉ እሳቸዉ ይደመስሱልሻል አሏት አግኝቸዉ አኮ አይሆንልኝም ብሎ ወዳንተ ልኮኛል ሳትል እሽ ብላ መንገድ ስትጀምር እንደቀድሞዉ በህይወት አታገኛቸዉም ሙተዉ ካህናት ሊቀብሯቸዉ ወደ ቤተክርስቲያን ይዘዋቸዉ ሲሄዱ ታገኘዋለች ሳትጠራጠሬ የተፃፈዉን ኃጢአትሽን ከአስክሬኑ ላይ ጣይዉ አሷም እሽ ብላ የቀኑ ሙቀት የሌሊቱ ብርድ እያሰቃያት ደረሰች፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ሙተዉ ካህናት ፍተሀት እየፈቱ አየች የእግዚአበሔር አገልጋይ ባስልዮስ ሆይ የባሪያህን ኃጢአት ደምስስልኝ ብላ ከአስክሬኑ ላይ ጣለቸዉ አስክሬኑመ ድምፅ አዉትቶ ኃጢአትሽ ተደምስሶልሻል አላት እሷም ገልጣ ብታይ ተደምስሶላታል ፡፡ አምላኳን አመሰገነች በደስታ ዘመረች ከዚህ በኋላ አለምን ንቃ ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች፡፡
እንደዚች ሰዉ ኃጢአቱን የሚያስታዉስ ማን ነዉ?
ወደካህን ሒዶ ንስሃ የገባስ ስንቱ ነዉ?
ስለሀጢአቱ በበርሀ የተንከራተተ ማን ይሆን?
የዚችን ሴት መጨለሻ ያሳመረ የኛንም መጨረሻ ያሳምርልን፡፡ሀጢአቷን የደመሰሰ የሁላችንንም ሀጢአት የደምስስልን፡፡
ምንጭ፡- መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

14/02/2020
12/02/2020

Address

Arba Minch
Addis Ababa
1234

Telephone

0946665466

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Atinafu Chafo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category