Ethio runners

Ethio runners An official social media Page Athletic news, Biography Writing, Analysis and reporting

Provide updated Athletic news
Athletic Biography Writer
Athletic Sport Analysis/Writer
Athletic Sport Reporter

ድንቅ ብቃት ሆኖ፤ግን ግን እንኳን ሀጎስንና አሰልጣኙን እኛንም ያስቆጨ ውድድር!!! 12:36.73👉 ውድድሩን ላየ ሀጎስ ገ/ህይወት የ5000 ሜ ክብረ ወሰንን  ከኡጋንዳ ወደ ቀድሞ ቤቱ ኢትዮ...
05/31/2024

ድንቅ ብቃት ሆኖ፤
ግን ግን እንኳን ሀጎስንና አሰልጣኙን እኛንም ያስቆጨ ውድድር!!! 12:36.73
👉 ውድድሩን ላየ ሀጎስ ገ/ህይወት የ5000 ሜ ክብረ ወሰንን ከኡጋንዳ ወደ ቀድሞ ቤቱ ኢትዮጵያ መለሰው ያላለ አልነበረም!
ነገር ግን ውድድር ነውና በአንድ ሰከንድ ምክንያት ክብረወሰኑ ኢትዮጵያ በር ላይ ደርሶ ኡጋንዳ ይሻለኛል ብሎ ተመልሷል።
ሀጎስ የአለምን ክብረወሰን ማሻሻል ባይችልም የሀገሩን የ5000 ሜ ክብረወሰን
ከጀግናው ቀነኒሳ በቀለ እጅ በማስወጣት የግሉ አድርጎታል።
ሀጎስ በዚህ አያያዙና በዛሬው ብቃቱ ክብረወሰኑን አንገቱን ይዞ ወደ ቀድሞ ቤቱ ይመልሰዋል የሚል እምነት እንድንጥል አድርጎናል!!
ብራቮ ሀጎስ!!

ከ10 ምርጥ የ5000 ሜ ሰዓቶች ውስጥ
ሰባቱ ፈጣን ሰዓቶች የኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ
ሁለቱ ማለትም 1ኛና 7ኛ የኡጋንዳዊያን 5ኛው በኬኒያዊ የተያዘ ነው።
ከመቶ ፈጣን ሰዓትች ስናይ
37 ኬኒያ
25 ኢትዮጵያ
8 የአሜሪካ
6 የሞሮኮ
4 የኡጋንዳ አትሌቶች የተቀጣጠሩት ሲሆን ቀሪዎቹን 20 ደረጃዎች በሌሎች ሀገር ዜጎቼ ተይዘዋል።

ተከታትለው ገቡ!!!👉 አዲዳስ በየአመቱ በጀርመን በሚያዘጋጀው አዲዜሮ በተሰኘው የ2024 ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት መዲና ኢሳ ስታሸንፍ ከአራተኛ ደረጃ በስተቀር እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረ...
04/27/2024

ተከታትለው ገቡ!!!

👉 አዲዳስ በየአመቱ በጀርመን በሚያዘጋጀው አዲዜሮ በተሰኘው የ2024 ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት መዲና ኢሳ ስታሸንፍ ከአራተኛ ደረጃ በስተቀር እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረጃ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት ተቆጣጥረውታል።

መዲናና ኢሳና መልክናት ውዱ በአሰልጣኝ ቴዎድሮስ ሀይሉ የሚሰለጥኑ አትሌቶች ሲሆኑ ሁለቱ አትሌቶች የወደፊት የሀገሪቱ የ5000 ሜ ተስፋዎች ናቸው።

በወንዶቹ 5 ኪ ሜ ውድድር ዮሚፍ በአንደኛነት ሲጨርስ አዲሱ ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል።

ዮሚፍ በአሰልጣኝ ንጋቱ የሚሰለጥን ሲሆን አዲሱ በኮማንደር ሁሴን ሰልጥኗል።

ADIZERO RACE TO RECORDS

Results: Women's 5km
Eisa Medina 14:38 🇪🇹

2.Melkanet Wudu 14:40 🇪🇹

3.Tesfay Fotyen 14:41 🇪🇹

4.Diana Chepkorir 15:01 🇰🇪

5.Mehari Hiwot 15:20 🇪🇹

6.Alemu Lemlem 15:20 🇪🇹

7.Dagnaw Tinebeb 15:39 🇪🇹

8.Seyaum Dawit 15:49 🇪🇹

9.A.Marinakau 15:50 🇬🇷

10.SMargaux 16:09 🇫🇷

ADIZERO RACE TO RECORDS

Results: Men's 5km

1.Yomif Kejelcha 13:00 🇪🇹

2.Yihune Addisun 13:05 🇪🇹

3.Belew Birhanu 13:12 🇧🇭

4.Dopash Raphae l 13:13 🇰🇪

5.T.Ndikumwenayo 13:17 🇪🇸

6.Daniel Kimaiyo 13:18 🇰🇪

7.Andrew Kiptoo 13:20 🇰🇪

8.Bekelemu Alemu 13:24 🇪🇹

9.Anteneneh Kibret 13:34 🇪🇹

10.M.Beadlescomb 13:35 🇺🇸

Adidas Road Running

Date: Saturday, April 27, 2024

Location: Herzogenaurach, Germany 🇩🇪

ዜናው የቶፕ ራን ነው

ቀነኒሳ በቀለ በፓሪስ ኦሊምፒክ ይሮጣል?ቀነኒሳ በሩጫው አለም ስላለው ታሪክ ብዙ ተብሏል። እሱ  እድሜ ሳይገድበው በየጊዜው ታሪክ እየሰራ የሚቀጥል ከሆነ መብቱ ነው። እኔ በግሌ በእሱ ጉዳይ ...
04/27/2024

ቀነኒሳ በቀለ በፓሪስ ኦሊምፒክ ይሮጣል?

ቀነኒሳ በሩጫው አለም ስላለው ታሪክ ብዙ ተብሏል።
እሱ እድሜ ሳይገድበው በየጊዜው ታሪክ እየሰራ የሚቀጥል ከሆነ መብቱ ነው።
እኔ በግሌ በእሱ ጉዳይ እድሜ ልኬን መለፍለፍም አልፈልግም ምንም ማለት አልፈልግም በቃኝ።

ቀነኒሳ በፓሪስ ኦሊምፒክ የመሳተፍ ጉዳይ ብዙ ጥያቄዎች በግል ስለቀረቡልኝ በዚህ ላይ ያንተ አስተያት ምንድን ነው ስለተባልኩ ለማከብራቸው ተሳታፊዎቼ ለመመለስ ያህል ብቻ ነው።

ቀነኒሳ በቀለ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈበት የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮና በ10,000 ወርቅ በወሰደባት ሀገር ፈረሳይ ፤ ማራቶንን አንድ ብሎ ሲጀምር በአሸናፊነት በጀመረባት ሀገር ፈረንሳይ፤ እንዲሁም የሀገር አቋራጭ ውድድሮችን እና ሌሎች ውድድሮችን በአንደኛነት በጨረሰባት የእድል ከተማው በሆነችው ፈረንሳይ ጀግናውን በኦሊምፒክ ለ4ኛ ጊዜ ልናየው
ነው? የሚለው ዜና የሚወዱትን ብቻ ሳይሆን በስራው የሚያደንቁትን ኬኒያዎችንም ጭምር እንዳሳሰበና እንዳስደነገጠ ነው የሚሰማኝ። ቀኒኒሳ ሩጫ ላይ እስካለ ኦሊምፒክና ቀነኒሳ አይለያዩም።
ኦሊምፒኩ እራሱ ድምፅ አውጥቶ ፓሪስ ላይ ናልን ያለው ይመስላል።

ይመረጣል ወይ ለሚለው ጥያቄ?
ባጭሩ ስመልስ

ልምዱ ይጠቅናል ወይም ቀነኒሳ
እድሜው ስለገፋ ፤
የመጨረሻው ኦሊምክ ስለሆነም እባካችሁ እንምረጠው ተባብለው ለሟሟያ ፤
ወይም ለሀገር ከሰራው ውለታ አኳያ ቀነኒሳን ለመርዳት ተብሎ አስተያየት ተደርጎለት የሚመረጥ የሚመስላችሁ ካላችሁ
ይህ ከላይ የዘረዘርኩት በሙሉ መሆን ከነበረበትም ብዙ የማራቶን ተመራጭና እራሱ ቀነኒሳም ተፎካካሪ ተመራጭ በነበረበት በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ምርጫ ላይ ነበረ!!!
ቶኪዮ የራሱን አሻራ ጥሎ አልፏል።
ነገር ግን በወቅቱ ተመራጭ ነበረ
ከላይ በዘረዘርኩት መስፈርት ተጨምሮለት ቢመረጥ ኖሮ በቶኪዮ የተሻለም ይሮጥም ነበረ።

አሁንማ ለፓሪሱ ኦሊምፒክ
!!!
የማራቶን ምርጥ አትሌቶች፤የአለማችን የወቅቱ ምርጥ አትሌቶች በሚሳተፉበት በአለማችን ትልቁ በሆነው የለንደን ማራቶን በሰዓትም ይሁን በብቃት እንዲሁም በወጥ አቋም ከማንም በልጦና ተሽሎ እንዲሁም ማንንም አሳምኖ እጅ በአፍ ላይ አስጭኖ ጭምር በፈጣን ሰዓት በ41 አመቱ 2ኛ ሆኖ መጨረሱ እንዲሁም በለንደን ጥሩ ከሮጡ ቀነኒሳን በልጠው ለፓሪሱ ኦሊምፒክ ሊመረጡ ይችላሉ ተብለው ግምት ከተሰጣቸው ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተሽሎ በመገኘቱ ምክንያት ከሲሳይ ለማ ቀጥሎ ሁለተኛው ምርጡ የሀገራችን የፓሪስ ኦሊምፒክ ተመራጭ እንዲሆን አስችሎታል። አበቃ። አለቀ።

ብዙ ማውራት የማይወደው ዝምተኛውና እልኸኛው በስራ ብቻ የሚያምነው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለ2024 የፓሪሱ ኦሊምክ ድምፁን አጥፎቶ በሚገባ ሰርቶ ከእሱ የሚጠበቀውን በሙሉ አሟልቶ ከተፍካካሪዎቹ ተሽሎ መራጭ አካል የሚለውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኝ ይመስለኛል።

ቀነኒሳ በ2023 በቫሌንሽያ ማራቶን 2:04.19 የሮጠ ሲሆን በ2024 ለንደን ማራቶን ደግሞ 2:04.15 በመሮጥ በወጥ አቋም ጨርሷል።

እኔ በግሌ መርጬዋለሁ።
ይህን አቋሙንም በፓሪስ ኦሊምፒክ ደግሞት ለእራሱም ለሀገሩም ታሪክ እንደሚሰራ እኔ በግሌ ጥርጥር የለኝም።

የ41 አመቱ ቀነኒሳ በቀለ ከ1999 እስከ 2024 በ25 አመት የኢንተርናሽናል የሩጫ ላይ ቆይታው ባለፈው እሁድ በ2024 የለንደን ማራቶኑ ውድድር ጋ 200ኛ ኢንተርናሽናል ውድድሩን አድርጓል ።
ይህ ማለት በሚታወቅባቸው ዋና ዋናዎቹ ውድድሮቹ ስናይ

በ3000 ሜ 37 ጊዜ
5000 ሜ 56 ጊዜ
10,000 19 ጊዜ
ማራቶንን 16 ጊዜ ሮጦታል።
ቀሪ 72 ውድድሮችን በተለያየ ርቀት ሮጧል።

ይህን ከሀይሌ ጋር ስናነፃፅረው ሀይሌ ከ1991 እስከ 2015 የኢንተርናሽል ውድድር የ25 አመት ኢንተርናሽናል ውድድር ቆይታው 220 ውድድሮችን አድርጓል።
ሀይሌ
3000 ሜ 38 ጊዜ
5000ሜ 40 ጊዜ
10,000ሜ 28 ጊዜ
ማራቶን 15 ጊዜ ሮጧል።
ቀሪ 79 ውድድሮችን በተለያየ ርቀት ሮጧል።

በኢንተርናሽናል ውድድር ቆይታ ቀነኒሳ የሀሌን
የ25አመት ቆይታን ክብረወሰን ተጋርቷል።
ብዙ በመሮጥ ሀይሌ የተሻለ ሲሆን
በኦሊምክ
በአለምሻምፒዮና
በሀገር አቋራጭ ውድድሮች እንዲሁም በየርቀቱ ፈጣን ሰዓቶችን በመሮጥ ቀነኒሳ የተሻለ ታሪክ አለው።

መልካም እድል ለጀግናው እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቡድን!!!

ጠንካራው አትሌት ሲሳይ ለማ የታዋቂው የማራቶን አትሌት ፀጋዬ ከበደን ክብረወሰን ለመጋራት አንድ የማራቶን ሩጫ ብቻ ቀረው!!!57 ኪሎ የሚመዝነው 33አመት ከ129 ቀን የሆነው ሲሳይ ለማ የአ...
04/19/2024

ጠንካራው አትሌት ሲሳይ ለማ የታዋቂው የማራቶን አትሌት ፀጋዬ ከበደን ክብረወሰን ለመጋራት አንድ የማራቶን ሩጫ ብቻ ቀረው!!!

57 ኪሎ የሚመዝነው 33አመት ከ129 ቀን የሆነው ሲሳይ ለማ የአሯሯጥ ስታይሉ በጣም ከሚማርክኝ አትሌቶች አንዱ ነው
1ሜ ከ70 ሳ ሜ ቁመት ያለው ሲሳይ ሰውነቱም ሆነ ቁመናው ለእግርኳስና ለቦክስ ቅርብ እንጂ የማራቶን ሯጭ አይመስልም!!

የሩጫን ዲስፕሊን በሚገባ ያከበረው
የማራቶን ሯጭ !!!
ሲሳይ ለማ!!!
አትሌት ከተማ ውስጥ በጭራሽ መቀመጥ የለበትም በማለት ቤቱን ከ6አመት በፊት ሽጦ ከአዲስ አበበ የወጣው አትሌት ሲሳይ ለማ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ውጤታማነቱን በተደጋጋሚ አሳየ!!!

በኢትዮጵያ የማራቶን ታሪክ ውስጥ በወንዶች ብዙ ማራቶኖችን በመሮጥ ፀጋዬ ከበደ ይመራል!!

ፀጋዬ ከበደ ከ2007 እሰከ 2023 በአስራ አራት አመት የማራቶን ሩጫ ታሪኩ ውስጥ 27 ማራቶኖችን ሮጧል።

ፀጋዬ በ14 አመት የማራቶን ቆይታው በአሰልጣኝ ጌታነህ ተሰማ እየሰለጠነ በኦሊምፒክና በአለም ሻምፒዮና ሜዳሊስ ት ሲሆን እንዲሁም በሜጀር ማራቶኖች ውጤታማ ነበር በሜጀር ማራቶንም የዙር ውድድሩንም በማሸነፍ ከፍተኛውን የገንዘብ ተከፋይ ነበረ!!

ከፀጋዬ ከበደ በመቀጠል አትሌት ሲሳይ ለማ ከ2012 እሰከ 2024 በ12 አመት የማራቶን ቆይታው እስከ 2017 በአስልጣኝ ይረፉ ብርሀኑ ከ2018 ጀመሮ ደግሞ በአሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ሰልጥኗል።

ሲሳይ ለማ በ12 አመት የማራቶን ቆይታው 26 ማራቶኖችን የሮጠ ሲሆን ከእነዚህ ማራቶኖች ውስጥ
10 ጊዜ 1ኛ
3 ጊዜ 2ኛ
5ጊዜ 3ኛ በመሆን ውጤታማነቱን አሳይቷል።

ፀጋዬ ከበደ ለንደደንን 2 ጊዜ ችካጎን አንድ ጊዜ በማሸነፍ በሜጀር 3ጊዜ አንደኛ በመሆን የተሻለ ሲሆን
ሲሳይ ለንደንን አንድ ጊዜ ቦስተንን አንድ ጊዜ አሸንፏል።
ሲሳይ ለማ እንደ ፀጋዬ ከበደ የሜጀር ማራቶንን የዙሩ አሸናፊ አይሁን እንጂ በሜጀር ማራቶኖች 2ኛ ና 3ኛ ደረጃን በማግኘት ከፀጋዬ ከበደ ተመሳሳይ ታሪክ አለው ።
ከውድድር ታሪኮቹ ተነስቼ ወቅታዊ አቋምን ተመልክቼ ሲሳይ ለማን በፓሪስ ኦሊምፒክ ተመራጭ አድርጌዋለሁ ሲሳይ በቦስተን ማሸነፍ አይደለም 4ኛም ቢወጣ ካለው ወጥ አቋም የእኔ የፓሪስ ኦሊምፒክ ተመራጭ ነው።

ሲሳይ ለማ የፀጋዬን ከበደን ክብረወሰን በቁጥር ደረጃ ሊያሟላ አንድ ውድድር ይቀረዋል። በሀገር ውክልና ደረጃ ፀጋዬ ከበደ በኦሊምፒክም በአለም ሻምፒዮናም ሜዳሊስት ስለሆነ ሲሳይ ሁለቱን ካሟላ በኢትዮጵያ ታሪክ በማራቶን ባለ አዲስ ታሪክ ይሆናል!!

በጣም የሚገርው ሲሳይ ለማ የቦስተን ማራቶን በ2017 አቋረጠ
እንደገናም በቦስን ማራቶን በ2019 ሮጦ 30ኛ ወጣ!
በቦስተን ተስፋ ያልቆረጡት ሲሳይ፤ ገመዶና ፤ከሊል ፤ በ2024 በቦስተን ማራቶን ነገሱበት!!!

ምን ይታወቃል ?
በቶኪዮ ያቋረጠው ሲሳይ
በማራቶን ያቋረጠባቸውን ውድድሮች የሚበቀልበት ዘመን ይሆን?

በጣም የሚገርመው ማራቶንን ብዙ በመሮጥ ከኢትዮጵያ የሚመሩት ሁለቱ አትሌቶች ማለትም ፀጋዬ ከበደና ሲሳይ ለማ ሁለቱም የሰንዳፋ ዙሪያ ልጆች መሆናቸው ነው!!!

ፎቶውን ከአፍሪካ ዮናይትድና ከለንደን ማራቶን ተጠቅመናል!!

ጠፍተሀል ላላችሁኝ ተከታታዮቼ በሙሉ የከበረ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ!!አዎ ጠፍቻለሁምክንያት 1ኛ  ስፅፍ በሞባይ ስለምጠቀም በፊት የጤፍ ላይ አሻራ አነብ ነበረ አሁን ግን የመነፅር ...
04/19/2024

ጠፍተሀል ላላችሁኝ ተከታታዮቼ በሙሉ
የከበረ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ!!

አዎ ጠፍቻለሁ

ምክንያት
1ኛ ስፅፍ በሞባይ ስለምጠቀም በፊት የጤፍ ላይ አሻራ አነብ ነበረ
አሁን ግን የመነፅር ተጠቃሚ ሆኜ ለተወሰነ ጊዜም ከሀኪም እረፍት ታዞልኝ ሲሆን ሁለተኛው እንደ አለፉት ዘመናት ሰፊ ጊዜ የለኝም ቶሎ ቶሎ አልከሰትም ይህ ማለት እተዋለሁ ማለት አይደለም

ሁኔታዎችን አስተካክዬ አልፎ አልፎ በመፀፍ እንዲሁም በሰፌው በዩቱብ ለመከሰት እቅድ አለኝ፤
ከዚህምም አልፎ ደግሞ ምኞት አይከለከልም አይደል? ወደ ፊት ሩጫ ብቻ የሚያወራ ሬድዮም ይሁን ቲቪም አስባለው ይሄ ቀላል እንዳልሆ ባውቅም ከፈጣሪና ከእናተ ጋር ሆኜ ወደፊት እሞክራለሁና በፀሎታችሁ አስቡኝ
እንጂ ከሩጫ ማንም አይለየኝም።
አመሰግናለሁ!!

👉 በፓሪስ  ኦሊምፒክ የሴት ማራቶን ቡድናችንን የሚቋቋም ሀገር ያለ አይመስለኝም!!!
04/14/2024

👉 በፓሪስ ኦሊምፒክ የሴት ማራቶን ቡድናችንን የሚቋቋም ሀገር ያለ አይመስለኝም!!!

የ21ኛ ዙር ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ. የሩጫ አሽናፊዎች!!1ኛ ጉተኒ ሻንቆ2ተኛ በርነሽ ደሴ3ተኛ መቅደስ ሽመልስ
03/17/2024

የ21ኛ ዙር ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ. የሩጫ አሽናፊዎች!!

1ኛ ጉተኒ ሻንቆ

2ተኛ በርነሽ ደሴ

3ተኛ መቅደስ ሽመልስ

ለሩጫ ቤተሰቦች!!የወቅቱ ምርቃቴ! "እንደ ገመዶ ደደፎና ከሊል አማን  የማሰልጠን ብቃት ፤ አዲሱ አመት 2024 ህይወታችሁ የተቀየረ እንዲሆን ምኞቴ ነው!!"ጠፋህ ብላችሁ በውስጥ መስመር አክ...
12/03/2023

ለሩጫ ቤተሰቦች!!

የወቅቱ ምርቃቴ!

"እንደ ገመዶ ደደፎና ከሊል አማን የማሰልጠን ብቃት ፤ አዲሱ አመት 2024 ህይወታችሁ የተቀየረ እንዲሆን ምኞቴ ነው!!"

ጠፋህ ብላችሁ በውስጥ መስመር አክብራችሁ ለጠየቃችሁኝ በሙሉ
ክብረት ይስጥልኝ አመሰግናለሁ !!

የጠፋሁት በግል ጉዳይ ምክንያት ቢሆንም
በሩጫውም ቢሆን በተለይ በማራቶኑ ትግስት አሰፋ 2:11 ከሮጠች በኋላ እንኳን እኔ አሰልጣኞቹ ሁሉ የሉም እኮ!!

እሩቅ ስለሆንኩ ወሬው እየተዛባ ይደርሰኛል መሰል አሰልጣኞቹ ሁሉ ኦሊምፒክም ስለደረሰ ወንዶች አትሌቶቻቸውን ለ2:10 እንዲሮጡ እያዘጋጁ ሲሉኝ ተስፋ መቁረጥ ውስጤ ገብቶ እደመደናገጥም ገጥሞኝ ከግል ጉዳይ ጋር ተደማምሮ ጠፍቼ ነበረ

ቀነኒሳ ቫሌንሽያ ይሮጣል ሲሉኝ ሌላው ይቅር ቀነኒሳማ ለ2:10 አይዘጋጅም
ባይሆን አስደንጋጭ ሰዓት ሮጦ አዲስ ህግ እንደ ቶኪዮው 35 ባይሆንም 36 ያስመጣብን ይሆናል የሚል ስጋትም ፈጥሮብኝ ነበረ
ዛሬ አትሌት ሲሳይ ለማ 2:01፡48 ገባ ሲሉኝ ከላይ ሰዎች ሩቅ ነው ብለው ያወሩልኝን ወሬ በሙሉ ከንቱ አድርጎ ልቤን
በስሱም ቢሆን መለስ አድርጎት ተመልሻለሁ።

ቀነኒሳ በ2019 በርሊን 2:01.41 ሮጦ ነበረ ዛሬ ደግሞ ሲሳይ ለማ 2:02 በታች የገባ ከቀነኒሳ ቀጥሎ ሌላኛው 2ኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆኗል ማለት ነው።

📍ሲሳይ ዛሬ በቫሌንሽያ ያስመዘገው የማራቶን ሰዓት የዓለማችን የምንግዜም 4ኛው ፈጣን ሰዓት ሲሆን ከኢትዮጵያ 2ኛው ፈጣን ሰዓት ሆኗል።
በደረጃው 1ኛና2ኛ ኬኒያዊያን ሲሆኑ 3ኛ ቀነኒሳ 4ኛ ሲሳይ ሆኗል።
በማራቶን ከመቶ የአለማችን ፈጣን ሰአት ካላቸው አትሌቶች ውስጥ
47 ኬኒያ
43 ኢትዮጵያ
1 ታንዛኒያ አትሌቶች ይገኙበታል።

ለአሰልጣኝ ገመዶ ደደፎና ከሊል አማን የተሳካ አመት ነበረ
በአማኔ
በታምራት
በትዕግስት
በሲሳይና በሌሎችም በወጣቶቹም በትልልቆቹም አትሌቶቹ እያስመዘገባቸው ያለው ውጤቶቹ እጅ በአፍ አስጭነው የሚያስገረሙ ውጤቶች ናቸው።
የገመዶንና የከሊልን የማሰልጠን ብቃት አድንቀን ውጤቶቹም ቀጣይነት እንዲኖራቸው በመመኘት ጭምር አደራ በመስጠት እዚህ ላይ እንቋጫለን!!

TOP RESULTS MEN MARATHON
1 LEMMA, SISAY 2:01:48
2 MUTISO, ALEXANDER2:03:11
3 WOLDE, DAWIT2:03:48
4 BEKELE, KENENISA 2:04:19
5 GEAY, GABRIEL
2:04:33
6
KANDIE, KIBIWOTT
2:04:48
7
DESO, CHALU
2:05:14
8
ESA HUSEYDIN, MOHAMED
2:05:40
9
FRERE, MEHDI
2:05:43
10
AYALE, GASHAU
2:05:46
11
NOVALES, TARIKU
2:05:48
12
KINDIE, DERSEH
2:05:51
13
AMARE, GIRMAW
2:05:52
14
NAVARRO, NICO
2:05:53
15
ALAME, HAIMRO
2:06:04
16
BOUR, Felix
2:06:46
17
MORHAD, AMDOUNI
2:06:55
18
Davlatov, Shokhrukh
2:07:02
19
RINGER, RICHARD
2:07:05
20
KIPRUTO, TITUS
2:07:22
21
CRIPPA, Nekagenet
2:07:35
22
Barata, Samuel
2:07:35
23
CHOUKOUD, KHALID
2:07:37
24
MPOFU, ISAAC
2:07:39
25
Gonzalez Mindez, Alberto
2:07:40

TOP RESULTS WOMEN MARATHON

1 DEGEFA, WORKNESH2:15:51
2 AYANA, ALMAZ
2:16:22
3 GEBREKIDAN, HIWOT 2:17:59
4 CHEPCHIRCHIR, CELESTINE
2:20:46
5 MAAYOUF, MAJIDA 2:21:27
6 HAYDAR, SULTAN 2:21:27
7 MOKONIN, DESI
2:22:29
8
Gregson, Genevieve
2:23:08
9
YAREMCHUK, SOFIIA
2:23:16
10
Batt-Doyle, Isobel
2:23:27
11
STEYN, GERDA
2:24:03
12
CHELIMO, JOAN
2:24:16
13
WEIGHTMAN, LISA
2:24:18
14
Schlumpf, Fabienne
2:24:30
15
Hottenrott, Laura
2:24:32
16
Richardsson, Camilla
2:24:38
17
WOLDU, Mekdes
2:24:44
18
Ortiz Morocho, Silvia Patricia
2:24:50
19
Mélody, JULIEN
2:25:01
20
Evans, Clara
2:25:04
21
Partridge, Lily
2:25:12
22
OUHADDOU, FATIMA AZAHARAA
2:25:30
23
LUENGO, LAURA
2:25:35
24
DA SILVA GODINHO, Susana Cristina
2:25:35
25
Stewartová, Moira
2:25:36

👉 መልክናት ዉዱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ የ23ኛው የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር በሴቶች ዘርፍ አሸናፊ ሆናለች!!  መገርቱ አለሙ ሁለተኛ ደረጃ ስታጠናቅቅ ፤ ተኪኔ አማር ...
11/19/2023

👉 መልክናት ዉዱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ የ23ኛው የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር በሴቶች ዘርፍ አሸናፊ ሆናለች!!

መገርቱ አለሙ ሁለተኛ ደረጃ

ስታጠናቅቅ ፤ ተኪኔ አማር ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

በወንዶች

1ኛ ቢኒያም መሀሪ

2ኛ ዘነበ አየለ

3ኛ ጅራ ለሊሳ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡




11/05/2023

የኒዩርክ ማራቶንን ኢትዮጵያዊው አትሌት አሸነፈ!!

የ2023 የኒዩርክ ማራቶንን ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ ተፎካካሪዎቹን በብቃት አሸንፏል።

በሴቶች ኬኒያዊቷ ኦብሪ ስታሸንፍ ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ሆናለች።

Men's

1.Tamirat Tola 2:04:58

2.Albert Korir 2:06:57

3.Shura Kitata 2:07:11

4.Abdi Nageeye 2:10:21

1st, 2:27:23

Hellen Obiri

2023 New York marathon.

Women's Results

1.Hellen Obiri 2:27:23

2.Letensebet Gidey 2:27:29

3.Sharon Lokedi 2:27:33

4.Brigid Kosgey 2:27:45

5.Mary Ngugi 2:27:53

6.Viola Cheptoo 2:28:11

7.Edna Kiplagat 2:29:40

10/29/2023

👉 የቻይና ቤጂንግ ማራቶንን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ!!!🇪🇹🇪🇹
👉 በቻይና ቤጂንግ በተካሄደ የ2023 ማራቶንን አትሌት #ኡልፈታ ዴሬሳ ገለታ አሸንፏል።
በውድድሩ በዴሬሳ በአጨራረስ ተበልጦ ሁለተኛ የወጣው የሀገሩ ልጅ አትሌት ይሁንልኝ አዳነ ሲሆን የኬኒያ አትሌት 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።

10/22/2023

👉 የሳምንቱ የአትሌትክስ ውጤቶች!!

👉 በስፔን ቫሌንሽያ በተካሄደ የ2023 የቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን ኬኒያዊው ፤
ኪቢወት ካንዲ 57:40 በመሮጥ ሲያሸንፍ ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ 57:41 በመሮጥ ሁለተኛ ሀጎስ 57:41 ሶስተኛ ሰለሞን ባረጋ 57:50 4ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
👉 ኢትዮጵያዊያኖቹ ዮሚፍና ሀጎስ የሮጡት ሰዓት የምንግዜም የሀገራችን ክብረወሰን ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ይህ ሰዓት የዓለማችን ፈጣኑ 4ኛ ሰዓት ሆኖም ተመዝግቧል።

👉 በግማሽ ማራቶን 100 የዓለማችን ፈጣን አትሌቶች ውስጥ 67 ኬኒያዊያን ሲኖሩ ከኢትዮጵያ 27 ከኡጋንዳ 2 አሉ።

👉በሴቶች ኬኒያዊያን ከ1ኛ እስከ3ኛ ተከታትለው በመግባት ሲያሸንፉ ኢትዮጵያዊያኖቹ ጎቲቶምና ትዕግስት 4ኛና 5ኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

👉 በጣሊያን ቬኒስ በተካሄደ የማራቶን ውድድር በሴቶች ኬኒያዊት አትሌት ስታሸንፍ ኢትዮጵያዊያኖቹ ጫላ እና ትዕግስት በዳኔ 2ኛና 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል።
በወንዶች ስፔናዊ አትሌት አሸንፏል።

በስፔን ቢልባኦ በተካሄደ ማራቶን በሴቶች ኬኒያዊት አትሌት ስታሸንፍ ኢትዮጵያዊያኑ ትዕግስት አያሌውና አየሁ ቢተው 2ኛና 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል በሴቶች በወንዶች ኬኒያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።

▪VALENCIA HALF MARATHON

1.Kibiwott Kandie 57:40 🇰🇪

2.Hagod Gebrhiwet 57:41 🇪🇹

3.Yomif Kejelcha 57:41 🇪🇹

4.Solomon Barega 57:50 🇪🇹

Women Results.

1.Margaret Chelimo 64:46 🇰🇪

2.Irene Cheptai 64:53 🇰🇪

3.Janet Chepngetich 65:15 🇰🇪

4.Gebreslase Gotytom 66:12 🇪🇹

5.Gezahgn Tigist 66:20 🇪🇹

▪VENICE MARATHON

WOMEN.

1.Rebbeca Tanui 2:25:35 🇰🇪

2.Chala Kebene 2:26:37 🇪🇹

3 Tigist Bedada 2:28:05 🇪🇹

4.Shamilah Tekaa 2:28:13 🇰🇪

5.Dekebo Muliye 2:32:09 🇪🇹

▪ BILBAO NIGHT HALF MARATHON

MEN'S RESULTS

1.Ayub Kiptum 60:34 🇰🇪

2.Peter Mwaniki 60:40 🇰🇪

3.Ali Chebures 61:19 🇺🇬

WOMEN'S RESULTS

1.Nelly Jeptoo 71:25 🇰🇪

2.Tegest Ayelew 71:26 🇪🇹

3.Ayehu Bitew 71:33 🇪🇹

VALENCIA HALF MARATHON2023
VENICE MARATHON 2023
BILBAO NIGHT HALF MARATHON 2023

በህንድና በሆላንድ በተካሄዱ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ኢትዮጵያዊቷያን ሴት አትሌቶች አሸነፉ!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹በህንድ ዴሊ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና አሸንፋለች!!በሆላድ...
10/15/2023

በህንድና በሆላንድ በተካሄዱ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ኢትዮጵያዊቷያን ሴት አትሌቶች አሸነፉ!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በህንድ ዴሊ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና አሸንፋለች!!
በሆላድ የአመስተርዳም ማራቶንን ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ መሰረት በለጠ አሸንፋለች!!!

TOP RESULTS WOMEN HALF MARATHON
1. Almaz Ayana (ETH) 67:582. Stella Chesang (UGA) 68:283. Viola Chepngeno (KEN) 69:094. Aberash Minsewo (ETH) 69:505. Vivian Cheriyot (KEN) 71:266. Anchinalu Dessie (ETH) 71:347. Bertukan Welde (ETH) 72:008. Mare Dibaba (ETH) 72:029. Betelihen Afenigus (ETH) 72:2510. Nurit Ahmed (ETH) 77:26

TOP RESULTS MEN HALF MARATHON
1. Daniel Ebenyo (KEN) 59:272. Charles Matata (KEN) 60:053. Addisu Gobena (ETH) 60:514. Isaac Kipkemboi (KEN) 60:525. Isaia Lasoi (KEN) 60:556. Leonard Barsoton (KEN) 61:367. Roncer Konga (KEN) 62:058. Vincent Kimaiyo (KEN) 63:189. Gideon Kiprotich Rop (KEN) 63:5110. Abhishek Pal (IND) 64:07

Amsterdam

TOP RESULTS WOMEN MARATHON
1. Meseret Belete - 2:18:192. Meseret Abebayehu - 2:19:473. Dorcas Tuitoek - 2:20:004. Ashete Bekere - 2:21:505. Anchalem Haymanot - 2:22:216. Meseret Gola - 2:14:297. Sofia Assefa - 2:23:318. Marion Kibor - 2:24:259. Anne Luijten - 2:26:3510. Meline Rollin - 2:26:55

TOP RESULTS MEN MARATHON
1. Joshua Belet (KEN) - 2:04:182. Cybrian Kotut - 2:04:333. Bethwel Chumba - 2:04:354. Birhanu Legese (ETH) - 2:04:435. Lemi Berhanu (EST) - 2:05:476. Bazezew Asmare (ETH) - 2:06:337. Mulugeta Debasu - 2:06:338. Haymanot Alew - 2:08:239. Abderrazak Charik - 2:08:3510. Khalid Choukoud - 2:08:36

Photo፦ TCS Amsterdam Marathon2023 &
2023 Vedanta Delhi Half Marathon,

"በሁለተኛ ማራቶኗ ሁለተኛውን የዓለማችንን ፈጣን ሰዓት ያስመወገበች፤በሁሉ ርቀት፤ጀግና ቆራጥ የሆነች ፤የምትገርም የምትደንቅ ምርጥ የዓለማችን  ዕንቁ አትሌት  ሲፋን ሀሰን !!"በስፖርቱ ላይ...
10/09/2023

"በሁለተኛ ማራቶኗ ሁለተኛውን የዓለማችንን ፈጣን ሰዓት ያስመወገበች፤

በሁሉ ርቀት፤

ጀግና ቆራጥ የሆነች ፤

የምትገርም የምትደንቅ ምርጥ የዓለማችን ዕንቁ አትሌት ሲፋን ሀሰን !!"

በስፖርቱ ላይ ለረጅም አመታት ላሳየችው ድንቅ ብቃት ምን የሚል ስያሜ እንስጣት?

📍በሮጠችባቸው ርቀቶች በዓለም ያላት የፈጣን ሰዓት ደረጃ ስንመለከት ይገርማል!

✔️1500ሜ 3:51,95 የዓለማችን 7ኛ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነች NR

✔️አንድ ማይል 4:12,33 የዓለማችን 2ኛ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነች NR

✔️3000ሜ 8:18,19 የዓለማችን 4ኛ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነች NR

✔️5000 ሜ 14:13,42 የዓለማችን 9ኛ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነች NR

✔️ 5ኪ ሜ 14:44 የዓለማችን 15ኛ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነች NR

✔️ 10,000ሜ የዓለማችን 2ኛ ፈጣን ሰዓት ባለቤት NR

✔️ ግማሽ ማራቶን 1:05,15 የዓለማችን 19ኛ ፈጣን ሰዓት ባለቤት NR

✔️ ማራቶን 2:13,44 የዓለማችን 2ኛ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነች NR

👉 እያንዳንዱን 5ኪ ሜ የሄደበት ሰዓት ዝቅተኛ የሚባለው 20ኛው ኪሎ ሜ ላይ 14:30ፈጣኑ ደግሞ 35ኛው ኪ ሜ ላይ 13:51 ይገርማል!!!👉 ይሄን ሳያዩ ሩጫ ያቆሙ እድለኞች ናቸው!!
10/08/2023

👉 እያንዳንዱን 5ኪ ሜ የሄደበት ሰዓት ዝቅተኛ የሚባለው 20ኛው ኪሎ ሜ ላይ 14:30
ፈጣኑ ደግሞ 35ኛው ኪ ሜ ላይ 13:51 ይገርማል!!!
👉 ይሄን ሳያዩ ሩጫ ያቆሙ እድለኞች ናቸው!!

የወንዶች ማራቶን ክብረወሰን ጉዳይ ለአንዴዬና ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተዘጋ ይመስለኛል። ከእንግዲህ ለማሸነፍ ብቻ ወይም ከቲጂ ፊት እንጂ ኋላ  አታርገኝ እያሉ በፀሎት መንፈስ ሆኖ...
10/08/2023

የወንዶች ማራቶን ክብረወሰን ጉዳይ ለአንዴዬና ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተዘጋ ይመስለኛል። ከእንግዲህ ለማሸነፍ ብቻ ወይም ከቲጂ ፊት እንጂ ኋላ አታርገኝ እያሉ በፀሎት መንፈስ ሆኖ መሮጥ እንጂ የክብረወሰን ጉዳይ አሁን ባሉ የኢትዮጵያ ወንድ አትሌቶች አይታሰብም።

የሴቶች ማራቶን ጉዳይም ቢሆን ፋይሉ ማንም የማይነካው ይመስላል።
ምን አልባት ወደ ፊት በእኔ እይታ ኬኒያዊቷ ፌዝ ጤና ሆና በሩጫ ከቆየች የሷ አሯሯጥና የእግር አጣጣል ዝላይ የሌለውና ለጎዳና ላይ ሩጫ ምቹ የሚመስል ስለሚመስል ከሷ ውጪ ያሉ በአሁን ዘመን ባሉ የዓማችን አትሌቶች አሯሯጥ የሚደፈር አይመስኝም።

TOP RESULTS MEN MARATHON
1 Kiptum, Kelvin (KEN) - 2:00:35 (World Record)2 Kipruto, Benson (KEN) - 2:04:023 Abdi, Bashir (BEL) - 2:04:324 Korir, John (KEN) - 2:05:095 Tura Abdiwak, Seifu (ETH) - 2:05:296 Mantz, Conner (USA) - 2:07:477 Young, Clayton (USA) - 2:08:008 Rupp, Galen (USA) - 2:08:489 Chelanga, Sam (USA) - 2:08:5010 Ichida, Takashi (JPN) - 2:08:5711 Shrader, Brian (USA) - 2:09:4612 Kiptoo, Wesley (KEN) - 2:10:2813 McDonald, Matt (USA - )2:10:3414 Reichow, Joel (USA) - 2:10:3715 Colley, Andrew (USA) - 2:11:2216 Salvano, Kevin (USA) - 2:11:2617 Wolde, Dawit (ETH) - 2:11:33

TOP RESULTS WOMEN MARATHON
1. Hassan, Sifan (NED) - 2:13:442. Chepngetich, Ruth (KEN) - 2:15:373. Alemu, Megertu (ETH) - 2:17:094. Jepkosgei, Joyciline (KEN) - 2:17:235. Teshome Nare, Tadu (ETH) - 2:20:046. Dibaba Keneni, Genzebe (ETH) - 2:21:477. Sisson, Emily (USA) - 2:22:098. Seidel, Molly (USA) - 2:23:079. Harvey, Rose (GBR) - 2:23:2110. Vaughn, Sara (USA) - 2:23:2411. Rooker, Gabriella (USA) - 2:24:3512. Lindwurm, Dakotah (USA) - 2:24:4013. Bates, Emma (USA) - 2:25:0414. Van Ord, Tristin (USA) - 2:25:5815. Kebede, Sutume Asefa (ETH) - 2:26:4916. Scott, Dominique (RSA) - 2:27:3117. Linden, Desiree (USA) - 2:27:3518. Montoya, Maggie (USA) - 2:28:2219. Delanis, Emeline (FRA) - 2:31:29

10/08/2023

ሰበረው!!
ኬኒያዊው የ23 አመት ወጣት ኬልቪን ኪፕተም ነው 2:00.35 በመሮጥ ክብረወሰኑን ያሻሻለው
2023 CHICAGO MARATHON

2023 ችካጎ ማራቶን ለሚሳተፉ አትሌቶች በሙሉ መልካም እድል!!!
10/07/2023

2023 ችካጎ ማራቶን ለሚሳተፉ አትሌቶች በሙሉ መልካም እድል!!!

👉 ክብረወሰን በኢትዮጵያዊት አትሌት ተሻሻለ!!!👍ለመጀመሪያ ጊዜ በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር  ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በተለያየ ርቀት የሻፒዮናው አሸናፊ ሆነዋል!!~...
10/01/2023

👉 ክብረወሰን በኢትዮጵያዊት አትሌት ተሻሻለ!!!👍

ለመጀመሪያ ጊዜ በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በተለያየ ርቀት የሻፒዮናው አሸናፊ ሆነዋል!!
~~~~
በሴቶች አንድ ማይል
ድርቤ ወልተጂ በ4:21.00 በሆነ ሰዓት የዓለምን ክብረወሰን በማሻሻል 1ኛ ስትወጣ፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ 4:23.06 በመሮጥ 2ኛ ሆና ጨርሳለች።

በ5ኪ ሜ ወንዶች

12:59 CR ሀጎስ ገ/ህይወት አንደኛ ሲሆን
13:02 ዮሚፍ ቀጀልቻ ሁለተኛ ሆኗል።

5ኪ.ሜ ሴቶች

14:40 SB እጅጋየሁ ታዬ 3ተኛ
14:41 PB መዲና ኢሳ 4ተኛ
በመሆን ዉድድሩን አጠናቀዋል።

በሴቶች ግማሽ ማራቶን
1:07:50 ፅጌ ገ/ሰላማ 4ኛ
1:08:31 ፍታው ዘራይ 6ኛ

ግማሽ ማራቶን ወንዶች

59:22 ጀማል ይመር 4ኛ
1:00:11 ንብረት መላክ 7ኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

ሁለቱ የማራቶን ባለክብረወሰኖች!!!ኢሉድ ኪፕቾጌ 🇰🇪 2:01.09  WRትዕግስት አሰፋ 🇪🇹  2:11.51  WR'ትዕግስት እግዚአብሔር ይስጥሽ!'ያንቺ እንዲህ መሮጥ  ተፅእኖው ከባድ ነው።ለው...
09/25/2023

ሁለቱ የማራቶን ባለክብረወሰኖች!!!

ኢሉድ ኪፕቾጌ 🇰🇪 2:01.09 WR
ትዕግስት አሰፋ 🇪🇹 2:11.51 WR

'ትዕግስት እግዚአብሔር ይስጥሽ!'
ያንቺ እንዲህ መሮጥ ተፅእኖው ከባድ ነው።
ለውጥም አለው።

ዛሬ ጠዋት ማራቶን ልሮጥ ብዬ ፔሱን 2:11 በታች አድርጌ ጀመርኩት ስሮጥም በውስጤ ቲጂ መጣች ቲጂ መጣችብኝ እያልኩ እያሰብኩሽ 5 ኪ ሜ አካባቢ እንደደረስኩ ሁኔታውን ሳየው ሰዓቱ 2:12:30 ሊሆንብኝ ሆነ ደረቴ እና ጎን እና ጎኔንም በተደጋጋሚ ወጋኝ ግን ከግማሽ ማራቶን በኋላ ህመሙ ከለቀቀኝ ፔሱን አፍጥኜ 2:11 በታች ሰዓቱን አመጣዋለሁ ብዬ ብቀጥልም ህመሙን ስላልቻልኩ አቋረጥኩ።

ቲጂ !
ያቋረጥኩት 2:11:53 በላይ ይሆንብኛል ብዬ ሳይሆን አሞኝ ነው እሺ!!

እግዜር ይስጥሽ ከእኔም ጨምሮ የሁሉንም ህልም 2:11 በታች አደረግሽው።



መሮጥ አትችይም የተባለችው አትሌት  #ክብረወሰን አሻሻለች !!
09/24/2023

መሮጥ አትችይም የተባለችው አትሌት #ክብረወሰን አሻሻለች !!

ክብረወሰን በጀርመን በርሊን ተሻሽሏል!!!👉 ክብረወሰኑ ሊያስጠይቃትም  ይችላል ተብሏል!! ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ ነች የአለም የማራቶኑን ክብረወሰን ያሻሻለችው አትሌቷ በኬኒያዊቷ ...
09/24/2023

ክብረወሰን በጀርመን በርሊን ተሻሽሏል!!!
👉 ክብረወሰኑ ሊያስጠይቃትም ይችላል ተብሏል!!

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ ነች የአለም የማራቶኑን ክብረወሰን ያሻሻለችው አትሌቷ በኬኒያዊቷ Brigid KOSGEI በ13 Oct 2019 2:14:04 ተይዞ የነበረውን ሰዓት ከሁለት ደቂቃ በላይ በማሻሻል ነው በበሪሊን 2:11.53 በመሮጥ ያሻሻለችው።

አትሌቷ በ2022 በፈጣን ሰዓት የኢትዮጵያን ክብረወሰን አሻሽላ በበሪሊን ማሸነፏ የሚታወሰ ነው።
በወቅቱ የሮጠችው 2:15.37 ሰዓት እጅግ በጣም ብዙዎችን አስገርሞ
ደግማ ትሮጥ ይሆን?ያስባለ ነበረ
አትሌቷም
ደግማ በመሮጥ
ክብረወሰኑንም ጭምር በማሻሻል
"ዝም በሉ ብላለች"።

ሰዓቱ ይገርማል !
ወንዶቹ 2:14 ሮጠው አሸንፈው ከደስታቸው ብዛት በሚደንሱበት ዘመን ላይ
ትግስት 2:11 ቤት መሮጧ
ትንሽ የወንዶቹን ሞራል ያልጠበቀና ያላገናዘበ ምንልባትም የወንዶች ማራቶንን ከ2:10 በላይ የሮጡ መብት ተከራካሪ ቢኖር ሊያስጠይቅ የሚችል ሰዓት ነው የሮጠችው።

አብረዋት ልምምድ የሚሰሩ የወንድ አትሌቶችም ቢሆኑ ከአሁን በኋላ ትግስትን በፈገግታ ሳይሆን በግልምጫ የሚያዩበት ሁኔታ ነው የሚፈጠረው።

👉 ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን በአለም ያላትን ደረጃ ስንመለከት
ከመቶ የአለማችን ፈጣን የማራቶን ሴት አትሌቶች ውስጥ
40 ኢትዮጵያዊያን
30 ኬኒያዊያን
6 ጃፓናዊያን በመሆን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ከ200 የአለማችን ፈጣን የማራቶን አትሌቶች ስናይ ደግሞ
83 ኢትዮጵያዊያን
55 ኬኒያ
20 ጃፓናዊያን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረውታል።

ሰዓቶቹን ስንመለከት በሴቶች ማራቶን ከአለም የተሻልን ነን።

ይህ ክብረወሰን እመኑኝ በቀላል የሚሻሻል አይሆንም።


የ5000ሜ ክብረወሰን ተሻሻለ!!ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋዬ በአሜሪካ ዮውጂን በተካሄደ የ2023 ዳይመንድ ሊግ 14:00.21 በመረጥ አሻሽላዋለች።
09/17/2023

የ5000ሜ ክብረወሰን ተሻሻለ!!
ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋዬ በአሜሪካ ዮውጂን በተካሄደ የ2023 ዳይመንድ ሊግ 14:00.21 በመረጥ አሻሽላዋለች።






📍 የዓመቱ የ2023 የመጨረሻው  ዳይመንድ ሊግ በአሜሪካ ዮጂን  ዛሬና ነገ ፍፃሜውን  ያገኛል በዚህም መሰረት የዛሬ የኢትዮጽያዊያን አትሌቶች ውጤት! በ3000ሜ መሰናክል ወንዶች ሳሙኤል ፍሬ...
09/17/2023

📍 የዓመቱ የ2023 የመጨረሻው ዳይመንድ ሊግ
በአሜሪካ ዮጂን ዛሬና ነገ ፍፃሜውን ያገኛል በዚህም መሰረት የዛሬ የኢትዮጽያዊያን አትሌቶች ውጤት!
በ3000ሜ መሰናክል ወንዶች ሳሙኤል ፍሬው 2ኛ ጌትነት 4ኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል።
1500 ሴ ድርቤ ወልተጂ 2ኛ ብርቄ 4ኛ ሆነው ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

09/11/2023

እንኳን ለ2016 ለአዲሱ አመት በጤና አደረሳችሁ!
አዲሱ አመት የሰላምና፣ የፍቅር አመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!
መልካም አዲስ አመት!!
Ethio runners

በእንግሊዝ ግሬት ኖርዝ  ረን  ኢትዮጵያዊው አትሌት አሸነፈ!!!  በእንግሊዝ ግሬት ኖርዝ  ረን የ 21 ኪሜ የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት  ታምራት ቶላ ሲያሸንፍ በውድድሩ ሌላው ...
09/10/2023

በእንግሊዝ ግሬት ኖርዝ ረን
ኢትዮጵያዊው አትሌት አሸነፈ!!!

በእንግሊዝ ግሬት ኖርዝ ረን የ 21 ኪሜ የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ ሲያሸንፍ በውድድሩ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሙክታር ኢድሪስ 3ኛ ሆኗል።
በሴቶች ኬኒያዊቷ ፒሬስ ጄብቼርቸር አሸንፋለች።



GREAT NORTH RUN, GBR 🇬🇧

ብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ 5000ሜ ሴቶች ኢትዮጵያዊቷ መዲና ኢሳ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራሯን ጨርሳለች።ሙሉ ውጤት ከፍቶው ላይ ይመልከቱ!!
09/08/2023

ብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ 5000ሜ ሴቶች ኢትዮጵያዊቷ መዲና ኢሳ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራሯን ጨርሳለች።
ሙሉ ውጤት ከፍቶው ላይ ይመልከቱ!!

👉 የኢትዮጵያ ኦሎፒክ ኮሚቴ በ19ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒይና ላይ ኢትዮጵያን ለወከለው ቡድንታዋቂ የቀድሞ የኦሎፒክ ጀግና አትሌቶች ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ስነስርዓት የገንዘ...
09/05/2023

👉 የኢትዮጵያ ኦሎፒክ ኮሚቴ በ19ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒይና ላይ ኢትዮጵያን ለወከለው ቡድን
ታዋቂ የቀድሞ የኦሎፒክ ጀግና አትሌቶች ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ስነስርዓት የገንዘብ ሽልማት ሰጠ!!

👉የኢትዮጵያ ኦሎፒክ ኮሜቴ የኦሎፒክ ጀግኖች በተገኙበት ለ19ኛው የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮናው ቡድን መሸለሙ ለወጣትና ለተተኪ አትሌቶች ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ነውና እሰይ ብለናል።

የኦሎፒክ ጀግኖቹ በየልምምድ ቦታም እየተገኙ ልምዳቸውን ለተተኪዎቹ አትሌቶች እንዲያካፍሉም የኦሎፒክ ኮሚቴው የቴክኒክ ክፍል አስፈላጊ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ብለን እናምናለን።

👉 ኦሎምፒክ ኮሚቴው በሽልማት ፕሮግራሙ ላይ
ለወርቅ 150ሺ ብር
ለብር 100ሺ ብር
ለነሀስ 75ሺ ብር
ለዲፕሎማ 30ሺ ብር
ለተሳታፊ 20ሺ ብር
ለቡድን መሪ 100ሺ ብር እንዲሁም የቡድን ስራ ላሳዩት ለአትሌት ፀሀይ ገመቹና ያለምዘርፍ የኋላው ተጨማሪ 50ሺ ብር ሸልሟል እጅግ በጣም ጥሩ ነው።

ውጤት መጣም አልመጣም መጠኑ ይለያይ እንጂ ሽልማት እንደሆነ ወግ ነው አይቀርም።
👉 ፌደረሹኑና እና ኦሎፒክ ኮሚቴው ጥሩ ውህደት እንደፈጠሩ ሰዎች ባይመሰክሩም ፎቶዎቹ ይናገራሉ።
ሌላው ይቅር
ፌደረሽኑና ኦሎምፒክ ኮሚቴው ፎቶዎቹ በሚናገሩት መልኩ በፓሪስ ኦሎምፒክም ደግመን እንድናያቸው
አመት ለማይሞላው (325) ቀን ለቀረው የፓሪስ ኦሎፒክ ምንም ኮሽታ እንዳንሰማ ከአሁኑ ስለ አትሌት መምረጫ ህግ ላይ ቢወያዩና ቁልጭ ያለ ነገር ለአትሌቱም ለሚዲያም ቢያሳውቁ የሰዎች የግል ፍላጎት እንዳይፀባረቅና በሁለቱ ተቋማት መሀል ያለውንም ግንኙነት ክፍተት እንዳይፈጥር ያጠናክረዋል እላለሁ።

ስለዚህ ያለፈው እንዳይደገም ካሁኑ በሁሉም ርቀት ላይ
በተለይ በ 5000, ሜ በ10,000 ሜ ግልፅ ያለ ነገር ቢኖር እንዲሁም በልዩ ሁኔታ በማራቶን ተሰላፌ አትሌቶቻችን የሚመረጡት
በአዲስ ሚኒማም ?
በነበራቸውም ሰዓት ?
በማጣሪያም ይሁን?
ብቻ በማንኛውም መመዘኛ ይምረጡ ግን ከአኑ ቀልጭ ያለ ህግን የተከተለ ማንም በመሰለኝ የማይለውጠው
የሚተገበር አትሌቶችም ሆኑ አሰልጣኞች ሁሉን ቢያውቁና እራሳቸውን በሳይኮሎጂም ቢዘጋጅ ለውጤቱ ትልቅ ግብዓት ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።

አትሌት ገዛኸኝ አበራ የዓለም አትሌቲክስ ቬትራን ፒን አዋርድ ተሸለመ፤የኢፌዲሪ መንግስት አትሌቶቻችን ሸለልሟል  1.5 ሚሊየን ተሸለሙ ሲባል አጨብጭቦ የሚወጣውን... በብሄራዊ ቤተመንግስት ለ...
09/04/2023

አትሌት ገዛኸኝ አበራ የዓለም አትሌቲክስ ቬትራን ፒን አዋርድ ተሸለመ፤

የኢፌዲሪ መንግስት አትሌቶቻችን ሸለልሟል

1.5 ሚሊየን ተሸለሙ ሲባል
አጨብጭቦ የሚወጣውን...

በብሄራዊ ቤተመንግስት ለ19ኛው የቡዳፔሽት ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተዘጋጅቶ በነበረው የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ላይ ለፌዴሬሽናችን ተቀ/ምክ/ ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኽኝ አበራ ከዓለም አትሌቲክስ እ.ኤ.አ. በ2022 በኮቪድ ምክንያት በአካል የኮንግረስ ስብሰባ ባይካሄድም በቨርችዋል በተካሄደ ስብሰባ ላይ ተበርክቶለት የነበረውን የቬትራን ፒን አዋርድ ከክቡር አቶ ቀጄላ መርዳሳ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር እጅ በክብር ተቀብሏል፡፡

የዓለም አትሌቲክስ የቬትራን ፒንን በክብር የሚሰጠው ግለሰቦች ለአትሌቲክስ ስፖርት ረዘም ላለ ጊዜ በተለየ መልኩ በታማኝነት የላቀ አገልግሎት እና አስተዋፅኦ ሲያደርጉ ነው።

በታሪክ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የኦሊምፒክንና የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያሸነፈው አትሌት ገዛኸኝ አበራ በ2000 የሲድኒ ኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆነና በወንዶች ከ32 አመታት የሜክሲኮው የ1968 የማሞ ወልዴ የማራቶን ድል በኋላ ድሉን የመለሰ ኢትዮጵያዊ አትሌት ሲሆን እንዲሁም ገዛኸኝ በ2001 የኤድመንተን አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የማራቶን ባለድል ነው፡፡
ገዛኸኝ 4 ጊዜ ሀገሩን ወክሎ ያሉት ውጤቶች
WC 1999: 11ኛ 2:16:42
OG 2000: 1 ኛ 2:10:11
WC 2001: 1 2ኛ 12:42
WC 2003: DNF

Gezahegn Abera ETH
Date of birth: 23 April 78
Age: 45 years 134 days
Height: 168 cm
Weight: 57 kg
Marathon Olympic Champion 2000
Marathon World Champion 2001
Marathon World Championships finalist 1999
Marathon World Alltime no. 560 2:07:54 Fukuoka 5 Dec 1999

ለ19ኛ ጊዜ በተካሄደው የቡዳቤስት አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሜዳልያ ያስመዘገቡ አትሌቶችና አሰልጣኞቻቸው እሁድ ነሃሴ 28/2015 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በቤተ መንግስት በተከናወነ መርኃ ግብር ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ሳህለ-ወርቅ ዘውዴ እጅ የኢፌዲሪ መንግስትን የገንዘብ ሽልማት ተቀብለዋል።

ለአትሌቶች :-
የወርቅ ሜዳልያ ላመጡ 2 አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዮን ብር
የብር ሜዳልያ ላመጡ 4 አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር
የነሐስ ሜዳልያ ላመጡ 3 አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 700ሺ ብር

ለአሰልጣኞች:-
ለወርቅ ሜዳልያ ላመጡ አሰልጣኞች ለእያንዳንዳቸው 750ሺ ብር
ለብር ሜዳልያ ላመጡ አሰልጣኞች ለእያንዳንዳቸው 500ሺ ብር
ለነሐስ ሜዳልያ ላመጡ አሰልጣኞች ለእያንዳንዳቸው 350ሺ ብር
ዲፕሎማ ላስመዘገቡ፣ ለተሳታፊዎችና ለቡድኑ አመራሮች እንዲሁ መንግስት የገንዘብ ሽልማ

👉 በመጀመሪያ ደረጃ መታወቅ ያለበት አትሌቶቹ ምንሞ የመወዳደሪያ ሜዳ ሳይኖራቸው በአለም ደረጃ ተወዳድረው ይህን ውጤት በማምጣቸው ሊደነቁና ሊያስመሰግናቸው ይገባል።
መንግስትም ይህን ገንዘብ ሲሸልምም መለማመጃ ቦታ ሳይኖራችሁ ይህን ውጤት በማምጣታችሁ ኮርተንባችኋል በማለት አመስግኖ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ በመቀጠልም ማድረግ የነበረበት ላመጣችሁት ውጤት ይህን የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ በ19ኛው አለም ሻምፒዮና ወርቅ ባመጡትና በተሳተፉት አትሌቶች ስም ሰጥቻለሁ ብሎ ካርታ ቢያስረክባቸው መልካም ነበር ።

1.5 ሚሊየን ተሸለሙ ሲባል
አጨብጭቦ የሚወጣን ያብዛልን!!
እያልኩ

የሀገራችንን ስም ከፍ ላደረጉ አትሌቶች በመንግስት ደረጃ የተሸለሙት ሽልማት ያንሳል። ለእኔ መንግስት ከሸለመው ሽልማት ይልቅ የፌደረሽኑ ሽልማት ይበልጣል
athletics





ክብረወሰኑ ባይሻሻልም ተሞክሯል!!በሚቀጥለው ይሻሻላል!!!ለተሰንበት የ10,000ሜ የ15 ኪሜ እና የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በእጇ ይገኛል!!ያለውን ይባርክልሽ ብለናል!!!5000ሜትርን ከ14...
09/03/2023

ክብረወሰኑ ባይሻሻልም ተሞክሯል!!
በሚቀጥለው ይሻሻላል!!!

ለተሰንበት የ10,000ሜ የ15 ኪሜ እና የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በእጇ ይገኛል!!
ያለውን ይባርክልሽ ብለናል!!!

5000ሜትርን ከ14:10 በታች የገቡ ሁለት አትሌቶች ብቻ ሲሆኑ ከሁለቱ አንዷ ለተሰንበት ግደይ ነች ለተሰንበት 3ጊዜ ከ14:10 በታች የሮጠች ሲሆን ኪፕዮገን አንድ ጊዜ እሱም ከለተሰንበት ጋር ሮጣ ክብረወሰኑን አሻሽላዋለች።

የ5000ሜ 10 ፈጣን ሰዓትች

5000 m Women Alltime List
1 14:05.20 WR
Faith Kipyegon
KEN Paris 9 Jun 2023
2 14:06.62 WR
Letesenbet Gidey
ETH Valencia 7 Oct 2020
3 14:11.15 WR
Tirunesh Dibaba
ETH Oslo 6 Jun 2008
4 14:12.29
Gudaf Tsegay
ETH London 23 Jul 2023
5 14:12.59
Almaz Ayana
ETH Roma 2 Jun 2016
6 14:12.88
Meseret Defar
ETH Stockholm/S 22 Jul 2008
7 14:12.92
Beatrice Chebet
KEN London 23 Jul 2023
8 14:12.98
Ejgayehu Taye
ETH Eugene OR 27 May 2022
9 14:13.42 AR
Sifan Hassan
NED London 23 Jul 2023
10 14:15.24
Senbere Teferi
ETH Hengelo 8 Jun 2021
athletics





Address

111 N Patsburg Street
Denver, CO
80018

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio runners posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio runners:

Videos

Share


Other News & Media Websites in Denver

Show All