15/06/2024
በሀረሪ ክልል 1 ሺህ 445ኛው የኢድ አል አደሃ(አረፋ) በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
1 ሺህ 445ኛው የኢድ አል አደሃ(አረፋ) በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ከበአሉ ጋር ተያይዞ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ገናናው ጥበቡ በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል ለሁሉም ፈፃሚ አመራር እና አባላት እንዲሁም አጋዥ ተቋማት የበአሉን አከባበር የተመለከተ የፀጥታ እቅድ ወቶ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።
በአሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው የሰው ኃይል ተመድቦ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በክልሉ ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ከኮሙዩኒቲ ፖሊሲንግ አደረጃጃቶች እና ከሰላም አምባሳደሮች ጋር በጋራ ተቀናጅቶ በመስራት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ም/ኮሚሽነሩ አክለው ባስተላለፉት መልዕክትም ሕዝበ ሙስሊሙና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ለወንጀልና ለደህንነት አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙ ለአካባቢው ፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በዓሉም የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።