Afro Soccer Ethiopia / አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ

Afro Soccer Ethiopia / አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን የእግር ኳስ ተጫዋቾችንና የአሰልጣኞችን ፕሮፋይ እንገነባለን፤ለአለም እናስተዋዉቃለን

አሸናፊ ግርማ ከበርካታ አመታት የውጪ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል ።አይረሴው የመሀል ሜዳ ኮከብ በወዳጆቹ አቀባበል ተደርጎለታል ። አሸናፊ ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ኑሮውን በካናዳ...
12/29/2024

አሸናፊ ግርማ

ከበርካታ አመታት የውጪ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል ።
አይረሴው የመሀል ሜዳ ኮከብ በወዳጆቹ አቀባበል ተደርጎለታል ። አሸናፊ ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ኑሮውን በካናዳ አድርጎ ታዳጊዎችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል ።

👉አሸናፊ ግርማን ሲጫወት ያያችሁት ትወዱለት የነበረውን ድንቅ ብቃቱን አካፍሉን ?

ተመልሷል ሀብታሙ ተከስተ - ጎላ ለበርካታ ወራት ከሜዳ ካራቀው ጉዳት አገግሞ ወደሜዳ ተመልሷል ።
12/29/2024

ተመልሷል

ሀብታሙ ተከስተ - ጎላ ለበርካታ ወራት ከሜዳ ካራቀው ጉዳት አገግሞ ወደሜዳ ተመልሷል ።

ወደ እስራኤል አፄዎቹ እና የጣናው ሞገድ እስራኤል ከሚገኙ ክለቦች ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ሊያደርጉ ወደ እስራኤል ይነጣሉ ።(የፊፋ ማች ኤጀንት ፍፁም አድነው )
12/29/2024

ወደ እስራኤል

አፄዎቹ እና የጣናው ሞገድ እስራኤል ከሚገኙ ክለቦች ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ሊያደርጉ ወደ እስራኤል ይነጣሉ ።

(የፊፋ ማች ኤጀንት ፍፁም አድነው )

ዛሬም ተሸንፈናልስለ ብሔራዊ ቡድናችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት አጋሩን
12/22/2024

ዛሬም ተሸንፈናል

ስለ ብሔራዊ ቡድናችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት አጋሩን

ዘመነ ካሴ V ሰኢድ ኪያር ጨዋታው ከባህር ዳር ስታዲየም በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ ነው ፣ ኡጋንዳዊው ኮሜንታተር የአፄዎቹ  ደጋፊዎች በሚያሰሙት ድምፅ ግራ ተጋባ ...." ዘመነ ካሴ ፣ ዘመ...
12/20/2024

ዘመነ ካሴ V ሰኢድ ኪያር

ጨዋታው ከባህር ዳር ስታዲየም በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ ነው ፣ ኡጋንዳዊው ኮሜንታተር የአፄዎቹ ደጋፊዎች በሚያሰሙት ድምፅ ግራ ተጋባ ....
" ዘመነ ካሴ ፣ ዘመነ ካሴ
ዘመነ ካሴ ፣ ዘመነ ካሴ.."

ኮሜንታተሩ ሰኢድን ጠየቀ
"Which Player is Zemene Kase ? (የትኛው ተጨዋች ነው ዘመነ ካሴ?)"

ሰኢድ ዝም እንዳይል ተጠየቀ፣ እንዳይመልስ 'ተጨነቀ '
"ዘመነ ካሴ ተጫዋች አይደለም"
በማለት ከጥያቄው ሸሸ ። በስፖርቱም ዘርፍ የሚዲያ ነፃነት የለም። ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ እራሱ ስፖርቱንም ነፃ ያወጣዋል ። ያኔ እነ ሰኢድ ኪያርም እያንዳንዱን የስታዲየም ክስተት እና የደጋፊዎችን ድምፅ ለመናገር ነፃነት ያገኛሉ ...

ዘገሊላ አሰግድ (New York)

'ኢትዮጵያ ጥሩ ሜዳ ተከራየች' 😎ብሄራዊ ቡድኑ ቀጣይ በሜዳው ከታንዛኒያ ጋር የሚያደርገውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኮንጎ ላይ ለማድረግ የኮንጎን ሜዳ መርጠው  መከራየታቸውን አቶ ባህሩ...
11/03/2024

'ኢትዮጵያ ጥሩ ሜዳ ተከራየች' 😎

ብሄራዊ ቡድኑ ቀጣይ በሜዳው ከታንዛኒያ ጋር የሚያደርገውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኮንጎ ላይ ለማድረግ የኮንጎን ሜዳ መርጠው መከራየታቸውን አቶ ባህሩ አስታውቀዋል ::

በዚህም ዋልያዎቹ በሜዳቸው ሊያደርጉት የሚገባውን የማጣሪያውን አምስተኛ ጨዋታ ከታንዛኒያ ጋር ከሜዳቸው ውጭ ኮንጎ ላይ ለሜዳ ኪራይ ረብጣ ዶላር ከፍለው ይጫወታሉ። ከቀናት በኋላም ስድስተኛ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ እዛው ኮንጎ ከኮንጎ ጋር (ለሜዳዋም ኪራይ ከፍለዋት) ይጫወታሉ :: ቡድኑ በሜዳ እጦት እስካሁን በኪራይ ረብጣ ዶላር ያስገባላቸው ሀገራት
✅ አይቮሪኮስት
✅ ሞሮኮ
✅ ታንዛኒያ
✅ ኮንጎ ( አሁን )
የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ለእግርኳሳችን እድገት የተሳካ ስራ እየሰሩ ነው😎

እንዲህም ይቻላልከጎዳና ሲጋራ አዟሪነት እስከ አውሮፓ ኮከብነት ኤሪክ ባይሊ እንዲህ ይላል፡ " ባርሴሎና ስደርስ በረጅሙ ተንፍሼ እግዚአብሄርን አመሰገንኩ። አሁን ሁሉም ጥሩ ነው አልኩ ወይም ...
11/03/2024

እንዲህም ይቻላል

ከጎዳና ሲጋራ አዟሪነት እስከ አውሮፓ ኮከብነት

ኤሪክ ባይሊ እንዲህ ይላል፡ " ባርሴሎና ስደርስ በረጅሙ ተንፍሼ እግዚአብሄርን አመሰገንኩ። አሁን ሁሉም ጥሩ ነው አልኩ ወይም እንደዛ አሰብኩ።

" ባርሴሎና ግን ከአቢጃን የተለየ ነበር። ዓይኔ የሚያየው ቦታ ሁሉ በመብራቶች ተሽቆጥቁጧል። የመኪኖች መርመስመስና ጫጫታው ሌላ ነው። በየመንገዱ ማንም ሰላምታ አይለዋወጥም ።

" በቃ አውሮፓ ማለት ይሄ ነው ? እና ቅዝቃዜው አይጣል ነው! በታሕሳስ አይቮሪ ኮስት ሁል ጊዜ ይሞቃል። እዚህ ግን ቅዝቃዜውን ልቋቋመው አልቻሉኩም።

" ቶሎ መላመድ እንዳለብኝ አውቅ ነበር። እንደ እድል ሆኖ፣ ከአንድ ወር በኋላ ክለቡ እንዲህ አለኝ፣ “እሺ፣ እስኪበቃን አይተንሃል። እንፈልግሃለን። በሁለተኛው ወር ከኤስፓኞል ጋር ውል ፈረምኩ።

" ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ሆኜ ወደ አይቮሪ ኮስት ስመለስ ሁሉም ሰው በጣም ደስተኛ ነበር። መላው ቤተሰቤ ዕለቱን አከበሩት። አባቴ በጣም ተደሰተ። ዶሮ ለመሥራት ወደ ኩሽና ገባ!

" ከዚያም ወደ እስፓኞል የወጣት ቡድኖችን ለመቀላቀል ወደ ስፔን ተመለስኩ። የመጀመሪያ ክፍያዬን ሳገኝ በቀጥታ ለቤተሰቤ በባንክ አዘዋወርኩ።

" ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ነገር በጣም በፍጥነት ሄዷል። እ.ኤ.አ. በ2011 ኤስፓኞልን በተቀላቀልኩ በሶስት ዓመቴ ወደ ዋናው ቡድን አደግኩ። ከዚያም በቪላሪያል 18 ወራትን አሳለፍኩ እና በድንገት ለማንቸስተር ዩናይትድ የመጫወት ዕድል አገኘሁ።

አይገርምም! በአምስት ዓመት ውስጥ ከአቢጃን ጎዳናዎች ላይ ሲጋራ ከመሸጥ ተነስቼ ትልቁ የዓለም ክለብ ውስጥ መጫወት ጀመርኩ። "

(ከሳሮን እንዳለ)

ምርጡ ፉልባክ ማነው ?አበባው ቡጣቆአማኑኤል ግደይያሬድ ዝናብ ወሰኑ ማዜ(ቀስቴ)ታዲዬስ(ኦርቴጋ)መሀሪ መናብርሀኑ ቦጋለ(ፋዲጋ)ደስታ ዮሐንስ (አባት) በእናንተ እይታ ምርጡ የግራ ፉልባክ ማነው...
10/29/2024

ምርጡ ፉልባክ ማነው ?

አበባው ቡጣቆ
አማኑኤል ግደይ
ያሬድ ዝናብ
ወሰኑ ማዜ(ቀስቴ)
ታዲዬስ(ኦርቴጋ)
መሀሪ መና
ብርሀኑ ቦጋለ(ፋዲጋ)
ደስታ ዮሐንስ (አባት)

በእናንተ እይታ ምርጡ የግራ ፉልባክ ማነው ?

10/25/2024

ካርሎስ 👏

ሐዘንአሰልጣኝ አስራት ሀይሌ  አረፈ💔
10/25/2024

ሐዘን

አሰልጣኝ አስራት ሀይሌ አረፈ💔

አቡበከር ሱፐር ስፖርትን ተቀላቀለኢትዮጵያዊው አጥቂ አቡበከር ናስር የ ደቡብ አፍሪካውን ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ መቀላቀሉ በይፋ ተገልጿል።ከማሚሎዲ ሰንዳውስ ጋር የተለያየው አጥቂው በሱፐር ስ...
10/24/2024

አቡበከር ሱፐር ስፖርትን ተቀላቀለ

ኢትዮጵያዊው አጥቂ አቡበከር ናስር የ ደቡብ አፍሪካውን ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ መቀላቀሉ በይፋ ተገልጿል።

ከማሚሎዲ ሰንዳውስ ጋር የተለያየው አጥቂው በሱፐር ስፖርት የአንድ ዓመት ቆይታ ይኖረዋል።

10/21/2024

የኛ ጉድ አያልቅም

👉 በቦክስ ተመቺው በቀይ ካርድ የሚሰናበተው፣ መቺው ግን አርቢትሩ እያየ በዝምታ የሚታለፍበት የሊጋችን ጉድ ።

10/20/2024

ድሬዳዋ ከነማ 1 : 1 ስሁል ሽሬ
ቀጥታ ስርጭት

10/19/2024

ሀድያ ሆሳዕና ከ ሐዋሳ ከተማ

ውበቱ v  ሰውነት v ገብረመድንገብረ መድህን ፡"ሽንፈቱን የዓለም ፍጻሜ አታድርጉት፤ ጊኒን የገጠምነው ትልቅ ቡድን ይዘን አይደለም ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ይዘን ነው " ውበቱ :  "ሊቢ...
10/17/2024

ውበቱ v ሰውነት v ገብረመድን

ገብረ መድህን ፡"ሽንፈቱን የዓለም ፍጻሜ አታድርጉት፤ ጊኒን የገጠምነው ትልቅ ቡድን ይዘን አይደለም ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ይዘን ነው "

ውበቱ : "ሊቢያዎች ጨዋታውን ማሸነፍ ይገባቸዋል ፣ የነበርንበት ምድብ ከባድ ነበር ማለት እንችላለን"

ሰውነት : " ተጋጣሚህ ብራዚልም ይሁን ፣ በተለይ ጎል አካባቢ አዳነ እንዳትምር ! ሳላ ! ጌታነህ! መረቡን ወዝውዘው - ድል የጠማው ህዝብ እየጠበቀን ነው ! ጎል አስቆጥር ! አሸንፍ !!! በቃ!! "

በእናንተ እይታ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚመጥነው አሰልጣኝ የቱ ነው ?

"ምርጡ አሰልጣኝ እኔ ነኝ "አዎ በኢትዮጵያ አንጋፋ እና ምርጥ አሰልጣኞች ተርታ  ስዩም ከበደ አንዱ ነው። አሁን ያሉት የሀገራችን አሰልጣኞች ሲቪ እና ብቃት ቢመዘን ከየትኛውም አሰልጣኝ የተ...
10/16/2024

"ምርጡ አሰልጣኝ እኔ ነኝ "

አዎ በኢትዮጵያ አንጋፋ እና ምርጥ አሰልጣኞች ተርታ ስዩም ከበደ አንዱ ነው። አሁን ያሉት የሀገራችን አሰልጣኞች ሲቪ እና ብቃት ቢመዘን ከየትኛውም አሰልጣኝ የተሻለው የስዩም ነው። ችግሩ ስዩም በየክለቡ ለተሰገሰጉ ሙሰኞች አይመችም። ለደላላ ጋዜጠኞችም በሩ ዝግ ነው። በያኔው በተጨዋችነት ዘመኑ በለመደው የንፅህና መንገድ ዛሬም ለመጓዝ ይታገላል ፤ የዛሬዎቹ ፈላጭ ቆራጭ ሙሰኞች ደግሞ "ቅድሚያ ለሀገር እግርኳስ እድገት " ማለትን አያቁም እና አያሰሩትም ፤ ሴራ ጠምጥመው ያደናቅፉታል።
በራሱ አንደበት "ከሀገሪቱ ምርጥ ሶስት አሰልጣኞች መሃል አንዱ እኔ ነኝ ሁለቱን ብትጠሩም አለሁበት " ያለው እውነት ነው። በተጫዋችነትም በአሰልጣኝነትም ኢትዮጵያ ፤ የመን ፤ ሱዳን ሌላም ሀገር ያስመዘገቡው ድል ታላቅ ምስክር ነው። በሲቪው ይታይ ፤ በልምዱና በብቃቱ ይመዘን ። ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሀላፊነት ብቁ መሆኑን እነ ባህሩ ቃኘው "ካለመነፅር" ካዩት ይታያቸዋል።

አሰልጣኙ "የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ከሀገር ውስጥ አሰልጣኝ ከፈለገ ለማሰልጠን ዝግጁ ነኝ ሲቪዬን አስገብቼ ለአሰልጣኝነት እወዳደራለሁ " ብሏል።

ማስታወቂያ  ለ ታዳጊዎች መድን የእግር ኳስ ክለብ ለታዳጊዎች ምልመላ ማስታወቂያ አውጥቷል መስፈርት* ዕድሜ ከ 20 አመት በታች * ፆታ ወንድ * ከዚህ ቀደም በኢትዬጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ...
10/05/2024

ማስታወቂያ ለ ታዳጊዎች

መድን የእግር ኳስ ክለብ ለታዳጊዎች ምልመላ ማስታወቂያ አውጥቷል

መስፈርት

* ዕድሜ ከ 20 አመት በታች
* ፆታ ወንድ
* ከዚህ ቀደም በኢትዬጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምርመራ MRI ምርመራ አድርጎ ማረጋገጫ ያለው
* የMRI መረጃ የሌላቹ የልደት ሰርተፊኬት ፣ የ 8ኛ ክፍል አልያም የ 10ኛ ክፍል ወይ ደሞ የ 12 ክፍል መረጃ ማቅረብ ትችላላችሁ
* ምልመላ ጊዜ ከ ጥቅምት 01 ቀን 2017 ከ ጠዋቱ 3:00 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 4 የሚቆይ ሲሆን ለአራት ቀናት የሚቆይ ምልመላ ይደረጋል

አድራሻ አቃቂ

የሚገኘው 07 ቀበሌ የመድን እግር ኳስ ክለብ መሰልጠኛ ሜዳ ላይ ሲሆን መልካም ዕድል ለታዳጊ ተጨዋቼች እያልን ይህንን መልእክት ለታዳጊዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንዲደርስ እናስተላልፍ ።

ሼር ሼር ለታዳጊዎች

አምሳሉ ጥላሁን ባህር ዳር ከተማን ተቀላቀለከአፄዎቹ የምንግዜም ምርጥ ተርታ የግራ መስመር ተከላካዩ አምሳሉ ጥላሁን አንዱ ነው ።አምሳሉ ከመከላከል ባሻገር ጎሎችን ያስቆጥራል ፤ በተለይ የግራ...
10/02/2024

አምሳሉ ጥላሁን ባህር ዳር ከተማን ተቀላቀለ

ከአፄዎቹ የምንግዜም ምርጥ ተርታ የግራ መስመር ተከላካዩ አምሳሉ ጥላሁን አንዱ ነው ።አምሳሉ ከመከላከል ባሻገር ጎሎችን ያስቆጥራል ፤ በተለይ የግራ እግር ጠንካራ ምቶቹ መለያዎቹ ናቸው።ከፋሲል ከነማ ታዳጊ ቡድን በመነሳት ለአውስኮድ እና ዳሽን ቢራ ክለቦች ተጫውቶ እራሱን በማሳየት ወደ አሳዳጊው ክለብ ተመልሶ አይረሴ ግልጋሎት ሰጥቷል። ከአፄዎቹ ጋር በርካታ የዋንጫ ክብሮችን ማሳካት የቻለው አምሳሉ ጥላሁን(ሳኛ) በመጨረሻም ውሉ በማለቁ ምክኒያት ከአፄዎቹ ተለያይቶ ባህር ዳር ከነማን ተቀላቅሏል።

Address

Alexandria, VA

Telephone

+251704149670

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afro Soccer Ethiopia / አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Afro Soccer Ethiopia / አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ:

Videos

Share

Category

Afro Soccer Ethiopia

Promotes Ethiopian Football players’ Talent , Gives Transfer Information Services , (Foreign Clubs , Ethiopian Clubs , Agents , Managers , Scouts )