Ethiopian Independent/ሉዓላዊት ኢትዮጵያ

Ethiopian Independent/ሉዓላዊት ኢትዮጵያ fast and real information provide for the audiance

ኮትዲቯር የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች  አስተናጋጇ ኮትዲቯር የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሆነች። ዛሬ ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ አስተና...
11/02/2024

ኮትዲቯር የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች

አስተናጋጇ ኮትዲቯር የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሆነች።

ዛሬ ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ አስተናጋጇ ኮትዲቯር ናይጄሪያን 2 ለ 1 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስታለች።

በዚህም ዝሆኖቹ የአፍሪካ ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ ማንሳት ችለዋል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ  : የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ተመስገን ጥሩነህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡የብልጽግና ማዕከ...
26/01/2024

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

: የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ተመስገን ጥሩነህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህንና የአሰራር ሥርዓት በመከተል ዛሬ ባካሄደው የማጠቃለያ ስብሰባ በሙሉ ድምፅ አቶ ደመቀ መኮንን በክብር ሸኝቷል፡፡

በምትካቸውም የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ በአብላጫ ድምጽ መርጧል።

የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝባቸውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተቸገሩ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)  : የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝባቸውን የልማት ጥያቄ ለመመለስና...
19/01/2024

የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝባቸውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተቸገሩ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

: የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝባቸውን የልማት ጥያቄ ለመመለስና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከፍተኛ የሆነ ፈተና እየተጋፈጡና እየተቸገሩ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የልዑካን ቡድናቸው በዑጋንዳ ካምፓላ በተካሄደው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያለባቸውን ፈተና በተመለከተ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝብን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ፈተናዎችን እየተጋፈጡ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የባህር በር የሌላት ኢትዮጵያም ችግሩን ለመፍታት በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ መሰረት ጥረት እያደረገች እንደሆነ ማስረዳታቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።

ጋዜጠኛ እና ፕሮግራም አቅራቢ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ  : ጋዜጠኛ አስፋው ባደረበት ህመም በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ህይወቱ ማለፉን  ኢቢኤስ እና የመንግስት ሚዲያዎ...
14/01/2024

ጋዜጠኛ እና ፕሮግራም አቅራቢ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

: ጋዜጠኛ አስፋው ባደረበት ህመም በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ህይወቱ ማለፉን ኢቢኤስ እና የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ተወዳጁ የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ በኤፍኤም አዲስ 97.1 “አይሬ” በተባለ የሙዚቃ ፕሮግራሙ ይታወቅ ነበር።

በኢቢኤስ ቴሌቪዥንም “ኑሮ በአሜሪካ” በተሰኘ ፕሮግራሙ ተወዳጅ የነበረው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በህመም አልጋ ላይ እስኪወድቅ ድረስ በቴሌቪዥን ጣቢያው በፕሮግራም አቅራቢነት ሲያገለግል ቆይቷል።

ህዳሴ‼የዓባይ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባካሄደው ስብሰባ የግድቡን የግንባታ ሂደትና የአምስት ወራት አፈጻጸምን ገምግሟል፤ በግምገማውም:✔የዓባይ ግድብ በኢትዮጵያውያን...
06/01/2024

ህዳሴ‼

የዓባይ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባካሄደው ስብሰባ የግድቡን የግንባታ ሂደትና የአምስት ወራት አፈጻጸምን ገምግሟል፤ በግምገማውም:

✔የዓባይ ግድብ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ጥረትና ፅናት ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ተሸጋግሯል፣

✔የግድቡ ከተጀመረበት እስከ ህዳር 30/2016 ድረስ ከ18 ቢሊዮን 734 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል፣

✔ የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት 12 ዓመታት በፅናት ገንዘቡን፣ እውቀቱንና ሙያውን ለግድቡ ግንባታ አውሏል፣

✔የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 94 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል፣

✔የኢትዮጵያውያን የአብሮነትና ሀገር ወዳድነት ቋሚ መገለጫ ነው፣

✔ግብፅ የሶስትዮሽ ድርድሩ አያስፈልግም የሚል አቋም ይዛ በመውጣቷ ድርድር መቋረጡ ይጠቀሳል፣

✔ባለፉት አምስት ወራት ለግድቡ ግንባታ የተደረገው የሀብት ማሰባሰብ ስራ የተሻለ አፈጻጸም አሳይቷል፣

✔በዚህ ዓመት ተጨማሪ ተርባይኖችን ወደ ኃይል ማመንጨት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው፣

✔የግድቡ 13ኛ ዓመት ኢትዮጵያውያን ቃላቸውን በተግባር ያጸኑበትን አውድ በሚገልፅ መልኩ ይከበራል የሚሉ ነጥቦች ተነስተዋል።
via EPA
ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ.ም

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ አዲስ አበባ ገቡ  :  የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅ...
31/12/2023

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ አዲስ አበባ ገቡ

: የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአዲስ አበባ ደርቢ ቡናማዎቹ ተጋጣሚያቸውን አሸነፉ  : በአዲስ አበባ ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ሦስት ነጥብ አሳክቷል፡፡9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴ...
30/12/2023

በአዲስ አበባ ደርቢ ቡናማዎቹ ተጋጣሚያቸውን አሸነፉ

: በአዲስ አበባ ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ሦስት ነጥብ አሳክቷል፡፡

9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ተስተካካይ ጨዋታ የቡናማዎቹን ብቸኛ ጎል ጫላ ተሺታ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ለመጋራት በተደጋጋሚ ያደረገውን ሙከራ ወደ ውጤት መቀየር ሳይችል ቀርቷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና በ11 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ፈረሰኞቹ በ16 ነጥቦች በነበሩበት 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

የገበታ ለሀገር ትሩፋት የሆነው የወንጪ አስገራሚ ገፅታ !!!!!
30/12/2023

የገበታ ለሀገር ትሩፋት የሆነው የወንጪ አስገራሚ ገፅታ !!!!!

ኢትዮጵያ የፊታችን ሰኞ ብሪክስን በይፋ በአባልነት ትቀላቀላለች  : በነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም በጆሃንስበርግ በተካሄደው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባዔ ኢትዮጵያ የአምስት ሀገራት ጥምረ...
30/12/2023

ኢትዮጵያ የፊታችን ሰኞ ብሪክስን በይፋ በአባልነት ትቀላቀላለች

: በነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም በጆሃንስበርግ በተካሄደው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባዔ ኢትዮጵያ የአምስት ሀገራት ጥምረት የሆነውን ማኅበር ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ግብጽ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ ዓረቢያና ኢራን በፈረንጆቹ ከ ጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ በይፋ የብሪክስ አባል እንደሚሆኑ ጥምረቱ አስታውቋል።

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) አየር ኃይል አባላት በጋራ ሆነው " ጥቁር አንበሳ " የተሰኘ የአየር ላይ ወታደራዊ ትርዒት አቀረቡ።ትርዒቱን ያቀረቡት የ...
16/12/2023

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) አየር ኃይል አባላት በጋራ ሆነው " ጥቁር አንበሳ " የተሰኘ የአየር ላይ ወታደራዊ ትርዒት አቀረቡ።

ትርዒቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደ ስነስርዓት ላይ ነው።

በስነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይሎች በጋራ የቀረበው ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት በትብብር ከሠራን የምንደርስበትን ደረጃ ያሳየ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው የአየር ትርዒቱ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢማራት በፖለቲካው እና በውትድርናው መስክ ያላቸውን መልካም ግንኙነት፣ ወዳጅነትና ትብብር ያሳየ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከተመሰረተ 88ኛ አመቱን የያዘ ሲሆን ካለፈው ህዳር 20 ጀምሮ የምስረታ በዓሉ እየተከበረ ነው።

Photo Credit -

16/12/2023


ይሰለቻል.....

የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።  : የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል...
03/11/2023

የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

: የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 255 ያመጡ

☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 234 ያመጡ

☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 218 ያመጡ

☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 200 ያመጡ

☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 224 ያመጡ

☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ

☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 192 ያመጡ

☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ

☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ

☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ

☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ

☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ

☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 ነጥብ 150 ያመጡ

☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 ነጥብ 150 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።

ምንጭ፦ፋና

የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚዬም ፕሮጀክት ግንባታን ጎበኙ  :  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚዬም ፕሮጀክት ግንባታ ሒደት የ...
02/11/2023

የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚዬም ፕሮጀክት ግንባታን ጎበኙ

: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚዬም ፕሮጀክት ግንባታ ሒደት የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
በግምገማ መድረኩ የተሳተፉት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችም የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚዬም ፕሮጀክት ግንባታ ሒደት የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ የተገኙት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክተው ለአመራሩ ገለፃ አድርገዋል።
በዚህም ፕሮጀክቱ የመላው ጥቁር ህዝብ ድል የሆነውን ታላቁን የአድዋ ድል ታሪክ እና የአባቶቻችንን የነፃነት ተጋድሎ እና ጀግንነት በሚመጥን መልኩ በከፍተኛ በጀት እየተገነባ ወደ መጠናቀቁ መቃረቡን ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የከተማ አስተዳደሩን በራስ አቅም ፕሮጀክቶችን የመጀመር፣ የመገንባትና የማጠናቀቅ ብቃት የሚያሳይ ነው ማለታቸውንም የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
አመራሩ በተለያዩ ዘርፎች የተጀመሩና የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት የሚቀይሩ ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶችን በዚሁ መንፈስ እንዲመራ እና እንዲያጠናቅቅም አሳስበዋል፡፡

Source:-Fana

  : የአዲስ አበባ ከተማ እና የደቡብ ኮሪያዋ ቾንቹን ከተማ 20ኛ ዓመት የእህትማማችነት ግንኙነት በአዲስ አበባ በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ይገኛል።ክበረ በዓሉን በማስመለክት ከንቲባ አዳነ...
01/11/2023

: የአዲስ አበባ ከተማ እና የደቡብ ኮሪያዋ ቾንቹን ከተማ 20ኛ ዓመት የእህትማማችነት ግንኙነት በአዲስ አበባ በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ይገኛል።

ክበረ በዓሉን በማስመለክት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተናገሩት አኳር ሀሳቦች መካከል፦

ኢትዮጵያ በኮሪያ ሰላም አስከባሪ የላከች ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር ናት። ይህም ለሁለቱ አገራት የህዝብ ለህዝብ ትስስር ትልቅ መሰረት ጥሏል፤

ለስድስት አስርት ዓመታት ተጠናክሮ የቀጠለው የሁለቱ አገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጎለብት ሁለቱ እህት ከተሞች እየሰሩ መሆናቸውን፤

ባለፈው ዓመት የሁለቱን አገራት ታሪካዊና ዘላቂ ግንኙነት የሚዘክር የኮሪያ ዘማቾች ሀውልት፣ የጎዳና ስያሜ እንዲሁም የኢትዮጵያውያን ባህሎችን ማሳያ ከመሰራቱ በተጨማሪ በኢትዮጵያም የኮሪያ ባለሀብቶችና ድርጅቶች እያደረጉት ላለው ተሳትፎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሁለቱ አገራት ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኮሪያ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

አዲስ አበባ የደቡብ ኮሪያዋን ቾንቹን ከተማ ጨምሮ ከ24 ከተሞች ጋር በእህትማማችነት እየሰራች መሆኑንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስረድተዋል።

ክበረ በዓሉ ዛሬም በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

ሊዮኔል ሜሲ ለ8ኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ  : ሊዮኔል አንደሬስ ሜሲ የ2023 ባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆኗል፡፡የ2022/ 2023 የባላንዶር አሸናፊ ሽልማት ሥነ- ሥርዓት በዛሬው ዕለት...
31/10/2023

ሊዮኔል ሜሲ ለ8ኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ

: ሊዮኔል አንደሬስ ሜሲ የ2023 ባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆኗል፡፡

የ2022/ 2023 የባላንዶር አሸናፊ ሽልማት ሥነ- ሥርዓት በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ተካሂዷል፡፡

በዚህም በወንዶች አርጀንቲናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለ8ኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማትን
ተቀዳጅቷል፡፡

ለአሜሪካው ኢንተር ሚያሚ እየተጫወተ የሚገኘው ሊዮኔል ሜሲ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ከአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ጋር የዓለም ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡

በሴቶች ደግሞ ስፔናዊቷ ኮከብ አይታና ቦንማቲ የባላንዶር አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡

የ25 ዓመቷ ቦንማቲ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የሴቶች ዓለም ዋንጫን አሸንፋለች፡፡

በሌላ በኩል የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ለሆኑ ተጫዋቾች የሚሰጠውን "የገርድ ሙለር" ሽልማት ሲያሸንፍ÷የአስቶን ቪላው ግብ ጠባቂ ኤሚ ማርቲኔዝ ለምርጥ ግብ ጠባቂ የሚሰጠውን "የያሲን ትሮፊ" አሸናፊ ሆኗል።

የሪያል ማድሪዱ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጁድ ቤሊንግሃም ከ21 ዓመት በታች ላሉ ታዳጊ ተጫዋቾች የሚሰጠውን" ኮፓ ትሮፊ" አሸንፏል።

ድምፃዊ አባይነህ ደጄኔ አረፈ !!!  : እጅግ የምናከብረው የጥበብ ሰው አባይነህ ደጄኔ ከዚህ አለም በሞት ተለዬ።አባይነህ ደጀኔ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሰርግ ሙዚቃን በሸክላ ያስቀረፀ ...
30/10/2023

ድምፃዊ አባይነህ ደጄኔ አረፈ !!!

: እጅግ የምናከብረው የጥበብ ሰው አባይነህ ደጄኔ ከዚህ አለም በሞት ተለዬ።አባይነህ ደጀኔ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሰርግ ሙዚቃን በሸክላ ያስቀረፀ የቀድሞው የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ ቡድን አባል ነበር።አባይነህ ባደረበት ህመም ምክንያት ዛሬ ጥቅምት 19/2016 ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።ለወዳጅ ዘመዱ መፅናናትን እመኛለሁ።

 #ኮንታ" እናትን ጨምሮ ሁለት ልጆች ህይወታቸውን አጥተዋል "በመሬት መንሸራተት አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ።በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ በኦፓላሸ ቀበሌ በግምት በሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ...
29/10/2023

#ኮንታ

" እናትን ጨምሮ ሁለት ልጆች ህይወታቸውን አጥተዋል "

በመሬት መንሸራተት አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ በኦፓላሸ ቀበሌ በግምት በሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የመሬት መምሸራረት አደጋው ሰሞኑን የጣለ ከባድ ዝናብ ተከትሎ እንደደረሰ የተነገረ ሲሆን በአደጋው እናትን ጨምሮ ሁለት ልጆች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ሟቾች የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ አግኔ አሉላ፣ ታናሽ ወንድሟና የ6ኛ ክፍል ተማሪ አማኑኤል አሉላ እና እናታቸው ወ/ሮ ዳምአሌ ደስታ ናቸው።

በደረሰው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ በኦፓ ላሸ እና በኮዳ ማጂ ቀበሌ 25 አባዎራዎችና 175 የቤተሰብ አባላት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በቀበሌ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

በአደጋው አምስት የቤት እንስሳት መሞታቸውንና በ5 ነጥብ 5 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል መውደሙም ተጠቁሟል

የዚህ መረጃ ባለቤት የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የንኢሌ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ ፕሮጀክት በአፋር ክልል አስጀመሩ  : ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ አካል የሆነውን የንኢሌ ፓልም ስፕ...
28/10/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የንኢሌ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ ፕሮጀክት በአፋር ክልል አስጀመሩ

: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ አካል የሆነውን የንኢሌ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ ፕሮጀክት ግንባታን በአፋር ክልል አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለትውልድ ስራ አካል የሆነውን የንኢሌ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ ፕሮጀክት በአፋር ክልል አስጀምረዋል። ይህ ስራ ጠቅላይ ሚኒስትር ከጀመሯቸውና ካከናወኗቸው የገበታ መርሃ ግብሮች በሶስተኛው ሊገነቡ ከታቀዱ ሰባት የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዱ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ኢ ኘ ድ

ዛሬ ምሽት ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ይኖራል ተባለ።   : ዛሬ ምሽት ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም የጨረቃ የተወሰነ ከፊል አካል የመሬት ጥላ ሲያርፍበት እንደሚሸፈን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስ...
28/10/2023

ዛሬ ምሽት ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ይኖራል ተባለ።

: ዛሬ ምሽት ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም የጨረቃ የተወሰነ ከፊል አካል የመሬት ጥላ ሲያርፍበት እንደሚሸፈን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህ ክስተት ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ሲባል ግርዶሹ በሁሉም የአፍሪካ ክፍል የሚይታይ እንደሆነ ከስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

ከፊል ግርዶሹ ከምሽቱ 4:35 ጀምሮ ምሽት 5:53 ላይ የሚያበቃ እንደሆነ ሲገለፅ 6 በመቶ የሆነው ዋናው ግርዶሽ ምሽት 5:14 ላይ እንደሚታይና ግርዶሹን ያለ ምንም መሳርያ በዓይን ብቻ የሚታይ እንዲሁም ቴሌስኮፕ እና ባይኑክላር ተጠቅሞም ማየት እንደሚቻል ተገልጿል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በመጀመሪያ ጨረቃ በመሬት ድብዝዝ ጥላ ወይም ፔኑምብራ ውስጥ ትገባለች ያለ ሲሆን ይሄም በጣም የደበዘዘ ስለሚሆን በባዶ ዓይን እንዳማይታይ ገልጾ በመቀጠል ጸሊም ጥላ ወይም አምብራ በሚባለው ከፊል ግርዶሽ ውስጥ ትገባለች ብሏል።

በዋናው ግርዶሽ ቅፅበት ወቅት የጨረቃ 12 ፐርሰንት አካሏ ብቻ የተጋረደ እንደሚሆንም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ገልጿል።

Amharic

116ኛውን የሠራዊት ቀን አከባበር!"በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት " በሚል መሪ ቃል የሠራዊት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል።ዛሬ ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ  በአዲስ አበ...
26/10/2023

116ኛውን የሠራዊት ቀን አከባበር!

"በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት " በሚል መሪ ቃል የሠራዊት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል።

ዛሬ ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው።

የ3ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ ድርድር ዛሬ ማምሻውን ተጠናቀቀ  : በግብጽ ካይሮ ሲካሄድ የነበረው 3ኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ዛሬ ማምሻውን መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ወገን ተ...
25/10/2023

የ3ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ ድርድር ዛሬ ማምሻውን ተጠናቀቀ

: በግብጽ ካይሮ ሲካሄድ የነበረው 3ኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ዛሬ ማምሻውን መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች ልዑካን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ።

አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፦ ድርድሩ መጠነኛ መሻሻልና መግባባት የታየበት ነው።

ቀጣዩን ድርድር በታህሳስ ወር በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ለመቀጠል ስምምነት መደረጉንም አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ በመርሆዎች መግለጫ ስምምነት መሰረት በሚደረግ ውይይት አዎንታዊ ውጤት ላይ መድረስ እንደሚቻል መግለጿ ይታወቃል።

ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኢጄታ …  : ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኢጄታ የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ሽልማትን ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን ተቀብለዋል። ፕሮፌሰር ጋቢሳ በፕሬዚዳ...
24/10/2023

ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኢጄታ …

: ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኢጄታ የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ሽልማትን ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን ተቀብለዋል።

ፕሮፌሰር ጋቢሳ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ብሔራዊ የክብር ሽልማት ከተሸለሙ 21 አሜሪካውያን ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ሆነዋል።

መምህርና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ ለሽልማቱ ያበቃቸው በከፍተኛ የምርምር ስራቸው የእፅዋት ዘረመል ምህንድስና በመጠቀም በረሃማ የአየር ንብረት እና ነፍሳትን የሚቋቋሙ የአዝርዕት ዘሮችን በማግኘታቸው ነው።

ግኝታቸው በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የምግብ ዋስትናን እንደሚያረጋግጥ ታምኖበታል።

ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ በምግብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ከዚህ በፊት ከዓለም የምግብ ፕሮግራሙ ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ፕሬዚደንት ባይደን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ይፋ ባድረጉት የተሸላሚዎች ዝርዝር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ ለሽልማት የበቁትን ተመራማሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

ለ116ኛው የሰራዊት ቀን ከረቡዕ ለሊት 8 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።  : 116ኛው የሰራዊት ቀን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይከበራል፡፡ በዚህም መርሃግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድ...
24/10/2023

ለ116ኛው የሰራዊት ቀን ከረቡዕ ለሊት 8 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።

: 116ኛው የሰራዊት ቀን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይከበራል፡፡

በዚህም መርሃግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳውቋል።

በዚህ መሰረት፦

- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ ፣

- ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ ፣

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ ዝግ ) ፣

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ፣

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ ላይ፣

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ራስ ሆቴል ላይ ፣

- ከሃያሁለት አደባባይ ወደ ኡራኤል የታችኛው መንገድ ሙሉ ለሙሉ

- መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ፣ልደታ ፀበል እና የመከላከያ ግቢ ድረስ በመምጫና በመመለሻ ወቅት ፣

- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ ፣

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባንቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ECA ጫፍ ላይ ለጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም አጥቢያ ረቡዕ ከለሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ግብረኃይሉ አሳውቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙትን የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በጽሕፈት ቤታቸ...
24/10/2023

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙትን የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው መክረዋል::

#ኢፕድ

24/10/2023

#ሰሞን በተለያዬ ምክንያት #ከአየሩ ጠፍተን ነበር #ተመልሰናል !!!!

የአማራና ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተፈናቃዮችን መልሶ በማቋቋም ዙሪያ ምክክር አደረጉ  : የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ባሕር ዳር በመገኘት ከአማራ ክልል ርዕሰ ...
24/10/2023

የአማራና ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተፈናቃዮችን መልሶ በማቋቋም ዙሪያ ምክክር አደረጉ

: የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ባሕር ዳር በመገኘት ከአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል።

ባለፉት ዓመታት ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎችና በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ መኾኑን በምክክሩ ወቅት ተገልጿል።

በጥፋት ኃይሎች ጥቃት ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉና ሐብት ንብረታቸው የወደመባቸውን ወገኖችን በመለየት በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር አብረው ከኖሩት የኦሮሞ ሕዝብ ጋር አብሮነታቸውን ለማስቀጠል ቅንጅታዊ ጥረት እንደሚያስፈልግም ተወያይተዋል።

የኹለቱን ክልል ሕዝቦች አንድነትና አብሮነት የሚጻረሩ ኃይሎችን በመታገል የዜጎችን ደኅንነትና ሐብት ንብረት የማፍራት ነጻነትን ማረጋገጥ እንደሚገባም መድረሳቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ተፈናቃዮች እያሳለፉት ያለውን ችግር ያገናዘበ ፈጣን ስምሪት በመውሰድ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ የማድረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግም አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ተነግሯል።

በሙስና እና ብልሹ አሠራር የተዘፈቁ  42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ  : ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት  አገልግሎት አሠጣጥ  ጋር በተያያዘ ከተገ...
18/10/2023

በሙስና እና ብልሹ አሠራር የተዘፈቁ 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

: ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ ከተገልጋዮች የሚነሱ ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ከመሰረቱ ለመፍታት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣ ግብረ-ኃይል ሕገ ወጦችንና ሙሰኞችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ለረጅም ጊዜ የተቀናጀ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል ይላል ጉዳዩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን የተላከው መግለጫ።

በመሆኑም ከተቋማቱ የተወጣጣውና ጉዳዩን እየተከታተለ ያለው የጋራ ግብረ-ኃይሉ በመግለጫው እንዳመለከተው፤ ተገልጋዮች በመደበኛ የመንግሥት ስርዓት የሚፈልጉትን የፓስፖርትና መሰል አገልግሎቶችን በአፋጣኝና በአነስተኛ ዋጋ ማግኘት ሲችሉ፤ ተጠርጣሪዎች የፈጠሯቸው የተንዛዙና እና የተወሳሰቡ አሠራሮች ዜጎችን ለከፋ እንግልት ከመዳረግ ባሻገር ላልተገባ ወጪ ሲዳርጉ ነበር፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቅ በሙስና ተግባር መሰመራታቸውና የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ እንደነበር ያመለከተው ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣው ግብረ-ኃይል ፤ ግለሰቦቹ በአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ የተሰጣቸውን ስልጣንና ሐላፊነት ወደ ጎን በመተው ለግል ጥቅማቸው ሲሉ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ በወንጀል ተከሰው የጉዞ ሰነዳቸው ለታገደባቸውና ሐሰተኛ የማንነት መገለጫ ላላቸው ሕገወጦች ጭምር የፓስፖርት፣ ሊሴፓሴና ቪዛ አየር በአየር በመሸጥ እና በማስተላለፍ፤ መንገደኞች በሌሉበት ጉዞ እንዳላቸው በማስመሰል እና የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ተለያዩ ሀገራት እንደተዘዋወሩ የሚገለፅ ማሕተም በማዘጋጀት ተግባር ተሰማርተው ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ተመልምለው ያለፉ እንደሆኑ በማስመሰል ግለሰቦች ባልተገባ መንገድ ለሥራ ወደ ተለያዩ የዓረብ ሀገራት እንዲወጡ በማድረግ እንዲሁም የሕጋዊ ግለሰብን ፓስፖርት ፎቶግራፍ በመቀየር ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽሙ እንደተደረሰባቸው የግብረ-ኃይሉ መግለጫ ጠቁሟል።

እነዚህ ወንጀለኞች ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች የጥቅም ትስስር በመዘርጋት ሙስና ሲፈጽሙ ከመቆየታቸውም ባሻገር፤ ሐሰተኛ የማንነት መታወቂያዎችን በማዘጋጀት ተግባር ላይ ተሰማርተው ከነበሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ጋርም ግንኙነት በመፍጠር ወንጀሉን ሲፈፅሙ እንደቆዩ ታውቋል።

ይህን ተከትሎም ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣው ግብረ-ኃይሉ ባደረገው ክትትል ከ200 በላይ የሚሆኑ በሕገወጥ መንገድ የተዘጋጁ ፓስፖርቶች እንዲመክኑ የተደረገ ሲሆን፤ የወንጀል ድርጊቱም መንግሥትን በሚሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ እንዳሳጣው በመግለጫው ተመልክቷል።

በጉዳዩ ላይ ምርመራ ሲያደርግ የቆየው ግብረ -ኃይሉ መግለጫ እንዳመለከተው፤ በአዲስ አበባ ከተማ፤ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በወንጀሉ የተሳተፉ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሲያገለግሉ የነበሩ ከከፍተኛ አመራርነት እስከ ባለሙያ ያሉ 42 ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በዙሁ መሰረትም በወንጀል ድርጊቱ ተሰማርተው ከተገኙና በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከልም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ አዋልሶን ጨምሮ ዘመድኩን ጌታቸው፣ ከድር ሰዒድ ስሩር፣ አስቻለው እዘዘው፣ አብዱላሂ አሊ መሀመድ (አብዱላሂ ጃርሶ)፣ ቴዎድሮስ ቦጋለ፣ ጌትነት አየለ፣ ጀማል ገዳ፣ ሙላት ደስታ፣ ጅላሎ በድሩ፣ ገነት ኃ/ማርያም፣ ደገፋ ቤኩማ ፣ ወንድይፍራው ሽመልስ ገ/ሰንበት እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣው ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

በተያዙት ተጠርጣሪዎች ዙሪያ የሚደረገው ምርመራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽም፤ በግለሰቦቹ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ያላቸው ዜጎች ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉም ገልጿል፡፡

በዚህ ኦፕሬሽንም የተለያዩ ፓስፖርቶች፣ የተለያዩ ሀገራት የብር ኖቶች፣ ሐሰተኛ መታወቂያዎች፣ አየር በአየር የወጡ ሊሴ ፓሴዎችና የታተሙ ቪዛ ካርዶች በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ቤትና የሥራ ቦታ በተደረገ ብርበራ በኢግዝቢትነት መያዛቸወን ግብረ -ኃይሉ አመልክቷል።

ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣው ግብረ -ኃይል በእንደዚህ አይነት ሕገ ወጥ ተግባር ዙሪያ የሚያካሂደውን ምርመራ፣ ክትትልና ኦፕሬሽን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ ለኦፕሬሽኑ መሳካት ማኅበረሰቡ ላሳየው የተለመደና ቀና ትብብር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

በጅግጅጋ በእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ነጋዴዎች ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ   : በጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማእከል በደረሰው የእሳት አደጋ ንብረት ለወደመባቸው ወ...
17/10/2023

በጅግጅጋ በእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ነጋዴዎች ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ


: በጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማእከል በደረሰው የእሳት አደጋ ንብረት ለወደመባቸው ወገኖች በ2ተኛ ዙር ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፉ በገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው ከተለያዩ አካላት የተሰበሰበ ሲሆን÷ ለ 339 ተጎጂዎች በተቋቋመው ኮሚቴ በኩል እንደወደመባቸው ንብረት ሁኔታ በመደልደል ነው 100 ሚሊየን 872 ሺህ 497 ብር እንዲከፋፈል የተደረገው።

በመጀሪያው ዙር ድጋፍ በእሳት አደጋው የደረሰባቸው ውድመት ከ100 ሺህ ብር በታች ለሆኑ ሙሉ በሙሉ ክፍያ የተፈፀመላቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ በዛሬው 2ተኛ ዙር ድጋፍ እንደ ወደመባቸው ንብረት ከ10 በመቶ እስከ 50 በመቶ ድጋፍ እንዲደርሳቸው ተደርጓል ተብሏል።

በስነ-ስርአቱ ላይ በአሜሪካ፣ኖርዌይና ደቡብ ሱዳን የሚኖሩ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራ ተወካዮች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 #ኢትዮጵያ  #ቻይናየኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው።ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢ...
17/10/2023

#ኢትዮጵያ #ቻይና

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው።

ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኃላም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከሪያ መንገዶች ላይ መክረዋል ተብሏል።

ከሁለትዮሽ ውይይቱ በመቀጠል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ጠ/ሚ ሊ ኪያንግ በተገኙበት በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ሁለት የፍላጎት ሰነዶች ተፈርመዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በቻይና ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ ከአራት ዓመት በኃላ ሲሆን በቀጣይ በሚካሄደው 3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ አለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦

  : ቻይና የሚገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካቸው ጋር በመሆን ከቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።ፕሬዝዳንት ሺ ፤ በኢትዮጵያ  #ብሪክስን መቀላቀል...
17/10/2023

: ቻይና የሚገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካቸው ጋር በመሆን ከቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ፕሬዝዳንት ሺ ፤ በኢትዮጵያ #ብሪክስን መቀላቀል ሁነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩን " እንኳን ደስ ያለዎ " ብለዋቸዋል።

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከሁሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት ወደ ሁኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት (All Weather Strategic Cooperation Partnership) ደረጃ ከፍ ማለቱን በይፋ አብስረዋል።

ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አድንቀው ከቻይናው አረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ጋር ተናባቢ በመሆኑ የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ሆኖ ሊደገፍ እንደሚችል አረጋግጠዋል ተብሏል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፤ የቻይና ኢንቬስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖ ያነሱ ሲሆን በተለይም በ5ቱ ቁልፍ ምሰሶዎች፦
- በግብርና
- ማኑፋክቸሪንግ
- አይሲቲ
- ማእድን ልማት እና ቱሪዝም #ተጨማሪ ኢንቬስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ ማቅረባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃ ያሳያል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Independent/ሉዓላዊት ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share



You may also like