Heeri Media

Heeri Media Visit Ethiopia

Omo Valley, Ethiopia🇪🇹
04/03/2024

Omo Valley, Ethiopia🇪🇹

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሜድካል ኮሌጅ ስር በሚገኘው የስነ ተዋልዶ እና የመካንነት ህክምና ማዕከል ዛሬ ለአንዲት እናት በተደረገ ቀዶ ህክምና ከማህፀኗ ውስጥ 110 የማህፀን ፅጢ (...
12/02/2024

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሜድካል ኮሌጅ ስር በሚገኘው የስነ ተዋልዶ እና የመካንነት ህክምና ማዕከል ዛሬ ለአንዲት እናት በተደረገ ቀዶ ህክምና ከማህፀኗ ውስጥ 110 የማህፀን ፅጢ (Myoma) ማውጣት ተችሏል። ቀዶ ህክምናው 4 ሰዓታትን የፈጀ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ታካሚዋ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።(ምስሉ በታካሚዋ ፍቀድ የተለጠፈ ነው)

Via: ዶ/ር ናሆም ግሩም

The men's marathon world record holder, Kenya's Kelvin Kiptum, has died in a road accident in his home country, age 24. ...
12/02/2024

The men's marathon world record holder, Kenya's Kelvin Kiptum, has died in a road accident in his home country, age 24. He was killed alongside his coach, Rwanda's Gervais Hakizimana.

His rise to fame had been rapid. He entered his first major competition in 2018, running in borrowed shoes because he couldn't afford a pair of his own. He only competed in his first full marathon in 2022.

And then, in just his third marathon, in Chicago, October 2023, Kiptum took 34 seconds off the world record, clocking the 26.2 miles (42km) in just two hours and 35 seconds. It was his last race.

Author Adharanand Finn pays tribute to the "insanely brilliant" runner who was a "complete paradigm shift for the sport”.

• Today's the best Photo 🌿🥰•🔴 Beautiful                                                                                 ...
05/02/2024

• Today's the best Photo 🌿🥰
•🔴 Beautiful


















































Today's the best Photo 🌿🥰
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚

የሲዳማ እውነተኛ ፍቅር መገለጫ የሆነው ''ዳኤ ቡሹ'' መረሃ ግብር  በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል ።************************          ሔሪ ሚዲያ ጥር 2016 ዓ.ም  ...
30/01/2024

የሲዳማ እውነተኛ ፍቅር መገለጫ የሆነው ''ዳኤ ቡሹ'' መረሃ ግብር በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል ።
************************
ሔሪ ሚዲያ ጥር 2016 ዓ.ም
ሀዋሳ
ከጥንት ጀምሮ የሲዳማ አባቶች እውነት በእግዚአብሔር ዘንድ መሆኑን የሚያውቁት ይህ እውነት እንዳይጣስ ድንቅ በሆነ በአፊኒ ባህል ያጠፋውን በእውነት ላይ ተመስተው በመዳኘት በምድር ላይ እውነት ከሰማይ በታችበፍቅር ፣በመቻቻል እና በአብሮነት አባቶችን በመፍራት እንደሆነ ያምናሉ።

ከዚህ የተነሳ ''ደወኤ በሹ'' የሲዳማ ድንቅ ባህል፣የሠላምታ አሰጣጥ እና እንግዳ አቀባበል ሥርዓት በዛሬው ቀን ሀዋሳ ከተማ በዚህ መልኩ እየተከበረ ይገኛል ።

«ኦሮሞን ጠልተህ ኢትዮጵያዊ ፣ ኢትዮጵያን ጠልተህ ኦሮሞ መሆን አትችልም» ጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ በገመዳ ሾው  ገመዳ:– ሰዎች ኦሮሞ መሆን ኢትዮጵያዊን መጥላት እንዲሁም ብሄራቸውን መው...
29/01/2024

«ኦሮሞን ጠልተህ ኢትዮጵያዊ ፣ ኢትዮጵያን ጠልተህ ኦሮሞ መሆን አትችልም» ጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ በገመዳ ሾው

ገመዳ:– ሰዎች ኦሮሞ መሆን ኢትዮጵያዊን መጥላት እንዲሁም ብሄራቸውን መውደድ ኢትዮጵያዊነትን መጥላት ነው ብለው ያስባሉ ይሄን እንዴት ታይዋለሽ?"

ደራርቱ:- «ኦሮሞነትን መርጬ አይደለም ያገኘውት፣ ፈጣሪ ኦሮሞ አድርጎ ፈጥሮኛል፣ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ነኝ ይህ እውነታ ነው:: ኦሮሞን ጠልተህ ኢትዮጵያዊ ፣ ኢትዮጵያን ጠልተህ ኦሮሞ መሆን አትችልም :: ይህ የማያከራክር ነገር ነው ኦሮሞንም መላውን የኢትዮጵያን ህዝብ እወዳለሁ አከብራለሁ::

ኦሮሞ መሆን እኮ ኢትዮጵያዊነት ውስጥ ነው ያለው ይሄን ደግሞ መካድ እና መነጣጠል አትችልም ራስህን ከወደድክ ቤተሰብህን ትወዳለህ፣ ቤተሰብህን ከወደድክ ማህበረሰብህን ትወዳለህ፣ ማህበረብህን ከወደድክ ህዝብህን ትወዳለህ፣ ህዝብህን የምትወድ ከሆነ ደግሞ ሀገርህን ትወዳለህ»

Hawassa the city of peace, tolerance & love❤
28/01/2024

Hawassa the city of peace, tolerance & love❤

Success Comes After Hundreds of Failure...🌸Follow Heeri Media
25/01/2024

Success Comes After Hundreds of Failure...🌸

Follow Heeri Media

ወንዶ ገነት  ወደ ምድር ገነቷ የሲዳማ ክልል ይምጡ የጎብኙ!! 🙏ውቢቷ ወንዶ ገነትን ስንጎበኝ ወንዶ ገነት በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የምትገኝ ስምጥ ሸለቆዋ ወንዶገነት ወረዳ በደቡብ...
23/01/2024

ወንዶ ገነት ወደ ምድር ገነቷ የሲዳማ ክልል ይምጡ የጎብኙ!! 🙏

ውቢቷ ወንዶ ገነትን ስንጎበኝ ወንዶ ገነት በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የምትገኝ ስምጥ ሸለቆዋ ወንዶገነት ወረዳ በደቡብ ከመልጋ ወረዳ በምዕራብ ከሃዋሳ ዙሪያ በሰሜን እና በምስራቅ ከኦሮሚያ ክልል ጋር የምትዋሰን ትንሽዬ የምድር ገነት ናት።

በወንዶ ከሚገኙ ተፈጥሯዊ ቦታዎች አንዱ የሆነው ፍል-ውሃ ሲሆን ዙሪያ በኢትዮጵያ አሉ በሚባሉ ደኖች የተከበበች አረንጓዴ ስፍራ ናት። በስዊዲን ሃገር እርዳታ በ1977 የተመሰረተው የአርቦሬተም እና የደን ኮሌጁ የወንዶ መገለጫ ናቸው።

በወንዶ ከሚገኙት ቅመማ ቅመም ፣ መልካም ማዕዛ ያላቸው እና ለመድኃኒትነት የሚጠቅሙ ተክሎች የተከበበች ከዛም በላይ ጠቃሚ የዘይት ምርቶች የሚመረትበት ንዑስ አከባቢ ነው።

በከተማዋ 1961 በስዊዲን ፊላዴልፊያ ቤተ-ክርስቲያን ሚስዮን የተመሰረተ ሲሆን ቤተ-ክርስቲያኒቱ ከመንፈሳዊ ተልዕኮ ውጪ የህክምና አገልግሎት ለወንዶ ገነት ከተማ ሲሰጥ ነበር።

በወንዶ የመጀመሪያው ሆቴል በ1964 የከተፈተ ሲሆን እስከ 1975 ድረስ ለንጉሳዊ ቤተሰብ መዝናኛ ሆኖ አገልግሏል።
ወንዶ ገነት የሚለውን ስያሜ ያሰጡት ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ሲሆኑ የስሙን ውርስ/ ትርጉም ሲሰጡ ❝ ወንዶገነት❞ ማለት የደን ፣ የዱር አራዊት ፣ የበለፀገ ስጦታ ያለውን ውብ ፓኖራማ በማመልከት የሰጡት መሆን ይነገረል።

የተትረፈረፈ ውሃ የሆቴሉ ይዞታ በወቅቱ ለነበረው የሆቴሎች ኮርፖሬሽን የተላለፈ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የዋቢ-ሸበሌ ሆቴሌች ቅርንጫፍ ነው።
የሆቴሉ መረጃ በአሁኑ ወቀት 54.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 40 መኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ፣ በውስጡ ሬስቶራንት ፣ ባር እንዲሁም የመዋኛ ገንዳ እና የፍል ውሃ አለው።

ወደ ሲዳማዋ የምድር ገነት ወንዶ-ገነት መሄድ ከተፈጥሮ ጋር ውብ እና አስደሳች ጊዜ ማሳለፍ ነዉ።
ወንዶ በሃገር ደረጃ ውብ መስህብ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የቡና እና ጫት (የወንዶ በለጬ) ተረፈ ምርት ለውጭ ገብያ የምታቀርብ ትንሽ ገነት ናት!
ወንዶገነት የወረዳ መቀመጫዋ ጩኮ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሌላኛዋም ከፍተኛ የንግድ ዕንቅስቃሴ ያላት ባሻ የምትባል ከተማ ያለቻት ሲሆን ሁለቱም ከተሞች ላይ ከምሽቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የጫት ግብይት የሚካሄድ ሲሆን ለዚሁ ግብይትም ከ 6 በላይ ወረዳዎችም ነጋዴዎች ጫት ጭነዉ ይመጣሉ ግብይቱም እስከ እኩለ ሌሊት ይዘልቃል።

ወንዶ ባሻ ከመልጋ ሲመጣም ባቦ ጮሮራ እና አባዬ ቀበሌዎችም በድምቀት ትታያለች።
ወንዶ ገነት
_የንጉሡ ቤተመንግስት
_የወንዶገነት ደን ኮሌጅ
_የወንዶገነት ፍልውሃ መገኛ
በታሪካዊና በተፈጥሯዊ ሀብቶቿ የታደለችዋን ወንዶ ገነትን ይጎብኙ።
ለምለሟ ምድር ሲዳማ ❤❤❤
Sidama
Wondogenet

Cote d'ivoire humiliated at home
22/01/2024

Cote d'ivoire humiliated at home

Ethiopia 🇪🇹
22/01/2024

Ethiopia 🇪🇹

The horse galloping in Dandi was truly magnificent and it will be an annual event. Stay tuned for more upcoming events i...
21/01/2024

The horse galloping in Dandi was truly magnificent and it will be an annual event. Stay tuned for more upcoming events in and around Wanchi and Dandi!

📷 Abenezer Yonas

አንድ ቱጃር ወዳጃችን በቅርቡ የVolvo የኤሌትሪክ መኪኖችን ለማስመጣትና ፡ ሀገር ውስጥ ለመሸጥ አስቦ ፡ ብዛት ያላቸውን የቮልቮ መኪኖችን ከስዊድን አስጭኖ ጅቡቲ መድረሳቸውን እየጠበቀ ነው...
21/01/2024

አንድ ቱጃር ወዳጃችን በቅርቡ የVolvo የኤሌትሪክ መኪኖችን ለማስመጣትና ፡ ሀገር ውስጥ ለመሸጥ አስቦ ፡ ብዛት ያላቸውን የቮልቮ መኪኖችን ከስዊድን አስጭኖ ጅቡቲ መድረሳቸውን እየጠበቀ ነው ።
እና እንደሰለጠነ የቢዝነስ ሰው ከወዲሁ ፕሮሞሽን ከተለያዩ ካምፓኒዎች ጋር ተዋውሏል ።
እና አንተም ማስታወቂያ ስራ እንጂ አለኝ ፡ እሽ አልኩት ፡ ግን ቆምረን ባሸነፍከው መጠን ነው የምከፍልህ ማለትም ፡ አንድ ሰው ላይክ ሲያደርግልህ ፡ በሀያ ብር አስበዋለሁ ፡ አንዱን ኮመንት ደግሞ አራት ብር ፡ በዚህም መሰረት ፡ ከኮመንቱ ውጭ በ24 ሰአት ውስጥ አንድ ሺህ ሰወች ላይክ ካረጉት ሀያ ሺህ ብር እከፍልሀለሁ ።
2ሺህ ሰወች ላይክ ካደረጉ ፡ አርባ ሺህ
3 ሺ ወዳጆችህ ላይክ ካደረጉ ስልሳ ሺህ ብር እከፍልሀለሁ
4ሺ ላይክ ካደረጉ ሰማንያ ሺህ ብር እከፍላለሁ ።
5 ሺህ ሰወች ላይክ ካረጉልህ 100 ሺህ
አስር ሺህ ላይክ ካደረጉ ሁለት መቶ ሺህ ብር. .. እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል ፡ አለኝ
ሰማንያ ሶስት ሺህ ወዳጆች ናቸው እኮ ያሉኝ ፡ ሆ ብለው ላይክ አርገው እንዳያከስሩህ ብዬ ያልተለመደ የወዳጅ ስምምነት አደረግን ። ...
እና ምን ትላላችሁ ፡ ስንት ብር እንደማገኝ የምትወስኑት እናንተ ናችሁ ። ......
VOLVO SUV coming soon
Wasihune Tesufaye

Pic of the day❤Beautifully Sidama Girls Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
13/01/2024

Pic of the day❤
Beautifully Sidama Girls Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

 Lokka abaya national park is found in sidama region loka abaya woreda at distance of 73km and 348km south from Hawassa ...
10/01/2024


Lokka abaya national park is found in sidama region loka abaya woreda at distance of 73km and 348km south from Hawassa and Addis Abeba respectively. It covers 500km square area and altitudenal range of 1000_1600 meter above sea level. It comprises of complex topography of hills,upland,plain,lake,grassland,wetland,gorges,reverine forest,valley and etc.
𝙳𝚒𝚜𝚌𝚘𝚟𝚎𝚛 𝚃𝚑𝚎 𝙱𝚎𝚊𝚞𝚝𝚒𝚏𝚞𝚕 Land
𝕐𝕠𝕦 𝕨𝕚𝕝𝕝 𝕖𝕟𝕛𝕠𝕪 𝕥𝕙𝕖 𝕨𝕒𝕣𝕞 𝕨𝕖𝕝𝕔𝕠𝕞𝕚𝕟𝕘 𝕠𝕗 SIDAAMA 𝕤𝕠𝕔𝕚𝕖𝕥𝕪.
🇪🇹

Visit Harar
30/12/2023

Visit Harar

Visit Hawassa
30/12/2023

Visit Hawassa

The fastest athlets in the world, Dibaba family.TIRUNESH DIBABA GROUP ♥2012♥
28/12/2023

The fastest athlets in the world, Dibaba family.

TIRUNESH DIBABA GROUP ♥2012♥

«ድሃ በበዛባት አገር ሀብታምም ደሀ ነው»ገመዳ:- "በውጭ ሀገር እንደምናውቀው አትሌቶች ቅንጡ Super Car የሚባሉትን መኪናዎች ነው የሚያሽከረክሩት ቀነኒሳስ?"ቀነኒሳ-  "እውነት ለመናገ...
18/12/2023

«ድሃ በበዛባት አገር ሀብታምም ደሀ ነው»

ገመዳ:- "በውጭ ሀገር እንደምናውቀው አትሌቶች ቅንጡ Super Car የሚባሉትን መኪናዎች ነው የሚያሽከረክሩት ቀነኒሳስ?"

ቀነኒሳ- "እውነት ለመናገር በሀገራችን አለኝ ብለህ ዘመናዊና ቅንጡ መኪና ይዘህ ለመውጣት ህሊናህ አይፈቅድም:: ምክኒያቱም ከቤትህ ወጥተህ እስክትመለስ በየመንገዱ ተቸግሮ ማደሪያና የሚበላው አጥቶ የሚለምንህ አለ። በዚህ ሁሉ ውስጥ አንተ አለኝ ብለህ በዚህ ህዝብ ላይ ልታይ ልታይ ማለት ምን ያደርጋል? አንድ አባባል አለ 'ድሀ በበዛባት አገር ሀብታምም ደሀ ነው' ።

በየመንገዱ የምታየው ሁሉ እናትህ፣ አባትህ እህትህ ወንድምህ ነው:: ታዲያ ማን ላይ ነው ይህን የምታደርገው? ስለዚህ እኔ የማሽከረክረው መኪና በጣምም የወረደ ባይሆንም መካከለኛ ነው።"

አስደሳች ዜና !!!*********************የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት ከአውስትራሊያ ሀገር ከሚመጡ ለረጅም ዓመታት ልምድ ካላቸዉ ስፔሳሊስት ሀኪሞች ጋር በመተባበር የደም ስር...
15/12/2023

አስደሳች ዜና !!!
*********************
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት ከአውስትራሊያ ሀገር ከሚመጡ ለረጅም ዓመታት ልምድ ካላቸዉ ስፔሳሊስት ሀኪሞች ጋር በመተባበር የደም ስር እና የደም ቱቦ ህመም ላለባቸዉ ታማሚዎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቅቆ በመጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡

ስለዚህ ተመርምረዉ የታወቀባቸዉ እና በደም ስር ህመም ራሳቸዉን የሚጠራጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፈጥነዉ በመመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
በዚህም መሠረት፡-
1. ለኩላሊት እጥበት የደም ስር ኦፕሬሽን(ፊስቱላ) እንዲሰሩ የታዘዘላቸው ወይም ሪፈር የተባሉ
2. የእግር የደም ቱቦ/ስር እብጠትና ህመም የለባቸው(ቫሪኮስ ቬይን)
3. በደም ቱቦ/ስር መጥበብ ምክንያት የእግር ህመም እና መጥቆር ያጋጠማቸው
4. በአንገት የደም ስር መጥበብ ወይም መዘጋት ምክንያት ስትሮክ ያለባቸው
እነዚህ እና ተያያዥ ችግር ያለባቸው ታካሚዎች መተው በመመዝገብ ህክምናውን ማግኘት ይችላሉ ፡፡

ቦታ- ጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል፤
የመመርመሪያ ቀናት፡ ከ ታህሳስ 1/2016 ጀምሮ
የ ኦፕራስዮን ቀናት ከ ታህሳስ 30 እስከ ጥር 8/ 2016
ለበለጠ ማብራሪያ - ይደውሉ

+251 472115689
+251 912407507

ይምጡና በአገልግሎቱ ይጠቀሙ!

ኩል፣ ቻፕስትክና ልፕስትክ የሚሉትን ዘመናዊ የመዋቢያ ኮተትን ቀድሞ በ   የዘመኑና የዋቡ ድንቅ የሲዳማ እናቶች ።  ❗
01/12/2023

ኩል፣ ቻፕስትክና ልፕስትክ የሚሉትን ዘመናዊ የመዋቢያ ኮተትን ቀድሞ በ የዘመኑና የዋቡ ድንቅ የሲዳማ እናቶች ።

Sidama, Ethiopia
08/11/2023

Sidama, Ethiopia

ይሄ መንገድ የሚገኘው ባሌ ዞን ውስጥ ከጊኒር ከተማ እስከ ባሌ ሮቤ ከተማ ድረስ የሚገኝ መንገድ ሲሆን ይሄ መንገድ የሚያገናኘው ሁለት ዞኖችን ነው ። እነዚህ ዞኖች ለሀገር ያላቸው አስተዋፅኦ...
03/11/2023

ይሄ መንገድ የሚገኘው ባሌ ዞን ውስጥ ከጊኒር ከተማ እስከ ባሌ ሮቤ ከተማ ድረስ የሚገኝ መንገድ ሲሆን ይሄ መንገድ የሚያገናኘው ሁለት ዞኖችን ነው ።

እነዚህ ዞኖች ለሀገር ያላቸው አስተዋፅኦ
- እንደ ሀገር ከፍተኛውና በዓመት ሁለቴ የስንዴ ምርት ለሀገር የሚያቀርብ አከባቢ ነው
- ዞኑ በውስጡ በያዛቸው ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስዕቦች ምክንያት በቱሪዝም ዘርፍ ለሀገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው አከባቢ ነው ከነዚህ ውስጥ፦ ሶፍዑመር ዋሻየድሬ ሼህ ሁሴን መስጊድ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ይገኛሉ ::
- በቁም እንሰሳት ንግድ በተለይ በግመልና በከብት ሽያጭ አቅርቦት ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽኦ ያለው አከባቢ ለረጅም ጊዜ የመንገድ ጥያቄ የሚያነሳና በተጨባጭ ችግር ውስጥ ያለ አከባቢ ነው የሚመለከተው አካል ለሀገር ዋልታ የሆነውን የባሌ ህዝብ የመንገድ ጥያቄ ብታደርሱልኝ ተስፋነህ አበበ ነኝ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ::************//*********ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓምየሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ በዛሬው ዕለት ባ...
29/10/2023

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ::
************//*********
ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል::

ቦርዱ ከተወያየባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች መካከል የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ ሲሆን በተጨማሪም በዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጉዳይ እና በመምህራን የፕሮፌሰርነት ደረጃ ዕድገት ጉዳዮች ላይ በሰፊው ተነጋግሮ ውሳኔ ሰጥቷል::

በዚህም መሰረት ዶ/ር አያኖ በራሶ ሁላ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ሆነው እንዲቀጥሉ የተወሰነ ሲሆን ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ ዲራ ደግሞ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው እንዲያገለግሉ ተወስኗል::

በተጨማሪም ለአራት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት የደረጃ ዕድገት በየደረጃው ተገምግሞ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት የፀደቀውን ውጤት ቦርዱ በዝርዝር ከመረመረ በኃላ ጥያቄውን አፅድቋል:: በዛሬው ዕለት ሙሉ ፕሮፌሰር የሆኑት ከወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ፕሮፌሰር መሰለ ነጋሽ በ"Forest Ecology and Agroforestry" ከማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ ፕሮፌሰር ዘለቀ አርፊጮ በ"TEFL" እና ፕሮፌሰር መብራቱ ሙላቱ በ"TEFL": እንዲሁም ከተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ፕሮፌሰር ጀመረ በቀለ በ"Veterinary Parasitology" ናቸው:: ዝርዝሩን በሌላ ዜና እንመለስበታለን::

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ለፕሬዚደንቱ ዶ/ር አያኖ በራሶ እና ለአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚደንቱ ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ በተሰጣችሁ ኃላፊነት እንኳን ደስ አላችሁ እያለ መልካም የስራና የስኬት ዘመን ይመኛል::

ሙሉ ፕሮፌሰር ለሆናችሁ የዩንቨርሲቲያችን ምሁራን ደግሞ ለዚህ ውጤት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን ለሀገራችሁ የበለጠ ምሁራዊ አስተዋፅኦ እንድታደርጉ አደራ እንላለን!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

©Hawassa University

  UniversityHaramaya University is more than a University.  It is a home for all.  Choose Haramaya for your study and re...
29/10/2023

University

Haramaya University is more than a University. It is a home for all. Choose Haramaya for your study and research.

Hawassa is a city in 🇪🇹Ethiopia. It serves as the capital of the Sidama Region  and is located on the eastern shore of L...
27/10/2023

Hawassa is a city in 🇪🇹Ethiopia. It serves as the capital of the Sidama Region and is located on the eastern shore of Lake Hawassa. It is known for its beautiful scenery, and pleasant climate has become a popular destination for tourists, and is also an important economic and cultural center in the region.
Hawassa offers various attractions and activities for visitors, such as the Hawassa University Arboretum, the Hawassa Fish Market, and the Hawassa Industrial Park. It provides opportunities for water sports and relaxation by the lakeside.

ጥቂት ስለ ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ ከአዲስ አበባ ስልሳ ሁለት ኪሎሜትር በስተ ምእራብ ርቀት ላይ በምትገኘው ኦሎንኮሜ በፈረንጆች አቆጣጠር 1950 ተወለዱ፡፡በእናታቸው...
25/10/2023

ጥቂት ስለ ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ

ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ ከአዲስ አበባ ስልሳ ሁለት ኪሎሜትር በስተ ምእራብ ርቀት ላይ በምትገኘው ኦሎንኮሜ በፈረንጆች አቆጣጠር 1950 ተወለዱ፡፡

በእናታቸው ከፍተኛ ድጋፍ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን 20 ኪሎ ሜትር በእግራቸው በመጓዝ ነበር የተማሩት፡፡

የኮሌጅ እድሜያቸው ላይ ሲደርሱም ኢንጂነሪንግ የማጥናት እቀድ የነበራቸው ቢሆንም እናታቸው ግብርና እንዲማሩ አሳምነዋቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጅማ የግብርና ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ ተከታተልዋል፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በእፅዋት ሳይንስ በቀድሞ ስሙ ከአለማያ ኮሌጅ ባሁኑ ሃረማያ ዩኒቨርስቲ በ1973 ዓ.ም ወስደዋል፡፡

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1976 በእፅዋት ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን እንዲሁም በ1978 በእጽዋት ማዳቀል እና ዘረመል ኢንጂነሪንግ አሜሪካ ከሚገኘው ፑርድ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ በአፍሪካ የመጀመርያውን ድርቅ የሚቋቋም የማሽላ ዝርያ በምርምር አበርክተዋል፡፡

ይህ ምርምር በ150 እጥፍ ምርታማነትን የሚጨምር መሆኑም ተነግሯል፡፡

በአፍሪካ ምርታማነትን በ40 በመቶ የሚቀንሰው “እስትራጋ” የሚል ስያሜ ያለውን አረም መቋቋም የሚችል የተሻሻለ የማሽላ ዝርያንም አቅርበዋል፡፡

ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2011 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የአለም አቀፍ የምግብ እና ግብርና ልማት ቦርድ አባል አድርገዋል ሾመዋቸዋል፡፡

ፕሮፌሰር ገቢሳ በተለያየ ጊዜ በማሽላ ላይ ባገኙት አስደናቂ ምርምር የተለያዩ ድቅል የሆኑ የማሽላ ዘሮችን መፍጠር የቻሉ ከ200 በላይ የምርምር መጽሃፍቶችን አሳትመዋል።

ከ17 በላይ ታላላቅ ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን፤ የምግብና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) 2009 የወርልድ ፉድ ፕራየዝ ተሸላሚም መሆናቸው ይታወሳል።
ፕሮፌሰር ገቢሳ በዚህ ዘርፍ የተሸለሙ ሁለተኛው አፍሪካዊ ናቸው፡፡

በአፍሪካ ናሽናሊቲ ሳይንስ ሂሮ ሽልማት ከተሸለሙ አፍሪካዊ ሰባት ተመራማሪዎችም አንዱ መሆን ችለዋል፡፡

ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ ከዚህ ቀደም ጥገኛ አረምን መቋቋም የሚችሉ ዝርያዎችን ለማዳቀል ለሚሰሩት ምርምር ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ግብረ-ሰናይ ድርጅት አምስት ሚሊዮን ዶላር አሸንፈዋል።

ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ በትናንትናው ዕለት የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ከፍተኛ የክብር ሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን 21 አሜሪካውያን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፎች ብሔራዊ የክብር ሜዳሊያ መሸለማቸውን አስታውቀዋል።

ብሔራዊ የክብር ሜዳሊያ ከተሸለሙት መካከል ትውለድ ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ እንደሚገኙበትም ባይደን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባወጡት ዝርዝር ላይ አመላክተዋል።

በዚህም ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ በሳይንስ ዘርፍ የአሜሪካ ብሔራዊ የክብር ሜዳሊያ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እጅ ተበርክቶላቸዋል።

መምህርና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ ለሽልማቱ ያበቃቸው በከፍተኛ የምርምር ስራቸው የእፅዋት ዘረመል ምህንድስና በመጠቀም በረሃማ የአየር ንብረት እና ነፍሳትን የሚቋቋሙ የአዝርዕት ዘሮችን በማግኘታቸው ነው።

ምንጭ፤ዊኪፒዲያና የተለያዩ ድረገጾች

The son of Oromo,  , a Distinguished Professor of Plant Breeding & Genetics and International Agriculture , Awarded Nati...
25/10/2023

The son of Oromo, , a Distinguished Professor of Plant Breeding & Genetics and International Agriculture , Awarded National Medal of Science by the US 🇺🇸 President Joe Biden at the White House ‼️

ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ አሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ከሚገኘው ትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደርስ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እና የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማትን ተቀብለዋል። ከ...
25/10/2023

ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ አሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ከሚገኘው ትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደርስ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እና የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማትን ተቀብለዋል።

ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ ለሕዝብ ተጠቃሚነት እና ለሰላም ላበረከቱት ታላቅ አስተዋፅዖ ፣ ያሳዩት በሳል እና ምሳሌያዊ አመራር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ መሪዎች ምሳሌ የሚሆንና መነሳሳት የሚፈጥር በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ይህንን Doctorate of Philosophy እንዳበረከተላቸው የትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደሪስ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ዶ/ር ዣክሊን ሞሀየር ገልፀዋል::

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ ላሳዩት ቁርጠኝነት እና ለሌሎች ሃገራት መሪዎች አርአያ የሚሆን ስራ በመስራታቸው የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማት እንደተበረከተላቸው የግዛቱ ሴናተር ጋይል ዴቨንፓርት በመድረኩ ላይ ተናግረዋል::

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ ዶ/ር አዳነች አቤቤ ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Heeri Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share