AberaHoeto ዘካፋ

AberaHoeto ዘካፋ studied plant science , biodiversity conservation and management . 0917825603

18/04/2024

ራእይ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።
⁵ እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።

18/04/2024

ሀይማኖት በቋንቋችን
-----------
ሰሞኑን የክርስትና ሥም እንዴት ይሰጣል የሚለውን የተወሰነውን ከአማርኛ ወደ ካፊ ኖኖ ተርጉሜ ስያቀርብ ብዙዎች የሰጡኝ ኮሜንት በጣም ተመችቶኛል። ነገር ግን የካፋ ክርስትና ሥም በዛ ልክ አይደለም። እኛ አልተረዳንም እንጂ አባቶቻችን ዛሬም እየተጠቀሙበት ነው።

ባጭሩ ካፋን ታሪክ ስናነብ መደበኛ ክርስቲያን (normal Christian) ነበሩ ይላል ቢበር። ከቢበር በፊት ሌሎችም ጽፎበታል። የትኛውም የሀይማኖት ተቋም ወደ ካፋ ከመምጣቱ በፊት ካፋ ራሱን ችሎ አምላኩ ጋር የሚገናኙበት የክርስትና መንገድ ነበረው። ከኋላ የአብሲኒያ ወረራ በኋላ 98% ኢኦተቤክ መቀላቀሉን የካፋ ታሪክ ያስረዳል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ያኔ የተጀመረው የክርስትና ሥም አሰጣጥ ዛሬም ብዙ ገጠራማ አካባቢ አልጠፋም። ይህን ቃል እንዲታመጡ ነበር ሀሳቤ
-Bushooyeer -ወልደእግዚአብሔር
-Yeerikishi_ክንደእግዚአብሔር
Garikishi_ገ/ጊስ
_Beshooyeri
-Hakkooyeeri
___
__
__ እነዚህ ሁሉ የክርስትና ሥም ናቸው። ባይሆን እንደካፋነቴ ምን ይጠበቅብኛል? ለሚለው ግድ ነው። መልሶ ማምጣት (restoration) ስራ መሥራት እና ማምጣት፣ አባቶች የክርስትና ሥም ስሰጡ እንድጠቀሙ በቅርበት ማማከር ተገቢ ይመስለኛል።

17/04/2024

ገላትያ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁷ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።
²⁸ አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።
²⁹ እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።
ሀይማኖት የሚባል የለም።

16/04/2024

ይሰማል ወይ!

15/04/2024
13/04/2024

Arabica coffee=Come to Kafa
Lucy =??

13/04/2024

ባሁኑ ሰዓት ሀይማኖት በየቋንቋው ይሰበክ ተብሏል።ክርስትና ሥም ለመስጠት እስቲ የተወሰነውን በኛ ቋንቋ ከትርጉም
-ወልደማርያም _Shiijjeemaariyami
-ክዳነ ማርያም _Qeree maariyami
-ሃይለሚካኤል_Iiqqoo mikaalli
-ገብረ ሚካኤል-Halleemikaalli
_ ወልደጻድቅ_ Shiijjeecaadiq.....

13/04/2024

Watch, follow, and discover more trending content.

11/04/2024

'ማለት' ማለት ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም በማለት የጠቅኸው ጥያቄ እኔም ምን ማለት ፈለገህ እንደሆነ አልገባኝም!

I've received 600 reactions to my posts in the past 30 days. Thanks for your support. 🙏🤗🎉
11/04/2024

I've received 600 reactions to my posts in the past 30 days. Thanks for your support. 🙏🤗🎉

10/04/2024

“.... በዚችም ዓለት ላይ እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።”
— ማቴዎስ 16፥18
መልካም ቀን🙌

The legend Muluken Melese we never forget for ever..Rest in peace
10/04/2024

The legend Muluken Melese we never forget for ever..
Rest in peace

የኑሮ ውድነት ሊያበቃ ነው መሰለኝ። በሜዳ ላይ የሚታዩ ቡቃያች ፊት ለፊት ላለው ዘመን ተስፋ ሰጪ ምልክት እያሳዩ ናቸው።
09/04/2024

የኑሮ ውድነት ሊያበቃ ነው መሰለኝ። በሜዳ ላይ የሚታዩ ቡቃያች ፊት ለፊት ላለው ዘመን ተስፋ ሰጪ ምልክት እያሳዩ ናቸው።

09/04/2024

🔻👉1 በህይወትህ ጥሩ ሰው መሆን ቢያቅትህ መጥፎ ሰው ግን ፈፅሞ አትሁን፡፡

🔻👉2 በህይወትህ ለራስህ ታማኝ ከሆንክ ሌሎችም ባንተ እምነት አላቸው፡፡

🔻👉3 በህይወትህ በጅህ የያዝከውን ነገር ከለቀከው በኃላ እየራቀህ መሄዱን እንዳትረሳ፡፡

🔻👉4.በዚች ምድር ላይ ሁሌም ስቆ ተደስቶ የሚኖረው ስቀን የተነሳንው ፎቶ ብቻ ነው፡፡

🔻👉5.ንፁህ ልብ ቆሻሻ ቦታ ብትገኝም እንኳን ሁሌም ንጹህ ናት ፡፡፡

🔻👉6.እውነትን መናገር የህሊና እረፍት ሲሆን ውሸት መናገር ግን የህሊና ውጥረት ነው፡፡

🔻🤗7.የጠወለጉ ቅጠሎች ሲረግፉ ለአረንጎዴዎች ማስጠንቀቂያ ናቸው።

🔻🤗8. በምድር ላይ ለሚፈጠረው ችግር ሁሉ መውጫ በር አለው አንዱ እና ዋነኛው ትግስት ነው"

🔻😔9.ትግስት የመከራ እና የሀዘን ማለፊያ ድልድይ ናት፡፡

🔻❤10. መልካም ሞት የመልካም ስራ ውጤት ነውና ለጥሩ ስራ ልዩ ቦታ ይኑረን፡፡

🔻😍11.በማንኛው ቦታ ማውራት እና መሆን ይለያያሉ በማውራት ውስጥ ሆኖ መገኘት ልዩ ውበት ነው፡፡

🔻👉12.በህይወትህ ጥሩ ሰው ከፈለግህ መጀመሪያ እራስህ ጥሩ ሰው መሆን አለብህ፡፡

🔻👉13.እውነተኛ ፍቅር እና እምነት በአፍ ላይ ሳይሆን በልብ ውስጥ ነው፡፡

🔻👉14.ፍቅር የሶስት ፊደሎች ጥምር ውጤት ቢሆንም አለምን እንደ ብር ላስቲክ ወጥሮ የመያዝ ትልቅ እምቅ ሀይል አለው ፡፡

🔻👉15.ህይወት እንደ ቂጣ ናት ለአስተዋይ ትበስላለች ለሌላው ታራለች፡፡

🔻👉 16.በዚች ምድር ላይ ያቃተን ትልቅ ሰው መሆን ሳይሆን ጥሩ ሰው መሆን ነው ፡፡

🔻👉 17.ለመከራ የታደለች ህይወት አንድ ቀን የደስታ ባለቤት ትሆናለች፡፡

🔻😍18.ውበት የአስተሳሰብ ስፋት እንጂ የሰውነት ቅርፅ አይደለም፡፡

🔻❤19.እውነት የህሊና ህግ ናት ማንም ከእውነት ያመለጠ ቢመስለውም የገዛ ህሊናው ሲያሳድደው ይኖራል፡፡

❤🙏20.ሰው ይቅርታ የሚጠይቅህ ስህተት ስለሰራ ብቻ ሳይሆን ከሰራው ስህተት ይልቅ ፍቅርህ ስለሚበልጥበት ነው፡፡ .

#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
Follow me and share it

ባህር ዛፍ ምንገጠመው?/whats up on eucalyptus?/በነገስታት ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የሚነገርለት ይህ ተክል በአሁኑ ወቅት አደጋ ገጥሞታል። አደጋውን ሁኔታ ሰዎች የየራሳቸው ...
08/04/2024

ባህር ዛፍ ምንገጠመው?/whats up on eucalyptus?/
በነገስታት ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የሚነገርለት ይህ ተክል በአሁኑ ወቅት አደጋ ገጥሞታል። አደጋውን ሁኔታ ሰዎች የየራሳቸው የሆነ መላምት እየሰጡበት ነው።

ይህ ተክል በተለያዩ ሥፍራዎች Negative and positive impact ስሰጥበት ነበር። እኔ ከጥሩ ግን ስነሳ በሀገራችን የብዙዎችን ኑሮው ለመሸፈን ከማገር እስከ መሪ፣ከወራጅ እስከ ፍልጥ ብቻ ሁሉ ነገር በመሆን የሚያደርሰውን ችግር እንድንረሳ አድርጎታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ስመ ጥሩ ውጤቶች ( luxury product) የሚሠራው ከባህር ዛፍ ነው። ለምሳሌ ከወጪ የሚገቡ በሮች፣የቢሮ ዕቃዎች የዚህ ውጤት ናቸው።

ወደ አሁኑ ወቅት ባህር ዛፍ ላይ እየታየ ያለውን የመድረቅ ሁኔታ አስደንጋጭ ነው። ምክንያቱ ይህ ነው ለማለት ይከብዳል። ያ ደግሞ ሰዎችን የራሳቸው የሆነ መላምት እንድወስዱ እያደረገ ነው። እኔ ግን የራሴ የሆነ ምልከታ አለኝ።

በርግጥ በ laboratory መረጋገጥ ያለበት ቢሆንም በውጫዊ ምልከታ(morphological expectation) እነዚህ ሶስት በሽታዎች ያልሆኑ ይችላሉ።የመጀመሪያው Anthracnose,phytophtora እና Eucalyptus canker የሚባሉ በሽታዎች አሉ። የመጀመሪያው በ fungi አማካኝነት የሚመጣ ስሆን የመጀመሪያ ቅርጫፍና ቅጠል ያጠቃል። ሁለተኛው(phytophtora) ከሆነ አስጊ ነው። በ fungi የሚመጣ ስሆን ወደ ሌሎች እንጨታማ ዝርያዎች ልተላለፍ ይችላል። ሦስተኛው ግን bacterial ሆኖ ቅርፍቱንና እንጨታማ አካል በመጉዳት ይገላል።

ለማንኛውም ጥናት ይጠይቃል
አድርጉኝ

07/04/2024

“ወደ ፊትም ደግሞ ደስ ይለኛል፤ ይህ በጸሎታችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ መሰጠት #ለመዳኔ እንዲሆንልኝ አውቃለሁና፥”
— ፊልጵስዩስ 1፥19

07/04/2024

ደብረ ዘይት
-------
ማቴዎስ 24
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
⁴ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
⁵ ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
⁶ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
⁷ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤
⁸ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።

መልካም ሰንበት ❤

06/04/2024

* ሕይወት * ምንድን ነው ?
-----------------
ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
* 1. ሆስፒታል *
* 2. እስር ቤት *
* 3. መቃበር *
ሀብታም ሰው መስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር
ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ ። እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን
አምላኬ ድሀ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ
ሰው አየ ። እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ እብድ እንኳ አልሆንኩ
አለ"።
:
እብዱ ሰውየ ወደ ፊት ተመለከተ እና አንድ አምቡላንስ አየ
አምቡላሱን ላይ በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ ።
እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ከዚያም የታመመው ሰውየ በሆስፒታል ውስጥ የሞተውን ሰው
ሬሳ ተመለከተ ። እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ
ምክንያቱም የሞተ ሰው እግዚአብሔር አያመሰግንምና አለ"። ዛሬ ስለ ሁሉም
የእግዚአብሔር በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም ?
:
:
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ
ትገነዘባለህ ።
:
በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ ።
:
በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምንም ዋጋ እንደሌለው ትገነዘባለህ

:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው ።
:
ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ ሁን ።

ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን !!!

🌷ከደራሲያን አለም ፔጅ🌷

መልካም አዳር🙏🙏

06/04/2024

Haye aye kafa hama hama..

04/04/2024

አንዱ ሠራተኛ አለቃው እጅግ ቅንጡ የሆነ መኪና እየነዳ የሚሠራበት ቦታ ድረስ መጣ። ሠራተኛው ላቡን ከጠረገ በኋላ
ሠራተኛ :-" አለቃዬ እንዴት የሚታምር መኪና ነች"
አለቃ:- " ወደድካት?"
ሠራተኛ :- በጣም እንጂ
አለቃው :-" በል ከዚች ሰዓት ጀምሮ ለደቂቃ እንኳ ፋታ ስትሰጥ ሥራ፣ ቀጣይ አመት ከዚህ በጣም የተሻለችውን እየነዳሁ እመጣለሁ " አለ ይባላል

መልካም ቀን❤

ተመስገን አምላኬ-----------🌗በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል ስንት ወርቅ ይዛችሁ እንደመዳብ ካቀለላችሁት ከእጃችሁ ሲወጣ ይቆጫችኋል። ዛሬ እናታችሁ አጠገባችሁ ስላለች አመስግኑ ዛሬ ...
04/04/2024

ተመስገን አምላኬ
-----------
🌗በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል ስንት ወርቅ ይዛችሁ እንደመዳብ ካቀለላችሁት ከእጃችሁ ሲወጣ ይቆጫችኋል። ዛሬ እናታችሁ አጠገባችሁ ስላለች አመስግኑ ዛሬ አባታችሁ ስላለ ተመስገን በሉ ዛሬ ጤና ስላላችሁ ፣ ዛሬ ወጥታችሁ መግባት ስለምትችሉ አመስግኑ።

💡ይህ ሁሉ ባይኖራቸሁ እንኳን በህይወት ስላላችሁ ተመስገን በሉ፣ በህይወት ያለ ነውና የተበላሸውን ማስተካከል የሚችለው። በህይወት ከመኖር በላይ ዋጋ ያለው ነገር የለም፤ የምናገኘውም የምናጣውም በህይወት ስላለን ነው። መኖርን ደግሞ በነፃ ነው ያገኘነው፣ ምሬት ዓይንን ያጨልማልና ደስተኛና አመስጋኝ እንሁን።

💡እጅግ ውድ የሆኑ ነገሮች በነፃ ነው የተሰጡን፡፡ ፈጣሪ የአቅማችንን ልክ ስለሚያውቅ የከበሩትን ነገሮች ያለክፍያ አስረከበን፡፡ አየር፣ውሀ፣ ደማችን፣ አካላችን፣ ፀሀይዋ፣ ዝናቡ እና አፈሩ በክፍያ ቢሆኑ ማን መግዛት ይችል ነበር? ህልውናችን በነኝህ ነገሮች እጅግ የመቆራኘቱን ያህል በገንዘብ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ እኔነኝ ያለ የምድር ባለጠጋስ ወጪውን ይችለው ነበር ወይ ?

❤️በነፃ የተሰጡን ባይኖሩ ኖሮ ሰው በውድ የሚራኮትባቸው ቁሶችስ መች ይኖሩ ነበር፡፡ ሰው ርካሹን በውድ ይሸጣል ፈጣሪ ግን ውዱን በነፃ ይሰጣል፣ ማጉረምረሙን ትተን ስለ ፈጣሪ ለጋስነት እናመስግን ከምናስበው በላይ ባለፀጎች ነን፡፡

🌗ስለ ሁሉ ነገር አመስጋኝ ሁን ማመስገን ስትጀምር አለም ወደአንተ ታዘነብላለች ነገሮች በሙሉ መልካም ይሆናሉ። ካሰብከው በላይ ሁሉ ነገር ሲስተካከል ሲያምር ታየዋለህ በምድር ላይ ሁሉ ነገር ለመልካም እንደሆነ ስታውቅ፣በማመስገን ስትታጀብ ቤትህም ይደምቃል ኑሮህም ይሞቃል በረከት ሁሉ ወዳንተ ይመጣል።

ልባችን ሁሌም ለምስጋና ክፍት ይሁን!

መልካም ቀን🙏❤️

እንደካሮት 🥕 የፈላ ውሃ ውስጥ ሲገባ የቀድሞ ጥንካሬውን ትቶ እንደሚልፈሰፈሰው አትሁን ፤ በህይወት በሚገጥሙህ ችግሮች አትዝለፍለፍ። እንደ እንቁላልም 🥚 የፈላ ውሃ እንደሚያጠነክረው አትሁን ...
02/04/2024

እንደካሮት 🥕 የፈላ ውሃ ውስጥ ሲገባ የቀድሞ ጥንካሬውን ትቶ እንደሚልፈሰፈሰው አትሁን ፤ በህይወት በሚገጥሙህ ችግሮች አትዝለፍለፍ። እንደ እንቁላልም 🥚 የፈላ ውሃ እንደሚያጠነክረው አትሁን ፤ ፈተናዎች ጨካኝና ልበ ደንዳና እንዲያደርጉህ አትፍቀድ። ይልቁንስ እንደ ቡና ሁን!
የፈላ ውሃ ቡናውን አይቀይረውም፤ ቡናው ውሃውን እንጂ። ☕️

ቡና ሰዎች አብዝተው የሚወዱት ፣ ተጠራርተው የሚጠጡት፣ እጣን፣ ፈንዲሻ፣ ቄጠማ ና ሌሎች ማድመቂያ ነገሮች ተጨምረውለት የሚጠጣ ነው። እንዲ እንዲሆን ግን ያሳለፈው ፈተና ቀላል አይደለም። ፍሬው ከዛፍ ከተቀነጠሰ በኃላ ይደርቃል ፤ ይፈለፈላል ፣ እሽት ፍትግ ተደርጎ ይታጠባል ፣ ይቆላል ፣ ይወቀጣል ፣ ያ ሳይበቃ የፈላ ውሃ ውስጥ ይንተከተካል። ይሄ ሁሉ ፈተና ግን ቡናውን ምርጥና ተወዳጅ አደረገው እንጂ አላሸነፈውም።

አንተስ እንደየትኛው ነህ? ፈተናና ችግር እንደ ካሮቱ ልፍስፍስ ወይስ እንደ እንቁላሉ ልበ ደንዳና ነው የሚያደርግህ? ወይስ እነደቡናው ችግሩ አንተን ሳይሆን አንተ ነህ ችግሩን ቀይረህ ተፅዕኖ ፈጣሪ የምትሆነው? ምርጫው🤷‍♀️
✍️ via ንቁ ትውልድ

መልካም ውሎ🙏

31/03/2024

ወጣትነትና ቋንቋ አጠቃቀም
"እስቅርጳጵ ኢቭ" ያለው ተማሪ ከባድ ክስ ቀረበበት

31/03/2024

ለሁሉም ይድረስ

I've received 500 reactions to my posts in the past 30 days. Thanks for your support. 🙏🤗🎉
29/03/2024

I've received 500 reactions to my posts in the past 30 days. Thanks for your support. 🙏🤗🎉

ሁለም ለምለምና አረንጓዴ ሚዛን አማን እውነተኛ የፍቅር የአንድነትናየልማት ከተማእንወድሻለን
29/03/2024

ሁለም ለምለምና አረንጓዴ ሚዛን አማን እውነተኛ
የፍቅር
የአንድነትና
የልማት ከተማ
እንወድሻለን

Address

Bonga

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AberaHoeto ዘካፋ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to AberaHoeto ዘካፋ:

Videos

Share