Ethiopia Today News

Ethiopia Today News Welcome to Ethiopia Today News
Follow us on You Tube
https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJw

ዲሽቃ በመስራት ወራሪ ጠላትን ለማጥፋት በፈጠራ ስራ የታገዘው የጠለምት ወጣቶች ተጋድሎ *********************************አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አ...
15/12/2021

ዲሽቃ በመስራት ወራሪ ጠላትን ለማጥፋት በፈጠራ ስራ የታገዘው የጠለምት ወጣቶች ተጋድሎ

*********************************
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ዲሽቃ የተሰኘውን የጦር መሳሪያ በመስራት በፈጠራ ስራ የታገዙት የጠለምት ወጣቶች ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተተጋድ ነው የፈጸሙት፡ አሸባሪው እና ወራሪው የህወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ላይ ለመስማት የሚዘገንን ሰብዓዊ እና ቁሳቂ ጉዳት አድርሷል፡፡ አሸበሪ ቡድኑን ለአንዴ እና…

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

UK ከአዲሱ ኦሚክሮን የኮቪድ ተህዋሲ ዝርያ ጋር በተያያዘ በ11 የአፍሪካ አገራት ላይ ጥላ የነበረውን የጉዞ ዕቀባ አንስታለች። *********************************የጉዞ እቀ...
15/12/2021

UK ከአዲሱ ኦሚክሮን የኮቪድ ተህዋሲ ዝርያ ጋር በተያያዘ በ11 የአፍሪካ አገራት ላይ ጥላ የነበረውን የጉዞ ዕቀባ አንስታለች።

*********************************
የጉዞ እቀባ የተነሳላቸው ፦
- አንጎላ፣
- ቦትስዋና፣
- ኢስዋቲኒ፣
- ሌሴቶ፣
- ማላዊ፣
- ሞዛምቢክ፣
- ናሚቢያ፣
- ናይጄሪያ፣
- ደቡብ አፍሪካ፣
- ዛምቢያ እና ዚምባብዌ ናቸው፡፡

አገራቱ በUK የጎዞ ዕቀባ የተጣለባቸው ባለፈው ኅዳር ወር የኦሚክሮን ተህዋሲ ዝርያ ከዚሁ ደቡባዊ አፍሪካ አካባቢ መገኘቱን ተከትሎ ነበር፡፡

የUK የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሳጂድ ጃቪድ ፥ ዕቀባውን ማንሳት ያስፈለገው ተህዋሲው አሁን በስፋት በሌሎች ቦታዎችም መሰራጨቱ ስለተረጋገጠ በነዚህ አገራት ላይ ጫና አድርጎ መቆየቱ ትርጉም ስለሌለው ነው ብለዋል።

ለወረርሽኝ ተጋላጭ አደገኛ አካባቢ በሚል ከተዘረዘሩ አገራት ወደ UK የሚገቡ ተጓዦች ለ10 ቀናት ራሳቸውን ለይተው መንግሥት ባዘጋጃቸው ሆቴሎች መቆየት ይኖባቸዋል፡፡

ወጪውን የሚችሉትም ተጓዦቹ እንደሚሆኑ የUK ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ያስነበበው ቢቢሲ ነው።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

የሽብር ቡድኑ ህወሓት በኮምቦልቻ ከተማ ከሚገኙ ፋብሪካዎች ምርቶችና ግብዓቶችን ዘርፏል *********************************አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ...
14/12/2021

የሽብር ቡድኑ ህወሓት በኮምቦልቻ ከተማ ከሚገኙ ፋብሪካዎች ምርቶችና ግብዓቶችን ዘርፏል
*********************************
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ ህወሓት በኮምቦልቻ ከተማ ከሚገኙ ፋብሪካዎች ምርቶችንና ግብዓቶችን መዝረፉ ተገለፀ፡፡ የጋዜጠኞች ቡድን በኮምቦልቻ ከተማ በሽብር ቡድኑ የወደሙና የተዘረፉ ፋብሪካዎችን ጎብኝቷል። በኮምቦልቻ ከተማ 200 የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት አልሚዎች ሀብታቸውን ማፍሰሳቸው ተገልጿል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም 37 የሚሆኑት ፋብሪካዎች ምርት ማምረትና ወደ ውጭ መላክ መጀመራቸውን የከተማው የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት…

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤትን አንዳንድ ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ እየተጠቀሙበት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። *************...
14/12/2021

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤትን አንዳንድ ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ እየተጠቀሙበት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

*********************************
ይህ ሁኔታ እጅግ እንዳሳዘነውም ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈፅመዋል በተባሉ ጥሰቶች ላይ በጋራ ጥናትና ምርመራ አድርገው የጋራ ሪፖርት ማውጣታቸውን መግለጫው አስታውሷል።

መንግስት ይህ የድርጅቶቹ የጋራ ሪፖርት ውጤትን ተቀብሎ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ግብረሃይል አቋቁሞ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

ይህ በሆነበት ሁኔታ አንዳንድ የUN የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ በመያዝና ይህንንም አጀንዳቸውን በምክር ቤቱ በኩል ለመፈፀም ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ልዩ ስብሰባ እንዲያደርግ በመጥራት ላይ መሆናቸውን አንስቷል።

ይህ ሁኔታ የኢትዮጵያን መንግስት በእጅጉ እንዳሳዘነው ነው ያስታወቀው።

ይልቁንም ም/ ቤቱ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች የፈፀማቸውን እጅግ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አጀንዳ አድርጎ ሊወያይና ሊያወግዘው በተገባ ነበር ብሏል።

የምክር ቤቱ አባል ሀገራት ይህንን የተወሰኑ ሀገራትን የፖለቲካ ፍላጎት ያነገበን ልዩ ስብሰባ እና ውጤቱን በጥብቅ እንዲቃወሙ ሚኒስቴሩ በአጽንኦት ጠይቋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም አቀፉ ህግ መሰረት ሰብዓዊ መብቶችን ለማክበር፤ ለማስከበርና ለማሟላት ያለውን ቁርጠኝነት ለሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት አባላትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዳግም ለማረጋገጥ ይወዳል ሲል አስገንዝቧል።

ምንጭ፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር/ኤፍቢሲ

ይህ ሁኔታ እጅግ እንዳሳዘነውም ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈፅመዋል በተባሉ ጥሰቶች ላይ በጋራ ጥናትና ምርመራ አድርገው የጋራ ሪፖርት ማውጣታቸውን መግለጫው አስታውሷል።

መንግስት ይህ የድርጅቶቹ የጋራ ሪፖርት ውጤትን ተቀብሎ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ግብረሃይል አቋቁሞ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

ይህ በሆነበት ሁኔታ አንዳንድ የUN የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ በመያዝና ይህንንም አጀንዳቸውን በምክር ቤቱ በኩል ለመፈፀም ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ልዩ ስብሰባ እንዲያደርግ በመጥራት ላይ መሆናቸውን አንስቷል።

ይህ ሁኔታ የኢትዮጵያን መንግስት በእጅጉ እንዳሳዘነው ነው ያስታወቀው።

ይልቁንም ም/ ቤቱ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች የፈፀማቸውን እጅግ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አጀንዳ አድርጎ ሊወያይና ሊያወግዘው በተገባ ነበር ብሏል።

የምክር ቤቱ አባል ሀገራት ይህንን የተወሰኑ ሀገራትን የፖለቲካ ፍላጎት ያነገበን ልዩ ስብሰባ እና ውጤቱን በጥብቅ እንዲቃወሙ ሚኒስቴሩ በአጽንኦት ጠይቋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም አቀፉ ህግ መሰረት ሰብዓዊ መብቶችን ለማክበር፤ ለማስከበርና ለማሟላት ያለውን ቁርጠኝነት ለሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት አባላትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዳግም ለማረጋገጥ ይወዳል ሲል አስገንዝቧል።

ምንጭ፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር/ኤፍቢሲ

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

በተለያዩ መፅሄቶች እኔን በተመለከተ የወጡት ጽሑፎች የተሳሳቱ ናቸው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ********************************* Jeune Afrique በተባለው የፈረን...
23/11/2021

በተለያዩ መፅሄቶች እኔን በተመለከተ የወጡት ጽሑፎች የተሳሳቱ ናቸው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
*********************************
Jeune Afrique በተባለው የፈረንሳይኛ መጽሔትና የእንግሊዝኛ ትርጉሙ The Africa Report ላይ እኔን በተመለከተ የወጡት ጽሑፎች የተሳሳቱ ናቸው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለፁ፡፡ ፕሬዚዳንቷ እኔን የተመለከቱ ጽሑፎች በመፅሄቶቹ መውጣታቸውን ተመልክቻለሁ፤ ከጋዜጠኛው ጋር ተገናኝቼ አላውቅም ነው ያሉት :: ፕሬዚዳንቷ እሳቸውን በተመለከተ ጂዩን አፍሪክና ዘ አፍሪካ ሪፖርት በተሰኘ…

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

በግንባር መሰለፍን ጨምሮ ለሕልውና ዘመቻው የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ********************************* "በግንባር መሰለፍን ጨምሮ ለሕልውና ዘመቻው የሚጠበቅብ...
23/11/2021

በግንባር መሰለፍን ጨምሮ ለሕልውና ዘመቻው የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ
*********************************
"በግንባር መሰለፍን ጨምሮ ለሕልውና ዘመቻው የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ" ሲል አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተናገረ፡፡
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ በኢትዮጵያ የተደቀነው አደጋ አፍሪካን የማንበርከክ ዓላማ ጭምር ያነገበ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ሙከራ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምልክት መሆኗን የገለጸው ኃይሌ፤ ኢትዮጵያን በማንበርከክ የጥቁር ሕዝቦችን አኩሪ ታሪክ ለመቀማት የተቀናጀ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግሯል።
ከዚህ አኳያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ክብር ወደ ግንባር መዝመታቸው አገሩን ከሚወድ መሪ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእርሳቸውን ፈለግ እንዲከተል ጥሪ አቅርቧል።
መላ አፍሪካዊያን ትግሉ የሁሉም ጥቁር ሕዝቦች መሆኑን በመገንዘብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርቧል፡፡
"ኢትዮጵያን ብለን ተሸንፈን አናውቅም፤ ኢትዮጵያ ሁሌም አሸናፊ ናት" ሲል ነው አትሌት ኃይሌ የተናገረው።
በአንድ ወቅት የጎበኛት የቱሪስት መናኸሪያ የነበረችውን የሶሪያዋ አሌፖ ከተማ በምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት ምክንያት ወደ ፍርስራሽነት መቀየሯን ጠቅሷል።
"በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን በአገራችን ላይ ይህን መፍቀድ የለብንም" ያለው አትሌት ኃይሌ፤ "ከዚህ አንጻር ከደጀንነት ባሻገር በግንባር በመሰለፍ ጭምር አገሬ በምትፈልገኝ ቦታ ለማገልግል ዝግጁ ነኝ" ብሏል፡፡
የአሁኑ ትውልድ አባቶቹ አድዋ ላይ የሰጡትን ነጻነት አሳልፎ መስጠት እንደሌለበት ገልጾ፤ በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ተነስተዋል፤ ማንም ሊያቆማቸው አይችልም ነው ያለው፡፡
ይህም ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ ለዓለም ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡
ኢትዮጵያዊያን በግንባር ከመዝመት ባሻገር በደጀንነትም በንቃት መሳተፍ እንደሚጠበቅባቸውም አትሌት ኃይሌ አስገንዝቧል።
በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ከዚህ ቀደም ከሚሰሩት በእጥፍ በማከናወን በጦርነቱ የጠፋውን ሃብት መተካት አለባቸው ነው ያለው፡፡
"የዕለት ተዕለት ተግባራችን አሸባሪው ህወሓት ያወደመውን ሃብትና ለወደፊት ለመልማት ያለንን ውጥን ታሳቢ ያደረግ መሆን አለበት" ሲል ገልጿል።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስራ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ፀድቋል። *********************************የዞን መዋቅሮች ደግሞ የራሳቸውን ቋንቋ እንደሚ...
23/11/2021

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስራ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

*********************************
የዞን መዋቅሮች ደግሞ የራሳቸውን ቋንቋ እንደሚገለገሉ ተገልጿል።

የስልጣን እርከን ፍትሃዊነትን በተመለከተ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ፣ አፈጉባኤየክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳትና የብሄረሰብ ምክር ቤት አፈጉባኤ በአንድ ጊዜ ከተመሳሳይ ብሄር እንዳይሆኑ ተቀምጧል።

የስልጣን ገደብም የተቀመጠ ሲሆን÷ በተለያየ ምክነያት ከጊዜያቸው ቀድሞ ሊለቁ መቻላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ረጅም ጊዜ ቢቆዩ ከ10 ዓመት እንዳይበልጥ ተመላክቷል።

የብዝሓ ማዕከል ወይንም ዋና ከተማ እንዲኖርም ተደንግጓል፣ የትኞቹ ከተሞች እንደሚሆኑ በዝርዝር ህግ በም/ ቤት እንዲወሰንም በህገ መንግስቱ መጠቀሱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመስርቷል። *********************************11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ህገ መንግስትም በምክር...
23/11/2021

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመስርቷል።
*********************************
11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ህገ መንግስትም በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

የምክር ቤቱ አባላትም ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

ምንጭ፦ የዳውሮ ዞን የመን/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

የአብኑ አመራር ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር አብረው እንደሚዘምቱ አሳወቁ። *********************************የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መከላከያን በግንባር ሆነው ለ...
23/11/2021

የአብኑ አመራር ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር አብረው እንደሚዘምቱ አሳወቁ።
*********************************
የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መከላከያን በግንባር ሆነው ለመምራት ከነገ ጀምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እንደሚዘምቱ ካሳወቁ በኃላ የአብን አመራር እና የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚዘምቱ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ፥ " ለአገር አንድነትና ለሕዝብ ደኅንነት የምንሰስተው ሕይወት የለምና እኛም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዘምታለን። ሕዝቤ ሆይ ተከተል " ሲሉ ነው በገፃቸው ላይ ያሰፈሩት።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

ባይደን ወደ ፕሬዜዳንት ስልጣናቸው ተመለሱ። *********************************ለ85 ደቂቃዎች ያህል በህክምና ክትትል ምክንያት የአሜሪካ ፕሬዜዳንትነት ስልጣናቸውን ለምክትላ...
20/11/2021

ባይደን ወደ ፕሬዜዳንት ስልጣናቸው ተመለሱ።
*********************************
ለ85 ደቂቃዎች ያህል በህክምና ክትትል ምክንያት የአሜሪካ ፕሬዜዳንትነት ስልጣናቸውን ለምክትላቸው ካማላ ሃሪስ አስረክበው የነበሩት የ79 ዓመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ፕሬዝዳንትነት መንበራቸው ተመልሰዋል።

ትላንት ካማላ ሐሪስ በአሜሪካ ታሪክ ለ85 ደቂቃዎች አገሪቱን በመምራት የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል። በተጨማሪ የመጀመሪያዋ ጥቁር ደቡብ ኤስያዊት ሴት ፕሬዜዳንትም ሆነዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሕክምና ላይ በነበሩበት ጊዜ ሐሪስ ከዋይት ሐውስ የምሥራቅ ክንፍ ካለው ቢሯቸው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነበር።

የጆ ባይደን ሐኪም ፕሬዝዳንቱ ደህና እንደሆኑ እና ወደ ሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

የጆ ባይደን ሐኪም ኬቨን ኦኮነር ፤ ፕሬዜዳንቱ ጤናማና ጠንካራ ናቸው ያሉ ሲሆን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ይችላሉ ብለዋል።

ባይደን ከሆስፒታል ወደ ዋይት ሐውስ ሲመለሱ "ጥሩ ስሜት ይሰማኛል" ብለው መናጋረቸውን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

ከሀሰተኛ መረጃ ተጠንቀቁ  *********************************ሰሞኑን አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ተክለኃይማኖት ቤ/ክርስቲያን ውስጥ  በአስክሬን ሳጥን ተደርጎ የጦር መሳሪያ...
16/11/2021

ከሀሰተኛ መረጃ ተጠንቀቁ
*********************************
ሰሞኑን አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ተክለኃይማኖት ቤ/ክርስቲያን ውስጥ በአስክሬን ሳጥን ተደርጎ የጦር መሳሪያ ተቀብሮ ተያዘ በሚል በተለየዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ወሬ ትክክለኛ መረጃ እንዳልሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ከልደታ ክ/ከተማ በተገኘው መረጃ መሰረት ግለሰቡ ከኢትዮጲያ ውጭ በመሞቱ ምክንያት ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሟቹን የሚያውቁት ነዋሪዎች አስፈላጊውን ህጋዊ ሂደት ተከትለው ከውጭ እንዲመጣ በማድረግ አሰክሬኑ በተክለ ሐይማኖት ቤ/ክርስቲያን እንዲያርፍ አደርገዋል፡፡

ቀብሩ ሲፈፀም ጥቂት ሰዎች በተገኙበት መሆኑና የአስክሬን ሳጥኑ ከመደበኛውና ከሚታወቀው አይነት ውጪ መሆኑ ያጠራጠራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለፖሊስ መረጃ ሰጥተዋል፡፡

ፖሊስ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ኮሚቴ አዋቅሮና ከቤተ-ክርስቲያኗ አባቶች ጋር በመሆን ፍተሻ በማድረግ በተቀበረው የአስክሬን ሳጥን የሰው አስክሬን እንጂ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ልተገኘ መሆኑን ተረጋግጧል፡፡

ፖሊስ ባስተላለፈው መልዕክት ማነኛውንም አጠራጣሪ ነገሮች ሲታዩ መረጃውን ለፀጥታ አካላት የማድረሱ ተግባር የሚደነቅና ሊበረታታ የሚገባው ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን ህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛ ቦታ የማግኘት ባህሉን ሊያጎለብት ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የወጣ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መመሪያመመሪያ ቁጥር 2 /2014 *********************************በሀገራችን ዘመናዊ የመታወቂያ...
15/11/2021

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የወጣ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መመሪያ
መመሪያ ቁጥር 2 /2014
*********************************
በሀገራችን ዘመናዊ የመታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት ያልተዘረጋ በመሆኑ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት መደበኛውን የመታወቂያ አሰጣጥ ስርዓትን ለማስቀጠል አስቸጋሪ በመሆኑ መደበኛውን የመታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት ለጊዜው በማገድ ጊዜያዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል የሚገኙ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ዜጎች በመደበኛው የመታወቂያ አሰጣጥ ሂደት መታወቂያ ያላገኙ በመሆኑ ለነዚህ ዜጎች ጊዜያዊ መታወቂያ በመስጠት ሰላማዊውን ህብረተሰብ ከፀረ-ሰላም ቡድኖች ለመለየት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሆኖ በመገኘቱ፣
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንቀፅ 6(6) ላይ ለመታወቂያነት የሚያገለግሉ ሰነዶች የሌለው ሰው ይህን ጉዳይ በተመለከተ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ ዝርዝር የአፈፃጸም መመሪያ ባወጣ በሁለት ሳምንት ውስጥ በአቅራቢያው በሚገኝ የቀበሌ፣ የወረዳ የፀጥታ እና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ወይም ፖሊስ ጣቢያ በመመዝገብ ጊዜያዊ የመታወቂያ ወረቀት የመያዝ ግዴታ እንዳለበት የተደነገገ በመሆኑና ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የሕግ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣
በሃገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል በወጣ አዋጅ ቁጥር 5/2014 አንቀፅ 10/1/ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌዎች
1. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መመሪያ ቁጥር 2/2014" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፣
2. ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-
1) አዋጅ ማለት በሃገር ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ነው፣
2) ጊዜያዊ መታወቂያ ማለት በዚህ መመሪያ መሰረት የሚሰጥ መታወቂያ ነው፣
3) ክልል ማለት በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 47 መሰረት የተቋቋመ ክልል ሲሆን ለዚህ መመሪያ ዓላማ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ያካትታል፤
4) በአዋጁ ትርጉም የተሰጣቸው ቃላትና ሀረጎች ለዚህ መመሪያም ተፈፃሚነት አላቸው፡፡
3. የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ በየትኛውም የኢትዮጵያ ከተማ ላይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡
ክፍል ሁለት
ጊዜያዊ መታወቂያ እንዲወስዱ የማይገደዱ ሰዎች እና ስለ ጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት
4. ጠቅላላ
1) የነዋሪነት መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሰነድ ያለው ሰው ጊዜያዊ መታወቂያ እንዲያወጣ አይገደድም፡፡
2) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ፀንቶ በሚቆይበት ወቅት መደበኛ መታወቂያ ማውጣትን አስመልክቶ የሚጣሉ ገደቦች፣ ከልከላዎች ወይም የሚተላለፉ ትዕዛዞች የመታወቂያ እድሳት ላይም ተፈፃሚ ይሆናሉ።
5. ተመጣጣኝ መታወቂያ ሰነዶች
የሚከተሉትን ሁኔታዎች ያሟሉ ሰዎች ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሰነድ እንዳላቸው ተቆጥረው ጊዜያዊ መታወቂያ እንዲወሰዱ አይገደዱም፡
1) በሚሰሩበት ተቋም ወይም ድርጅት የተሰጠ የሰራተኛነት መታወቂያ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞች፣ ሕጋዊ ሰውነት ያለው የንግድ ድርጅት ሰራተኞች፣ የመንግስት የልማት ድርጅት ሰራተኞች፣ ህጋዊ ሰውነት ያለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሰራተኞች፣
2) አግባብነት ካለው አካል የተሰጣቸው የማንነት መታወቂያ ያላቸው ስደተኞች፣
3) ህጋዊ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም የተማሪነት መታወቂያ ያላቸው ተማሪዎች፡፡
6. ስለ መስፈርቶች
ማንኛውም እድሜው 18 ዓመት የሞላው ሰው የሚከተሉትን መስፈርቶች ካሟላ ጊዜያዊ መታወቂያ እንዲሰጠው ማመልከት ይችላል፡-
1. የአዲስ አበባ ነዋሪ ስለመሆኑ ህጋዊ የመኖሪያ መታወቂያ ያለው እና በአካባቢው ነዋሪነት የሚታወቅ የቤተሰብ ሃላፊ ስለአመልካቹ ማንነት እና ሰላማዊነት ሙሉ ሃላፊነቱን በመውሰድ ዋስ ሆኖ ለጊዜያዊ መታወቂያ የቀረበውን ማመልከቻ ከደገፈ፣ ወይም
2. አሁን ከሚኖርበት አካባቢ ውጪ ሌላ ቦታ ሲኖር የነበረ ሆኖ ከነበረበት ቦታ ሸኚ ወረቀት ማምጣት የሚችልና አሁን የሚኖርበት ቤት ህጋዊ ሰነድ ያለው ሆኖ የቤቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሉ ካስመዘገበው ወይም ዋስ ለመሆነ ፍቃደኛ ከሆነ፤
3. በካምፕ፣ በማሰልጠኛ ወይም በአባላት የጋራ መኖሪያ ቤት የሚኖሩ የፖሊስ ሰራዊት ወይም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተሰባቸውና ራሳቸው በሚኖሩበት ቤት ቁጥር አገልግሎቱን እንዲያገኙ ከሚመለከተው አካል ተፈቅዶ ደብዳቤ ከተፃፈላቸው፣
4. ጊዜያዊ መታወቂያ እንዲሰጥ ጥያቄ በቀረበበት አካባቢ ነዋሪ የሆነ ባለትዳር ባል ወይም ሚስት ከሌላ ቦታ በስራ ምክንያት የተዛወረ ከሆነና ስለመዘዋወሩ እና ህጋዊ ትዳር ስለመኖሩ በቂ ማስረጃ ካቀረበ፣
7. የጊዜያዊ መታወቂያ የጊዜ ቆይታ እና ስለሚይዛቸው መረጃዎች
1. ጊዜያዊ መታወቂያ የሚሰጠው ለ6 ወር ሲሆን መታወቂያውን የያዘው ሰው በየወሩ መታወቂያውን የወሰደበት ቦታ በመቅረብ ሪፖርት ማድረግና ማሳደስ ይኖርበታል፣
2. ጊዜያዊ መታወቂያ ላይ ግለሰቡ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ የተነሳው ፎቶ የሚለጠፍ ሆኖ በመታወቂያው ላይ የሚሰፍሩ መረጃዎች ይዘት መደበኛው መታወቂያ የሚይዛቸው መረጃዎች ይሆናሉ::
8. ጊዜያዊ መታወቂያ የመስጠት ሀላፊነት ያለባቸው አካላት
የሚከተሉት አካላት ጊዜያዊ መታወቂያ የመስጠት ሀላፊነት አለባቸው፡-
1) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ መዋቅር፣
2) በድሬዳዋ እና በክልሎች ደግሞ የፖሊስ መዋቅር፡፡
9. ማንነትን ስለማረጋገጥ
ጊዜያዊ መታወቂያ ለመውሰድ የሚያመለክት ማንኛውም ግለሰብ ስለትክክለኛ ማንነቱ መታወቂያውን በሚወስድበት ቦታ በመንግስት አካል በሚዘጋጅ ቅፅ ላይ የተመለከቱ ማንነትን ለማረጋገጥ የሚጠቅሙ መረጃዎችን በመሙላትና ቃለ መሀላ በመፈጸም ያረጋግጣል።
10. የጊዜያዊ መታወቂያ አገልግሎት
በዚህ መመሪያ መሰረት የሚሰጥ ጊዜያዊ መታወቂያ መታወቂያውን የወሰደውን ሰው ማንነትን ከማረጋገጥ ውጪ መደበኛው የነዋሪነት መታወቂያ የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች ወይም መብቶች አያስገኝም፡፡
ክፍል ሶስት
ግዴታዎችና የተከለከለ ተግባራት
11. ማህበራዊ ጉዳይን የሚመለከት ተግባርና ሀላፊነት ያለባቸው የመንግስት ተቋማት ግዴታዎች
ማህበራዊ ጉዳይን በተመለከተ ሀላፊነት ያለባቸው የፌዴራልና የክልል የመንግስት ተቋማት ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመተባበር ጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ ቋሚ አድራሻ እና ስራ የሌላቸውንና ሌሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በማደራጀት ወደ መጠለያ ወይም ጊዜያዊ መቆያ እንዲገቡ እና በዚያ ቦታ እንዲቆዩ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
12. ጊዜያዊ መታወቂያ የወሰደ ሰው እና የመታወቂያ ሰጪው አካል ግዴታዎች
1) ጊዜያዊ መታወቂያ የጠፋበት፣ የተበላሸበት ወይም በሌላ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ወይም በማናቸውም ምክንያት ከእጁ የወጣበት ማንኛውም ሰው ለፖሊስ በ24 ሰዓት ውስጥ ሪፖርት የማድረግ ሀላፊነት አለበት፣
2) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከተው ሁኔታ ሪፖርት ፖሊስ ተቋም በሚሰጠው ማረጋገጫ መሰረት ጊዜያዊ መታወቂያ የመስጠት ስልጣን የተሰጠው አካል፣ ምትክ ጊዜያዊ መታወቂያ ይሰጣል::
13. የተከለከሉ ተግባራት
የሚከተሉትን ተግባራት መፈጸም በአዋጁ እና ሌሎች ህጎች መሰረት የወንጀል ኃላፊነት ያስከትላል፡-
1) ጊዜያዊ መታወቂያ ለመውሰድ ሀሰተኛ መረጃ መስጠት ፣
2) መስፈርቱን ለማያሟላ ሰው ጊዜያዊ መታወቂያ መስጠት፤
3) መስፈርቱን የማያሟላ ሰው ጊዘያዊ መታወቂያ እንዲሰጠው በማሰብ ማረጋገጫ ደብዳቤ መፃፍ ወይም ምስክር መሆን፣
4) ከአንድ በላይ ጊዜያዊ መታወቂያ ይዞ መገኘት፡፡
ክፍል አራት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
14. ተፈፃሚነት የሌላቸው መመሪያዎች ወይም ልማዳዊ አሰራሮች
ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛዉም መመሪያ ወይም የአሰራር ልምድ በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ይህ መመሪያ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተፈፃሚነት አይኖረዉም፡፡
15. መመሪያዉ የሚፀናበት ግዜ
ይህ መመሪያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
አዲስ አበባ ህዳር 06 ቀን 2014 ዓ.ም
የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ እዝ

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

በዱባይ የአየር ላይ ትዕይንት አቀረበ ********************************* የኢትዮጵያ አየር መንገድ በA350-900 በዱባይ የአየር ላይ ትዕይንት አቀረበ፡፡በትዕይንቱ ከ1 ሺ...
15/11/2021

በዱባይ የአየር ላይ ትዕይንት አቀረበ
*********************************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በA350-900 በዱባይ የአየር ላይ ትዕይንት አቀረበ፡፡
በትዕይንቱ ከ1 ሺህ 200 በላይ አውደ ርዕይ አቅራቢዎች እና ከ148 በላይ የአገራት ተወካዮች መሳተፋቸውን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

ሮይተርስ የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁን በሚመለከት  የተዛባ እና የተሳሳተ ዘገባ  አውጥቷል ********************************* ሮይተርስ የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁን በተመለከተ   ...
12/11/2021

ሮይተርስ የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁን በሚመለከት የተዛባ እና የተሳሳተ ዘገባ አውጥቷል
*********************************
ሮይተርስ የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁን በተመለከተ የተዛባ ፤የተሳሳተ እና የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ መስፈርት ያልሆነ የዘገባ ሽፋን መስጠቱን የወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
መረጃ ማጣሪያው በማህበራዊ ገጽ ትስስር እንዳለው ሮይተርስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ "ዜጎችን የብሄር ማንነትን እንዲገልጹ ያስገድዳል" በሚል ያሰራጨው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን ገልጿል።
የሮተርስ የተዛባ ዘገባ የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ ታስክ ፎርስ መረጃዎች ለማግኘት የሚጠቀመው መስፈርት አለመሆኑንም ነው የጠቀሰው።
በአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ ወቅት ከዜጎች የሚፈለግ መረጃ በሚኖርበት ጊዜ የተሽከርካሪ መንጃ ፍቃድ፤የስራ ስምሪት መታወቂያ፤የብሄራዊ ፓስፖርትን ጨምሮ ሌሎች አማራጮች እንደሚፈቀድ ገልጿል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የወጣው መንግሥት የአገርን ህልውና፣ ሉዐላዊነት እና የግዛት አንድነት ከውስጥም ሆነ ከውጭ ጠላቶች የመጠበቅ የሕግም ሆነ የሞራል ኃላፊነት እና ግዴታ ያለበት መሆኑን በመገንዘብ፤
የሽብርተኛው ሕውሃት እና የሽብር ግብረአበሮቹ እንቅስቃሴ በሃገር ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ ጉልህ እና ድርስ አደጋ የደቀነ በመሆኑ፤
ሽብርተኛው ሕውሃት እና የሽብር ግብረአበሮቹ ለዕኩይ አላማቸው መሳካት በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ እየፈፀሙ ያሉት ግድያ፣ ዝርፍያ እና ሌሎችም ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላባቸው ኢሰብዐዊ ጥቃቶች እጅግ አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ከግምት በማስገባት፤
ከቀጥተኛ እና መደበኛ የውግያ አውድ በተጨማሪም የሽብርተኛው ሕወሃት እና የሽብር ግብረአበሮቹን ተልዕኮ ያነገቡ ግለሰቦች ከሰላማዊ ዜጎች ጋር በመመሳሰል በህዝብ እና በሃገር ላይ የደቀኑትን ከፍተኛ እና ተጨባጭ የደህንነት ስጋት በመረዳት፤
ሽብርተኛው ሕወሃት ኢትዮጵያን የማዳከም እና ብሎም የማፍረስ ምኞት ካላቸው የውጭ ሃይሎች ጋር በከፍተኛ ቅንጅት እየሰራ እንደሆነ በመገንዘብ፤
የተደቀኑ አደጋዎችን በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ለመቋቋም አዳጋች በመሆኑ እንደሆነ ይታወቃል።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

የጦር መሳሪያዎች በየቦታው እየተጣሉ ነው *********************************የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ጠንካራ ጥበቃ ከተጀመረ በኃላ የተለያዩ የጦር መ...
12/11/2021

የጦር መሳሪያዎች በየቦታው እየተጣሉ ነው
*********************************
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ጠንካራ ጥበቃ ከተጀመረ በኃላ የተለያዩ የጦር መሪያዎች በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች፣ በየጥሻው እና በየመንገድ ዳር ተጥሎ እየተገኘ ነው ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ይህን ያለው ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጠው ቃል ነው።

ፖሊስ የጦር መሳሪያዎች ፣ የእጅ ቦንብ፣ ጥይቶች በየጥሻው ፣ በየመንገድ ዳሩ ፣ በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ውስጥ እየተገኙ ስለሆነ ህብረተሰቡ በእነዚህ አካባቢዎች ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና ጥቆማም እንዲሰጥ አሳስቧል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ህብረተሰቡ በቡድን በቡድን እየሆነ በየአካባቢው ጠንካራ ጥበቃ እያደረገ ነው ያለ ሲሆን በዚህም በርካታ ውጤት መገኘቱን አሳውቋል።

ፖሊስ ለከተማው የፀጥታ ስጋት ናቸው የተባሉ ፣ ሀገርን ለማፍረስ ለተሰለፉ ኃይሎች በተለያዩ መልኩ ሲደግፉ የነበሩ፣ ስልጠና እና ስምሪት ተሰጥቷቸው በከተማው የተሰገሰጉትን እየለየን እየያዝን ነው ብሏል።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ አርማውን ቀየረ ********************************* የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን ተቋማዊ አርማ መቀየሩን የመከላከያ ኢ...
11/11/2021

የኢትዮጵያ መከላከያ አርማውን ቀየረ
*********************************
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን ተቋማዊ አርማ መቀየሩን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብ/ጄ አስፋው ማመጫ አስተወቁ።
ጄነራል መኮንኑ፣ ተቋሙ ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን አርማ የቀየረው አዲስ ከፈጠረው አደረጃጀትና እየተገበረ ካለው ሪፎርም አኳያ ገላጭ ባለመሆኑ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡
እንደ ብ/ጄ አስፋው ማመጫ ገለፃ፣ ተቋሙ አዲስ ይፋ ያደረገው አርማ ከተቋሙ ተልዕኮና ባህርይ አንፃር ልዩ ልዩ ትርጓሜዎችን የያዘ ነው።
ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መግለጫ  *********************************የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ሀገራዊ ሁኔታና የአዋጁን አፈጻጸም ማምሻ...
10/11/2021

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መግለጫ
*********************************
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ሀገራዊ ሁኔታና የአዋጁን አፈጻጸም ማምሻውን ገሞግሟል። ዕዙ ለኅብረተሰቡ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ፣ የአዋጁን አፈጻጸምና ወታደራዊ ርምጃዎች በመገምገም የተለያዩ ድሎች መመዝገባቸውን አረጋግጧል።
በዚህም መሠረት፦
1. የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር በሚደረገው ዘመቻ፣ የአማራ፣ የአፋርና የኦሮሚያ ክልሎች ሕዝብ የተደረገላቸውን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል ወደሁሉም ግንባሮች ከትቷል። ሌሎችም በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።
2. በባቲ- አሳጊታ ግንባር የጥፋት ኃይሉ ባለፉት ዘጠኝ ቀናት ከ20 ያላነሡ የማጥቃት እንቅስቃሴዎችን አድርጓል። ጀግኖቹ የአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀትና በንሥሮቹ የአየር ኃይል በመታገዝ፣ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሣራ በማድረስ፣ ሁሉንም የማጥቃት እንቅስቃሴዎች አክሽፈው ወራሪው ሽንፈትን እንዲከናነብ አድርገውታል። ሚሌን ለመያዝ የነበረውንም ፍላጎት የሕልም እንጀራ አድርገውበታል።
3. በትግራይ እና አፋር ክልል ወሰን ላይ ቢሶበር አካባቢ ጁንታው ዛሬ የከፈተውን አዲስ የማጥቃት ሙከራ፣ አንበሶቹ የአፋር ሚሊሻና ልዩ ኃይል የጠላትን አከርካሪ ሰብረው በዚህ ግንባር የመጣውን ጠላት አሳፍረው መልሰውታል።
4. በወረኢሉ ግንባር ለመስፋፋት አስቦ የተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል፣ በደቡብ ወሎ ሚሊሻና በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተመትቶ መክኗል።
5. በአቀስታ ግንባር ለመንቀሳቀስ አስቦ የነበረው የጁንታ ኃይል በአዊ፣ በምዕራብ ጎጃም፣ በምሥራቅ ጎጃምና በደቡብ ወሎ ሚሊሻ ተመትቶ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ተገድዷል።
6. በከሚሴ ግንባር ያሉት የመከላከያ ሠራዊት፣ የኦሮሞ ብሔረሰብና የሰሜን ሸዋ ዞኖች ሚሊሻዎች ባለፉት አምስት ቀናት ባደረጉት ተጋድሎ፣ ወረራውን በመቀልበስ፣ ወደ ፀረ ማጥቃት እንቅስቃሴ ተሸጋግረዋል።
7. በማይጠብሪ ግንባር የጥፋት ኃይሉ ተደጋጋሚ ፀረ ማጥቃት ቢያደርግም እንቅስቃሴው ከሽፏል።
በአጠቃላይ በአማራና በአፋር ክልሎች የክተት አዋጁን ተከትሎ በጠላት ላይ እየተወሰደ ያለው ርምጃ አመርቂ ኾኖ ተገኝቷል። ለዚህ መሠረቱ የሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ መነሣሣትና ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የፈጠረው ንቅናቄ መሆኑ ተረጋግጧል።
8. በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በሆሮጉድሩ እና በምሥራቅ ወለጋ አንዳንድ ወረዳዎች ላይ ሰላማዊውን ሕዝብ በመግደልና ንብረት በመዝረፍ፣ የጁንታውን ተልዕኮ ለማስፈጸም ሲንቀሳቀስ የነበረውን አሸባሪውን የሸኔ ቡድን በመደምሰስና ግብረ አበሮቹን በቁጥጥር ሥር በማድረግ፣ የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ፣ የፌዴራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ የጋራ ጥምረት ከፍተኛ ድል ተጎናጽፈዋል።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተደረገለትን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበልና ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ይህ አኩሪ ድል እንዲመዘገብ አድርጓል። ለዚህም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ የጀመረውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያደርጋል።
ድላችንን አጽንተን መቀጠል እንድንችል፣ ዕዙ የሚከተሉትን ሦስት ትዕዛዞችን አስተላልፏል።
1. የጸጥታ ኃይሎች የተቀናጀ እንቅስቃሴ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌዎችን በማስፈጸም ባለፉት ቀናት አኩሪ ውጤቶችን አስመዝግቧል፣ ሕገ ወጦችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፣ በርካታ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎችም ተይዘዋል። ይህ ያስደነገጠው ጠላት የጸጥታ አካላትን መልካም ስም ለማጥፋት፣ ለማሸማቀቅና ሥራቸውን በሙሉ አቅም እንዳይሠሩ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አጋጣሚ ለመጠቀም የሚፈልጉ ጥቂት የጸጥታ አካለት መኖራቸውን ዕዙ አረጋግጧል። በእነዚህ አካላት ላይ በጠራ መረጃ ላይ በመመሥረት የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ተሰጥቷል።
2. የጸጥታ ኃይሎች ለሕዝቡ ደኅንነት ሥጋት የሚሆኑትን ለመመንጠር ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲያግዝ ማንኛውም ቤት አከራይ የተከራይን ማንነት የሚገልጽ ሙሉ መረጃ ይህ መግለጫ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ፣ በአቅራቢያው በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ እንዲያስመዘገብ ታዟል። ይህን በማያደርጉት ላይ አስፈላጊው ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ተላልፏል።
3. ሕገወጥ ግለሰቦች ብሔራዊ ባንክ ካወጣቸው ደንቦችና የአፈጻጸም መመሪያዎች እንዲሁም ከባንኮች ሕጋዊ አሠራር ውጭ፣ በተጭበረበረ መንገድ የገንዘብ ዝውውር እያካሄዱ መሆኑ ተደርሶበታል። ለዚህም በጊዜው ተገቢው ርምጃ ተወስዷል። በመሆኑም ቀደም ብለው ከወጡ ሕጎችና መመሪዎች ውጭ ሲሠሩ በሚገኙት ባንኮች ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሕግ አስፈጻሚ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥብቅ ርምጃ እንዲወስድ ታዟል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማንኛውም የተጭበረበረ የገንዘብ ማዘዋወሪያ ሰነድ ይዘው በተገኙ ላይ ከወትሮው በተለየ ጥብቅ ርምጃ እንዲወሰድ ታዟል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው መንግስት ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመሆን ለመስራት ተዘጋጅቷል -ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ********************************* በዲሞክራሲያዊ መንገ...
09/11/2021

በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው መንግስት ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመሆን ለመስራት ተዘጋጅቷል -ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
*********************************
በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠዉ የኢትዮጵያ መንግስት በተጀመረዉ የለዉጥ ጉዞ ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመሆን ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ገንቢ በሆነ መልኩ ለመስራት መዘጋጀቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ።
በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መንግሥት በሚፈተን ግን በማይቀለበስ የለውጥ ጉዞ ላይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
መንግሥት ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የልማት ግቦችን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ ለመሥራት ምንጊዜም ዝግጁ ነውም ብለዋል።
መሰናክሎች ያስተምሩናል እንጂ አያስቆሙንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ በያዝነው የለውጥ ጎዳና ወደ ፊት ለመጓዝ ቁርጠኞች ነን ብለዋል።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

ከተማ አስተዳዳሩ ወሎ ግንባር ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ ********************************* የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ወሎ ግንባር ለሚገኙ የመከላከያ ...
09/11/2021

ከተማ አስተዳዳሩ ወሎ ግንባር ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ
*********************************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ወሎ ግንባር ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ20 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ወሎ ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል፡፡
የተደረገው የአይነት ድጋፍም 100 ሰንጋዎችን ጨምሮ 20 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የዕለት ምግብ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ወይዘሮ አዳነች አበቤ እናንተ ለኢትዮጵያ ስትሉ ህይወታችሁን እየሰጣችሁ እና የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ ኢትዮጵያ ቀና እንድትል እየተፋለማችሁ ነው ውለታችሁ አለብን ብለዋል፡፡
ሀገር ለማፍረስ የመጣውን የሽብር ቡድን ለመፋለም ብቻችሁን አይደላችሁም፤ ገንዘብ ብቻም አይደለም ህይወት ለመስጠት ዝግጁ ነን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ዛሬ ይዘን የመጣነው ድጋፍ አብረናችሁ ነንለማለት ነው ያሉት ከንቲባዋ÷ በቀጣይም ለሰራዊቱ ቤተሰብ ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡
የወሎ ግንባር ኮማንድ ፖስት ድጋፍ ሰጪ ቡድን አስተባባሪ ተወካይ ሜጄር ጄነራል ሀብታሙ ጥላሁን በበኩላቸው÷መከላከያ አሸናፊ የሚሆነው የህዝብ ደጀንነቱ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን አንስተዋል፡፡
እስካሁን ሰራዊቱ ከህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ አልተለየውም፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ድጋፍም ሰራዊቱን ይበልጥ እንደሚያበረታታው አውስተዋል፡፡
ሀገር ለማፍረስ እያሴሩ ያሉትን የሽብር ቡድኖችም በአጭር ጊዜ ቀብረን ድል እናበስራለን ነው ያሉት፡፡

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

09/11/2021

ጠላቶቿ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ይሸነፋሉ ! ኢትዮጵያ ለምልማ ባንዲራዋ ከፍ ብሎ የምናይበት ጊዜ ይመጣል- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ማዕቀቡን ተቃወሙ *********************************ቻይና እና ሩስያ በኢትዮጵያ ላይ የሚወሰድን ማዕቀብ ተቃወሙየፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል። ...
09/11/2021

ማዕቀቡን ተቃወሙ
*********************************
ቻይና እና ሩስያ በኢትዮጵያ ላይ የሚወሰድን ማዕቀብ ተቃወሙ
የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል። በዚህ ስብሰባም ቻይና እና ሩስያ በኢትዮጵያ ላይ የሚወሰድ የተናጥል ማዕቀብ ተቀባይነት እንደሌለው አሳውቀዋል።
የሩስያ ተወካይ እየተካሄደ በሚገኘው የፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ከተናገሩት፦
- ኢትዮጵያዊያን በታሪካቸው በብዝሃነት ውስጥ ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደሚቻል ያሳዩ ናቸው።
- ማዕቀብ መጣል እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍን ማቋረጥ ተቀባይነት የለውም።
- የአፍሪካ ህብረትን ጥረት ከመደገፍ ውጭ ማድረግ የምንችለው ነገር የለም።
- ህወሓት በደሴ እና ኮምቦልቻ የፈጸመው ወረራ ዜጎችን ለችግር ዳርጓል
- ሩስያ የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ ከኢትዮጵያ ጎን ትሰለፋለች።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

አምስት መገናኛ ብዙኃን በአራት ቀናት በኢትዮጵያ ላይ 72 የሀሰት ዜናዎችን ሰርተዋል ********************************* ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ፣ አሶሼትድ ፕረስ እና ...
08/11/2021

አምስት መገናኛ ብዙኃን በአራት ቀናት በኢትዮጵያ ላይ 72 የሀሰት ዜናዎችን ሰርተዋል
*********************************
ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ፣ አሶሼትድ ፕረስ እና ፍራንስ 24 የተሰኙ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በአራት ቀናት ውስጥ ብቻ በኢትዮጵያ ላይ 72 የሀሰት ዜናዎችን መልቀቃቸው ታውቋል።
በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ የሚተላለፈው የ"ቴክቶክ" ፕሮግራም አዘጋጅ ሰለሞን ካሳ በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ ÷ ምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙኃን ሆን ብለው በህዝቡ ውስጥ ሽብር ለመፍጠር የሀሰት ዘገባዎችን በስፋት እያሰራጩ ናቸው ብሏል።
ዛሬም የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ በህይወት አለ ያለው ሰሎሞን ÷ ከሰሞኑ የሚሰራጩት ሀሰተኛ ዘገባዎች ዋና አላማም አዲስ አበባ በሽብር ቡድኖች እንደተከበበች በማስመሰል ሽብር መንዛትና ሥነ ልቦናዊ አለመረጋጋት መፍጠር ነው ብሏል።
በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ሰልፍ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰራጩትን የሀሰት ዘገባ በማውገዝ የተቃውሞ ድምጻቸውን ማሰማታቸውን አስታውሶ ኢፕድ ዘግቧል።

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

“ እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትዋረድም!” የሚል ታላቅ  ሰላማዊ ሰልፍ በመዲናዋ እየተካሄደ ነው *********************************  ከአራቱም አቅጣጫዎች እየተመመ የወጣው የአ...
07/11/2021

“ እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትዋረድም!” የሚል ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመዲናዋ እየተካሄደ ነው
*********************************
ከአራቱም አቅጣጫዎች እየተመመ የወጣው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ አሽባሪውን ህወሓትና ተላላኪውን ሸኔን አምርሮ በማውገዝ ወደ መስቀል አደባባይ ተጉዟል።
በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ፈረሰኞችን ጨምሮ በተለያዩ አገራዊና ወኔ ቀስቃሽ ባህላዊ ሙዚቃዎችና ዜማዎች ታጅበውና በርካታ መልዕክቶችን የሚገልጹ መፈክሮችን እያሰሙ መስቀል አደባባይ የተገኙት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ አሸባሪዎቹን ህወሃትንና ሸኔን ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ዘገቢዎቻችን ከየአካባቢው ባደረሱን መረጃ መሰረት፥ ሰልፈኞቹ “እኛ በህይወት እያለን እንደ ዓይናችን ብሌን የምንጠብቃት አገራችን አትፈርስም፥ በድምፃችን የመረጥነው መንግሥታችን በማንም ባንዳ ሊተካ አይችልም፥ መንግስታችን ኢትዮጵያን ለማዳን የሚያካሂደውን የህልውና ዘመቻ እንደግፋለን፥ ለኢትዮጵያ ክብር በመዋደቅ ላይ ከሚገኙት ጀግኖች ጎን በጽናት እንሰለፋለን፥የአገርና የሊጥ ሌባ የሆነው ወያኔ ዳግም ሊገዛን አይችልም” የሚሉ መልዕክቶችን ሲያስተጋቡ ተደምጠዋል።
ሰልፈኞቹ በጽሁፍ ከያዟቸው መፈክሮች መካከልም ፥ “ ኢትዮጵያዬ እኔ አለሁልሽ! ኢትዮጵያ ታሸንፋለች! ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ እንታደጋለን! እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትበታተንም! በህወሓት ዳግመኛ የሚታለል አንድም ኢትዮጵያዊ አይኖርም!! ለባንዳዎችና ወራሪዎች አንንበረከክም! እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትዋረድም! ኢትዮጵያን ለአሸባሪዎች አሳልፌ አልሰጥም! ከኢትዮጵያዬ የሚበልጥብኝ የለም! የአባቶቼ ልጅ ነኝ ለኢትዮጵያ እሞታለሁ! ለውጫዊ ጫና የሚንበረከክ ማንነት የለንም!! ይህ ትውልድ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በክብር ያስቀጥላል! “ የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡

ይህን መረጃ ሼር ማድረጎን አይርሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Ethiopia-Today-News-104568651850494/?ref=pages_you_manage
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCMp7cMud1q4yJwkE-8pnUNg
ቴሌግራም፦ https://t.me/ETNETN
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopianToday1
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፡፡

Address

Piassa
Addis Ababa
100

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Today News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share