05/07/2023
😭
ለሚ ኩራ
አባቱን ና ወንድሙን በቤንዚል አርከፍክፎ ያቃጠለው ግለሰብ
* አባቱ ሲሞቱ 😭
* ወንድምየው ተርፏል🙏
ቤተሰቦቼ ለእኔ ምንም ቦታ የላቸውም በሚል ምክንያት
* ወላጅ አባቱንና ታላቅ ወንድሙን
ቤንዚል በመርጨት በቁም ያቃጠላቸው ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ክብረ ደመና ሙሉ ወንጌል አካባቢ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ነው።
ተከሳሹ ግለሰብ ከዚህ ቀደም በሌላ ወንጀል ተከሶ ታስሮ የነበረና በፍርድ ቤት ዋስትና የተለቀቀ ሲሆን ከእናቴ በስተቀር ለእኔ የሚያስብልኝ የለም በሚል ምክንያት ከሳምንት በፊት በአንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር ቤንዚል በመግዛት
አባቱና ታላቅ ወንድሙ የግል ጉዳያቸውን ፈፅመው በመምጣት ቤት ውስጥ ቁጭ ባሉበት እናትዬውን ውሃ አምጭልኝ ብሎ ከቤት መውጣታቸውን ጠብቆ ቤንዚሉን አርከፍክፎባቸው
ክብሪት በመለኮስ ማምለጥ እንዳይችሉ በሩን ቆልፎ ለማምለጥ ሲል በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ተጎጂዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ወደ ህክምና ቢወስዱም
አባትዬው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን😭
ታላቅ ወንድሙ በህክምና ላይ ይገኛል
በተከሳሹ ላይ ምርመራ እየተጣራበት ይገኛል።
Via AAP
NfasNfas Mereja NetworkeNfas Mereja NetworkwNfas Mereja Network