Ankuar

Ankuar We are a team of neutral observers - to provide you with core analysis of politics, culture and society in Ethiopia. www.ankuar.com

በኢትዮጵያ የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀቶች (ጥናታዊ ጽሁፍ)በጥቅምት 2021 ዩሮፒያን ኢንስቲትዩት ኦፍ ፒስ አስጠንቶ ባሳተመው ጽሁፍ የልዩ ኃይል አደረጃጀት በኢትዮጵያ እንዴት እና በምን ሁኔ...
08/04/2023

በኢትዮጵያ የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀቶች
(ጥናታዊ ጽሁፍ)

በጥቅምት 2021 ዩሮፒያን ኢንስቲትዩት ኦፍ ፒስ አስጠንቶ ባሳተመው ጽሁፍ የልዩ ኃይል አደረጃጀት በኢትዮጵያ እንዴት እና በምን ሁኔታ እንደተፈጠረ፣ የአደረጃጀቱን ሕጋዊ እና ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት አጠያያቂነት፣ በአደረጃጀቱ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ስለያዙት አቋም እና ስለነበሩት ክርክሮች፣ የክልል ልዩ ኃይሎች መጠን እና አቅም በተመለከተ፣ እንዲሁም የተለያዩ ጉዳዮችን በዝርዝር አስፍሯል። ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ልናጋራችሁ ወደድን።

እዚህ ያገኙታል፡ https://ankuar.com/ethiopia-regional-special-force-research/

የጀዋር መሐመድ ትንታኔያዊ ጽሁፍ በአማሪኛ - ቀጣዩ የትግል ምዕራፍበቅርቡ ጀዋር መሐመድ 76 ገጽ ያለው ሰፊ ትንታኔያዊ ጽሁፍ “Boqonnaa Qabsoo Itti Aanu” በሚል ርዕስ በኦሮም...
21/03/2023

የጀዋር መሐመድ ትንታኔያዊ ጽሁፍ በአማሪኛ - ቀጣዩ የትግል ምዕራፍ

በቅርቡ ጀዋር መሐመድ 76 ገጽ ያለው ሰፊ ትንታኔያዊ ጽሁፍ “Boqonnaa Qabsoo Itti Aanu” በሚል ርዕስ በኦሮምኛ አዘጋጅቶ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል። ሙሉውን ጽሁፍ በአማርኛ ለማግኘት ሊንኩን ይከተሉ።

https://ankuar.com/jawar-mohammed-next-chapter-of-the-struggle-amharic/

English version of Jawar’s Paper – The Next Chapter of the StruggleJawar Mohammed recently published a political analysi...
21/03/2023

English version of Jawar’s Paper – The Next Chapter of the Struggle

Jawar Mohammed recently published a political analysis on the past, present, and future Oromo Struggle and on Ethiopia’s political situation in over 70 pages of paper. The paper is originally written in Afan Oromo, entitled “Boqonnaa Qabsoo Itti Aanu”.

You can find the full English version, The Next Chapter of Struggle", with the link below.

https://ankuar.com/jawars-paper-in-english-the-next-chapter-of-the-struggle/

The Final and Signed Agreement of Cessation of Hostilities between the FDRE and the TPLFThe Federal Democratic Republic ...
04/11/2022

The Final and Signed Agreement of Cessation of Hostilities between the FDRE and the TPLF

The Federal Democratic Republic of Ethiopia and Tigray Peoples Liberation Front signed an agreement on 2nd of October 2022 to end the two-year war through a permanent cessation of hostilities. Please find the final, agreed, and signed agreement document using the link below:

https://ankuar.com/the-final-and-signed-agreement-between-the-fdre-and-the-tplf-on-cessation-of-hostilities/

Hostilities -Talk

A media in Ethiopia that provides major stories and analysis on politics, society and entertainment.

ከአመጿ ጀርባ«ከአመጿ ጀርባን ለዳሰሳ የመረጥኩት፤ በአብዛኛው በውስጣችን የያዝናቸውና ጮክ ብለን ለማውራት የማንደፍራቸውን ርዕሰ-ጉዳዮች በግልፅ ስለሚያነሳ፣ በግሌ እንደ ሀገር ለማደግ ራሳችን...
25/02/2022

ከአመጿ ጀርባ

«ከአመጿ ጀርባን ለዳሰሳ የመረጥኩት፤ በአብዛኛው በውስጣችን የያዝናቸውና ጮክ ብለን ለማውራት የማንደፍራቸውን ርዕሰ-ጉዳዮች በግልፅ ስለሚያነሳ፣ በግሌ እንደ ሀገር ለማደግ ራሳችንን መፈተሽና ምክንያታዊ የሆኑ ማህበራዊ ሂሶችን መለማመድ፣ መሻሻልና እንደ ግለሰብም ወደ ውስጥ መመልከት እንዳለብን ስለማምን ነው።» በማለት ዳሰሳዋን ትጀምራለች ማህደር አካሉ። የመጽሐፉ ደራሲ ኤደን ሀብታሙ ናት።

እድሉን አግኝታችሁ መጽሐፉን ያነበባችሁ መለስ ብላችሁ እንድታጤኑት፣ ያላነበባችሁ ደግሞ ያመለጣችሁን በጨረፍታ እንድትመለከቱና ለማንበብ እንድትቆርጡ ይህንን ግሩም ዳሰሳ ተጋብዛችኋል።

እነሆ፦ https://ankuar.com/keametswa-jerba/

#ከአመጿጀርባ

Mahder Akalu

A media in Ethiopia that provides major stories and analysis on politics, society and entertainment.

የጳጉሜ ቀናት ተንገላቱ፤ ስያሜው ዘላቂ ፋይዳ ቢኖረው! . . ላለፈው አንድ ዓመትና ከዚያም በላይ ሀገሪቱ የነበረችበት ሁኔታ ከማንም የተደበቀ አይደለም። ካቻምና የነበሩት የሰላም ቀን እና የ...
04/09/2021

የጳጉሜ ቀናት ተንገላቱ፤ ስያሜው ዘላቂ ፋይዳ ቢኖረው!
. . ላለፈው አንድ ዓመትና ከዚያም በላይ ሀገሪቱ የነበረችበት ሁኔታ ከማንም የተደበቀ አይደለም። ካቻምና የነበሩት የሰላም ቀን እና የብሔራዊ አንድነት ቀን ምን እያደረግን ስለዋልንባቸው ነው ዛሬ እዚህ ላይ የደረስነው? አምና የነበረው የይቅርታ ቀንስ ፋይዳው ከምን ደርሶ ነው በዚህ ጊዜ ላይ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን የተፈለገው?

እባክዎ ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡-
https://ankuar.com/pagume-days-designation-and-celebration/

#ጳጉሜ #ኢትዮጵያ

Appreciating what we have!This video presents the magnificent Suba Menagesha Forest with the breathtaking music "Hiwoteg...
28/08/2021

Appreciating what we have!

This video presents the magnificent Suba Menagesha Forest with the breathtaking music "Hiwotegna Lelit" by Girma Yifrashewa, featuring Michael Belayneh. Photographer: Gizaw Legesse

https://www.youtube.com/watch?v=F25KZXjkmck

This video presents the magnificent Suba Menagesha Forest with the breathtaking music "Hiwotegna Lelit" by Girma Yifrashewa, featuring Michael Belayneh.Photo...

የባሕላዊ ሀገር ግንዛቤው የኢንላይትመንት የማህበራዊ ውል እና የሉዓላዊነት እሳቤዎችን ሊተካ እንደሚችል ሄርደር ያስባል። መንግሥት አርቴፊሻል ፅንሰ-ሀሳብ ሲሆን፣ ሀገር ግን የተፈጥሯዊ እድገት...
17/08/2021

የባሕላዊ ሀገር ግንዛቤው የኢንላይትመንት የማህበራዊ ውል እና የሉዓላዊነት እሳቤዎችን ሊተካ እንደሚችል ሄርደር ያስባል። መንግሥት አርቴፊሻል ፅንሰ-ሀሳብ ሲሆን፣ ሀገር ግን የተፈጥሯዊ እድገት ውጤት ነበር። ይህ፣ ህብረተሰብን፣ በውስጡ ያሉት አካላት በሕብራዊ (harmonious) ዝምድና የተሳሰሩበት አንድነት (organic unity) አድርጎ የመመልከት ራዕይ ነው። ሄርደር ይህንን ሲል የህብረተሰብ አንድ ክፍል ከአጠቃላዩ ወይም ከመላው ያንሳል ማለቱ አይደለም፣ ወይም አንድ ግለሰብ ከአጠቃላዩ ማህበረሰብ ያነሰ መሆኑን አያመለክትም።

ዘርዘር ያለውን የዮኃን ጎትፍሬድ ሄርደር የፖለቲካ ጽንሰ-ሀሳብ በዚህ ሊንክ ማንበብ ይችላሉ፦
https://ankuar.com/johann-gottfried-herder/

A media in Ethiopia that provides major stories and analysis on politics, society and entertainment.

ለተሰንበት ግደይ - የፅናት ማማ!በቶክዮ ኦሎምፒክ የ10000ሜ ሴቶች ሩጫ። አየሩ ከፍተኛ ሙቀት ነበረው። በዚህ ወበቅ ሁሉንም በራሷ ፔስ እያስሮጠች ስንቱን እያረገፈች ሩጣለች - ለተሰንበት ...
07/08/2021

ለተሰንበት ግደይ - የፅናት ማማ!

በቶክዮ ኦሎምፒክ የ10000ሜ ሴቶች ሩጫ። አየሩ ከፍተኛ ሙቀት ነበረው። በዚህ ወበቅ ሁሉንም በራሷ ፔስ እያስሮጠች ስንቱን እያረገፈች ሩጣለች - ለተሰንበት ግደይ። ብዙዎቹ እያቋረጡ መውጣት ጀመሩ።

ከግማሽ በኋላ የአራት ሴቶች ውድድር ሆነ። ለተሰንበትን ተጣብቀው 5000ሜ ብር ሜዳሊያ ያጠለቀችው የኬንያዋ ኦብሪ፣ 5000ሜ ወርቅ እና 1500ሜ ነሃስ ያጠለቀችው የሆላንዷ ሲፋን ሀሰን ትንፋሽ ለትንፋሽ እየተማማጉ ይታገሏት ጀመር።

ይህ ሁሉ ሲሆን በአስገራሚ አቋም ርቀቷን ጠብቃ በማድፈጥ አራተኛ ሆና ስትከተል የነበረችውን የባህሬኗን ቃልኪዳን ገዛኽኝ የጠበቀ አልነበረም።

ሩጫው እየተገባደደ ሲመጣ ሙቀቱን እና የለተሰንበትን አመራር መቋቋም ያልቻለችው ኦብሪ ወደኋላ አፈገፈገች። ከዚያም ሩጫው በሦስቱ መካከል ሆነ - በኢትዮጵያዊዋ ለተሰንበት እና በትውልደ ኢትዮጵያዊያኖቹ ሲፋን እና ቃልኪዳን።

ባለፉት ቀናት ተደጋጋሚ ማጣሪያዎችን እና ፍፃሜ ውድድሮች ያደረገችውን ሲፋን ሀሰን ጭምር ማድከም እና ተስፋ ማስቆረጥ የሚቻለው በዚህ መልኩ እንደሆነ ለተሰንበት ያመነችበት ይመስላል። ግን አልተሳካም፤ ሲፋን ደብዛዛው ወላፈናዊ ንፋስ እንኳን እንዳይነካት በለተሰንበት ጀርባ ላይ ተጣብቃ መታገሏን ቀጠለች።

ለተሰንበት የምትችለውን ብታደርግም በመጨረሻው ዙር ሲፋን ታግላ ወጣች፤ ቃልኪዳን ተከተለች። ሲፋን ይባስ ተስፈነጠረች፤ ተሳካላት፤ በ10ሺም ወርቅ አጠለቀች። ቃልኪዳን ብር ሜዳሊያ ተቀዳጀች። ሙሉ ውድድሩን በአስገራሚ ብቃት የመራችው ለተሰንበት ሦስተኛ ወጣች።

ለተሰንበት እና ሲፋን ከውድድሩ በኋላ ድካማቸው ይታያል። የባህሬኗ ቃልኪዳን ግን ገና ለመሮጥ የምታሟሙቅ ትመስል ነበር።

25 አትሌቶች በተሳተፉበት በዚህ የቶክዮ ኦሎምፒክ 10000ሜ ሦስቱ ኢትዮጵያዊያንን (እነ ለተሰንበትን) ጨምሮ ስምንት ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወይም ከኢትዮጵያ ጋር የቆየ ቁርኝት ያላቸው አትሌቶች ይገኙበታል። እነዚህም የሆላንዷ ሲፈን፣ የባህሬኗ ቃልኪዳን፣ የስዊዲኗ ምዕራፍ ባህታ፣ የእስራኤሏ ሰላማዊት ተፈሪ እና የኤርትራዋ ዶልሺ ተስፉ ናቸው።

በዚህ ውድድር ሲፋን እና ቃልኪዳንን አለማድነቅ ባይቻልም፣ የለተሰንበትን አስደሳች እና አኩሪ ፅናት መላው ኢትዮጵያዊ ሲያስታውስ እና ሲገረምበት ይኖራል።

Picture copyright: Tokyo2020 Olympics, Japan Olympics Committee






አስገራሚ  ሜዳሊያ፡ ተወዳዳሪዎች ሜዳሊያዎችን ቆርጠው የተካፈሉበት የበርሊኑ ኦሎምፒክበ1936፣ በበርሊኑ የኦሎምፒክ ውድድር ሁለት ጃፓናዊያን አሎሎ ወርዋሪዎች እኩል ርቀት በመወርወራቸው 2ኛ ...
03/08/2021

አስገራሚ

ሜዳሊያ፡ ተወዳዳሪዎች ሜዳሊያዎችን ቆርጠው የተካፈሉበት የበርሊኑ ኦሎምፒክ

በ1936፣ በበርሊኑ የኦሎምፒክ ውድድር ሁለት ጃፓናዊያን አሎሎ ወርዋሪዎች እኩል ርቀት በመወርወራቸው 2ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ። ውጤታቸውን ለመለየት ውድድራቸውን እንዲቀጥሉ ቢጠበቅም፣ እነርሱ ግን አይሆንም አሉ። ይልቁንም ውጤታቸው ሳይለይ ሁለቱም የብር እና የነሃስ ሜዳሊያዎቹን ይዘው ወደ ሀገራቸው ለመሄድ ተስማሙ። እናሙ ሁለቱን ሜዳሊያዎች ሁለት-ሁለት ቦታ ቆርጠው ግማሽ-ብር እና ግማሽ-ነሃስ ሜዳሊያዎችን ተከፋፈሉ።

ምንጮች፦
Olympics.com
newsbytesapp.com
skysports.com
Wikipedia.org

አስገራሚ  ወጪ፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የቶክዮ ኦሎምፒክን ውድ አድርጎታልለቶክዮ ኦሎምፒክ ቀድሞ የተያዘው በጀት 12.6 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ሆኖም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ወጪው...
03/08/2021

አስገራሚ

ወጪ፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የቶክዮ ኦሎምፒክን ውድ አድርጎታል

ለቶክዮ ኦሎምፒክ ቀድሞ የተያዘው በጀት 12.6 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ሆኖም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ወጪው 22% በማደግ 15.4 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተሰምቷል። ሆኖም የጃፓን መንግሥት በሚያደርገው ኦዲት ወጪው ከዚህም እንደሚልቅ እየተነገረ ነው፤ እስከ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ተገምቷል። ለአንድ ዓመት መራዘሙና ለዝግጅት ክንውን የተገቡ ውሎች መሻሻል የነበረባቸው መሆኑ ወጪው ለመጨመሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተነግሯል።

ምንጮች፦
Olympics.com
newsbytesapp.com
skysports.com
Wikipedia.org

አስገራሚ  ታሪክ፦ የመጀመሪያው (ጥንታዊ) ኦሎምፒክ በ776 ቢ.ሲ. ተካሄደጥንታዊው ወይም የመጀመሪያው የኦሎምፒክ ውድድር የተካሄደው በ776 ቢ.ሲ. (ከክርስቶስ ልደት በፊት) ነበር። ውድድሩ...
03/08/2021

አስገራሚ

ታሪክ፦ የመጀመሪያው (ጥንታዊ) ኦሎምፒክ በ776 ቢ.ሲ. ተካሄደ

ጥንታዊው ወይም የመጀመሪያው የኦሎምፒክ ውድድር የተካሄደው በ776 ቢ.ሲ. (ከክርስቶስ ልደት በፊት) ነበር። ውድድሩ የተጀመረው ታላቁን የግሪክ አምላክ፣ ዚዮስን ለማወደስ ዓላማ ሲሆን፣ ትግል፣ ቦክስ፣ ምድር ዝላይ፣ ጦር ውርወራ፣ ዲስከስ፣ እና የሰረገላ እስሽቅድድም የመሳሰሉትን ጨዋታዎች ያካተተ ነበር። ይህ ጥንታዊው ኦሎምፒክ ለወራት የሚቆይ ሕዝባዊ ፌስቲቫል ነው። የመጀመሪያው የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ኤሊስ በምትባል ከተማ ምግብ አብሳይ የነበረ ኮሮበስ የተባለ ሰው ነበር። ዘመናዊው ኦሎምፒክ እ.አ.አ ከ1896 ጀምሮ (በ1916 በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እና በ2020 በኮቪድ-19 ምክንያት ከመዝለሉ በስተቀር) በየ4 ዓመቱ እየተካሄደ ይገኛል።

ምንጮች፦
Olympics.com
newsbytesapp.com
skysports.com
Wikipedia.org

አስገራሚ  ክብረ-ወሰን: ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር የቆየ ክብረ-ወሰንየኦሎምፒክ ሪከርዶች ወይም ክብረ-ወሰኖች የሆነ ጊዜ መሰበራቸው እንደማይቀር ይጠበቃል፤ እስከዛሬም በብዙ ውድድሮች በተደጋጋሚ ...
03/08/2021

አስገራሚ

ክብረ-ወሰን: ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር የቆየ ክብረ-ወሰን

የኦሎምፒክ ሪከርዶች ወይም ክብረ-ወሰኖች የሆነ ጊዜ መሰበራቸው እንደማይቀር ይጠበቃል፤ እስከዛሬም በብዙ ውድድሮች በተደጋጋሚ ተሰብረዋል። እስከዛሬ ሐምሌ 27 ድረስ በቶክዮ ኦሎምፒክ 12 ሪከርዶች ተሰብረዋል። ሆኖም ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር የቆየው የኦሎምፒክ ክብረ-ወሰን አሜሪካዊው ቦብ ቤሞን በ1968 የሜክሲኮ ኦሎምፒክ በምድር ዝላይ ውድድር የተመዘገበው ክብረ-ወሰን ነው። 8.90 ሜትር የተመዘገበው የቤሞን ዝላይ ለ23 ዓመታት ሳይሰበር ቆይቷል።

ምንጮች፦
Olympics.com
newsbytesapp.com
skysports.com
Wikipedia.org

03/08/2021

🏃‍♂️🏃🏃‍♀️
1500ሜ ወንዶች የመጀመሪያ ማጣሪያ ሁለት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አልፈዋል፡፡

ዛሬ ሌሊት በተካሄደው የ1500ሜ ወንዶች የመጀመሪያ ማጣሪያ ላይ ሳሙኤል ዘለቀ፣ ሳሙኤል ተፈራ፣ እና ታደሰ ለሚ ነበሩ በተለያየ ምድብ የተወዳደሩት፡፡

ታደሰ ለሚ እና ሳሙኤል ዘለቀ 2ኛ እና 5ኛ በመውጣት ወደሚቀጥለው ማጣሪያ አልፈዋል፡፡

ጉዳፍ ፀጋዬ ለኢትዮጵያ ሦስተኛውን ሜዳሊያ አስገኝታለችበቶክዮ ኦሎምፒክ በ5000ሜ የሴቶች ፍፃሜ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ሦስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አግኝታለች።በውድድሪ ሲፋን ...
02/08/2021

ጉዳፍ ፀጋዬ ለኢትዮጵያ ሦስተኛውን ሜዳሊያ አስገኝታለች

በቶክዮ ኦሎምፒክ በ5000ሜ የሴቶች ፍፃሜ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ሦስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

በውድድሪ ሲፋን ሀሰን አንደኛ፣ የኬንያዋ ሯጭ ኦብሪ ሁለተኛ ወተዋል።

የጉዳፍ ውጤት ለሀገሯ ሦስተኛውን ሜዳሊያ ያስገኘ ሲሆን፣ በሜዳሊያ ዝርዝር ከ74 የዓለም ሀገራት ኢትዮጵያን 39ኛ ላይ እንድትገኝ አድርጓታል።

ለሜቻ ግርማ ሁለተኛውን ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝቷልበወንዶች 3000ሜ መሰናክል ፍፃሜ ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።
02/08/2021

ለሜቻ ግርማ ሁለተኛውን ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል

በወንዶች 3000ሜ መሰናክል ፍፃሜ ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ኢትዮጵያ ዛሬ ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን ትጠብቃለች!በቶክዮ ኦሎምፒክ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት በወንዶች 10000ሜ ሩጫ የመጀመሪያዋን የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀችው ኢትዮጵያ፣ ዛሬ ከጥቂት ቆይታ በኋ...
02/08/2021

ኢትዮጵያ ዛሬ ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን ትጠብቃለች!

በቶክዮ ኦሎምፒክ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት በወንዶች 10000ሜ ሩጫ የመጀመሪያዋን የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀችው ኢትዮጵያ፣ ዛሬ ከጥቂት ቆይታ በኋላ በሚደረጉ ሁለት ውድድሮች ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን ትጠብቃለች።

በወንዶች 3000ሜ መሰናክል ፍፃሜ ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ 9:15 ሰዓት ላይ ይወዳደራሉ።

በሴቶች 5000ሜ ለዛሬው ፍፃሜ ያለፉት ሰንበሬ ተፈሪ፣ እጅጋየሁ ታዬ፣ እና ጉዳፍ ፀጋዬ 9:40 ሰዓት ላይ ይወዳደራሉ።

መልካም እድል!

ለምለም ኃይሉ እና ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሔር ለግማሽ ፍፃሜ አለፉዛሬ ሌሊት በተካሄደው የቶክዮ ኦሎምፒክ 1500ሜ የሴቶች ማጣሪያ ለምለም ኃይሉ እና ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሔር ለግማሽ ፍፃሜ አል...
02/08/2021

ለምለም ኃይሉ እና ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሔር ለግማሽ ፍፃሜ አለፉ

ዛሬ ሌሊት በተካሄደው የቶክዮ ኦሎምፒክ 1500ሜ የሴቶች ማጣሪያ ለምለም ኃይሉ እና ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሔር ለግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል። ሁለቱም በየምድባቸው አምስተኛ በመውጣት ነበር ያለፉት።

ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ትውልደ-ኢትዮጵያዊዋ ሲፋን ሀሰን ወድድሩ ላይ ተደናቅፋ ብትወድቅም እንደገና ተነስታ ማጣሪያውን አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች።

ሀብታም አለሙ ለ800ሜ ፍፃሜ አለፈች!ሀብታም አለሙ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሴቶች 800ሜ ሩጫ የመጀመሪያውን ማጣሪያ ትናንት ተወዳድራ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፏ ይታወቃል።አሁን በተካሄደው ግማሽ ፍፃሜ...
31/07/2021

ሀብታም አለሙ ለ800ሜ ፍፃሜ አለፈች!

ሀብታም አለሙ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሴቶች 800ሜ ሩጫ የመጀመሪያውን ማጣሪያ ትናንት ተወዳድራ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፏ ይታወቃል።

አሁን በተካሄደው ግማሽ ፍፃሜ ውድድ ላይ በ1:58.40 በመሮጥ ሁለተኛ የወጣች ሲሆን ለፍፃሜው በቀጥታ አልፋለች።

1 and counting . . . Solomon Barega won Gold in 10000m at Tokyo2020
30/07/2021

1 and counting . . .
Solomon Barega won Gold in 10000m at Tokyo2020

ሰለሞን ባረጋ የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አጠለቀ

በቶክዮ ኦሎምፒክ በወንዶች 10000ሜ ፍፃሜ አትሌት ሰለሞን ባረጋ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አለን!

ሰለሞን ባረጋ የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አጠለቀበቶክዮ ኦሎምፒክ በወንዶች 10000ሜ ፍፃሜ አትሌት ሰለሞን ባረጋ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።ኢትዮጵ...
30/07/2021

ሰለሞን ባረጋ የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አጠለቀ

በቶክዮ ኦሎምፒክ በወንዶች 10000ሜ ፍፃሜ አትሌት ሰለሞን ባረጋ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አለን!

በቶክዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ አትሌቶች ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ሰለሞን ባረጋ፣ እና በሪሁ አረጋዊ በ10000ሜ ፍፃሜ እየተወዳደሩ ይገኛሉ።
30/07/2021

በቶክዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ አትሌቶች ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ሰለሞን ባረጋ፣ እና በሪሁ አረጋዊ በ10000ሜ ፍፃሜ እየተወዳደሩ ይገኛሉ።

ሰንበሬ ተፈሪ፣ እጅጋየሁ ታዬ፣ እና ጉዳፍ ፀጋዬ በ5000ሜ የሴቶች ሩጫ በቶክዮ ኦሎምፒክ ማጣሪያውን አልፈው ለፍፃሜ ቀርበዋል።
30/07/2021

ሰንበሬ ተፈሪ፣ እጅጋየሁ ታዬ፣ እና ጉዳፍ ፀጋዬ በ5000ሜ የሴቶች ሩጫ በቶክዮ ኦሎምፒክ ማጣሪያውን አልፈው ለፍፃሜ ቀርበዋል።

በቶክዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ አትሌቶች ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ በ3000ሜ የወንዶች መሰናክል፣ እንዲሁም ሀብታም አለሙ በ800ሜ የሴቶች ሩጫ ማጣሪያውን አልፈዋል።
30/07/2021

በቶክዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ አትሌቶች ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ በ3000ሜ የወንዶች መሰናክል፣ እንዲሁም ሀብታም አለሙ በ800ሜ የሴቶች ሩጫ ማጣሪያውን አልፈዋል።

በነገው እለት ሀገራችን የምትሳተፍባቸው የኦሎምፒክ ውድድሮች፦3000ሜ መሰናክል ማጣሪያ (ወንድ)800ሜ ማጣሪያ (ሴት)5000ሜ ማጣሪያ (ሴት)50ሜ ዋና ማጣሪያ (ወንድ)10000ሜ ፍፃሜ (ወን...
29/07/2021

በነገው እለት ሀገራችን የምትሳተፍባቸው የኦሎምፒክ ውድድሮች፦

3000ሜ መሰናክል ማጣሪያ (ወንድ)
800ሜ ማጣሪያ (ሴት)
5000ሜ ማጣሪያ (ሴት)
50ሜ ዋና ማጣሪያ (ወንድ)
10000ሜ ፍፃሜ (ወንድ)

ሙሉ ፕሮግራሙ እና በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በምስሎቹ ላይ ተያይዟል፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን አትሌቶች እነማን ናቸው?ሐምሌ 16 ቀን 2013 የቶኪዮ ኮሊምፒክ በድምቀት ይጀመራል። የኢትዮጵያ አትሌቶች ቀደም ሲል ሽኝት እንደተደረገ...
22/07/2021

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን አትሌቶች እነማን ናቸው?

ሐምሌ 16 ቀን 2013 የቶኪዮ ኮሊምፒክ በድምቀት ይጀመራል። የኢትዮጵያ አትሌቶች ቀደም ሲል ሽኝት እንደተደረገላቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ አትሌቶች በኦሊምፒኩ በተለይም በመካከለኛ እና በረዥም ረቀት የሩጫ ውድድሮች ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጣቸው ተወዳዳሪዎች መካከል ናቸው።

BBC News Amharic በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚጠበቁ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የአፍሪካ አትሌቶችን በዝርዝር አስተዋውቋል። ለበለጠ ንባብ ሊንኩን ይከተሉ፦

https://www.bbc.com/amharic/news-57911750

የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ፡ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ተወዳዳሪዎች እነማን ናቸው?

Addis Standard Resumed: via a loophole in the law or an intended protection of freedom?Ethiopian Media Authority - ኢመብባ ...
22/07/2021

Addis Standard Resumed: via a loophole in the law or an intended protection of freedom?

Ethiopian Media Authority - ኢመብባ (EMA) temporarily suspended Addis Standard a week ago on the 15th of July for the reason EMA described “… that the Media has been a platform to advance the terrorist group’s agenda, to the extent of refusing to abide by the decisions of the House of People’s Representative: legitimizing a terrorist group as a ‘Defence Force’”.
. . Addis Standard is not a licensed broadcaster, but a registered and recognized online media based on Article 6 (3) of the proclamation. How come the Authority mandated to recognize and provide a registration certificate for online media is not provided with the power to un-recognize or suspend and/or revoke the registration certificate? Is it a loophole in the law? Or is it a deliberate omission in order to safeguard freedom of expression as indicated under Article 22 (1)? . . .

Please read the full article, written by Gizaw Legesse:
https://ankuar.com/addis-standard-resumed-via-a-loophole-in-the-law-or-an-intended-protection-of-freedom/

ምርጫ በአማራ ክልል | ተወዳዳሪ ፓርቲዎች እና የእጩዎቻቸው ብዛትበአማራ ክልል ለክልል ምክር ቤት 18፣ ለፌደራሉ ፓርላማ 17 ፓርቲዎች ለመወዳደር እጮዎቻቸውን አቅርበዋል። የሚከተሉት ምስሎች...
17/06/2021

ምርጫ በአማራ ክልል | ተወዳዳሪ ፓርቲዎች እና የእጩዎቻቸው ብዛት

በአማራ ክልል ለክልል ምክር ቤት 18፣ ለፌደራሉ ፓርላማ 17 ፓርቲዎች ለመወዳደር እጮዎቻቸውን አቅርበዋል። የሚከተሉት ምስሎች በክልሉ ለምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎችን እና የእጩዎቻቸውን ሁኔታ ያሳያሉ።



(ግዛው ለገሠ አሰናድቶ እንዳጋራው)

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ankuar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ankuar:

Videos

Share

Category

Nearby media companies