ሀበሻ Live

ሀበሻ Live News and entertainment page. An authentic and reliable page for all. A news and entertainment broadcasting page dedicated in publishing reliable information.

This page aspires to be a destination for the latest news for all.

04/22/2024

Kare Baltena International Marketing

ታሰሩትናንት ከኃላፊነት መነሳታቸው በተገለፀው በአቶ ታዬ ደንደዓ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ ከላይ በምስሉ የሚታዩት ተገኝተዋል ተብሏል።ይህንን ተከትሎ አቶ ታዬ ደንደዓ መታሰራቸው ተነግሯል።
12/12/2023

ታሰሩ

ትናንት ከኃላፊነት መነሳታቸው በተገለፀው በአቶ ታዬ ደንደዓ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ ከላይ በምስሉ የሚታዩት ተገኝተዋል ተብሏል።
ይህንን ተከትሎ አቶ ታዬ ደንደዓ መታሰራቸው ተነግሯል።

ሰበር ዜና፡መንግስትን በመተቸት የሚታወቁት ታዬ ደንደአ በጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣን መነሳታቸውን በፌስብክ ገፃቸው እንደሚከተለው አስታውቀዋል-----ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የተናገሩትን...
12/11/2023

ሰበር ዜና፡

መንግስትን በመተቸት የሚታወቁት ታዬ ደንደአ በጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣን መነሳታቸውን በፌስብክ ገፃቸው እንደሚከተለው አስታውቀዋል
-----
ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ

የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት:: አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ:: እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር:: ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ:: ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ:: ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ::

እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል!

Kabajamoo Muummicha Ministeeraa Abiyyi Ahimadiif

Yaada Ida’amuu dubbattee fi barreessite amanee isin hordofe. Dhawaata garuu nama waan dubbatu hin jiraanne qofa otoo hin taane cubbamaa dhiiga namaatiin taphatu ta’uu keessanin hubadhe. Gaafan dhugaa sehee waraana bilaasha maqaa walabummaa biyyaatiin bantan, isa Itoophiyaanota wal-nyaachise, fi diinagdee biyyaa kuffise gegeessaa turtan deeggaretti na faarsaa turtan. Hardha gaafan dubbii argee gara nagaa goruun wal-ajjeechaan obboleeyyanii haa dhaabatu jennaan aangoo narraa fudhattan. Otoon shira Oromoo Oromoodhaan balleessuu fi obboleeyyan isaatiin walitti buusuuf kaatan argaa callisuu dhabuu kootii baayyeen gammada. Turtii waliin qabaannef galatoomaa!

Hagan jirutti qabsoon nagaa fi obbolummaa ummataatiif godhu itti fufa!

09/03/2023

የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ዓለማቀፍ ቴሌቶን ቀጥታ ስርጭት

በቴሌቱኑ ለመሳተፍና ለመርዳት እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ፦ https://www.amharapopularfront.net/

08/28/2023

ዳኘ ዋለ

የ " ገመና ቁጥር 1 " እና “ ቁጥር 2 “ድራማዎች ዳይሬክተር አሸብር ካብታሙ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለየየ " ገመና ቁጥር 1 "  "ገመና ቁጥር 2 " እና " መለከት " የቴሌቪዥን ድራማዎ...
08/25/2023

የ " ገመና ቁጥር 1 " እና “ ቁጥር 2 “ድራማዎች ዳይሬክተር አሸብር ካብታሙ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለየ

የ " ገመና ቁጥር 1 " "ገመና ቁጥር 2 " እና " መለከት " የቴሌቪዥን ድራማዎችን ጨምሮ በበርካታ የጥበብ ስራዎች ላይ አሻራውን ያሳረፈው ዳይሬክተር አሸብር ካብታሙ ዛሬ ነሐሴ 19 2015 ዓ.ም በሞት መለየቱ ተሰምቷል፡፡

አርቲስቱ በዛሬው እለት ጠዋት 1 ሰዓት አካባቢ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የተሰማ ሲሆን ከአመት በፊት ባጋጠመው የጤና እክል ወዳጆቹ እና የሙያ አጋሮቹ ባደረጉለት ድጋፍ መሻሻል አሳይቶ እንደነበር ተነግሯል፡፡

አሸብር ካብታሙ በገመና ሆነ በመለከት እና በሌሎችም የኪነ ጥበብ ስራዎች ላይ ከነበረው አስቷፅኦ በተጨማሪ ትኩረቱን በህግ ዙሪያ ባደረገው " ችሎት " የተሰኘው አስተማሪ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ለ14 ዓመታት በዝግጅት መሳተፍ የቻለ ባለሙያ ነው፡፡

መልካም የ አሸንዳ በዓል
08/22/2023

መልካም የ አሸንዳ በዓል

08/22/2023
በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን  በሳኡዲ አረብያ የድንበር ጠባቂዎች መገደላቸው ተነገረሂዮማን ራይትስ ዋች (Human Rights Watch) ይዞት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያዊያን የየመንን ድን...
08/21/2023

በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በሳኡዲ አረብያ የድንበር ጠባቂዎች መገደላቸው ተነገረ

ሂዮማን ራይትስ ዋች (Human Rights Watch) ይዞት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያዊያን የየመንን ድንበር አቋርጠው ወደ ሳኡዲ አረብያ ሊሻገሩ ሲሉ በድንበር ጠባቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው አልፏል ነው ያለው፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ ምናልባትም ወደሺዎች የሚጠጉ ስደተኞቹ ከባለፈው አመት መጋቢት እስከዘንድሮው ሰኔ ድረስ ነው የተገደሉት

ሪፖርቱ የአየን እማኞችን ጠቅሶ እንዳስነበበው “ወታደሮቹ መሳርያ በታጠቁ ሰዎች ላይ የሚተኩሱ በሚመስል ጭካኔ በስደተኞቹ ላይ የጥይት ናዳ አዝንበዋል” ሲል ጠቅሷል፡፡

ሌላ ግዜ ደግሞ በማጎርያ ውስጥ የሚገኙ ህገ ወጥ ስደተኞችን ከእስር ቤት በማስወጣት “ማንን ተኩሰን እንምታ” በሚል አንዱ በአንዱ ላይ እንዲፈርድ በማድረግ የሰበአዊ መብት ጥሰት እንደሚፈጽሙ ሪፖርቱ አክሏል፡፡

የመን ሃውቲ ታጣቂዎች በቁጥጥራቸው ስር የሚገኙ ስፍራዎችን ተሻግረው ወድ ሳኡዲ አረቢያ የሚጓዙ ስደተኞችን እስከ 50 ሺ ዶላር ያስፍላሉ፡፡

በአሁን ሰዓት በሳውዲ አረቢያ ከ750 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ የአለማቀፉ ስደተኞች ተቋም (IOM) ትንበያውን ያስቀመጠ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ከ450 ሺሕ በላይ ወደ አገሪቱ በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

Ethiopian airstrike on a town square in the restive Amhara region kills 26, health official says
08/14/2023

Ethiopian airstrike on a town square in the restive Amhara region kills 26, health official says

A senior health official says an airstrike on a crowded town square in Ethiopia’s restive Amhara region has killed at least 26 people and wounded more than 55 others

08/14/2023
5 ሀገራት በቅርቡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተፈጠረውን አለመረጋጋት አስመልክተው እንዳሳሰባቸው የሚገልፅ  የጋራ መግለጫ ሰጡ  የአውስትራሊያ ፣ የጃፓን ፣ የኒውዚላንድ፣ የእንግሊዝ እና ...
08/11/2023

5 ሀገራት በቅርቡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተፈጠረውን አለመረጋጋት አስመልክተው እንዳሳሰባቸው የሚገልፅ የጋራ መግለጫ ሰጡ

የአውስትራሊያ ፣ የጃፓን ፣ የኒውዚላንድ፣ የእንግሊዝ እና የዩናይትድ ስቴትስ መንግስታት በቅርቡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሰላማዊ ዜጎች ሞት እና አለመረጋጋት ያስከተለው ግጭት እንዳሳሰባቸው ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ሀገራቱ ፤ ሁሉም ወገኖች ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ እና የሚያጋጩ ውስብስብ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተባብረው እንዲሰሩ አበረታተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ድጋፉን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

ተዋናይ አብነት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ተዋናይ አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ነበር።ከዚህ ውስጥ አሉላ...
08/09/2023

ተዋናይ አብነት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ተዋናይ አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ነበር።

ከዚህ ውስጥ አሉላ አባነጋ፣ የቼዝ ዓለም፣ ዳኛው፣ እስረኛው ንጉስ እና ነቅዕ ቴአትሮች ላይ ተውኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አያስቅም፣ አንድ እድል፣ ላምባዲና፣ ሰበበኛ፣ ባንቺ የመጣ፣ ቁልፉን ስጭኝ፣ የነገርኩሽ እለት፣ ፍቅር እስከ መቃብር እና አትሸኟትም ወይ በተሰኙ ፊልሞች ላይ በመተወን አድናቆትን አግኝቷል።

ስንቅ ፣መለከት፣ ትርታ እና ለወደዱት ደግሞ የተሳተፈባቸው የቴሌቪዥን ድራማዎች ሲሆኑ፥ በግሉም የቅብብሎሽ ድራማን ደርሷል።

በስህተት ላይ ስህተት
08/03/2023

በስህተት ላይ ስህተት

08/02/2023
ኒጀር መፈንቅለ መንግስት አካሄደች ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ባዙምን በትናንትናው እለት ያፈኑት የኒጀር ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት ማካሄዳቸውን ገለጹ። ኮሎኔል ማጅ አማዱ አብድራማን ከ9 ወታደሮች ...
07/27/2023

ኒጀር መፈንቅለ መንግስት አካሄደች

ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ባዙምን በትናንትናው እለት ያፈኑት የኒጀር ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት ማካሄዳቸውን ገለጹ።

ኮሎኔል ማጅ አማዱ አብድራማን ከ9 ወታደሮች ጋር በመሆን በሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ነው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት መካሄዱን ያወጁት።

የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ አስተዳደር በየጊዜው እያሽቆለቆለ መሄዱንም ለመንግስት ግልበጣው በምክንያትነት አንስተዋል።

የአፍሪካ ህብረት እና የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) የመንግስት ግልበጣውን የተቃወሙ ሲሆን፥ የቤኒን ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎን ለማሸማገል ኒያሚ ገብተዋል።

ኒጀር በፈረንጆቹ 1960 ከፈረንሳይ ነጻነቷን ካወጀች በኋላ አራት የተሳኩ የመንግስት ግልበጣዎችን አስተናግዳለች።

ጎረቤቶቿ ማሊ እና ቡርኪናፋሶም መፈንቅለ መንግስት ባካሄዱ ወታደራዊ አዛዦች እየተመሩ ነው።

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም መፈንቅለ መንግስቱን “በጥብቅ” ተቃውመው ፕሬዝዳንት ባዙምን ለማስለቀቅ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ አል አይን

 ዛሬ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተበረከተለት የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ በመድረክ ያደረገው ንግግር እጅግ ስሜትን የሚነካ ስለነበር ተመራቂዎ...
07/20/2023


ዛሬ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተበረከተለት የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ በመድረክ ያደረገው ንግግር እጅግ ስሜትን የሚነካ ስለነበር ተመራቂዎች እና ታዳሚያንን እያለቀሱ ሲያዳምጡት ነበር።
አቶ ቢንያም በለጠ ምን አለ?

" ...ለእኔ ብዙ ትልቅ ቦታ አትስጡኝ ፤ እኔ የማልረባ ሰው ነኝ ፤ ቅድም ስለእኔ ስትገልፁ ከብዶኛል።

እውነቴን ነው እግዚአብሔር ይሰራል እሱን አልክድም መቄዶንያ ላይ ፤ ምክንያቱም ካለምንም እርዳታ ይሄን ሁሉ ሺህ ሰው በሀገር ውስጥ በየቀኑ አንድ ሚሊዮን የእግዚአብሔርን ስራ መሆኑ ግልፅ ነው በጣም።

እኔኮ በሽተኛ ነኝ ሲጀምር ብዙ ጊዜ ተኝቼ ነው የምውለው ፤ ስራ ያቆምኩ ሰው ነኝ እኔ እንደውም የህብረተሰብ ሸክም መሆን ያለብኝ ሰው ነኝ እውነት ለመናገር።

እንደ እኔ አይነት ሰው ዝም ብላችሁ ብታስቡት እንኳን እንደዚህ ለማድረግ ይቅርና እራሴንም ለመቻል ወይ አግብቶ ወልዶ ለመኖር ሰው ለመርዳት ቀርቶ ለመለመን እንኳን አንድ ሰው ጤነኛ መሆን አለበት ፤ ለመለመን ወጣ ብሎ አንድ ቦታ መቀመጥ አለበት እኔ መቀመጥም አልችልም።

ለመኖር እራሱ የማይገባኝ ሰው ነኝ ፤ በእግዚአብሔር ኃይል ነው ያለሁት ፤ እውነቴን ነው የምነግራችሁ ቀልዴን አይደለም። አንድ ሰው ለመለመን መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ሰው መጠየቅ አለበት አይደል እንደዛ እንኳን የምችል ሰው አይደለሁም። ስለዚህ እግዚአብሔር ነው የሚሰራው።

አንድ የህብረተሰብ ሸክም የሆነ ሰው ፤ እግዚአብሔር ምን ያህል ሃጥያተኛ ሰዎችን በመንፈስም በስጋም ደካማ የሆኑ ሰዎችን እንዴት መርዳት እንደሚችል አንዳንድ ሰዎች በቤተሰብ፣ በትዳር፣ ወይ ሰው አስቀይሟችሁ እንደው እግዚአብሔርን የለም ብላችሁ/ እግዚአብሔር ረሳኝ ብላችሁ ከሆነ እግዚአብሔር እንደዚህ ይሰራል። በማይረቡ ሰዎች፣ በተራ በጣም በወንጀለኛ ሰዎች መስራቱን ስታዩ ሁሉንም ሰው እግዚአብሔር እንደሚረዳ የሚያሳይ ነገር ነው።

ክብር ዶክትሬት ተብሏል ፤ እኔ ትንሽ ከብዶኛል በጣም ምክንያቱም እናተ ሸልማችሁኛል ፤ የእግዚአብሔር ፍርድ ደግሞ ከባድ ነው እውነት የእግዚአብሔር ፍርድ በጣም አስፈሪ ነውና ከሲኦል እንድድን እግዚአብሔር ከዚያ እንዲያወጣኝ ፀሎት አድርጉልኝ የእውነት። ይሄ በጣም ከባድ ነገር ስለሆነ ነው። ቀልድ አይደለም እግዚአብሔር ዝም ብለን ሃጥያት ስንሰራ ዝም የሚለን አምላክ አይደለም። የእግዚአብሔር ፍርድ ከባድ ነውና እኔ የምፈራው እሱን ነው እንኳን ልሸለም ለፍርድ እንዲቀልልኝ የማስብ ሰው ነኝ።

መቄዶንያ ላይ ብዙ ሰው አስተዋጽኦ ያደርጋል። እኔ የተለየ አስተዋጽኦ የለኝም ከዛ ያነሰ ነው የእኔ አስተዋፅኦ። በሽተኛ ስለሆንኩኝ ስራም ስለሌለኝ አንደኛው ተደጓሚ ነኝ እራሴ በመቄዶንያ ነገር ግን መቄዶንያ ባልፉት ዓመታት እዚህ ለመድረስ ብዙ አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ ሰዎች አላችሁ ምስጋናም ክብርም የሚገባው ለእናተ ነው።"

 እምዬ አገሬ ውድ አገሬ ኢትዮጵያ...እንዲሁም በጣም የምወዳችሁ፣ የማከብራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ፥ ሰላም ሰላም ሰላም ብያለሁ! በአክብሮት የሰጣችሁኝን የአክብሮት ዶ...
07/20/2023



እምዬ አገሬ ውድ አገሬ ኢትዮጵያ...እንዲሁም በጣም የምወዳችሁ፣ የማከብራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ፥ ሰላም ሰላም ሰላም ብያለሁ!

በአክብሮት የሰጣችሁኝን የአክብሮት ዶክትሬት በጣም በትልቅ ደስታ ነው የተቀበልኩት። በጣም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እኔ በጣም፣ በጣም ነው የገረመኝ........ ታጭቼ ብገኝ እንኳን የሚያስደንቀኝ ነበር፤ .......ተመርጬ ስለተነገረኝ በጣም ነው የማመሰግነው። በጣም እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

ፍቅራችሁ እንዲሁ አክብሮታችሁ ስለሆነ፣ በእኔ እና በወገኖቼ ስም፤ እንዲሁም በዚህ ሁሉ ደስ በሚላቸው ኢትዮጵያውን ስም ከልቤ በጣም በጣም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ሕይወታችሁን ይባርከው።

የኢትዮጵያ፥ ዛሬ ያሉትን ተማሪዎች፣ እንዲሁም የወደፊቱን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክ። አገራችንን መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅልን።

ያስቸግራል ለመግለጽ ደስታዬን። በጣም አመሰግናለሁ። በጣም ክብራችሁ እና ፍቅራችሁ ከልክ ያለፈ ነው በቃ... ለእኔ የሚገባኝ አይደለም። ግን ይኽን ሁሉ ስላከበራችሁኝ በጣም እግዚአብሔር ይስጥልኝ። በጣም አመሰግናለሁ።

የኢትዮጵያን ሕዝብ እግዚአብሔር ይጠብቅልን። ምስጋናዬ በጣም ከፍ ያለ ነው።

በአካል ተገኝቼ አንድ ቀን እዚያ መጥቼ አያችኋለሁ። በሰላም ቆዩኝ። ይኽንን አጭር መልእክቴን ይቅር በሉኝ። ሌላ ጊዜ በደንብ አመሰግናችኋለሁ። (ሳቅ)

በጣም እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እጅጋየሁ ነኝ። Thank You!

💚💛❤️

ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑንን ገለጸ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ...
07/13/2023

ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑንን ገለጸ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ5 እና 6 ቀን 2015 ለኹለት ተከታታይ ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ በማጠናቀቅ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪን ቸል ከማለት ባሻገር ሐምሌ 9 ቀን 2015 እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ፤ የሚመለከታቸው አካላት ሂደቱን በማስቆም ከቤተክርስቲያን ጎን እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል።

የመግለጫው ሙሉ ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት በቤተ ክርስቲያናችን የበላይ መዋቅርና በክልል ትግራይ አህጉረ ስብከት መካከል የነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ተቋርጦ መቆየቱን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት ተፈቶ መዋቅራዊ አንድነታችን በድጋሚ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ሀገራዊ የሰላም እርቁ ከተፈጸመበት ማግስት ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ሲጠየቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ምንም እንኳን ቅዱስ ሲኖዶሱ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም በክልሉ ያሉት ብፁዓን አባቶችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተከፈተው የሰላምና የውይይት በር ከመጠቀም ይልቅ መዋቅራዊ አደረጃጀቱን በመጣስ መንበረ ሰላም የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት መሥርተናል በሚል ተገቢነት የሌለው መግለጫ ከመስጠትም አልፎ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸም አለበት የሚል ውሳኔ በማሳለፍ 10 ኤጲስ ቆጶሳትን ሐምሌ 9 ቀን 2015 ለመሾም ፕሮግራም መያዙን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሰኔ 29 ቀን 2015 ባደረገው ስብሰባ በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ በጦርነቱ ወቅት ለነበረው የመዋቅራዊ ግንኙነት ጉድለትና የሰብአዊ ድጋፍ እጥረት በይፋዊ መግለጫ ይቅርታ የተጠየቀ ቢሆንም ለይቅርታው አዎንታዊ ምላሽ አለመሰጠቱ በእጅጉ አሳዛኝ መሆኑ፤

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለችግሩ መፈታት ባላት ቁርጠኝነት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የሰላም ልዑክ ወደ ክልሉ በመላክ በክልሉ ለደረሰው ጉዳት ሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ብር 20,000,000.00 (ሃያ ሚሊየን ብር) ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያስረከበች ሲሆን በዚህም ወቅት ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ለተደረገው የከበረ አቀባበል ቅዱስ ሲኖዶስ አመስግኗል፡፡

ይሁን እንጁ የሰላም ልዑኩ ዋና ተልእኮ የሆነውን በክልሉ ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር ለመወያየት የተያዘውን አጀንዳ በተመለከተ በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የተመራው የሰላም ልዑክ በመቀሌ ሀገረ ስብከት በደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የተገኘ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን በመዘጋቱ ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ በእጅጉ አዝኗል፡፡

በመሆኑም የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 13 የሕግ ድንጋጌ መሠረት ሐምሌ 6 ቀን 2015 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

1. በትግራይ ክልል ሐምሌ 9 ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሕገ ቤተ ክርስቲያንና አንቀጽ 37 እና 38 ያላከበረና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

2. በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ይገልጻል፡፡

3. በመሆኑም ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙልን ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹልን ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

4. በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ሐምሌ 6 ቀን 2015
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ንግግር ለማስጀመር በግብፅ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ካይሮ ማቅናታቸው ተሰምቷል።የኤርትራ የማስታወቂያ...
07/12/2023

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ንግግር ለማስጀመር በግብፅ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ካይሮ ማቅናታቸው ተሰምቷል።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከግብፁ አቻቸው አብደል ፈታህ አል-ሲሲ በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት የሱዳን ጎረቤት አገራት መሪዎች በሚያደርጉት ውይይት ላይ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ ረፋድ ወደ ካይሮ መጓዛቸው ተገልጿል።

የሱዳን ጎረቤት የሆነችው ግብፅ ሁለቱን የጦር ጄኔራሎችን ሐሙስ ሐምሌ 06/2015 ዓ.ም. ለማደራደር ማቀዷ ተነግሯል።

በሌላ በኩል፥ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " የውጭ ኃይሎችን " ወደ ሱዳን የመላክን ጥሪ እንደማይቀበለው አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ሱዳን ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት(ኢጋድ) ልትወጣ እንደምትችልም አስጠንቅቋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን መግለጫ ያወጣው ኢጋድ በትናንትናው እለት በሱዳን ጉዳይ በአዲስ አበባ መምከሩን ተከትሎ ነው።

ሚኒስቴሩ እንደገጸው የሱዳን ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ መገኘት ፣ ሱዳን ለሰላማዊ መፍትሄ ያላትን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብሏል።

በሱዳን ጦር መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሐን እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ መካከል የተፈጠረው የሥልጣን ሹክቻ በሱዳን ሉዓላዊ እና አንድነት ላይ አደጋ ከመጋረጡ በላይ በቀጠናው ላሉ አገራት የደኅንነት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።

የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሱዳን ወደለየለት የዕርስ በዕርስ እየገባች ነው ፤ይህም ቀጠናውን ወደ ትርምስ ሊወስድ ይችላል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

በትግራይ የሚገኙ አባቶች የፊታችን እሁድ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ።
07/12/2023

በትግራይ የሚገኙ አባቶች የፊታችን እሁድ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ።

ሲኖዶሱ ይቅርታ ጠየቀ በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ፦- ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመሰጠቷ...
07/06/2023

ሲኖዶሱ ይቅርታ ጠየቀ

በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ፦

- ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመሰጠቷ፣

- በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣

- ጦርነቱ ቁሞ በአገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

በጦርነቱ ወቅት የታሰሩ ወታደሮች የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለፀበሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በተካሄደው ጦርነት በኹለቱም ወገኖች የታሰሩት ተዋጊዎች የት እንዳ...
06/15/2023

በጦርነቱ ወቅት የታሰሩ ወታደሮች የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለፀ

በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በተካሄደው ጦርነት በኹለቱም ወገኖች የታሰሩት ተዋጊዎች የት እንዳሉ እስካሁን እንደማይታወቅ ተገለጸ።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የሕግ አማካሪ ፍስሃ ተክሌ፤ በእስር ላይ የሚገኙ የፌደራል መንግሥቱ እና የሕወሓት ወታደሮች እንዲሁም በየአካባቢው በጦርነቱ ተሳትፋችዋል ተብለው ያለክስ የታሰሩ የሚሊሻ አባላት የት እንዳሉ አይታወቅም ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

በሁለቱ ኃይሎች መካከል በተደረገው ጦርነት የት እንዳሉ ከማይታወቁት ከታሰሩት ተዋጊዎች በተጨማሪ እስካሁን ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱም በፌደራል መንግሥቱም ይሁን በሕወሓት በኩል ይፋ የተደረገ ቁጥር የለም ተብሏል፡፡

በፌደራል መንግሥቱና በሕወሓት መካከል በነበረው የሰላም ድርድር የአፍሪካ ህብረት የሰላም ድርድር ዋነኛ መሪ የነበሩት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ፤ በሰሜኑ ጦርነት ከ600 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጄንሲ ባለፈው ህዳር ወር ባወጣው ዘገባ፤ ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ከ70 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ ወደ ሱዳን ተሰደዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ

ማንችስተር ሲቲ ለሶስተኛ ተከታታይ አመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆኑ።
05/20/2023

ማንችስተር ሲቲ ለሶስተኛ ተከታታይ አመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆኑ።

Address

Alexandria, VA

Telephone

+251911156054

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሀበሻ Live posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሀበሻ Live:

Videos

Share

Nearby media companies


Other Broadcasting & media production in Alexandria

Show All